ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ አገራት ድርጅት (አካፓድ) ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች
Jul 17, 2026 263
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 10/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ አገራት ድርጅት (አካፓድ) ሊቀመንበር ሆና ተመርጣለች። 121ኛው የአካፓድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ሐምሌ 8-9 ቀን 2018 ዓ.ም. ቤልጅየም መዲና ብራስልስ ተካሂዷል። በጉባኤው ላይ በገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው የተመራ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ የልኡካን ቡድን ኢትዮጵያን በመወከል ተሳትፏል። የሚኒስትሮቹ ስብሰባ የትኩረት አጀንዳዎች የማላቦ ዲክላሬሽን አተገባበር ሂደትን መገምገም፣ የድርጅቱን የፋይናንስ አቅም በዘላቂነት ለመገንባት ስለሚወሰዱ እርምጃዎች መምከር ላይ ያተኮረ ነው። እንዲሁም የድርጅቱ ማሻሻያ ሂደት ያለበትን ደረጃ መገምገም፣ የሳሞአ ስምምነትን የትግበራ ሂደት መገምገም እንዲሁም ሌሎች የድርጅቱንና የአባል ሀገራትን ጥቅም ስለሚያስጠብቁ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። ኢትዮጵያ አቋሟን የሚያንጸባርቁ እና ድርጅቱን በፕሬዚዳንትነት በምትመራበት ወቅት የምትከተላቸውን የትኩረት አቅጣጫዎች የሚያመለክቱ ንግግሮች አቅርባለች። በጉባኤው ማጠናቀቂያም ኢትዮጵያ ከኦገስት 1 ቀን 2026 እስከ ጃንዋሪ 31 ቀን 2027 የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓስፊክ አገራት ድርጅት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች። ኢትዮጵያ በቀጣይ ስድስት ወራት የጉባኤው ሰብሳቢነቷ ወቅት ቅድሚያ የምትሰጣቸውን የትኩረት ጉዳዮች አስተዋውቃለች። እነዚህም ከወቅቱ ጂኦፖለቲካዊ እውነታ አኳያ የድርጅቱን ጽ/ቤትና የአባል አገራትን የፖሊሲ ነጻነት ማረጋገጥ፣ በራስ አቅም ሊከናወኑ ስለሚችሉ የልማት ስራዎችና የአገር ውስጥ ሃብት ማሰባሰብ የኢትዮጵያን ተሞክሮ በማጋራት በምሳሌነት መምራት፣ በተቋሙ ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲጠናከር በማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲወገድ መስራት፣ የድርጅቱ የፋይናንስ እጥረት በዘላቂነት እንዲፈታ የተጀመረው የሀብት ማሰባሰብ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ እና የአውሮፓ ህብረት እና የአካፓድ ግንኙነት መሠረት የሆነው የሳሞአ ስምምነት አፈጻጸም በተሻለ መልኩ እንዲጓዝ መስራት ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ኢትዮጵያ ድርጅቱ ከተመሰረተ እ.ኤ.አ. 1975 ጀምሮ ሁለት ጊዜ (እ.ኤ.አ. ከነሀሴ 1 ቀን 1986 እስከ ጥር 31 ቀን 1987 እና ከየካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ ሀምሌ 31 ቀን 2017 ) ተቋሙን በሰብሳቢነት ማገልገሏን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የአካፓድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሆና መመረጧ፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን የዲፕሎማሲ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በድጋሚ የሚያረጋግጥ ታላቅ ስኬት መሆኑም ተገልጿል። ይህ ታሪካዊ ኃላፊነት ኢትዮጵያ በደቡብ-ደቡብ ሁለንተናዊ ትብብር ላይ ያላትን ተሳትፎ ይበልጥ ከማጠናከሩ ባሻገር፣ ከአባል አገራቱና ከአውሮፓ ህብረት ጋር የሚደረጉ ትብብሮችን በበላይነት ለመምራት፣ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር እና መልካም ገፅታዋን ለመገንባት የዲፕሎማሲ ዕድሎችን ይከፍታል። ጉባኤውም ለኖቬምበር 2026 ዓ.ም. የታቀደው የ122ኛው የአካፓድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት አዲስ አበባ እንዲካሄድ በድርጅቱ አባል ሀገራት ተወስኖ ተጠናቋል።
ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ለከፋ ጉዳት የዳረገ የጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርቷል
Jul 17, 2026 255
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 10/2018 (ኢዜአ) ፦ ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን ሻዕቢያን ጨምሮ ከተለያዩ ሕገ-ወጥ ኃይሎች ጋር በመጣመር የትግራይን ሕዝብ ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ የጥፋት ተግባር ላይ በመሰማራት ጠላትነቱን አረጋግጧል ሲሉ የትግራይ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድርና የዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ አስራት ገለጹ። የትግራይ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር እና የዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ አስራት በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ላይ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቆይታቸውም ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ፖለቲካዊና ወታደራዊ መሪዎች የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ ጎን በመተው፣ በስምምነቱ መሰረት የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳይሠራ በማድረግና በማፍረስ የክልሉን ሥልጣን በኃይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ለሥልጣን ሲል ከትግራይ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች፣ ከሻዕቢያና ከሌሎች የውጭና የሀገር ውስጥ ቡድኖች ጋር በመተባበር ለሌላ ግጭት እየተዘጋጀ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። ሻዕቢያ የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት ይጥራል ያሉት የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ፤ ለዚህ ደግሞ ቀደም ብሎ በክልሉ የፈጸመው ጭፍጨፋ እና ያስከተለው ውድመት ማረጋገጫ ነው ብለዋል። የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሻዕቢያ የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት የነበረውን ሕልም እንዳከሸፈበት ተናግረው፤ ስምምነቱ ሲፈረምም 'ተሰናክለናል' ሲል በአደባባይ መግለጹን አስታውሰዋል። ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን አሁንም ትግራይን የግጭት ማዕከል ለማድረግ ከተለያዩ ሕገ-ወጥ ኃይሎች ጋር በመጣመር የትግራይን ሕዝብ ለመጉዳት እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል። ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ ከውጭ ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመመስረት ሥልጣን ለፌዴራል መንግሥት ብቻ መሆኑን እንደሚደነግግ ያስታወሱት አቶ ገብሩ፤ ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ከኤርትራ፣ ከሱዳን እና ከሌሎች ሀገራት ጋር እያደረገ ያለው ግንኙነት ሕጋዊ መሠረትና አግባብነት እንደሌለው ገልጸዋል። ይህ ሕገ-ወጥ ቡድን ካለፈው ስህተቱ መማር ያልቻለና የማይማር መሆኑን ጠቁመው፤ ቡድኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላት ከሻዕቢያ ጋር በመተባበርና ጥምረት በመፍጠር እኩይ ድርጊቶችን እየፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል። በተግባር ተፈትነው ለውድቀት የተዳረጉት እነዚህ ኃይሎች፣ ምንም ዓይነት የፖለቲካም ሆነ የርዕዮተ-ዓለም ለውጥ ሳያደርጉ ባረጀ አስተሳሰባቸው መጓዛቸው ለትግራይ ሕዝብ ምንም ዓይነት ፋይዳ ሊያስገኝ እንደማይችል አስረድተዋል። ሕገ-ወጡ ቡድን ባወጣው ሕገ-ወጥ አዋጅ ምክንያት የትግራይ ሕዝብ በከባድ ቀውስና በደል ውስጥ እንደሚገኝና የትግራይ ወጣትም ሀገሩን ትቶ እየተሰደደ መሆኑን ተናግረዋል። ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ካለፈው የአፋኝነቱ፣ የጭቆና እና የአምባገነንነት ተግባሩ ባደረሰው በደል ያልተጸጸተ መሆኑን አመልክተው፤ አሁን ደግሞ ዝርፊያን እና ቅሚያን መሠረት ያደረገ አስተዳደር በመዘርጋት የክልሉን ሕዝብ ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑን አስረድተዋል። ወጣቶችን በማፈን እና ታጣቂዎችን ወደ ሱዳን በመሸጥ ገቢ እየሰበሰበ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ይህም የቡድኑን የጥፋት ተልዕኮ መገለጫዎች በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን አስረድተዋል። መላው የትግራይ ሕዝብ እያደረገ ያለውን ሰላማዊ ትግል አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው፤ ለትግራይ ችግር ዋና መፍትሔው ወደ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መመለስ መሆኑን ጠቁመዋል። ነገር ግን ቡድኑ በብዙ መንገድ ተጠያቂ የሚያደርጉት በርካታ በደሎችን ማድረሱና በሕገ-ወጥ ተግባራት ላይ በመዘፈቁ ምክንያት ሰላምን ቀዳሚ ምርጫው ያደርጋል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል። ሕገ-ወጡ ቡድን በፈጸማቸው ተደጋጋሚ ድርጊቶች ምክንያት ለሕግ ተጠያቂ የሚሆንበት ዕድል ሰፊ መሆኑንም አስረድተዋል።
የጭስ አልባ ትራንስፖርት ዘርፍን ለማስፋፋት ከዓለም ባንክ ጋር በአጋርነት ለመሥራት ተስማምተናል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Jul 17, 2026 233
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት አገልግሎት ይበልጥ ለማሻሻል ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ከሆኑት ማርያም ሳሊም ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እና በተለይም የጭስ አልባ ትራንስፖርት (E-mobility) ተደራሽነትን በስፋት ለማዳረስ እያከናወነ ባለው ሥራ ዙሪያ በዝርዝር መምከራቸውን ገልጸዋል። በውይይታቸውም አስተዳደሩ የጀመራቸውን ሥራዎች ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል። እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ የግል ተቋማትን ለመደገፍ ከዓለም ባንክ ጋር በአጋርነት እና በትብብር በጋራ ለመሥራት ተግባብተናል ብለዋል። ከንቲባ አዳነች ለዳይሬክተሯ ማርያም ሳሊም እና አብረዋቸው ለነበሩት የቴክኒካል ቡድን አባላት በራሳቸው እና በአዲስ አበባ ሕዝብ ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በነገው እለት በአዲስ አበባ ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
Jul 17, 2026 276
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 10/ 2018 (ኢዜአ)፦ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቃወምና ለማስቆም እንዲሁም ለፌደራል መንግሥትና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ''አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን'' በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፉ ይደረጋል። ሰልፉ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ። በዚህም መሰረት:- ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል ለገሀር መብራት ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲዮም ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ከአራት ኪሎ ወደ መሰቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ከካሳንቺስ በመቅረዝ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ መቅረዝ ሆስፒታል አጠገብ ከአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ። ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ረዥም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያስከበረችውን ስትራቴጂክ ጥቅም በቀይ ባሕር የመድገም ሕጋዊና ተፈጥሯዊ መብት አላት
Jul 17, 2026 233
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 10 /2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያስከበረችውን ስትራቴጂክ ጥቅም በቀይ ባሕር የመድገም ሕጋዊና ተፈጥሯዊ መብት አላት ሲሉ አሜሪካዊው የፖለቲካ ተንታኝ አንድሪው ኮሪብኮ ገለጹ። ሕዳሴ ግድብ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያፋጥን ስትራቴጂካዊ የልማት ውጤት መሆኑንም አስገንዝበዋል። አንድሪው ኮሪብኮ እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት የተስተካከለ የውሃ ፍሰት በመፍጠር፣የጎርፍ መጥለቅለቅንና የውሃ ብክነትን የታደገ አህጉራዊ ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ ግድቡን መገንባቷ ሀገራዊና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያፋጥን የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር አቅም እንዲጎለብት ማስቻሉን ተናግረዋል። በዚህም ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚላከው የኤሌክትሪክ ኃይል፣ቀጣናዊ ትብብርን በማጎልበት ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ውህደት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የገነባችበት መንገድ፣በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል የሚለውን የግብፅ መሰረተ ቢስ አጀንዳ ሙሉ ለሙሉ የቀለበሰ መሆኑን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያስከበረችውን ስትራቴጂክ ጥቅም በቀጣይም በቀይ ባሕር የመድገም ሕጋዊና ተፈጥሯዊ መብት እንዳላት አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚከተሉት ስትራቴጂ በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ ግፊትና በተላላኪዎች አማካይነት የሚፈጸም መሆኑን ጠቁመዋል። ስግብግብ ፍላጎትና በሌሎች ሀገር ላይ የሚጫን ተስፋፊነትን ያነገቡ የግብፅ ገዥ መደቦች በኢትዮጵያ ውስጥና በኤርትራ የሚገኙ ፅንፈኛና ታጣቂ ቡድኖችን እንደ መሳሪያ በመጠቀም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማደናቀፍ በተደጋጋሚ ሲሞክሩ መስተዋላቸውን አውስተዋል። ይህ የማያዋጣ አካሄድ መሆኑን በመጠቆም በተፋሰሱ ሀገራት የሚነሱ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ጥያቄዎችን፣የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካዊ መፍትሔ በሚል መርህ በሰለጠነ ውይይትና በጋራ ተጠቃሚነት መፍታት እንደሚቻል አስረድተዋል። የዓባይ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ውጥረት ከሚያባብስ አካሄድ ሊቆጠቡ ይገባል ያሉት ተንታኙ፥ ቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋትን በማስቀደም የጋራ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ትብብር ማድረግ እንደሚኖርባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።
ፖለቲካ
ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ለከፋ ጉዳት የዳረገ የጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርቷል
Jul 17, 2026 255
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 10/2018 (ኢዜአ) ፦ ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን ሻዕቢያን ጨምሮ ከተለያዩ ሕገ-ወጥ ኃይሎች ጋር በመጣመር የትግራይን ሕዝብ ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ የጥፋት ተግባር ላይ በመሰማራት ጠላትነቱን አረጋግጧል ሲሉ የትግራይ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድርና የዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ አስራት ገለጹ። የትግራይ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር እና የዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ አስራት በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ላይ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቆይታቸውም ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ፖለቲካዊና ወታደራዊ መሪዎች የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ ጎን በመተው፣ በስምምነቱ መሰረት የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳይሠራ በማድረግና በማፍረስ የክልሉን ሥልጣን በኃይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ለሥልጣን ሲል ከትግራይ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች፣ ከሻዕቢያና ከሌሎች የውጭና የሀገር ውስጥ ቡድኖች ጋር በመተባበር ለሌላ ግጭት እየተዘጋጀ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። ሻዕቢያ የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት ይጥራል ያሉት የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ፤ ለዚህ ደግሞ ቀደም ብሎ በክልሉ የፈጸመው ጭፍጨፋ እና ያስከተለው ውድመት ማረጋገጫ ነው ብለዋል። የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሻዕቢያ የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት የነበረውን ሕልም እንዳከሸፈበት ተናግረው፤ ስምምነቱ ሲፈረምም 'ተሰናክለናል' ሲል በአደባባይ መግለጹን አስታውሰዋል። ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን አሁንም ትግራይን የግጭት ማዕከል ለማድረግ ከተለያዩ ሕገ-ወጥ ኃይሎች ጋር በመጣመር የትግራይን ሕዝብ ለመጉዳት እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል። ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ ከውጭ ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመመስረት ሥልጣን ለፌዴራል መንግሥት ብቻ መሆኑን እንደሚደነግግ ያስታወሱት አቶ ገብሩ፤ ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ከኤርትራ፣ ከሱዳን እና ከሌሎች ሀገራት ጋር እያደረገ ያለው ግንኙነት ሕጋዊ መሠረትና አግባብነት እንደሌለው ገልጸዋል። ይህ ሕገ-ወጥ ቡድን ካለፈው ስህተቱ መማር ያልቻለና የማይማር መሆኑን ጠቁመው፤ ቡድኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላት ከሻዕቢያ ጋር በመተባበርና ጥምረት በመፍጠር እኩይ ድርጊቶችን እየፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል። በተግባር ተፈትነው ለውድቀት የተዳረጉት እነዚህ ኃይሎች፣ ምንም ዓይነት የፖለቲካም ሆነ የርዕዮተ-ዓለም ለውጥ ሳያደርጉ ባረጀ አስተሳሰባቸው መጓዛቸው ለትግራይ ሕዝብ ምንም ዓይነት ፋይዳ ሊያስገኝ እንደማይችል አስረድተዋል። ሕገ-ወጡ ቡድን ባወጣው ሕገ-ወጥ አዋጅ ምክንያት የትግራይ ሕዝብ በከባድ ቀውስና በደል ውስጥ እንደሚገኝና የትግራይ ወጣትም ሀገሩን ትቶ እየተሰደደ መሆኑን ተናግረዋል። ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ካለፈው የአፋኝነቱ፣ የጭቆና እና የአምባገነንነት ተግባሩ ባደረሰው በደል ያልተጸጸተ መሆኑን አመልክተው፤ አሁን ደግሞ ዝርፊያን እና ቅሚያን መሠረት ያደረገ አስተዳደር በመዘርጋት የክልሉን ሕዝብ ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑን አስረድተዋል። ወጣቶችን በማፈን እና ታጣቂዎችን ወደ ሱዳን በመሸጥ ገቢ እየሰበሰበ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ይህም የቡድኑን የጥፋት ተልዕኮ መገለጫዎች በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን አስረድተዋል። መላው የትግራይ ሕዝብ እያደረገ ያለውን ሰላማዊ ትግል አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው፤ ለትግራይ ችግር ዋና መፍትሔው ወደ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መመለስ መሆኑን ጠቁመዋል። ነገር ግን ቡድኑ በብዙ መንገድ ተጠያቂ የሚያደርጉት በርካታ በደሎችን ማድረሱና በሕገ-ወጥ ተግባራት ላይ በመዘፈቁ ምክንያት ሰላምን ቀዳሚ ምርጫው ያደርጋል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል። ሕገ-ወጡ ቡድን በፈጸማቸው ተደጋጋሚ ድርጊቶች ምክንያት ለሕግ ተጠያቂ የሚሆንበት ዕድል ሰፊ መሆኑንም አስረድተዋል።
በነገው እለት በአዲስ አበባ ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
Jul 17, 2026 276
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 10/ 2018 (ኢዜአ)፦ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቃወምና ለማስቆም እንዲሁም ለፌደራል መንግሥትና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ''አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን'' በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፉ ይደረጋል። ሰልፉ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ። በዚህም መሰረት:- ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል ለገሀር መብራት ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲዮም ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ከአራት ኪሎ ወደ መሰቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ከካሳንቺስ በመቅረዝ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ መቅረዝ ሆስፒታል አጠገብ ከአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ። ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ረዥም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
የኢትዮጵያን የቆዩ ስብራቶች በመጠገን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ እድል ነው
Jul 17, 2026 220
ሀዋሳ፤ሐምሌ 10/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያን የቆዩ ስብራቶች በመጠገን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ እድል መሆኑን ምሁራን ገለጹ። በኢትዮጵያ የቆዩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ሀገራዊ ምክክር ታሪካዊ ዕድል ሆኖ መጥቷል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ተቋቁሞ ከዝግጅት እስከ ምክክር ምዕራፍ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ በአሁኑ ወቅት አካታች የሆነ የምክክር ሂደት እያከናወነ ይገኛል። በኮሚሽኑ የተለዩ አጀንዳዎች ላይ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የማጠቃለያ የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። አጠቃላይ የምክክር ሂደቱንና ጉባኤውን በተመለከተ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፤ የኢትዮጵያን የቆዩ ስብራቶች በመጠገን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ ዕድል መሆኑን አንስተዋል። በዩኒቨርሲቲው የስነዜጋና ስነምግባር መምህር ብሩክ ደስታ፤ ሀገራዊ ምክክሩ እንደ ሀገር ትልቅ ተስፋ የሰነቅንበት የጋራ እጣ ፋንታችን ነው ብለዋል። በመሆኑም ለሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለመሻት ለዓመታት የዘለቀው የምክክር ሂደት በውጤታማነት እንዲደመደም የሁላችንም ቅንንት፣መሻትና ለዘላቂ ሰላም መትጋት የግድ ነው ሲሉ አንስተዋል። ለምክክሩ የተለዩ አጀንዳዎችን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው የኢትዮጵያን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ አንኳር ጉዳዮች መሆናቸውን ተናግረዋል። ምክክሩ ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለመፍጠር ካለው ፋይዳ በተጨማሪ፣ የቆዩ ቁርሾዎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት መፍትሄ ይሆናል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር)፤ በምክክር ችግሮችን የመፍታት ባህልን ማዳበር ዘመኑ የሚጠይቀው ጉዳይና የስልጣኔ መገለጫም ጭምር መሆኑን አንስተዋል። የሀገር ግንባታ ሂደት የሚሳካው በሰለጠነ ውይይትና ህብረ ብሔራዊ ሀገራዊ አንድነትን በማፅናት መሆኑን ገልጸው፥ታሪካዊ እድል የሆነውን ምክክር ስኬታማ ለማድረግ በሃላፊነት ስሜት መጠቀም ይገባል ብለዋል።
ሀገራዊ ለውጡ የፈጠረው አሳታፊ የፖለቲካ ምህዳር ለሰለጠነ የፖለቲካ ባህል መሰረት ጥሏል
Jul 17, 2026 351
ሆሳዕና፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የፈጠረው አሳታፊ የፖለቲካ ምህዳር የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላምና በልማት ጉዳዮች ላይ ተቀራርበው የመስራት ባህል እንዲያዳብሩ ማድረጉን የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። ኢዜአ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተመራማሪዎች እንዳሉት፤ ሀገራዊ ለውጡ የፈጠረው አሳታፊ ስርአት በህዝብ ይሁንታ የተመሰረተ መንግስት በማዋቀር ዴሞክራሲያዊ መንግስት ለመመስረት ይረዳል። ሂደቱም የበለጸገችና የተረጋጋች ሀገርን ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ ጠንካራ መሰረት እንደሚሆን አስገንዝበዋል። በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ዳንኤል ሀንዲኖ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የተፈጠረው አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀሳብ ልዩነቶቻቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለሀገር ሰላምና ልማት ተቀራርቦ መስራታቸው እንዲጠናከር አድርጓል። ይህም ለዴሞክራሲያዊ ሥርአት ዕድገት ከሚኖረው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ከመፈራረጅና ከቂም በቀል ዕሳቤ ወጥተው ለትብብርና ለሰለጠነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። የዴሞክራሲ ተቋማት አሰራር እና የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻል ተአማኒ፣ ጠንካራና የማስፈጸም እቅማቸው እንዲጨምር መደረጉ ውጤት እያመጣ መሆኑንም ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው የሰላምና ግጭት ጥናት መምህር ጌታሁን አበራ በበኩላቸው፤ የለውጡ መንግስት የመድበለ ፓርቲ ስርአትን በማስፋት ፓርቲዎች በሀገራዊ ጉዳዮች ተቀራርብው የሚሰሩበትን አውድ መፍጠሩን ተናግረዋል። ለዚህም ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመንግስት ከፍተኛ የሀላፊነት ቦታ ላይ ጭምር በቅንጅት በመስራት እያከናወኑት ያለው ተግባር በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸዋል። በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ሚናቸውን እንዲያጠናክሩ መንግስት ምቹ ምህዳር ከመፍጠር ባለፈ የተቋማትን የመፈጸም አቅም በማጠናከር የተገልጋይን እርካታ ለማሳደግ መሰራቱን አንስተዋል። በተለይ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት መጠናከራቸው ዴሞክራሲን በማጠናከር የበለፀገች ሀገርን ለትውልድ ለማስተላለፍ ያስችላል ብለዋል።
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ረቂቅ አዋጆችን እና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ
Jul 17, 2026 314
ሀረር፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት አስረኛ መደበኛ ጉባዔ ረቂቅ አዋጆች እና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ። ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ የሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲን የሀረሪ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ በሚል ስያሜ እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። ማሻሻያ አዋጁ ተቋሙ ከዚህ ቀደም ይጠራበት የነበረውን የሀረሪ ብዙሃን መገናኝ ኤጀንሲ ስያሜ ከመቀየር ጀምሮ ለውጥ የተደረገበት ነው። የተቋሙን ሥልጣንና ተግባራት የሕዝብ ብሮድካስት አገልግሎት ተቋማት በአሁኑ ወቅት ከደረሱበት የዕድገት ደረጃ ጋር እንዲጣጣም በማድረግ በብቃት፣ በጥራትና ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል በብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ደረጃ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ማሻሻያ ማድረጉ እንዳስፈለገ ተገልጿል። አዋጁ ከጸደቀበት ከዛሬ ጀምሮ የሀረሪ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት እንደሚሆን በአዋጁ ተቀምጧል። ምክር ቤቱ የቀረበለትን የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅም አጽድቋል፡፡ አዋጁም ዜጎች መብትና ግዴታቸውን ተረድተው የሚያጋጥሟቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። እንዲሁም ምክር ቤቱ የሶስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመትም አጽድቋል። ምክር ቤቱም ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስድስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት አስረኛ መደበኛ ጉባዔ አጠናቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
Jul 17, 2026 349
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል ብለዋል። ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ በበጀት ዓመቱ ለመፈፀም ያስቀመጥናቸውን ግቦች፣ እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዳችን ማጠቃለያ ዓመትም በመሆኑ ከባለፉት 5 ዓመታት አፈፃፀም ጋር አያይዘን የምንገመግም ይሆናል ነው ያሉት። እንደሚታወቀው ባለፉት 5 ዓመታት ያቀድናቸውን ስትራቴጂክ ግቦች በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር በታማኝነትና በቅንነት ያለ እረፍት 24/7 ሰርተን በርካታ ውጤቶችን አስመዝግበናል ሲሉም ገልጸዋል። በተለይም መዲናችንን አዲስ አበባን ከማይጠቅሙ አጀንዳዎች አውጥተን የልማት እና የሰላም ማዕከል እንድትሆን አድርገናታል ብለዋል። እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ፅዱ፣ አረንጓዴና ውብ እየሆነች በመምጣቷ የዓለምን ትኩረትን ስባለች ሲሉ ጠቁመዋል። በእርግጥ ከስኬቶቻችን ባሻገር ዛሬም ያልተሻገርናቸው ተግዳሮቶች አሉብን። በተለይ የአመራራችን የውጤታማነት ልዩነቶች፣ በከተማችን የሚታዩ የኑሮ ውድነት እና ፍልሰት ችግሮችን በጥልቀት የምንገመግም ይሆናል ነው ያሉት። በርካታ ስኬቶችን ብናስመዘግብም ከህዝቡ የመልማት ፍላጎት እና ከብልፅግና ግባችን አንፃር ብዙ ስለሚቀረን ስኬቶቻችንን ማስፋት፤ ተግዳሮቶች ደግሞ ለይተን መፍታት በቀጣይ በጀት ዓመት የላቀ ስኬት ማስመዝገብ የግምገማችን ማዕከል ይሆናል ብለዋል። በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችም ላይ እንወያያለን ሲሉም በመልዕክታቸው አስታውቀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ እሳቤዎችን በተግባር በመተርጎም ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል
Jul 17, 2026 401
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ አመራሩ የብልፅግና ፓርቲ እሳቤዎችን በተግባር በመተርጎም ውጤታማ የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራት ማከናወኑን በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ። አቶ ጌቱ ወዬሳ በተጠናቀቀው በጀት አመት በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ በሰጡት መግለጫ በ2018 በጀት ዓመት ፓርቲውን በአሰራር፣ በሰው ሀይል እና በአደረጃጀት የማጠናከር ስራ ተሰርቷል ብለዋል። አባልና አመራሩ በፓርቲው እሳቤዎችና አቋሞች ላይ የጠራ ግንዛቤና አመለካከት እንዲኖረው በማድረግ በኩል አበረታች ስራዎች መሰራታቸውንም አክለዋል። ገዥ ትርክትን ለማስረጽ በተሰራ ስራ ውጤት መገኘቱን ጠቁመው የአመራሩና የአባላት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በጉልህ የታየበት በመሆኑም ተደራራቢ ተልዕኮዎች ስኬታማ መሆናቸውን አብራርተዋል። አባላት የተግባር ተልዕኮዎችን ውጤታማ በማድረጋቸው ለክልሉ ፈጣን ዕድገት ጉልህ አሻራ ማሳረፍ መቻሉን ገልፀዋል። የፓርቲውን እሳቤዎች በተግባር በመተርጎም በየዘርፉ የተመዘገቡ ድሎች በቁርጠኛ አመራር የተመሩ፣ የሁሉም አሻራ ያረፈባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫን ጨምሮ በርካታ ግቦች ማሳካት መቻሉን ጠቁመው የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰራ ስራም ውጤት ተገኝቷል ነው ያሉት። በቀጣይም በአገልግሎት አሰጣጥ የህዝብን እርካታ ማሳደግ እንዲሁም ብልሹ አሰራሮችን ከማስወገድ አንፃር በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል። አመራሩም የተገኙ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የብልጽግና ግቦች እንዲሳኩ በላቀ ቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለበት ነው ያስገነዘቡት።
ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው - በኢትዮጵያ የኦስትሪያ እና ቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደሮች
Jul 16, 2026 1226
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 9/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የኦስትሪያ እና የቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደሮች በሀገሪቱ በነበራቸው የሥራ ቆይታ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ገለጹ። አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ በነበራቸው የሥራ ቆይታ፣ በሀገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጊዜ ያጠናቀቁት የኦስትሪያ አምባሳደር ሲሞን ክናፕን (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በቆዩባቸው አራት ዓመታት የሀገሪቱን ውብና የተለያዩ ባህላዊና ተፈጥሯዊ መስህቦች መጎብኘት በመቻላቸው እጅግ አስደሳች ጊዜ አሳልፈዋል። ኢትዮጵያ እና ኦስትሪያ ለረጅም ዓመታት ታሪካዊና ጠንካራ ወዳጅነት እንዳላቸው ጠቅሰው፤ በኢኮኖሚና በንግድ ዘርፍ ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ሰፋፊ ዕድሎች መኖራቸውን ጠቁመዋል። በቆይታቸውም በርካታ የኦስትሪያ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲገነዘቡ የጋራ አጋርነትና የንግድ ትስስር እንዲመሰርቱ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ገልጸዋል። ይህ ግንኙነት ወደፊት ይበልጥ እንደሚጠናከር ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጊዜ ያጠናቀቁት የቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሚሮስላቭ ኮሴክ በበኩላቸው፤ ላለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ያደረጉት ቆይታ እጅግ ፍሬያማና ስኬታማ እንደነበር ገልጸዋል። በተለይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢኮኖሚና የባህል ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል።
ፖለቲካ
ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ለከፋ ጉዳት የዳረገ የጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርቷል
Jul 17, 2026 255
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 10/2018 (ኢዜአ) ፦ ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን ሻዕቢያን ጨምሮ ከተለያዩ ሕገ-ወጥ ኃይሎች ጋር በመጣመር የትግራይን ሕዝብ ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ የጥፋት ተግባር ላይ በመሰማራት ጠላትነቱን አረጋግጧል ሲሉ የትግራይ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድርና የዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ አስራት ገለጹ። የትግራይ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር እና የዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ አስራት በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ላይ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቆይታቸውም ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ፖለቲካዊና ወታደራዊ መሪዎች የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ ጎን በመተው፣ በስምምነቱ መሰረት የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳይሠራ በማድረግና በማፍረስ የክልሉን ሥልጣን በኃይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ለሥልጣን ሲል ከትግራይ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች፣ ከሻዕቢያና ከሌሎች የውጭና የሀገር ውስጥ ቡድኖች ጋር በመተባበር ለሌላ ግጭት እየተዘጋጀ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። ሻዕቢያ የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት ይጥራል ያሉት የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ፤ ለዚህ ደግሞ ቀደም ብሎ በክልሉ የፈጸመው ጭፍጨፋ እና ያስከተለው ውድመት ማረጋገጫ ነው ብለዋል። የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሻዕቢያ የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት የነበረውን ሕልም እንዳከሸፈበት ተናግረው፤ ስምምነቱ ሲፈረምም 'ተሰናክለናል' ሲል በአደባባይ መግለጹን አስታውሰዋል። ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን አሁንም ትግራይን የግጭት ማዕከል ለማድረግ ከተለያዩ ሕገ-ወጥ ኃይሎች ጋር በመጣመር የትግራይን ሕዝብ ለመጉዳት እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል። ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ ከውጭ ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመመስረት ሥልጣን ለፌዴራል መንግሥት ብቻ መሆኑን እንደሚደነግግ ያስታወሱት አቶ ገብሩ፤ ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ከኤርትራ፣ ከሱዳን እና ከሌሎች ሀገራት ጋር እያደረገ ያለው ግንኙነት ሕጋዊ መሠረትና አግባብነት እንደሌለው ገልጸዋል። ይህ ሕገ-ወጥ ቡድን ካለፈው ስህተቱ መማር ያልቻለና የማይማር መሆኑን ጠቁመው፤ ቡድኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላት ከሻዕቢያ ጋር በመተባበርና ጥምረት በመፍጠር እኩይ ድርጊቶችን እየፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል። በተግባር ተፈትነው ለውድቀት የተዳረጉት እነዚህ ኃይሎች፣ ምንም ዓይነት የፖለቲካም ሆነ የርዕዮተ-ዓለም ለውጥ ሳያደርጉ ባረጀ አስተሳሰባቸው መጓዛቸው ለትግራይ ሕዝብ ምንም ዓይነት ፋይዳ ሊያስገኝ እንደማይችል አስረድተዋል። ሕገ-ወጡ ቡድን ባወጣው ሕገ-ወጥ አዋጅ ምክንያት የትግራይ ሕዝብ በከባድ ቀውስና በደል ውስጥ እንደሚገኝና የትግራይ ወጣትም ሀገሩን ትቶ እየተሰደደ መሆኑን ተናግረዋል። ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ካለፈው የአፋኝነቱ፣ የጭቆና እና የአምባገነንነት ተግባሩ ባደረሰው በደል ያልተጸጸተ መሆኑን አመልክተው፤ አሁን ደግሞ ዝርፊያን እና ቅሚያን መሠረት ያደረገ አስተዳደር በመዘርጋት የክልሉን ሕዝብ ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑን አስረድተዋል። ወጣቶችን በማፈን እና ታጣቂዎችን ወደ ሱዳን በመሸጥ ገቢ እየሰበሰበ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ይህም የቡድኑን የጥፋት ተልዕኮ መገለጫዎች በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን አስረድተዋል። መላው የትግራይ ሕዝብ እያደረገ ያለውን ሰላማዊ ትግል አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው፤ ለትግራይ ችግር ዋና መፍትሔው ወደ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መመለስ መሆኑን ጠቁመዋል። ነገር ግን ቡድኑ በብዙ መንገድ ተጠያቂ የሚያደርጉት በርካታ በደሎችን ማድረሱና በሕገ-ወጥ ተግባራት ላይ በመዘፈቁ ምክንያት ሰላምን ቀዳሚ ምርጫው ያደርጋል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል። ሕገ-ወጡ ቡድን በፈጸማቸው ተደጋጋሚ ድርጊቶች ምክንያት ለሕግ ተጠያቂ የሚሆንበት ዕድል ሰፊ መሆኑንም አስረድተዋል።
በነገው እለት በአዲስ አበባ ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
Jul 17, 2026 276
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 10/ 2018 (ኢዜአ)፦ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቃወምና ለማስቆም እንዲሁም ለፌደራል መንግሥትና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ''አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን'' በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፉ ይደረጋል። ሰልፉ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ። በዚህም መሰረት:- ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል ለገሀር መብራት ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲዮም ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ከአራት ኪሎ ወደ መሰቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ከካሳንቺስ በመቅረዝ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ መቅረዝ ሆስፒታል አጠገብ ከአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ። ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ረዥም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
የኢትዮጵያን የቆዩ ስብራቶች በመጠገን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ እድል ነው
Jul 17, 2026 220
ሀዋሳ፤ሐምሌ 10/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያን የቆዩ ስብራቶች በመጠገን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ እድል መሆኑን ምሁራን ገለጹ። በኢትዮጵያ የቆዩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ሀገራዊ ምክክር ታሪካዊ ዕድል ሆኖ መጥቷል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ተቋቁሞ ከዝግጅት እስከ ምክክር ምዕራፍ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ በአሁኑ ወቅት አካታች የሆነ የምክክር ሂደት እያከናወነ ይገኛል። በኮሚሽኑ የተለዩ አጀንዳዎች ላይ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የማጠቃለያ የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። አጠቃላይ የምክክር ሂደቱንና ጉባኤውን በተመለከተ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፤ የኢትዮጵያን የቆዩ ስብራቶች በመጠገን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ ዕድል መሆኑን አንስተዋል። በዩኒቨርሲቲው የስነዜጋና ስነምግባር መምህር ብሩክ ደስታ፤ ሀገራዊ ምክክሩ እንደ ሀገር ትልቅ ተስፋ የሰነቅንበት የጋራ እጣ ፋንታችን ነው ብለዋል። በመሆኑም ለሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለመሻት ለዓመታት የዘለቀው የምክክር ሂደት በውጤታማነት እንዲደመደም የሁላችንም ቅንንት፣መሻትና ለዘላቂ ሰላም መትጋት የግድ ነው ሲሉ አንስተዋል። ለምክክሩ የተለዩ አጀንዳዎችን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው የኢትዮጵያን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ አንኳር ጉዳዮች መሆናቸውን ተናግረዋል። ምክክሩ ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለመፍጠር ካለው ፋይዳ በተጨማሪ፣ የቆዩ ቁርሾዎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት መፍትሄ ይሆናል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር)፤ በምክክር ችግሮችን የመፍታት ባህልን ማዳበር ዘመኑ የሚጠይቀው ጉዳይና የስልጣኔ መገለጫም ጭምር መሆኑን አንስተዋል። የሀገር ግንባታ ሂደት የሚሳካው በሰለጠነ ውይይትና ህብረ ብሔራዊ ሀገራዊ አንድነትን በማፅናት መሆኑን ገልጸው፥ታሪካዊ እድል የሆነውን ምክክር ስኬታማ ለማድረግ በሃላፊነት ስሜት መጠቀም ይገባል ብለዋል።
ሀገራዊ ለውጡ የፈጠረው አሳታፊ የፖለቲካ ምህዳር ለሰለጠነ የፖለቲካ ባህል መሰረት ጥሏል
Jul 17, 2026 351
ሆሳዕና፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የፈጠረው አሳታፊ የፖለቲካ ምህዳር የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላምና በልማት ጉዳዮች ላይ ተቀራርበው የመስራት ባህል እንዲያዳብሩ ማድረጉን የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። ኢዜአ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተመራማሪዎች እንዳሉት፤ ሀገራዊ ለውጡ የፈጠረው አሳታፊ ስርአት በህዝብ ይሁንታ የተመሰረተ መንግስት በማዋቀር ዴሞክራሲያዊ መንግስት ለመመስረት ይረዳል። ሂደቱም የበለጸገችና የተረጋጋች ሀገርን ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ ጠንካራ መሰረት እንደሚሆን አስገንዝበዋል። በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ዳንኤል ሀንዲኖ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የተፈጠረው አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀሳብ ልዩነቶቻቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለሀገር ሰላምና ልማት ተቀራርቦ መስራታቸው እንዲጠናከር አድርጓል። ይህም ለዴሞክራሲያዊ ሥርአት ዕድገት ከሚኖረው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ከመፈራረጅና ከቂም በቀል ዕሳቤ ወጥተው ለትብብርና ለሰለጠነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። የዴሞክራሲ ተቋማት አሰራር እና የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻል ተአማኒ፣ ጠንካራና የማስፈጸም እቅማቸው እንዲጨምር መደረጉ ውጤት እያመጣ መሆኑንም ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው የሰላምና ግጭት ጥናት መምህር ጌታሁን አበራ በበኩላቸው፤ የለውጡ መንግስት የመድበለ ፓርቲ ስርአትን በማስፋት ፓርቲዎች በሀገራዊ ጉዳዮች ተቀራርብው የሚሰሩበትን አውድ መፍጠሩን ተናግረዋል። ለዚህም ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመንግስት ከፍተኛ የሀላፊነት ቦታ ላይ ጭምር በቅንጅት በመስራት እያከናወኑት ያለው ተግባር በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸዋል። በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ሚናቸውን እንዲያጠናክሩ መንግስት ምቹ ምህዳር ከመፍጠር ባለፈ የተቋማትን የመፈጸም አቅም በማጠናከር የተገልጋይን እርካታ ለማሳደግ መሰራቱን አንስተዋል። በተለይ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት መጠናከራቸው ዴሞክራሲን በማጠናከር የበለፀገች ሀገርን ለትውልድ ለማስተላለፍ ያስችላል ብለዋል።
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ረቂቅ አዋጆችን እና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ
Jul 17, 2026 314
ሀረር፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት አስረኛ መደበኛ ጉባዔ ረቂቅ አዋጆች እና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ። ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ የሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲን የሀረሪ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ በሚል ስያሜ እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። ማሻሻያ አዋጁ ተቋሙ ከዚህ ቀደም ይጠራበት የነበረውን የሀረሪ ብዙሃን መገናኝ ኤጀንሲ ስያሜ ከመቀየር ጀምሮ ለውጥ የተደረገበት ነው። የተቋሙን ሥልጣንና ተግባራት የሕዝብ ብሮድካስት አገልግሎት ተቋማት በአሁኑ ወቅት ከደረሱበት የዕድገት ደረጃ ጋር እንዲጣጣም በማድረግ በብቃት፣ በጥራትና ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል በብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ደረጃ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ማሻሻያ ማድረጉ እንዳስፈለገ ተገልጿል። አዋጁ ከጸደቀበት ከዛሬ ጀምሮ የሀረሪ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት እንደሚሆን በአዋጁ ተቀምጧል። ምክር ቤቱ የቀረበለትን የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅም አጽድቋል፡፡ አዋጁም ዜጎች መብትና ግዴታቸውን ተረድተው የሚያጋጥሟቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። እንዲሁም ምክር ቤቱ የሶስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመትም አጽድቋል። ምክር ቤቱም ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስድስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት አስረኛ መደበኛ ጉባዔ አጠናቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
Jul 17, 2026 349
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል ብለዋል። ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ በበጀት ዓመቱ ለመፈፀም ያስቀመጥናቸውን ግቦች፣ እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዳችን ማጠቃለያ ዓመትም በመሆኑ ከባለፉት 5 ዓመታት አፈፃፀም ጋር አያይዘን የምንገመግም ይሆናል ነው ያሉት። እንደሚታወቀው ባለፉት 5 ዓመታት ያቀድናቸውን ስትራቴጂክ ግቦች በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር በታማኝነትና በቅንነት ያለ እረፍት 24/7 ሰርተን በርካታ ውጤቶችን አስመዝግበናል ሲሉም ገልጸዋል። በተለይም መዲናችንን አዲስ አበባን ከማይጠቅሙ አጀንዳዎች አውጥተን የልማት እና የሰላም ማዕከል እንድትሆን አድርገናታል ብለዋል። እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ፅዱ፣ አረንጓዴና ውብ እየሆነች በመምጣቷ የዓለምን ትኩረትን ስባለች ሲሉ ጠቁመዋል። በእርግጥ ከስኬቶቻችን ባሻገር ዛሬም ያልተሻገርናቸው ተግዳሮቶች አሉብን። በተለይ የአመራራችን የውጤታማነት ልዩነቶች፣ በከተማችን የሚታዩ የኑሮ ውድነት እና ፍልሰት ችግሮችን በጥልቀት የምንገመግም ይሆናል ነው ያሉት። በርካታ ስኬቶችን ብናስመዘግብም ከህዝቡ የመልማት ፍላጎት እና ከብልፅግና ግባችን አንፃር ብዙ ስለሚቀረን ስኬቶቻችንን ማስፋት፤ ተግዳሮቶች ደግሞ ለይተን መፍታት በቀጣይ በጀት ዓመት የላቀ ስኬት ማስመዝገብ የግምገማችን ማዕከል ይሆናል ብለዋል። በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችም ላይ እንወያያለን ሲሉም በመልዕክታቸው አስታውቀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ እሳቤዎችን በተግባር በመተርጎም ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል
Jul 17, 2026 401
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ አመራሩ የብልፅግና ፓርቲ እሳቤዎችን በተግባር በመተርጎም ውጤታማ የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራት ማከናወኑን በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ። አቶ ጌቱ ወዬሳ በተጠናቀቀው በጀት አመት በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ በሰጡት መግለጫ በ2018 በጀት ዓመት ፓርቲውን በአሰራር፣ በሰው ሀይል እና በአደረጃጀት የማጠናከር ስራ ተሰርቷል ብለዋል። አባልና አመራሩ በፓርቲው እሳቤዎችና አቋሞች ላይ የጠራ ግንዛቤና አመለካከት እንዲኖረው በማድረግ በኩል አበረታች ስራዎች መሰራታቸውንም አክለዋል። ገዥ ትርክትን ለማስረጽ በተሰራ ስራ ውጤት መገኘቱን ጠቁመው የአመራሩና የአባላት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በጉልህ የታየበት በመሆኑም ተደራራቢ ተልዕኮዎች ስኬታማ መሆናቸውን አብራርተዋል። አባላት የተግባር ተልዕኮዎችን ውጤታማ በማድረጋቸው ለክልሉ ፈጣን ዕድገት ጉልህ አሻራ ማሳረፍ መቻሉን ገልፀዋል። የፓርቲውን እሳቤዎች በተግባር በመተርጎም በየዘርፉ የተመዘገቡ ድሎች በቁርጠኛ አመራር የተመሩ፣ የሁሉም አሻራ ያረፈባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫን ጨምሮ በርካታ ግቦች ማሳካት መቻሉን ጠቁመው የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰራ ስራም ውጤት ተገኝቷል ነው ያሉት። በቀጣይም በአገልግሎት አሰጣጥ የህዝብን እርካታ ማሳደግ እንዲሁም ብልሹ አሰራሮችን ከማስወገድ አንፃር በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል። አመራሩም የተገኙ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የብልጽግና ግቦች እንዲሳኩ በላቀ ቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለበት ነው ያስገነዘቡት።
ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው - በኢትዮጵያ የኦስትሪያ እና ቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደሮች
Jul 16, 2026 1226
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 9/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የኦስትሪያ እና የቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደሮች በሀገሪቱ በነበራቸው የሥራ ቆይታ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ገለጹ። አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ በነበራቸው የሥራ ቆይታ፣ በሀገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጊዜ ያጠናቀቁት የኦስትሪያ አምባሳደር ሲሞን ክናፕን (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በቆዩባቸው አራት ዓመታት የሀገሪቱን ውብና የተለያዩ ባህላዊና ተፈጥሯዊ መስህቦች መጎብኘት በመቻላቸው እጅግ አስደሳች ጊዜ አሳልፈዋል። ኢትዮጵያ እና ኦስትሪያ ለረጅም ዓመታት ታሪካዊና ጠንካራ ወዳጅነት እንዳላቸው ጠቅሰው፤ በኢኮኖሚና በንግድ ዘርፍ ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ሰፋፊ ዕድሎች መኖራቸውን ጠቁመዋል። በቆይታቸውም በርካታ የኦስትሪያ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲገነዘቡ የጋራ አጋርነትና የንግድ ትስስር እንዲመሰርቱ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ገልጸዋል። ይህ ግንኙነት ወደፊት ይበልጥ እንደሚጠናከር ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጊዜ ያጠናቀቁት የቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሚሮስላቭ ኮሴክ በበኩላቸው፤ ላለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ያደረጉት ቆይታ እጅግ ፍሬያማና ስኬታማ እንደነበር ገልጸዋል። በተለይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢኮኖሚና የባህል ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል።
ማህበራዊ
በውጭ ሀገር ተደብቀው በኢትዮጵያዊያን ላይ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽሙ የነበሩ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተያዙ
Jul 17, 2026 285
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10/ 2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዱባይ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በውጭ ሀገር ተደብቀው በኢትዮጵያውያን ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ዳውድ ተፈሪ ለገሰ እና ደስታ ተገኝ አበጋዝ የተባሉ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ሁለቱ ዋና ተጠርጣሪዎች የተለያዩ የማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም 105 ዜጎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዱባይ በመውሰድና ከ188 ሚሊዮን ብር በላይ ከተጎጂዎች በመሰብሰብ፣ በበርካታ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ የቆዩ በመሆናቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከዱባይ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ሥር ውለው ለሀገራችን ተላልፈው እንዲሰጡ አድርጓል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዱባይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በደረሰው ጥቆማ፣ ተጠርጣሪዎቹ ዱባይ ተቀምጠው ሀገር ውስጥ ባሉ ተባባሪዎቻቸው አማካኝነት ወጣቶችን በመመልመል ወደ ዱባይ በመላክ፣ በተዘጋጀ የማገቻ ቦታ በማቆየት፣ በተለይ በሴቶች ላይ ጥቃት በማድረስና በማሰቃየት ከፍተኛ ወንጀል ሲፈጽሙ የቆዩ መሆናቸው ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስም ጉዳዩን ሲያጣራ ቆይቶ በሀገር ውስጥና በውጭ ሆነው በተቀናጀ መንገድ ወንጀሉን ሲፈፅሙ በቆዩ ዳውድ ተፈሪ ለገሰ ፣ ደስታ ተገኝ አበጋዝ እና በግብረአበሮቻቸው ላይ የፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ በማውጣት፣ ውጭ ሀገር ያሉትን ከዱባይ ፖሊስ ጋር በትብብር በመስራት ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለው ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለሀገራችን ተላልፈው እንዲሰጡ አድርጓል። ተጠርጣሪዎቹ ምንም ዓይነት ሰውን ወደ ውጭ መላክ የሚያስችል ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው፣ በሀገር ውስጥ ያለው ቡድን ከውጪ ካለው ቡድን ጋር ትስስር በመፍጠርና በተቀናጀ መልኩ "በተለያዩ ካምፓኒዎች ስራ እናስቀጥራችኋለን’’ በማለት ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ዜጎችን ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመመልመል፣ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨትና ያልተገባ ተስፋ በመስጠት ከአንድ ሰው ከ320 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር በመቀበል ማታለያ የቱሪስት ቪዛ አዘጋጅተው በመላክ፣ በሀገር ውስጥ ባሉ ተባባሪዎቻቸው በተከፈተ የባንክ አካውንት ገንዘቡን በኢትዮጵያ ብር፣ በድርሃም እና በሪያል ገቢ የሚያስደርጉ መሆናቸውን ፖሊስ ደርሶበታል። ገንዘቡን የከፈሉ ተጎጂዎች ዱባይ እንደገቡ በጉልበት ሥራ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ፣ ከተጎጂዎች "ኮሚሽን" በሚል ተጨማሪ ገንዘብ በማስከፈል እንዲሁም የሁለት ወር የቱሪስት ቪዛ ሲያልቅ "የሁለት ዓመት የመኖሪያ ፍቃድ እናሰጣችኋለን፤ ካልከፈላችሁ ግን ወደ ኢትዮጵያ ትመለሳላችሁ" በማለት በአንድ ሰው 1 ሺህ 200 ድርሃም እንዲከፍሉ በማድረግ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ግፍና ስቃይ ሲያደርሱ ቆይተዋል ብሏል ፖሊስ። ተጠርጣሪዎቹ ተጎጂዎችን ከዱባይ ኤርፖርት ከተቀበሉ በኋላ ሰዎችን የሚያከማቹበት ቦታ በመውሰድ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ በርካታ ወንዶችንና ሴቶችን በማገት፣ ምግብ በስምንት ቀን አንድ ጊዜ ደረቅ ሩዝ በመስጠት ለከፍተኛ ርሃብ እና እንግልት እንዲሁም ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት ሲያደርሱባቸው መቆየታቸው ተደርሶበታል። በተጨማሪ ባደረገው ክትትል፣ በሀገር ውስጥ ሆነው ዱባይ ካሉት ግብረ-አበሮቻቸው በሚሰጣቸው ትዕዛዝ ሰዎችን መልምሎ በመላክና የባንክ አካውንት ከፍተው ገንዘብ እያሰባሰቡ የነበሩ 1ኛ ብዙአየሁ አውግቸው በሀይሉ እና 2ኛ ራህመት አበበ እሸቴ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራውን በስፋት በማከናወን ላይ መሆኑንም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገልጿል። ፖሊስ ምርመራውን ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች ተጠቅሞ ይህንን ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ለማጣራት እንዲሁም በእነዚህ ተጠርጣሪዎች አማካኝነት ከሀገር ወጥተው ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸው ከነበሩ ግለሰቦችና ተጎጂዎች ካሉበት ዱባይ የቀጥታ ቨርቹዋል የምስክርነት ቃላቸውን በመቀበል ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። ፖሊስ ሕጋዊ ፍቃድን ሽፋን በማድረግ ከሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ጋር በመመሳጠር ሕገ-ወጥ ተግባር የሚፈጽሙና በዜጎች ከፍተኛ ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጽሙ ኤጀንሲዎችም መኖራቸውን ማረጋገጡን ጠቅሶ በቀጣይ ምርመራውን በእነዚህ አካላት ላይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዚህ ውስብስብ ወንጀል ውስጥ በህጋዊ ሽፋን ህገ-ወጥ ተግባር የሚፈጽሙ አካላትን ለመያዝ ከዱባይ ፖሊስና በዱባይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በቅንጅት በመስራት ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ጠንካራ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናውን እያቀረበ፤ ኅብረተሰቡ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፣ 991 ነፃ የስልክ መስመር እና ሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያ (SPS)ን በመጠቀም መረጃ በመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፏል።
የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሥርአት ለህብረተሰቡ ፈጣንና ተደራሽ ፍትህ ለመስጠት እያስቻለ ነው
Jul 17, 2026 206
ድሬዳዋ፣ ሐምሌ 10/2018 (ኢዜአ):- የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሥርአት ለህብረተሰቡ ፈጣንና ተደራሽ ፍትህ በመስጠት ማህበራዊ ትስስር እንዲጠናከር እያስቻለ መሆኑ ተገለጸ። በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ድሬዳዋ ምድብ ችሎት የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሥርአትን ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል። መግባቢያ የሰነዱን የፈረሙት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ኪያር እና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ናቸው። የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሥርአት አንዳንድ ቤተሰባዊ ጉዳዮችን በማስማማት በፍጥነትና በውጤታማነት ለመጨረስ የሚያስችል የዳኝነት ሥርአት ነው። የጋራ መግባቢያ ሰነዱም በድሬዳዋ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ማዕከልን በማቋቋም ከባህል ሽማግሌዎች እና ከኃይማኖት ተቋማት አባቶች ጋር በመቀናጀት ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ኪያር በስምምነቱ ወቅቱ እንደገለጹት፤ ከአገራዊ ለውጡ በኋላ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች አዳዲስ ሪፎርሞች እና በቴክኖሊጂ የታገዙ አሰራሮችን በመተግበር ለህብረተሰቡ ፈጣንና ተደራሽ ፍትህ መስጠት ተችሏል። ማህበረሰብ ተኮር ፍትህ እያሰፈኑ ካሉት መካከል በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በመተግበር ላይ የሚገኘው የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ስርአት አንዱ መሆኑን አንስተዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ ሥርአቱ አንዳንድ ቤተሰባዊ ጉዳዮችን በማስማማት በፍጥነትና በውጤታማነት በመጨረስ የህዝብ አመኔታን ያተረፈ የዳኝነት ሥርአት ለመገንባት እያገዘ ነው። ለዚህም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በ13 ምድብ ችሎቶች ከውርስ፣ ከቤተሰብ እና መሰል ጉዳዮች ጋር የተያያዙ 1ሺህ 690 መዝገቦችን በስምምነት በመጨረስ ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ ፍትህ መስጠት ተችሏል ብለዋል። በዚህም የማስማማት ጥበብ እና ተቀባይነት ያላቸው የባህልና የኃይማኖት አባቶች የፍርድ ቤት ሥርአትና ነፃነትን ተከትለው የድርሻቸውን እንዲወጡ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ዛሬ በድሬዳዋ የተፈረመው የሥራ መግባቢያ ሰነድ ተቀባይነትና ዕውቀት ላላቸው የአገር ሽማግሌዎች፣ የኡጋዝ፣ የአባገዳና የእምነት አባቶች ተገቢውን ስልጠና በመስጠት ሥርአቱን ወደ ተግባር የሚያሸጋገር መሆኑን ገልጸዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው፣ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሥርአት በቤተሰብ፣ በዘመድ አዝማድ እና በነዋሪዎች መካከል የሚነሱ ክርክሮችን በማስማማት ማህበረሰባዊ ትስስርና ግንኙነት በዘላቂነት ለማስቀጠል ያስችላል ብለዋል። ይህም የፍርድ ቤቶችን ጊዜ በመቆጠብ የመዛግብት ፍሰት ለመቀነስ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህ ሥራ የሚሳተፉት ተቀባይነት ያላቸው የባህል አባቶች የህግ ሥርአትን ተከትለው እንደሚሰሩ አመልክተዋል። የስምምነት ፊርማው ሲፈጸም የአገር ሽማግሌዎች፣ የአባገዳ እና የኡጋዝ ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን ለስምምነቱ ውጤታማነት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ድሬዳዋ ምድብ ችሎት በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ማዕከል የሚከናወኑ ሥራዎች በየሦስት ወራት በተቋቋመ ቴክኒክ ኮሚቴ የሚገመገም መሆኑም ታውቋል።
የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ቀጣይነት ያለው አጀንዳችን ነው- ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ
Jul 17, 2026 259
አዳማ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ )፡-የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ቀጣይነት ያለው አጀንዳችን ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አወሉ አብዲ ገለጹ። 3ኛው የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ጠቅላላ ጉባኤ በአዳማ ገልመ አባገዳ አዳራሽ ዛሬ ተካሄዷል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ በወቅቱ እንደገለፁት በክልሉ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቷል። ይህም ለሰው ሰራሽና ለተፈጥሮ አደጋዎች በራስ አቅም ፈጣን ምላሽ ለመስጠትና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ድርሻው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል። ለተግባራዊነቱም ከኦሮሞ ሕዝብ የመረዳዳት ባህል የተቀዳውን ቡሳ ጎኖፋ ሥራ ላይ በማዋል ውጤት መገኘቱን ጠቁመዋል። ቡሳ ጎኖፋ የማኅበረሰቡን የመረዳዳት ባህል ይበልጥ ለማጎልበትና በምግብ ራስን ለመቻል ተደማሪ አቅም መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህም በክልሉ ዝናብ አጠር በሆኑ 59 ወረዳዎች ሊከሰቱ የሚችሉ ማህበራዊ ችግሮችን መቋቋም የሚያስችል ዝግጅት ለማድረግ ማገዙን ተናግረዋል። ተግባሩ ለሰዎች የሚሆን የምግብ ክምችትን ከማሳደግ ባለፈ ውሃን በማቆር የእንስሳት መኖ ለማልማት ማስቻሉን ጠቅሰዋል። የቡሳ ጎኖፋ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው ቡሳ ጎኖፋ በክልሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም እያገዘ ነው ብለዋል። ለዚህም በእርሻ ሥራና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እየተሰማራ ይገኛል ያሉት አምባሳደር አለማየሁ፣ ለዚህም በቡልቡላና በነቀምቴ ከተሞች የተቀናጀ የማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች እየገነባ ነው ብለዋል። በአዲሱ በጀት ዓመት ይህንን በቅንጅት ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ሃላፊ አቶ ሙሐመድ ጁንዳ እንደገለፁት በክልሉ እስካሁን ድረስ 29 ነጥብ 4 ሚሊዮን አባላት ማፍራት መቻሉን አንስተዋል። በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት በማሰባሰብ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል። በአይነት ከተሰበሰበው ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ እህልም ለተማሪዎች ምገባና ለመጠባበቂያነት መዋሉን ገልጸዋል። ተግባሩን ለማሳካትም በእርሻ፣ በእንስሳት እርባታና በመጋዘን ግንባታዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በማረሚያ ቤቶች የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል
Jul 17, 2026 274
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ በማረሚያ ቤቶች የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሚ በዶ ገለጹ። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፥ በማረሚያ ቤቶች የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት በቋሚ የጤና ሥርዓት ውስጥ በማካተት፣ ተደራሽነቱንና ጥራቱን ለማሻሻል የተቀናጀ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። የ2018 ዓ.ም የጤና ዘርፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር በሸገር ከተማ ዳለቲ ማረሚያ ቤት በይፋ ተጀምሯል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሚ በዶ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ ማረሚያ ቤቶች የሕግ የበላይነት የሚከበርባቸው ስፍራዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ ሰብዓዊነት የሚነግስባቸውና ታራሚዎች በዕውቀት፣ በክህሎትና በሥነ-ልቦና ታንጸው ወደ ማኅበረሰቡ የሚቀላቀሉባቸው የለውጥ ማዕከላት ናቸው ብለዋል። ታራሚዎች እንደማንኛውም ዜጋ ማግኘት ያለባቸውን ሰብዓዊና የጤና ክብካቤ ሁሉ የማግኘት መብት አላቸው ያሉ ሲሆን የሚያገኙትን የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል። የክረምት በጎ ፈቃድ የጤና አገልግሎትም ለህክምና ተደራሽነት የራሱ አጋዥ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፥ በማረሚያ ቤቶች የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ይበልጥ ማስፋት ያስፈልጋል ነው ያሉት። የመንግሥትና የግል የጤና ባለሙያዎችን በማስተባበር በየወቅቱ ሰፋ ያለ የሕክምናና የምርመራ ተግባርን ማከናወን እንደሚገባ አመላክተዋል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረ ሀገራዊ ንቅናቄ ሲሆን፣ ሚኒስቴሩም ይህንን ተሞክሮ በጤናው ዘርፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በጤና ዘርፉ በየዓመቱ የሚካሄደው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀገር ውስጥ ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በተጨማሪ፣ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዳያስፖራ የጤና ባለሙያዎችንና ሌሎች በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ እየተከናወነ ነው ብለዋል። ይህም ለበርካታ ዜጎች ተደራሽ የጤና አገልግሎትን ለማስፋት ዕድል እየፈጠረ መሆኑን አመልክተዋል። በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎችም ነጻ፣ ጥራት ያለውና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑን ጠቅሰዋል። በማረሚያ ቤቶቹ ያሉ የጤና ተቋማት አቅም እንዲጠናከርና የአገልግሎት ደረጃቸው እንዲሻሻል የሚያስችሉ ሥራዎች እንደሚከናወኑ አስረድተዋል። መርሐ ግብሩ የአንድ ቀን ወይም የአንድ ጊዜ እንቅስቃሴ ሳይሆን፣ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የጤና ተቋማትና ማረሚያ ቤቶች በቀጣይነት የሚተገበር ዘላቂ ፕሮግራም መሆኑንም አብራርተዋል። በመርሐ ግብሩ የተሳተፉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ አገራት ድርጅት (አካፓድ) ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች
Jul 17, 2026 263
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 10/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ አገራት ድርጅት (አካፓድ) ሊቀመንበር ሆና ተመርጣለች። 121ኛው የአካፓድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ሐምሌ 8-9 ቀን 2018 ዓ.ም. ቤልጅየም መዲና ብራስልስ ተካሂዷል። በጉባኤው ላይ በገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው የተመራ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ የልኡካን ቡድን ኢትዮጵያን በመወከል ተሳትፏል። የሚኒስትሮቹ ስብሰባ የትኩረት አጀንዳዎች የማላቦ ዲክላሬሽን አተገባበር ሂደትን መገምገም፣ የድርጅቱን የፋይናንስ አቅም በዘላቂነት ለመገንባት ስለሚወሰዱ እርምጃዎች መምከር ላይ ያተኮረ ነው። እንዲሁም የድርጅቱ ማሻሻያ ሂደት ያለበትን ደረጃ መገምገም፣ የሳሞአ ስምምነትን የትግበራ ሂደት መገምገም እንዲሁም ሌሎች የድርጅቱንና የአባል ሀገራትን ጥቅም ስለሚያስጠብቁ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። ኢትዮጵያ አቋሟን የሚያንጸባርቁ እና ድርጅቱን በፕሬዚዳንትነት በምትመራበት ወቅት የምትከተላቸውን የትኩረት አቅጣጫዎች የሚያመለክቱ ንግግሮች አቅርባለች። በጉባኤው ማጠናቀቂያም ኢትዮጵያ ከኦገስት 1 ቀን 2026 እስከ ጃንዋሪ 31 ቀን 2027 የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓስፊክ አገራት ድርጅት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች። ኢትዮጵያ በቀጣይ ስድስት ወራት የጉባኤው ሰብሳቢነቷ ወቅት ቅድሚያ የምትሰጣቸውን የትኩረት ጉዳዮች አስተዋውቃለች። እነዚህም ከወቅቱ ጂኦፖለቲካዊ እውነታ አኳያ የድርጅቱን ጽ/ቤትና የአባል አገራትን የፖሊሲ ነጻነት ማረጋገጥ፣ በራስ አቅም ሊከናወኑ ስለሚችሉ የልማት ስራዎችና የአገር ውስጥ ሃብት ማሰባሰብ የኢትዮጵያን ተሞክሮ በማጋራት በምሳሌነት መምራት፣ በተቋሙ ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲጠናከር በማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲወገድ መስራት፣ የድርጅቱ የፋይናንስ እጥረት በዘላቂነት እንዲፈታ የተጀመረው የሀብት ማሰባሰብ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ እና የአውሮፓ ህብረት እና የአካፓድ ግንኙነት መሠረት የሆነው የሳሞአ ስምምነት አፈጻጸም በተሻለ መልኩ እንዲጓዝ መስራት ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ኢትዮጵያ ድርጅቱ ከተመሰረተ እ.ኤ.አ. 1975 ጀምሮ ሁለት ጊዜ (እ.ኤ.አ. ከነሀሴ 1 ቀን 1986 እስከ ጥር 31 ቀን 1987 እና ከየካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ ሀምሌ 31 ቀን 2017 ) ተቋሙን በሰብሳቢነት ማገልገሏን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የአካፓድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሆና መመረጧ፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን የዲፕሎማሲ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በድጋሚ የሚያረጋግጥ ታላቅ ስኬት መሆኑም ተገልጿል። ይህ ታሪካዊ ኃላፊነት ኢትዮጵያ በደቡብ-ደቡብ ሁለንተናዊ ትብብር ላይ ያላትን ተሳትፎ ይበልጥ ከማጠናከሩ ባሻገር፣ ከአባል አገራቱና ከአውሮፓ ህብረት ጋር የሚደረጉ ትብብሮችን በበላይነት ለመምራት፣ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር እና መልካም ገፅታዋን ለመገንባት የዲፕሎማሲ ዕድሎችን ይከፍታል። ጉባኤውም ለኖቬምበር 2026 ዓ.ም. የታቀደው የ122ኛው የአካፓድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት አዲስ አበባ እንዲካሄድ በድርጅቱ አባል ሀገራት ተወስኖ ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያስከበረችውን ስትራቴጂክ ጥቅም በቀይ ባሕር የመድገም ሕጋዊና ተፈጥሯዊ መብት አላት
Jul 17, 2026 233
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 10 /2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያስከበረችውን ስትራቴጂክ ጥቅም በቀይ ባሕር የመድገም ሕጋዊና ተፈጥሯዊ መብት አላት ሲሉ አሜሪካዊው የፖለቲካ ተንታኝ አንድሪው ኮሪብኮ ገለጹ። ሕዳሴ ግድብ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያፋጥን ስትራቴጂካዊ የልማት ውጤት መሆኑንም አስገንዝበዋል። አንድሪው ኮሪብኮ እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት የተስተካከለ የውሃ ፍሰት በመፍጠር፣የጎርፍ መጥለቅለቅንና የውሃ ብክነትን የታደገ አህጉራዊ ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ ግድቡን መገንባቷ ሀገራዊና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያፋጥን የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር አቅም እንዲጎለብት ማስቻሉን ተናግረዋል። በዚህም ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚላከው የኤሌክትሪክ ኃይል፣ቀጣናዊ ትብብርን በማጎልበት ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ውህደት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የገነባችበት መንገድ፣በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል የሚለውን የግብፅ መሰረተ ቢስ አጀንዳ ሙሉ ለሙሉ የቀለበሰ መሆኑን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያስከበረችውን ስትራቴጂክ ጥቅም በቀጣይም በቀይ ባሕር የመድገም ሕጋዊና ተፈጥሯዊ መብት እንዳላት አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚከተሉት ስትራቴጂ በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ ግፊትና በተላላኪዎች አማካይነት የሚፈጸም መሆኑን ጠቁመዋል። ስግብግብ ፍላጎትና በሌሎች ሀገር ላይ የሚጫን ተስፋፊነትን ያነገቡ የግብፅ ገዥ መደቦች በኢትዮጵያ ውስጥና በኤርትራ የሚገኙ ፅንፈኛና ታጣቂ ቡድኖችን እንደ መሳሪያ በመጠቀም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማደናቀፍ በተደጋጋሚ ሲሞክሩ መስተዋላቸውን አውስተዋል። ይህ የማያዋጣ አካሄድ መሆኑን በመጠቆም በተፋሰሱ ሀገራት የሚነሱ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ጥያቄዎችን፣የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካዊ መፍትሔ በሚል መርህ በሰለጠነ ውይይትና በጋራ ተጠቃሚነት መፍታት እንደሚቻል አስረድተዋል። የዓባይ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ውጥረት ከሚያባብስ አካሄድ ሊቆጠቡ ይገባል ያሉት ተንታኙ፥ ቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋትን በማስቀደም የጋራ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ትብብር ማድረግ እንደሚኖርባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።
በዞኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የተገኘውን ስኬት ለማስቀጠል ይሰራል
Jul 17, 2026 101
ምስራቅ ጎጃም ፤ሐምሌ10/2018(ኢዜአ)፡- በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች የተገኝውን ስኬት ለማስቀጠል ርብርብ እንደሚደረግ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር አስታወቀ። በዞኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በልማትና መልካም አስተዳደር ዘርፎች የነበሩ አፈፃፀሞችን የሚገመግምና የ2019 በጀት ዓመት እቅድን የሚያስተዋውቅ መድረክ በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሂዷል። የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዋለ አባተ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በማከናወን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መሰራቱን ገልጸዋል። በተለይ በመኸር ሰብል፣ በመስኖ እና የእንስሳት ሃብት ልማት፣በስራ እድል ፈጠራ፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ስራዎች የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል። ከዚሁ ጎን ለጎንም ህብረተሰቡንና የፀጥታ ኃይሉን በማስተባበር ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር የተከናወኑት ተግባራት ለውጥ እንዲመዘገብ አያደረጉ መሆኑን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅትም የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍም በየተቋማቱ በዲጅታል ቴክኖሎጀ የታገዘ ቀልጣፋ፣ ተጠያቂነት ያለውና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ የታዩ ክፍተቶችን ለማረምና ጠንካራ ጎኖችን ደግሞ ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በመታቀዱ የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ጥላሁን ንጋቱ በበኩላቸው፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የአርሶ አደሩንና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ መደረጉን አብራርተዋል። በዚሁ ወቅት በመኸር ሰብል ልማት ከ21 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት በማምረት ከእቅድ በላይ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መቻሉን አስረድተዋል። የመንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ማናየ አዳነ በበኩላቸው ፤በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዘርፉ ስኬታማ ስራዎችን ለማከናወን መቻሉን ነው የተናገሩት።
ከጋምቤላ ክልል ጋር የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በሌሎች ሰው ተኮር ስራዎች ዙሪያ በትብብር እንሰራለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Jul 17, 2026 154
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 10/ 2018 (ኢዜአ)፦ ከጋምቤላ ክልል ጋር የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በሌሎች ሰው ተኮር ስራዎች ዙሪያ በትብብር እንሰራለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል፡፡ በዚህም ወቅት በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ፣ በኮሪደር ልማት፣ እንዲሁም በሌሎች የሰው ተኮር ስራዎች ዙሪያ እርስ በርስ ልምድ እየተለዋወጥን፣ትብብራችንን አጠናክረን በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የኢትዮጵያ የዲጂታል እመርታ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማሳለጥ ውጤታማነት እያሳደገ ነው
Jul 17, 2026 179
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የዲጂታል እመርታ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማሳለጥ ውጤታማነት እያሳደገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ30ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፣ በሀገሪቱ በትምህርት ዘርፍ የተመዘገበው ስኬት እጅግ የሚያኮራ እና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጸዋል። መንግሥት ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ለጥራት፣ ለቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የሰጠው ትኩረት ዘርፉን በአዲስ ምዕራፍ ላይ ለማስቀመጥ የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ይህ የተቀናጀ ጥረት የትምህርት ጥራትን አስተማማኝ መሰረት ላይ ለመጣልና የትውልዱን ብቃት ለማሳደግ በሚደረገው ጉዞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ መንግሥት በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ስብራቶችን ለመጠገንና ጥራትን ለማረጋገጥ በለውጡ ዓመታት መጠነ ሰፊ የሪፎርም ሥራዎችን አከናውኗል። በዚህም የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን በዘላቂነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ተግባራዊ መደረጋቸውን ገልጸዋል። ተማሪዎችን በቴክኖሎጂ፣ በእውቀትና በክህሎት ለማብቃት ከዋና ዋና ከተሞች እስከ ገጠር ትምህርት ቤቶች የኮምፒውተር ላብራቶሪዎችን የማደራጀትና የማስፋፋት ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል። አጠቃላይ የትምህርት ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት። ዘመኑ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እንደመሆኑ መጠን ይህንን ቴክኖሎጂ ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጋር ማጣመር የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ሥርዓቱን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ለመደገፍ ሰፊ የዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል። ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር የመምህራንን የሥራ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ፣ የተማሪዎችንና የመምህራንን ጊዜ በመቆጠብ የትምህርት ጥራትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የላቀ ፋይዳ እንደሚኖረው አስረድተዋል። በተጨማሪም፣ ይህ የፈጠራ ሽግግር የክፍል ውስጥ ትምህርትን ይበልጥ ሳቢና ቀልጣፋ ከማድረጉ በላይ፣ መምህራን በክህሎት የበለጸገ እና ለቴክኖሎጂው ዓለም ዝግጁ የሆነ ትውልድ እንዲያፈሩ ያስችላቸዋል ነው ያሉት። ቴክኖሎጂ በትምህርት ዘርፍ ላቅ ያለ ሚና ያለው በመሆኑ፣ ሀገራዊ ተደራሽነቱን ለማስፋት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ አረጋግጠዋል።
የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ለምርምር ስራዎቹ ተደራሽነት ከኢዜአ ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ ይቀጥላል
Jul 16, 2026 439
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 9/2018 (ኢዜአ) ፦ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በምርምርና ሃገር በቀል እውቀቶች የሚያከናውናቸውን ስራዎች ተደራሽነት ለማስፋት ከኢዜአ ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተመስገን ደበሎ (ዶ/ር) ገለጹ። የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በምርምር ስራዎችና ሀገር በቀል እውቀቶች ተደራሽነት ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት፤ ኢዜአ ሰፊ ተደራሽነት ያለው ተጽዕኖ ፈጣሪ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም ስለሆነ ስምምነቱ ለዩኒቨርሲቲው ትልቅ ዋጋ አለው። ዩኒቨርሲቲው ከሶስተኛው ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል እንደሚመደብ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ የመማር ማስተማር፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛልም ብለዋል። በተለይም በግብርና፣ በማዕድን እና ከገዳ ስርዓት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሀገር በቀል እውቀቶች ከዘመናዊ የትምህርት ስርዓት ጋር በማቀናጀት ለሀገር እድገት የሚጠበቅበትን እየተወጣ መሆኑንም አስረድተዋል። ስምምነቱ ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን ተግባራት በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ለማስተዋወቅ፣ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር ዶክተር ተመስገን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ በበኩላቸው ከ85 ዓመታት በላይ የካበተ ልምድ ያለው ኢዜአ፤ በለውጥ ሂደት ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው ሁለቱ ተቋማት የፈጸሙት ስምምነትን የያዟቸውን የጋራ ግቦች ለማሳካት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል። በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችና ሀገር በቀል እውቀቶችን በአህጉራዊ ደረጃ ለማስተዋወቅ ኢዜአ በዘርፉ ካለው የላቀ አቅም አኳያ ተመራጭ አጋር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ስምምነቱ በመደመር እሳቤ ሀገር በቀል እውቀትን ተጠቅሞ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ለተያዘው ግብ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አስረድተዋል። ኢዜአ ከዜና ስራዎች ባሻገር በዓለም አቀፍ ምርምር፣ በዶክመንተሪ እና በተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲው በአፍሪካ ደረጃ ተጠቃሽ ተቋም ለመሆን ለሚያደርገው ጥረት አጋዥ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
አገልግሎቱ የአሰራር ሥርዓቱን በማዘመን ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል
Jul 16, 2026 423
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 9 /2018 (ኢዜአ)፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋት፣ የአሰራር ሥርዓቱን በማዘመን እና ምቹ የስራ ከባቢን በመፍጠር የተገልጋዩን እርካታ የሚያሳድጉ ተጨባጭ ለውጦች ማምጣቱን ዋና ዳይሬክተሯ ሰላማዊት ዳዊት ገለጹ፡፡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፤ ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፥ተቋሙ ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋት፣ የአሰራር ሥርዓቱን በማዘመን እና ምቹ የስራ ከባቢን በመፍጠር የተገልጋዩን እርካታ የሚያሳድጉ ተጨባጭ ለውጦች ማምጣቱን ገልጸዋል። የፓስፖርት እና የቪዛ አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች የይለፍ ሰነዶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደግፈው በጥራት እና በደህንነት እንዲመረት ተደርጓል ብለዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ፓስፖርቶች ታትመው ለዜጎች መሰራጨታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት መስጫ ማዕከላት ከነበሩበት 12 ወደ 23 በማሳደግ ተደራሽነቱ ማስፋፋት መቻሉን ጠቅሰው፥ በአየር እና በየብስ የድንበር መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ከ7 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ መንገደኞች ቀልጣፋ አገልግሎት መሰጠቱን ጠቅሰዋል፡፡ የተቋሙን የሰው ኃይል አደረጃጀት እና ልማት በማሻሻል አገልግሎቱን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ለውጡን ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደነበሩም ገልጸዋል።
የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እየፈታ ነው
Jul 14, 2026 1025
አርባ ምንጭ፤ ሐምሌ 7/2018 (ኢዜአ)፡-የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መንግስታዊ አሰራርን በማቀናጀት ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንደፈታላቸው ተገልጋዮች ገለጹ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ክላስተር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው ተገልጋዮች እንዳሉት የማዕከሉ ቀልጣፋ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አስችሏል፡፡ ከተገልጋዮቹ መካከል ፓስፖርት ለማውጣት በማዕከሉ የተገኙት አቶ ገብረእግዚአብሔር ሃይለስላሴ በማዕከሉ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘታቸው ጉዳያቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ አስችሏቸዋል። ይህም ቀደም ሲል በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ሲስተዋል በነበረ መጓተት ይፈጠር የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግር መፍታት ችሏል ብለዋል። የማዕከሉ ሠራተኞች አክብሮት የተሞላበት አገልግሎት እንደሰጧቸው ገልጸው፣ በማዕከሉ የተለያዩ አገልግሎቶች መስጠታቸው ጊዜ፣ ወጪና እንግልትን አስቀርቶልናል ብለዋል። አገልግሎቱ በዲጂታል ሥርአት የታገዘ መሆኑ ቀልጣፋና ከሙስና የጸዳ አገልግሎት በፍትሀዊነት ለማግኘት እንዳስቻላቸው ገልጸዋል። ዜጎችን ለምሬት ይዳርግ የነበረውን የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ ያስተካከለው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለጹት ደግሞ ወይዘሮ ዘላለም አሸናፊ ናቸው። የአገልግሎቱ ቀልጣፋና ውጤታማነት መንግስት አሰራሩን በማዘመን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። እሳቸውም የንግድ ፈቃዳቸውን ለማውጣት በመጡበት ወቅት ወደ ተለያዩ ተቋማት መሄድ ሳያስፈልጋቸው አገልግሎቶቹን ከመሶብ አገልግሎት ብቻ በተሟላ ሁኔታ ማግኘት መቻላቸውን ገልጸዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ክላስተር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ይበቃል አሰፋ በበኩላቸው በማዕከሉ አምስት የክልልና አራት የፈደራል ተቋማት 32 አይነት አገልግሎቶች በዲጅታል ታግዘው እየተሰጡ መሆኑን አስረድተዋል። ይህም ዜጎች ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ከእንግልት፣ ከእጅ መንሻና መሰል ችግሮች እንደታደጋቸው ገልጸዋል። አሰራሩ መዘመኑ ስራን ከማቀላጠፍ ባለፈ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በዘላቄታው ለመፍታት አስችሏል ብለዋል።
ስፖርት
አርጀንቲና እንግሊዝን በመርታት ለፍጻሜ አለፈች
Jul 15, 2026 1274
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር አርጀንቲና ከመመራት ተነስታ እንግሊዝን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ማምሻውን በአትላንታ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የ25 ዓመቱ የክንፍ መስመር ተጫዋች አንቶኒ ጎርደን በ55ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል እንግሊዝን መሪ አድርጓል። ሞርጋን ሮጀርስ ኳሷን አመቻችቶ አቀብሏል። አርጀንቲና ከግቡ መቆጠር በኋላ ተጭና ተጫውታለች። ኤንዞ ፈርናንዴዝ በ85ኛው ደቂቃ በግሩም ሁኔታ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል አርጀንቲናን አቻ አድርጓል። ላውታሮ ማርቲኔዝ በ92ኛው ደቂቃ የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። እንግሊዝ መሪነቷን ማስጠበቅ አልቻለችም። ጨዋታው ጉልበት እና ኃይል የተቀላቀለበት ነበር። በርካታ ጥፋቶችም ተሰርተዋል። ሊዮኔል ሜሲ ለ12ኛ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ለግብ የሚሆን ኳስ በማቀበል አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ስምንት ጎሎችን አስቆጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ አርጀንቲና ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ አልፋለች። የወቅቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ አርጀንቲና ለስድስተኛ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ደርሰዋል። አርጀንቲና በፍጻሜው ከስፔን ጋር ትገናኛለች። እንግሊዝ ለሁለተኛ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ የማለፍ ህልሟ አልተሳካም። እንግሊዝ ከፈረንሳይ ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ይጫወታሉ። ስፔን ከአርጀንቲና ዋንጫውን ለማንሳት እሁድ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም ይፋለማሉ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስፖርት መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ብቁ ዜጋ የማፍራት ሥራ ተጠናክሯል
Jul 15, 2026 527
ወልቂጤ፤ ሐምሌ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በክልሉ የስፖርት መሰረተ ልማትን በማስፋፋት በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ዜጋን ለማፍራት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ገለጸ። በወልቂጤ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር ተካሄዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ሌሊሾ እንደገለጹት፤ በክልሉ የስፖርት ልማትን በማስፋፋት በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ጤናማና ብቁ ዜጋ ለማፍራት እየተሰራ ነው። ለዚህም በየአካባቢው የስፖርት ማዘወተሪያዎችን ከማስፋፋት ባለፈ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተው፣ የዛሬው ስፖርታዊ እንቅስቃሴም የዚሁ አካል ነው ብለዋል። በተለይ ወጣቶች ስፖርትን በማዘወተር ያላቸውን ተሰጥኦ እንዲያጎለብቱ መሰራቱን ገልጸዋል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴው የእርስ በርስ ትስስርንም ያጠናክራል ብለዋል። የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በበኩላቸው፤ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከጤና ጥቅሙ ባለፈ የዜጎችን የአብሮነት እሴት የሚያጎለብትና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመቅረጽ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም ከተማዋ በብስክሌት፣ በቅርጫት ኳስ፣ በእግር ኳስ ጠንካራ ስፖርተኞች ለማፍራት የሚያስችል የስፖርት መሰረተ ልማቶችን እየገነባች መሆኑን አክለዋል። ይህም ለከተማዋ ኢኮኖሚና የስፖርት ቱሪዝም መነቃቃት ጉልህ ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከተሳታፊዎች መካከል ኢንስፔክተር አብድልሰመድ መሃመድ፤ በከተማዋ የስፖርት ልማቱን የሚያቀላጥፉ መሰረተ ልማቶች መከናወናቸው የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሀግብሩ በስፖርት ጤናማና ብቁ ዜጋ ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት አጋዥ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ አቶ ካሚል ጀማል ናቸው። መርሀግብሩ የእርስ በርስ ግንኙነትን በማጠናከር የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን በጋራ ለማከናወን ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸውም ጠቅሰዋል።
ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ማን ያልፋል? እንግሊዝ ወይስ አርጀንቲና? ተጠባቂው ፍልሚያ!
Jul 15, 2026 681
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ሁለተኛ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር እንግሊዝ ከአርጀንቲና ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ጨዋታው ምሽት አራት ሰዓት ላይ በአትላንታ ስታዲየም ይካሄዳል። እንግሊዝ በሩብ ፍጻሜው ኖርዌይን 2 ለ 1 በማሸነፍ የመጨረሻ አራት ውስጥ ገብታለች። ሶስቱ አናብስቶች ለግማሽ ፍጻሜ ሲያልፉ የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ ነው። ተጋጣሚዋ አርጀንቲና ስዊዘርላንድን 3 ለ 1 በመርታት ለግማሽ ፍጻሜ አልፋለች። የወቅቱ የዓለም ሻምፒዮን አርጀንቲና አራት ውስጥ ስትገባ ለሰባተኛ ጊዜ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የደቡብ አሜሪካዋ ሀገር ከዚህ ቀደም ያደረጋቻቸውን ስድስት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በሙሉ በማሸነፍ ስኬታማ ክብረ ወሰን አላት። እንግሊዝ በበኩሏ ከሶስት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች መካከል ያሸነፈችው አንዱን ብቻ ነው። ሁለቱ ሀገራት በዓለም ዋንጫው ከዚህ ቀደም አምስት ጊዜ ተገናኝተዋል። እ.አ.አ በ1962 በቺሊ በተካሄደው ሰባተኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በምድብ አራት ተገናኝተው እንግሊዝ አርጀንቲናን 3 ለ 1 አሸንፋለች። እንግሊዝ እ.አ.አ በ1966 ባዘጋጀችው ስምንተኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ላይ ተገናኝተው አዘጋጇ ሀገር 1 ለ 0 ያሸነፈች ሲሆን እስከ መጨረሻው በመጓዝ ምዕራብ ጀርመን (በወቅቱ በነበረው ስያሜዋ) በማሸነፍ ዋንጫውን አንስታለች። በሀገራቱ የዓለም ዋንጫ ግንኙነት ውስጥ ሁሌም የሚታወሰው ጨዋታ እ.አ.አ በሜክሲኮ አዘጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በሩብ ፍጻሜው የተገናኙበት መርሐ ግብር ነው። አርጀንቲና እንግሊዝን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አልፋለች። ዲያጎ ማራዶና ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በወቅቱ ማራዶና በእጁ ያስቆጠራት አወዛጋቢ ጎል “ የፈጣሪ እጅ” (Hand of God) እየተባለች ትጠራለች። አርጀንቲና ፍጻሜ በመድረስ ምዕራብ ጀርመንን (በወቅቱ የነበረው አጠራሯ) በማሸነፍ ዋንጫውን ለሁለተኛ ጊዜ አንስታለች። ፈረንሳይ እ.አ.አ በ1998 ባዘጋጀችው 16ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በሩብ ፍጻሜው መርሐ ግብር 16 ውስጥ ተገናኝተው በጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቆ አርጀንቲና በመለያ ምት 4 ለ 3 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜው አልፋለች። ቡድኖቹ ለመጨረሻ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተገናኙት ኮሪያ ሪፐብሊክ እና ጃፓን እ.አ.አ በ2002 ባዘጋጁት 17ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ላይ ነበር። በምድብ ስድስት ባደረጉት ጨዋታ እንግሊዝ በዴቪድ ቤካም የፍጹም ቅጣት ምት ጎል 1 ለ 0 አሸንፋለች። ሁለቱ ሀገራት ከ24 ዓመታት በኋላ በመድረኩ ለፍጻሜ ለማለፍ የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረትን ስቧል። ብሔራዊ ቡድኖቹ በውድድር እና ወዳጅነት ጨዋታዎች በአጠቃላይ 14 ጊዜ ተገናኝተው እንግሊዝ ስድስት ጊዜ ድል ሲቀናት አርጀንቲና በሶስቱ ጨዋታዎች አሸንፋለች። በቀሪ አምስት ጨዋታዎች ላይ አቻ ተለያይተዋል። በ14ቱ ጨዋታዎች ላይ እንግሊዝ 21 ጎሎችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ አርጀንቲና 15 ግቦችን አስቆጥራለች። እንግሊዝ የዓለም ዋንጫን አንድ ጊዜ ስታነሳ አርጀንቲና የሶስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ናት። በዘንድሮው ዓለም ዋንጫ በተመሳሳይ ስድስት ግቦችን ያስቆጠሩት ሃሪ ኬን እና ጁድ ቤሊንግሃም በዛሬው ጨዋታ የሚጠበቁ ተጫዋቾች ናቸው። የ39 ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ በጨዋታው ትኩረትን ያገኘ ተጫዋች ነው። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ስምንት ግቦችን በማስቆጠር ለኮከብ ግብ አግቢነት እየተፎካከረ ይገኛል። ሜሲ በአጠቃላይ በዓለም ዋንጫ 21 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። የአማካይ ተጫዋቹ ሮድሪጎ ዲ ፖል ከአርጀንቲና በኩል በጨዋታው ልዩነት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል። አርጀንቲና በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በርካታ ግቦችን (17) ያስቆጠረች ሀገር ናት። እንግሊዝ ለሁለተኛ ጊዜ፣ አርጀንቲና ለሰባተኛ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ለማለፍ ይፋለማሉ። ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል። አሸናፊው ሀገር ከስፔን ጋር በፍጻሜው ይገናኛል። ትናንት በተደረገው የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ስፔን ፈረንሳይን 2 ለ 0 በመርታት የፍጻሜው ተፋላሚ ሆናለች።
ስፔን ፈረንሳይን በመርታት ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ አለፈች
Jul 14, 2026 854
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተጠባቂ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ስፔን ፈረንሳይን 2 ለ 0 አሸንፋለች። ማምሻውን በዳላስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ኦያርዛባል በ22ኛው ደቂቃ የመጀመሪያውን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። ፍጹም ቅጣት ምቱ የተገኘው የፈረንሳዩ ተከላካይ ሉካ ዲኝ በላሚን ያማል ላይ በሰራው ጥፋት ነው። የ29 ዓመቱ አጥቂ ኦያርዛባል በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት አምስት አድርሷል። ፔድሮ ፖሮ በ58ኛው ደቂቃ ሁለተኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። በጨዋታው ስፔን በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድሎችን በመፍጠር አንጻራዊ ብልጫ ነበራት። የፈረንሳይ የአጥቂ መስመር ክፍል በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ያሳየውን አስፈሪነት በዛሬው ጨዋታ መድገም አልቻለም። በአጠቃላይ ፈረንሳይ በሚጠበቀው የብቃት ደረጃ ላይ አልነበረችም። የ25 ዓመቱ የፈረንሳይ ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ በ30ኛው ደቂቃ በጉዳት ምክንያት ተቀይሮ ወጥቷል። ውጤቱን ተከትሎ ስፔን ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ አልፋለች። ስፔን ከ19ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ የፍጻሜውን ትኬት ቆርጣለች። የአንድ ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ስፔን በዘንድሮው ውድድር ምንም ሽንፈት ያላስተናገደች ሀገር ሆናለች። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫም የተቆጠረባት አንድ ግብ ብቻ ነው። ስፔን በፍጻሜው ከእንግሊዝ እና አርጀንቲና አሸናፊ ጋር ትጫወታለች። ለዋንጫው የተጠበቀችው ፈረንሳይ ለፍጻሜ መብቃት አልቻለችም። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ሽንፈቷን አስተናግዳለች። የሁለት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ፈረንሳይ ለአምስተኛ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ የማለፍ ህልሟ ሳይሳካ ቀርቷል። ፈረንሳይ ከእንግሊዝ እና አርጀንቲና ተሸናፊ ጋር ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ትጫወታለች። በዓለም ዋንጫው ስምንት ጎሎችን ያስቆጠረው ኪሊያን እምባፔ ለሁለት ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ የማለፍ ህልሙ ሳይሳካ ቀርቷል። እምባፔ አሁንም ለከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱ መፎካከሩን ይቀጥላል። የ27 ዓመቱ አጥቂ 21ኛ የዓለም ዋንጫ በማድረግ ለፈረንሳይ በውድድሩ ላይ በርካታ ጨዋታዎችን ያደረገ ተጫዋች ሆኗል። በነዚህ ጨዋታዎች ላይ 20 ግቦችን አስቆጥሯል። ሁለተኛው የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ነገ በእንግሊዝ እና አርጀንቲና መካከል ይደረጋል።
አካባቢ ጥበቃ
የጭስ አልባ ትራንስፖርት ዘርፍን ለማስፋፋት ከዓለም ባንክ ጋር በአጋርነት ለመሥራት ተስማምተናል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Jul 17, 2026 233
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት አገልግሎት ይበልጥ ለማሻሻል ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ከሆኑት ማርያም ሳሊም ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እና በተለይም የጭስ አልባ ትራንስፖርት (E-mobility) ተደራሽነትን በስፋት ለማዳረስ እያከናወነ ባለው ሥራ ዙሪያ በዝርዝር መምከራቸውን ገልጸዋል። በውይይታቸውም አስተዳደሩ የጀመራቸውን ሥራዎች ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል። እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ የግል ተቋማትን ለመደገፍ ከዓለም ባንክ ጋር በአጋርነት እና በትብብር በጋራ ለመሥራት ተግባብተናል ብለዋል። ከንቲባ አዳነች ለዳይሬክተሯ ማርያም ሳሊም እና አብረዋቸው ለነበሩት የቴክኒካል ቡድን አባላት በራሳቸው እና በአዲስ አበባ ሕዝብ ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በምዕራብ ሸዋ ዞን በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ8 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በፍራፍሬ እየለማ ነው
Jul 16, 2026 399
አምቦ፤ሐምሌ 9 /2018 (ኢዜአ)፦በምዕራብ ሸዋ ዞን በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 8 ሺህ 463 ሄክታር መሬት የሚሸፍን የፍራፍሬ ልማት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። በምዕራብ ሸዋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት የደን ልማት ባለሙያ አቶ ጉደታ ጡር ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በተያዘው ክረምት ከ15 ሚሊዮን በላይ የተሻሻሉ የፍራፍሬ ችግኞች ተዘጋጅተው እየተተከሉ ይገኛሉ። የሚተከሉት የፍራፍሬ ችግኞች በአካባቢው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ማኅበረሰቡ ተጨማሪ ገቢ በማግኘት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን እንዲያሳድግ ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸውም ገልጸዋል። በመርሐ ግብሩ ከተዘጋጁት የፍራፍሬ ዝርያዎች መካከል ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ ሙዝ እና አፕል እንደሚገኙበትም ባለሙያው ጠቁመዋል። በልማት ሥራው ዙሪያ ለአርሶ አደሮቹ ሥልጠና መሰጠቱን የጠቀሱት አቶ ጉደታ፤ በአሁኑ ወቅትም አስፈላጊው ሙያዊ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስረድተዋል። በዞኑ በክረምቱ ወቅት በአጠቃላይ በ8 ሺህ 463 ሄክታር መሬት ላይ የፍራፍሬ ችግኝ ተከላ እየተካሄደ መሆኑንና በዚህ የልማት ሥራ ላይ 131 ሺህ 576 አርሶ አደሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙም አስታውቀዋል። በዞኑ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከመደበኛ የግብርና ሥራቸው በተጓዳኝ በፍራፍሬ ልማት ላይ በመሰማራታቸው ተጨማሪ ገቢ ማግኘት መቻላቸውን ጠቅሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ ባለፉት ዓመታት የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች የአፈር መሸርሸርን ለመከላከልና የደረቁ ምንጮች እንዲያንሰራሩ በማድረጋቸው፣ የአርሶ አደሮቹን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አክለዋል። በምዕራብ ሸዋ ዞን በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን ከ11 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በፍራፍሬ ልማት መሸፈኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ በመቅረጽ፣ ለአረንጓዴ ልማት ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይታለች
Jul 16, 2026 297
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 9 /2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ በመቅረጽ፣ ለአረንጓዴ ልማት ያላትን ፅኑ ቁርጠኝነት በተግባር ማሳየቷን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ ፀጋ ገለጹ። በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር ላይ ለተቀረጸው የምርምር ፕሮጀክት የተዘጋጀ የማስጀመሪያ አውደ ጥናት እየተካሄደ ይገኛል። በአውደ ጥናቱ መክፈቻ ላይ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ በመቅረጽ፣ ለአረንጓዴ ልማት ያላትን ፅኑ ቁርጠኝነት በተግባር አሳይታለች። ይህም በታዳሽ ኃይል መስፋፋት፣ በዘላቂ ግብርና እና ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ በሆኑ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በግልጽ ይንጸባረቃል ብለዋል። አረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት የመንግሥትን ጥረት ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አካላት ንቁ ተሳትፎ እንደሚጠይቅም አንስተዋል። በተለይም አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ማሳተፍ ወሳኝና አማራጭ የሌለው ተግባር መሆኑን ገልጸው፤ እነዚህ ኢንተርፕራይዞች ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግር፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለእሴት ሰንሰለት ዕድገት፣ ለሀገር ውስጥ ምርት እንዲሁም ለኢኮኖሚ ብዝኃነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስገንዝበዋል። እነዚህ ኢንተርፕራይዞች ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግር፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለእሴት ሰንሰለት ዕድገት፣ ለሀገር ውስጥ ምርት እንዲሁም ለኢኮኖሚ ብዝኃነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስገንዝበዋል። ወደ አረንጓዴ ማኑፋክቸሪንግ የሚደረገው ሽግግር የመንግስት፣ የግልና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ አካሄድ ያስፈልጋል ብለዋል። በኢንስቲትዩቱ በአምራች ዘርፍ የማዕድን ዘርፍ ክፍል ኃላፊ እና መሪ ተመራማሪ ነጻነት ጆቴ (ዶ/ር)፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ አካባቢን የማይበክልና ዘላቂ የምርት ሥርዓት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ የአረንጓዴ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን የሚዳስስ ጥናት እንደሚደረግ ነው የገለጹት። የጥናቱ ዋና ዓላማ የኢንተርፕራይዞቹን ወቅታዊ ሁኔታ፣ ዕድሎችና ፈተናዎች በማመላከት ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ ነው ብለዋል። በአፍሪካ ክላይሜት ፋውንዴሽን የፕሮጀክት ማናጀር ሳህሌ ታምሩ፤ ፋውንዴሽኑ በታዳሽ ኃይል፣ አረንጓዴ ኢንዱስትሪ፣ የትራንስፖርትና የፋይናንስ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ጥናቶችና ምርምሮችን እየደገፈ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም በዓለም አቀፍ ገበያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተወዳዳሪነቷንና ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ ጥናቱ አስተዋጽኦ የሚያደርግ በመሆኑ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም የተገቡ ቃሎች ወደ ተጨባጭ ተግባር መቀየር አለባቸው
Jul 15, 2026 1317
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 8/2018(ኢዜአ) ፦ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለመቋቋም የተገቡ ቃሎችን ወደ ተጨባጭ ተግባር መቀየር አስፈላጊ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቴዎስ ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ፕሬዚዳንት ዶክተር ጌዲዎን ጢሞቴዎስ ዛሬ ከኮፕ 21 ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሎረን ፋቢየስ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ሎረን ፋቢየስ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ላይ ታላቅ ስኬት የተመዘገበበትን የፓሪስ ስምምነት በማጽደቅ የተጠናቀቀውን ኮፕ 21ን የመሩበትን ልምድ አካፍለዋል። በተጨማሪም ለኮፕ 32 በሚደረጉ ዝግጅቶች እንዲሁም ስኬታማ የኮፕ 32 ጉባኤን ለማካሄድ አስተዋጽኦ ሊኖራቸው በሚችሉ ጉዳዮችና ካለፉት የኮፕ ጉባኤዎች በተገኙ ትምህርቶችና ግንዛቤዎች ላይ የሁለቱ መሪዎች ውይይት ትኩረት አድርጓል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) የፓሪሱ ስምምነት ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት እርምጃዎች ያለውን ዘላቂ ጠቀሜታ ገልጸው፣ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለመቋቋም የተገቡ ቃሎችን ወደ ተጨባጭ ተግባር የመቀየርን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ላይ እምነትን የሚያጠናክር፣ ግልጽ፣ አካታች እና በአባል ሀገራት የሚመራ የኮፕ 32 ሂደትን ለመተግበር ያላትን ቁርጠኝነትም በድጋሚ አረጋግጠዋል። ሚኒስትሩ አክለውም በይዘትና ድርድር፣ በሎጂስቲክስና ኦፕሬሽን፣ በአጋርነት እንዲሁም ሚዲያና ኮሙኒኬሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች በዝግጅት ረገድ የተመዘገቡት ተጨባጭ እድገቶችን አሳይተዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 20019
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 12964
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 11759
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 11654
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
ኢትዮጵያ፤ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የዕውቀት፣ የሰላምና የልማት ድልድይ!!
Jul 16, 2026 447
ድንበር ያልገደበው ትስስር ኢትዮጵያ፤ የኢትዮጵያ ቀጣናዊ የዕውቀት፣ የሰላምና የልማት ድልድይ!! በቤተልሔም ባህሩ የሀገራት ድንበር በካርታ ላይ የተሳሉ መስመሮች ናቸው። በሰዎች ሕይወት ውስጥ ግን አንዳንድ ጊዜ ወንድማማችነትን የሚያሳድጉ ድልድዮች ይሆናሉ። በደቡብ ሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ያደገው ኒክሰን አንቶኒ ድንበርን የሚያውቀው እንደ መለያ መስመር ሳይሆን፣ እንደ መገናኛ መስመር ነው። በልጅነቱም በድንበር አካባቢ ባሉ መንደሮች መካከል የሚኖረውን የገበያ ትስስር፣ የባህል መመሳሰል፣ የቋንቋ መቀራረብና ከሁሉም በላይ የሰዎች ተፈጥሯዊ መተማመን እየተመለከተ አድጓል። ስለዚህም ኢትዮጵያ በእርሱ አዕምሮ ውስጥ ከጎረቤት ሀገርነት ይልቅ የሁለተኛ ቤት ስሜት የፈጠረች ሀገር ሆናለች። ጥቁር አንበሳ፤ ከሆስፒታል በላይ የቀጣናውና የአፍሪካ የእውቀት ማዕከል ያ የልጅነት ትዝታ ግን አንድ ቀን የሕይወቱን መስመር የሚቀይስበት አጋጣሚ እንደሚፈጠር አላሰበም ነበር። ዛሬ ዶክተር ኒክሰን አንቶኒ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሕፃናት ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊቲ ትምህርቱን እየተከታተለ ይገኛል። በልጅነቱ በድንበር አካባቢ ያየው ወንድማማችነት ዛሬ ላይ በዕውቀትና በሕይወት ማዳን ሙያ እየታነጸ ይገኛል። በልጅነቱ በድንበር ላይ የተመለከተው የሕዝቦች ወንድማማችነት ዛሬ በእጆቹ ውስጥ ሕይወትን የሚያድን ሙያ ሆኗል። ይህ የአንድ ሰው የሙያ ስኬት ብቻ አይደለም፤ ሀገራት በእምነት ሲተባበሩ የሚፈጠረው የሰው ታሪክ ነው። እዚህ ላይ ኢትዮጵያ የምትሰጠው ትምህርት ዲግሪ ብቻ አይደለም፤ ኃላፊነትም ጭምር ነው። ዛሬ በአዲስ አበባ የሚማረው ሐኪም ነገ በጁባ፣ በኪጋሊ ወይም በሞቃዲሾ ውስጥ የሺዎችን ሕይወት ሊታደግ ይችላል። ስለዚህ ዛሬ በክፍል ውስጥ የሚሰጥ አንድ ትምህርት ነገ በሌላ ሀገር የሚድን አንድ ሕፃን ሕይወት ሊሆን ይችላል። ይህም ነው በትብብር ላይ የተመሠረተ የሰው ኃይል ልማት የሚሰኘው ቃል፣ ከፖሊሲ ሰነድ ወጥቶ ሕይወት የሚያገኘው። ነግቶ ሲጠባ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ኮሪደሮች ውስጥ ነጭ ጋውን የለበሱ ወጣት ሐኪሞች በፍጥነት ሲመላለሱ ይታያሉ። ከሩቅ ለሚመለከታቸው ሰው ማን ኢትዮጵያዊ፣ ማን ደቡብ ሱዳናዊ ወይም ማን ሩዋንዳዊ እንደሆነ መለየት ያዳግታል። ሁሉም አንድ ቋንቋ ይናገራሉ—የሕክምናን። ሁሉም አንድ ዓላማ አላቸው—ሕይወትን ማዳን። ይህ ምስል ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና እየገነባች ያለውን አዲስ የትብብር ምዕራፍ በደማቅ ቀለም አጉልቶ ያሳያል። ዛሬ በኢትዮጵያ በሚገኙ 19 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከ430 በላይ ከጎረቤት ሀገራት የመጡ ሐኪሞች በነፃ የስፔሻሊቲና የሰብ-ስፔሻሊቲ ስልጠና በመከታተል ላይ ናቸው። በዚህ መርሃ ግብር የተመረቁ 105 ሐኪሞችም ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሕዝባቸውን እያገለገሉ ነው። እነዚህ ቁጥሮች በራሳቸው ግን ሙሉ ታሪኩን አይነግሩም። ታሪኩ የሚጀምረው እንደ ኒክሰን ባሉ ወጣቶች ዐይን ውስጥ ከሚነበበው ተስፋ ነው። "ይህ ዕድል ለእኔ ትምህርት ብቻ አይደለም፤ ወደ ሀገሬ ተመልሼ ልጆችን የማድንበት ተልዕኮ ነው" ይላል። ያገኘው ልምድ የደቡብ ሱዳንን እንዲሁም የቀጣናውን አጠቃላይ የጤና ሥርዓት በጋራ ለማጠናከር እንደሚረዳ ያብራራል። ይህም የአንድ ወጣት ሐኪም ሃሳብ ብቻ አይደለም፤ የቀጣናው የጋራ የወደፊት ርዕይም ጭምር ነው። የዶክተር ኒክሰን ታሪክ ብቻውን አይቆምም። በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መማሪያ ክፍሎችና በቀዶ ሕክምና ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ በርካታ ወጣት ሐኪሞች በየራሳቸው የተለያየ ታሪክ ቢኖራቸውም፣ የሚያገናኛቸው አንድ የጋራ ዕሴት አለ። እርሱም ኢትዮጵያ የዕውቀት ዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗን ነው። በአፍሪካ ታሪክ የሀገራት ግንኙነት ብዙ ጊዜ የሚገለጸው በፖለቲካ፣ በድንበር ወይም በደኅንነት መነፅር መሆኑን የታሪክ ድርሳናት ያስረግጣሉ። ዛሬ ግን አዲስ ታሪክ በመፃፍ ላይ ይገኛል። የዚህ ታሪክ ቋንቋ የጦር መሣሪያ ሳይሆን የሕክምና አገልግሎት ነው፤ የጦር ሜዳ ሳይሆን የቀዶ ሕክምና ክፍል ነው፤ የፉክክር ምልክት ሳይሆን የጋራ ዕውቀት ነው። ይህንን እውነታ የሚያሳይ ሌላ ምሳሌ ደግሞ ደቡብ ሱዳናዊው ዶክተር ሲስቶ ዶሚኒክ ነው። በኢትዮጵያ የኦርቶፔዲክና ትራኦማ ቀዶ ሕክምና ስልጠና እየተከታተለ የሚገኘው ይህ ወጣት፣ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ የተቀበለው የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ከሙያው በላይ የሰው ልጅን ሰብዓዊ ክብር በጉልህ እንደሚያንጸባርቅ ይናገራል። "ሌሎች ሀገራት ሄጄ ተምሬያለሁ፤ ኢትዮጵያ ስመጣ ግን እንደ እንግዳ አልተሰማኝም። እንደ ቤቴ ነበር የተሰማኝ፤ እየኖርኩ ያለሁትም እንደዚያ ነው" የሚለው ንግግሩ ከአንድ ግለሰብ ልምድ በላይ ነው። ይህም የሀገራቱን ሕዝቦች ለዘመናት የተገነባ መተማመን የሚገጥ ማስረጃ ነው። ዶክተር ሲስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን ሲመለስ የሚያክመው የሀገሩን ዜጎች ብቻ አይሆንም፤ በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም የእርሱ ታካሚዎች ይሆናሉ። በዚህ መልኩ በአንድ የቀዶ ሕክምና ክፍል የተገኘ ዕውቀት ድንበርን ተሻግሮ ሌላ ሀገር ውስጥ ሕይወት ያድናል። ይህ ደግሞ የዕውቀት ዲፕሎማሲ በተግባር ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ሕያው ምስል ነው። ከኪጋሊ የተጀመረ ሕልም፤ በአዲስ አበባ የዘለቀ የመሻት ስኬት የሩዋንዳዊው ዶክተር ሙሂር ፍራንክ ታሪክ ደግሞ ሌላ የቀጣናዊ ትብብር ገጽን ያሳያል። በኪጋሊ ሆስፒታሎች ውስጥ በትጋት የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞችን ሲመለከት ያደገው ይህ ወጣት፣ በፊታቸው ላይ ያየው ሙያዊ ብቃትና ርህራሄ አንድ ቀን እርሱንም ወደ አዲስ አበባ እንደሚያመጣው አስቦ አያውቅም። ዛሬ ግን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኒውሮ ሰርጀሪ ስፔሻሊቲ ተማሪ ነው። ለእርሱ ኢትዮጵያ የትምህርት መዳረሻ ብቻ አይደለችም፤ በሩዋንዳ የሚያልመውን የጤና ሥርዓት የሚገነባበት ሁለተኛ ቤቱና የዕውቀት መሠረት ጭምር ነው። ሩዋንዳ በጤና ዘርፍ ያላትን የሰው ኃይል በፍጥነት ለማሳደግ በተያዘው ብሔራዊ ዕቅድ ውስጥ፣ በኢትዮጵያ የሚሰጠው ስልጠና የሚያበረክተው ሚና ትልቅ መሆኑን ይገልጻል። እንደ ወጣቱ ዶክተር ገለፃም ''ይህ የሚያሳየው አንድ እውነት አለ፤ አንድ ሀገር የሌላውን ሀገር የሰው ኃይል ሲያጠናክር፣ በእውነቱ የጋራ የቀጣናውን መጪ ጊዜ እየገነባ መሆኑን ነው የሚያስገነዝበው'' ይላል። በጤና ሚኒስቴር የጤና ዘርፍ ሰው ኃይል ልማት ማሻሻያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሰግድ ሳሙኤል በበኩላቸው፣ ባለፉት ስድስት ዓመታት ሲሰጥ በቆየው ነፃ የሕክምና ስልጠና ዕድል እጅግ ውጤታማ እንደነበር ይገልጻሉ። ይህ ትብብርና አጋርነት በቀጣናው ሀገራት የሕክምና ዕውቀት እንዲጎለብትና የተሻለ የጤና ሥርዓት እንዲኖር ከማገዙም በላይ፣ በሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ድንበር ተሻጋሪ የጤና ችግሮችን በጋራ ለመለየትና ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም ያነሳሉ። ዛሬ በነጭ ጋውን፤ ትናንት በሰማያዊ ቆብ የዛሬውን ምስል ለመረዳት ወደ ትናንቱ መመለስ ያስፈልጋል። ዛሬ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ኮሪደሮች የሚታዩት ከደቡብ ሱዳንና ከሩዋንዳ የመጡ ወጣት ሐኪሞች ናቸው። ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ግን በእነዚያ ሀገራት የሚታዩት በሰማያዊ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር መለያ ያሸበረቁ ኢትዮጵያውያን የሰላም አስከባሪዎች ነበሩ። ዛሬ ግን ቦታው ተለውጧል፤ ዩኒፎርሙ ተለውጧል። ነገር ግን ተልዕኮው አልተለወጠም። ያኔ ሰላምን በማረጋጋት ሕይወትን ከጦርነት መታደግ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ሕይወትን ከበሽታ የመፈወስ ተልዕኮ ነው። በዚህ መልኩ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላት ሚና ከአንድ መልክ ወደ ሌላ ቢሸጋገርም፣ መሠረታዊ ዓላማው ግን አልተቀየረም። ይህም ሰላምን መገንባት፣ ሰውን ማገልገልና ጎረቤቶችን ማጠናከር ሆኗል። የኢትዮጵያ የሰላም ማስከበር ታሪክ በ1950ዎቹ በኮሪያ በታዋቂው "ቃኘው ሻለቃ" የተጀመረ ሲሆን፣ በመቀጠል በኮንጎ፣ በላይቤሪያ፣ በቡሩንዲ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በሶማሊያ ድረስ የታሪክ ማህደር የተዘረጋ ነው። ይህም በታሪክ ድርሳናት መጻሕፍት ላይ የሚነበብ ብቻ አይደለም፤ ዛሬ በአዲስ አበባ በሚማሩ የአፍሪካ ወጣት ሐኪሞች ሕይወት ውስጥ በሕያው መልኩ ጎልቶ ይታያል። ሩዋንዳ፤ የኢትዮጵያ የማይረሳ ውለታ በ1994 ሩዋንዳ የተከሰተው የዘር ፍጅት በሰብዓዊነት ላይ የተቃጣ የአፍሪካና የዓለም ጥቁር ታሪክ ሆኖ ተመዝግቧል። በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ብዙዎች ሩዋንዳን በሩቅ ሆነው ሲመለከቱ፣ ኢትዮጵያ ግን ከሰላም አስከባሪዎቿ ጋር በመቆም የሰው ልጅ ሕይወት ከማንኛውም ጉዳይ እንደሚቀድም በተግባር አሳይታለች። ይህን ታሪክ የሚያስታውሱት በኢትዮጵያና በጅቡቲ የሩዋንዳ አምባሳደር ቻርለስ ካሮምባ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት፣ ''ሩዋንዳ በከባድ ፈተና ውስጥ በነበረችበት ወቅት ኢትዮጵያ ያደረገችልን ውለታ በሩዋንዳዊያን ልብ የታተመ፤ በሀገራቱ የግንኙነት ታሪክ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጭምር በወቅቱ የነበረው የኢትዮጵያ ወታደራዊ ልዑክ አባልና ተሳታፊ ነበሩ፤ ይህ በሀገራቱ መካከል ያለው ጥብቅ ቁርኝት ማሳያ ነው።'' ስለዚህ ዛሬ አንድ ሩዋንዳዊ ወጣት በአዲስ አበባ ተምሮ ወደ ሀገሩ ሲመለስ፣ ያ ጉዞ በድንገት የተጀመረ አይደለም፤ ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት የተዘራ የመተማመን ፍሬ ዛሬ በዕውቀት እየጎመራ መሆኑን ነው። ሀገራ አቋራጭ ወንዝ እንደ ደም ሥር፤ ኃይል እንደ አዲሱ የትስስር ቋንቋ የሀገራት ጉርብትና በሰላም ማስከበርና ግጭት ማረጋገጥ በሚደረግ ትብብር ብቻ አይደለም፤ በሚጋሩት ዕውቀት፣ የተፈጥሮ ሀብትና በሚገነባ የጋራ ዕድገትም ጭምር ነው። ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የቀጣናውን ግንኙነት ከፖለቲካ ግንኙነት መገለጫነት ወደ ተግባራዊ ትብብር ለመቀየር የቻለችባቸው መስኮች ብዙ ናቸው። የኤሌክትሪክ ኃይልና የውሃ ሀብት ትብብርም ወሳኞቹ የመተሳሰሪያ ማዕከሎች ናቸው። ዛሬ ከኢትዮጵያ የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል የጅቡቲን ኢንዱስትሪዎች ያንቀሳቅሳል፤ በኬንያ የከተሞችን መብራት ያበራል፤ ወደ ሱዳንና ታንዛኒያ በማቅናትም የቀጣና ትስስር መስመር እየዘረጋ ነው። ይህም የኢትዮጵያ ዕይታ የእርስ በርስ መተማመንን የሚገነባ የሰላም መሠረት ነው። ውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ደኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ጥምረት ማዕቀፍ ውስጥ ቀጣናውን በኃይል የማስተሳሰር ታሪካዊ ሚናዋን ይበልጥ አጠናክራ ትቀጥላለች። የኢትዮጵያ ቀጣናዊ የኃይል ትስስርም የጋራ ልማትን እያሳለጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አንድ ሀገር የጎረቤቷን ቤት የሚያበራ ኃይል ስታቀርብ፣ በተመሳሳይ ጊዜ የጋራ ዕጣ ፈንታንም እየገነባች መሆኑን ያመላክታል። ይህንን እውነታ የደቡብ ሱዳን የውሃና መስኖ ሚኒስትር ጀምስ ማዊች ሲገልጹት፤ ''ኢትዮጵያ የውሃና የኃይል ልማቷን የምታከናውነው ለራሷ ብቻ ሳይሆን የቀጣናውን የጋራ ተጠቃሚነት መርህ በማስቀደም ጭምር ነው።'' በተመሳሳይ አረንጓዴ አሻራን የመሳሰሉ የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራሞች ከአንድ ሀገር ድንበር አልፈው ለመላው ዓለምና ቀጣናዊ የአየር ንብረት ደኅንነት ጉልህ ፋይዳ ያበረክታሉ። ወንዞች በሀገራት ካርታ ላይ ድንበር አያውቁም፤ የአየር ንብረትም ፓስፖርት አይጠይቅም። ስለዚህ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ትብብር ትዕምርትና የጋራ ህልውና ጉዳይ ነው። የኢኮኖሚ ትስስር፤ የአዲሱ ዓለም የዕድገት ምኅዋር እንደ ዶክተር ኒክሰን ያሉ ወጣቶች የኢትዮጵያን ታሪክ በሆስፒታል ውስጥ እየኖሩ ሲሆን፣ የቀጣናው የወደፊት ታሪክ ደግሞ በንግድ፣ በመጓጓዣና በኢኮኖሚ ትስስር እየተገነባ ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት በቅድሚያ ለጎረቤት መርህ የተቃኘ መሆኑ የሚታየው በዲፕሎማሲ መድረኮች ብቻ አይደለም። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የረጅም ዘመን የታሪክ ባለቤትና ከበርካታ ሀገራት ጋር የቆየ የንግድ ትስስር ያላት ሀገር ናት። ይህንን የንግድ ዲፕሎማሲዋን ይበልጥ ለማዘመንና ለማስፋፋት በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ብሪክስ (BRICS) ባሉ ጥምረቶች በንቃት በመሳተፍ ላይ ናት። የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆንም የጀመረችውን የድርድርና የዝግጅት ጉዞ በቁርጠኝነት እያስቀጠለች ትገኛለች። በአህጉር ደረጃም ቀድሞ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ)፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) አማካኝነት ቀጣናዊና አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስሯን በማጠናከር የአፍሪካን የጋራ ገበያ ዕውን ለማድረግ እየተጋች ነው። ይህ አጠቃላይ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ የንግድ ስትራቴጂ ነው። ለዚህ ማሳያም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን ሶስት ጊዜ ወደ ሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ የሚያደርጋቸው የቀጥታ በረራዎች፣ የቀጣናውን የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርና የንግድ ፍሰት እጅግ እያቀላጠፉት መሆኑ ነው። በአሁኑ ወቅት የሁለቱ ሀገራት የንግድ ሚዛን ተመጣጣኝ ደረጃ ላይ ነው። ሩዋንዳ ወደ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ገደማ የሚጠጋ ምርት ከኢትዮጵያ ስታስገባ፣ በምላሹ ደግሞ ስድስት ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ምርቷን ወደ ኢትዮጵያ ትልካለች። ወደ 40 የሚጠጉ የኢትዮጵያውያን ኩባንያዎች በሩዋንዳ ውስጥ በንግድና ልማት ሥራዎች ተሰማርተዋል። እነዚህ ኩባንያዎች በአጠቃላይ ከ73 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ካፒታል ይዘው መንቀሳቀሳቸው፣ ትስስሩ ከቀላል የንግድ ግንኙነት አልፎ የሀገራቱ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ሕይወት ወደ ማስተሳሰር ደረጃ መሸጋገሩን የሚያሳይ መሆኑን አምባሳደር ቻርለስ ካሮምባ ይገልጻሉ። መደምደሚያ፡ የድንበር ልጅ... የአፍሪካ ተስፋ ትናንት የኢትዮጵያ ወታደሮችና የሰላም አስከባሪዎች የቀጣናውን ሀገራት ሰላም ለመጠበቅ ኪጋሊና ጁባ ዘምተዋል። ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ አንድ ሕፃን ልጅ ጎረቤቶች በፍቅር ሲኖሩ ይመለከት ነበር። ዛሬ ያ ሕፃን በአዲስ አበባ ሕይወት የሚያድን ዶክተር ሆኗል። ነገ ደግሞ ወደ ሀገሩ ተመልሶ የሚያክማቸው ሕፃናት የሚያገኙት ሕክምና፣ በኢትዮጵያ የተቀሰመ ዕውቀት ይሆናል። ምናልባት የዚህ ታሪክ ትልቁ ትምህርት ይሄ ይሆናል። ሀገራትን በጣም የሚያስተሳስራቸው ነገር ስምምነት ብቻ አይደለም፤ የአንዱ ሕዝብ ልጅ በሌላው ሕዝብ ልጅ ሕይወት ውስጥ የሚያሳርፈው አሻራ ነው። ዶክተር ኒክሰን፣ ዶክተር ሲስቶና ዶክተር ሙሂር የተማሩትም የሕክምና ትምህርት ብቻ አይደለም፤ ድንበርን በሰብዓዊነት መሻገር የሚቻልበትን የአፍሪካ አዲስ ትርክት እንጂ። ስለዚህ ይህ የአንድ ወጣት ሐኪም ጉዞ ብቻ አይደለም፤ ይህ ከድንበር መንደር የተጀመረ፣ በጥቁር አንበሳ ነጥሮ የወጣና በአፍሪካ የወደፊት ተስፋ የሚያስቀጥል የጋራ ታሪክ ነው። ይህ የታሪክ፣ የደም፣ የጥበብ፣ የውኃ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የንግድ ትስስር የአፍሪካ ህብረት የሚያልማትን የበለጸገችና የተሳሰረች አፍሪካ በተግባር ለማየት እንደሚቻል የሚያመላክት ህያውና ተስፋ ሰጪ ምስክር ነው።
የኢትዮጵያ ማኛ ወርቅ፤ ከተንጣለለው የጎጃም ማሳ ወደ ዓለም ገበያ
Jul 14, 2026 910
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞኑ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የጤፍ ምርት ከሚገኝባቸው አካባቢዎች መካከል ይጠቀሳል። ለዚህ ስኬት የተፈጥሮ ጸጋው ብቻ ሳይሆን የአርሶ አደሮች ትብብር፣ ዘመናዊ የእርሻ አሰራርና የገበያ ትስስር መጠናከር ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። የተንጣለለው የምስራቅ ጎጃም ማሳ በጤፍ ተሸፍኖ ማየት ስሜትን ይገዛል። በማሳው መካከል ደግሞ አርሶ አደሮች በጋራ እየሰሩ መመልከት ከትውልድ ትውልድ የተላለፈ የመረዳዳትና ለሺህ ዘመናት ለዘለቀ አስተራረስ አብነት ነው። የጎጃም ጤፍ በጥራቱ ቢታወቅም፣ ምርቱን በተሻለ ዋጋ ለመሸጥ የሚያስችል የገበያ ትስስር ውስን ነበር። አርሶ አደሩ በብዙ ድካም ያመረተውን ምርት ለደላሎች በዝቅተኛ ዋጋ ለመሸጥ ይገደዳል። በምርቱ ላይ የሚፈጠረው እሴትም እምብዛም ነው። ዛሬ ግን ያ ታሪክ እየተለወጠ ይመስላል። በደብረ ማርቆስ ከተማ የተቋቋመውና የማኛ ጤፍ ዱቄትን ወደ ዓለም ገበያ መላክ የጀመረው ፋብሪካ የአርሶ አደሩን ምርት በቀጥታ በመቀበል ወደ እሴት የሚቀይር ድልድይ ሆኗል። ከእርሻ ወደ ፋብሪካ፣ ከፋብሪካ ወደ ውጭ ገበያ የሚዘልቀው ይህ የእሴት ሰንሰለት የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማሳደግ አዲስ የለውጥ ምዕራፍን ከፍቷል። የማኛ ጤፍ ዱቄት ማምረቻ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ሰማኸኝ ጌታቸው እንደሚገልጹት፣ ፋብሪካው በቀን በአማካይ ከ600 እስከ 800 ኩንታል ጤፍ የሚፈጭ ሲሆን፥ ሥራ በጀመረባቸው ጥቂት ወራት ውስጥ 600 ቶን እሴት የተጨመረበት ጤፍ ለውጭ ገበያ አቅርቧል። በዚህም አንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለሀገር አስገኝቷል። ይህ አሃዝ የጤፍ ምርት በፋብሪካ እሴት ሲጨምር የሚፈጠረውን የኢኮኖሚ ጥቅም በግልጽ ያሳያል ብለዋል። ከዚህ በላይ ደግሞ ፋብሪካው ለ70 የሚጠጉ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠሩ የግብርና ልማት ከኢንዱስትሪ ጋር ሲሰናሰል የሚፈጠረውን ተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያመለክታል። ይህ ማለት አንድ የጤፍ ሰብል ከማሳ እስከ ውጭ ገበያ ድረስ በሚያደርገው ጉዞ በርካታ የሥራ ዕድሎችን፣ የገቢ ምንጮችንና የኢኮኖሚ እሴቶችን ይፈጥራል ማለት ነው። በምስራቅ ጎጃም ዞን ትርፍ አምራች ከሆኑ አካባቢዎች መካከል በደጀን ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችም ይህንን ለውጥ በቀጥታ እየተጠቀሙበት ነው። በክላስተር ማረስ የምርት ጥራትን በማሻሻል ጉልህ ጠቀሜታ ያስገኛል። ኢዜአ ከዚህ ቀደም በወረዳው በኩታ ገጠም የጤፍ ምርት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን በጎበኘበት ወቅት የተመለከተው እውነትም ይህንኑ ነው። ፋብሪካው ደግሞ ከተጠቃሚነት ላይ ተደማሪ ጠቀሜታ የሚያገኙበትን ዕድል ፈጥሯል። በደጀን ወረዳ በክላስተር ተደራጅተው ጤፍን በስፋትና በጥራት ከሚያመርቱ አርሶ አደሮች መካከል አርሶ አደር መኩሪያው ታደለ አንዱ ሲሆኑ፤ የኩታ ገጠም እርሻ የጉልበት ወጪን በመቀነስ የምርት ጥራትና ብዛትን በማሳደግ ከፍተኛ ውጤት እንደሚያስገኝ ይገልፃሉ። በክላስተር ማምረት በአንድ ጊዜ መዝራት፣ መከታተልና መሰብሰብ በመቻሉ የምርት ብክነትን መቀነስ እንደተቻለም ሌላው አርሶ አደር ሸጋው ከፍያለው ያብራራሉ። እንደ እርሳቸው ገለጻም፤ አርሶ አደሮች በአንድነት መስራታቸው የግብርና ሥራዎችን በወቅቱ ለማከናወን አስችሏል። ይህም በምርታማነት ላይ ቀጥተኛ አወንታዊ ተፅዕኖን ፈጥሯል። በተመሳሳይ አቶ ውዱ ሞሱ እንደሚሉት፤ የአርሶ አደሮች መተባበር ከዘር እስከ ምርት አሰባሰብ ድረስ በሁሉም ሂደት ውጤታማ አድርጓቸዋል። ምርቱ ሲደርስም በደቦ በመሆን በአጭር ጊዜ በመሰብሰብ የጊዜና የጉልበት ብክነትን አስቀርቷል። የአርሶ አደሩ ስኬትም በማሳ ብቻ የሚቆም አይደለም። ከምርቱ መገኛ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ደብረ ማርቆስ ከተማ የተቋቋመው የማኛ ጤፍ ዱቄት ማምረቻ ፋብሪካ ሥራ መጀመሩ የደጀንና የአካባቢውን አርሶ አደሮች ከማሳ በቀጥታ ወደ ዓለም ገበያ የሚያገናኝ አዲስ የእሴት ሰንሰለት ፈጥሯል። ከዚህ ቀደም ጤፍ እንደ ጥሬ ምርት ብቻ ይሸጥ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ግን በፋብሪካ ተበጥሮ፣ ተፈጭቶ፣ በዘመናዊ መልክ ታሽጎ እሴት ተጨምሮ ወደ ውጭ ገበያ እየተላከ ነው። የደብረ ማርቆስ ከተማም በዚህ ሂደት የኢንዱስትሪ ማዕከል እየሆነች ነው። በከተማዋ የሚገኙ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የአካባቢውን ጥሬ እቃ በመጠቀም እሴት የሚጨምሩ በመሆናቸው ግብርናን ከኢንዱስትሪ ጋር የሚያስተሳስሩ የልማት ሞዴሎች እየሆኑ መጥተዋል። ይህም ለጎጃም ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ የግብርና ሽግግር አቅጣጫን የሚያሳይ ጠቃሚ ልምድ ነው። የኢትዮጵያ ጤፍ በባህላችን ያለውን ክብር ተጠብቆ በዓለም ገበያም ተፈላጊነቱን እያሳደገ ነው። ይህን ዕድል በተሻለ መንገድ ለመጠቀም የምርት ጥራትን ማሻሻል፣ የማቀነባበር አቅምን ማስፋት፣ የአርሶ አደሩን የገበያ ትስስር ማጠናከርና ተመሳሳይ የእሴት ጭማሪ ኢንዱስትሪዎችን በሌሎች አምራች አካባቢዎች ማስፋፋት ቀጣዩ የልማት ምዕራፍ ይሆናል። ከጎጃም የተንጣለለ የእርሻ ማሳ የሚነሳው የጤፍ እህል ዛሬ በፋብሪካ እሴት ተጨምሮ ወደ ዓለም ገበያ እየተጓዘ ነው፤ ይህም የኢትዮጵያ ግብርና ከባህላዊ አመራረት ወደ እሴት ጭማሪ ኢኮኖሚ እየተሸጋገረ መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ ውጤት ሆኗል። የደብረ ማርቆስ ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ተመስገን ተድላ፣ ከተማዋ ለኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ተመራጭ እየሆነች የመጣችው በቂ ጥሬ ዕቃ፣ የሰው ኃይል፣ የተሻለ የመጓጓዣ አገልግሎትና የሰላም ሁኔታ በመኖሩ መሆኑን ያብራራሉ። በተለይም የጎጃም አካባቢ የግብርና ሃብት ለእሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎች ጠንካራ መሠረት እየፈጠረ መሆኑን ይጠቅሳሉ። በለውጡ ዓመታት 253 የአምራች ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸውና አብዛኞቹ ወደ ምርት መሸጋገራቸው የአካባቢው ኢኮኖሚ እያደገ መምጣቱን ያሳያል። ከእነዚህ መካከል የጤፍ ማቀነባበሪያ ፋብሪካው የጎጃም ማኛ ወርቅ የሆነውን የጤፍ ምርት እሴት ጨምሮ ወደ ዓለም ገበያ በማቅረብ ለአርሶ አደሩ፣ ለከተማዋና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ተጨባጭ ጥቅም የሚያስገኝበትን አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል ይላሉ። በዚህ መልኩ በምስራቅ ጎጃም ዞን ያለውን ሰፊ የጤፍ ምርት በደብረ ማርቆሱ ፋብሪካ እሴት ተጨምሮ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ገበያ መድረሱ የኢትዮጵያ ግብርና ከጥሬ ምርት ሽያጭ ወደ እሴት ጭማሪ፣ ከአካባቢ ገበያ ወደ ዓለም ገበያ እየተሸጋገረ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። ይህም ጤፍ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የሚያጠናክር ስትራቴጂያዊ ሀብት መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን አብራርተዋል።
ለብሩህ ነገዋ በአዲስ ምዕራፍ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ
Jul 14, 2026 650
ለብሩህ ነገዋ በአዲስ ምዕራፍ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በሙሴ መለሰ ረጅም ታሪክ፣ቱባ ባህልና ሕብረ-ብሔራዊነት መለያዋ የሆኑት ኢትዮጵያ፣ የነገ ተስፋዋን አስተማማኝ ለማድረግ አዲስ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።የኢትዮጵያን መጻኢ ዕድል ይበልጥ ብሩህ ለማድረግ ሀገራዊ ምክክር ቁልፍና ታሪካዊ ሚና ይጫወታል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በመላ ሀገሪቱ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ አጀንዳዎችን የመሰብሰብ ስራ ያጠናቀቀ ሲሆን ነገ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በይፋ ይጀመራል። ኮሚሽኑ በመላ ሀገሪቱ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰቡትን ሀሳቦችን በማደራጀት ለዋናው ሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎችን በይፋ ለይቷል። እነዚህም የሀገር ግንባታ ታሪካዊ ሂደቶች፣ የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ስርዓት፣ የፌዴራል ከተሞች የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታ፣ የህግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ ሙስናና መልካም አስተዳደር፣ እንዲሁም የሰላም ግንባታ ናቸው። ስምንቱን መሠረታዊ አጀንዳዎች መነሻ በማድረግ የሚደረገው ውይይት፣ የፖለቲካ መረጋጋትን ከመፍጠር ባለፈ ለአስተማማኝ የኢኮኖሚ እድገትና ለጠንካራ ተቋማት ግንባታ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ምክክሩ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ ነው።ባለፉት የታሪክ ሂደቶች የተፈጠሩ ቅሬታዎችን በጠረጴዛ ዙሪያ በሰላማዊ ውይይት በመፍታት፣እርስ በርስ ለመደማመጥ እና ታሪካዊ ቁስሎችን በይቅርታ ለመፈወስ የሚያስችል ዋነኛ መንገድ ነው። ከጠመንጃና ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሀሳብ የበላይነት የሚነግስበትን፣አለመግባባቶችና ልዩነቶች በሰላማዊ ውይይትና በንግግር የሚፈቱበትን ባህል ያሰፍናል።ይህም ልዩነቶችን በመቀበል በአንድነትና በጋራ መኖር የሚያስችሉ የጋራ እሴቶችና ሀገራዊ መግባባቶች ለማጠናከር ይረዳል። ከዚህም ባለፈ፣ምክክሩ ለተቋማዊ እድገትና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዋነኛ ምሰሶ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ የሚጀመረውን ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አስመልክቶ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ምክክሩ ፍቱን የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን፣ የእኛን እና የመጪውን ትውልድ እጣ ፈንታና የወደፊት ተስፋ ሙሉ በሙሉ የሚወስን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ጭምር ነው ሲሉ ገልጸውታል። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፣ዛሬ ሀገራችን የምትሻው ጠመንጃ ያነገቡ ሳይሆን በሀሳብ ብስለት፣ በእውነት፣ በዕውቀትና በጽናት ታጥቀው የተሰናዱ የሰላም ታጋዮችን ነው ያሉ ሲሆን እኛ ዛሬም እንደ ትናንቱ በታላቅ የድል ዋዜማ ላይ እንገኛለን፤ ምክንያቱም የኢትዮጵያና የሕዝቦቿ ማሸነፍ አይቀሬ ነው ብለዋል። ይህንን በጎ ዕድል ለመጠቀምም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንነትና በኃላፊነት ስሜት በመሳተፍ ለሀገር ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል። ይህ ሀገራዊ ምክክር የኢትዮጵያን መጻኢ ዕድል በራስ አቅምና ጥበብ ለመወሰን የሚያስችል ትልቅ እድል ነው።የኢትዮጵያ መጻኢ ተስፋና ሁለንተናዊ ብልጽግና ከሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ጋር የተሳሰረ ነው። ባለፉት የታሪክ ሂደቶች ውስጥ የተፈጠሩ ቅሬታዎችን በንግግር መፍታት፣ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሃሳብ የበላይነት የሚነግስበትን ምቹ መደላድል ይፈጥራል። ዛሬ በምክክሩ ጠረጴዛ ዙሪያ የሚታየው የመነጋገር እና የመደማመጥ ባህል እንዲሁም ችግሮችን በውይይት ብቻ የመፍታት አማራጭ የተሻለች ኢትዮጵያን እውን የሚያደርግ ታሪካዊ መሰረት ይጥላል።
የሌማት ትሩፋት ሀገራዊ ስኬት- ከአመጋገብ ለውጥ እስከ ገቢ ምንጭ
Jul 13, 2026 862
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ለብዙ ኢትዮጵያውያን ወተት፣ እንቁላል፣ ማርና ሥጋ በምግብ ገበታ የማይገኙ፣ ለረጅም ዓመታት የቅንጦት ያህል የሚታዩና በቂ ምርት ባለመኖሩም በገበያ ላይ በስፋት የማይገኙ ነበሩ። ይህንን እውነታ ለመቀየርና የዜጎችን የሥርዓተ ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የሌማት ትሩፋት ሀገራዊ መርሃ ግብር ዛሬ ላይ ትልቅ ተስፋና ተጨባጭ ውጤት እያሳየ ይገኛል። ቀደም ሲል ትኩረት አጥቶ የነበረውን የእንስሳት ተዋጽኦ ልማት በቅንጅትና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ረገድ በአካባቢው ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። በግብርና ሚኒስቴር መረጃ መሠረት መርሃ ግብሩ ከመጀመሩ በፊት የነበረው 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሊትር የወተት ምርት ዘንድሮ 15 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር መድረሱ፣ በዓመት የሚሰራጨው የዶሮ ጫጩት ከ26 ሚሊዮን ወደ 184 ሚሊዮን ማደጉ እንዲሁም የእንቁላል ምርት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ከፍ ማለቱ የዚሁ ሀገራዊ ስኬት ማሳያዎች ናቸው። ይህ የተጀመረው አበረታች ሂደት እንደ ወተት፣ ማር፣ ሥጋ፣ አሳ እና እንቁላል ያሉ ምርቶች የቅንጦት ሳይሆኑ የዜጎች የዕለት ተዕለት የሥርዓተ ምግብ አካል እንዲሆኑ በማስቻል ረገድም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። መርሐግብሩ በቢሾፍቱ ከተማና አካባቢዋ ለሚኖሩ በርካታ ዜጎችም የአመጋገብ ሥርዓትን ከመቀየር ባለፈ፣ የኢኮኖሚ አቅማቸውን የለወጠ የሕይወት ጉዞን ፈጥሮላቸዋል። አቶ ከፈለኝ ጫላ ቀደም ሲል በመንግሥት ሥራ በደመወዝ ነበር የሚተዳደሩት። የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ላይ ዜጎች እንዲሳተፉ ጥሪ ሲቀርብ ግን የቀደማቸው አልነበረም። ገንዘብ በብድር በማመቻቸት በአንድ የወተት ላም ሥራቸውን ጀመሩ። በአሁኑ ወቅት የወተት ላሞቻቸውን ቁጥር 15 ማድረስ ችለዋል። የአካባቢው አስተዳደርና ባለሙያዎች ያደረጉላቸው ተከታታይ ድጋፍና ክትትል አሁን ለደረሱበት ውጤት እንዲበቁ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከተላቸው ያነሳሉ አቶ ከፈለኝ። የራሳቸውን ኑሮ ከመቀየር ባለፈ፣ የሚያመርቱትን ወተት ለአካባቢው ማኅበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያውን በማረጋጋት ረገድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። የተመጣጠነ አመጋገብን እንድንከተል የሌማት ትሩፋት ትልቅ ለውጥ አምጥቷል የሚሉት አቶ ከፈለኝ፥ በተጨማሪም በመስኩ ለሌሎች ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ተናግረዋል። ሌላኛው በዚሁ መርሃ ግብር ሕይወታቸው የተቀየረው ሥራ ፈጣሪ አቶ ጌቱ ብሩ ናቸው። እሳቸው ደግሞ በተቀናጀ የዶሮና የዓሣ ልማት ዘርፍ ላይ ነው የተሰማሩት። የሌማት ትሩፋት ያመጣላቸው በረከት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከመጥቀም አልፎ የንግድ አድማሳቸውን አስፍቶላቸዋል። ከልማቱ በሚያገኙት የምርት ውጤት የራሳቸውን ሆቴል መክፈት የቻሉ ሲሆን፣ ለበርካታ ዜጎችም የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። "ለሆቴላችን የምግብ ግብዓት የሚሆነውን ምርት የምናቀርበው ከራሳችን የዶሮና የዓሣ እርባታ ማዕከል ነው" የሚሉት አቶ ጌቱ፣ ዘርፉ ሰፊና ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የሚቻልበት መሆኑን ይመሰክራሉ። አቶ ጌቱ እቅዳቸው እዚህ ላይ ብቻ አያበቃም፤ በቀጣይ የሌማት ትሩፋት ምርቶችን እሴት ጨምረው ለከተሞች ከማቅረብ ባለፈ ወደ ውጭ ሀገር ለመላክና ለሀገር የውጭ ምንዛሬ የማስገኘት ውጥን አላቸው። ሌሎችም በዚህ ሥራ ላይ ቢሰማሩ ከራሳቸው አልፈው ሀገርንና ወገንን መለወጥ እንደሚችሉም ነው የጠቆሙት። በተመሳሳይ በዶሮ እርባታ ሥራ ላይ የተሰማሩት አቶ ደረጄ አበበ መርሃ ግብሩ ከፍተኛ ገቢ እንዲያገኙ እንዳስቻላቸው ይናገራሉ። የዶሮ እንቁላል በተመጣጣኝ ዋጋ ለአካባቢው ማኅበረሰብ በስፋት በማቅረብ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ጠቅሰዋል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)፥ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበትና የዜጎችን የምግብና ሥርዓተ ምግብ አቅም እያሳደገ የሚገኝ ኢኒሼቲቭ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ሀገራዊ ጥረት ለማሳካት የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አክለውም፤ ኢኒሼቲቩ በቤተሰብ ደረጃ የዶሮ እርባታ ባህል እንዲሆን በማድረግ፣ በተለይም ሕፃናትና እናቶች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ በማስቻል ረገድ መሠረታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑንና ምርቶች በስፋት ለገበያ እንዲቀርቡ በማስቻል ረገድ ትርጉም ያለው ውጤት ማምጣቱን ገልጸዋል።
ትንታኔዎች
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ
Jul 3, 2026 4235
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ (በቀደሰ ተክሌ ከኢዜአ-ሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥቃቅን ችግሮች እያደጉ ሔደው ሀገር የማፍረስ አደጋን ከመደቀናቸው በፊት ከሥር መሠረቱ ማስተካከያ ማድረግ ብቸኛው መንገድ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክርን ማካሔድ ነው። በዚህም ራሳቸውን ከመጥፋት ታድገው ሀገር በሚል ስያሜ ሕልውናቸውን ያቆዩ ሀገራት አሉ። ከእነዚህም መካከል በአካታች ምክክር ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የተሸጋገሩትን ማንሳት ይቻላል። ለአብነት የቱኒዚያ ሀገራዊ ምክክር በዓለም ላይ ካሉ የቅርብ ጊዜ ስኬታማ ተሞክሮዎች ቀዳሚው ነው። እ.አ.አ በ2011 የ"አረብ አብዮት" መነሻ የነበረችው ቱኒዚያ፣ የፖለቲካ መሪዎች መገዳደል እና ከፍተኛ አለመረጋጋት ገጥሟት ነበር። አራት የሲቪክ ማህበራት (የሰራተኞች ማህበር፣ የጠበቆች ማህበር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የነጋዴዎች ማህበር) በጋራ በመሆን "የቱኒዚያ ብሔራዊ ምክክር ኳርትት አቋቋሙ። ፖለቲከኞችን አስገድደው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲቀመጡ አደረጉ። በዚህም ሳቢያ ሀገሪቱ አዲስ እና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ቀረጸች፤ ሰላማዊ ምርጫ ተካሄደ፤ ሀገሪቱ ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ከመግባት ዳነች። ይህንን ምክክር የመሩት አራት ድርጅቶችም እ.አ.አ በ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አግኝተዋል። ደቡብ አፍሪካም ለዘመናት የዘለቀውን የዘረኝነት እና የአፓርታይድ ስርዓት ያቆመችው በጦርነት ሳይሆን በሁሉን አካታች ብሔራዊ ምክክር ነው። በኔልሰን ማንዴላ የሚመራው ኤ.ኤን.ሲ እና የነጮች ገዥ ፓርቲ በጥላቻ ፋንታ "ለነገዋ ሀገር" በሚል ይቅርታን እና ድርድርን አስቀደሙ። በምክክሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የነገዶች ተወካዮች በሙሉ ተሳትፈዋል። ያለምንም ደም መፋሰስ የስልጣን ሽግግር ተደረገ፤ በአለም ላይ እጅግ ተራማጅ የሚባል አዲስ ህገ-መንግስት ተቀረጸ፤ "የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን" በማቋቋም ያለፈው ቁስል እንዲሻር ተደረገ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሁዋን ማኑኤል ሳንቶስን የኖቤል ተሸላሚነት ያበቃው ምክክር የተካሄደው በኮሎምቢያ መንግስት እና በኤፍ.ኤ.አር.ሲ አማፂያን መካከል ለአምስት አስርት ዓመታት የዘለቀው እና ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ላለቁበት ጦርነት እልባትን ሰጥቷል። ምክክሩ ከሀገር ውጭ (በኩባ እና ኖርዌይ) በተደረጉ ድርድሮች የተደገፈ ሲሆን፣ ዋናው ትኩረቱ ግን የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ እና የአደንዛዥ ዕፅ ንግድን ማቆም ላይ ያተኮረ ነበር አማፂያኑ ሙሉ በሙሉ ጦርነቱን አቁመው ነፍጣቸውን አስረክበው፤ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲነት በመቀየር ሰላማዊ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ያስቻለ ነው። ኢትዮጵያም ዛሬ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣን ዕዳ በጫንቃዋ ላይ ተሸክማ ቆማ ያንን አሳራፊ መድኃኒት ሽታለች። በዘመነኛው ዓለም ውስጥ ሆና በትላንት በሽታ ትታመማለች። የቀደሙት የጣሉት የስህተት እርሾ ዛሬም ከሊጥ ጋር እየተቦካ የኮመጠጠ የአኗኗር ሥርዓትን ትውልዱ እንዲጋፈጥ ምክንያት መሆን ከጀመረ ከራርሟል። ይህም የማይነጋ ሌሊት መስሎ ታይቶ ብዙዎችን ለቀቢጸ-ተስፋ ዳርጓል። የሰላም በር ዘግቶ ሰላም መፈለግ፣ መክፈቻ ቁልፍ በእጅ ይዞ ወደ ሌላ ማማተር ሆነና ነገሩ፤ ችግሩ ከነግሳንግሱ እያደገ ጥቁር ደመናን በሀገሬ ሰማይ ላይ ለመጋረድ አቅሙን ተጠቀመ። ሆኖም እንደተባለው የማይነጋ ሌሊት፣ የማይፈታ ሕልም የለም። "ፈጣሪም ሀገርን ያለ አንዳች አይተውም" ነውና ቃሉ፤ የተስፋ ብርሃን በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ፈነጠቀ። ወደ ውስጥ የሚመለከት፣ የራስ ማንነትን በኢትዮጵያዊ ቀለም የሚፈትሽ፣ ችግርን ሳይሆን መፍትሔን አነፍንፎ ገሃድ የሚያወጣ፣ ሀገር በቀል ዕውቀትን ያከበረና መልካም የሆኑ ነባር እሴቶችን ለችግሮቻችን ወጌሻ ያደረገ የለውጥ ተስፋ ከተፍ አለ። የመጋቢት ብስራት ኢትዮጵያን ወደ ፍካት ለመለወጥ በሀገር ፍቅር ስሜት አዳዲስ የሰላም መንገዶችን መክፈት ጀምሯል። ከመገፋፋት ይልቅ መደመርን፣ ከመካሰስም ይቅርታን የሚያስቀድመው የመደመር መንግሥት ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ሀሳብ ይዞ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋሙ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስብል ተግባር በኢትዮጵያ ተወጠነ። በፖለቲካ እሳቤም ሆነ በሐሰት ትርክት አልያም የማያግባባ የትኛውንም ጉዳይ በመምዘዝ አኩርፎ ነፍጥ ማንገብን ልምድ ያደረገ የፖለቲካ ሥርዓት ባለበት፤ በአንጻሩ አቅም ኖሮት ሥልጣን የጨበጠ በሀሳብ የተቃረነውን በሚኮንንበትና ቀፍድዶ በወህኒ ቤት በሚያሰቃይባት ምድር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መመካከር ትልቅ ትርጉም አለው። ይህ በደማቅ የታሪክ ቀለም የሚመዘገብ ክስተትም ነው። ምክክር በባህላችን አብሮን የኖረ የማንነታችን አካል የሆነ እሴታችን ቢሆንም ለፖለቲካው ሜዳ ግን እንግዳ ነገር ነውና። ጠላቶቻችን የኢትዮጵያን ሰላምና ዕድገት ማየት አይሹምና ሂደቱን ለማደናቀፍ ጥረዋል። በዚህም የመለወጥ መንገዳችንን ለመዝጋት ብዙ ጉድጓዶችን ምሰዋል። ጉድጓድ ለማዘጋጀት ከሩቅ ያመጡት ቁሳቁስ የለም፤ ከራሳችን ጋር አብሮ ባደገው የዘርኝነት፣ የጽንፈኝነትና አክራሪነት ገሶ (ትልቅ የጉድጓድ መቆፈሪያ) ነው እንጂ። በተለይ የኢትዮጵያ ጌጥ የሆነው ብዝኃ-ብሔር እና ሃይማኖት ብዙ ሳይደክሙ ያጠመዷቸው ፈጣን ውጤት የሚያስገኙላቸው ወጥመዶች ነበሩ። የወል ትርክት በሐሰተኛ ትረካ ተሞልቶ ለብዙዎች ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሆነ። ጠንካራዋ ሀገር ኢትዮጵያ ግን መሠረቶቿ ዓለት ላይ ስለሆኑ ይህ ሁሉ የጥፋት ጎርፍና ነፋስ ሊያነቃንቃት አልቻለም። ይልቁንም በጽናት ቆማ ወጀብ ማዕበሉን ጸጥ የሚያደርግ ሀገርኛ መሣሪያ ታጥቃለች - የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን! በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ አማረ ፈንታው (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋምና በአግባቡ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን አጠናቆ አጀንዳ መለየት መቻሉ የኢትዮጵያውያንን የሥነ-ልቦና እና የሞራል ከፍታ ማሳያ ነው። ለዚህም አመክንዮ ሲያስቀምጡ፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለችግር መፍቻ ወደ ጠረጴዛ ሳይሆን ወደ ጫካ የሚሮጥ የፖለቲካ ሥርዓትን ነው ስታስተናግድ የቆየችው ብለዋል። ዛሬ ላይ ግን ያ ልክ አለመሆኑን የተረዳ ትውልድ በስብዕና ሞራል ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን አሳድሮ በጥይት ሳይሆን በሀሳብ ለማሸነፍ ራሱን አዘጋጅቷል። በጦር ግንባር ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍትሔ ሊያገኝ ከራሱ ጋር ተስማምቷል። ይህ የመማርና የማደግ ውጤት ነው። የትናንት አካሔድ ሞትና ችግርን እንጂ ብልጽግናን አላተረፈም። መመካከር በእጃችን የነበረ አውጥተን ያልተጠቀምንበት ሀብታችን ነው። እንደ ተፈጥሮው ሁሉ እሴታችን የተሸፈነበት አቧራ በምክክር ተራግፎ በአብሮነት እና ዘላቂ ሰላም የምንደምቅባትን ጀንበር ልናይ ንጋት ላይ ተቃርበናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ትልቅ ተስፋ የጣለበት ጉዳይና ውጤቱን አጥብቆ የሻተበት አጀንዳ ምን ይሆን ተብሎ ቢጠና፤ "የምክክር ኮሚሽን ወደ ተግባር መግባት" ከሚለው በላይ ሌላ አጀንዳ ይኖራል ብሎ በልበ-ሙሉነት መግለጽ አይቻልም። ያለ ልዩነት ሁሉም ደግፎ በብርቱ ናፈቀው። የጥንት የአያት ቅድመ-አያቱ ወግ ነባርና አዲስ ሳይሆንበት በብርሃን ፍጥነት ዓላማውን ተረዳ። ተረድቶም ሳይቀር ተስፋውን ወደ ሚጨበጥ ውጤት ለመቀየር ባለው አቅም ሁሉ ለመደገፍ ተረባረበ። ዕድል የገጠመውም በቁርጠኝነት ሂደቱ ላይ ተሳተፈ። የዚህ ድምር ውጤት የምክክር ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ የነበሩ አለመግባባቶች ቁልፍ መፍቻዎች ናቸው ያላቸውን 8 ዋና ዋና የምክክር አጀንዳዎችን በስኬት ለመለየት አበቃው። የምክክሩ አጀንዳ ልየታ ሥርዓት ከአጀንዳ መለየት ያለፈ ትርጉም ያለው ነው። ስኬታማ የተቋም ግንባታ አንጸባራቂ ክስተት ጭምር እንጂ። አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ የሁሉንም አካባቢ ወግ፣ ባህልና ሥርዓት ተገንዝቦ ለሀገር የሚሆን አጀንዳ በስኬት መሰብሰብ የተቋማዊ ብቃት ማሳያ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ማድረግ የምትችል መሆኗን ገላጭ ሌላኛው የድል ገጽ ቢባል ግነት አይሆንም። አጀንዳዎቹ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ናቸው። ኃይል የተሞላበት የፖለቲካ ሥርዓትን በመገርሰስ ወደ ዴሞክራሲያዊ እና የተሟላ የሰላም ደሴት የሚያሸጋግር አጋጣሚ እንደሚሆንም ዶ/ር አማረ ይገልጻሉ። ምክክሩ ለኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በታሪክ ድርሳን የምናስቀምጠውና ወደፊት መጪው ትውልድ የሚያወሳው ኩነት ነው ብለዋል። መምህር ቢመርቅ በርሁን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ናቸው። እርሳቸው የምክክር ኮሚሽንን ተግባር ለኢትዮጵያ ያለውን መልካም ዕድልነት ሲገልጡ፤ ስር የሰደዱ ችግሮችን ከሥር የሚነቅል መሣሪያ ብለውታል። ከግለሰቦች የፖለቲካ ትርክት ተላቆ ወደ ተቋማዊ አሠራር መሸጋገሪያ ድልድይም እንደሆነ እንዲሁ። ኢትዮጵያ በበርካታ ነጠላ ትርክቶች ለሰላም እጦት ተዳርጋለች፣ በግለሰቦች ግላዊ ፍላጎት ብዙዎች ሕይወታቸውን ገብረዋል። ይህ የመጠፋፋት ሰንሰለት ይበጠስ ዘንድ ምክክሩ አስፈላጊ ነው። ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተግባራት ስኬት አካታችነት ትልቅ አቅም እንደሆነውም መምህር ቢመርቅ ያነሳሉ። በኮሚሽኑ የተሠራው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ እንዲሁም የምክክሩ ተሳታፊ መረጣ ሂደት በተማሩ ኃይሎች አልያም በፖለቲካ ልሂቃን ላይ ብቻ መሠረት ያደረገ አይደለም። በታችኛውም እርከን ወርዶ አርሶ አደሩን፣ አካል ጉዳተኛውንና ሌሎችንም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን የጉዳዩ ባለቤቶች ናችሁ ብሎ ማሳተፉ በጎ ውጤት አመልካች ቅድመ-ሂደት ነበር ነው ያሉት። የአካታችነቱ ወሰን መስፋት ሰፊውን የማኅበረሰብ ጥያቄ ይዞ ለመነሳት አስችሎታል። የሁሉም ጥያቄ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ማለትም፦ በሀገር ግንባታ፣ በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልና እና በምርጫ ሥርዓት፣ በፌዴራል ከተሞች (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ አስተዳደር) ጉዳይ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በሰብዓዊ መብቶች፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ በሙስና እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ሥር ተጠልሏል። እነዚህ አጀንዳዎች በአንድም በሌላም የመከፋፈል፣ በጎሪጥ የመተያየትና የጥርጣሬ መንፈስን በመንዛት ዜጎች እርስ በእርስ ከመተማመንና በአብሮነት ከመቀጠል ይልቅ "የኔ" የሚል አጥር ውስጥ እንዲገቡ ያደረጉ ናቸው። በሌላ በኩል "ተበደልኩ"ን ወልደው ኩርፊያን አስፍተዋል። ይህም በአንድ ወገን ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በተለያየ መጠን የሚንጸባረቅ ችግር ነው። አሁን የመጣ ሳይሆን ትናንት የነበረ፣ ለዛሬ የተዘራና እንክርዳድ እያበቀለ ያለ የግጭት ዘር ነው። ሀገራዊ የሆኑ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የአስተዳደር ሥርዓት ፈትሾ እውነትን እና ለነገ የሚበጀውን የወል ትርክት በሕዝብ ይሁንታ ሊያጸና ቀጠሮ የያዘው ኮሚሽኑ፤ በሁሉም ዜጎች ትብብር ሀገራዊ ድልን ያጎናጽፋል። ሰላምና ስኬት ለኢትዮጵያችን! አበቃሁ!!
በመደመር የተቃኘ ኢትዮጵያን የሚመጥን የከተሜነት ጉዞ
Jul 3, 2026 3329
በዮሐንስ ደርበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ጥቅምት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙ ጊዜ፤ የኮሪደር ልማት ዓላማ ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። ከተማ ሲለማ ደግሞ ለነዋሪም ሆነ ለጎብኚ፤ ለዐይንም፣ ለጤናም ለእንቅስቃሴም ውበትና ምቾት ማላበሱ አይካድም። ትናንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ማስተሣሠር የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ! የኮሪደር ልማት ጽዱ ከተሞችን ይሠራል፤ከትራንስፖርት፣ ከትራፊክ ምልክቶች፣ ከብስክሌትና እግረኛ መንገድ ደኅንነት ጋርም ተጣጥሞ ተሠርቷል። በዚህ ዐውድ የኮሪደር ልማት ውበትም ምቾትም ነው። መሠረተ-ልማት ተጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲጠቅምም የኮሪደር ልማት ሚና የላቀ ነው። ኢትዮጵያ በከተሞቿ እና ገጠራማ አካባቢዎቿ የኮሪደር ልማት እያከናወነች ነው። ይህ በኢትዮጵያ ከውበት በላይ ነው። · ማኅበራዊ መሥተጋብርን በመጠገን፡- ኢትዮጵያውያን ከሚታወቁባቸው አንዱ በየዐውዱ የሚገለጠው ጥብቅ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸው ነው። በጋራ መንቀሳቀስ፣ መጫወት፣ ከቤት ወጣ ብለው መመካከር የኑሯቸው አካል ነው። ይሁን እንጂ በተለይም ከተሜው ከወዳጅ ጋር በኅብረት በእግር ወይም በብስክሌት ለመንቀሳቀስ፣ አረፍ ብሎ የሚያወጋበት በቂ አረንጓዴ ስፍራና ፓርኮች ባለመኖራቸው ማኅበራዊ መሥተጋብሩ እየላላ የመጣ ይመስላል። አሁን የኮሪደር ልማት በደረሰባቸው ከተሞች፤ሰዎች ሲያሻቸው በእግር አሊያም በብስክሌት ከወዳጆቻቸው ጋር የልባቸውን እያወጉ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው መሐል ዐረፍ ማለት ቢሹም ችግር የለም፤ አሁን እንደ ድሮ አይደለምና። አረንጓዴ መናፈሻ ስፍራ ፍለጋ ከከተማ መውጣት አያሻም። በሌላ በኩል ወጣቶች እና ሕጻናት ኳስ የሚጫወቱበት ስፍራ መመቻቸቱ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር፤ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸውን ያጠናክራል። · ጤናማ አከባቢን በመፍጠር፡- የኮሪደር ልማት ለሰው ልጆች ከቸራቸው ጥቅሞች አንዱ፤ ጤናማ ከባቢን መፍጠር ነው። በተለይም በደካማ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ለሚታሙ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሁነኛ መፍትሔ ሆኗል። ይህ ደግሞ በቀጥታ ከነዋሪዎች ጤና ጋር ይገናኛል። ደግሞም በንጹህ አካባቢ የመኖር መብትን ማስጠበቅ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመሥራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሠርተዋል ያሉትም ለዚሁ ነው። · በሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኮሪደር ልማት የዘመቻ ሥራ አይደለም።በትንሹ በአንድ ከተማ ወይም አካባቢ ተጀምሮ እየሰፋ ይቀጥላል። በዚህ ሂደት የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ማሰብ አያዳግትም። እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ፤ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያገለግሉ የመኪና ማቆሚያ፣ ሱቆች እና መሰል ለንግድ ተግባራት እንዲበጁ ተደርገው ነው። የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው ይታወሳል። · በገጽታ ግንባታ ረገድ፡- ከተሞች ሲጸዱና ምቹ ሲሆኑ በዓለም ዘንድ መታወቂያ ይሆናሉ። ነዋሪም በኩራት ስለአካባቢው በየሄደበት አምባሳደር ሆኖ ይመሠክራል። ቱሪስቶችንም ይስባሉ። የቆይታ ጊዜያቸውንም ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉ። ዓለም አቀፍ፣ አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎች እንዲካሄድባቸውም እንዲመረጡ ያስችላል። በከተሞች ከሚሠራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት በውጤታማነት እየተሠራ ነው። ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ መሰረተ-ልማት ለዜጎች መቅረቡን ያሳያል። ኮሪደር ልማት ኢትዮጵያውያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ተናግረዋል። የተሟላ ብልጽግና የምናረጋግጠው በዚሁ መንገድ ነውም ብለዋል። የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገት በሁሉም አካባቢ ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት መጠናከር ጠቀሜታው የጎላ ነው። የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ብዙ ጥቅም አለው፤ ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የከተሞች መዋብና ምቹ መሆን ለነዋሪው ነው፤ በቀጥታ ተጠቃሚውም ሕዝቡ። ስለዚህ መንግሥት ከሚያከናውናቸው በተጨማሪ ባለሃብቱ፣የመንግሥትም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ኅብረተሰቡ የኮሪደር ልማትን በተነሳሽነት ለማስፋፋት መትጋት ይጠበቅበታል።
ትላንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ማስተሳሰር - የመደመር መንግስት እይታ በቱሪዝም
Jul 1, 2026 3314
በዮሐንስ ደርበው ቱሪዝም ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመላው ዓለም ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ዘርፍ ነው። ይህ ዘርፍ በአህጉራችን አፍሪካም ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙበት ሃገራት እንዳሉ ይታወቃል። ቱሪዝም ከገቢነት ከኢኮኖሚያዊ እቅምነት ባለፈ ትውልድን ያስተሳስራል ብሄራዊ ትርክትን ለመገንባትም ያግዛል ። ትላንትን ከዛሬ ዛሬንም ከነገ ጋር የሚያስተሳስር ነው። “ሀገራችን ከቱሪዝም ልታገኛቸው የምትችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መላዎች ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን (የመደመር መንግሥት 273)። የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የለውጡ መንግሥት እመርታዎችን ካስመዘገበባቸው ዘርፎች አንዱ ነው። መንግስት ከአምሥቱ የትኩረት መስኮች አንዱ አንድርጎም በጥናት፣ አካባቢያዊ ፀጋን ዐውቆና ለይቶ በተደመረ ዐቅም ባከናወናቸው ሥራዎች በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እሠየው ያሰኙ ተግባራት አከናውኗል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ከእንጦጦ - ቀበና የተከናወነው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም ለጎብኚም ለነዋሪም ምቹ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እየተደረገ ያለውን ትጋት ያስረዳል። ምረቃውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ፤ “መቆሸሽ እኛ አይገባንም፣ መጠልሸት እኛ አይገባንም፣ ማነስ እኛ አይገባንም! ሠርተን እንደምንችል ማሳየት ያስፈልጋል” ሲል የሥራውን ማራኪነትና ውበት ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ወቅት፤ የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ሲሉ በቀጣይ ካለፈው የበለጠ እንደሚሠራ አመላክተዋል። ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ጉልበትን፣ ሐሳብን፣ የአመራር ብቃትን ስንደምር የሚከሰተው ነገር እንደዚህ ያለው ውበት ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው (ገጽ 256) ላይም፤ “የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሀገራት በዘመናቸው ሁሉ የሠሩትንና ተፈጥሮ ያደለቻቸውን መልካም ገጽታ በኩራት ለዓለም የሚያስተዋውቁበት፣ ‘ሀገሬ ይሄንን ትመስላለች’ የሚሉበት መድረክ ነው። ሀገርን በሚያኮራና ለሌሎች ለመጋበዝ በማያሳፍር መልኩ መገንባት፣ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መሠረቱ ነው።” ያሉትም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በቁጭት መነሳታቸውን ይገልጻል። ነገን ዛሬ እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ካላት ላይ ሳትነፍግ የገንዘብም ሆነ የሰው ኃብቷን ቱሪዝም ላይ ስታውል፤ አንድም የኢንዱስትሪውን ዐዋጭነት ብሎም የዜጎቿን በየዘርፉ ዘላቂ ተጠቃሚነት በመገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለሀገር ገቢ በማስገኘት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅም ማጤን ይገባል። በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ቁልፍ የቱሪዝም ልማቶች መከካከል፤ የመስቀል ዐደባባይ ቅርስን ማንበርና ማዘመን፣ ከአዲስ አበባ ልማት ጋር ተሣሥሮ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ መልክ የታደሠው ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ የአምሥቱ ዕውቀት ተኮር ማዕከላት (አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የሀገር በቀል ዕጽዋት ማሳያ፣ የአንድነት ቤተ-መዛግብት እና የማዕድን ሙዝየም) ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ጎብኚዎች የሚያርፉበት ሎጂና ሆቴሎች ግንባታም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ገበታ ለሸገር ብሎ ከአዲስ አበባ የተነሳው የቱሪዝም ልማት በገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ወደ ክልሎች ተስፋፍቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጂዎች እንዲገነቡ አስችሏል። የተገነቡት ሎጂዎች ደግሞ ለጎብኚዎቹ ምቾትን የሚያስጠብቁ መሠረተ-ልማቶችን ስበዋል። በርካታ ጎብኚ መሳብና ገቢን ማሳደግ፣ በጎ ገጽታን መሸጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ተግባራት ሁሉ ግቦች ናቸው። መንግሥት ዕምቅ የጎብኚዎች መስኅብ ዐቅም የሆኑና አቧራ ለብሰው የተደበቁትን ፀጋዎች ውበታቸውን ገላልጦ እያሳዬ ያለውም ለዚህ ነው። ቱሪዝም በቀጥታ ዜጎች (ሰዎች) የሚጠቀሙበት ኢንዱስትሪ ነው። ለዚህ ደግሞ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።መሠረተ-ልማቶችን በመጠበቅ እንዲሁም ከመንግሥት ጎን በመሆን በሚፈለጉበት ሁሉ ንቁ ተሳትፎ በማድረግም ይጠበቅባቸዋል።
ምክክር - ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ!
Jun 24, 2026 7087
በዮሐንስ ደርበው በአመለካከት መለያየት ሥሪቱ ተፈጥሯዊ ነው። ሰዎች ልክ በመልክ፣ ቁመት ውፍረት ወይም ቅጥነት ሥብጥር፤ ምድርም በተፈጥሮ አቀማመጥ እና በዓየር ጠባይዋ ወጥ እንዳልሆኑት ሁሉ ማለት ነው። ለአንድ ሕዝብ እና ሀገር ብልጽግና ሲባል ከተበተነ ይልቅ የተደመረ ሐሳብ በእጅጉ ይጠቅማል። ሀገርኛ ብኂላችን “ከአንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ” ብሎ መሰባሰብን እንደሚሰብከው። የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ጀምሮ ይካሄዳል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ትውልዱ ዛሬንም ነገንም በሚጠቅመው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ንቁ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅበታል የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት ከሥሪታቸው አንጻር ዕሳቤዎች የግድ ተጨፍልቀው አንድ እንዲሆኑ ባይጠበቅም፤ ሀገርና ሕዝብን ወዳስቀደመው በይበልጥ ገዥ ሐሳብ መቅረብ ግን ተገቢ ይሆናል። በአንጻሩ በተለያዩ ዋልታዎች ቆሞ መጓተት ለማን ይጠቅማል? በምክክር ሁሉንም አሸናፊ አድርጎ መቋጨት እየተቻለ ለበርካታ ዓመታት የሐሳብ ልዩነቶች የወለዷቸው ግጭቶች፤ እንደ ሀገር አያሌ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ-ልቡናዊ እና ማኅበራዊ ክስረቶች ማስከተላቸውን ታሪክ ይነግረናል። የለውጡ መንግሥት ለኢትዮጵያ ከቸራቸው ትልልቅ ጉዳዮች የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙ አንዱ ነው። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ሀገር ውስጥ የምንኖር ሕዝቦች ራሳችንን በታማኝነት ፈትሸን በሐሳብ ልዩነቶች ላይ ለመነጋገር መፍቀዳችንን የሚጠይቅ ሂደት እንደመሆኑ፤ በቁጥር የማይተመኑ ረቂቅ የሆኑ ዋጋዎች አሉት። ይህም ፍላጎትን በኃይል ለመተግበር ሕይወትና ንብረት ከሚያወድመው ጦርነት ይልቅ አዋጭ የመግባቢያ መንገድ መሆኑን ያሳያል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል። እዚህ ደረጃ ከመደረሱ በፊት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ኮሚሽኑ በየጊዜው ማሳወቁም ይታወሳል። ሀገራዊ ምክክር በአካታችና አሳታፊ ውይይት ወደ የጋራ መግባባት መድረሻ አትራፊ መንገድ ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም ኃላፊነቱን ለመወጣት ለምክክር በሩን ለሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ክፍት አድርጓል። በዚህም መሠረት ከዳያስፖራው፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በተለያዩ ክልሎች ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩና ሰላምን ከመረጡ ብሎም ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ፤ አጀንዳዎችንም ተቀብሏል። ኮሚሽኑ የመጨሻው የምክክር ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የሚገልጹት ዋና ኮሚሽነሩ፤ አካታች የምክክር ጉባዔ ለማካሄድ በማንኛውም ጊዜ ወደ ምክክሩ ለሚመጡ አካላት በሩ ክፍት መሆኑንም አረጋግጠዋል። የኪንታሮት ህመም እንዴት ይከሰታል? እንዳይከሰት መከላከል የሚቻልበት ብልኀትስ አለ? 👉 ሀገራዊ ምክክር ምን ይጠግናል? የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሥራ በሆነው የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 384 ላይ እንደተቀመጠው፤ በሀገረ-መንግሥት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሕዝብ ተመካክሮ፣ የጋራ መግባባት ላይ ደርሶ፣ የተግባባባቸውን በሕግና በሥርዓት አጽንቶ፤ ያልተግባባባቸውን ለወደፊት ምክክሮች አቆይቶ አልተጓዘም። በዚህ የተነሣ በየጊዜው ቅሬታ፣ ኩርፊያ፣ አብዮት፣ ዐመጽ ይፈጠራል። ነገሮች በተናጠል እየቀረቡ ለፖለቲካ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታ ይመቻቻል። ሁለንተናዊ ዕይታ ይጠፋል። ሀገራዊ ምክክር ይህን የዘመናት ስብራት ይጠግናል። 👉 ሀገሬው ለበለጸገችና ጠንካራ ሀገሩ ምን ይጠበቅበታል? መንግሥት በኢትዮጵያ የሐሳብ ገበያን ባሕል ለማድረግ እየተከተላቸው ካሉ መንገዶች አንዱ ሀገራዊ ምክክር ነው። በመደመር መንግሥት መጽሐፍ (ገጽ 383) ላይ እንደሰፈረው ደግሞ፤ በኢትዮጵያ የሚደረገው ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሐሳቦች በአንድ መድረክ ቀርበው፤ በምክክርና ውይይት ጎልብተው አሰባሳቢና አስማሚ ሆነው የሚወጡበት መድረክ ነው። ስለሀገር የሚያገባው ሁሉም አካል በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ አዋጥቶና ተነጋግሮ መግባባት የሚፈጥርበት ምኅዳር መሆኑም ተገልጿል። ስለዚህ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚከናወነው ለዚህ ታሪካዊ ሁነት መሳካት ኢትዮጵያውያን ከኮሚሽኑ ጎን በመሆን የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል። በሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ለመሳተፍ የተመረጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የባለ ድርሻ አካላት ወኪሎችም ውጤታማ ጉባዔ ማካሄድ የሚችሉበትን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ በኩል፤ አንድነትና ኅብረትን በማጠናከር ልሂቃንና ሕዝብ ለአንድ ከፍ ላለ ዓላማ በአንድ ላይ እንዲቆሙ ያደርጋል። በዚህም ጥረቶች ሁሉ በአንድ አቅጣጫ እንዲፈስሱ ያደርጋል። በሌላ በኩል ፖለቲካዊ መረጋጋትና ሰላምን በመፍጠር የመንግሥት ትኩረት፣ ሀብትና ጊዜ ሳይበታተን ብልጽግናን ለማረጋገጥ ብቻ እንዲውል ያደርጋል (የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 403)። #እንመካከር! #በምክክር_ከሰፈር_እስከ_ሀገር_የተሻለ_ነገን_እንገንባ! #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #ኢትዮጵያ_እየመከረች_ነው
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 10384
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 20647
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 13690
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 19441
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
ቱሪዝም- የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ
Jun 29, 2026 6661
በዮሐንስ ደርበው “ሀገራችን ከቱሪዝም ልታገኛቸው የምትችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መላዎች ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን (የመደመር መንግሥት 273)። የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የለውጡ መንግሥት እመርታዎችን ካስመዘገበባቸው ዘርፎች አንዱ ነው። መንግሥት ከአምሥቱ የትኩረት መስኮች አንዱ አንድርጎም በጥናት፣ አካባቢያዊ ፀጋን ዐውቆና ለይቶ በተደመረ ዐቅም ባከናወናቸው ሥራዎች በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እሠየው ያሰኙ ተግባራት አከናውኗል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች ለአስም በሽታ አጋላጭ ምክንያቶችና ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ከእንጦጦ - ቀበና የተከናወነው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም ለጎብኚም ለነዋሪም ምቹ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እየተደረገ ያለውን ትጋት ያስረዳል። ምረቃውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ፤ “መቆሸሽ እኛ አይገባንም፣ መጠልሸት እኛ አይገባንም፣ ማነስ እኛ አይገባንም! ሠርተን እንደምንችል ማሳየት ያስፈልጋል” ሲል የሥራውን ማራኪነትና ውበት ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ወቅት፤ የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ሲሉ በቀጣይ ካለፈው የበለጠ እንደሚሠራ አመላክተዋል። ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ጉልበትን፣ ሐሳብን፣ የአመራር ብቃትን ስንደምር የሚከሰተው ነገር እንደዚህ ያለው ውበት ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው (ገጽ 256) ላይም፤ “የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሀገራት በዘመናቸው ሁሉ የሠሩትንና ተፈጥሮ ያደለቻቸውን መልካም ገጽታ በኩራት ለዓለም የሚያስተዋውቁበት፣ ‘ሀገሬ ይሄንን ትመስላለች’ የሚሉበት መድረክ ነው። ሀገርን በሚያኮራና ለሌሎች ለመጋበዝ በማያሳፍር መልኩ መገንባት፣ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መሠረቱ ነው።” ያሉትም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በቁጭት መነሳታቸውን ይገልጻል። ነገን ዛሬ እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ካላት ላይ ሳትነፍግ የገንዘብም ሆነ የሰው ኃብቷን ቱሪዝም ላይ ስታውል፤ አንድም የኢንዱስትሪውን ዐዋጭነት ብሎም የዜጎቿን በየዘርፉ ዘላቂ ተጠቃሚነት በመገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለሀገር ገቢ በማስገኘት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅም ማጤን ይገባል። በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ቁልፍ የቱሪዝም ልማቶች መከካከል፤ የመስቀል ዐደባባይ ቅርስን ማንበርና ማዘመን፣ ከአዲስ አበባ ልማት ጋር ተሣሥሮ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ መልክ የታደሠው ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ የአምሥቱ ዕውቀት ተኮር ማዕከላት (አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የሀገር በቀል ዕጽዋት ማሳያ፣ የአንድነት ቤተ-መዛግብት እና የማዕድን ሙዝየም) ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ጎብኚዎች የሚያርፉበት ሎጂና ሆቴሎች ግንባታም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ገበታ ለሸገር ብሎ ከአዲስ አበባ የተነሳው የቱሪዝም ልማት በገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ወደ ክልሎች ተስፋፍቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጂዎች እንዲገነቡ አስችሏል። የተገነቡት ሎጂዎች ደግሞ ለጎብኚዎቹ ምቾትን የሚያስጠብቁ መሠረተ-ልማቶችን ስበዋል። በርካታ ጎብኚ መሳብና ገቢን ማሳደግ፣ በጎ ገጽታን መሸጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ተግባራት ሁሉ ግቦች ናቸው። መንግሥት ዕምቅ የጎብኚዎች መስኅብ ዐቅም የሆኑና አቧራ ለብሰው የተደበቁትን ፀጋዎች ውበታቸውን ገላልጦ እያሳዬ ያለውም ለዚህ ነው። ቱሪዝም በቀጥታ ዜጎች (ሰዎች) የሚጠቀሙበት ኢንዱስትሪ ነው። ለዚህ ደግሞ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።መሠረተ-ልማቶችን በመጠበቅ እንዲሁም ከመንግሥት ጎን በመሆን በሚፈለጉበት ሁሉ ንቁ ተሳትፎ ማድረግም ይጠበቅባቸዋል። ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡበት ጠቅላላ ምርጫ ምክክር - ወደ መግባባት መሻጋገሪያው ድልድይ! ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #ቱሪዝም #PMOEthiopia #በኢዜአ_ዐይን #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት - የሕዝብ ድምጽ
Jun 26, 2026 4561
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት - የሕዝብ ድምጽ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ፍኖቷ ለአፍሪካ አርአያ ሆና አሳይታለች... የአፍሪካውያን ቀንዲል ናት። የክፉ ቀን መሸሸጊያቸው፣ የመከራ ጊዜ መጽናኛቸው፣ የነጻነት ተምሳሌትና የጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በረጅም ዘመናት ታሪካዊ መስተጋብር የተፈጠረ የሀገረ መንግሥት መዋቅር ባለቤት ናት። በተፈጥሮ ጸጋዎች፣ ምድሯን ሰንጥቀው በሚያልፉ ወንዞቿ የምትታወቅ አገር ናት። የተለያዩ ማዕድናት በብዛት የሚገኙባት ከመሆኗም በላይ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህልና እሴቶች ሕብር ሠርተው፣ ተስማምተው የሚኖሩባት የታሪክ ማህደር ናት። ይሁን እንጂ ይህ ታሪካዊ ግርማ ሞገስና የነጻነት አርማነት፣ በውስጣዊ የፖለቲካ ጉዞዋ ውስጥ ካጋጠሟት መዋቅራዊ ስብራቶችና የሥልጣን ፍትጊያዎች ሊታደጋት አልቻለም። ለዘመናት በሀገሪቷ የሰፈነው የሥልጣን ሥርዓት የሰፊውን ሕዝብ ፍላጎትና ተሳትፎ ያገለለ፣ በጥቂት የሕብረተሰብ ክፍሎችና ልሂቃን ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሠረተ ነበር። ይህ አካሄድ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ አንዱን ሥርዓት በሌላው እየተካ፣ የተተካው አገዛዝ ደግሞ የባሰ ጭቆናን ይዞ የሚመጣበትን አዙሪት ፈጥሯል። ከብዙ መቶ ዓመታት የዘውድ አገዛዝ በኋላ የመጣው ወታደራዊ ሥርዓት፣ በመቀጠልም ለ30 ዓመታት ገደማ የዘለቀው የአንድ ወገን የበላይነት የሰፈነበት አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሀገሪቱንና ዜጎቿን ለከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ዳርገው አልፈዋል። ይህ ዓይነቱ የመከራና የጭቆና ሰንሰለት ግን በ2010 ዓ.ም በተቀጣጠለው ሀገራዊ ለውጥ ተገርስሶ ወደ አዲስ የፖለቲካና የዴሞክራሲ ምሕዳር ተሸጋግሯል። ያለፉትን ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ጉዞ ስንመረምር፣ ሀገሪቷ ከአሮጌውና ከተለመደው የአፈና ሥርዓት ወጥታ አዲስ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ አቅም ይዛለች። ይህ ወቅት የዜጎች የፖለቲካ ተሳትፎ መብት በተግባር የተረጋገጠበትና የሐሳብ ብዝኃነት የተስተናገደበት ምዕራፍ ነው። ከዚህ ቀደም የሥልጣን ማራዘሚያ ሆነው ያገለግሉ የነበሩ ዋና ዋና ተቋማት ገለልተኛና ነፃ ሆነው እንዲደራጁ መደረጉ የለውጡ ትልቁ ስኬት ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል። በዚህ የሽግግር ሂደት ውስጥ የለውጡ የመጀመሪያ ፍሬ የታየው በ2013 ዓ.ም የተካሄደው ስድስተኛው ምርጫ ነበር። በወቅቱ የነበሩትን ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተቆቁሞ ሕዝቡ ያሳየው የባለቤትነት ስሜት የዴሞክራሲ ናፍቆቱን በግልጽ ያሳየ ነው። ይህንን ተሞክሮ መሠረት በማድረግ፣ በዘንድሮው የ2018 ዓ.ም የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበልጥ የነቃ አስደናቂ የፖለቲካ ተሳትፎ አሳይቷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ታሪካዊ መድረክ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን የማይናወጥ አቋም አሳይተውበታል። ከንጋት እስከ እኩለ ሌሊት ረጅም ሰዓታትን ተሰልፈው የተፈጥሮ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችንና ልዩ ልዩ ፈተናዎችን በሙሉ በትዕግሥት በመሻገር ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ይህ ሂደት የሚያሳየው ሕዝቡ የሥልጣን ምንጭነቱን በተግባር የተረዳበትና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የወሰነበት ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ነው። በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞና የውስጥ መረጋጋት ሁልጊዜም በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተሉት ጉዳይ ነው። ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የሚነሱ ሥጋቶችና የጂኦፖለቲካ ጫናዎች ቢኖሩም፣ ይህ በስኬት የተጠናቀቀው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቷን የውስጥ ጥንካሬና ሉዓላዊነት በተግባር ያስመሰከረ ሆኗል። በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነፃነትና በሰላም ድምፅ የሰጡበት ይህ ሂደት፣ ኢትዮጵያ የራሷን የውስጥ ጉዳይ በራሷ ዜጎች ፍላጎት የመወሰን ሙሉ አቅም እንዳላት ለዓለም አሳይቷል። ምርጫው ከሁሉ በላይ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ታላቅ ታሪካዊ ክስተት ነው። ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን በመስጠት የሀገሩን ሉዓላዊነትና አንድነት አስከብሯል። የፖለቲካ ሥልጣን የሚገኘው በጠመንጃ አፈሙዝ ወይም በሁከት ሳይሆን በሕዝብ የላቀ ውሳኔ ብቻ መሆኑን በማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካለፈችባቸው የፖለቲካ ስብራቶች በላይ ከፍ ብላ እንድትቆም አድርጓታል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላትን ተደማጭነትና የድርድር አቅም ከፍ የሚያደርግ ነው። የምርጫው ዝርዝር ስኬቶች ምን ምን ናቸው የሚለውን ስንመለከት፦ 👉የአፈሙዝ ድምፅንና የጽንፈኛ ዛቻን ያሸነፈው የሕዝብ ጽናት ግንቦት 24 ታሪካዊ ቀን ናት። በዚህች ታሪካዊ ዕለት፣ በየምርጫ ጣቢያው በነቂስ ወጥቶ ድምፁን የሰጠው ሕዝብ ያሳየው የነጻነት፣ የሉዓላዊነት እና የጽናት ማረጋገጫ ነው። ምርጫውን ለማደናቀፍና ሕዝቡን ለማስፈራራት የተቃጡ የአፈሙዞች ድምፆችና የሁከት ዛቻዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ሕዝብ ከመምረጥ አላፈገፈገም። መራጮች የጽንፈኛ ኃይሎችን ዛቻ ወደ ጎን ትተው፣ የአካላቸውን ሕመም፣ የበሽታን ሥቃይ፣ አልፎ ተርፎም የወሊድ ምጥንና የቅርብ ዘመድ ሞት ያመጣውን ጥልቅ ሐዘን በሕሊናቸውና በሥጋቸው ተሸክመው ነበር ረጅሙን ሰልፍ ተሰልፈው ይበጀኛል ያሉትን በካርዳቸው የመረጡት። ይህ የሚያሳየው እውነት ለኢትዮጵያውያን የምርጫ ካርድ ሰላማቸውን የሚገዙበት፣ መብታቸውን የሚያስከብሩበትና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን በገዛ እጃቸው የሚወስኑበት ብቸኛ የነጻነት አዋጃቸው መሆኑን ነው። ሕዝቡ ከምርጫ ውጭ በሆነ መንገድ፣ በኃይል ወይም በሁከት ሥልጣን ለመያዝ ምኞትና የቆየ የሥልጣን ናፍቆት ላላቸው ወገኖች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግልጽና የማያሻማ መልዕክት አስተላልፏል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የኃይልና የሁከት አካሄድን እንደማይቀበል፣ በድምፅ ላይ ብቻ የተመሠረተ ሕጋዊ ሥርዓትን ለማፅናት እንደሚታገል አረጋግጧል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ይህን ጉዳይ በተመለከተ በአፅንኦት ሲያነሱ፤ "የዘመናችን ዲሞክራሲ አስተምህሮቱ ሰላምና ዕድገት፣ ቋንቋው ደግሞ መምረጥና መመረጥ ብቻ በመሆኑ የፖለቲካ ቅኝታችሁንና አካሄዳችሁን ከዚሁ ስልጡን መስመር ጋር ማስተካከል ይበጃችኋል። ካሁን በኋላ የሕዝብ ድምፅ ያልጎበኘው፣ የምርጫ ካርድ ያልዳሰሰው የፖለቲካ ሥልጣን መያዣ መንገድ በኢትዮጵያ ዝግ መሆኑን እነሆ እንዳየነው መሠረት የጣለ ስለሆነ ይህኑ ስልጡን መንገድ ለመቀበል የማትፈቅዱ ሁሉ ግን ግፋ ቢል የዘመናችን የፖለቲካ ድርሳን ሲጻፍ ልትሆኑ የምትችሉት የግርጌ ማስታወሻ ብቻ ነው።" ብለዋል። ስለሆነም ከዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ሕጋዊ አካሄድ ውጭ የሚደረግ ሙከራ የጥፋት ተዋናይ ከመሆን ባሻገር ለሀገር የሚያተርፈው አንዳች ነገር እንደሌለ በዚህ ስሑት መንገድ ላይ የሚገኙ አካላት ሊገነዘቡ ይገባል። 1. ምርጫው በቁጥሮች ሲገለጽ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በጉልህ የሚጠቀሱ አኃዛዊ መረጃዎች አሉት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ እንደገለጹት፤ ቦርዱ ከ120 ሚሊዮን በላይ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን በውጭ ሀገር አሳትሞ ካስመጣ በኋላ፣ ከምርጫው 4 ቀናት በፊት በሀገሪቱ ባሉት ከ52 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች በታማኝነትና በጥንቃቄ ማድረስ ተችሏል። ይህንን እጅግ ግዙፍና ውስብስብ የሎጂስቲክስ ሥራ ሙሉ በሙሉ ያከናወኑት የቦርዱ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ብቻ መሆናቸው ተቋማዊ አቅሙ ምን ያህል እንደጎለበተ ማሳያ ነው። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ እንደተናገሩት፤ የቦርዱ ሠራተኞችና የምርጫ አስፈጻሚዎች በዕረፍት ቀናትና በሌሊት በመጋዘን ውስጥ ጭምር እያደሩ የቁሳቁስ ማሸግ ሥራዎችን በትጋት አከናውነዋል። ሩቅና ተደራሽነታቸው አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ ቁሳቁሶችን በእግር፣ በእንስሳት ጀርባና በጀልባ ጭምር በማጓጓዝ፣ ወንዞችን ለመሻገር የራሳቸውን የፕላስቲክ ጀልባ ሠርተው ሀገራዊ አደራቸውን ተወጥተዋል። በድምፅ መስጫ ቀን ሥራቸውን ከንጋት እስከ ንጋት በልዩ ብርታት ፈጽመዋል። ይህ ልብ የሚነካ እውነታ የሚያሳየው፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታና የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር የሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ዋጋ ያለው የተናጥልና የጋራ ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን ነው። ሰፊ ተሳትፎ፦ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና 80 የግል ዕጩዎች ተሳትፈዋል። 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲና የግል ዕጩዎች ተወዳድረዋል። ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓርቲዎች ፖሊሲዎቻቸውን ለሕዝብ የሚያስተዋውቁበት የክርክር መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህ ተግባር ፓርቲዎች ከምርጫው ውጭም ራሳቸውን ለሕዝብ የሚያቀርቡበትን ባህል ያዳብራል። የመራጮችና አስፈጻሚዎች ቁጥር፦ በአጠቃላይ 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 861 መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ምርጫውን ለማስፈጸም ከ350 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል። ታዛቢዎችና ወኪሎች፦ ከ260 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ያሰማሯቸው ከ60 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች፣ እንዲሁም 63 የአፍሪካ ኅብረት እና 26 የኢጋድ ታዛቢዎች ተሳትፈዋል። ለመራጩ ሕዝብ የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት ለመስጠት መስፈርቱን ላሟሉ 169 ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰጥቷል። እንዲሁም 21 ሚሲዮኖችና አንድ የውጭ ሀገር የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ምርጫውን ተመልክተዋል። የአየር ሰዓት አጠቃቀም፦ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ነፃ የአየር ሰዓት የማግኘት መብት ስለነበራቸው ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 752.5 ነፃ የሬዲዮ ሰዓት፣ 57.5 ነፃ የቴሌቪዥን ሰዓትና 576 የጋዜጣ ኮለምን በዘመናዊ የዕጣ ማውጣት ሥርዓት ተደልድሎ እንዲጠቀሙ ተደርጓል። መገናኛ ብዙኃን፦ 73 የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃንን የወከሉ 1 ሺህ 827 የሀገር ውስጥና 45 የውጭ ጋዜጠኞች ለዘገባ ሥራ ተሰማርተዋል። የሕግ ማሻሻያ እና ዲጂታላይዜሽን፦ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ተሻሽሎ በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 ተተክቷል። ቦርዱ 10 አዳዲስ መመሪያዎችን አጽድቋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር፦ ለመጀመሪያ ጊዜ በገለልተኛ ባለሙያዎች የሚመራ፣ እያንዳንዳቸው 2 ሰዓት የሚወስዱ 19 የክርክር መድረኮች በቦርዱ ተዘጋጅተዋል። 14ቱ በአማርኛ፣ 5ቱ በክልል ቋንቋዎች (አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ፣ ሲዳምኛ፣ አፋርኛ) ተካሂደው በሰባት መገናኛ ብዙኃን በፕራይም ታይም ተላልፈዋል። አካታችነት፦ 28 ሺህ 632 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ከ20 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲመዘገቡ ተደርጓል። የቅሬታ አፈታትና ክትትል፦ የቅድመ አደጋ ማሳወቂያ ሥርዓት (Early Warning System) ተዘርግቷል። 663 የምርጫ ክልል ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችና ልዩ የአጣሪ ጉባኤ ተደራጅተው 129 አቤቱታዎችን መርምረዋል። የሕግ ጥሰት በተገኘባቸው ጣቢያዎች ውጤት እንዲሰረዝ እና በፈጻሚዎች ላይ አስተዳደራዊና የወንጀል ተጠያቂነት እንዲኖር ተወስኗል። 2. ጠንካራና ገለልተኛ ተቋም፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የሀገር ውስጥ አቅም ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠነ ሰፊ ተቋማዊና ሕጋዊ ማሻሻያዎች የተደረጉበት ከመሆኑም በላይ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ ሀገራዊ አቅምን በተግባር ያሳየ ነበር። የዚህ ምርጫ ትልቁ ትርፍ ጠንካራና የማይናወጡ ብሔራዊ ተቋማትን መገንባት መቻላችን ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳየው ፍጹም ገለልተኝነት፣ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ብቃት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የመተግበር አቅም፣ ተቋማት ከግለሰቦችና ከፖለቲካ ጫና በላይ መሆናቸውን ያስመሰከረ ነው። ይህም ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር አስተማማኝ የመንግሥት መዋቅር መሠረት ነው። ለምርጫው ስኬት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መራጮችን በትዕግሥት በማስተናገድ፣ ብቁ አስፈጻሚዎችን በማሰማራትና ሂደቱን በታማኝነት በመምራት ረገድ ቦርዱ አድናቆት የተቸረው ሥራን ፈጽሟል። የሠራተኞቹ ቀንና ሌሊት መትጋት እንዲሁም በግንባር ቀደምትነት የሚመሩት አመራር አባላት ያሳዩት ቁርጠኝነት የላቀና ለሀገር ኩራት የሆነ ተግባር ነው። በዚህ ምርጫ ውስጥ ትልቁን ትኩረት የሳበውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ሥርዓት ነው። ይህ ዘመናዊ አሠራር ለምርጫው ከተመዘገቡ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች መካከል ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በአካል መጓዝ ሳይጠበቅባቸው፣ ባሉበት ቦታ ሆነው በነፃነት እንዲመዘገቡ ዕድል ፈጥሯል። ቴክኖሎጂው የመራጮችን ማንነት በፎቶግራፍ ጭምር በማረጋገጡ በድምፅ መስጫ ቀን ሊፈጠሩ የሚችሉ ግድፈቶችንና ማጭበርበሮችን በከፍተኛ ደረጃ መከላከል ተችሏል። የዚህ ሥርዓት ዋነኛውና ትልቁ ድል ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የበለጸገ መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የዚህን የቴክኖሎጂ ስኬት አስፈላጊነት ሲያብራሩ፤ "እነዚህ የዲጂታል የምዝገባ ሥርዓቶች በውጭ ሀገር አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች የለሙ ሳይሆን በራሳችን ወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተገነቡ ናቸው። ይህም ተቋሙን ከውጭ አቅራቢዎች ጥገኝነት ነፃ በማድረግ በራሱ አቅም እንዲቆምና ለወደፊቱ ማሻሻያዎችን በራሱ እንዲያከናውን መሠረት ጥሏል።" ይህ እርምጃ ቦርዱ የውጭ የቴክኒክ ጥገኝነትን በመቀነስ የሀገር ውስጥ አቅምን ለመገንባትና የሉዓላዊነትና የደኅንነት ዋስትናን በራስ ቴክኖሎጂ ለማረጋገጥ የቻለበትን ስትራቴጂካዊ አካሄድ በግልጽ ያሳያል። በተጨማሪም በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በውጭ ዜጎች ይሠራ የነበረው የቴክኒክ ድጋፍ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መተካቱ የተሳካ የእውቀት ሽግግር መኖሩን አሳይቷል። 3. ሕጋዊ ማሻሻያዎች፣ አካታችነትና ተጠያቂነት ዴሞክራሲ እውነተኛ ትርጉም የሚኖረው ዜጎች፣ በተለይም ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ያለ ፍርሃትና ጫና፣ ደኅንነታቸው ተጠብቆ በፖለቲካዊ ሂደቶች እኩል መሳተፍ ሲችሉ ነው። ይህንን እውን ለማድረግ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ለምሳሌ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በታዛቢነት በመሳተፍ፣ ሴቶች የዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በነፃነት እንዲጠቀሙና በሂደቱ በንቃት እንዲሳተፉ አስችሏል። ቦርዱ የሴቶችን መብት ከማስከበር ባለፈ፣ ጾታዊ ጥቃትና ትንኮሳን ለመከላከል የሚያስችል ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ አድርጓል። ከዚህም በላይ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ግብረ ኃይል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ አቋቁሟል። በተጨማሪም የምርጫውን ግልጽነትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ቀድሞ የነበረው አዋጅ ቁጥር 1162/2011 በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 እንዲተካ የተደረገ ሲሆን፣ ቦርዱ ይህንን መነሻ በማድረግ 10 አዳዲስ መመሪያዎችን አጽድቋል። በነዚህ ማሻሻያዎች ውስጥ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደ ዋና መርህ የተወሰደ ነው። 4. ፈተናዎችን መጋፈጥና ገለልተኝነትን ማስከበር ይህ ሁሉ ስኬት ግን ያለ ፈተና አልመጣም። ምርጫው በተያዘለት ጊዜ አይካሄድም የሚሉ ጥርጣሬዎችና የተሳሳቱ መረጃዎች ተቋሙን ፈትነውት ነበር። ሆኖም ቦርዱ ጫናዎችን በመቋቋም ሕግና መርህን ብቻ ተከትሎ በመሥራት ምርጫውን ለስኬት ማብቃቱን ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ያረጋግጣሉ። ቦርዱ በምርጫው ወቅት የተቋሙን ነፃነት ከማንኛውም ዓይነት ጫናና ጣልቃገብነት በመጠበቅ በሕግና በመርህ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ ቆይቷል። በምርጫ አፈጻጸም የአሠራር ግድፈቶች እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ ቅሬታዎችን በመመርመር በአንዳንድ የምርጫ ክልሎች በድምፅ መስጫው ቀን ጭምር አስፈጻሚዎችን አሰናብቷል፤ በምርጫ ውጤቶች ላይም ውሳኔ ሰጥቷል። ይህም ቦርዱ ለሕግ የበላይነትና ለምርጫ ታማኝነት ያለውን ጽኑ አቋም ያሳያል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በአንድ ተቋም ወይም በጥቂት ግለሰቦች ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮች በፀሐይና በዝናብ ሳይበገሩ በትዕግሥት የሰጡት ድምፅ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች (እንደ አፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ) እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው። 5. የምርጫው ግልጽነትና ዓለም አቀፍ እውቅና የምርጫውን ታሪካዊ ሂደትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ የሀገር ውስጥና የውጭ አካላት በሰፊው ተሳትፈዋል። ሂደቱን ለመዘገብ 73 ለሚሆኑ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 1 ሺህ 827 ጋዜጠኞች የዘገባ ሥራቸውን አከናውነዋል። ከ260 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች እና ከ64 ሺህ በላይ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበራት ታዛቢዎች በሂደቱ ላይ ተሳትፈዋል። በተለይም በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተሰጣቸው 55 የሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች 60 ሺህ 277 ታዛቢዎችን በማሰማራት ሂደቱን የተከታተሉ ሲሆን፤ 169 ድርጅቶች ደግሞ ለመራጮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተዋል። በአህጉር ደረጃም የኬንያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ60 በላይ ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እና 26 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ታዛቢዎች ሂደቱን በታዛቢነት ተከታትለዋል። ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምርጫው ግልጽ፣ አሳታፊና ተዓማኒ ሆኖ በስኬት መካሄዱንም አረጋግጠዋል። 👉የአፍሪካ ህብረት እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች ምስክርነት የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሰጡት መግለጫ፣ የምርጫው ዕለት ሰላማዊ፣ ሥነ ሥርዓት የሰፈነበት እና ግልፅነት የታየበት መሆኑን ነው ያረጋገጡት። በቴክኖሎጂ የታገዘ የመራጮች ምዝገባ መተግበሩ ወጣቶችን መሳቡን፣ ዜጎች በትዕግሥት ሰልፍ በመያዝ ጥልቅ ፍላጎታቸውን ማሳየታቸውን፣ የሎጂስቲክስ ዝግጅቱ የተሟላ መሆኑንና የምርጫ ሰዓት መራዘሙ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል። በመስተንግዶ ረገድም ወንበሮችና የምግብ አቅርቦቶች መኖራቸው ረጅሙን ሰልፍ ታጋሽ እንዳደረገውና ለአረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መሰጠቱን አረጋግጠዋል። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት "ቅኝ ግዛትን በአንድነት የተከላከለች Couch፣ ለአፍሪካ ነፃነት የቆመች እና የአህጉሪቱ ዋና ከተማ በሆነች ሀገር ውስጥ የተደረገው ይህ ምርጫ ትልቅ ምዕራፍ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ሊኮሩ ይገባል፤ ወደፊት ለመራመድም በሕዝቦች መካከል ያለውን የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ ውይይት ይበልጥ ማሳደግ፣ ወደ ኋላ የተተዉ የሚሰማቸውን አካላት ወደ መድረኩ በማምጣት እና አካታችና የተባበረች ኢትዮጵያን መገንባት ያስፈልጋል" ብለዋል። በሌላ በኩል፣ የኡጋንዳ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ (IGAD) የምርጫ ታዛቢ ቡድን በሰባት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች 28 ጣቢያዎችን በመጎብኘት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን አውጥቷል። ቡድኑ ጣቢያዎቹ በሰዓታቸው መከፈታቸውን፣ በቂ ቁሳቁስና አስፈጻሚዎች እንደነበሩ፣ የሳጥኖች አስተሻሸግ የድምፅ ምስጢራዊነትን ያረጋገጠ መሆኑንና የድምፅ አሰጣጡ ያለምንም መሰናክል በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን በመታዘብ ምስክርነቱን ሰጥቷል። ለአረጋውያን፣ ሕፃናት ለያዙ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መሰጠቱንና መራጮች የሚቀመጡባቸው ወንበሮች መኖራቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በማዘጋጀትና በመምራት ረገድ ከፍተኛ አስተዳደራዊና ኦፕሬሽናል አቅም ማሳየቱን አጉልቷል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ለሰላማዊና ተዓማኒ ምርጫ የተደረገውን የጋራ ቁርጠኝነት ያደነቀ ሲሆን፣ "ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ እና ምርጫ ዕድገት ላይ በተለይም የምርጫ አስተዳደርን ለማሻሻል፣ አካታችነትን እና ተዓማኒነትን ለማሳደግ የተነደፉ ዋና ዋና ቴክኖሎጂያዊ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች የተስተዋሉበት ትልቅ ምዕራፍ ነው" ሲል ቡድኑ ምስክርነታቸውን በአፅንኦት የገለጹት። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ "ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ይበልጥ እንዲጠናከርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲመዘገብ አብረን ለመሥራት ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት እናረጋግጣለን።" ሲሉ ነው የተደመጡት። 6. የምርጫው ውጤት፣ የሕዝቡ ጽናትና የአሸናፊው ፓርቲ ከባድ ሸክም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት፣ ብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 መቀመጫዎችን በማግኘት አሸንፏል። በሌላ በኩል ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎችም በምክር ቤቶቹ ወንበሮችን ማግኘት የቻሉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) 13፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ስድስት፣ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሦስት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሦስት፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ሦስት፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ሁለት ወንበሮችን አሸንፈዋል። በሌላ በኩል ኦብነግ፣ ጉህዴን፣ አርጎባ አንድነት ጀበርቲ፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ፣ የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ፣ ኅብረት ለዴሞክራሲና ለነጻነት፣ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት፣ የጌዴዮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እያንዳንዳቸው አንድ ወንበር ሲያገኙ 8 የግል ተወዳዳሪዎችም ምክር ቤት ለመግባት አሸንፈዋል። ይህን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ከሌሎች ጊዜያት ለየት የሚያደርገው ታላቅ ክስተት፣ መራጩ ሕዝብ በታጋሽነት ተሰልፎ የመምረጥ መብቱን ለመጠቀም ያሳየው ወደር የለሽ ጽናት ነው። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ይህንን የሕብረተሰብ አደራ "አሸናፊው ፓርቲ ትልቅ ሀገራዊ ሸክም የተጣለበት መሆኑን ብልፅግና ፓርቲ በሚገባ ይረዳል። ፓርቲያችን በማኒፌስቷችንና በአጠቃላይ በምርጫ ቅስቀሳችን ወቅት ለሕዝብ ቃል የገባናቸውን በተግባር ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ይንቀሳቀሳል" ብለዋል፡፡ 👉የፉክክርና የትብብር ሚዛን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምሕዳር በቀጣይነት ሊመራበት የሚገባው ስልጡን መስመር በፉክክርና በትብብር መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቆ መጓዝ ነው። ብልፅግና ፓርቲ ከሌሎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በሀገር ግንባታ ላይ ሚና ካላቸው አካላት ጋር በብሔራዊ ጥቅም ላይ በትብብር ለመሥራት ያለው አቋም የጸና መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በሰጡት አስተያየት፤ "ባለፉት ዓመታት የጀመርነውን በፉክክርና በትብብር መካከል ሚዛን ጠብቆ የሚሄድ ጥረታችንን በቀጣይ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል። በምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ሕዝቡን በማሳተፍ፣ በየጊዜው የሕዝቡን ግብረ መልስ በመስማት፣ ያንን እንደ ግብዓት ተጠቅመን የእቅድ አካል አድርገን ወደ ተግባር ለመተርጎም በቁርጠኝነት እንንቀሳቀሳለን።" ብለዋል። ይህ ዕይታ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሕዝብን ድምፅና ግብረ መልስ በየጊዜው የሚያዳምጥ፣ እንዲሁም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለሀገር ጥቅም በጋራ የመሥራትን ስልጡንና አካታች የአሠራር ሥርዓት መከተል መጀመሩን ያሳያል። 7. ዴሞክራሲና ምርጫው የሚገለጽባቸው አራቱ ምሰሶዎች ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ማለት አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይና የሁለንተናዊ ብልጽግናችን መሠረት ነው። ብዝኃነትን በአግባቡ ማስተናገድ፣ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥና ጠንካራ ሀገር መገንባት የሚቻለው በዴሞክራሲያዊ ምሰሶዎች ላይ በመመሥረት ብቻ ነው። መንግሥት ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሲሠራ ቆይቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ የሲቪል ማኅበራት ሚና የማይተካና አዎንታዊ ሚና አላቸው። መራጩን ሕዝብ ከማስተማር፣ ሕገ መንግሥታዊ የመምረጥ መብቱን እንዲጠቀም ከማስቻል፣ እስከ ሰላም እሴት ግንባታና በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ድልድይ በመሆን የዜጎችን ባለቤትነት ከማረጋገጥ አኳያ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ እንደገለጹት፣ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በአራት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ የቆመ ነው። አንደኛው ምሰሶ፦ ምርጫ የሰላም ዋስትና መሆኑን መረዳት ነው። ሕዝቡ ልዩነቶችን በፀብና በአምባጓሮ ከመፍታት አዙሪት ተላቆ፣ በሰላማዊ መንገድ የመሻገር ባህልን መርጧል። በነቂስ ድምፁን መስጠቱ ኋላ ቀር የአመፃ መንገድን ለሚከተሉ ሁሉ "በቃችሁ" የሚል መልዕክት ያስተላለፈበት ሲሆን፣ የሰፊው ሕዝብ ማዕበላዊ ድምፅ ከአሮጌው የብጥብጥ ባህል መላቀቅ እንደሚፈልግ ማረጋገጫ ነው። ሁለተኛው ምሰሶ፦ የምርጫ ውግንና ከሕዝብ ጋር መሆኑን ማወቅ ነው። የምርጫ ተዓማኒነትና ክብሩ የሚገለጠው ሥልጣን ከሚመነጭበት ከሰፊው ሕዝብ ሉዓላዊ መብትና ፍላጎት ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ነው። ምርጫ ከሚሰጠው ኃላፊነት በላይ ለእያንዳንዱ ዜጋ የዕለት ተዕለት ሕይወት መሻሻልና ከሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ሕዝቡ በትክክል ተገንዝቧል። ሦስተኛው ምሰሶ፦ የምርጫው የፖሊሲ ሐሳቦችና አማራጮች ከፍታ የታየበት ነው። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የክርክር መድረኮች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያነሷቸውን የፖሊሲ አማራጮች ሕዝቡ በጥንቃቄ አዳምጧል። እነዚህ ሐሳቦች ለሀገር ዕድገት፣ ለጠንካራ መንግሥትና ለሰከነ የፖለቲካ ባህል ግንባታ መሠረት እንዲሆኑ በእያንዳንዱ ዜጋ ሕሊና ማስረፅ፣ በሰነድ በማዘጋጀትም መተግበር ይገባል። አራተኛው ምሰሶ፦ ምርጫ እንደ ማኅበራዊ ሀብት፤ ምርጫ ፖለቲካዊ ኩነት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ማኅበራዊ ሀብት መሆኑን በተግባር አሳይቷል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የዚህን ማኅበራዊ እሴት አንድምታ ሲያብራሩም "ሕዝባችን ስለ ኢትዮጵያዊ ቀናነቱና ፍቅሩ ጩኸቱን ሳይሆን የምርጫ ካርድ ድምፁን፣ ስላቅና ሃኬትን ሳይሆን ትሑትነቱን፣ የትኛውንም የፖለቲካ ሐሳብ ቢያራምድ እንኳን ማኅበራዊና ሀገራዊ ፍቅሩን ከጎኑ ላለው ወገኑ አለመንፈጉን ያየንበት እጅግ የተዋበ መድረክ ነበር። ስለዚህ የኢትዮጵያ ምርጫ ከፖለቲካዊ ፋይዳው ባልተናነሰ ሁኔታ ማኅበራዊ ፋይዳውም ከፍ ያለ ትልቅ የማኅበራዊ መሠረትን የሰጠው ነው።" ብለዋል። 8. የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ታሪካዊ ሚና፦ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስብራቶች የመፈወስ ዕድል ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥትና የፖለቲካ ሥርዓት ጉዞዋ ውስጥ በርካታ አኩሪ ታሪኮችን ብታስመዘግብም፣ በሂደቱ ውስጥ የተፈጠሩና ዛሬም ድረስ ሀገራዊ አንድነቷን፣ ሰላሟንና የዴሞክራሲ ግንባታዋን እየተፈታተኑ ያሉ ሥር የሰደዱ የፖለቲካ ስብራቶች መኖራቸው አይካድም። እነዚህን ለዘመናት የዘለቁ ስብራቶች በመጠገን ረገድ ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሀገሪቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊያሻግር የሚችል ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ ዕድል ይዞ መጥቷል። ምርጫው በበሰለና አካታች መንገድ በመመራቱ በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ላይ ጉልህና አዎንታዊ አሻራ ማሳረፍ የሚችልባቸው ዋና ዋና አቅጣጫዎች አሉት። እነዚህም፦ የቅቡልነት ስብራትን ማከም፦ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመንግሥታት ሥልጣን አመጣጥ አብዛኛውን ጊዜ ከኃይል ፖለቲካ ወይም ሙሉ በሙሉ ነፃ ካልሆኑ ምርጫዎች ጋር የተያያዘ በመሆኑ፣ የመንግሥት ሕዝባዊ ቅቡልነት ማጣት ለግጭቶች መነሻ ሲሆን ቆይቷል። ይህ ምርጫ ነፃና ታማኝ ሆኖ መካሄዱ አሸናፊው አካል ከሕዝብ የሚሰጠው እውነተኛ የሥልጣን አደራ እንዲኖረው ያደርጋል፤ ይህም በገዥው አካልና በሕዝቡ መካከል ያለውን መተማመን በማደስ ረገድ ትልቅ ዕድል ይሰጣል። የሰላማዊ ሥልጣን ሽግግር ባህልን መገንባት፦ ሥልጣንን በአፈሙዝ የመያዝ ልምድ ሀገሪቱን በተደጋጋሚ ለድቀት የዳረጋት መሆኑ ብዙ ትምህርት ሰጥቷል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሁሉም ወገኖች የሕዝብን ድምፅ አክብረው የሚቀበሉበት ድባብ መፈጠሩ ምርጫን ብቸኛ የሥልጣን መያዣና መልቀቂያ መንገድ የማድረግ አዲስና ጤናማ የፖለቲካ ባህል በሀገሪቷ ውስጥ እንዲለመድ ያደርጋል። በተቋማት ላይ ያለውን አመኔታ ማደስ፦ ሕዝቡ እንደ ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤቶችና የዴሞክራሲ ተቋማት ባሉ ገለልተኛ መሆን በሚገባቸው ተቋማት ላይ ያለው እምነት መሸርሸሩ ሌላው ስብራት ሲሆን፣ ይህንንም ምርጫ በስኬትና በገለልተኝነት ማካሄድ መቻሉ የተቋማቱን ነፃነትና ብቃት በተግባር የሚያሳይ በመሆኑ ዜጎች በሀገሪቷ የሕግ የበላይነት ላይ ያላቸው እምነት መልሶ እንዲያገግም ያደርጋል። ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር፦ አካታች የሆነ ምርጫ ማካሄድ መሣሪያ ያነሱ ወይም በሰላማዊ መንገድ የሚያምፁ የፖለቲካ ኃይሎች ቅሬታቸውን በሕዝብ ድምፅ እንዲፈትሹ በር ይከፍታል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዘመናት የፖለቲካ ስብራቶች ለመፈወስ የራሱ አሻራ ሊያኖር የሚችለው ሂደቱ ፍትሐዊ፣ ግልጽና በርካታ የፖለቲካ ኃይሎችን ያሳተፈ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በንቃት የተሳተፈበት በመሆኑ ነው። በዚህም ምርጫው በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ በራሱ ወደ ሰፊው ብሔራዊ ምክክር ለመሻገር እንደ ትልቅ መነሻ ሆኖ ያገለግላል። ማጠቃለያ፦ ምርጫው ለአፍሪካ ዴሞክራሲ የብርሃን ፍኖት አፍሪካ በፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች፣ በወታደራዊ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትና ኢ-ሕገመንግሥታዊ መንገድ መምራት፣ የመንግሥት ግልበጣዎች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ የታሪክ ምዕራፍ፣ ኢትዮጵያ በሰላማዊና ስልጡን መንገድ ምርጫዋን ማጠናቀቋ ለአህጉሪቱ አዲስ ፍኖተ ዴሞክራሲ ሆና እንድትወጣ አድርጓታል። 'የአፍሪካ ችግሮች የአፍሪካውያን መፍትሔዎች' የሚለውን መርህ በተግባር በማሳየት፣ የራሳችንን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በራሳችን አቅም መቅረጽ እንደምንችል ለዓለም አሳይተናል። በዚህ አስቸጋሪ አህጉራዊ ድባብ ውስጥ፣ የፓን አፍሪካኒዝም ማዕከልና የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊና ፍትሐዊ መንገድ በስኬት ማጠናቀቋ ለአፍሪካ ትልቅ ተስፋን የሚሰጥ ነው። ኢትዮጵያ ለጫናዎች ሳትበገር፣ በራሷ ሁለንተናዊ አቅም ያከናወነችው ይህ ታሪካዊ መድረክ ሀገር በቀል ዴሞክራሲን እና አህጉራዊ ሉዓላዊነትን ያረጋገጠ በመሆኑ ለመላው አፍሪካ ኩራትና ተምሳሌት ሆኗል። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፤ አህጉሪቱ ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ዲሞክራሲ አማራጭ የሌለው መንገድ መሆኑን ገልጸው፤ ሰላምና ልማት ሊመጡ የሚችሉት በጠመንጃ ኃይል ሳይሆን ሕዝብ በነፃነት የራሱን መሪ በሚመርጥበት ስልጡን መንገድ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም፦ "አህጉራችን ከዲሞክራሲ ውጭ ሌላ ምርጫ የላትም። ወደፊት ለመራመድ፣ ዕድገትን ለማረጋገጥና በተለይም ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ዴሞክራሲ ብቻ ነው" ሲሉ በአፅንኦት ጠቅሰዋል። በአጠቃላይ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ ኢትዮጵያ ተቋማዊ አቅሟንና ሕጋዊ መሠረቷን በማጠናከር ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የተሻገረችበት እና የጋራ የትብብር አቅምን ያሳየችበት አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል። ለዚህም ስኬት በየሚናቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ የጸጥታ ኃይሎች፣ የአፍሪካ ኅብረትና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እንዲሁም ሀገር በቀል ታዛቢ ድርጅቶች በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል። በምርጫው ወቅት የተሰጠው የሕዝብ አመኔታና ድምፅ ለተመራጮች ትልቅ አደራና ኃላፊነትን ጥሏል። ያሸነፉ ፓርቲዎችና ዕጩዎች ይህንን ታሪካዊ አደራ በመሸከም ለሕዝብ ፍላጎት ቅርብ የሆነ አገልግሎት በመስጠት፣ በታማኝነት፣ በቅንነትና ንጹሕ በሆነ ሕሊና በመሥራት የሕዝቡን ተስፋ ወደ ተጨባጭ ውጤት የመቀየር ግዴታ አለባቸው። የምርጫው ትልቁና የመጨረሻው ስኬት የሚለካው በተመራጮችና በሕዝብ መካከል በሚገነባው መተማመን፣ በሚረጋገጠው ዘላቂ ሰላምና ለሁሉም ተጠቃሚነትን በሚያሰፍነው ሀገራዊ ዕድገትና ብልጽግና ብቻ ነው።