ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በትግራይ ክልል ከሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በትግራይ ክልል ከሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር ተወያዩ
የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በትግራይ ክልል ከተሰማሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር በቀጣናው ወቅታዊ የግዳጅ አፈጻጸምና ቀጣይ ተልዕኮዎች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
ውይይቱ ሕገ-ወጡ የህወሓት ቡድን የከፈተውን አራተኛ ዙር ጦርነት ለመመከት በተደረጉ ውጊያዎች አፈጻጸምና በተመዘገቡ ውጤቶች ላይ ያተኮረ ነው።
በመድረኩም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የውጊያውን ሂደት በዝርዝር ከመገምገም ባለፈ፣ ሠራዊቱ ላሳየው የላቀ ጀግንነትና ዝግጁነት አድናቆታቸውን በመግለጽ አባላቱን አበረታትተዋል።
በተጨማሪም ሠራዊቱ በቀጣይ በሚያከናውናቸው ወታደራዊ ግዳጆችና ተልዕኮዎች ዙሪያ ዝርዝር የሥራ መመሪያ አስተላልፈዋል።
#Ethiopia #ENDF #NationalSecurity