የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በቢሾፍቱ በድምቀት እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በቢሾፍቱ በድምቀት እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2019 (ኢዜአ)፦የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በቢሾፍቱ መልካ አርሰዴ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች የምርቃት ስነስርዓት የተጀመረ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በሀርሰዴ መልካ የኢሬፈና (የምስጋና) ስነስርዓት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ሁሉን ነገር ለፈጠረ አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም እንዲሆን ፈጣሪን የሚለመንበት በዓል ነው፡፡