የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውጤቶች - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውጤቶች
አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሃዋሳ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ገብርኤላ አበበ እና አረጋሽ ካልሳ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሰባት ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 2ኛ ከፍ አድርጓል።
ሃዋሳ ከተማ በአምስት ነጥብ ከነበረበት 6ኛ ደረጃ ወደ 7ኛ ዝቅ ብሏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ቦሌ ክፍለ ከተማ በአምስት ነጥብ ስምንተኛ፣ ሲዳማ ቡና በአራት ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዘዋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ነገ ይጠናቀቃል።