የሳምንቱ ተጠባቂ መርሐ ግብር ፣ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቻል - ኢዜአ አማርኛ
የሳምንቱ ተጠባቂ መርሐ ግብር ፣ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቻል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 6 /2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ከቀኑ 10 ሰዓት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቻል በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረትን ስቧል።
የወቅቱ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዘጠኝ ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው።
ተጋጣሚው መቻል በአራት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ይዟል።
በአራተኛ ሳምንት መቻል ድሬዳዋ ከተማን 7 ለ 0 በመርታት በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል።
ሁለቱ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ቡድኖቹ በ2018 ዓ.ም በሊጉ በተገናኙባቸው ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከልደታ ክፍለ ከተማ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ድሬዳዋ ከተማ ከሸገር ከተማ በድሬዳዋ ስታዲየም እና ይርጋጨፌ ቡና ከጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ በተመሳሳይ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
ሌላኛው መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ እና አዳማ ከተማ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባህር ዳር ስታዲየም ያገናኛል።