ኢትዮጵያ እና ካናዳ ለኮፕ 32 ስኬት በጋራ እንደሚሰሩ ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ካናዳ ለኮፕ 32 ስኬት በጋራ እንደሚሰሩ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ካናዳ ለኮፕ 32 ስኬት በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ።
31ኛው የተባበሩት መንግስት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) እየተካሄደ ይገኛል።
የገንዘብ ሚኒስትርና የኮፕ 32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን፣ ከካናዳ የአካባቢ፣ የአየር ንብረት ለውጥና ተፈጥሮ ጥበቃ ሚኒስትር ጁሊ ዳብሩዚን ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ትብብርና አጋርነትን ማጠናከርን ያለመ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመቋቋም፣ የአየር ንብረት መቋቋም አቅምን ለማጠናከርና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በጋራ የተለዩ ቅድሚያ ጉዳዮችን ለማራመድ ትብብርን ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል።
በተጨማሪም ውይይቱ የኢትዮጵያን የኮፕ 32 ራዕይ ለማሳካት በጋራ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።