ቀጥታ፡

በዲጂታል ዘመን የግለሰብ መረጃ እና የዜጎችን እምነት ለመጠበቅ ዳታን በአግባቡ መንከባከብ ወሳኝነት አለው

አዲስ አበባ ፤መስከረም 20/2019 (ኢዜአ) ፦ በዲጂታል ዘመን የግለሰብ መረጃ እና የዜጎችን እምነት ለመጠበቅ ዳታን በአግባቡ መንከባከብ ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ገለጸ።

ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ጋር በመተባበር በግል ዳታ ጥበቃ ዙሪያ ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።


 

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሚሊዮን ኃይለሚካኤል በዲጂታል ዘመን የግላዊነትንና የዜጎችን እምነት ለመጠበቅ ዳታን መንከባከብ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

እንዲሁም የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 1321/2016 መረጃን በኃላፊነትና በግልጽነት ለማስተዳደር ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ መዘርጋቱን ገልጸዋል።

ጠበቆችም የደንበኞቻቸውን መረጃ በሥራቸው የሚይዙ በመሆናቸው በዘርፉ ትልቅ ባለድርሻ አካል መሆናቸውን አስረድተዋል።

አቶ ሚሊዮን አያይዘውም የተገኘው ግንዛቤ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ወደ ተግባር ሊለወጥ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ደረሰ በበኩላቸው ጠበቆች የደንበኞቻቸውን ምስጢራዊ መረጃ በሕጉ መሠረት መጠበቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ጠበቆች ሕጉን ከማክበር ባለፈ ደንበኞቻቸው የግል ዳታ ጥበቃ ሕጉን እንዲያከብሩ የሙያ ማማከር ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም