በትግራይ ክልል አዲስ ጊዜያዊ አስተዳደር በማዋቀር በወራት ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ እየተሠራ ነው - አብረሃም በላይ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
በትግራይ ክልል አዲስ ጊዜያዊ አስተዳደር በማዋቀር በወራት ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ እየተሠራ ነው - አብረሃም በላይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል ፈጣን ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት ሕዝቡ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበትን አዲስ መዋቅር እየዘረጋ መሆኑን አብረሃም በላይ (ዶ/ር) ገለጹ።
አብረሃም በላይ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ በአሁኑ ወቅት የመከላከያ ሠራዊት ክልሉን ከሕገ-ወጥ ኃይሎች እያጸዳ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ይህንን ተከትሎም ከቀበሌ ጀምሮ አዳዲስ የአስተዳደር መዋቅሮች በሕዝቡ ተሳትፎ ይደራጃሉ ብለዋል።
ይህ የሽግግር ሂደት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህ ሂደትም የትግራይ ሕዝብ የሀገራችን ልማት ተቋዳሽ እንዲሆን መላው ኢትዮጵያዊ ከፌዴራል መንግሥት ጎን በመቆም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!