የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታውን ዛሬ ያከናውናል።
ጨዋታው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል።
በአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን እ.አ.አ በ2028 በሎስ አንጀለስ በሚካሄደው 34ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ከመስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዝግጅቱን እያደረገ ነው።
ቡድኑ የዚሁ ዝግጅት አካል የሆነ የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ያደረገ ሲሆን 16 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
ሁለቱ ቡድኖች ከጨዋታው በፊት የመጨረሻ ልምምዳቸውን ትናንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አከናውነዋል።
ኢትዮጵያ የሁለተኛ ዙር የ2026 የሎጅ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ጨዋታዎቿን ከሩዋንዳ ጋር መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።