ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የልማት እቅዶችን ለመፈፀምና ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተናል - የስራ ሃላፊዎች
Oct 4, 2026 18
ሀዋሳ ፤መስከረም 24/2019(ኢዜአ) :- የተያዙ የልማት እቅዶችን ለመፈፀምና ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት በገባነው ቃል መሰረት ሃላፊነታችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉ የሲዳማ ክልል የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ገለጹ። የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው መስራች ጉባኤ ርእሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎችን ሹመት በማጽደቅ በይፋ ስራ የተጀመረ መሆኑ ይታወቃል። በርእሰ መስተዳደሩ የቀረቡ አስፈፃሚዎችም በምክር ቤቱ ሹመታቸው ፀድቆ ቃለ ማሃላ ፈፅመው የመንግስትና የህዝብ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ከተሿሚዎቹ መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አበራ አርጎ (ዶ/ር)፤ በተለይም የትውልድ ግንባታ መሰረት በሆነው የትምህርት ሴክተር ህዝብን ማገልገልና ሃላፊነትን መወጣት ትልቅ እድል መሆኑን ተናግረዋል። በትምህርት ዘርፉ ባለፉት አምስት አመታት የመጡ ለውጦችና የተመዘገቡ ስኬቶች የሚደነቁ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ህዝብንና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በተደመረ አቅም ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የተሰጠው ትኩረትና የመጣው ውጤት መልካም መሆኑን የገለጹት ሃላፊው የተሻለ ውጤት ለማምጣት በቀጣይ ብዙ ስራ ይጠብቀናል ብለዋል። በክልሉ የተያዙ የልማት እቅዶችን ለመፈፀምና ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት በገባነው ቃል መሰረት በተደመረ አቅም ሃላፊነታችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉም ተናግረዋል። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ አዳዲሶችን በመገንባትና የመምህራንን አቅም በማጎልበት ጭምር የዘርፉን እድገትና ማንሰራራት ለማስቀጠል እንሰራለን ብለዋል። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ወሰንየለህ ስምኦን፤ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የገዥ ትርክት ግንባታ ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር ለህብረ ብሄራዊ አንድነትና የሀገር ግንባታ በልዩ ትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ትልቅ ሃላፊነት ያለበት መሆኑን በማንሳት የክልሉ መንግስት ኮሙንኬሽን በትጋት የሚሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል። በክልሉ የተያዙ የልማት እቅዶችን ለመፈፀምና ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ሃላፊዎቹ ገልጸዋል።
በዞኑ የሚገኙ የየቱሪዝም መስህቦችን የማልማትና የማስተዋወቅ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው
Oct 4, 2026 24
ጭሮ ፤ መስከረም 24/2019 (ኢዜአ)፦ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የሚገኙ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶችን በመለየት የማልማትና የማስተዋወቅ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ምዕራብ ሐረርጌ በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙና በታሪካዊ፣ ባህላዊ እንዲሁም ተፈጥሯዊ ሀብቶቻቸው ከሚታወቁ ዞኖች አንዱ ነው። አካባቢው በረጅም የደጋ፣ ወይናደጋና ቆላማ የአየር ንብረት የተከፋፈለ በመሆኑ ለተለያዩ የተፈጥሮና የዱር አራዊት ሀብቶች ምቹ ስነ-ምህዳር አለው። በዞኑ ከሚገኙ ደኖችና የተፈጥሮ ተራሮች መካከል የጨርጨር ተራሮች ሰንሰለትና የጭላሞ ደን የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክና ከሐረር ዝሆን መጠለያ ጋር የሚያያዙት ቆላማ ቦታዎች ደግሞ የበርካታ አጥቢ እንስሳትና አእዋፋት መኖሪያ ናቸው። በሌላ በኩል፣ ዞኑ በርካታ ሰው ሰራሽና ሃይማኖታዊ ቅርሶችን አቅፎ ይዟል። በአሁኑ ወቅት የቱሪዝም ሴክተሩን በመደገፍና የአካባቢ ቅርሶችን በማልማት የገቢና የሥራ ዕድል ምንጭ ለማድረግ ለተያዘው ሀገራዊ አቅጣጫ ምላሽ ለመስጠት፣ የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ቅርሶቹን የመለየት፣ በካርታ የመደገፍ፣ ይዞታቸውን የማረጋገጥና ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች የማስተዋወቅ የተቀናጀ ሥራ እየሰራ ይገኛል። በዞኑ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት የቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት ቡድን መሪ አቶ ሳኖ አደም ለኢዜአ እንደገለፁት በዞኑ የቱሪዝም አቅምን በማሳደግ የጎብኚዎችን ቁጥር እንዲጨምር እና ከዘርፉ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ጥቅም ለማስፋት ትኩረት ተሰጥቷል። በዞኑ 15 ወረዳዎች የሚገኙ ከ50 በላይ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን በመለየት የማልማት እና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በዞኑ በቅርስነት ከተለዩት መካከል የተለያዩ ዕድሜ ጠገብ ዋሻዎች ፣ ፓርኮች፣ ሃይማኖታዊ ቅርሶች እና የጨርጨር ሀይቅ እንደሚገኙበት አብራርተዋል። በዞኑ ዳሮ ለቡ ወረዳ የሚገኘውና ከሶስት ሺህ ዓመት በላይ ዕድሜ እንዳለው የሚገመተውን የአይናጌ ዋሻን ለቱሪዝም ልማቱ ለማዋል በተለያዩ ዘዴዎች ከማስተዋወቅ በተጨማሪ አካባቢውን ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። የዳሮ ለቡ ወረዳ አስተዳደር በዚህ ዓመት ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመያዝ የመንገድ መሰረተ ልማት የማሻሻል ስራ እያከናወነ መሆኑን አመልክተዋል። ከአይናጌ ዋሻ በተጨማሪ የጨርጨር ሀይቅ ዳርቻን የቱሪዝምና የመዝናኛ መዳረሻ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በሀይቁ ዙሪያ የመዝናኛና የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለማስፋፋት የዞኑን 15ቱንም ወረዳዎች በማሳተፍ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አካባቢውን ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ለማከናወን መታቀዱን አንስተዋል። በሀይቁ ላይ ከመሰረተ ልማት ግንባታ በተጨማሪ የመጓጓዣ አገልግሎትም እየተሻሻለ መሆኑን የገለፁት ቡድን መሪው፤ የቦኬ፣ ኦዳ ቡልቱምና ሀብሮ ወረዳዎች የሀይቅ ላይ መጓጓዣ ጀልባዎችን ገዝተው ወደ አገልግሎት ማስገባታቸውን አስረድተዋል። በዞኑ ከሶስት ዓመታት ወዲህ የተመሰረቱት ሁለት ፓርኮችን ጨምሮ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ ጥንታዊ ቤተ እምነቶችም ለቱሪዝም መስህብነት ትልቅ አቅም መሆናቸውን ተናግረዋል። ከእነዚህ የቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል የኡላ ቁኒ መስጊድና የአሰቦት ገዳም ዋነኞቹ መሆናቸውንና በስፋት ለማስተዋወቅ፣ ለጎብኚዎች ተደራሽ ለማድረግና የቱሪዝም ሀብትነታቸውን ለማጎልበት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። የቦኬ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ዘይን ጀማል እንዳሉት፣ የወረዳው አስተዳደር በተጠናቀቀው ዓመት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የጨርጨር ሐይቅ አካባቢን ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ የመንገድ መሰረተ ልማት የማሻሻል ስራ አከናውኗል። ሀይቁ ለበርካታ ዓመታት ደርቆ በአረንጓዴ አሻራ ስራ ዳግም ነፍስ የዘራ በመሆኑ በአካባቢው የተፈጥሮ ጥበቃ ስራውን በማጠናከር እንክብካቤ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ እየተመዘገበ የሚገኘው ተጨባጭ ለውጥ ቀጣይነት እንዲኖረው የምክር ቤት አባላት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል
Oct 4, 2026 49
ሐረር ፤ መስከረም 24/2019 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል እየተመዘገበ የሚገኘው ተጨባጭ ለውጥ ዘላቂነት እንዲኖረው የምክር ቤት አባላት የሚያደርጉትን የክትትልና ድጋፍ ስራቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 7ኛ ዙር 1ኛ ዓመት መስራች ጉባዔው የምክር ቤቱን አፈ ጉባዔና ምክትል አፈ-ጉባኤዎችን እንዲሁም የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ሾሟል። እንዲሁም ምክር ቤቱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የቀረበውን የክልሉን መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሹመት አፅድቋል። ይህን በማስመልከት አስተያየታቸውን የሰጡት የከተማው ነዋሪዎች የምክር ቤት አባላቱ በክልሉ እየተመዘገበ የሚገኘውን የለውጥ ስራዎች ለማስቀጠል የሚያስችሉ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ወጣት ደረጀ መስፍን እንዳለው በአገሪቷም ሆነ በክልሉ ከተማና ገጠር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተጨባጭ የለውጥ ስራዎች ተግባራዊ ተደርገዋል። መንግስትና ህዝብ በጋራ በመሆን የነዋሪውን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ገልጾ፤ የምክር ቤቱ አባላትም በልማቱ ቀጣይነት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ነው የተናገረው። አቶ ፈጠነ በጅጋ የተባሉ የከተማው ነዋሪ በበኩላቸው በምክር ቤቱ ምስረታ ላይ አዳዲስና ልምድ ያላቸው አመራሮች ወደ አመራርነት መምጣታቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም በክልሉ የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል ትልቅ ሃላፊነት መሆኑን ጠቁመው እንደ ህዝብም የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የለውጥ ስራዎች ሐረርን ውብና ማራኪ በማድረግ ቱሪስቶች እንዲበራከቱ ማስቻሉት የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ቲማጅ ጃሚ ናቸው። በክልሉ የተጀመሩ ስራዎችን የምክር ቤቱ አባላትና አመራሩ በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። አቶ አማረ አበበ የተባሉ የከተማው ነዋሪ በበኩላቸው መንግስት ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረገ እና ክልሉን የለወጡ በርካታ የልማት ስራዎች አከናውኗል ብለዋል፡፡ በቀጣይም የክልሉ መንግስት ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ በርካታ ስራዎችን እንደሚያከናውን ተስፋ እንደሚያደርጉ ጠቁመው ህዝቡም ይህን መደገፍ እንደሚገባው ተናግረዋል።
የኢሬቻ በዓል የህዝቦችን አንድነት፣ አብሮነትና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ ታላቅ በዓል ነው
Oct 4, 2026 92
አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2019 (ኢዜአ)፦የኢሬቻ በዓል የህዝቦችን አንድነት፣ አብሮነትና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ ታላቅ በዓል ነው ሲሉ የቢሾፍቱ ሆረ ሀርሰዴ በዓል ታዳሚዎች ገለጹ፡፡ የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በአባገዳዎች የምርቃት ስነ-ስርዓት ተጀምሮ በአሁኑ ወቅት የኢሬፈና ስነ-ስርዓት በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም እንዲሆን ፈጣሪን የሚለምንበት በዓል ነው፡፡ የኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ በዓል ታዳሚ ደረጄ ፍቅሩ በሰጠው አስተያየት፤ ህዝቡ ባህልን የሚገልጹ አልባሳትን ለብሶ በዓሉን በጋራ በፍቅርና በአንድነት እያከበረ ይገኛል ብሏል፡፡ የኢሬቻ በዓል ማራኪና ውብ በሆነ ሁኔታ ሁሉም በአንድነት የሚያከብረው በዓል መሆኑን ጠቅሶ በዓሉ አብሮነትንና አንድነትን የሚያጎለብት ነው ብሏል፡፡ ቦረና አበራ በበኩሉ፤ በዓሉ ሥርዓቱን ጠብቆ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው ብሏል፡፡ ኢሬቻ የኢትዮጵያውያን ህብረ-ብሔራዊ አንድነት መገለጫ በመሆኑ የእርስ በእርስ መስተጋብርን የሚያጎለብት በዓል መሆኑን ተናግረዋል። ኢሬቻ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ሁሉም የሚሳተፍበት፣ አንድነትንና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ በዓል መሆኑን ገልጿል። ሌላኛዋ የበዓሉ ታዳሚ ሲፈን ኡርጌሳ በበኩሏ፤ የበዓሉ ባህላዊ እሴቱ ሳይበረዝ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ጠቅሳለች፡፡
የክልሉ መንግስት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን አዲስ የአስተዳደር መዋቅር መዘርጋቱ አስደስቶናል
Oct 4, 2026 79
አዳማ ፤ መስከረም 24/2019 (ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ክልል መንግስት መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ልማትን ለማፋጠን አዲስ የአስተዳደር መዋቅር መዘርጋቱ እንዳስደሰታቸው የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። በኦሮሚያ ክልል አዲስ የተዋቀረው የመንግስት አስተዳደር የሕዝቡን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል። ክልላዊ መንግሥቱ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጠንካራ ሥርዓትንና ብቁ መንግሥትን የሚመሠርት አዲስ ሪፎርም ወደ ሥራ ካስገባቸው ታሪካዊ ውሳኔዎች መካከል አንዱ የዞኖች መዋቅር ነው። የክልሉ መንግስት አዳዲስ ዞኖችን በማዋቀር አስተዳዳሪዎችን በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ በመመደብ በሥራ ላይ ባዋለው በአዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት ክልሉ በስድስት ዞኖች እንዲዋቀር ተደርጓል። በዚህም በክልል ደረጃ ተንጠልጥሎ ቀርቶ የነበረው አገልግሎት በአዲስ መልክ እስከ ዞን፣ ወረዳ እና ቀበሌ ድረስ መዋቅር ተዘርግቶ ወደ ስራ ተገብቷል። ይህም በአዲስ አዋጅ የተደነገገ ሲሆን፣ በዚህ አዲስ አደረጃጀት በዞን ደረጃ ሕጋዊ ሥልጣንና የሥራ ድርሻ ያላቸው 23 መሥሪያ ቤቶች ወደ ሥራ የሚገቡ ይሆናል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት፤ የክልሉ መንግስት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እና የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የዘረጋውን አዲስ የአስተዳደር መዋቅር በደስታ ተቀብለዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ፋይሳ መገርሣ እንደገለጹት አዲስ የተዘረጋው መዋቅር በክልሉ የተጀመረውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል የሚያስችል ነው። ክልሉ በ21 ዞኖች ተለጥጦና ተበታትኖ ነበር ያሉት አቶ ፈይሳ፤ አመች የአስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋትና ሀብቱንና የሰው ሃይሉን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችል ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል። በተለይም ብቃት ባለው የሰው ሃይል ለመምረት፣ ቴክኖሎጂን ተደራሽ ለማድረግና ፈጣን ለውጥ በሁሉም መስክ ለማምጣት የሚያስችል የክልሉን ካፒታልና የሰው ሃይሉን በተቀናጀ መልኩ ወደ ልማት ለማስገባት አጋዥ የሆነ የአስተዳደር መዋቅር ነው ብዬ አምናለው ብለዋል። በተጨማሪም አሁን የተጀመረውን አገልግሎትን ዲጂታል የማድረግና ብቃት ባለው የሰው ሃይልና አመራር ለመምራት እድል የሚሰጥ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። አዲሱ የዞኖች አደረጃጀት የመንግስት አገልግሎትና አመራሩ ህዝቡን በቅርበት እንዲያገለግሉ የሚያስችል ነው ያሉት ደግሞ አቶ ዲሪባ ጫላ ናቸው። "ስንመኘውና ስንጠብቀው የነበረ የአስተዳደር አደረጃጀት ነው ተግባራዊ የሆነው" ያሉት አቶ ዲሪባ፤ መዋቅሩ አገልግሎቱን ህዝቡ በቅርበት እንዲያገኝ ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል። በ21 ቦታ ተበታትነው የነበሩ ዞኖችን ጨምቆ በስድስት ዞኖች ማደራጀቱ አመራሩ ህዝቡን በሙሉ አቅም እንዲያገለግልና ፈጣን ልማትና እድገት እንዲመጣ የሚያስችል ነው ብለዋል። በተለይም ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ፣ የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ፣የተጀመረውን ልማትና እድገት አጠናክሮ ለማስቀጠል የጎላ ሚና ያለው አደረጃጀት መሆኑን ገልጸዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ሙሀመድ አብዱልጀሊል በበኩላቸው አዲሱ አደረጃጀት በብዙ ቦታ የተበታተኑ ዞኖችን ወደ ውስን ዞኖች የመለሰ ከመሆኑም ባለፈ ልማቱን የሚያፋጥን ነው ብለዋል። በፊት በነበረው የተበታተነ አደረጃጀት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ጥያቄዎችን ወጥነት ባለው መልኩ ለመመለስ አስቸጋሪ ነበር ያሉት አቶ ሙሀመድ፤ አዲሱ አደረጃጀት በተቀናጀ መልኩ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። በተለይ አዲሱ መዋቅር ብቃትና ስነ ምግባር ባላቸው የሰው ሃይል እንዲመራ መደረጉ ህብረተሰቡ በየጊዜው ለሚያነሳው ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ ሚናው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል።
ፖለቲካ

ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማተራመስ የፈጠሩት ጥምረት እየመከነ ነው - አብረሃም በላይ (ዶ/ር)
Oct 3, 2026 214
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23/ 2019 (ኢዜአ) ፦የውጭ ጠላቶች እና የውስጥ ባንዳዎች ተናበው ኢትዮጵያን ለማተራመስ የፈጠሩት ጥምረት በጸጥታ ኃይሎች እየመከነ መሆኑን አብረሃም በላይ (ዶ/ር)። አብረሃም በላይ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በትርምስ ውስጥ እንድትቆይ የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶች ተናበው በመስራት ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ጠላቶች ከውስጥ ባንዳዎች ጋር በመቀናጀት የከፈቱት ጥቃት በመከላከያ ሠራዊት እየተቀለበሰ መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ አቅሟ እንዳይዳብር እና ጠንካራ እንዳትሆን የሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች፣ በተለይም የኤርትራ (ሻዕቢያ) መንግሥት ከህገ ወጡ ሕወሃት እና ከሌሎችም ጸረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ትጥቅ በማስታጠቅ እና ሠራዊት በማዝመት በጦርነቱ በቀጥታ መሳተፋቸውን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ የጸጥታ ተቋማት ባላቸው ከፍተኛ ወታደራዊ ዲሲፕሊን፣ የቴክኖሎጂ አቅም እና ዝግጁነት የጥፋት ኃይሎቹን ተልዕኮ እያመከኑ ነው ብለዋል። በተለይም የትግራይ ሕዝብ የቡድኑን የጥፋት መንገድ በመገንዘብ ጀርባ የሰጠው በመሆኑ፣ የጥፋት ጥምረቱ ዓላማ ሊሳካ አለመቻሉ አብራርተዋል። #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ህዝብ #ታላቅ_ርዕይ
በትግራይ ክልል አዲስ ጊዜያዊ አስተዳደር በማዋቀር በወራት ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ እየተሠራ ነው - አብረሃም በላይ (ዶ/ር)
Oct 3, 2026 226
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል ፈጣን ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት ሕዝቡ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበትን አዲስ መዋቅር እየዘረጋ መሆኑን አብረሃም በላይ (ዶ/ር) ገለጹ። አብረሃም በላይ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ በአሁኑ ወቅት የመከላከያ ሠራዊት ክልሉን ከሕገ-ወጥ ኃይሎች እያጸዳ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ይህንን ተከትሎም ከቀበሌ ጀምሮ አዳዲስ የአስተዳደር መዋቅሮች በሕዝቡ ተሳትፎ ይደራጃሉ ብለዋል። ይህ የሽግግር ሂደት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። በዚህ ሂደትም የትግራይ ሕዝብ የሀገራችን ልማት ተቋዳሽ እንዲሆን መላው ኢትዮጵያዊ ከፌዴራል መንግሥት ጎን በመቆም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። #ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በልዩነት ውስጥ መግባባት በመፍጠር ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ መስጠት እንደሚቻል ማሳያ ሆኗል - ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
Oct 3, 2026 238
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በልዩነት ውስጥ መግባባት በመፍጠር ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ መስጠት እንደሚቻል ማሳየቱን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የምክክር አጀንዳ ነጥቦችና ምክረ ሐሳቦች ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌዴራልና ለክልል መንግሥታት በይፋ የማስረከብ ሥርዓት አካሂዷል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን ዐበይት ተግባራት አብራርተዋል። በዚህም የሀገራዊ ምክክር ጥንስስ ሕዝባዊ ፍላጎት እንደነበረው አስታውሰው፤ የለውጡ መንግሥትም ሕዝባዊ ፍላጎትን በማሰብ በቁርጠኝነት ሀገራዊ ምክክር እንዲካሄድ ማድረጉን ገልጸዋል። በአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታም ከሀገር ውስጥ እስከ ተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ተወካዮችን በግልጽ በመለየት ከሐምሌ 8 2018 ዓ.ም ጀምሮ በስምንት ዐበይት አጀንዳዎች ላይ ውጤታማ የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄዱን አስታውሰዋል። አራት ሺህ የኢትዮጵያውያን ወኪል ተመካካሪዎችም በ10፣ በ50፣ በ250 እና በሥራ ቡድን አማካኝነት ውጤታማ ምክክር በማካሄድ ለሀገራዊ መግባባት መሠረት የጣሉ ምክረ ሐሳቦች ማቅረባቸውን አንስተዋል። በዚህም 400 የሚጠጉ ዝርዝር ምክረ ሐሳቦችና 80 የሚጠጉ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያና የሕግ አሠራር ሥርዓት የሚሹ እጅግ መሰረታዊ ምክረ ሐሳቦች መቅረባቸውን አስረድተዋል። በምክክር ሂደቱም ድጋፍ ላደረጉ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ተቋማት፣ አመራሮች፣ ዓለም አቀፍ አጋሮችና ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ምክረ ሐሳቦችን በመሰነድ ለፌዴራል መንግሥት፣ ለሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ማስረከባቸውን ተናግረዋል። የፌዴራል መንግሥት፣ የክልል መንግሥታትና የከተማ አስተዳደሮች የምክክር ምክረ ሀሳቦችን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በልዩነት ውስጥ መግባባት በመፍጠር፣ የምክክር ባህል በማዳበርና ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ መስጠት እንደሚቻል ያሳየ ወሳኝ ሁነት መሆኑን አስታውቀዋል። በተለይም ተመካካሪዎች በልዩነት ውስጥ መግባባት ላይ መድረስ እንደሚቻል ያሳዩበት ታሪካዊ ሂደት እና የጋራ ችግሮችን በምክክር መፍታት እንደሚቻል ትምህርት የተገኘበት መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ የሀገራዊ ምክክር ምክረ ሐሳቦች ተፈጻሚ የሚሆኑበትን የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ተግባራዊነቱን በቅርብ ይከታተላል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
Oct 3, 2026 221
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ምክረ ሐሳቦች ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ የሚሆኑበትን የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋትና የቅርብ ክትትል በማድረግ ተፈጻሚነታቸውን እንደሚያረጋግጥ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ አስታወቁ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የምክክር አጀንዳ ነጥቦችና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌዴራልና ለክልል መንግሥታት በይፋ የማስረከብ ሥነ ሥርዓት አካሂዷል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ሀገራዊ ምክክር በስኬት በማጠናቀቅ የምክክሩን ምክረ ሐሳብ ያዘለ ሰነድ መዘጋጀቱ አስደሳች ነው። ኢትዮጵያውያን በሉዓላዊነታቸውና ብሔራዊ አንድነታቸው ላይ የሚቃጣውን ማንኛውንም ዓይነት ትንኮሳ በብቃትና በከፍተኛ መስዋዕትነት ሲመክቱና ሲያስከብሩ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ በመላው አፍሪካና በዓለም ደማቅ የዘመናት አኩሪ ታሪክ ያለን ሕዝቦች ነን ብለዋል። ይህ የጀግንነት፣ አርበኝነትና አትንኩኝ ባይነት መንፈስ እንደተጠበቀ ሆኖ በውስጥ ጉዳዮች ተደማምጦና ተመካክሮ በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን መፍጠር አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱን ጠቁመዋል። በሀገራዊ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን በመገንባት የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማፋጠን ፈታኝ ሆኖ መቆየቱንም ተናግረዋል። በዚህም ባለፉት ዓመታት የትርክት መዛባትን፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስብራቶችን ለማስተካከል መጠነ ሰፊ ርብርብ በማድረግ የሚታይና የሚዳሰስ ውጤት መገኘቱን አስገንዝበዋል። ለዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነትና በወሰዱት ቁርጠኛ አቋም አካታችና ውጤታማ ሀገራዊ ምክክር መካሄድ መቻሉን አብራርተዋል። ይህንን ርዕይና የመንግሥትን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙን አስታውሰዋል። በማቋቋሚያ አዋጁም ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪል ማኅበራት፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች አስተያየት ተካቶበት በሥራ ላይ መዋሉን አስገንዝበዋል። በአዋጁ መሠረትም መስፈርቱን የሚያሟሉ፣ የምክክር ሂደቱን የሚመሩና የሚያስተባብሩ 11 ኮሚሽነሮችን ለመሰየም 632 ዕጩዎች መመዝገባቸውን አስታውሰዋል። በዚህም ዕጩዎቹን ወደ 75፣ 42 እንዲሁም ወደ 11 ለመውሰድ የትምህርት ዝግጅትንና የሥራ ልምድን ጭምር በማካተት አሳታፊና አካታች ምልመላ በማካሄድ መሾማቸውንና ሂደቱ የነበረውን ግልጽነት አስረድተዋል። ኮሚሽኑም ተቋሙን በማደራጀት፣ ዕቅድ በማዘጋጀት፣ የምክክር ሥነ-ዘዴ በመቅረጽ፣ ሀገራዊ ጉባኤ አጀንዳዎችን በማሰባሰብና ተሳታፊዎችን በማስመረጥ ሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጉባኤው መጀመሩን አስታውሰዋል። አራት ሺህ የምክክር ጉባኤ ተመካካሪዎችም በስምንት ዐበይትና ንዑሳን አጀንዳዎች ተከባብረውና ተደማምጠው የሀገርን የውይይትና የፖለቲካ ባህል የሚቀይር መሠረት የጣለ አስደማሚ ምክክር ማካሄዳቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያውያን ወኪል ተመካካሪዎች በአጀንዳዎቹ ዙሪያ ያቀረቧቸው ምክረ ሐሳቦችም በምክክር ኮሚሽኑ ምክር ቤት በዝርዝር ታይቶና አስተያየት ታክሎበት በሰነድ መልክ ተዘጋጅቶ መረከባቸውን ተናግረዋል። ሰባተኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክረ ሐሳቦቹ ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ የሚሆኑበትን የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋትና ቅርብ ክትትል በማድረግ ተፈጻሚ እንዲሆኑ እንደሚያደርግም አስታውሰዋል። የፌዴራል መንግሥት፣ የክልል መንግሥታትና የከተማ አስተዳደሮች ለምክረ ሐሳቦቹ ተግባራዊነት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። የክልል መንግሥታትና ከንቲባዎች የተረከቡትን ሰነድ በዝርዝር በማጤን፣ ዕቅድ በማዘጋጀትና ተስማሚ የአሠራር ሥርዓት ተበጅቶለት ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል። የምክክር ጉባኤው ምክረ ሐሳቦች ተፈጻሚነትም አስፈላጊው ክትትል ይደረጋል ያሉት አፈ ጉባኤው፤ ለምክክር ሂደቱ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ለነበራቸው ተቋማትና አመራሮችም ምስጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከብሔራዊ ምክክሩ የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦችንና ምክረ ሐሳቦችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ለፌደራል እና ለክልል መንግሥታት ዛሬ አስረከበ
Oct 3, 2026 241
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ) ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች በተገኙበት በተካሄደ መርሃ ግብር፤ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከብሔራዊ ምክክሩ የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦችንና ምክረ ሐሳቦችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ለፌደራል እና ለክልል መንግሥታት ዛሬ በይፋ አስረክቧል። ይህ የሰነድ ርክክብ፤ በምክክርና በሰላማዊ መንገድ የኢትዮጵያን የቆዩ ሀገራዊ ፈተናዎች መፍታት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ፤ በመደመር መንግሥት ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ የተበጀለትን የሀገራዊ ምክክር ሂደት አንድ ትልቅ ምዕራፍ እንደሚያበስር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ሂደቱ ለውይይት፣ ለጋራ መግባባት እና ስምምነትን ለመፍጠር የሚያስችል አካታች መድረክ መመስረቱን አመልክቷል። ባለፉት አራት ዓመታትም ይህ ሂደት በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ማሳተፍ ችሏል። ተሳታፊዎች ባደረጓቸው ሰፊ ምክክሮች እና በተጠናቀቀው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አማካኝነት እይታዎቻቸውን ለማንጸባረቅ፣ ልዩ ልዩ አመለካከቶችን ለመስማት እና የጋራ መግባባት የተደረሰባቸውን መስኮች ለመለየት ዕድል አግኝተዋል። የእነዚህ ውጤቶች በይፋ መቅረብ በምክክሩ የተሰበሰቡ እይታዎችንና የውሳኔ ሐሳቦችን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለማሸጋገር የተቀየሰ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
የተጀመሩ የልማት ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ይጠናከራሉ
Oct 3, 2026 259
ቦንጋ፤ መስከረም 24/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የተጀመሩ የልማት ስራዎች ለስኬት እንዲበቁና የሕዝቡ ተጠቃሚነት ይበልጥ እንዲጠናከር እንደሚሰሩ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ገለጹ። የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን በመሰየም የምስረታ ተከናውኖ በይፋ ስራ የተጀመረ መሆኑ ይታወቃል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የክልሉ ምክር ቤት አባላትም የልማት ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው አስፈፃሚውን አካል በማገዝ፣ በመደገፍና ቁጥጥር በማድረግ ኃላፊነታቸውን የሚወጡ መሆኑን ገልጸዋል። የምክር ቤት አባላቱ በህዝብ የተጣለባቸውን አደራ በቅንነትና በታማኝነት ለመወጣት ስለመዘጋጀታቸውም አረጋግጠዋል። ከምክር ቤቱ አላት መካከል ኡስታዝ ሸረፈዲን ኑሩ እና አቶ ዳዊት ተሰማ፤ የህዝብ አደራና ሃላፊነት ቀላል አለመሆኑን አንስተው በገቡት ቃል እና በወሰዱት አደራ መሰረት ሃላፊነታቸውን ለመወጣት በጽናት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ሌላኛው የምክር ቤት አባል አቶ መስፍን ጉብላ፤ አዲስ የተመሰረተው መንግስት ብዙ ስራዎች የሚጠብቁት መሆኑን አንስተው ለስኬት እንዲበቃ የሚጠበቅብንን አደራ እንወጣለን ብለዋል። የክልሉ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም በታርጫ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል። #ትልቅ_ሀገር፣ #ትልቅ_ሕዝብ፣ #ታላቅ_ርዕይ

ማህበራዊ
የኢሬቻ በዓል የህዝቦችን አንድነት፣ አብሮነትና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ ታላቅ በዓል ነው
Oct 4, 2026 92
አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2019 (ኢዜአ)፦የኢሬቻ በዓል የህዝቦችን አንድነት፣ አብሮነትና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ ታላቅ በዓል ነው ሲሉ የቢሾፍቱ ሆረ ሀርሰዴ በዓል ታዳሚዎች ገለጹ፡፡ የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በአባገዳዎች የምርቃት ስነ-ስርዓት ተጀምሮ በአሁኑ ወቅት የኢሬፈና ስነ-ስርዓት በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም እንዲሆን ፈጣሪን የሚለምንበት በዓል ነው፡፡ የኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ በዓል ታዳሚ ደረጄ ፍቅሩ በሰጠው አስተያየት፤ ህዝቡ ባህልን የሚገልጹ አልባሳትን ለብሶ በዓሉን በጋራ በፍቅርና በአንድነት እያከበረ ይገኛል ብሏል፡፡ የኢሬቻ በዓል ማራኪና ውብ በሆነ ሁኔታ ሁሉም በአንድነት የሚያከብረው በዓል መሆኑን ጠቅሶ በዓሉ አብሮነትንና አንድነትን የሚያጎለብት ነው ብሏል፡፡ ቦረና አበራ በበኩሉ፤ በዓሉ ሥርዓቱን ጠብቆ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው ብሏል፡፡ ኢሬቻ የኢትዮጵያውያን ህብረ-ብሔራዊ አንድነት መገለጫ በመሆኑ የእርስ በእርስ መስተጋብርን የሚያጎለብት በዓል መሆኑን ተናግረዋል። ኢሬቻ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ሁሉም የሚሳተፍበት፣ አንድነትንና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ በዓል መሆኑን ገልጿል። ሌላኛዋ የበዓሉ ታዳሚ ሲፈን ኡርጌሳ በበኩሏ፤ የበዓሉ ባህላዊ እሴቱ ሳይበረዝ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ጠቅሳለች፡፡
የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በቢሾፍቱ በድምቀት እየተከበረ ነው
Oct 4, 2026 97
አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2019 (ኢዜአ)፦የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በቢሾፍቱ መልካ አርሰዴ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች የምርቃት ስነስርዓት የተጀመረ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በሀርሰዴ መልካ የኢሬፈና (የምስጋና) ስነስርዓት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ሁሉን ነገር ለፈጠረ አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም እንዲሆን ፈጣሪን የሚለመንበት በዓል ነው፡፡ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች በሆራ ሀርሰዲ የ‘ኢሬፈና’ ሥነ-ሥርዓትን አስጀመሩ
Oct 4, 2026 123
ቢሾፍቱ፤መስከረም 24/2019(ኢዜአ)፦አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዲ የ‘ኢሬፈና’ (የምስጋና) ሥነ-ሥርዓትን በይፋ አስጀመሩ። በዚሁ መርሃ-ግብር መሰረት አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም የበዓሉ ታዳሚዎች ወደ ሆራ ሀርሰዲ በመሄድ እርጥብ ሳርና አበባ በመያዝ የፈጣሪን ታላቅነትና በጎነት የሚያስቡበትን የ‘ኢሬፈና’/ምስጋና ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀምረዋል። ይህንንም ተከትሎ ከየአቅጣጫው የተወጣጡ በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በኦሮሞ ማህበረሰብ ውብ ባህላዊ አልባሳት አጊጠው፣ የሰላም፣ የፍቅርና የእርቅ ምልክት የሆኑ ባህላዊ እሴቶችን በማንጸባረቅ የ‘ኢሬፈና’ (ምስጋና) ሥነ-ሥርዓቱን በደመቀ ሁኔታ በማከናወን ላይ ይገኛሉ።
ኢኮኖሚ
በዞኑ የሚገኙ የየቱሪዝም መስህቦችን የማልማትና የማስተዋወቅ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው
Oct 4, 2026 24
ጭሮ ፤ መስከረም 24/2019 (ኢዜአ)፦ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የሚገኙ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶችን በመለየት የማልማትና የማስተዋወቅ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ምዕራብ ሐረርጌ በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙና በታሪካዊ፣ ባህላዊ እንዲሁም ተፈጥሯዊ ሀብቶቻቸው ከሚታወቁ ዞኖች አንዱ ነው። አካባቢው በረጅም የደጋ፣ ወይናደጋና ቆላማ የአየር ንብረት የተከፋፈለ በመሆኑ ለተለያዩ የተፈጥሮና የዱር አራዊት ሀብቶች ምቹ ስነ-ምህዳር አለው። በዞኑ ከሚገኙ ደኖችና የተፈጥሮ ተራሮች መካከል የጨርጨር ተራሮች ሰንሰለትና የጭላሞ ደን የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክና ከሐረር ዝሆን መጠለያ ጋር የሚያያዙት ቆላማ ቦታዎች ደግሞ የበርካታ አጥቢ እንስሳትና አእዋፋት መኖሪያ ናቸው። በሌላ በኩል፣ ዞኑ በርካታ ሰው ሰራሽና ሃይማኖታዊ ቅርሶችን አቅፎ ይዟል። በአሁኑ ወቅት የቱሪዝም ሴክተሩን በመደገፍና የአካባቢ ቅርሶችን በማልማት የገቢና የሥራ ዕድል ምንጭ ለማድረግ ለተያዘው ሀገራዊ አቅጣጫ ምላሽ ለመስጠት፣ የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ቅርሶቹን የመለየት፣ በካርታ የመደገፍ፣ ይዞታቸውን የማረጋገጥና ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች የማስተዋወቅ የተቀናጀ ሥራ እየሰራ ይገኛል። በዞኑ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት የቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት ቡድን መሪ አቶ ሳኖ አደም ለኢዜአ እንደገለፁት በዞኑ የቱሪዝም አቅምን በማሳደግ የጎብኚዎችን ቁጥር እንዲጨምር እና ከዘርፉ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ጥቅም ለማስፋት ትኩረት ተሰጥቷል። በዞኑ 15 ወረዳዎች የሚገኙ ከ50 በላይ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን በመለየት የማልማት እና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በዞኑ በቅርስነት ከተለዩት መካከል የተለያዩ ዕድሜ ጠገብ ዋሻዎች ፣ ፓርኮች፣ ሃይማኖታዊ ቅርሶች እና የጨርጨር ሀይቅ እንደሚገኙበት አብራርተዋል። በዞኑ ዳሮ ለቡ ወረዳ የሚገኘውና ከሶስት ሺህ ዓመት በላይ ዕድሜ እንዳለው የሚገመተውን የአይናጌ ዋሻን ለቱሪዝም ልማቱ ለማዋል በተለያዩ ዘዴዎች ከማስተዋወቅ በተጨማሪ አካባቢውን ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። የዳሮ ለቡ ወረዳ አስተዳደር በዚህ ዓመት ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመያዝ የመንገድ መሰረተ ልማት የማሻሻል ስራ እያከናወነ መሆኑን አመልክተዋል። ከአይናጌ ዋሻ በተጨማሪ የጨርጨር ሀይቅ ዳርቻን የቱሪዝምና የመዝናኛ መዳረሻ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በሀይቁ ዙሪያ የመዝናኛና የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለማስፋፋት የዞኑን 15ቱንም ወረዳዎች በማሳተፍ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አካባቢውን ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ለማከናወን መታቀዱን አንስተዋል። በሀይቁ ላይ ከመሰረተ ልማት ግንባታ በተጨማሪ የመጓጓዣ አገልግሎትም እየተሻሻለ መሆኑን የገለፁት ቡድን መሪው፤ የቦኬ፣ ኦዳ ቡልቱምና ሀብሮ ወረዳዎች የሀይቅ ላይ መጓጓዣ ጀልባዎችን ገዝተው ወደ አገልግሎት ማስገባታቸውን አስረድተዋል። በዞኑ ከሶስት ዓመታት ወዲህ የተመሰረቱት ሁለት ፓርኮችን ጨምሮ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ ጥንታዊ ቤተ እምነቶችም ለቱሪዝም መስህብነት ትልቅ አቅም መሆናቸውን ተናግረዋል። ከእነዚህ የቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል የኡላ ቁኒ መስጊድና የአሰቦት ገዳም ዋነኞቹ መሆናቸውንና በስፋት ለማስተዋወቅ፣ ለጎብኚዎች ተደራሽ ለማድረግና የቱሪዝም ሀብትነታቸውን ለማጎልበት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። የቦኬ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ዘይን ጀማል እንዳሉት፣ የወረዳው አስተዳደር በተጠናቀቀው ዓመት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የጨርጨር ሐይቅ አካባቢን ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ የመንገድ መሰረተ ልማት የማሻሻል ስራ አከናውኗል። ሀይቁ ለበርካታ ዓመታት ደርቆ በአረንጓዴ አሻራ ስራ ዳግም ነፍስ የዘራ በመሆኑ በአካባቢው የተፈጥሮ ጥበቃ ስራውን በማጠናከር እንክብካቤ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ እየተመዘገበ የሚገኘው ተጨባጭ ለውጥ ቀጣይነት እንዲኖረው የምክር ቤት አባላት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል
Oct 4, 2026 49
ሐረር ፤ መስከረም 24/2019 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል እየተመዘገበ የሚገኘው ተጨባጭ ለውጥ ዘላቂነት እንዲኖረው የምክር ቤት አባላት የሚያደርጉትን የክትትልና ድጋፍ ስራቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 7ኛ ዙር 1ኛ ዓመት መስራች ጉባዔው የምክር ቤቱን አፈ ጉባዔና ምክትል አፈ-ጉባኤዎችን እንዲሁም የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ሾሟል። እንዲሁም ምክር ቤቱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የቀረበውን የክልሉን መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሹመት አፅድቋል። ይህን በማስመልከት አስተያየታቸውን የሰጡት የከተማው ነዋሪዎች የምክር ቤት አባላቱ በክልሉ እየተመዘገበ የሚገኘውን የለውጥ ስራዎች ለማስቀጠል የሚያስችሉ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ወጣት ደረጀ መስፍን እንዳለው በአገሪቷም ሆነ በክልሉ ከተማና ገጠር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተጨባጭ የለውጥ ስራዎች ተግባራዊ ተደርገዋል። መንግስትና ህዝብ በጋራ በመሆን የነዋሪውን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ገልጾ፤ የምክር ቤቱ አባላትም በልማቱ ቀጣይነት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ነው የተናገረው። አቶ ፈጠነ በጅጋ የተባሉ የከተማው ነዋሪ በበኩላቸው በምክር ቤቱ ምስረታ ላይ አዳዲስና ልምድ ያላቸው አመራሮች ወደ አመራርነት መምጣታቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም በክልሉ የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል ትልቅ ሃላፊነት መሆኑን ጠቁመው እንደ ህዝብም የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የለውጥ ስራዎች ሐረርን ውብና ማራኪ በማድረግ ቱሪስቶች እንዲበራከቱ ማስቻሉት የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ቲማጅ ጃሚ ናቸው። በክልሉ የተጀመሩ ስራዎችን የምክር ቤቱ አባላትና አመራሩ በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። አቶ አማረ አበበ የተባሉ የከተማው ነዋሪ በበኩላቸው መንግስት ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረገ እና ክልሉን የለወጡ በርካታ የልማት ስራዎች አከናውኗል ብለዋል፡፡ በቀጣይም የክልሉ መንግስት ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ በርካታ ስራዎችን እንደሚያከናውን ተስፋ እንደሚያደርጉ ጠቁመው ህዝቡም ይህን መደገፍ እንደሚገባው ተናግረዋል።
በተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከ69 በመቶ በላይ አድጓል
Oct 3, 2026 324
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች የማምረት አቅማቸው ከ69 በመቶ በላይ ማደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ ገለጹ። ኢትዮጵያን የአፍሪካ የአምራች ኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ዘርፉን በተኪ ምርት፣ በምርታማነት፣ በጥራትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ በመሰነቅ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተጋች ትገኛለች። በዚህም ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ በተደረጉ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ዘርፉን በማነቃቃት በርካታ ውጤቶች ተገኝተዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄና የብሔራዊ አምራች ካውንስል የኢንዱስትሪዎችን ማነቆዎች በመፍታት የአምራች ዘርፉን ተግባራዊ አቅም እያሳደጉ ይገኛሉ። በተለይም ከዚህ በፊት ተዘግተው የነበሩ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ ለመመለስ የኤሌክትሪክ፣ የውሃ፣ የካፒታልና የግብዓት እጥረት ጨምሮ የተለያዩ ችግሮች እየተፈቱ መሆኑን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ካሉ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑንም አመልክተዋል። ባለፈው ዓመት ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 5 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ገልጸው፣በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በምግብና መጠጥ፣ በብረታ ብረትና በቆዳ ዘርፎች የተኪ ምርት እየተስፋፋ መምጣቱን ጠቁመዋል። የተኪ ምርት መስፋፋት የውጭ ምንዛሬ ወጪን ከመቀነስ ባለፈ የንግድ ሚዛንን ለማሻሻል፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና የአምራች ዘርፉን በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ እንደሚያግዝ ገልጸዋል። በዚህም የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች የማምረት አቅማቸው ወደ 69 ነጥብ 2 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል። የኢንዱስትሪ ዘርፉ የምርት ጥራትንና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የዋጋ ጨማሪን ማስፋፋት፣ ከግብርና ጋር ያለውን የኋልዮሽና የፊት ለፊት ትስስር ማጠናከር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የአምራች ማዕከል በመሆን የአፍሪካ ሀገራትን በአምራች ዘርፍ ለማሰልጠንና የካይዘን ፍልስፍናን በአህጉሩ ለማስፋፋት እየሰራች መሆኗንም ገልጸዋል። የኢንዱስትሪ ዘርፉ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ ኢንቨስትመንትንና የወጪ ንግድን በማሳደግ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ እንዲያሳድግ በቀጣይ የተለያዩ ዕቅዶች መያዛቸውን ገልጸዋል። በዚህ መሠረት በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት ዕቅድ የኢንዱስትሪ ዘርፉን የወጪ ንግድ 9 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን ወደ 5 ሚሊዮን ለማሳደግና የዘርፉን በኢኮኖሚው ያለውን ድርሻ 17 ነጥብ 2 በመቶ ለማድረስ ዕቅድ መያዙን አስታውቀዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከኢንዱስትሪው በፊት የነበሩ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ጨምሮ ማነቆዎችን ለመፍታት ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል። በተለይም የመለዋወጫ ዕቃዎችን፣ ማሽኖችንና ቴክኖሎጂዎችን ከውጭ ለማስመጣት የነበሩ የውጭ ምንዛሬ ችግሮች መቀነሳቸውን ጠቅሰው፣ የተሻሻሉ ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችም ለአምራች ዘርፉ ምቹ ሁኔታ እየፈጠሩ መሆኑን አስረድተዋል። የአምራች ዘርፉ የውጭ ገበያን በመያዝ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘትም አቅሙን እያሳደገ መምጣቱን ጠቅሰዋል። የኢንዱስትሪ ልማት የአንድ ተቋም ብቻ ሥራ ባለመሆኑ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና የተለያዩ የፌዴራል ተቋማት በቅንጅት መሥራታቸውን ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል።
የሁለት ግድቦች ወግ
Oct 3, 2026 395
ሕዳሴ የቀጣናው የምስራች፤ አስዋን የበደልና ጥፋት ምንጭ ዓባይ ከኢትዮጵያ ተራሮች ፈልቆ፤ አለት ሰንጥቆ፤ ሸለቆዎችን ተሻግሮ ወደ ምስር ይፈስሳል። ማኅፀኑ ኢትዮጵያ ብትሆንም፣ ጠብታ አብርክቶ ለማታውቀው ግብፅ የሕይወት ምንጭ ሆኖ ኖሯል።ዓባይ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ነው፤ የግብፅን ሐሩር ያረሰረሰ፣ የቀጣናውን የኢነርጂና የኢኮኖሚ ልማት ዕድል የተሸከመ ወንዝ ነው። አሁን ላይ በዓባይ ወንዝ ላይ ኢትዮጵያም ግብፅም እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ግዙፍ ግድቦች አሏቸው፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድን እና አስዋን ግድብ።ሁለቱ ግድቦች ግድብነታቸው ሊያመሳስላቸው ቢችልም፣ ታሪካቸው፣ ተፅዕኖአቸውና ለትውልድ የሚያስተላልፉት መልዕክት ግን ለየቅል ነው። በዚህ ወንዝ ላይ ለዓመታት በአልጠግብ ባይነት የተበየነው የግብፅ የውሃ ፖሊሲ፣ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት የልማት ፍላጎትን በተደጋጋሚ የሚገድብ አካሄድን ይዞ ቆይቷል። በዚህም መነሻ ያለምንም ማማከርና ያለ ቴክኒካል ውይይት ዓባይን ብቻችንን መቆጣጠር አለብን በሚል እብሪት አስዋን ተገንብቷል። የአስዋን ግድብ ሥር እንባዎች አስዋን የግብፅን ታሪክ በእጅጉ የቀየረ፣ የበረሃዋን ምድር በመስኖ ያለመለመ፣ የኃይል ምርቷን እንድታሳድግ ያስቻለ ግዙፍ መሠረተ ልማት ነው። ነገር ግን ከዚህ የልማት ገጽታ ጀርባ ብዙ ዋጋ የተከፈለባቸው የሕይወት ዋጋዎች፣ የተሰደደ ማኅበረሰብና በውሃ ስር የተቀበሩ ታሪካዊ ርስቶች አሉ። ይህ በአስዋን ግንብ ስር በእንባ የተጻፈ የበደል ታሪክ ነው።አስዋን ሲገነባ የኑቢያ ምድር በሰፊው የናስር ሐይቅ ተጥለቅልቋል። ወደ 100 ሺህ የሚደርሱ ኑቢያውያን ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ኑሯቸው ተናግቷል። ያላቸውን ጥሪት አጥተዋል። ለብዙ ሺህ ዓመታት በትውልድ ተሻግሮ የመጣው ርስታቸውና የኑሮ መሠረታቸው በናስር ሐይቅ ምክንያት ወድሟል። የኑቢያ ጥንታዊ ቅርሶችም በሐይቁ ስር የመቀበር አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ብዙ ቅርሶች በውሃ ስር ቀርተዋል፤ ሌሎች ደግሞ በዓለም አቀፍ የቅርስ ጥበቃ ዘመቻ ከነበሩበት ተነቅለው ወደ ሌላ ቦታ ተዛውረዋል።የአስዋን ሐይቅ በሰው ልጅና በውሃ ሀብት ላይ ያሳረፈው ጫና በዚህም አያበቃም። በበረሃማው ስፍራ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ሐይቅ በየዓመቱ እስከ 16 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ በትነት እንዲጠፋ በማድረግ ውሃ ያለ አግባብ እንዲባክን ያደርጋል። 16 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ ማለት ደግሞ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከሚይዘው 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ አንጻር ስንመለከተው፤ አስዋን ግድብ በየ አራት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ የሕዳሴ ግድብ የያዘውን ሙሉ ውሃ በትነት ያባክናል እንደ ማለት ነው። ይህ በሰው ልጅ ይውሃ ፍጆታ አንጻር ደግሞ አስዋን ድግብ ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለአንድ ዓመት ሙሉ መጠቀም የሚችለውን የቤት ውስጥ የውሃ ፍላጎት በትነት እያባከነ ቀጥሏል። አስዋን ግድብ የያዘው የናስር ሃይቅ በጣም ሰፊ እና ጥልቀቱ አነስተኛ (Shallow and Wide) በመሆኑ ለፀሐይ ብርሃን የሚጋለጠው አካል ሰፊ ነው። ይህ ደግሞ የትነት መጠኑ በእጅጉ እንዲጨምር አድርጓል።ይህ በትነት የሚጠፋው የውሃ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት በውሃ አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ ሁልጊዜም በግብፅ ስሁት አካሄድና ደካማ የውሃ አስተዳደር ላይ የሚነሳ አጀንዳ ሆኗል። ከዚህም በባሰ ግብፅ የላይኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት እንድም ልማት እንዳያለሙ በሴራ በማቀብ እርሷ ግን በአስዋን ግድብ ላይ የተመሠረተውን የናስር ሐይቅ ውሃ ከፍተኛ የውሃ ፍጆታ በሚጠይቁ የሸንኮራ አገዳ፣ የጥጥና የሩዝ ልማቶች በማዋል ለብዙ ዓመታት በደል ስትፈጽም ኖራለች። ይህም የአሰዋን ግድብ የበደል ታሪክ ነው። አስዋን የዓባይን ውሃ በብቸኝነት የመጠቀም ፍላጎትን፣ የውሃ ሀብትን በአንድ ወገን ላይ በማስቀመጥ የሌሎችን የልማት መብት የሚገድብ አስተሳሰብን የሚወክል ታሪካዊ ምልክት ሆኖ ቆይቷል። ዛሬ ግን ይህ ትርክት ተለውጧል። ሕዳሴ ቀልብሶታል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ -የቀጣናው የምስራች በዓባይ ወንዝ ላይ አዲስ ምዕራፍ ተጽፏል።ሕዳሴ የተኛን ኃይል አንቅቷል። የተዘነጋን ሀብት ወደ ልማት ቀይሯል። የትናንትን ጥገኝነት ወደ የራስ አቅም አሸጋግሯል። ለዘመናት በኢትዮጵያውያን ደጅ ወርቁን፣ አፈሩን፣ ግንዱንና ሌላውንም እያግበሰበሰ ሲጓዝ የኖረውን፣ ኢትዮጵያውያን ከኩበት ጭስ ጋር እየታገሉ፣ በጨለማ ስር ተቀምጠው በቁጭት ሲያዜሙለት የኖሩትን ዓባይን፣ ሕዳሴ ወደ ብርሃን ምንጭነት አዙሮታል። ታላቁ የሕዳሴ ግድብ 5 ሺህ 150 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫል። በንጋት ሐይቅ ወደ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያከማቻል። ይህም የኢትዮጵያን ከውሃ ኃይል የሚመነጭ የኢነርጂ አቅምን በእጅጉ የሚያሳድግ፣ የኢኮኖሚ ልማቷን የሚደግፍ ትልቅ መሠረተ ልማት ነው። የሕዳሴ የምስራችነት በዚህ አያበቃም። የሕዳሴ ግድብ የቀጣናው የኢነርጂና የልማት ምንጭ ነው። ለሱዳን፣ ለጅቡቲ፣ ለኬንያ፣ ኃይል ማስተላለፍ ጀምሯል። ለሌሎችም ለመድረስ ጥናት በመካሄድ ላይ ይገኛል። የግድቡ መገንባት የጠቀመው እንጂ የጎዳው አካል የለም። የሱዳንን የጎርፍ አደጋ በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚና አለው። ለሱዳንም ሆነ ለግብፅ ከደለል ንጹህ የሆነ፣ ዓመታዊ ፍሰቱ የተስተካከለ ውሃ እንዲያገኙ ያስችላል። የሕዳሴ ግድብ የሚገኝበት አካባቢ የአየር ሁኔታና ጂኦግራፊ እንደ እቶን በሚንተከተከው በረሃ ከተገነባውና ውሃን ያለቅጥ ከሚያተነው የአስዋን ግድብ አንጻር እጅግ ቀዝቃዛና ለውሃ ብክነትና ትነት ተጋላጭ ያልሆነ የውሃ ማከማቻ ነው። የንጋት ሐይቅም ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ የውሃው የላይኛው ክፍል እጅግ ያነሰ የፀሐይ ተጋላጭነት አለው። ይህም ትነትን በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን፤ ለዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ከ10 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ በላይ ውሃ በትነት እንዳይባክን ታድጓል። ይህ ውሃ በደረቅ ወቅት፣ የበረሃ ቅንጦተኞቹን፣ የአዞ እንባ አፍሳሾችን እነግብፅንም ጭምር የሚያረሰርስ ነው።ሕዳሴ ዓባይን የፍትሐዊና የዘላቂ ልማት ምንጭ፣ የተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ዕድገት ምሰሶ እንዲሆን አዲስ መንገድ ከፍቷል።የሁለቱ ግድቦች ወግም ይኸው ነው። አስዋን ግድብ በሐይቅ ስር የኑቢያን ምድር ሲሰለቅጥ፤ የሚሊዮኖችን እርዛት የሚያስቀረውን ውሃ ሲያተን፣ ሌላው ግን በጨለማ የተዋጠውን በልማት ወደ ኋላ የቀረውን ቀጣና ከተኛበት ቀሰቀሰ፣ ብርሃኑን አዳረሰ። የልማት ተስፋ ሆነ። ይኸው ነው!
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል
Oct 3, 2026 122
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮ-ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ። የአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ዜጎች ተገቢው የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው በማድረግ ስራ እና ሀብትን በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማጠናከር ተግባራዊ የተደረገ ፕሮግራም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ5 ሚሊየን የኮደርስ መርሐ ግብር ወደ 7 ሚሊየን ከፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ስዩም መንገሻ እንደገለጹት፤ በዲጂታል ኢትዮጵያ የስኬት ጉዞ በዋናነት ትልቁ የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ማጎልበት ነው። የኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሲጀመር አምስት ሚሊዮን ዜጎችን ስልጠና እንዲወስዱ መታቀዱን አንስተው፤ ከታቀደው በላይ ለማሳካት በመቻሉ ሰባት ሚሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ ዜጎች ቁጥር 5 ነጥብ 4 ሚሊየን መድረሱን ገልጸው፤ በዚህም ክህሎታቸውን ማሳደግና በኦን ላይን የስራ እድል ተጠቃሚነታቸውን ማጎልበታቸውን ተናግረዋል። የኮደርስ ስልጠናው መሰረታዊ ነው፤ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ መንደርደሪያ፣ መስፈንጠሪያ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድጉ ተግባራትን እያከናወነች መሆን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች ዲጂታላይዜሽን በማስፋፋት ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎቶች ተጨባጭ ለውጦች መገኘታቸውንም ገልጸዋል። የዲጂታል ክህሎት ሀገርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ግብዓት በመሆኑ በዘርፉ ላይ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ነው የገለጹት። የኢትዮ ኮደርስ ዜጎች የዲጂታል ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸው፤ በቀጣይም እንደዚሀ አይነት ስልጠናዎች በላቀ ደረጃ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስታርትአፕ ዴቨሎፕመንት ኤክስፐርት አብይ ታደሰ በበኩሉ በኢትዮ ኮደርስና በሌሎች ኢኒሼቲቮች ስታርት አፖችን መደገፍ የሚችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። የኮደርስ ስልጠና መሰረታዊ ክህሎትን ለማስጨበጥና የስራ ፈጠራዎችን ለማስፋፋት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በኤ. ይ ዘርፍ የወጣቶችን ክህሎት የሚያዳብሩ ወደ ስታርት አፕ እንዲገቡ የሚያስችሉ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ነው የገለጸው። ወጣቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ክህሎታቸውን ማሳደጋቸው ለስራ ፈጠራና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልጿል። በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይበር ሴኪዩሪቲ ኦዲተር ማርታ ሀዲስ አራቱንም ኮርሶች መውሰዳቸውንና በዘርፉ የነበራቸውን እውቀት ለማዳበር እንደጠቀማቸው ገልጸዋል። ኢኒሼቲቩ ለወጣቶች በጣም ትልቅ እድል ነው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን፣ ክህሎትን ለማሳደግ ከወቅቱ ጋር ለመራመድ መሰረታዊ ስልጠና ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በሰው ሰራሽ የታገዙ ስራዎች እየተስፋፉ መምጣታቸውን ገልጸው፤ ኮርሶቹ ለቀጣይ የስራ እድሎችና ሙያን ለማሳደግ መሰረት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የዲዲጂታል እመርታን የሚያሳልጥ የሰው ሃይል እያፈራ ነው
Oct 1, 2026 274
አዲስ አበባ፣መስከረም 21/2019(ኢዜአ)፡-የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የዲጂታል እመርታን የሚያሳልጥ የሰው ሃይል እያፈራ መሆኑን የትምህርት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር መሳይ ኃይለማሪያም ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ባላት ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ በሁሉም መስክ የሀገርን ማንሰራራት የሚያበስር እመርታዊ ውጤት እያስገኘ ነው። የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የ50 ዓመታት የምርምር፣ ኢኖቬሽን፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ኢንተርፕርነርሽፕ ጉዞን እና ቀጣይ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል። ለሦስት ቀናት በተካሄደው ጉባኤ ማጠናቀቂያም የኢትዮጵያ ተሰጥኦ እና ተውህቦ ማበልፀጊያ ኢንስቲትዩት የቡራዩ ተሰጥኦ ልማት ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸው ባለልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎችን አስመርቋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ዋና ዳይሬክተር መሳይ ኃይለማሪያም ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለልዩ ተሰጥኦ ወጣቶችን በማሰልጠን የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የሚያስችል የሰው ኃይል እያፈራ ነው። በትምህርት ቤቱ ሥልጠና የሚሰጣቸው ባለልዩ ተሰጥኦ ወጣቶችም ከፍተኛ የማሰብ፣ የማገናዘብና የመተንተን አቅማቸውን ታሳቢ ባደረጉ መስፈርቶች ተመልምለው የሚሰለጥኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም ታዳጊዎች የፈጠራ ክህሎትና ልዩ ተሰጧቸውን በማበልጸግ ችግር ፈቺ የመፍትሔ ውጤቶችን የሚያፈልቁበት ወሳኝ ዕድል እንዲፈጠርላቸው እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ተመራቂዎችም በትምህርት ቤቱ ቆይታቸው ንድፈ ሃሳብን ከተግባር ተኮር ያቀናጀ ዕውቀትና ክህሎት ማግኘታቸውን አስረድተዋል። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የሚመለከታቸው አካላትም ታዳጊዎች ክህሎታቸውን የሚያበለጽጉበትን ዕድል በማመቻቸት ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሥራት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ተመራቂ ተማሪዎቹ በበኩላቸው፤ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ተፈጥሯዊ ተሰጥኦቸውን በተግባር ልምምድ የታገዘ ሥልጠና የሚያገኙበትን የዕውቀትና ክህሎት ማበልፀጊያ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ማክዳ ወርቅሸት፤ ትምህርት ቤቱ ልዩ ተሰጥኦቸውን የሚያበለጽጉበትን ወሳኝ ትምህርትና ሥልጠና ዕድል ሰጥቶናል ብላለች። የሥልጠና ቆይታቸውም የልዩ ተሰጥኦ ዕውቀትና ክህሎታቸውን በማበልጸግ ከዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነትን እንደሚያጎለብትላቸው ገልጻለች። የኢትዮጵያ ዲጂታል ልማት የቴክኖሎጂ ልዩ ተሰጧቸውን የምናጎለብትበትን ወሳኝ ዕድል ፈጥሮልናል ያለው ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት በተሻለ አበበ ነው። በአሁኑ ወቅት የክረምት ሥልጠናዎችና ልዩ ልዩ የፈጠራ ማሳያ መድረኮች በርካታ ዕድሎችን በመፍጠር ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች የሚጠቀሙበትን ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጿል። ወጣቶችም የኢንተርኔት አክሰስንና አዳዲስ ዕድሎችን በመጠቀም የራስን ጥረት ማዕከል በማድረግ አዳዲስ ሶፍትዌሮችን በማልማት ዕድሉን መጠቀም እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፏል።
በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችል ነው
Oct 1, 2026 196
ሸገር ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችልና ለትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን የኦሮሚያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ። የኦሮሚያ ዲያስፖራ አባላቱ ለኢሬቻ በዓል አከባበር ወደ ሀገር ቤት የመጡ ሲሆን፣ በሸገር ከተማ በሚገኘው የሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው። የዲያስፖራ አባላቱ በኢንስቲትዩቱ በተከናወኑ የዲጂታል ልማት ስራዎቹ መደመማቸውንም ገልጸዋል። ከአሜሪካ የመጡት ዶክተር ተመስገን ሻሾ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተመለከቱት ስራ ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችልና ለተተኪው ትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው። "ዓለም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እየተደገፈች ያለችበት ወቅት በመሆኑ፣ ሀገራችን ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች ከውጭ ይገቡ የነበሩ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የጀመረችው እንቅስቃሴ እጅግ የሚበረታታ ነው" ብለዋል። በተለይም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እንዲደገፉና ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ የተሰራውን ስራ ያደነቁት ዶክተር ተመስገን፤ አሁን የተጀመሩት ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ በተሻለ የልማት ጉዞ ላይ መሆኗን የገለጹት ዶክተር ተመስገን፤ በተለይም የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በሀገራቸው መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ የልማቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ከደቡብ አፍሪካ የመጡት አቶ ኡመር ኡስማን በበኩላቸው፤ በኢንስቲትዩቱ ባዩት ስራ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው፣ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚከናወኑት ተግባራት ትውልዱ በሀገሩ ሰርቶ እንዲለወጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስረድተዋል። በኦሮሚያ ክልል በቴክኖሎጂው ዘርፍ እየተከናወነ ያለው ስራ ሀገራችን በቴክኖሎጂ አስተማማኝ አቅጣጫ ላይ መሆኗን የሚያመላክት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። ሀገሪቱ በአስተማማኝ የዕድገት መስመር ላይ የምትገኝ መሆኗን በመጠቆም፣ ዲያስፖራው በሀገሩ መዋዕለ ንዋዩን በማፍሰስ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። በተመሳሳይ ከኖርዌይ የመጡት ወይዘሮ ሌንሴ ለሜሳ፤ በኢንስቲትዩቱ ለተማሪዎች እየተሰጠ ያለው ትምህርት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ወጣቶች በሀገራቸው ጥራት ያለው ትምህርት አግኝተው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን እውቀት እንዲጨብጡ የሚያስችል ነው ብለዋል። የኦሮሚያ ዲያስፖራ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዲማ እንዳሉት፤ ጉብኝቱ በየዓመቱ በኢሬቻ ሳምንት በክልሉ የሚገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመጎብኘት ባህል አካል ነው። አክለውም በኢንስቲትዩቱ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰልጥነው ለነገዋ ሀገር ተስፋ የሚሆኑበትን አሰራር መመልከታቸው ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። የኦሮሚያ ዲያስፖራ ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ አሚን ጁንዲ በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሞላው መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ እስካሁን በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ከ200 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። ይህም ከፍተኛ የዕውቀት ብቃት (IQ) ያላቸውን ተማሪዎች በማፍራት ሀገራቸውን ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ ስራ መሆኑን ያብራሩት አቶ አሚን፤ የጉብኝቱ ዋና ዓላማም በሀገራችን እየመጣ ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ በተግባር በማሳየት አባላቱ ሀገራቸውን በዕውቀትም ሆነ በኢንቨስትመንት ለመደገፍ እንዲዘጋጁ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
በዲጂታል ዘመን የግለሰብ መረጃ እና የዜጎችን እምነት ለመጠበቅ ዳታን በአግባቡ መንከባከብ ወሳኝነት አለው
Sep 30, 2026 164
አዲስ አበባ ፤መስከረም 20/2019 (ኢዜአ) ፦ በዲጂታል ዘመን የግለሰብ መረጃ እና የዜጎችን እምነት ለመጠበቅ ዳታን በአግባቡ መንከባከብ ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ገለጸ። ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ጋር በመተባበር በግል ዳታ ጥበቃ ዙሪያ ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሚሊዮን ኃይለሚካኤል በዲጂታል ዘመን የግላዊነትንና የዜጎችን እምነት ለመጠበቅ ዳታን መንከባከብ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። እንዲሁም የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 1321/2016 መረጃን በኃላፊነትና በግልጽነት ለማስተዳደር ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ መዘርጋቱን ገልጸዋል። ጠበቆችም የደንበኞቻቸውን መረጃ በሥራቸው የሚይዙ በመሆናቸው በዘርፉ ትልቅ ባለድርሻ አካል መሆናቸውን አስረድተዋል። አቶ ሚሊዮን አያይዘውም የተገኘው ግንዛቤ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ወደ ተግባር ሊለወጥ እንደሚገባ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ደረሰ በበኩላቸው ጠበቆች የደንበኞቻቸውን ምስጢራዊ መረጃ በሕጉ መሠረት መጠበቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ጠበቆች ሕጉን ከማክበር ባለፈ ደንበኞቻቸው የግል ዳታ ጥበቃ ሕጉን እንዲያከብሩ የሙያ ማማከር ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ስፖርት
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሲሸልስን በድጋሚ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ
Oct 3, 2026 175
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ባደረገው ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ሲሸልስን 10 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳግማዊ ሰለሞን ሁለት በጨዋታ እና አንድ በፍጹም ቅጣት ምት በአጠቃላይ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች። እሙሽ ዳንኤል ሁለት ጎሎችን ከመረብ ላይ ስታገናኝ ቱሪስት ለማ፣ ቤተልሄም መንተሎ፣ ቤተልሄም በቀለ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ እና የሲሸልሷ አሻንታ ማሪ በራሷ ላይ ቀሪዎቹን ጎሎች ለሉሲዎቹ አስቆጥረዋል። ሀገራቱ ከቀናት በፊት ባደረጉት የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ 16 ለ 0 ማሸነፏ የሚታወስ ነው። በቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በሁለቱ ጨዋታዎች 26 ጎሎችን በማስቆጠር የበላይነቱን አሳይቷል። ብሔራዊ ቡድኑ በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅት ላይ ይገኛል። የወዳጅነት ጨዋታዎቹም የዚህ ዝግጅት አካል ናቸው። ኢትዮጵያ የሁለተኛ ዙር የ2026 የሎጅ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ጨዋታዎቿን ከሩዋንዳ ጋር መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል
Oct 3, 2026 136
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታውን ዛሬ ያከናውናል። ጨዋታው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል። በአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን እ.አ.አ በ2028 በሎስ አንጀለስ በሚካሄደው 34ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ከመስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዝግጅቱን እያደረገ ነው። ቡድኑ የዚሁ ዝግጅት አካል የሆነ የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ያደረገ ሲሆን 16 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። ሁለቱ ቡድኖች ከጨዋታው በፊት የመጨረሻ ልምምዳቸውን ትናንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አከናውነዋል። ኢትዮጵያ የሁለተኛ ዙር የ2026 የሎጅ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ጨዋታዎቿን ከሩዋንዳ ጋር መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።
2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ ተካሄደ
Oct 1, 2026 215
ቢሾፍቱ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የ2019 የኢሬቻ በዓልን በማስመልከት 10 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው 2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ ተካሂዷል። ኢሬቻ የምስጋና፣ የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል ከመሆኑ በላይ መግባባትን፣ ሰላምንና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እየሆነ መጥቷል። በዓሉ የኦሮሞን ባህልና እሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ ከማስተላለፍ አልፎ፣ በልዩነት ውስጥ መከባበርንና ፍቅርን በማሳደግ የኢትዮጵያ የጋራ ሀብት በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራችንን ለማስተዋወቅ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል። የዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ ዓላማም ኢሬቻ የወንድማማችነት፣ የአንድነትና የይቅርታ መድረክ መሆኑን ለዓለም በማሳወቅ ሳቢነቱን ማሳደግ መሆኑ ተገልጿል። 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለው በዚህ የኢሬቻ የጎዳና ላይ ሩጫ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር አትሌቶች እንዲሁም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል። በዚሁ መሰረት በወንዶች አትሌት ጅራታ ሌሊሳ (ከሸገር) 1ኛ፤ አትሌት ለሚ ተሾመ (ከሸገር) 2ኛ፤ አትሌት አቤል ቼቤት (ከኡጋንዳ) 3ኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፈዋል። እንዲሁም በሴቶች አትሌት ብርነሽ ደሴ (ከፀዳይ ባንክ) 1ኛ በመውጣት የ2019 የ2ኛው የኢሬቻ ታላቅ ሩጫ አሸናፊዎች ሆነዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ቢያ ባደረጉት ንግግር፣ ኢሬቻ ፍቅርንና አንድነትን በማጠናከር ለብሔራዊ መግባባት መሠረት በመጣል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ይህንን በስፖርት በማስደገፍ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ የመግባባት ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ እናሳድጋለን ብለዋል። የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው፤ የኢሬቻ ሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የሀገሪቱን ቱሪዝም እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል። የቢሾፍቱ ከተማም ከምንጊዜውም በላይ ዘንድሮ የኢሬቻ እንግዶችን ለመቀበል በኮሪዶር ልማት አጊጣ እየጠበቀች መሆኑን ተናግረዋል።
2ኛው የኢሬቻ ሩጫ “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ በመካሄድ ላይ ይገኛል
Oct 1, 2026 162
ቢሾፍቱ ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የ2019 የኢሬቻ በዓል ዋዜማን በማስመልከት የተዘጋጀው 2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ “ኢሬቻ፡ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ኢሬቻ የምስጋና፣ የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል ከመሆኑ በላይ፣ የተለያዩ ብሔሮችና ብሔረሰቦችን አንድ ላይ የሚያመጣ እንዲሁም መግባባትን፣ ሰላምንና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እየሆነ መጥቷል። በዓሉ የኦሮሞን ባህልና እሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ ከማስተላለፍ አልፎ፣ በልዩነት ውስጥ መከባበርንና ፍቅርን በማሳደግ የኢትዮጵያ የጋራ ሀብት በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራችንን ለማስተዋወቅ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል። የዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ ዓላማም ኢሬቻ የወንድማማችነት፣ የአንድነትና የይቅርታ መድረክ መሆኑን ለዓለም በማሳወቅ ሳቢነቱን ማሳደግ መሆኑ ተገልጿል። 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለው በዚህ የኢሬቻ የጎዳና ላይ ሩጫ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር አትሌቶች እንዲሁም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
አካባቢ ጥበቃ
አረንጓዴ ዐሻራ ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ሳቢ በማድረግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Oct 3, 2026 128
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የሀገሪቱን የአረንጓዴ ልማት ግቦች ከማሳካት ባለፈ፣ ከተሞችን ለኑሮ ምቹ እና ተስማሚ እያደረገ እንደሚገኝ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የጀመረችው ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ትልቅ አርአያ መሆን ችሏል። በዚህ ግዙፍ ሀገራዊ ተነሳሽነት አማካኝነት ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ 56 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ተችሏል። በመርሃ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች ስነ-ምህዳርን ከማስጠበቅና ከተሞችን አረንጓዴ ከማላበስ ባለፈ ለምግብነት እና ለቱሪስት መዳረሻነት ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል። ይህ ሁሉን አቀፍ ጥረት ሀገሪቱ የተፈጥሮ ጸጋዎቿን ጠብቃ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ብሩህ ጉዞ ጠንካራ እና አዲስ መሰረት ጥሏል። በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናት ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ አማን አሰፋ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በከተሞች የሚካሄዱ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ስራዎች ከተሞች ለኑሮ ምቹ፣ ዘመናዊና ማራኪ አድርጓቸዋል። በከተሞች አካበቢ ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መኖር እና የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆናቸው ለከፍተኛ ካርቦን ልቀትና ብክለት ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። በመሆኑም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ይህንን ችግር በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም የሙቀት መጠንን በመቀነስ፣ የአካባቢ ስነ-ምህዳርን በመጠበቅ እና በከተሞች አካባቢ ጎርፍ እንዳይከሰት በመከላከል ለአየር ንብረት ለውጥ ትልቅ አዎንታዊ ድርሻ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት አዳዲስ የከተማ ፕላን አሠራር ላይ ማሻሻያ ማድረጉንም ተናግረዋል። በዚህም አዲስ የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት፣ 30 በመቶ ለመሠረተ ልማት እና 40 በመቶው ደግሞ ለመኖሪያነት እንዲውሉ የሚያስችል ሞዳሊቲ እንዲከተሉ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። በዚህ መሰረት የሚከናወኑ የከተማ ፕላን ዝግጅቶች የሀገሪቱን አረንጓዴ የልማት ግቦች ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋት ትግበራ ውጤታማነትን እያጎለበተ ነው
Oct 1, 2026 164
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦የጽዱ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋት ትግበራ ውጤታማነትን በማጎልበት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ። የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል። በተለይም የከተሞችን ሁለንተናዊ ጽዳትና ውበት ከማሻሻል ባሻገር ለአካባቢ ጥበቃና ሥነ-ምኅዳር ድኅንነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም የጽዱ ኢትዮጵያ ተነሳሽነት ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ዘመናዊ ምኅዳርን በማጎናጸፍ የኮሪደር፣ የወንዝ ዳርቻና መሰል ውጤታማ የልማት ሥራዎችን የሚያፋጥን አስቻይ ምኅዳር መፍጠሩን ተናግረዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንም የሕብረተሰብ ተሳትፎን በማሳደግ የጽዱ ኢትዮጵያን ግብ የሚያሳካ የአካባቢ ጥበቃ፣ የጽዳትና ውበት ባህልን የሚያጎለብት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ እያካሄደ መሆኑን አመልክተዋል። በዚህም በመጀመሪያው ዙር "ውበት ይንቃ፤ ብክለት ይብቃ" በሚል መሪ ሀሳብ ለስድስት ወራት የብክለት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መከናወኑን አስታውሰዋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ "ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድርግ" በሚል መሪ ሀሳብ የጽዳት ባህልን ማጠናከር የሚያስችል መሰረት መጣል እንደተቻለ አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ከሰኔ እስከ መስከረም ለ3 ወራት የሚቆይ 3ኛ ዙር ''የጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ'' ሀገር አቀፍ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል። በየዓመቱ የሚካሄዱት የጽዱ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄም የማኅበረሰቡን የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ በማጎልበት ተቋማት በብክለት መከላከል ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ እያደረገ ነው ብለዋል። መርሐ ግብሩም የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋትና መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ በውጤታማነት በማስፈጸም ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል። የተገኘውን ውጤት ይበልጥ ለማጠናከር በቀጣይም ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃን ለማረጋገጥና ብክለትን ለመከላከል የተቀናጁ የአካባቢ የጽዳትና ውበት ጥበቃ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የኤልኒኖ ክስተት ተጽዕኖዎችን ለመከላከል መዘጋጀት ይገባል
Sep 29, 2026 224
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ ክስተት የሚያመጣቸውን መልካም እድሎች ለመጠቀምና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ። የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የኤልኒኖ ክስተት ከጥቅምት ወር ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ እየጠnነከረ ይሄዳል። ኤልኒኖ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ አካባቢዎች እንዲሁም በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ የደቡብ አጋማሽ የሀገራችን ክፍሎች ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን እና ስርጭት እንዲኖር አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል። ከጥቅምት ጀምሮ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት በተለይም ለሱማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፣ ለጉጂ፣ ለቦረና፣ ለሲዳማ እና ለደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ይህም ዝናብ ከወዲሁ የመስኖ ስራዎችንና የተለያዩ የግብርና እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን፣ እንዲሁም ለአርብቶ አደሩና ለከፊል አርብቶ አደሩ የእንስሳት መኖ አቅርቦትን በማሻሻል በእንስሳት ምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የምዕራብ ህንድ ውቅያኖስም በከፍተኛ ሁኔታ እየሞቀ ይገኛል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የኤልኒኖ ክስተት እና የህንድ ውቅያኖስ ሙቀት መጨመር በአንድ ጊዜ በሚጣመሩበት ወቅት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል። በዚህም መሰረት ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ አማራ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የመፈጠር እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከመደበኛ በላይ በሚኖረውና ተደጋጋሚነት ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በዋቢ ሸበሌ እና በገናሌ ዳዋ ተፋሰሶች አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ የመከሰት እድሉ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ ይህም በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ስለሚችል ከወዲሁ በዋቢ ሸበሌ፣ በኦጋዴን እና በገናሌ ዳዋ አካባቢዎች የተቀናጀ የወንዝ አመራር ስርዓትን መተግበር አስፈላጊ መሆኑ ገልጸዋል፡፡ በዘንድሮው የበጋ ወቅት ከመደበኛ በላይ የሚኖረው የዝናብ መጠን ያለው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሊከሰቱ የሚችሉ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል ለማህበረሰቡ ተደጋጋሚነት ያለው የግንዛቤ መፍጠሪያ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቀጣናው የታዳሽ ኃይል ማዕከል
Sep 27, 2026 460
ኢትዮጵያ በውሃ፣ በንፋስ፣ በፀሐይ እና በጂኦተርማል ሀብቶቿ ለታዳሽ ኃይል ልማት እጅግ ግዙፍ አቅም ያላት ሀገር ስትሆን፤ የመደመር መንግስት ይህንን የተፈጥሮ ጸጋ በብቃት በመጠቀም የኢትዮጵያን የኢነርጂ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ታላላቅ ሥራዎችን አከናውኗል። በዚህ ረገድ የመደመር መንግስት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከማጠናቀቅ ባሻገር ሌሎች የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በማልማት ረገድ ያከናወነው ስራ ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማቷን ከራሷ አልፎ ለጎረቤት አገራት በማዳረስ ቀጣናውን በኢነርጂ የማስተሳሰር ስትራቴጂካዊ ሚናዋን በተግባር እያሳየች ትገኛለች። እንደ ሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኬንያ ላሉ አገራት የሚደረገው የኤሌክትሪክ ሃይል ንግድ የምስራቅ አፍሪካን አገራት በኢነርጂ በማስተሳሰር በጋራ ማደግ እንደሚገባ ያሳየ ነው።ይህ የሃይል ትብብር የአፍሪካን አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና እውን ለማድረግ እና በቀጣናው የኃይል ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሰረት ሆኖ ቀጥሏል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ
Sep 21, 2026 883
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 1011
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው። በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 905
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 1089
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
የወጣቱ የዲጂታል ክህሎትና የኢትዮጵያ ነገ
Oct 1, 2026 179
በዜናው ፈንቴ!! ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይን ሰንቃ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመትጋት ላይ ትገኛለች። በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በፈጣን የቴክኖሎጂ ምጥቀት በመመራት ላይ ትገኛለች። የካፒታልና የጉልበት ብዛት ብቻቸውን የአንድን ሀገር የበላይነት የሚያረጋግጡበት ዘመን አክትሞ የዲጂታል እውቀትና ፈጠራ የኢኮኖሚ ጥንካሬ ዋና መስፈርት ወደመሆን ተሸጋግሯል። የፋይናንስ ሥርዓቱ፣ የንግድ ክፍለ-ኢኮኖሚው፣ የትምህርትና ሕክምና አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በዲጂታል መሠረተ-ልማት ላይ የተደገፉ ሆነዋል። በዚህ እጅግ ተወዳዳሪ በሆነው የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ተመዝኖ ለመገኘትና ውድድሩን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ የቴክኖሎጂ እውቀትን መታጠቅ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የቴክኖሎጂ እውቀት ወጣቶችን በግል፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ዘርፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ በርካታ መሠረታዊ ጥቅሞች አሉት። የወረቀት ገንዘብና ባህላዊ የገበያ መስተጋብር በዲጂታል ክፍያዎች እና በኢ-ኮመርስ እየተተኩ ነው። የቴክኖሎጂ እውቀት ያለው ወጣት በቀላሉ ዓለም አቀፍ የንግድ እድሎችን የመጠቀምና የፋይናንስ አካታችነት ተጠቃሚ የመሆን አቅም ይኖረዋል። ባህላዊ የሥራ አማራጮች እየጠበቡ ባሉበት በዚህ ዘመን፣ የቴክኖሎጂ እውቀት የታጠቀ ወጣት በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአለበት ሆኖ በዓለም አቀፍ ገበያ ሥራ በመቀጠርና የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ረገድ ከፍተኛ እድል አለው። በተጨማሪም ቴክኖሎጂ ወጣቶች በትንሽ ካፒታል ትላልቅ የፈጠራ ሀሳቦችን ወደ ስታርታፕ ቢዝነሶች እንዲቀይሩ ያስችላቸዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በዳታ ሳይንስ የታገዙ መፍትሔዎች የማህበረሰቡን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት ይችላሉ። መረጃን በስርዓት የመተንተን፣ ውስብስብ ችግሮችን በጥበብ የመፍታትና ምክንያታዊ ውሳኔዎችን የመስጠት አቅምን ማሳደጉም ሌላው የቴክኖሎጂ እውቀት ጥቅም ነው። በተለይም በአሁኑ ወቅት የሀገራችን የፋይናንስ ሥርዓት በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ዲጂታል አሠራር እየተሸጋገረ ይገኛል። የባንክ አገልግሎቶች፣ የገንዘብ ዝውውሮች፣ የንግድ ክፍያዎችና የዕለት ተዕለት መስተጋብሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በሞባይል ባንኪንግ፣ በቴሌብር፣ በኢ-ብር እና በሌሎች የዲጂታል ክፍያ አማራጮች የታገዙ ሆነዋል። ይህ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራር አገልግሎትን ፈጣንና ቀልጣፋ ከማድረጉ ባሻገር፣ ከዚህ ቀደም የባንክ አገልግሎት ያላገኙ ሰፊ የማህበረሰብ ክፍሎችን በፋይናንስ ሥርዓቱ ውስጥ በማካተት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ነገር ግን የዚህን ዘመናዊ አሠራር ፍሬ ሙሉ በሙሉ ለማጨድና የፋይናንስ አካታችነትን እውን ለማድረግ የዲጂታል ፋይናንስ እውቀት ከመቸውም ጊዜ በላይ ወሳኝ ሆኗል። ባህላዊው የባንክ አሠራር በአካል ወደ ቅርንጫፍ በመሄድና በባንክ ሠራተኞች ቀጥተኛ ድጋፍ የሚከናወን እንደመሆኑ፣ የቴክኖሎጂ እውቀት ማነስ ከፍተኛ ችግር አይፈጥርም ነበር። የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ግን ሙሉ በሙሉ በምስጢራዊነትና በግል ኃላፊነት ላይ የተመሠረተ ነው። የሞባይል ባንኪንግ ወይም የዲጂታል ዋሌት አገልግሎቶችን ስንጠቀም የምንጠቀማቸው የምስጢር ቁጥሮች እና አንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግሉ የማረጋገጫ ኮዶች ለሌላ ወገን ተልፈው ሊሰጡ የማይገባቸው የግል ቁልፎቻችን ናቸው። እውቀቱ የሌለው ሰው ግን አገልግሎቱን ለመጠቀም፣ ገንዘብ ለመላክ ወይም ለማውጣት የሌሎችን ሰዎች እርዳታ ለመጠየቅ ይገደዳል። ይህ ደግሞ የምስጢር ቁጥርን አሳልፎ ለመስጠትና ለገንዘብ ዘረፋ በሰፊው ያጋልጣል። ስለሆነም የዲጂታል ፋይናንስ አሠራርን በስፋት ከመዘርጋት ጎን ለጎን፣ እያንዳንዱ ዜጋ የዘርፉን መሠረታዊ እውቀት እንዲጨብጥ ማድረግ የህልውና ጉዳይ ነው። እውነተኛ የፋይናንስ አካታችነት ማለት አካውንት መክፈት ወይም አፕሊኬሽን መጫን ብቻ ሳይሆን፤ አሠራሩን በጥበብ፣ በደህንነት እና በራስ ተማምኖ የመጠቀም አቅም መገንባት ጭምር ነው። የዲጂታል ፋይናንስ እውቀት የራሳችንንና የቤተሰባችንን ሀብት ከዘረፋ የመጠበቂያ ጋሻችን በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ይህን እውቀት በመጨበጥ ራሱን ከአጭበርባሪዎች ሊጠብቅና የዘመናዊው ኢኮኖሚ እውነተኛ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል። ይህን አጠቃላይ እውነታ በማስመልከት የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ወጣቶችን በዲጂታል እውቀት ለማብቃትና ሀገሪቱን የቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ በርካታ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። ከእነዚህ ጥረቶች መካከል ግንባር ቀደሙ የኢትዮጵያ ሰባት ሚሊዮን ኮደሮች ሥልጠና ነው። ይህ የስልጠና ፕሮጀክት፣ ወጣቶች በነጻ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የቴክኖሎጂ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ መንገድ ከፍቷል። ፕሮግራሙ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በየቀኑ እየተመዘገቡ ሥልጠናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ። ፕሮግራሙ ማንኛውም ወጣት ባለው ስማርትፎን፣ ታብሌት ወይም ኮምፒውተር በራሱ ጊዜና ፍጥነት ኦንላይን መማር እንዲችል ተደርጎ የተቃኘ በመሆኑ ከከተማ እስከ ገጠር ያሉ ወጣቶችን የማካተት አቅም አለው። ሥልጠናውን ያጠናቀቁ ወጣቶች ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የክህሎት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቶችን እያገኙ ሲሆን፣ ይህም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሥራ እድሎችን ለማግኘት በር ከፍቶላቸዋል። ይህ ጥረት የኢትዮጵያን "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ ለማሳካትና ሀገሪቱን በአፍሪካ ዋና የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት፤ "ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ላይ የምታደርገው ኢንቨስትመንት የወደፊት እጣ ፈንታዋን የሚወሰን ስትራቴጂ ነው። ወጣቶችና ምሁራን ይህንን የቴክኖሎጂ ማዕበል ተከትለው ሙያቸውን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ካስደገፉ፣ የሀገራቸውን ችግር ከመፍታት ባለፈ በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ እና ተፈላጊ የመሆን ሰፊ እድል አላቸው" ማለታቸው ይታወሳል። የዲጂታል ዘመን ማዕበል ወደፊት ከመገስገስና ዓለምን ከመቀየር አይቆምም። የቴክኖሎጂ እውቀትን መታጠቅ ለወጣቱ የነገው ስኬት መያዣ፣ ለሀገራችን ደግሞ የኢኮኖሚ እድገት ማፋጠኛ ሞተር ነው። የመንግሥት የኮደሮች ሥልጠና ወጣቶች አቅማቸውን የሚያወጡበትና በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ የሚሆኑበት ትልቅ እድል በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ወጣት ይህን ወርቃማ እድል በመጠቀም የቴክኖሎጂ እውቀቱን ሊያዳብርና የዲጂታሏ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ሊሆን ይገባል።
በፈተናዎች የማትታወክ ታላቅ ሀገር- ኢትዮጵያ
Oct 1, 2026 194
ኢትዮጵያን ታላቅ የሚያሰኛት በርካታ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሮአዊ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል። ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጭም ለሚገጥሟት ተደራራቢ ፈተናዎች በቂና ምልዑ ምላሽ የመስጠት የካበተ ልምድ፣ ጥበብና አቅም አላት። በታሪኳ አያሌ ውጣ ውረዶችንና ማዕበሎችን አስተናግዳ ያለፈች ቢሆንም፣ አንድም ጊዜ ቢሆን ታላቅነቷን፣ ነጻነቷንና ኩራቷን አጥታ አታውቅም። ለዚህ ነው በባዕዳን እጅ ያልወደቀችው፤ ለዚህ ነው ተስፈኛና ተስፋፊ ጠላቶቿን በማሳፈር በተግባር የተፈተነ ዝናን የተቀዳጀችው። በክብርና በነጻነት መሠረት ላይ የተገነባችው ታላቋ ኢትዮጵያ፣ ዛሬም በማይናወጥ አቋም ጽንታ ቆማለች። ኢትዮጵያውያን በዘመናት ሁሉ ሉዓላዊነታቸውንና ህልውናቸውን የሚፈታተን ሙከራ በተደረገ ቁጥር በጀግንነትና በጽናት አጸፋ የመመለስ ታሪካዊ ባህል አላቸው። የሕዝቦቿ ጠንካራ የአንድነትና የነጻነት መንፈስ ማንም በማይገምተው መልኩ ጠላትን እያሳፈረ የወዳጅን ልብ ሲሞቅ ኖሯል፤ ዛሬም ቀጥሏል። ሀገር በጫናዎችና በፈተናዎች ውስጥ በወደቀች ቁጥር ሕዝቦቿ ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው ለአንዲት ኢትዮጵያ ህልውና በአንድነት የቆሙበት አጋጣሚ በርካታ ነው። አድዋ ላይ የተቀዳጀነው ድል የዚሁ የማይናወጥ የአንድነት፣ የጽናትና የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ምልክት ነው። ይህ የነጻነትና የሉዓላዊነት ፍቅር በትውልድ ዘንድ እንደ ሕያው እሳት እየተሸጋገረ የመጣ በመሆኑ፣ ሀገሪቱን ከማንኛውም ወቅታዊ ማዕበል በላይ አድርጎ አቆይቷታል። እንደ ዳግማዊ ዓድዋ የሚቆጠረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ብቻ አይደለም። የይቻላል፣ የአይበገሬነት እና የጽናታችን ዘመን ተሻጋሪ የታሪክ አሻራ እንጂ። ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም፣ ገንዘብና እውቀት ይህንን ታላቅ ተጋድሎ በመፈጸም ዓለምን ማስደመም ችለዋል። ግድቡ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም የማደግና የመለወጥ ትልቅ አቅም ያላት ሀገር መሆኗን ማረጋገጫ ነው። ለም መሬቷን፣ የተፈጥሮ ጸጋዎቿን፣ ማዕድኖቿን፣ ወንዞቿንና የሥራ ወዳዱን ሕዝቧን አስተናጅታ ወደፊት የምትገሰግስበትን መንገድ አመላክቷል። ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የሚገጥሟትን ወቅታዊ ፈተናዎች በብልህነትና በጽናት በማለፍ፣ የወደፊት ብሩህ ተስፋዋን መገንባት የምትችል ሀገር መሆኗን በዚሁ ታላቅ ፕሮጀክት ደግማ አረጋግጣለች። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ እየተመራች ታላቅነቷን እያስቀጠለች ትገኛለች። የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ በልኳ እንድትቀመጥ ማድረግ ነው። የኢትዮጵያ ልክ ደግሞ ነጻነቷን፣ ኩራቷን፣ የልማት ፍላጎቷንና ታላቅነቷን ማስቀጠል መቻል ነው። በታሪክ አጋጣሚዎች የሚያጋጥሙ የውስጥ ችግሮችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች ሀገሪቱን ለማዳከም ይሞክራሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ ባዕዳንንና ባንዳዎችን ማሳፈር የሁልጊዜ ተግባሯ ነው። የመደመር እሳቤ ሀገሪቱን ከድህነት አውጥቶ ከታሪኳና ከገጽታዋ ጋር የሚመጥን ደረጃ ላይ ለማስቀመጥ ይተጋል። ይህ አካሄድ የሰው ኃይልን፣ የተፈጥሮ ጸጋን፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሀብቶችን አስተናብሮ ለጋራ ብልጽግና ማዋልን መዳረሻው ያደረገ ነው። የውስጥ ልዩነቶችን ወደ ውበትና ጥንካሬ በመቀየር፣ ኢትዮጵያን በራሷ እግር በጽኑ እንድትቆም ያደርጋል። ዛሬም የማትናወጠውና የማትሸበረው ኢትዮጵያ በልጆቿ ብርቱ ክንድ ወደፊት እየተመለከተች በፍጥነት እየተራመደች ነው። ኢ-ፍትሐዊነትን ለማረም፣ ሉዓላዊነቷን ለማጽናት እና የሕዝቡን የልማት መሻት ለመፈጸም ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ወቅታዊ ማዕበሎች፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ውጣ ውረዶች ወይም የውጭ ጫናዎች የቱንም ያህል ቢበረቱ፣ የኢትዮጵያን ሕልውናና ታላቅነት ሊያናውጡት አይችሉም። የኢትዮጵያን ታላቅነት እውን የሚያደርጉና ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው እንዲኮሩ የሚያደርጉ ሜጋ ፕሮጀክቶች እውን እየሆኑ ነው። በኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ በማድረግ ላይ ይገኛል።በሌማት ትሩፋት የዜጎችን የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጥና የካፒታል አቅምን የሚያሳድግ ስራ ነው። በገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ የተፈጥሮ ሀብቶችንና የታሪክ ስፍራዎችን ወደ ትልቅ የቱሪዝምና የኢኮኖሚ አቅም የለወጡ ፕሮጀክቶች ናቸው። በግብርናው ዘርፍ የተመዘገበው የስንዴ ምርታማነት፦ ሀገሪቱን ከፈላጊነት ወደ ላኪነት ያሸጋገረ የብሄራዊ አቅም ማሳያ ነው። በትክክለኛ ጎዳና ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በምንም የማትናወጥና የማትሸበር ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ትናንት በጽናት አልፋለች፤ ዛሬም ፈተናዎችን በልማትና በአንድነት እያሸነፈች ትራመዳለች። ነገም ቢሆን ጠላቶቿን እያሳፈረች፣ ሉዓላዊነቷን አስከብራ፣ የታሪኳና የጽናቷ ባለቤት እንደሆነች በከፍታና በክብር ጉዞዋን ትቀጥላለች።
የቀጣናው ልማት እና ስበት ማዕከል - ኢትዮጵያ
Sep 30, 2026 248
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በዘላቂ ሰላምና ጸጥታ ማስከበር ስራዎች ውስጥ ዘመን አይሽሬ ሚና ያላት ሀገር ናት። ኢትዮጵያ በቀጣናው ዲፕሎማሲ ማዕከል ሆና እያገለገለች ሲሆን፣ ለዚህም በምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ምስረታ እና ማጠናከር ውስጥ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የቀጣናው ሀገራት በትብብር እንዲሰሩ መንገድ የጠረገችበትን ታሪክ ማንሳት ይቻላል። በቀጣናው ያለውን የአልሸባብ እና መሰል አክራሪ ቡድኖችን ስጋት በመቀነስ ረገድ የድንበር እና የቀጣናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ግንባር ቀደም ሚናም እየተወጣች መሆኗን ማንሳት ይቻላል። ይህ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት እና በአፍሪካ ህብረት ስር በመሆን በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሶማሊያ እና በሩዋንዳ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በማሰማራት በሀገራቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የማይተካ ሚና የተጫወተችና አሁንም በሶማሊያና ደቡብ ሶዳን የቀጠለች የቀጣናው አርአያ ናት። ኢትዮጵያ በቀጣናው ግጭቶች በዘላቂነት ተወግደው የልማት ትስስሮች እንዲፋጠኑ በሰላም ማስከበር ተልዕኮም ጭምር ከፍተኛ ሚና እየተወጣች ትገኛለች። ቀጣናው በኢኮኖሚ እና መሠረተ-ልማት የበለጠ እንዲተሳሰር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ቀጣይነት ያለው ስራ ሰርታለች። ለአብነትም ለሱዳን፣ ለጅቡቲ እንዲሁም ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሃይል በማቅረብ የቀጠናውን የሃይል ትስስር እውን እያደረገች ትገኛለች። በትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ ዘርፍም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀጣናውን ሀገራት በማስተሳሰር ሂደት የአንበሳውን ሚና እየተወጣ ይገኛል። በተጨማሪም ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሶማሊያ እና ከኤርትራ በተለያየ ምክንያት ለተሰደዱ ወገኖች ጋሻ እና መከታ በመሆን ዓለም አቀፍ ምስጋና የተቸራት ሀገር መሆኗንም መጥቀስ ይቻላል። ዛሬም ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና አጋርነትን ማዕከል ያደረጉ ትብብሮች እንዲጠነክሩ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ተግታ እየሰራች ትገኛለች። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በቁርጠኝነት እየሄደችበት የሚገኘው ይህ መንገድ የቀጣናውን የጋራ ተጠቃሚነትና ራስን የመቻል ጥረት የሚያፋጥን መሆኑ እሙን ነው። ሂደቱ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከጎረቤት ሀገራት ጋር አብሮ ለመልማት ያላትን ጽኑ ፍላጎት በገሃድ እየገለጠ ይገኛል። ባለፉት ጥቂት ቀናትም በምሥራቅ አፍሪካ መሪዎች መካከል የተደረጉት በከፍተኛ ደረጃ የሚታዩት ውይይቶች ቀጣናዊ ትስስርን እና የኢኮኖሚ አቅምን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የተወሰዱ ቁርጠኛ እርምጃዎችን ያሳያሉ። እነዚህ ግንኙነቶች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማስቀደም እና እምነትን ለመገንባት እድል የሚፈጥሩ ናቸው። ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ከዳመርጆግ እስከ ደወሌ የሚዘረጋውን 120 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክት ይፋ ያደረጉ ሲሆን፣ ይህም የድንበር ተሻጋሪ ንግድ እንቅስቃሴን በከፍተኛ ሁኔታ ይለውጣል ተብሎ ይጠበቃል። በሌላ በኩል የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ግንኙነቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ውይይት በአዲስ አበባ አካሂደዋል። በተለይ 120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧው፣ የባሕር ዳርቻ የነዳጅ ማከማቻና ማሰራጫን ከሀገር ውስጥ የመሰረተ ልማት አውታሮች ጋር ለማገናኘት የታቀደ የልማት ስራ ነው። የቧንቧው የማከማቸት አቅም 400 ሚሊዮን ሊትር ነው። ይህ የነዳጅ ቧንቧ መስመር በኢትዮጵያና ጂቡቲ የንግድ ኮሪደር ላይ ያለውን ትልቅ ማነቆ የሚቀርፍ ነው። የቧንቧ መስመሩ መዘርጋት በመንገድ ላይ የሚባክነውን ጊዜ ይቀንሳል፤ የትራንስፖርት ወጪን ይቀንሳል፣ እንዲሁም የነዳጅ አቅርቦትን አስተማማኝ የሚያደርግ ሲሆን ይህም በቀጣናው ላሉ የንግድ ተቋማትና ድርጅቶች ትልቅ ጥቅም ይሰጣል። ዛሬም በላሙ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና ሌሎች መሪዎች ከዳንጎቴ ጋር በመሆን የ16 ቢሊዮን ዶላር ነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባት የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል። በላፕሴት ኮሪደር አቅራቢያ የሚገኘው ይህ ማጣሪያ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ያካተቱ ገበያዎችን ለማገልገል የታለመ ነው። ዳንጎቴ ለምሥራቅ አፍሪካ መንግሥታት የ30 በመቶ የድርሻ ባለቤትነት እንዲኖራቸውም ጋብዟል። ፕሮጀክቱ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2030 ይጠናቀቃል ተብሎ የታቀደ ሲሆን፣ ከ50 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድሎችን እንደሚፈጥር ተገምቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እነዚህ ጅምር ስራዎች መሬት እንዲነኩ እና ፍሬ እንዲያፈሩ በከፍተኛ ትጋት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴዎቻቸው ዲፕሎማሲን ወደ ተጨባጭ ውጤት የመቀየር ጉዞ ማሳያ ነው። ይህ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ እና ምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ጠንካራ የንግድ ትስስርን ለማጠናከር ተስፋ ሰጪ ጥረት መሆኑን ማየት ይቻላል። በጥቅሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚህ ቀጣና እየተወጡ ያሉት የመሪነት ሚና ኢትዮጵያን እንደ ትልቅ ገበያ፣ በድንበር ተሻጋሪ መሰረተ ልማት አጋር እና ለተሻለ ቀጣናዊ ቅንጅት አነቃቂ ኃይል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቀጣናው የልማት ማዕከል እንድትሆን የጀመሩትን በጎ እርምጃ ወደ ሌሎች በማጋራት የአፍሪካ ቀንድን የበለጠ ለማስተሳሰር ምቹ መደላደል ይፈጠራል። በታሪክ ኢትዮጵያ ያካበተችውን የቀጣናው ልማት እና ስበት ማዕከልነቷን ለማስቀጠል የሚያስችል እንቅስቃሴ ነው።
ኢትዮጵያ የሥነ-ምግብ መሶብ፤ አፍሪካዊት የጤናማ ትውልድ ግንባታ ተምሳሌት
Sep 30, 2026 136
በአፍሪካ ሕፃናት ላይ የሚያጋጥመው የምግብና የሥነ-ምግብ ደኅንነት ችግር ከጤና ተቋማት አቅም የዘለለና የፖሊሲ አፋጣኝ ጣልቃ ገብነትን የሚጠይቅ ብሔራዊና አህጉራዊ አጀንዳ ነው። የግብርና፣ የጤና፣ የውሃ፣ የትምህርት፣ የገቢ ማስገኛና የማኅበራዊ ጥበቃ ፖሊሲዎች በተቀናጀ መንገድ የሚመልሱት ብሔራዊ የልማት ጉዳይ ነው። ሕፃናትን ለመመገብ የሚያስፈልገው ምግብ ከየት ይመጣል? የሚመረተውስ በቂና ገንቢ ነውይ? ሀገራት ይህን ታላቅ ሀላፊነት በራሳቸው ሀብትና ተቋም ለማስቀጠል ምን ያህል ተዘጋጅተዋል? የሚሉት ጥያቄዎች ዛሬ ላይ ሊመለሱ የሚገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ናቸው። እነዚህ ወሳኝ ሐሳቦች በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ በተካሄደው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን በተካሄደው ''Our Children Cannot Wait'' መድረክ ላይ በሰፊው ተስተጋብተዋል። መድረኩ የሕፃናትን ሕይወት መጠበቅ የነገ ተስፋ ሳይሆን የዛሬ አጭርና ግልጽ ውሳኔ መሆኑን በደማቅ ሁኔታ አሳይቷል። የአፍሪካ የሥነ-ምግብ ሉዓላዊነት ጥሪ፤ በአህጉሪቷ መሪዎች አንደበት!! የአፍሪካ ሕብረት የሥነ-ምግብ ሻምፒዮን እና የሌሶቶ ንጉሥ ሌትሲ ሳልሳዊ በአህጉራዊው መድረክ ላይ እንዳሰመሩበት፣ አፍሪካ የልጆቿን ሥነ-ምግብ በራሷ መንግሥታትና ሃብት ማስተዳደር የሚያስችላትን የሥነ-ምግብ ሉዓላዊነት ማጠናከር አለባት። የአንድ ሀገር የወደፊት አቅም ከሚገለጽባቸው መለኪያዎች መካከልም የሕፃናቷ ጤናና የአእምሮ እድገት ይገኙበታል። ይህ አቋም የውጭ እርዳታን ሙሉ በሙሉ በመካድ የቀረበ ሳይሆን የሀገር ውስጥ ፋይናንስና የራስን አቅም ከዘላቂ የምግብ ሥርዓት ጋር የማጣመር ራዕይ ነው። የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶም በበኩላቸው የሕፃናት ሥነ-ምግብ ደኅንነት ከአስተማማኝ የሰው ሃብት ግንባታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን አንስተዋል። የሕፃናትን ሕይወት ማዳን መርሆዎችና የተግባር ጥሪ በሚል ዐበይት ርዕስ የቀረበው ሰነድም፤ የሕፃናትን ሕይወት መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ብሔራዊ አጀንዳነት ቀርቧል። የሀገር ውስጥ ፋይናንስን ማጎልበትና ዓለም አቀፍ አጋርነቶች በሀገራት በሚመሩ ዕቅዶች ላይ እንዲመሰረቱ ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ የሥነ-ምግብ ደኅንነት ሉዓላዊነት ትልም፤ የጤናማ ትውልድ ግንባታ መሰረት!! ኢትዮጵያ እስከ 2030 ድረስ ከሁለት ዓመት በታች ባሉ ሕፃናት ላይ መቀንጨርን ለማስወገድ የያዘችውን የ15 ዓመት ብሔራዊ ግብ የሰቆጣ ቃል ኪዳንን በመተግበር ላይ ትገኛለች። ይህ ጥረት በጤና ዘርፍ ብቻ የተገደበ አይደለም። ግብርናን፣ ውሃን፣ ትምህርትን፣ ገቢ ማስገኛንና ሌሎች ዘርፎችን በማስተሳሰር የሥነ-ምግብ ጉዳይን ከምግብ ምርት እስከ ቤተሰብ ማዕድ ድረስ በሚዘልቅ ሁለንተናዊ አቅጣጫ ለመመለስ የሚያስችል ሥርዓት እየተገነባ ነው። በዚህ ሰንሰለት ውስጥ የምግብ ብዝኅነት የላቀ ሚና አለው። የወተት፣ የእንቁላል፣ የዶሮ ሥጋ፣ የማር፣ የአትክልትና የፍራፍሬ ምርትን በማቀናጀት የሚተገበረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርም የምግብ መጠንን ከማሳደግ ባሻገር የምግብ ዓይነትና ጥራትን ለማስፋት የሚያግዝ አቅጣጫ ሆኗል። በተመሳሳይ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የሀገር ውስጥ የስንዴ አቅርቦትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር ያግዛል። ይሁንና የሥነ-ምግብ ደኅንነት ከአንድ የሰብል ምርት በላይ ስለሆነ ስንዴን ከሌሎች የምግብ ምርቶች ጋር ማጣመር የተሟላ የምግብ መሶብ ለመገንባት ወሳኝ ነው። የ2023 ብሔራዊ የምግብና ሥነ-ምግብ ስትራቴጂ መነሻ ጥናት እንደሚያመለክተው 39 በመቶ የሚሆኑ ከአምስት ዓመት በታች ሕፃናት የመቀንጨር ተጠቂ እንደነበሩ ያመላክታል። የካናዳ ዓለም አቀፍ የሥነ-ምግብ ድርጅት ኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል የ2024 ግምገማ እንደሚያሳየው በሀገሪቱ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት የመቀንጨር ተጠቂዎች ናቸው። ለዚህም የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የሥነ-ምግብና የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ አጀንዳ ወሳኝ የምላሽ መስጫ አቅም መገንባ መሳሪያ ሆኖ ይጠቀሳል። የሥነ-ምግብ ብዝኅ ምርታማነት አቅም፤ የሕፃናት የሥነ-ምግብ ደኅንነት ዋስትና መቀንጨር የሕፃናትን የዕድገት አቅም ይጎዳል። ደም ማነስም በእናቶች፣ በሕፃናትና በሴቶች ጤና ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል። ሲዳመርም የዛሬ የሥነ-ምግብ ችግር የነገ የትምህርት፣ የምርታማነትና የኢኮኖሚ ጉዳይ ይሆናል። የኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል የሥነ-ምግብ ዋጋ ትንታኔ እንደሚስረዳው፤ የኢትዮጵያ የሥነ-ምግብ ኢንቨስትመንት የትውልድ ዘላቂነትን የሚያስጠብቅ ወሳኝ አጀንዳ መሆኑን ያብራራል። የኢትዮጵያ የሰቆጣ ቃልኪዳን፣ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር፣ የስንዴ ምርታማነትና አጠቃላይ ሁለንተናዊ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ እመርታዊ ስኬትም ጤንነቱ የተጠበቀና ቀጣይነት ያለው ሀገር ተረካቢ ትውልድ የመገንባት አቅጣጫን የተከተለ ራዕይ ነው። ከአስመጪነት ወደ ራስን መመገብ፤ የኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነት ፍኖት በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የ2026 ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጫናን መቋቋም የሚችለውን የስንዴ ምርት በማስፋፋት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከስንዴ አስመጪነት ወደ አፍሪካ ትልቋ የስንዴ አምራችነት መሸጋገሯን አብስረዋል። ይህ ታላቅ ስኬት አፍሪካ በራሷ አቅም ራሷን መመገብ እንደምትችል የሚያሳይ ትልቅ ተምሳሌታዊ መልዕክት ነው። የምግብ ዋስትና ከውጭ ገበያ በመግዛት ብቻ የሚጠበቅ ሳይሆን የሀገር ውስጥ ምርት፣ የተሻሻሉ ዝርያዎች፣ መስኖና የገበያ ሥርዓትን በማጣመር የሚገነባ የሉዓላዊነት ማሳያ መሆኑን አሳይቷል። ይህንንም አፍሪካ በራሷ አቅም ራሷን መመገብ እንደምትችል የሚያስተምር ተምሳሌታዊ መልዕክት ሆኖ ተላልፏል። ይህ መልዕክትም የምግብ ዋስትና ከውጭ ገበያ በመግዛት ብቻ የሚጠበቅ ጉዳይ ሳይሆን የሀገር ውስጥ ምርት፣ ቴክኖሎጂ፣ የተሻሻሉ ዝርያዎች፣ መስኖና የገበያ ሥርዓትን በማጣመር የሚገነባ አቅም መሆኑን ነው። በተለይም በማዕድ ላይ የሚቀርበው ምግብ ብዝኅነት ሕፃናትና ቤተሰቦች የተመጣጠነ ሥርዓተ ምግብ የሚያገኙበት ነው። ሕፃናት በትክክለኛው ዕድሜ ተገቢውን ምግብ ማግኘታቸውም ጤናማ ትውልድ የመገንባት ወሳኝ አቅም ይሆናል። የኢትዮጵያ ማዕድ ምልዑነት፤ የትውልድ ግንባታ መሰረት የገበሬው የምርታማነት አቅም ምግብ በበቂና ተመጣጣኝ ዋጋ ለቤተሰብ እንዲደርስ ያግዛል። ቤተሰቡ የተለያየና ገንቢ ምግብ ሲያገኝ የሕፃናት ሥነ-ምግብ ደኅንነት ይጠናከራል። ጤናማ ሕፃናት ደግሞ በትምህርት የተሻለ የመማር፣ በኋላም በሥራ የመሳተፍና ምርታማ የመሆንና ሀገርን የመገንባት አቅም ይኖራቸዋል። ከሰቆጣ ቃል ኪዳን እስከ ሌማት ትሩፋት፣ ከአትክልትና ፍራፍሬ እስከ ወተት፣ እንቁላልና ማር፣ ከመስኖ ስንዴ እስከ የቤተሰብ የምግብ ቅርጫት ድረስ የተመዘገቡ እመርታዊ ለውጦችም የዛሬ የምግብ ምርት ውሳኔ የነገ ትውልድ ጤና ላይ የተመሰረተ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል። የአፍሪካ መሪዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 2026 ጠቅላላ ጉባኤ ያነሱት ጥያቄም ሕፃናትና ታዳጊ ልጆች እስኪያድጉ ድረስ እራሳቸውን መጠበቅ አይችሉም የሚለውን ነው። የምግብና የሥነ-ምግብ ደኅንነትን የማረጋገጥ ጉዳይም የዛሬ የልማት ውሳኔ ብቻ ሳይሆን ውጤቱ በነገ ጤናማ፣ የተማረና ምርታማ ትውልድ ላይ የተመሰረተ ይሆናል። የኢትዮጵያ የምግብና ሥነ-ምግብ ጉዞ ከአፍሪካ የሥነ-ምግብ ሉዓላዊነት ጥሪ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ የራስን ምግብ ማምረት የዛሬን ማዕድ ለመሙላት ብቻ ሳይሆን፣ ነገ ሀገርን የሚረከብ ጤናማ፣ የነቃና ብቁ ትውልድ ለመገንባት የሚያስችል የዘላቂ ልማት ምሰሶ ነው።
ትንታኔዎች
የሁለት ግድቦች ወግ
Oct 3, 2026 395
ሕዳሴ የቀጣናው የምስራች፤ አስዋን የበደልና ጥፋት ምንጭ ዓባይ ከኢትዮጵያ ተራሮች ፈልቆ፤ አለት ሰንጥቆ፤ ሸለቆዎችን ተሻግሮ ወደ ምስር ይፈስሳል። ማኅፀኑ ኢትዮጵያ ብትሆንም፣ ጠብታ አብርክቶ ለማታውቀው ግብፅ የሕይወት ምንጭ ሆኖ ኖሯል።ዓባይ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ነው፤ የግብፅን ሐሩር ያረሰረሰ፣ የቀጣናውን የኢነርጂና የኢኮኖሚ ልማት ዕድል የተሸከመ ወንዝ ነው። አሁን ላይ በዓባይ ወንዝ ላይ ኢትዮጵያም ግብፅም እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ግዙፍ ግድቦች አሏቸው፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድን እና አስዋን ግድብ።ሁለቱ ግድቦች ግድብነታቸው ሊያመሳስላቸው ቢችልም፣ ታሪካቸው፣ ተፅዕኖአቸውና ለትውልድ የሚያስተላልፉት መልዕክት ግን ለየቅል ነው። በዚህ ወንዝ ላይ ለዓመታት በአልጠግብ ባይነት የተበየነው የግብፅ የውሃ ፖሊሲ፣ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት የልማት ፍላጎትን በተደጋጋሚ የሚገድብ አካሄድን ይዞ ቆይቷል። በዚህም መነሻ ያለምንም ማማከርና ያለ ቴክኒካል ውይይት ዓባይን ብቻችንን መቆጣጠር አለብን በሚል እብሪት አስዋን ተገንብቷል። የአስዋን ግድብ ሥር እንባዎች አስዋን የግብፅን ታሪክ በእጅጉ የቀየረ፣ የበረሃዋን ምድር በመስኖ ያለመለመ፣ የኃይል ምርቷን እንድታሳድግ ያስቻለ ግዙፍ መሠረተ ልማት ነው። ነገር ግን ከዚህ የልማት ገጽታ ጀርባ ብዙ ዋጋ የተከፈለባቸው የሕይወት ዋጋዎች፣ የተሰደደ ማኅበረሰብና በውሃ ስር የተቀበሩ ታሪካዊ ርስቶች አሉ። ይህ በአስዋን ግንብ ስር በእንባ የተጻፈ የበደል ታሪክ ነው።አስዋን ሲገነባ የኑቢያ ምድር በሰፊው የናስር ሐይቅ ተጥለቅልቋል። ወደ 100 ሺህ የሚደርሱ ኑቢያውያን ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ኑሯቸው ተናግቷል። ያላቸውን ጥሪት አጥተዋል። ለብዙ ሺህ ዓመታት በትውልድ ተሻግሮ የመጣው ርስታቸውና የኑሮ መሠረታቸው በናስር ሐይቅ ምክንያት ወድሟል። የኑቢያ ጥንታዊ ቅርሶችም በሐይቁ ስር የመቀበር አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ብዙ ቅርሶች በውሃ ስር ቀርተዋል፤ ሌሎች ደግሞ በዓለም አቀፍ የቅርስ ጥበቃ ዘመቻ ከነበሩበት ተነቅለው ወደ ሌላ ቦታ ተዛውረዋል።የአስዋን ሐይቅ በሰው ልጅና በውሃ ሀብት ላይ ያሳረፈው ጫና በዚህም አያበቃም። በበረሃማው ስፍራ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ሐይቅ በየዓመቱ እስከ 16 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ በትነት እንዲጠፋ በማድረግ ውሃ ያለ አግባብ እንዲባክን ያደርጋል። 16 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ ማለት ደግሞ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከሚይዘው 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ አንጻር ስንመለከተው፤ አስዋን ግድብ በየ አራት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ የሕዳሴ ግድብ የያዘውን ሙሉ ውሃ በትነት ያባክናል እንደ ማለት ነው። ይህ በሰው ልጅ ይውሃ ፍጆታ አንጻር ደግሞ አስዋን ድግብ ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለአንድ ዓመት ሙሉ መጠቀም የሚችለውን የቤት ውስጥ የውሃ ፍላጎት በትነት እያባከነ ቀጥሏል። አስዋን ግድብ የያዘው የናስር ሃይቅ በጣም ሰፊ እና ጥልቀቱ አነስተኛ (Shallow and Wide) በመሆኑ ለፀሐይ ብርሃን የሚጋለጠው አካል ሰፊ ነው። ይህ ደግሞ የትነት መጠኑ በእጅጉ እንዲጨምር አድርጓል።ይህ በትነት የሚጠፋው የውሃ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት በውሃ አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ ሁልጊዜም በግብፅ ስሁት አካሄድና ደካማ የውሃ አስተዳደር ላይ የሚነሳ አጀንዳ ሆኗል። ከዚህም በባሰ ግብፅ የላይኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት እንድም ልማት እንዳያለሙ በሴራ በማቀብ እርሷ ግን በአስዋን ግድብ ላይ የተመሠረተውን የናስር ሐይቅ ውሃ ከፍተኛ የውሃ ፍጆታ በሚጠይቁ የሸንኮራ አገዳ፣ የጥጥና የሩዝ ልማቶች በማዋል ለብዙ ዓመታት በደል ስትፈጽም ኖራለች። ይህም የአሰዋን ግድብ የበደል ታሪክ ነው። አስዋን የዓባይን ውሃ በብቸኝነት የመጠቀም ፍላጎትን፣ የውሃ ሀብትን በአንድ ወገን ላይ በማስቀመጥ የሌሎችን የልማት መብት የሚገድብ አስተሳሰብን የሚወክል ታሪካዊ ምልክት ሆኖ ቆይቷል። ዛሬ ግን ይህ ትርክት ተለውጧል። ሕዳሴ ቀልብሶታል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ -የቀጣናው የምስራች በዓባይ ወንዝ ላይ አዲስ ምዕራፍ ተጽፏል።ሕዳሴ የተኛን ኃይል አንቅቷል። የተዘነጋን ሀብት ወደ ልማት ቀይሯል። የትናንትን ጥገኝነት ወደ የራስ አቅም አሸጋግሯል። ለዘመናት በኢትዮጵያውያን ደጅ ወርቁን፣ አፈሩን፣ ግንዱንና ሌላውንም እያግበሰበሰ ሲጓዝ የኖረውን፣ ኢትዮጵያውያን ከኩበት ጭስ ጋር እየታገሉ፣ በጨለማ ስር ተቀምጠው በቁጭት ሲያዜሙለት የኖሩትን ዓባይን፣ ሕዳሴ ወደ ብርሃን ምንጭነት አዙሮታል። ታላቁ የሕዳሴ ግድብ 5 ሺህ 150 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫል። በንጋት ሐይቅ ወደ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያከማቻል። ይህም የኢትዮጵያን ከውሃ ኃይል የሚመነጭ የኢነርጂ አቅምን በእጅጉ የሚያሳድግ፣ የኢኮኖሚ ልማቷን የሚደግፍ ትልቅ መሠረተ ልማት ነው። የሕዳሴ የምስራችነት በዚህ አያበቃም። የሕዳሴ ግድብ የቀጣናው የኢነርጂና የልማት ምንጭ ነው። ለሱዳን፣ ለጅቡቲ፣ ለኬንያ፣ ኃይል ማስተላለፍ ጀምሯል። ለሌሎችም ለመድረስ ጥናት በመካሄድ ላይ ይገኛል። የግድቡ መገንባት የጠቀመው እንጂ የጎዳው አካል የለም። የሱዳንን የጎርፍ አደጋ በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚና አለው። ለሱዳንም ሆነ ለግብፅ ከደለል ንጹህ የሆነ፣ ዓመታዊ ፍሰቱ የተስተካከለ ውሃ እንዲያገኙ ያስችላል። የሕዳሴ ግድብ የሚገኝበት አካባቢ የአየር ሁኔታና ጂኦግራፊ እንደ እቶን በሚንተከተከው በረሃ ከተገነባውና ውሃን ያለቅጥ ከሚያተነው የአስዋን ግድብ አንጻር እጅግ ቀዝቃዛና ለውሃ ብክነትና ትነት ተጋላጭ ያልሆነ የውሃ ማከማቻ ነው። የንጋት ሐይቅም ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ የውሃው የላይኛው ክፍል እጅግ ያነሰ የፀሐይ ተጋላጭነት አለው። ይህም ትነትን በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን፤ ለዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ከ10 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ በላይ ውሃ በትነት እንዳይባክን ታድጓል። ይህ ውሃ በደረቅ ወቅት፣ የበረሃ ቅንጦተኞቹን፣ የአዞ እንባ አፍሳሾችን እነግብፅንም ጭምር የሚያረሰርስ ነው።ሕዳሴ ዓባይን የፍትሐዊና የዘላቂ ልማት ምንጭ፣ የተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ዕድገት ምሰሶ እንዲሆን አዲስ መንገድ ከፍቷል።የሁለቱ ግድቦች ወግም ይኸው ነው። አስዋን ግድብ በሐይቅ ስር የኑቢያን ምድር ሲሰለቅጥ፤ የሚሊዮኖችን እርዛት የሚያስቀረውን ውሃ ሲያተን፣ ሌላው ግን በጨለማ የተዋጠውን በልማት ወደ ኋላ የቀረውን ቀጣና ከተኛበት ቀሰቀሰ፣ ብርሃኑን አዳረሰ። የልማት ተስፋ ሆነ። ይኸው ነው!
ብሔራዊ ጥቅም - የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ቀይ መስመር
Oct 2, 2026 368
ትልቅ ሀገር ፤ ትልቅ ሕዝብ ፣ ታላቅ ርዕይ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ባለው የረዥም ዘመን ታሪክ በተለያዩ ታሪካዊ፣ ጂኦፖለቲካዊና ውስጣዊ የፖለቲካ ሁነቶች ውስጥ አልፏል። የዓለም መንግሥታት ማኅበር ፣ በመቀጠልም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስራች አባል በመሆን ለዓለም አቀፍ ሕግ የበላይነት፣ ለሉዓላዊነትና ለጋራ ደህንነት መከበር የጸና አቋም ስትሟገት ቆይታለች። በዚህ መርህ መሰረት ባደረገ ዲፕሎማሲያዊ አካሄዷ፣ ኢትዮጵያ ለፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መጠናከር፣ ለቀጣናዊ ወንድማማችነት እንዲሁም ለአፍሪካ ሀገራት የነፃነት ትግል ትልቅ ድጋፍ በማድረግ የአህጉሪቱ የነፃነትና የአንድነት ምልክት መሆን ችላለች። የዚህ ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ውጤት በመሆንም፣ መዲናዋ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት (የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት) እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆን የአህጉሪቷ ዲፕሎማሲያዊ ማዕከልነቷን አስመስክራ ቀጥላለች። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ታሪክ ከህልውና፣ ነጻነት እና ብሔራዊ ጥቅሟን ከማስከበር ጋር ተሳስሮ የዘለቀ የጽናት ጉዞ ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለብሔራዊ ጥቅሟና ለሉዓላዊነቷ የማይደራደር ቀይ መስመር በመዘርጋት፣ የጂኦፖለቲካዊ ውጣ ውረዶችን በብልሃትና በጽናት ስትሻገር ቆይታለች። በዚህም መስመር ለዘመናት በዓለም አቀፍ መድረኮች ጥቅሞቿን አስጠብቃለች። ለሌሎች ጥቅምም ቆማለች። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ስኬት ሆኖ የሚጠቀሰው የዓድዋ ድል ነው። ይህ ድል፣ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምልክት ከመሆኑ ባሻገር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ እኩል ሀገር እንድትታይና የዲፕሎማሲያዊ ገዢነት ምሳሌ እንድትሆን አድርጓታል። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ጉዞ ከረጅም ታሪካዊ መሠረቱና የፓን-አፍሪካኒዝም ማዕከልነቱ ባልተራቀቀ መልኩ፣ አሁን ባለንበት ዘመን አዲስ የልማት፣ የሉዓላዊነትና የስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ ምዕራፍ ውስጥ ይገኛል። የመደመር መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት መርሆዎች በአዲስ መነቃቃት ላይ ይገኛል። የዚህ አዲስ የዲፕሎማሲ እይታ ዋና መሠረት ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ጥቅምንና ሉዓላዊነትን ቀይ መስመር ያደረገ፣ ነገር ግን ለጎረቤት ሀገራት ሰላም፣ ልማትና የጋራ እድገት ቅድሚያ የሚሰጥ ተግባራዊ አቀራረብ ነው። የመደመር መንግስት ዲፕሎማሲ አብሮ የመበልጸግ ፅንሰ-ሐሳብን ያቀነቅናል። ኢትዮጵያ ሰላምና ልማት የሚረጋገጠው ጎረቤቶቿ ሰላምና ልማት ሲያገኙ ብቻ እንደሆነ በማመን "ቅድሚያ ለጎረቤት" የሚል መርህ ይከተላል። ይህ መርህ ከቀደመው ባህላዊ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ተሻግሮ ወደ ተግባራዊ የኢኮኖሚ፣ ንግድና መሠረተ-ልማት ትስስር ተቀይሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጎረቤት ሀገራት መሪዎች በተለይም በቅርቡ ከኬኒያና ከጂቡቲ መሪዎች ጋር ያደረጓቸው ውይይቶች የአፍሪካ ቀንድን የማስተሳሰር ጥረት ማሳያ ናቸው። ይህ የኢኮኖሚ ትስስር በተጨባጭ የሚገጥም ጭምር ነው። ኢትዮጵያ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ለኬኒያ፣ ለጂቡቲና ለሱዳን በማቅረብ ቀጣናውን በኢነርጂ ድልድይ አስተሳስራለች።አዲስ አበባን ከጂቡቲ ወደብ የሚያገናኘው የባቡር መስመርና ወደ ኬኒያ (ላሙ ወደብ) የሚያቀኑት የላፕሴት (LAPSSET) ኮሪደር ፕሮጀክቶች የንግድ ፍሰቱን ለማሳለጥ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ናቸው።የጋራ የውሃ ሀብቶችን በጋራ የመጠቀምና ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ቀጠናዎችን የማስፋፋት ሥራዎች ተከናውነዋል። ነገር ግን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስከብሩ አበይት አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የማትንበረከክና የማታወላውል አቋም አላት።ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከፍተኛ የጂኦፖለቲካዊና የዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች ቢኖሩበትም፣ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብቷን በማስከበር የግድቡን ግንባታና የውሃ ሙሌት በውጭ ጫና ሳታቋርጥ ከፍጻሜ አድርሳለች። ለዘመናት የቆየውን ታሪካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ መሠረት በማድረግ፣ ኢትዮጵያ ዘላቂና ሕጋዊ የባህር በር ፍላጎቷን በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሠራች ትገኛለች። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነትና ግዛት አንድነቷን በተግባር የተጻረሩና አላስፈላጊ ጫናዎችን ለመጫን የሞከሩ አካላትን ዓለም አቀፍ ሕግንና ደንብን መሠረት ባደረገ መልኩ የመመከትና ምላሽ ለመስጠትም ወደ ኋላ የማትል መሆኗን በተግባር አሳይታለች።
ከአባይ እስከ ቀይ ባህር - የኢትዮጵያ አይበገሬነት እና የግብጽ ሴራ
Oct 2, 2026 411
ኢትዮጵያ በረጅም የታሪክ ጉዞዋ የብዙ ውጫዊ እና ውስጣዊ ፈተናዎች ማዕከል ሆና የቆየች ሀገር ናት።ሀገሪቱ ያሏትን ተፈጥሮአዊ ሀብቶች እንዳትጠቀም ፣የጂኦፖለቲካዊ አሰላለፍ ውስጥ የሚገባትን ቦታ እንዳትይዝ ለዘመናት የተደራጀ እና የተቀናጀ ሴራ እና ጫና ሰለባ ሆናለች። ከእነዚህ ዘመናትን ከተሻገሩ ሴራዎች ጀርባ ደግሞ ግብጽ ትገኛለች። የግብፅ አቋም እና የውጭ ፖሊሲ በዋናነት የሚያተኩረው የዓባይን ወንዝ ውኃ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የተረጋጋች፣ጠንካራ እና በኢኮኖሚ የበለጸገች ኢትዮጵያ እንዳትፈጠር በማድረግ ላይ ነው። ግብፅ ይህን ዓላማዋን በተለያዩ ጊዜያት በቀጥታ በጦርነት ለማስፈጸም ያደረገችው ጥረት በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ሽንፈት ተከናንባ እንድትመለስ አድርጓታል።ይህ አልሳካ ሲላት ደግሞ የኢትዮጵያን የውስጥ ተቃዋሚዎች እና አማጺ ቡድኖችን በመደገፍ ሀገሪቱን የማዳከም ስልት ስትከተል ኖራለች። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ባሉት አስርት ዓመታት፣ ግብፅ በአፍሪካ እና በአረብ ዓለም ውስጥ ተፅዕኖዋን ለማስፋት ስትጥር፣ የዓባይ ተፋሰስን እና ቀይ ባሕርን ለደህንነቷ እንደ ዋና መሠረት አድርጋ ተመልከታቸዋለች።ኢትዮጵያ፣ በዓባይ ወንዝ ላይ ያለች ትልቅ እና እየጎለበተች ያለች ሀገር በመሆኗ በተፈጥሮ ሀብቷ እንዳትጠቀም ሴራዋን አጠናከረች።ለዚህም ዓላማ ስኬት በሰሜን ኢትዮጵያ የተዳፈነ እሳት ማስቀመጥ ነበረባት።ኤርትራን ለመገንጠል፤ ጉዳይ ፈጻሚውን ሻዕቢያን መመስረት ግቧ አደረገች። የኤርትራ ነፃነት ግንባር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1960 በካይሮ በተሰደዱ የኤርትራ ፖለቲከኞች እና ተማሪዎች ተመሠረተ። በዚህ ሂደት ግብፅ የኤርትራ የመገንጠል እንቅስቃሴ እንዲፋጠን ፖለቲካዊ ምህዳር የፈጠረች ሲሆን፣ የግብፅ ሚዲያዎች ደግሞ ለእዚህ እኩይ ዓላማ የሚያግዝ ፕሮፓጋንዳ አሰራጮች ነበሩ። በዚህ አሰላለፍ ውስጥ ሻዕቢያ የግብፅ ዋና ስትራቴጂካዊ መሳሪያ ሆኖ አገልግሏል። ግብፅ ለሻዕቢያ አስፈላጊውን ወታደራዊ፣ የገንዘብ እና የዲፕሎማሲያዊ ሽፋን በመስጠት በሰሜን ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ለተካሄደው ውጊያ ስንቅ እና ትጥቅ እንዲያገኝ አድርጋለች። የኤርትራ መገንጠል ዋነኛ ውጤት ኢትዮጵያ ታሪካዊ የባህር በሮቿን አጥታ የተዘጋች ሀገር እንድትሆን ማድረግ ነበር። ይህ ደግሞ የግብፅን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ያሳካ እርምጃ ሆኗል። ለዚህ እኩይ ዓላማ ለተወለደው ቡድን ደግሞ ቀጥተኛ የገንዘብ፣ የወታደራዊ እና የስልጠና ድጋፍ የመስጠት ፖሊሲን ተከትላለች።በግብፅ ስሌት፣ ለእንደዚህ ዓይነቶቹ አካላት የሚደረገው ድጋፍ በተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታት ላይ ጫና ለመፍጠር ይረዳል የሚል ነው።በመጠኑ የተሳካለት ቢመስልም ያሰበችውን ማግኘት አልቻለችም።ብርቱዋ ኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አሳክታ አጀንዳዋን ቀይ ባህር ላይ አድርጋለች። ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ፖለቲካዊ ጫና እንደ ጠቃሚ መንገድ አድርጋ ቀጠለችበት። ግብፅ ከሻዕቢያ ባለፈ ለሀገር ውስጥ ታጣቂዎች ድጋፍ በመስጠት የተወሰኑ የትንኮሳ ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ ረድታለች። አስመራ በታሪክ በተረጋገጠ መልኩ የፀረ-ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎች ሁሉ መነሻ እና ማዕከል ሆና አገልግላለች። ስውሩ ጣልቃ ገብነት ኢትዮጵያ ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን መተግበር እንዳትችል አደረጋት። የተረጋጋች ኢትዮጵያን እውን ከማድረግ አንጻር የራሱን መጥፎ ጠባሳ ጥሎ አልፏል። አሁንም ግብጽና ሻዕቢያ በቀረጹት ኢትዮጵያን የማዳከም ሥራ ላይ ሕገ-ወጡ ሕወሓት በዋና ተላላኪነት እና ጉዳይ ፈጻሚነት ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ሕወሓት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በሻዕቢያ የፖለቲካ እና የወታደራዊ ሥልጠና ሲያገኝ ነበር።ሕወሓት ሥልጣን በያዘበት ወቅት፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ የባሕር በር ባለቤትነት መብት ከሕግ አግባብ ውጭ አሳልፎ በመስጠት የሻዕቢያን እና የግብፅን ዓላማ በተሻለ መልኩ አሳክቷል። ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ ምክንያት በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለወደብ ኪራይ እንድታወጣ ተገዳለች። ይህም የኢኮኖሚ እድገቷን የገታ እና ለውጭ ጥገኝነት የዳረጋት ዋነኛ ምክንያት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ አካባቢ ኢትዮጵያ የነበራትን ታሪካዊ እና ስትራቴጂካዊ የበላይነት እንድታጣ አድርጓታል። የውስጥ አለመረጋጋት እና ጦርነቶች ዓባይን ጨምሮ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶቿን በጊዜው እንዳትጠቀም እንቅፋት ሆነው ቆይተዋል። አሁንም ቢሆን ግብፅ ከኢትዮጵያ አልፋ የአፍሪካ ቀንድን ወደ አንድ ግዙፍ የጦር ሜዳ ለማሸጋገር ለሚሰሩ ወገኖች ይፋዊ ወታደራዊና የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ በመስጠት ቀጣናዊ ስጋት መደቀኗን ቀጥላበታለች።] ኢትዮጵያ ለዘመናት በወራሪዎችና በውጭ ተጽዕኖዎች ሳትንበረከክ ሉዓላዊነቷን አስከብራ የኖረችበት ምስጢር፣ ታሪካዊ ጥንካሬዋንና የሕዝቦቿን አንድነት መሠረት ባደረገ ጽናት ነው። ግብፅ የኢትዮጵያን ግዛት ለመያዝ ያደረገቻቸው ተደጋጋሚ የወረራ ሙከራዎች በጉራዕና በጉንደት አውደ ውጊያዎች በኢትዮጵያውያን ጀግንነት ተመክተዋል። በተመሳሳይ መልኩ በዓለም አቀፍ መድረኮች፣ በወገንተኛ ሚዲያዎችና በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ለዘመናት ሲሰራጩ የቆዩ ሀሰተኛ መረጃዎችና የሳይኮሎጂካል ጦርነቶች በኢትዮጵያ እውነተኛ ዲፕሎማሲ ተሸንፈዋል ። አሁንም የግብፅና የኤርትራ (የሻዕቢያ) ወቅታዊ ስትራቴጂካዊ አሰላለፍም ሆነ የሕወሓት ተላላኪነት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጊዜያዊ ፈተናዎች ሆነው የሚያልፉ አኩይ ተግባራት እንጂ የኢትዮጵያን የሺህ ዓመታት የሀገርነት መሠረት ሊያናጉ አልቻሉም። ከዚህ አኳያ ያለፈውን ታሪክ በጥልቀት መረዳት፣ የታሪካዊ ጠላቶችን ሴራ መገንዘብና የጥፋት አሰላለፎችን ማወቅ የዛሬዋንና የነገዋን የበለጸገችና የተከበረች ኢትዮጵያ ለመገንባት፣ ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ወሳኝና መተኪያ የሌለው መንገድ ነው። ኢትዮጵያ ለታሪካዊ ጠላቶቿ በየትኛውም መልኩ የማትንበረከክ ጽኑ አገር መሆኗን ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም ታረጋግጣለች!
የኢትዮጵያ ከተሞች ትንሳኤ
Oct 1, 2026 172
በመጽሔት አንለይ ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ ሰንቃ እየተጋች የምትገኝ የገናና ሥልጣኔና የታሪክ ማኅደር፣ የቱባ ባህልና የሕብረብሔራዊ አንድነት ካስማ ናት። በክትመትና ከተሜነት ሥልጣኔም የሺህ ዘመናት የሥልጣኔ ዐሻራ በጉያዋ ታቅፋለች። የከተሜነት አመጣጥ የሁሉም ክፍለ አህጉራት አባል ሀገራት የጋራ ታሪክ ነው። አፍሪካም ከጥንት ጀምሮ የተደራጁና የደረጁ የከተማ ሥልጣኔዎች የታሪክ መናኸሪያ መሆኗን ድርሳናትና መዛግብት ያስረዳሉ። ጥንታውያኑ የአክሱም፣ ጎንደርና ሐረር በኢትዮጵያ፤ ቲምቡክቱ፣ ካኖና ኦዮ በምዕራብ አፍሪካ፤ ግሬት ዚምባብዌ በደቡብ አፍሪካ፤ ኪልዋና ሞምባሳ በሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ የአፍሪካ ከተሜነት ሥልጣኔ ረጅም ታሪክ እንዳለው አስረጂዎች ናቸው። በአሁኑ ወቅትም አፍሪካ የዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን ቀልብ የሚስቡ ማራኪ፣ ውብና ጽዱ ገጽታን የተላበሱ ከተሞችን መገንባቷን ኪጋሊ፣ ራባት፣ ኮቶኑ፣ ታንጀር፣ ማራካሽ፣ አቡጃ፣ ጋቦሮኔ፣ ዊንድሁክ፣ ኬፕ ታውን እና መሰሎችም ሁነኛ አብነቶች ናቸው። በአፍሪካ ከተማና የከተሜነት ሥርዓትና ምኅዳር ከጉስቁልና ወደ ተሻለ የልዕልና መንገድ የሚያመራበት ከፍተኛ ዕድል አለው። ይህም የአህጉሪቷ የከተማ ሕይወት በተሰናሰለ መሰረተ ልማት የሚመራና ብሩህ ተስፋ ያለው መሆኑን ያስረዳል። ኢትዮጵያ፤ የጥንታዊ ሥልጣኔ ዐሻራ ያረፈባቸው ከተሞች ሀገር!! የኢትዮጵያ የከተሜነት ዐሻራ ከጥንታዊ የሥልጣኔ ታሪኳ ጋር ተሰናስሎ የቀጠለና ያልተቋረጠ ሂደት ነው። አክሱም የንግድና የሥልጣኔ ማዕከል፣ ሐረር የንግድ፣ የባህልና የኃይማኖት መናኸሪያ ሆና ቆይታለች። ጎንደር ደግሞ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ አስተዳደር ማዕከል ሆና በማገልገል ታሪክ ሰርታለች፤ ሰንዳለችም። አዲስ አበባ ደግሞ በዘመናዊ ኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ማዕከል በመሆን የኢትዮጵያ ዘመናዊ የከተሜነት ጉዞን መርታለች፤ እየመራችም ይገኛል። የከተማ ዕድገት ፈጣን ሲሆን ተጓዳኝ ጫናዎችም ይመጣሉ። የዓለም ባንክ በአዲስ አበባ ላይ ያደረገው የከተማ ጽናት ጥናት ፈጣን የከተማ ዕድገት ከጎርፍ፣ ከውሃ እጥረት፣ ከትራንስፖርት፣ ከሥራ አጥነትና ከማህበራዊ ተጋላጭነት ጋር የሚያያዙ ጫናዎችን እንደሚያመጣ ያመለክታል። ከዓመታት በፊትም አዲስ አበባና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች በመሰረተ ልማት ክፍተትና በእርጅና ብዛት የሚያቃናቸውን የለውጥ አብዮት ሲጠባበቁ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። በዚህም የኢትዮጵያ የከተማ ትንሳኤ ትርጉሙ የከተሞችን ፊት በማስዋብ ብቻ የተወሰነ እንዳልሆነ መመልከት ይቻላል። የኑሮ ጥራትን፣ ምርታማነትን፣ የሥራ ዕድልን፣ የመጓጓዣ ቅልጥፍናን፣ የአካባቢ ጥበቃንና የሕዝብ ተሳትፎን አስናስሎ የሚጓዝ ሂደትን መፍጠር ይጠይቃል። ከቢሮ ጽዳትና ውበት ወደ የኢትዮጵያ ከተሞች የትንሳኤ ብስራት፤ ከእርጅና ወደ ልዕልና!! በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የመደመር መንግሥት በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጡ ማግስት ጽዳትና ውበት ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ይገባል የሚል ጽኑ አቋምን አብስሯል። በዚህም በመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቢሮ ዕድሳት ማራኪ የሥራ ከባቢን መፍጠር አስችሏል። በቢሮ ዕድሳት የተመዘገበው እመርታዊ ውጤትም የኢትዮጵያ ከተሞችን የውበት አክሊል የሚያጎናጽፍ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት የሚገነባበትን ዕድል ፈጥሯል። ይህም የኢትዮጵያ ከተሞችን በማፍካት የከተሜነት የአኗኗር ምኅዳር ዝማኔን የውበት አክሊል አቀዳጅቷል። ይህ ለውጥም የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት የተደራሽነት አድማስን በበርካታ ከተሞች የኮሪደር፣ የፓርኮች፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች፣ የቅርስ ጥበቃና ማራኪ የሕዝብ መዝናኛ ግንባታ በማስፋፋት የኢትዮጵያን ልክና መልክ ገልጠዋል። የአዲስ አበባ የገበታ ለሸገር ፕሮጀክቶች፣ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እመርታም የሕዝብን የከተሜነት የአኗኗር ሥርዓት ከከተማ ሕይወት ጋር የማስተሳሰር ተምሳሌቶች ናቸው። በክልሎችም ተመሳሳይ የከተማ ውበት፣ የቱሪዝም፣ የቅርስና የሕዝብ መዝናኛ ሥፍራዎች ልማት በስፋት ተከናወነዋል፤ እየተከናወኑም ነው። የዚህ ሂደት ዋና እሴት ውበት ብቻ እንዳልሆነ ያሳያል። የተሻለ የከተሜነት ምኅዳር ምቹ የንግድ፣ ቱሪዝም፣ መዝናኛ፣ ማህበራዊ ትስስርና የከተማ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በመፍጠር ጉልህ አስተዋጽኦ አለው። ይህም የከተሞችን የኢኮኖሚ መነቃቃት የሚያሳልጥ የመሰረተ ልማት ግንባታና የሥራ ዕድል ፈጥሯል። ገበታ ለሸገር ከገለጣት አዲስ አበባ የተሻገረው፤ የገበታ ለሀገርና ለትውልድ እመርታ!! የኢትዮጵያ ከተሞች ለውጥ ዘላቂ የከተሜነት ሽግግርን የማፋጥን መሰረት እየጣለ ይገኛል። የአዲስ አበባን ልማት ከክልል ከተሞች፣ የከተማ ልማትን ከገጠር ምርት፣ ቱሪዝም ከቅርስ ጥበቃ፣ የሕዝብ መዝናኛ ሥፍራን ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር አሰናስሎ ማስቀጠልም ቀጣይነት ያለው ሥራን ይጠይቃል። በዚህ አቅጣጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ በተሰኙት የልማት ሐሳቦች የተገነቡ ማራኪ የልማት ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ፣ የባህል፣ የቱሪዝምና የሕዝብ መዝናኛ ሃብቶችን ወደ ኢኮኖሚያዊ እሴት መቀየር ያስቻሉ ናቸው። በአዲስ አበባ በገበታ ለሸገር የተገነቡት የአንድነት፣ ወዳጅነትና የእንጦጦ ፓርኮች የመዲናዋን ስምና ግብር ከገለጡት የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር ተዳምረው ማራኪ የመስህብ መዳረሻ ምኅዳርን ፈጥረዋል። ይህም የከተማ ልማት ከውበት ወደ ምርታማነት መሻገሩን የሚያሳይ ወሳኝ ብስራት ነው። በገበታ ለሀገር የተገነቡት የጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ሐላላ ኬላ፣ ኮይሻና ሌሎች የኢኮኖ ቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎችም የኢትዮጵያን ጥንታዊ የከተሜነት ሥልጣኔ ከዘመናዊ የዓለም ከተሜነት ጋር ያሰናሰሉ የልማት ብስራቶች ናቸው። ፕሮጀክቶቹም የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም በተግባር አስመስክረዋል። የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶችም የተገነቡት የሎጎ ሐይቅ፣ ዓርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት፣ ኒን ሊ ፓልም ስፕሪንግ ሎጅ፣ የሸበሌ ሪዞርት፣ ደንዲ ኢኮ-ሎጅ እና ሌሎችም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የቱሪዝም ዘርፍ የማንሰራራት ጉዞ በማነጽ የብልፅግናን ብርሃን ፈንጥቀዋል። የከተማ እመርታ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኘዎችን የስበት ማዕከል እንደሚያደርግ ሁሉ፤ የተደራጀ ከተማም የተመቻቸ የንግድና ኢንቨስትመንት ምኅዳርን በመፍጠር የምርታማነት አቅም ያጎለብታል። የከተማ መሰረተ ልማት ደግሞ ምርታማነትን ያሳድጋል። ሦስቱ ሲጣመሩም ከተማ የኢኮኖሚ ሞተር ትሆናለች። የኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት ሕልም!! የከተሞች ትንሳኤ የሚለካው በአዲስ እሳቤ ተሰናስለው በሚገነቡ መሰረተ ልማቶች መሆኑ እሙን ነው። የከተማ ልማት ሲቀጥል ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት፣ ውሃና ፍሳሽ፣ የቆሻሻ አያያዝ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት፣ አረንጓዴ ስፍራ፣ የአካባቢ ጽናትና የሥራ ዕድል ፈጠራን አብረው መሄድ አለባቸው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ2025 የከተማ ትንበያም የከተማ ልማትን ከሁሉን አቀፍ፣ አስተማማኝ፣ ጽኑና ዘላቂ የከተማ ሕይወት ጋር አቆራኝቶ መምራት እንደሚስፈልግ ያመላክታል። ይህም ለኢትዮጵያ ከተሞችን ማስዋብ እና መሰረተ ልማትን ማስፋፋት አንዱ ክፍል ሲሆን፤ የከተማን ኢኮኖሚ ማሳደግ፣ ሥራ መፍጠር፣ ለዜጎች የተሻለ የኑሮ ዕድል መፍጠርና የከተሞችን የወደፊት እጣ ፋንታ የሚወስን ሽግግርን የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ትምህርት ይሰጣል። ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ከተሞች የነገ ሽግግራቸውን የሚያፋጥን ምቹ መደላድል ፈጥረዋል። የኢትዮጵያ ከተሞች ትንሳኤ፤ ከእርጅና ወደ ልዕልና የዓለም ከተሞች የሚያመሳስላቸው አንድ የታሪክ እውነት አለ። ከተማ በአንድ ቀን የሚገነባ ሳይሆን በትውልድ ቅብብሎሽ በሚደረግ የዕውቀት፣ የሥራ፣ የዕቅድና የፈጠራ ሥራ የሚቀጥሉ ናቸው። ኢትዮጵያም ከአክሱም እስከ ጎንደር፣ ከሐረር እስከ አዲስ አበባ ረጅሙ የከተሜነት ታሪክ አላት። ዛሬ የተከፈተው አዲስ ምዕራፍም የአረጁና የኮሰመኑ ከተሞች አዲስ የከተሜነት ቅርፅና መልክ የሚይዙበትን ዕድል ፈጥሯል። ይህም አዳዲስ ከተሞችን በተቀናጀ ዕቅድ በመገንባት ከተሞችን የኢኮኖሚ ዕድገት ሞተር እያደረገ ነው። በዚህም በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች ድሬ ዳዋ፣ ሐረር፣ አዳማ፣ ባሕር ዳር፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ አርባ ምንጭ፣ ሐዋሳ፣ ሶዶ፣ ጅግጅጋ፣ አሶሳ፣ ነቀምትና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችን ከእርጅና ወደ ልዕልና የተሸጋገሩበትን ወርቃማ ዕድል ፈጥሮላቸዋል። የአዲስ አበባ፣ የጎንደር አብያተ መንግሥታት፣ የጅማ አባጅፋር ቤተ-መንግሥትና ሌሎች ከተሞች የቅርስ ዕድሳቶችም ታሪክን ለትውልድ በማሻገር ከተሞቹን ተደማሪ የውብት አከሊልን አቀዳጅቷል። የከተሞቹ የኮሪደር ልማትም ከእርጅና ወደ ልዕልና የሚለው ሐሳብ የከተሞችን የቆዩ መዋቅራዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ ችግሮች በአዲስ ዕይታ የመፍታት የሽግግር ተምሳሌት ነው። የኢትዮጵያ ከተሞች ዛሬ የሚገኙበት የለውጥ ሂደትም በዚህ ሰፊ የዓለም የከተሜነት ጉዞና ሥልጣኔ የሚታይ ነው። ጥንታዊ የከተሜነት ሥልጣኔን የወረሰች ኢትዮጵያም የወደፊቱን የከተሜነት ምኅዳር በዕውቀት፣ ፈጠራ፣ መሰረተ ልማት፣ በባህልና በሰው ኃይል መቅረፅ የሚያስቻለትን መሰረት በመጣል ወሳኝ አቅም ገንብታለች።
ልዩ ዘገባዎች
የግብፅ የሴራ ፖለቲካ ውድቀት እና ያከተመለት የቅኝ ግዛት እሳቤ
Oct 1, 2026 225
ኢትዮጵያ እና ግብፅ በአንድ በማይለወጥ ተፈጥሯዊና ጂኦግራፊያዊ እውነታ ለዘመናት የተሳሰሩ ሀገራት ናቸው፤ ይኸውም ከኢትዮጵያ ተራራዎች የሚፈልቀው ታላቁ የዓባይ ወንዝ ነው። ነገር ግን ግብፅ ለዘመናት ከተከተለችው የተዛባና ራስ ወዳድነት የሰፈነበት የዓባይ ወንዝ አጠቃቀም አኳያ አንድ መሠረታዊ እና ፍትሃዊ ጥያቄ ግንባር ቀደም ሆኖ ይነሳል፦ የውሃው ምንጭ ባለቤት የሆኑት ኢትዮጵያውያን ተፈጥሯዊ ሀብታቸውን እንዳይጠቀሙና ከድህነት እንዳይወጡ የማገድ መብት ለግብፅ ማን ሰጣት? ይህ ጥያቄ የውሃ ክፍፍል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ ግብፅ በቅኝ ግዛት ዘመን የተገኙ ኢ-ፍትሃዊ ጥቅሞችን ለማስቀጠል ስትል የኢትዮጵያን የመልማት መብት ለማካድ የምትከተለው አሉታዊና አጥፊ ሴራ አካል ነው። ታሪክ እንደሚያሳየው ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ብቸኛ ተጠቃሚ ለመሆን በማሰብ፣ ኢትዮጵያን በወታደራዊ ጥቃት፣ በውክልና ጦርነቶች እና በድብቅ የዲፕሎማሲ ሸፍጦች ለማዳከም ስትጥር ቆይታለች። በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በኬዲቭ ኢስማኢል ፓሻ መሪነት የተካሄደውና እ.አ.አ በ1875 በጉንደት እንዲሁም በ1876 በጉራ ጦርነት የግብፅን ዕብሪት ያስተነፈሰ የታሪክ ምዕራፍ ነበር። የግብፅ ሴራዎች ከዘመን ዘመን መልክ ቢቀይሩም ዋናው ዓላማቸው ሁልጊዜም ኢትዮጵያን ማዳከም ነው፤ ግብጽ ከቀጥተኛ ወታደራዊ ሽንፈት በኋላ፣ በገማል አብዱል ናስር ዘመን (1956–1970) ስልቷን በመቀየር ወደ ስውር የጥፋት ዘመቻ ተሸጋገረች። በዚህም ዲፕሎማሲን እንደ መሳሪያ በመጠቀም፣ የኦጋዴን ግጭት በማቀጣጠል እና የኢትዮጵያን የውሃ መሠረተ ልማት ስራዎች ብድር እንዳይሰጥ ዘመቻ በማድረግ ጠላትነቷን በግልጽ አሳይታለች። የዚህ ዘመን የከፋ ሴራ ማሳያ ደግሞ እ.አ.አ በ1959 ከሱዳን ጋር ብቻ የተፈረመው ኢ-ፍትሃዊ የዓባይ ውሃ ስምምነት ሲሆን፣ እሱም ኢትዮጵያን እና ሌሎች የተፋሰሱ ሀገራትን ሙሉ በሙሉ በማግለል ወንዙን በብቸኝነት ለመቆጣጠር የተደረገ ህገ-ወጥ እርምጃ ነበር። በአንዋር ሳዳት ዘመን (1970–1981) ደግሞ ግብፅ ዓባይን እንደ የፖለቲካ መሳሪያ በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማዳከም አዲስ የጸጥታ ስጋት ፈጠረች፤ ይህም ሳዳት በኢትዮጵያ የውሃ ግድቦች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስዱ በግልጽ በማስፈራራት ራስ ወዳድነታቸውና የኃይል ፖለቲካ ፍላጎታቸውን በግልጽ አሳይተዋል። በሆስኒ ሙባረክ ዘመን (1981–2011) ግብፅ ቀጥተኛ የጦርነት አቅሟ በመዳከሙ ወደ ስውር ቀጣናውን የመክበብ አካሄድ ቀይራለች። በዚህም የታጠቁ አማጽያንን በድብቅ በመደገፍ እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፎችን በማስተጓጎል የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ ለመግታት ሴራዎችን መጎንጎኗን ቀጥላለች። ከፕሬዝዳንት አብዱልፋታህ ኤል-ሲሲ መምጣት ጋር የግብፅ ሴራ ይበልጥ እየሰፋ መጥቷል። ዲፕሎማሲን እንደ መሸፈኛ በመጠቀም፣ ወታደራዊ ጥምረቶችን በመፍጠር እና በባህር ዳርቻዎች ኃይል በማሰባሰብ ኢትዮጵያን የማፈን እና የመክበብ አደገኛ የፖሊሲ አካሄድን መከተል ጀምራለች። ግብፅ የኢትዮጵያን ልማት እንደ “ቀይ መስመር” በመፈረጅ፤ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት እና የአረብ ሊግን በመጠቀም የግድቡ ሙሌት ስራዎችን ለማስተጓጎል ጸረ-ኢትዮጵያ ጫናዎችን አድርጋለች። ነገር ግን የኢትዮጵያ ጽናት እና የልማት ቁርጠኝነት የግብፅን የከበባ እና የጥፋት ፖሊሲዎች አምክኗል፤ የዘመናት ጫናዎችና ሴራዎችንም ከንቱ አድርጓል። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታም ግብፅ የኢትዮጵያ ሃብቶችም ሆነ የህዝቦቿን የነገ እጣ ፈንታ በጉልበት መቆጣጠር እንደማትችል ያሳየ ህይው ምስክር ሆኗል። ከዚህ ረጅም የታሪክ ሂደት መረዳት የሚቻለውም፤ የግብፅ ዛቻዎች እና ማስፈራሪያዎች የዓባይ ወንዝን ዕጣ ፈንታን ሊወስኑ እንደማይችሉ ነው። ይልቁንም ለሁሉም የሚበጀው ኢትዮጵያ የውሃ ሃብቷን ተጠቅማ ድህነትን የማሸነፍ ውጥኗ ፍትሃዊ እና ማንም ሊነጥቀው የማይችል የሕልውና ጉዳይ መሆኑን በቅጡ ያስገነዘበ ሆኗል። ዛሬ ላይ በተፋሰሱ ሀገራት እየጨመረ የመጣው የህዝብ ቁጥር እና የአየር ንብረት ለውጥ በፍትሃዊነትና በትብብር እንዲሰሩ ያስገድዳቸዋል። ከዚህ አኳያ ዘላቂ ሰላምና ልማት የሚረጋገጠው ግብፅ የቅኝ ዘመን ኢ-ፍትሃዊ የይገባኛል ጥያቄዋን ስትተው እና የሁሉንም ተፋሰስ ሀገራት ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም መርህ የተቀበለ የትብብር ማዕቀፍ ሲሰፍን ብቻ ነው።
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 14002
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 22870
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15894
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
መጣጥፍ
ኢትዮጵያ እና ቡና
Sep 30, 2026 282
ኢትዮጵያ- ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ ፤ታላቅ ርዕይ በኢትዮጵያ የተገኘውና በዓለም ላይ የተስፋፋው ቡና ተቆልቶና ተፈጭቶ በብዛት የሚጠጣ ተፈለጊና ተወዳጅ ምርት በመሆን የዓለምን ገበያ ተቆጣጥሮት ይገኛል። በተለይም በማደግ ላይ ባሉ አገሮችም እስከ 25 ሚሊዮን የሚደርሱ የአርሶ አደሮች የዓለምን 80 በመቶ ቡና እንደሚያመርቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ብራዚል፣ ቪትናም እና ኮሎምቢያ ተጠቃሽ አገሮች ሲሆኑ ሌሎችም ይጠቀሳሉ። በመሆኑም የቡናን ዓለም አቀፍ ግብይትና ተፈላጊነት እንዲሁም የተጠቃሚዎች ብዛት መሰረት በማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 1 የዓለም የቡና ቀን አድርጎ ሰይሞታል። በዚሁ መሰረትም የመጀመሪያው የዓለም የቡና ቀን እ.ኤ.አ ከጥቅምት 1 ቀን 2015 ጀምሮ በመከበር ላይ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ቡና ለኢትዮጵያዊያን የገቢ ምንጭ ብሎም የባህል መገለጫ፣ የእንግዳ መቀበያ፣ የአብሮነት ማሳያ፣ የማኅበራዊ ትስስርና የውይይት መድረክም ነው። የኢትዮጵያ ቡና በልዩ ልዩ የጣዕም የሚገለጽና በእጅጉም ተፈላጊ ምርት በመሆኑ በተለይም በአርሶ አደሮች ህይወትና አጠቃላይ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ወሳኝ ድርሻ አለው። በአንዳንድ አካባቢዎች ቡና ተፈልቶ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ዙር የመጠጣት ልምድም አለ። ምንም እንኳን አጠራራቸውና ከእያንዳንዱ ዙር ጋር የሚያያዙ ትርጓሜዎች በአካባቢው ባህል መሠረት የሚለያይ ቢሆንም የመጀመሪያው “አቦል”፣ ሁለተኛው “ቶና” እንዲሁም ሶስተኛው “በረካ” እየተባለ ይጠራል። የዚህ የቡና ስነ ስርአት ዋነኛ ዓላማ በተደጋጋሚ መጠጣት ሳይሆን በአንድነት መቆየትን፣ ለሌላው ጊዜ መስጠትንና የማኅበረሰብ ትስስርን የሚያጠናክሩ የባህል ምልክቶች ናቸው። ከቡናው ጋር የሚቀርብ (የቡና ቁርስ) እንደየ ሁኔታው ፋንዲሻ፣ ቆሎ፣ ዳቦ ወይም ሌሎች ቀለል ያሉ ምግቦች የሚቀርቡ ሲሆን እጣን አጭሶ በመመራረቅ የሚጠጣም ይሆናል። በዘመናዊው ዓለም ቡና የንግድ፣ የሥራና የመዝናኛ አካል ሆኗል። በቡና ቤቶች፣ በሥራ ቦታዎችና በዘመናዊ የቡና ማቅረቢያ ሥፍራዎች ሰዎች ይገናኛሉ። ሆኖም በኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ሥነ ሥርዓት ውስጥ ያለው ልዩ ትርጉም ከጣዕምና ከንግድ በላይ ይዘልቃል። ከቤት እስከ ጎረቤት ፤ ከታሪክ እስከ ትውልድ የቆየ ትስስር ያለው የኢትዮጵያን ልዩ መገለጫ ባህል ነው። የቡና ባህላዊ ሥነ ሥርዓትን በማስተዋወቅ እንዲሁም የቡና ታሪክን ከተፈጥሮ ሃብት ጋር አጣምሮ በማሳየት የሀገሪቱን ባህላዊ ቅርስ ለዓለም ማስተዋወቅ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ቡና የባህል ይዘቱ እንዳለ ሆኖ ለሀገሪቷ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ በመሆን ለእድገትና ማንሰራራት ሁነኛ መሰረት እየሆነ ይገኛል። የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የቡና ቀን የቡና ዘርፍ ለዘላቂ ልማት የሚኖረውን አስተዋጽኦ በማድረግ “ቡና የዘላቂ መፍትሄ አካል” በሚል መሪ ሃሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ በነገው እለት የሚከበር ይሆናል።
የሰውና የተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ
Sep 29, 2026 205
ጋምቤላ ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የሰውና የተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ የጋምቤላ ክልል በሰፊ የተፈጥሮ ሀብት፣ የውሃ ሀብት፣ ደኖች፣ የሣር ምድሩና በዱር እንስሳትና ብዝሃ ሕይወት እምቅ ሃብት ያለው መሆኑ ይታወቃል። የአኙዋሃና የማጃንግ የተፈጥሮ ሃብቶች ለልዩ የቱሪዝም መስህቦች ሆነው ይጠቀሳሉ። በተለይም ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ በሰፊ የሳር ሜዳዎች፣ በውሃ አካላትና በተለያዩ የዱር እንስሳት የበለፀገ የተፈጥሮ ሀብት ነው። የዱር እንስሳት ጉብኝት፣ የአዕዋፍ እይታ፣ የተፈጥሮ ጉዞና አጠቃላይ የኢኮ-ቱሪዝም ሃብት ፓርኩ የታደለ ነው። በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወንዞችና ረግረጋማ መሬቶች፣ የደን ሃብት ከሰዎች አኗኗርና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ጋር በማሰናሰል የቱሪዝም ሃብት ማድረግ ተችሏል። በመሆኑም ጋምቤላ ያለውን የተፈጥሮና የባህል እምቅ ሃብት በዘላቂነት በማልማት፣ የተፈጥሮ ጥበቃን ከቱሪዝም ልማት ጋር በማስተሳሰር ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት አዲስ አቅም መፍጠር እየተቻለ ነው። የባዮስፌር ሪዘርቭ ዋና ዓላማ ተፈጥሮን ከሰው ልጅ የኢኮኖሚና የኑሮ ሁኔታ ጋር በማጣጣም የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ፣ የዘላቂ ልማትና የምርምር ከባቢን መፍጠር በመሆኑ በዚሁ መሰረትም የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ እና የማጃንግ የተፈጥሮ ደን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ሊመዘገብ ችሏል። የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሰፊ ምድር ያካለለ ሲሆን በውስጡ በርካታ የዱር እንስሳትና የዕፅዋት ዝርያዎች ይገኛሉ። በጥብቅ ደኑ ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ የዕፅዋት፣ ከ327 የሚልቁ የአእዋፍ፣ ከ86 በላይ አጥቢና ተሳቢ የእንስሳት ዝርያዎች መኖራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ የተፈጥሮ ሃብት ብቻ ሳይሆን የሰውና ተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ፣ የዱር እንስሳት ሃብት ኮሪደር እና የዘላቂ ልማት ማዕከል ነው ማለት ይቻላል። የአካባቢው ሕዝብ ከተፈጥሮው ጋር ተስማምቶ በመኖር የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅና ለትውልድ ጠብቆ በማቆየት ረገድ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነው። በ225 ሺህ 490 ሄክታር ላይ የተንጣለለው የማጃንግ የተፈጥሮ ደንም በውስጡ 550 የዕፅዋት ዝርያዎች፣ 33 የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎች እንዲሁም 130 የአእዋፍ ዝርያዎች እንዳሉት መረጃዎች ይጠቁማሉ። ዝቅተኛና ከፍተኛ መልክአ ምድርን አካቶ የያዘው ጥብቅ የተፈጥሮ ሃብቱ በተለይም ለንብ ማነብና ለፍራፍሬ ልማት እጅግ ተመራጭ አካባቢ ነው። የጋምቤላ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ ለምግብ ዋስትና እንዲሁም ለቱሪዝም ዘርፉ ወሳኝ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።