በተጠባቂው መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 7/2019 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሀሳቤ ሙሶ እና እሙሽ ዳንኤል ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ቱሪስት ለማ የመቻልን ብቸኛ ጎል አስቆጥራለች።
በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ12 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
ንግድ ባንክ በውድድር ዓመቱ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በሙሉ ያሸነፈ ብቸኛ ክለብ ነው።
መቻል በአራት ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ሸገር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
የይርጋጨፌ ቡና ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከልን 3 ለ 1፣ አዳማ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 0 እና ልደታ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ አራተኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከህዳር 18 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።
የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን የሸገር ከተማዋ ማርታ ወልዴ እና ቱሪስት ለማ ከመቻል በተመሳሳይ አራት ጎሎች በጋራ እየመሩ ነው።