ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ የቀጣናው የታዳሽ ኃይል ማዕከል

ኢትዮጵያ በውሃ፣ በንፋስ፣ በፀሐይ እና በጂኦተርማል ሀብቶቿ ለታዳሽ ኃይል ልማት እጅግ ግዙፍ አቅም ያላት ሀገር ስትሆን፤ የመደመር መንግስት ይህንን የተፈጥሮ ጸጋ በብቃት በመጠቀም የኢትዮጵያን የኢነርጂ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ታላላቅ ሥራዎችን አከናውኗል።

በዚህ ረገድ የመደመር መንግስት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከማጠናቀቅ ባሻገር ሌሎች የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በማልማት ረገድ ያከናወነው ስራ ተጠቃሽ ነው።

ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማቷን ከራሷ አልፎ ለጎረቤት አገራት በማዳረስ ቀጣናውን በኢነርጂ የማስተሳሰር ስትራቴጂካዊ ሚናዋን በተግባር እያሳየች ትገኛለች። እንደ ሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኬንያ ላሉ አገራት የሚደረገው የኤሌክትሪክ ሃይል ንግድ የምስራቅ አፍሪካን አገራት በኢነርጂ በማስተሳሰር በጋራ ማደግ እንደሚገባ ያሳየ ነው።ይህ የሃይል ትብብር የአፍሪካን አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና እውን ለማድረግ እና በቀጣናው የኃይል ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሰረት ሆኖ ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም