ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ያሸነፉባቸው ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድሮች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ያሸነፉባቸው ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድሮች
አዲስ አበባ፤ ህዳር 7/2019 (ኢዜአ)፦ በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲነየም ደረጃ በተሰጠው የሆንግ ኮንግ ግማሽ ማራቶን ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል አስመዝግበዋል።
በወንዶች አትሌት አዲሱ ጎበና በ1 ሰዓት ከ01 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ አሸንፏል። አትሌት አሊዪ ቃሲም በ1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ31 ሴኮንድ በመግባት ሁለተኛ ወጥቷል።
አትሌት ታፈረ አዲሱ 1 ሰዓት 05 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ 8ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በሴቶች ምድብ አትሌት ውዴ ከፋሌ ሰዓት ከ09 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ አሸንፋለች።
አትሌት ፋንቱ ወርቁ በ1 ሰዓት 09 ደቂቃ ከ16 ሴኮንድ ሶስተኛ ወጥታለች። አትሌት ባራኪ ረዳኢ አራተኛ ፣አትሌት አስማረች አንለይ አምስተኛ እና አትሌት ዘውዴ ውዱ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በኔዘርላንድስ በተካሄደ በ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር አትሌት አሳየች አይቸው የዓለም ሁለኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ በድንቅ ብቃት ማሸነፏን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያመለክታል።
45 ደቂቃ ከ29 ሴኮንድ አትሌቷ የገባችበት ጊዜ ነው።