ቀጥታ፡

በክልሉ በበጋ መስኖ ልማት 95 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል

ባህር ዳር፣ህዳር 7/2019(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በበጋ መስኖ ልማት 95 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ለበጋ መስኖ ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁሟል።

የቢሮው የመስኖ ተቋማት አጠቃቀም፣ አስተዳደርና ጥገና ዳይሬክተር አቶ ምኒሊክ ሙላት ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዘንድሮው የበጋ ወቅት 734 ሺህ 432 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እስካሁን ከ108 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ፣ በአትክልትና ሌሎች ሰብሎች ተሸፍኗል።

ከታቀደው መሬት ውስጥም 250 ሺህ ሄክታሩ በአዲስ የሚለማ መሆኑን ጠቁመዋል።በዚህም በበጋ መስኖ ልማቱ 95 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ነው የገለፁት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም