ቀጥታ፡

የዳካር የወጣቶች ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ያላትን ታላቅነት በድጋሚ አረጋግጧል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ የዳካር የወጣቶች ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ያላትን ታላቅነት በድጋሚ ያረጋገጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የ2026 የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ አስደናቂና ታሪካዊ ድል ላስመዘገቡ ወጣት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቴን ማስተላለፍ እወዳለሁ ብለዋል።

አትሌቶቹ 5 የወርቅ እና 3 የብር ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 8 ሜዳሊያዎችን በማግኘት የአትሌቲክስ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን በአንደኛነት መምራታቸው፣ የኢትዮጵያን ጥልቅ የስፖርት ተሰጥኦ እና በአትሌቲክሱ ዘርፍ ያላትን ታላቅነት በድጋሚ ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ከፍ አድርጋችሁ ማውለብለባችሁን እንዲሁም አዲሱን ትውልድ ለላቀ ድል እንዲተጋ ማነሳሳታችሁን ቀጥሉ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም