ቀጥታ፡

አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች በሆራ ሀርሰዲ የ‘ኢሬፈና’ ሥነ-ሥርዓትን አስጀመሩ

ቢሾፍቱ፤መስከረም 24/2019(ኢዜአ)፦አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዲ የ‘ኢሬፈና’ (የምስጋና) ሥነ-ሥርዓትን በይፋ አስጀመሩ።

በዚሁ መርሃ-ግብር መሰረት አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም የበዓሉ ታዳሚዎች ወደ ሆራ ሀርሰዲ በመሄድ እርጥብ ሳርና አበባ በመያዝ የፈጣሪን ታላቅነትና በጎነት የሚያስቡበትን የ‘ኢሬፈና’/ምስጋና ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀምረዋል።

ይህንንም ተከትሎ ከየአቅጣጫው የተወጣጡ በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በኦሮሞ ማህበረሰብ ውብ ባህላዊ አልባሳት አጊጠው፣ የሰላም፣ የፍቅርና የእርቅ ምልክት የሆኑ ባህላዊ እሴቶችን በማንጸባረቅ የ‘ኢሬፈና’ (ምስጋና) ሥነ-ሥርዓቱን በደመቀ ሁኔታ በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም