ቀጥታ፡

‎ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማተራመስ የፈጠሩት ጥምረት እየመከነ ነው - አብረሃም በላይ (ዶ/ር)


አዲስ አበባ፣ መስከረም 23/ 2019 (ኢዜአ) ፦የውጭ ጠላቶች እና የውስጥ ባንዳዎች ተናበው ኢትዮጵያን ለማተራመስ የፈጠሩት ጥምረት በጸጥታ ኃይሎች እየመከነ መሆኑን አብረሃም በላይ (ዶ/ር)።
‎
‎አብረሃም በላይ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት፤  ኢትዮጵያ በትርምስ ውስጥ እንድትቆይ የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶች ተናበው በመስራት ላይ ናቸው።
‎
‎የኢትዮጵያ ጠላቶች ከውስጥ ባንዳዎች ጋር በመቀናጀት የከፈቱት ጥቃት በመከላከያ ሠራዊት እየተቀለበሰ መሆኑን አብራርተዋል።
‎
‎ኢትዮጵያ አቅሟ እንዳይዳብር እና ጠንካራ እንዳትሆን የሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች፣ በተለይም የኤርትራ (ሻዕቢያ) መንግሥት ከህገ ወጡ ሕወሃት እና ከሌሎችም ጸረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ትጥቅ በማስታጠቅ እና ሠራዊት በማዝመት በጦርነቱ በቀጥታ መሳተፋቸውን ጠቁመዋል። 

‎
‎ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ የጸጥታ ተቋማት ባላቸው ከፍተኛ ወታደራዊ ዲሲፕሊን፣ የቴክኖሎጂ አቅም እና ዝግጁነት የጥፋት ኃይሎቹን ተልዕኮ እያመከኑ ነው ብለዋል። 
‎
‎በተለይም የትግራይ ሕዝብ የቡድኑን የጥፋት መንገድ በመገንዘብ ጀርባ የሰጠው በመሆኑ፣ የጥፋት ጥምረቱ ዓላማ ሊሳካ አለመቻሉ አብራርተዋል።
#ትልቅ_ሀገር  #ትልቅ_ህዝብ  #ታላቅ_ርዕይ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም