ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሲሸልስን በድጋሚ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ

አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ባደረገው ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ሲሸልስን 10 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳግማዊ ሰለሞን ሁለት በጨዋታ እና አንድ በፍጹም ቅጣት ምት በአጠቃላይ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች።

እሙሽ ዳንኤል ሁለት ጎሎችን ከመረብ ላይ ስታገናኝ ቱሪስት ለማ፣ ቤተልሄም መንተሎ፣ ቤተልሄም በቀለ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ እና የሲሸልሷ አሻንታ ማሪ በራሷ ላይ ቀሪዎቹን ጎሎች ለሉሲዎቹ አስቆጥረዋል።

ሀገራቱ ከቀናት በፊት ባደረጉት የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ 16 ለ 0 ማሸነፏ የሚታወስ ነው።

በቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በሁለቱ ጨዋታዎች 26 ጎሎችን በማስቆጠር የበላይነቱን አሳይቷል።

ብሔራዊ ቡድኑ በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅት ላይ ይገኛል።

የወዳጅነት ጨዋታዎቹም የዚህ ዝግጅት አካል ናቸው።

ኢትዮጵያ የሁለተኛ ዙር የ2026 የሎጅ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ጨዋታዎቿን ከሩዋንዳ ጋር መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም