አርእስተ ዜና
የጤና ተቋማትን ንጽህና መጠበቅ ከንቅናቄ ባሻገር የዘወትር ተግባር መሆን አለበት -ዶክተር መቅደስ ዳባ
May 7, 2024 65
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016(ኢዜአ)፦ የጤና ተቋማትን ንጽህናን መጠበቅ ከንቅናቄ ባሻገር የዘወትር ተግባር ሊሆን እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትሯ የ "ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና" ንቅናቄ አካል የሆነውን ጽዱ የጤና ተቋማትና አካባቢን የመፍጠር ንቅናቄ በአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በጴጥሮስ ጻውሎስ ሆስፒታል ተገኝተው በይፋ አስጀምረዋል።   ዶክተር መቅደስ ዳባ ንቅናቄውን ባስጀመሩበት ወቅት ፤ የንጽህና ጉድለት ኢትዮጵያን ጨምሮ የታዳጊ አገራት የጤና እክል መንስኤ መሆኑን በመጥቀስ የንጽህና ጉድለት ከሚስተዋልባቸው ስፍራዎች መካከል ደግሞ የጤና ተቋማት ይገኙበታል ብለዋል። እኤአ በ 2019 በተደረገ ጥናት በሆስፒታል ተወልደው በኢንፌክሽን ከሚጠቁ ህጻናት መካከል 56 በመቶው በንጽህና ጉድለት የሚጠቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ችግሩን ማስቀረት የሚቻለው ምቹ እና ንጽህናው የተጠበቀ የጤና ተቋም በመፍጠር ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ይፋ የተደረገው ንቅናቄ በህጻናትና እናቶች ላይ የሚከሰተውን የጤና እክል ለመቀነስ የጎላ ሚና እንደሚኖረው አመላከተዋል። ሚኒስቴሩ በጤናው ዘርፍ የሚተገበሩ መስፈርቶችን በመጠበቅ የላቀ ፈጻሚ ሆኖ ለመገኘት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ንጽህናው የተጠበቀ አካባቢን ለመፍጠር ስራው ከንቅናቄ ባሻገር የዘወትር ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡   የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አብርሃም እሸቱ በበኩላቸው፤የአካባቢ ንጽህናን መጠበቅ ቅንጦት ሳይሆን ግዴታ ነው ብለዋል፡፡ ሆስፒታሉ ለታካሚዎቹና ሰራተኞቹ ምቹና ጽዱ አካባቢን ለመፈጠር የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡   በንቅናቄው መታጠቢያ ቤቶች፣ የታካሚ ማቆያና ሽንት ቤቶችን የማስዋብ እንዲሁም አዳዲስ ግንባታዎች ለማካሔድ ዝግጅት መደረጉን የተናገሩት ደግሞ የአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሽመልስ ገዛኽኝ ናቸው።   ዶክተር መቅደስ ዳባ በሆስፒታሎቹ አዳዲስ መጸዳጃ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡          
የኢትዮጵያ ደምና ህብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ
May 7, 2024 51
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 29 /2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ደምና ህብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ። ከነገ ጀምሮ እስከ ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ "ደሜን እለግሳለሁ ደስታውም ሽልማቴ ነው" በሚል መሪ ሃሳብ የደም ልገሳ መርኃ ግብር በአዲስ አበባ እንደሚጀመር ተገልጿል። የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አሸናፊ ታዘበው (ዶ/ር)ና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምክትል ዋና ፀሃፊ አቶ አበራ ሉሌሳ ስምምነቱን ተፈራርመዋል። ስምምነቱ የበጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾችን ቁጥር በማሳደግና በማስተባበር የሚፈለገውን ደም ለመሰብሰብ አላማ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አሸናፊ ታዘበው (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት አገልግሎቱ 48 ቅርጫፎችን በመክፈትና አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማዘመን በቂ ደም ለመሰብሰብ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።   ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት የሚሰሩትን የበጎ ፍቃድና የሰብዓዊነት ስራ ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል። በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስና በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾችን በማስተባበር የሚፈለገውን ደም ለመሰብሰብ እንደሚያግዝ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምክትል ዋና ፀሃፊ አቶ አበራ ሉሌሳ በበኩላቸው የቀይ መስቀል ማህበር በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ጉዳት የሚደርስባቸውን ዜጎች የመደግፍና መልሶ የማቋቋም ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።   የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የሚሰራው ሰብዓዊ ስራ ከተቋማቸው ጋር የሚገናኝ በመሆኑ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ገልፀዋል። ማህበሩ በጎ ፍቃደኞ ደም ለጋሾች በንቃት እንዲሳተፉ እንዲሁም በቂ የሆነ ደም በመሰብሰብ የሰውን ህይወት ለመታደግ አበክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከነገ ጀምሮ እስከ ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ "ደሜን እለግሳለሁ ደስታውም ሽልማቴ ነው" በሚል መሪ ሃሳብ የደም ልገሳ መርኃ ግብር በአዲስ አበባ እንደሚጀመር ተገልጿል። የደም ልገሳ መርኃ ግብሩ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እንደሚካሄድ ተመላክቷል።
የታላቁ አል-ነጃሺ 00 መንደር ጅማሮ ማብሰሪያ እየተካሄደ ነው
May 7, 2024 60
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 29 /2016 (ኢዜአ)፦የታላቁ አል-ነጃሺ 00 መንደር ጅማሮ ማብሰሪያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ አደም አብዱልቃድር ተገኝተዋል፡፡ እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዘሀራ ሁመድ ፣የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የማህበራዊ ልማት ሴክሬተርያት ካቢኔ ሀላፊ ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወትና ከፍተኛ የፌዴራልና የክልሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል። በመርሀ ግብሩ የታላቁ አል-ነጃሺን ታሪካዊ ዳራ የሚያስቃኝ ዶክመንተሪ ፊልም ለእይታ ቀርቧል። የመድረኩ አላማ አልነጃሺን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለአለም ማስተዋወቅ መሆኑ ተመላክቷል። የዜሮ ዜሮ መጠርያ ሃሳቡ የመነጨው ከሸህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ሲሆን መነሻ ሃሳቡ እስልምና በኢትዮጵያ የተጀመረበትንና የታሪኩን መነሻና መገኛ ለመጠቆም መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፣ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እንዲሁም የአልነጃሺ መልሶ ግንባታና ልማት ኢኒሸቲቭ በጋራ የሚያከናውኑት መሆኑ ተገልጿል የፕሮጀክቱ አላማ በኢትዮጵያ ብሎም በአለም ትልቁ የሙስሊሞች ታሪክና ቅርሰ የሆነውንና ከመካ መዲና ቀጥሎ በአለም የእስልምና መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ የሚገኘውን ሃብት በስፋት ማስተዋወቅ ነው፡፡ በተጨማሪ በከባዱ ፈተና ወቅት ለሙስሊሞች ከለላ የሆኑት የነጃሺ መካነ ቅርስ አሻራ ባለበት በትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ ክብራቸውና ታሪካቸውን በሚመጥን መልኩ አለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የቱሪስት መንደር ለመገንባት ያለመ ነወ፡፡ በቱሪስት መንደሩ የተለያዩ ንዑስ ፕሮጀከቶች የታቀፉ ሲሆን ከነዚህም ደረጃውን የጠበቀ ሙዚየም፣ ሃላል ሆቴሎችና ሎጆች ፣የእምነት ስፍራዎች ፣ የጥናትና ምርምር ተቋማት እንደሚገነቡ ተመላክቷል፡፡ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲ ፣የቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ፣ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ፣ደረጃቸውን የጠበቁ ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት ፣ለህዝብ አገልገሎት የሚውሉ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራዎችና መሰብሰብያ አዳራሾች እንደሚኖሩት ተመላክቷል። መርኃ ግብሩ የተዘጋጀው ኢትዮጵያውያንና በአለም የሚኖሩ የታሪኩ ባለቤቶች የቦታውን ታላቅነት በማሰብ በፕሮጀክቱ ላይ በቻሉት አቅም ርብርብ እንዲያደርጉ ለማብሰር መሆኑ ተገልጿል።  
የግሉ ዘርፍ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ያለውን ሰፊ የገበያ እድል ለመጠቀም ራሱን ማዘጋጀት አለበት
May 7, 2024 61
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና የሚፈጥረውን ሰፊ የገበያ እድል ለመጠቀም የንግዱ ማህበረሰብ ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት ለማቅረብ ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ተገለጸ። የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና በሚፈጥረው ዕድል የግሉ ዘርፍ ተጠቃሚ ለመሆን ያለውን ዝግጁነት በተመለከተ የፓናል ውይይት አካሂዷል። በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የዓለም አቀፍና ቀጠናዊ ንግድ ትስስር መሪ ስራ አስፈጻሚ ታገስ ሙሉጌታ ኢትዮጵያ ለአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠናው እያደረገች ያለውን ዝግጅት አብራርተዋል።   ስምምነቱ ላይ በሚካሄዱ ድርድሮችና ስምምነቱን ለመተግበር በሚደረጉ ዝግጅቶች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ረገድ የንግዱ ማህበረሰብ የስምምነት ሂደቱን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ በመያዝ፣ ቀጠናዊ ትስስርን በማጠናከር ፣ ተአማኒነትን በማሳደግ ተወዳዳሪ ለመሆን ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል። እንደ መሪ ስራ አስፈጻሚው ገለጻ አግሮ ፉድ፣ የጨርቃጨርቅና የቆዳ ምርቶች በነጻ ንግድ ቀጠናው ተጠቃሚ ለመሆን ትልቅ አቅም ያላቸው ዘርፎች ናቸው። በጉምሩክ ኮሚሽን የታሪፍና ስሪት አገር ዳይሬክተር ካሳዬ አየለ በበኩላቸው ለአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ትግበራ በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል ያለውን ቅድመ ዝግጅት አስረድተዋል።   ምርቶች በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የስሪት ሀገር ህግ መሰረት መመረታቸውን በማረጋገጥ ሰርተፍኬት ለመስጠት የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት መሰንበት ሸንቁጤ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያላት የወጪ ንግድ ድርሻ 20 በመቶ እንዲሁም የገቢ ንግድ ምጣኔው ከስድስት በመቶ እንደማይበልጥ ጠቅሰዋል።   ከዚህ አኳያ ነጻ የንግድ ቀጠናው የሀገሪቱን ንግድ በማሳደግ ሰፊ የገበያ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል። በተጨማሪም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ፣ ካፒታል ለመሳብ፣ የቴክኖሎጂና የሙያ ክህሎት በማሳደግ አማራጭ ምርቶችን በተሻለ ዋጋ ለተጠቃሚዎች ለማቅረብና ለስራ እድል ፈጠራ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል፡፡ የንግዱን ማህበረሰብ ተወዳዳሪ ሊያደርጉት የሚችሉት ጥራት ያላቸው ምርትና አገልግሎቶች በመሆናቸው በዚሁ ረገድ የንግዱ ማህበረሰብ መዘጋጀት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም በመንግስት በኩል ጠንካራ የቁጥጥር ስርአት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን አክለዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ነጻ የንግድ ቀጠናው በሚያስገኘው እድል ለመጠቀም ራሳቸውን እያዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና እአአ በ2021 ስራ ላይ እንዲውል የጸደቀ ስምምነት ሲሆን 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ገበያ ሊፈጥር እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ።                
በቀጣይ አራት አመታት 10 ሺህ ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድ ለመገንባት እቅድ ተይዟል
May 7, 2024 60
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016 (ኢዜአ)፦ በቀጣይ አራት አመታት 10 ሺህ ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድ ለመገንባት እቅድ መያዙን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ በተለይም ሰፊ የግብርና ልማት በሚከናወንበት የገጠሩ አካባቢ የመንገድ መሰረተ ልማት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የገበያ ትስስር ለመፍጠርና የምርት አቅርቦትን ለማሳለጥ እንዲሁም ሌሎች የልማት ክንውኖችን ለማሳካትም መንገድ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። በገጠር ተደራሽነትና ትስስር ፕሮግራም የገጠር መንገድ ልማት የሚከናወን መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ከዓለም ባንክ 300 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል ብለዋል። በመሆኑም በዓለም ባንክ ድጋፍ፣ በፌዴራል መንግስትና በክልሎች ትብብር በቀጣይ አራት አመታት 10 ሺህ ኪሎ ሜትር መንገድ የሚገነባ መሆኑን ገልጸዋል። ለመንገድ ፕሮጀክቱ ክልሎች 30 በመቶ ተጨማሪ የበጀት ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚደረግ መሆኑንም ጠቁመዋል። የመንገድ ፕሮጀክቱ የምርት አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳለጥና የገበያ ትስስርን በመፍጠር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እገዛ የሚኖረው መሆኑን ሚኒስትር ዴታው ገልጸዋል። በገጠር ተደራሽነትና ትስስር ፕሮግራም መሰረት የሚከናወነው የመንገድ ልማት 128 ወረዳዎችን ከዋና መንገድ ጋር የሚያገናኝ ይሆናል። በአገሪቷ ባለፉት ስድስት አመታት 5 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ መገንባቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የሚታይ

የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ልማትና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው - የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር
May 7, 2024 58
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ልማትና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ የሁሉንም ድጋፍ ይሻል ሲሉ የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ፍሎሬንስ አዶንጎ (ዶ/ር) ተናገሩ። የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ፍሎሬንስ አዶንጎ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን ጨምሮ እያከናወነች ያለው የአካባቢ ጥበቃ ሥራ የላቀ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። የአባይ ተፋሰስ ሀገራት በየራሳቸው የአካባቢ ጥበቃ መርሃ-ግብር እያከናወኑ መሆኑን አንስተው፤ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተጠቃሽ ነው ብለዋል። በየዓመቱ በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ ለጎረቤት አገራት ጭምር ችግኞችን በመለገስ እያበረከተች ያለው አስተዋጽኦ አስደናቂ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ልማትና ተጠቃሚነትን የሚያመጣ በመሆኑ የሁሉንም ድጋፍ ይሻል ሲሉ ተናግረዋል። ኤኒሼቲቩ ተፋሰስ አቀፍ ፕሮጀክቶችን እስካሁን ገቢራዊ ማድረግ ባይችልም ሀገራት በብሔራዊ ደረጃ እያካሄዱ ያለውን የደን ልማት ያግዛል ብለዋል። የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚያከናውኗቸው የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በቀጣናው ዘላቂ የአካባቢ ስነ-ምህዳር ጥበቃ ለማድረግ የሚያግዙ መሆናቸውንም ገልፀዋል። የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ይህን ጥረት ለመደገፍ የኃብት ማሰባሰብ ሥራ የሚሰራ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሯ አረጋግጠዋል። የተፋሰሱ ሀገራት የኃይል ማመንጫ ግድቦችን ጨምሮ በተፋሰሱ የሚገነቡ የመሠረተ-ልማቶች ደኅንነትና የአገልግሎት ዘመን ለማራዘም የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ወሳኝ ስለመሆኑም አንስተዋል። በዚህ ረገድ 25 ዓመታትን ያስቆጠረው የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ በተፋሰሱ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ይሰራል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገር በቀል አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አሳድጓል- የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች
May 7, 2024 75
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አዳዲስ ሀገር በቀል አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ዘርፉን እንዲቀላቀሉ እና የማምረት አቅም እንዲጨምር በማድረግ እመርታዊ ለውጥ ማምጣቱን የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ገለጹ። " የኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉ ማነቆዎችን በመፍታትና የዘርፉን እምርታ ለማሳለጥ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ መጀመሩ ይታወሳል። የሀገራዊ ንቅናቄው ዓላማ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት፣ ለዘርፉ ዘላቂ ልማትና ተወዳዳሪነት እንዲሁም ዘርፉ ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩ ያለውን ሚና ማሳደግ ነው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ ያመጣውን ለውጥ በሚመለከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ መንግሥት በሀገር አቀፍ ደረጃ የአምራች ዘርፉን ለማሳደግ በአሥር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል። በተለይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በጥራትና በብዛት ለማምረት፣ እንዲሁም የግብርና እና የማዕድን ምርቶች ላይ እሴት ጨምሮ ለገበያ ለማቅረብ አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በማምረቻ ኢንዱስትሪው ላይ እመርታዊ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸው፤ በተለያዩ ችግሮች ማምረት አቁመው የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ምርት እንዲገቡ ማድረጉን አውስተዋል። የፋብሪካዎች ምርታማነት ማደጉን እና ትላልቅ የውጭ ኢንቨስተሮችም በማምረቻው ዘርፍ እንዲሰማሩ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል። ክልሉ ወጣቶችን በማደራጀት ከጥቃቅን እና አነስተኛ እስከ መካከለኛ ፋብሪካዎችን በመክፈት ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ማድረጉን ገልፀዋል። ክልሉ በግብርና ዘርፍ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆን የፍራፍሬ፣ ቅመማቅመም፣ ማርና እንስሳት ተዋፅኦ እምቅ አቅም ያለው በመሆኑ፤ የአካባቢው ማኅበራት እሴት የሚጨምር የምርት ማቀነባበር ሥራን ጀምረዋል ነው ያሉት። በዚህም ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፈጠሩም በላይ የኃብት ፈጣሪ ወጣቶች ቁጥር እያደገ መሆኑን ጠቁመዋል።   የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በየክልሉ የሥራና የሀገር ምርትን የመጠቀም ባህል ላይ ለውጥ ማምጣቱን ተናግረዋል። እንዲሁም መንግሥት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል በማሳደግ የምርት ጥራትና ተወዳዳሪነት እንዲጨምር ማድረጉን ገልፀዋል። በክልሉም በግብርና ምርት ማቀነባበር፣ በጨርቃጨርቅና ሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ 74 ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ተደርጎላቸው በሙሉ አቅም ወደ ማምረት መግባታቸውን ነው ያነሱት። ርዕሳነ መስተዳድሮቹ አክለውም ሁለቱ ክልሎች በተለይ በግብርናው ዘርፍ ያላቸው እምቅ የጥሬ ግብዓት ለአምራች ዘርፉ ትልቅ ዕድል መሆኑን አውስተዋል። በመሆኑም በቀጣይ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የማምረቻና የመሸጫ ቦታዎችን የማመቻቸት፣ መሠረተ-ልማቶችን የማሟላት እና የቴክኒክና የፋይናንስ አቅርቦቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል። ኢንዱስትሪው ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አበርክቶ እንዲኖረው በሥራ ላይ የሚገኙ አምራቾች ምርታማነትን እንዲያሳድጉ በመጠቆም፤ አዳዲስ አምራቾችም በዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የሁለት ዓመታት ጉዞን የሚያስቃኝ ኤክስፖ ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በኤክስፖው ላይ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ጨምሮ 230 ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ለዕይታና ለግብይት የሚያቀርቡ ሲሆን፤ የምርትና ቴክኖሎጂ ግብይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት በንቅናቄው አምራች ኢንዱስትሪውን በመደገፍ በኩል የተሠሩ ሥራዎች እና አዲሱን የኢንዱስትሪ ፖሊሲ በሚመለከት ውይይትና የማስተዋወቂያ መርሃ-ግብሮች ይካሄዳሉ።        
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 18226
ኢዜአ
ፖለቲካ
በክልሉ ልማትን በዘላቂነት ለማስቀጠል ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል-አቶ እንዳሻው ጣሰው
May 7, 2024 63
ሆሳዕና፤ ሚያዚያ 29/2016 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልማትን በዘላቂነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ። የክልሉን የሰላምና ጸጥታ ሥራ የሚገመግም መድረክ ዛሬ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በወቅቱ እንደገለጹት፣ በክልሉ ሰላምና ጸጥታ እንዲረጋገጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በቅንጅት በተሰሩ ሥራዎች ውጤት ተመዝግቧል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተረጋገጠ የመጣው ልማት የዚህ ውጤት መሆኑን ጠቁመው፣ ልማቱን በዘላቂነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በቅንጅት መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በተለይ የሰላምና ጸጥታ ሥራው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች አካላትን ማሳተፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።   የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በክልሉ ያለውን ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠል ማህብረሰቡን በማሳተፍ እየሰራ ይገኛል። በተለያየ መንገድ ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት የቅድመ መከላከል ተግባር እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል። መድረኩም በህብረተሰብ ተሳትፎ የቅድመ መከላከል ሥራውን የማጠናከር ዓላማ እንዳለው አመልክተዋል። በመድረኩ በክልሉ ባለፉት ወራት በተከናወኑ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች ላይ በጋራ በመምከር ለቀጣይ ወራት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተመላክቷል። ለአንድ ቀን በተዘጋጀው መድረክ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ መዋቅሮች እየተሳተፉ ናቸው።
ሃብታቸውን የማስመዝገብ ግዴታ የተጣለባቸው ግለሰቦች ንብረታቸውን በቴክኖሎጂ የሚያስመዘግቡበት አሰራር  እየተዘረጋ ነው
May 7, 2024 93
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016 (ኢዜአ)፦ ከመንግሥትና ከሕዝብ ሃብትና ንብረት ጋር ግንኙነት ያላቸውና የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ህግ የሚያስገድዳቸው ግለሰቦች ሃብታቸውን በቴክኖሎጂ የሚያስመዘግቡበትን አሰራር ለመዘርጋት እየሰራ መሆኑን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ፡፡ ሙስናና ብልሹ አሰራር ልማትን በማዳከም የሀገርን የኢኮኖሚ እድገት የሚጎዳ፤ የሞራልና ሥነ ምግባር ቀውስ የሚያባብስ እንዲሁም ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር የሚያደርግ አለም አቀፍ ወንጀል ነው ፡፡ በኢትዮጵያም ችግሩን ለማስወገድ የተቋቋመውና ከለውጡ ወዲህ አገራዊ የፀረ ሙስና ትግሉን በበላይነት የመምራት ተልዕኮ በአዋጅ ቁጥር 1236/2013 የተሰጠው የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ነጻና ገለልተኛ ተቋም ነው ፡፡ ኮሚሽኑ በትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታና በሙስና ቅድመ መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ፡፡ በኮሚሽኑ የጥቅም ግጭት መከላከል ዋና መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን በላይነህ ለኢዜአ እንደገለጹት በመንግስት ተቋማትና የልማት ድርጅቶች እንዲሁም በህዝባዊ ድርጅቶች የግልጽነትና ተጠያቂነት አሰራር ለማስፈን እንዲሁም ሙስናን ለመከላከል የሃብት ምዝገባና ማሳወቅ መረጃ ሚናው የጎላ ነው ፡፡ የተመዘገበው ሃብት እንደ አስፈላጊነቱ ለህዝብ ተደራሽ የሚሆንበት አሰራር መኖሩንም መቁመዋል፡፡ ኮሚሽኑ የሃብት ምዝገባና ማሳወቅ መረጃን መነሻ በማድረግ የመረጃ ትክክለኛነት የማረጋገጥ ሥራ እያካሄደ እንደሚገኝም አስታውቀዋል ፡፡ በመሆኑም በማጣራት ጊዜ በሚገኙ ግኝቶችና ከዜጎች በሚመጡ ጥቆማዎች መሰረት ለሙስና ወንጀል ምርመራና ክስ ለመመስረት የሃብት ምዝገባና ማሳወቅ መረጃ ሁነኛ መሳሪያ ነው ብለዋል ፡፡ ተቋሙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በፌደራል፣ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የ106 ሺህ 96 የመንግስት ሠራተኞች፣ አመራርና ተሿሚዎች ሃብት ምዝገባ ማካሄዱን አብራርተዋል ፡፡ በኢትዮጵያ የሃብት ምዝገባ ከተጀመረ ከ10 ዓመት በላይ ቢያስቆጥርም በበጀት ውስንነትና ከኦንላይን ምዝገባ ጋር በተያያዘ የሚከሰተው የሲሰተም ችግር ምዝገባው በታሰበው ልክ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡ ከመንግስትና ከሕዝብ ሃብትና ንብረት ጋር ግንኙነት ያለው ሁሉ ሃብቱን በቴክኖሎጂ ማስመዝገብ የሚችልበትን አሰራር ኮሚሽኑ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ተቋም ጋር በመተባበር በማበልጸግ ላይ ይገኛል ብለዋል ፡፡ ሲስተሙ ወደ ስራ ከገባ በኋላ ተቋሙ የተመዘገበውን ሃብት የማጣራትና ዜጎች ምንጩ ላልታወቀ ሀብት እንዳይጋለጡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡  
የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ክፍለ ጦሮችና ሬጅመንቶች ተልዕኳቸውን በአኩሪ ሁኔታ እየፈፀሙ ይገኛሉ- ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
May 6, 2024 122
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2016 (ኢዜአ)፦ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ክፍለ ጦሮችና ሬጅመንቶች ተልዕኳቸውን በአኩሪ ሁኔታ እየፈፀሙ እንደሚገኙ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ተናገሩ። የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ በግዳጅ አፈፃፀሙና በተገኘው ውጤት ላይ ውይይት ተደርጓል። የዕዙ ክፍለ ጦሮች ፅንፈኛውን ሀይል በመደምሰስ፣ በመማረክና እጅ እንዲሰጥ በማድረግ የተሰጣቸውን ሀገራዊ ግዳጅ በተሳካ ሁኔታ መፈፀማቸውንና ታላላቅ ድሎችን ማስመዝገባቸው በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡ ሠራዊቱ በላቀ ጀግንነትና ሀገራዊ ፍቅር ጠላትን በኃይል በመምታት ቆሞ መዋጋት የማይችልበት ደረጃ ላይ አድርሶታል ያሉት ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ፤ የሠራዊቱ ጀግንነት፣ ፅናትና ቁርጠኝነት ከሀገሩ ፍቅር የመነጨ ነው ብለዋል፡፡   አመራሩም በሠራዊቱ ላይ መተማመንን በመፍጠር በጠላት ላይ የበላይነቱን እንዲቀዳጅ ማድረጉን ያወሱት የዕዙ አዛዥ ፤ ፅንፈኛው ኃይል በተወሰደበት ፈጣን እርምጃ ተስፋ ቆርጦ በዘረፈው የህዝብ ሀብት እርስ በእርሱ እየተገዳደለ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡ ታሪካዊ ጠላቶች ከውስጥ ተላላኪ ባንዳዎች ጋር በማበር ሀገሪቱ የተፈጥሮ ሀብቷን ተጠቅማ እንዳትበለፅግና ህዝቦቿ በድህነት ውስጥ እንዲኖሩ ዕልቂት ቢደግሱም ይህንን በመቀልበስ ጠላቶቿ የሚመኟት የደከመችና የተበታተነች ኢትዮጵያን ሳይሆን የበለፀገችና ጠንካራ ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማሻገር አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡ ሁሉም አመራር ወቅታዊ ሁኔታዎችን በመረዳት ለሀገሩ እና ለህዝቦቿ ሰላም ዛሬም እንደ ትላንቱ በፅናት ያለ ዕረፍት መስራት እንዳለበት ማሳሰባቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመለክታል፡፡ ዛሬም ለሀገሩ የአባቶቹን አደራ የማይዘነጋ ራሱን አሳልፎ ሀገሩን የሚያሻግር ጀግና ትውልድ አካል በመሆናቸው ኩራት እንደሚሰማቸው የገለፁት የውይይቱ ተሳታፊ አመራሮች በተላላኪነት የህዝቡን ሰላም እያወከ የሚገኘውን ፅንፈኛ ሀይል ተከታትለው በመጨረስ የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ በሙሉ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የሴቶችን እገዛና ጠንካራ ተሳትፎ የሚያጎለብቱ ስራዎች እየተከናወኑ ነው
May 6, 2024 109
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 28/2016(ኢዜአ)፡- ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የሴቶችን እገዛና ጠንካራ ተሳትፎ የሚያጎለብቱ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በክልሎች በአመራርነት ላይ የሚገኙ ሴቶች ገለጹ። በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ በሂደት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል። በሂደቱ በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማኅበራት እና የተለያዩ አደረጃጀቶች እገዛና ተሳትፎ የላቀ ሚና እንዳለው ይታመናል። በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በተለይም የሴቶች ተሳትፎ የሚጠበቅ በመሆኑ በዚህ ረገድ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው በክልሎች የተለያዩ ሃላፊነቶች ላይ የሚገኙ ሴቶች ተናግረዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤና የሴቶች ኮከስ ሰብሳቢ አለምነሽ ይባስ፤ በሀገራዊ ምክክሩ የሴቶችን ተሳትፎ ለማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህ ስራ ከተለያዩ አደረጃጀቶች የተወጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ በምክክር ሂደቱ ተሳትፎ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ከዞን ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የኮሚሽኑን ስራዎች ለማሳካት እገዛ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የአፋር ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሴቶች ተሳትፎና ንቅናቄ ማስፋፊያ ዳይሬክተር ፋጡማ ሃንፈሬ፤ ለሀገራዊ ምክክሩ የሴቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።   በሂደቱ እየተደረጉ ባሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በርካቶች ለምክክሩ በሚችሉት ሁሉ እገዛና ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን አሳይተዋልም ብለዋል። የጋምቤላ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ክርሙስ ሌሮ፤ የሀገራዊ ምክክሩ ጉዳይ የሁላችንም የጋራ አጀንዳ ሆኖ በልዩ ትኩረት ተይዟል ብለዋል።   በምክክር ሂደቱ በክልልም ይሁን በሀገር አቀፍ ደረጃ ሴቶች ጠንካራ ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድጅታል አሰራር በታገዘ አመራርነት ወጪ ቆጣቢና የተፋጠነ አገልግሎት እየተሰጠ ነው -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
May 6, 2024 126
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 28/2016(ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድጅታል አሰራር በታገዘ አመራርነት ወጪ ቆጣቢና የተፋጠነ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ተመስርቶ በስሩ ስድስት የአስተዳደር ማዕከላትንና 12 ዞኖችን በማካተት በይፋ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል። ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ በኋላ እስካሁን የተሰሩ የልማት፣ የአስተዳደርና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ኢዜአ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ጋር ቆይታ አድርጓል። ከምስረታው በኋላ ክልሉን የሰላም፣ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ አመራሩ ለህዝብ ቃል ገብቶ ወደ ስራ መግባቱን አንስተዋል። ለዚህም ችግሮችን በጋራ ለመሻገር ህዝቡንና ምሁራንን በማሳተፍ የሽግግር ጊዜና መደበኛ እቅዶች ተዘጋጅተው በአሰራር፣ አደረጃጀት፣ የሰው ኃይልና መሰል ጉዳዮች በአግባቡ እንዲሟላ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በኢንዱስትሪና ዲጅታል ዘርፍ ክልሉ ያለውን እምቅ አቅም ወደ ልማት ለመለወጥም ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን አንስተዋል። በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአመራሩ ጥረትና በህዝቡ የነቃ ተሳትፎ የክልሉን የልማትና የሰላም ርዕይ ለማሳካት መሰረት የጣሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል። ለህዝቡ አገልግሎትን በቅርበት ተደራሽ ለማድረግ በጥናት ላይ በመመስረት በዲላ፣ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ካራት፣ ጂንካና ሳውላ ከተሞች ክልሉ በስድስት ማዕከላት እንዲደራጅ መደረጉን ገልጸዋል። ማዕከላቱ እንደ አንድ ማዕከል ሆነው ለህዝቡ ወጥ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ በጥናት እና በህግ የተመሰረተ የዲጅታል አሰራር በማስቀመጥ ወደ ስራ መገባቱንም ተናግረዋል። በስድስቱም የክልሉ ማዕከላት የሚገኙ የካቢኔ አባላትና የዘርፍ የስራ ኃላፊዎች በዲጅታል የታገዘ የአመራር ስረአት እንዲከተሉ መደረጉን ገልጸዋል። የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) አባላት በስድስቱም ማዕከላት የሚገኙ የቢሮ ኃላፊዎች በአካል መገናኘት ሳይጠበቅባቸው ወርኃዊ መደበኛ ስብሰባቸውን በቨርቹዋል የሚያካሂዱ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል። በዚህም የዲጅታል አመራርን በመከተል ፈጣን፣ የተቀላጠፈና ወጪ ቆጣቢ የውሳኔ አሰጣጥ እየተተገበረ ስለመሆኑ ነው የተናገሩት።      
በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መክረን ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል- የእድሮች ምክር ቤት
May 6, 2024 102
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 28/2016(ኢዜአ)፡- በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መክረን ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማና ሀገር አቀፍ የእድሮች ምክር ቤት አመራሮች ተናገሩ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በመሥራት ላይ ይገኛል። በሂደቱ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ የተሳታፊዎች ልየታ በማድረግም አጀንዳ ለማሰባሰብ የሚያስችሉ ተግባራትን ለመጀመር በሂደት ላይ መሆኑ ይታወቃል። በእነዚህ ሂደቶች አጠቃላይ የሕዝቡ ተሳትፎና እገዛ እንዳለ ሆኖ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የሲቪል ማኅበራት ምክር ቤት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እድሮችና ሌሎችም አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ይታመናል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማና ሀገር አቀፍ የእድሮች ምክር ቤት አመራሮች ኮሚሽኑን ከማገዝ ባለፈ በሀገራችን ጉዳይ ላይ ለመምከር ተዘጋጅተናል ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማና ሀገር አቀፍ እድሮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ታምራት ገብረማርያም፤ በምክክርና በውይይት የሀገራችንን የቆዩ ችግሮች በጋራ መፍታት የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል። በመሆኑም የእድሮች ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ኮሚሽኑን በማገዝና የሕዝቡን ተሳትፎ በማጠናከር የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ተዘጋጅቷል ሲሉ ተናግረዋል። በሀገራዊ ችግሮቻችን ላይ በጋራ መክረን ለሁላችንም የምትመች ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉም አረጋግጠዋል። በአዲስ አበባ የየካ ክፍለ ከተማ የእድሮች ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፍቅሬ ሙላት፤ የሀገራችንን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ከምንም በላይ ምክክር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም በሀገራችን ጉዳይ ላይ መክረን ለትውልዱ የምትመች ሀገር ለመገንባት ተዘጋጅተናል ብለዋል። በአራዳ ክፍለ ከተማ የእድሮች ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ስለሺ መለሰ በበኩላቸው፤ የምክክር ጉዳይ ለሀገርም ይሁን ለሕዝብ ሁነኛ መፍትሔ በመሆኑ ሁላችንም ለዚሁ ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል። ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የሚጠበቅብንን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ ነን ሲሉም አመራሮቹ አረጋግጠዋል።    
በሐረሪ ክልል በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ  የተከናወኑ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል -ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
May 4, 2024 206
ሐረር፤ ሚያዝያ 26//2016 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተከናወኑ አበረታች ስራዎች እንዲጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አሳሰቡ። የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በክልሉ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተከናወኑ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ዛሬ ገምግሟል።   የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ባቀረቡት ሪፖርት በክልሉ በልማት፣ በሰላምና በሌሎች መስኮች የተከናወኑ ስራዎችን መረጃ ለማድረስ መሰራቱን ገልጸዋል። በክልሉ መረጃን ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ ረገድ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽንና ብዙሃን መገናኛ እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ አገር አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በማስተባበር ረገድ አመርቂ ተግባራትን ማከናወናቸውን አስታውቀዋል።   ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች የተሻሉና አበረታች ናቸው። በአገራዊ ጉዳዮች ላይ "ብሔራዊ መግባባት ከመፍጠርና ዴሞክራሲን ከመገንባት ረገድ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል" ብለዋል። ዘርፉን በማጠናከርና በማዘመን በህዝብና በመንግስት መካከል ሁነኛ የመረጃ ድልድይ ሆኖ ተግባቦትን የማሳለጥ ሥራዎች እየተካሄዱ መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ አመልክተዋል። ዘርፉን በስትራቴጂክ እቅድ የመምራት፣ መረጃን ለህዝብ ተደራሽ የማድረግ እና በመረጃ የዳበረ ማህበረሰብን የመፍጠር ስራዎች እንዲጠናከሩም አስገንዝበዋል። በዘርፉ የስራ ተነሳሽነትን በማሳደግና ተቋማዊ ግንኙነትን በማጠናከር ውጤታማ ለመሆን እንዲሰራም አቶ ኦርዲን አሳስበዋል።                  

ማህበራዊ
የጤና ተቋማትን ንጽህና መጠበቅ ከንቅናቄ ባሻገር የዘወትር ተግባር መሆን አለበት -ዶክተር መቅደስ ዳባ
May 7, 2024 65
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016(ኢዜአ)፦ የጤና ተቋማትን ንጽህናን መጠበቅ ከንቅናቄ ባሻገር የዘወትር ተግባር ሊሆን እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትሯ የ "ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና" ንቅናቄ አካል የሆነውን ጽዱ የጤና ተቋማትና አካባቢን የመፍጠር ንቅናቄ በአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በጴጥሮስ ጻውሎስ ሆስፒታል ተገኝተው በይፋ አስጀምረዋል።   ዶክተር መቅደስ ዳባ ንቅናቄውን ባስጀመሩበት ወቅት ፤ የንጽህና ጉድለት ኢትዮጵያን ጨምሮ የታዳጊ አገራት የጤና እክል መንስኤ መሆኑን በመጥቀስ የንጽህና ጉድለት ከሚስተዋልባቸው ስፍራዎች መካከል ደግሞ የጤና ተቋማት ይገኙበታል ብለዋል። እኤአ በ 2019 በተደረገ ጥናት በሆስፒታል ተወልደው በኢንፌክሽን ከሚጠቁ ህጻናት መካከል 56 በመቶው በንጽህና ጉድለት የሚጠቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ችግሩን ማስቀረት የሚቻለው ምቹ እና ንጽህናው የተጠበቀ የጤና ተቋም በመፍጠር ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ይፋ የተደረገው ንቅናቄ በህጻናትና እናቶች ላይ የሚከሰተውን የጤና እክል ለመቀነስ የጎላ ሚና እንደሚኖረው አመላከተዋል። ሚኒስቴሩ በጤናው ዘርፍ የሚተገበሩ መስፈርቶችን በመጠበቅ የላቀ ፈጻሚ ሆኖ ለመገኘት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ንጽህናው የተጠበቀ አካባቢን ለመፍጠር ስራው ከንቅናቄ ባሻገር የዘወትር ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡   የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አብርሃም እሸቱ በበኩላቸው፤የአካባቢ ንጽህናን መጠበቅ ቅንጦት ሳይሆን ግዴታ ነው ብለዋል፡፡ ሆስፒታሉ ለታካሚዎቹና ሰራተኞቹ ምቹና ጽዱ አካባቢን ለመፈጠር የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡   በንቅናቄው መታጠቢያ ቤቶች፣ የታካሚ ማቆያና ሽንት ቤቶችን የማስዋብ እንዲሁም አዳዲስ ግንባታዎች ለማካሔድ ዝግጅት መደረጉን የተናገሩት ደግሞ የአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሽመልስ ገዛኽኝ ናቸው።   ዶክተር መቅደስ ዳባ በሆስፒታሎቹ አዳዲስ መጸዳጃ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡          
የኢትዮጵያ ደምና ህብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ
May 7, 2024 51
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 29 /2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ደምና ህብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ። ከነገ ጀምሮ እስከ ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ "ደሜን እለግሳለሁ ደስታውም ሽልማቴ ነው" በሚል መሪ ሃሳብ የደም ልገሳ መርኃ ግብር በአዲስ አበባ እንደሚጀመር ተገልጿል። የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አሸናፊ ታዘበው (ዶ/ር)ና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምክትል ዋና ፀሃፊ አቶ አበራ ሉሌሳ ስምምነቱን ተፈራርመዋል። ስምምነቱ የበጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾችን ቁጥር በማሳደግና በማስተባበር የሚፈለገውን ደም ለመሰብሰብ አላማ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አሸናፊ ታዘበው (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት አገልግሎቱ 48 ቅርጫፎችን በመክፈትና አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማዘመን በቂ ደም ለመሰብሰብ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።   ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት የሚሰሩትን የበጎ ፍቃድና የሰብዓዊነት ስራ ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል። በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስና በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾችን በማስተባበር የሚፈለገውን ደም ለመሰብሰብ እንደሚያግዝ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምክትል ዋና ፀሃፊ አቶ አበራ ሉሌሳ በበኩላቸው የቀይ መስቀል ማህበር በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ጉዳት የሚደርስባቸውን ዜጎች የመደግፍና መልሶ የማቋቋም ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።   የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የሚሰራው ሰብዓዊ ስራ ከተቋማቸው ጋር የሚገናኝ በመሆኑ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ገልፀዋል። ማህበሩ በጎ ፍቃደኞ ደም ለጋሾች በንቃት እንዲሳተፉ እንዲሁም በቂ የሆነ ደም በመሰብሰብ የሰውን ህይወት ለመታደግ አበክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከነገ ጀምሮ እስከ ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ "ደሜን እለግሳለሁ ደስታውም ሽልማቴ ነው" በሚል መሪ ሃሳብ የደም ልገሳ መርኃ ግብር በአዲስ አበባ እንደሚጀመር ተገልጿል። የደም ልገሳ መርኃ ግብሩ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እንደሚካሄድ ተመላክቷል።
የታላቁ አል-ነጃሺ 00 መንደር ጅማሮ ማብሰሪያ እየተካሄደ ነው
May 7, 2024 60
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 29 /2016 (ኢዜአ)፦የታላቁ አል-ነጃሺ 00 መንደር ጅማሮ ማብሰሪያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ አደም አብዱልቃድር ተገኝተዋል፡፡ እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዘሀራ ሁመድ ፣የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የማህበራዊ ልማት ሴክሬተርያት ካቢኔ ሀላፊ ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወትና ከፍተኛ የፌዴራልና የክልሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል። በመርሀ ግብሩ የታላቁ አል-ነጃሺን ታሪካዊ ዳራ የሚያስቃኝ ዶክመንተሪ ፊልም ለእይታ ቀርቧል። የመድረኩ አላማ አልነጃሺን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለአለም ማስተዋወቅ መሆኑ ተመላክቷል። የዜሮ ዜሮ መጠርያ ሃሳቡ የመነጨው ከሸህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ሲሆን መነሻ ሃሳቡ እስልምና በኢትዮጵያ የተጀመረበትንና የታሪኩን መነሻና መገኛ ለመጠቆም መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፣ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እንዲሁም የአልነጃሺ መልሶ ግንባታና ልማት ኢኒሸቲቭ በጋራ የሚያከናውኑት መሆኑ ተገልጿል የፕሮጀክቱ አላማ በኢትዮጵያ ብሎም በአለም ትልቁ የሙስሊሞች ታሪክና ቅርሰ የሆነውንና ከመካ መዲና ቀጥሎ በአለም የእስልምና መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ የሚገኘውን ሃብት በስፋት ማስተዋወቅ ነው፡፡ በተጨማሪ በከባዱ ፈተና ወቅት ለሙስሊሞች ከለላ የሆኑት የነጃሺ መካነ ቅርስ አሻራ ባለበት በትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ ክብራቸውና ታሪካቸውን በሚመጥን መልኩ አለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የቱሪስት መንደር ለመገንባት ያለመ ነወ፡፡ በቱሪስት መንደሩ የተለያዩ ንዑስ ፕሮጀከቶች የታቀፉ ሲሆን ከነዚህም ደረጃውን የጠበቀ ሙዚየም፣ ሃላል ሆቴሎችና ሎጆች ፣የእምነት ስፍራዎች ፣ የጥናትና ምርምር ተቋማት እንደሚገነቡ ተመላክቷል፡፡ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲ ፣የቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ፣ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ፣ደረጃቸውን የጠበቁ ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት ፣ለህዝብ አገልገሎት የሚውሉ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራዎችና መሰብሰብያ አዳራሾች እንደሚኖሩት ተመላክቷል። መርኃ ግብሩ የተዘጋጀው ኢትዮጵያውያንና በአለም የሚኖሩ የታሪኩ ባለቤቶች የቦታውን ታላቅነት በማሰብ በፕሮጀክቱ ላይ በቻሉት አቅም ርብርብ እንዲያደርጉ ለማብሰር መሆኑ ተገልጿል።  
በዞኑ በዘንድሮው የበጋ በጎ ፍቃድ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል
May 7, 2024 70
ደሴ ፤ሚያዝያ 29/2016(ኢዜአ) ፦በደቡብ ወሎ ዞን በዘንድሮው የበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የወጣቶች ማካተት፣ ንቅናቄና ተሳትፎ ቡድን መሪ አቶ ምስጋናው ደምሴ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለማቃለል የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡ በዘንድሮ የበጋ ወቅትም በዞኑ 181 ሺህ 526 በጎ ፍቀደኞችን በተለያዩ የስራ ዘርፎች በማሳተፍ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወነ የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡ በአገልግሎቱ እስካሁን 41 የአቅመ ደካሞችና የአረጋዊያን ቤት ጥገናና አዲስ ግንባታ፣ 158 ዩኒት ደም ልገሳ፣ 300 ኩንታል ዱቄት ለተፈናቃዮች ድጋፍ፣ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው አልባሳትና ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም 600 ሄክታር መሬት ላይ አፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ፣ ከ250 ሄክታር መሬት ላይ በበጋ መስኖ የለማ ሰብል ከአረም የማጽዳት ስራ መስራት መቻሉንና ሌሎችም ተግባራት መከናወናቸውን አስገንዝበዋል፡፡ አገልግሎቱ ከጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ መከናወኑን ጠቁመው፤ እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ተግባራትን መስራት እንደተቻለ አስረድተዋል።   የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የወጣቶችን የማህበራዊ አገልግሎት ከማሻሻሉም በላይ የበርካታ ወገኖች ችግር እንዲቃለል እያገዘ እንደሆነም አመልክተዋል። በዞኑ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በመሳተፍ ላይ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል ወጣት አልዩ ሐሚድ እንዳለው በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ እንዲሁም በበጋ መስኖ የለማ የአቅመ ደካሞች ሰብልን ከአረም የማጽዳት ስራ ማከናወን ችለዋል። በነጻ በሚሰራው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ውስጣዊ እርካታ እንደሚሰማው ጠቅሶ፤ በክረምቱም በተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች በመሳተፍ ህብረተሰቡን በሚችለው ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል፡፡ በኩታ በር ወረዳ የ06 ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ሰዓዳ ኡመር በሰጡት አስተያየት ደግሞ ቤታቸው አርጅቶ በክረምት በዝናብ፣ በበጋ ደግሞ በፀሐይና በንፋስ ሲቸገሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ በበጎ ፈቃደኞች ቤቴ በአዲስ መልኩ ተሰርቶልኝ ከችግሩ በመላቀቄ ተደስቻለሁ፤ አመሰግናለሁም ብለዋል፡፡ በዞኑ ባለፈው የክረምት ወቅት 488 ሺህ ወጣቶችን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት በማሳተፍ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ከመምሪያው የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡  
ኢኮኖሚ
የግሉ ዘርፍ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ያለውን ሰፊ የገበያ እድል ለመጠቀም ራሱን ማዘጋጀት አለበት
May 7, 2024 61
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና የሚፈጥረውን ሰፊ የገበያ እድል ለመጠቀም የንግዱ ማህበረሰብ ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት ለማቅረብ ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ተገለጸ። የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና በሚፈጥረው ዕድል የግሉ ዘርፍ ተጠቃሚ ለመሆን ያለውን ዝግጁነት በተመለከተ የፓናል ውይይት አካሂዷል። በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የዓለም አቀፍና ቀጠናዊ ንግድ ትስስር መሪ ስራ አስፈጻሚ ታገስ ሙሉጌታ ኢትዮጵያ ለአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠናው እያደረገች ያለውን ዝግጅት አብራርተዋል።   ስምምነቱ ላይ በሚካሄዱ ድርድሮችና ስምምነቱን ለመተግበር በሚደረጉ ዝግጅቶች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ረገድ የንግዱ ማህበረሰብ የስምምነት ሂደቱን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ በመያዝ፣ ቀጠናዊ ትስስርን በማጠናከር ፣ ተአማኒነትን በማሳደግ ተወዳዳሪ ለመሆን ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል። እንደ መሪ ስራ አስፈጻሚው ገለጻ አግሮ ፉድ፣ የጨርቃጨርቅና የቆዳ ምርቶች በነጻ ንግድ ቀጠናው ተጠቃሚ ለመሆን ትልቅ አቅም ያላቸው ዘርፎች ናቸው። በጉምሩክ ኮሚሽን የታሪፍና ስሪት አገር ዳይሬክተር ካሳዬ አየለ በበኩላቸው ለአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ትግበራ በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል ያለውን ቅድመ ዝግጅት አስረድተዋል።   ምርቶች በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የስሪት ሀገር ህግ መሰረት መመረታቸውን በማረጋገጥ ሰርተፍኬት ለመስጠት የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት መሰንበት ሸንቁጤ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያላት የወጪ ንግድ ድርሻ 20 በመቶ እንዲሁም የገቢ ንግድ ምጣኔው ከስድስት በመቶ እንደማይበልጥ ጠቅሰዋል።   ከዚህ አኳያ ነጻ የንግድ ቀጠናው የሀገሪቱን ንግድ በማሳደግ ሰፊ የገበያ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል። በተጨማሪም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ፣ ካፒታል ለመሳብ፣ የቴክኖሎጂና የሙያ ክህሎት በማሳደግ አማራጭ ምርቶችን በተሻለ ዋጋ ለተጠቃሚዎች ለማቅረብና ለስራ እድል ፈጠራ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል፡፡ የንግዱን ማህበረሰብ ተወዳዳሪ ሊያደርጉት የሚችሉት ጥራት ያላቸው ምርትና አገልግሎቶች በመሆናቸው በዚሁ ረገድ የንግዱ ማህበረሰብ መዘጋጀት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም በመንግስት በኩል ጠንካራ የቁጥጥር ስርአት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን አክለዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ነጻ የንግድ ቀጠናው በሚያስገኘው እድል ለመጠቀም ራሳቸውን እያዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና እአአ በ2021 ስራ ላይ እንዲውል የጸደቀ ስምምነት ሲሆን 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ገበያ ሊፈጥር እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ።                
በቀጣይ አራት አመታት 10 ሺህ ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድ ለመገንባት እቅድ ተይዟል
May 7, 2024 60
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016 (ኢዜአ)፦ በቀጣይ አራት አመታት 10 ሺህ ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድ ለመገንባት እቅድ መያዙን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ በተለይም ሰፊ የግብርና ልማት በሚከናወንበት የገጠሩ አካባቢ የመንገድ መሰረተ ልማት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የገበያ ትስስር ለመፍጠርና የምርት አቅርቦትን ለማሳለጥ እንዲሁም ሌሎች የልማት ክንውኖችን ለማሳካትም መንገድ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። በገጠር ተደራሽነትና ትስስር ፕሮግራም የገጠር መንገድ ልማት የሚከናወን መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ከዓለም ባንክ 300 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል ብለዋል። በመሆኑም በዓለም ባንክ ድጋፍ፣ በፌዴራል መንግስትና በክልሎች ትብብር በቀጣይ አራት አመታት 10 ሺህ ኪሎ ሜትር መንገድ የሚገነባ መሆኑን ገልጸዋል። ለመንገድ ፕሮጀክቱ ክልሎች 30 በመቶ ተጨማሪ የበጀት ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚደረግ መሆኑንም ጠቁመዋል። የመንገድ ፕሮጀክቱ የምርት አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳለጥና የገበያ ትስስርን በመፍጠር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እገዛ የሚኖረው መሆኑን ሚኒስትር ዴታው ገልጸዋል። በገጠር ተደራሽነትና ትስስር ፕሮግራም መሰረት የሚከናወነው የመንገድ ልማት 128 ወረዳዎችን ከዋና መንገድ ጋር የሚያገናኝ ይሆናል። በአገሪቷ ባለፉት ስድስት አመታት 5 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ መገንባቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በጋምቤላ ክልል በበጋ የመስኖ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የሚበረታቱ ናቸው - የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
May 7, 2024 60
ጋምቤላ፤ ሚያዝያ 29/2016 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በበጋ የመስኖ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በማጃንግ ዞን መንገሺ ወረዳ በበጋ መስኖ እየለማ ያለውን ስንዴና የሩዝ እርሻ ጎብኝተዋል።   ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በሀገር ደረጃ የስንዴና የሩዝ ልማት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው የሰብል ዓይነቶች መካከል መሆናቸውን አስታውሰዋል። ሰለሆነም በጋምቤላ ወይና ደጋ የአየር ንብረት ባለበት የማጃንግ ዞን ካለፈው ዓመት ጀምሮ በሙከራ ደረጃ ሲከናወን የነበረ የስንዴና የሩዝ ልማት ውጤቱ እየታየበት መጥቷል ብለዋል። በዘንድሮው የበጋ ወቅትም በመንገሺ ወረዳ ብቻ ከ43 ሄክታር በላይ መሬት በስንዴና በሩዝ እንዲሸፈን መደረጉን ጠቅሰው፤ ውጤቱም አርሶ አደሩን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን አይተናል ብለዋል። የበጋ መስኖ ልማቱ የምግብ ዋስትናን በቤተሰብና በአካባቢው ደረጃ ለማረጋገጥ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት የሚያስችል ለመሆኑም ማሳያ ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።   የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ሉዋል በበኩላቸው በክልሉ የስንዴንና የሩዝ ልማትን አርሶ አደሩ ዘንድ ለማስፋት የተደረገው ጥረት ውጤት አስገኝቷል ብለዋል። በተለይም አርሶ አደሮቹ በፊት በማይታወቅባቸው የስንዴና ሩዝ ልማት ዘርፍ በበጋ መስኖ ልማት ላይ ተሰማርተው ምርታማነታቸውን እያሳደጉ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ክልሉም ለስንዴና ለሩዝ ልማት ምቹ አካባቢ መሆኑን በተደረጉ ሙከራዎች መረጋገጡን ተናግረዋል። በመሆኑም በቀጣይ ጊዜያት አርሶ አደሩንና ባለሃብቱን በማስተባበር የስንዴና የሩዝ ልማቱን ለማስፋት እንደሚሰራም አብራርተዋል። በመስክ ጉብኝቱ ላይ የተገኙ አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት ካለፈው ዓመት ጀምረው ስንዴንና ሩዝን ማልማት መጀመራቸውን ገልፀዋል። በተለይም በሙከራ ደረጃ የጀመሩት የስንዴ ምርት በመሸጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዘንድሮው የበጋ ወራትም እያንዳንዳቸው በኩታ ገጠም እርሻ ከአንድ ሄክታር መሬት በላይ ስንዴንና ሩዝ እያለሙ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ከዚህም ከአምናው የተሻለ ውጤት እናገኛለን የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ የአመራር አባላቱ በበጋው ወራት ከለማው የስንዴና የሩዝ እርሻ በተጨማሪ በበልግ እርሻ እየለማ ያለን የቦቆሎ ቡቃያና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።    
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሚኒስቴሩ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ውጤታማነትን ለማጠናከር በትኩረት መስራት እንዳለበት የህዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት አሳሰበ
May 7, 2024 55
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016(ኢዜአ)፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ የህብረተሰቡን የዲጂታል አጠቃቀምና ግንዛቤ ማሳደግ ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 3ኛ አመት የስራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የ2016 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል። ሚኒስቴሩ ለምክር ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚያስችሉ አምስት የትብብር ስምምነቶችን መፈጸሙን ገልጿል። በዚህም ዘመናዊ የስታርት አፕ ከተማ ለመገንባት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ስምምነት መደረሱን አስታውቋል፡፡ ቀሪዎቹ አራቱ ስምምነቶች የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን ለማሳለጥ በውጭ አገራት ካሉ ድርጅቶች ጋር የተፈፀሙ መሆናቸውን አስረድቷል። የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ለማስፋት በቅድመ ደረጃ ስታርት አፖች ሃሳባቸውን እንዲያበለፅጉ ለ558 ጀማሪ ስታርት አፖች የቢዝነስ ስልጠና እና ሜንቶሪንግ ድጋፍ መደረጉ በሪፖርቱ ተመላክቷል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ችግር ፈቺ ምርምሮችን ለመደገፍ በመንግስት ትኩረት በተሰጣቸው የምርምር ዘርፎች ለሚከናወኑ 24 ምርምሮች የገንዘብና ቴክኒካል ድጋፍ መደረጉም ተገልጿል። በምርምር የተገኙ ስምንት ቴክኖሎጂዎችን ማልማት እንዲሁም ሰባት ቴክኖሎጂዎችን ማላመድ መቻሉና የሳተላይትና ጂኦስፓሻል መረጃዎችን በማደራጀት ስድስት ተቋማትን ተጠቃሚ መደረጉም ተመላክቷል። በዚህ ወቅት የምክር ቤቱ የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ(ዶክተር )ሚኒስቴሩ እቅዱን ከሰራተኞቹና ከክልሎች ጋር የጋራ በማድረግ መስራቱ እንደ ጥንካሬ የሚወሰድ ነው ብለዋል።   የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ችግር ፈቺ ምርምሮችን መስራቱ በጥንካሬ እንደሚወሰድና የስፔስና ጂኦስፓሻል መረጃዎች ለአገራዊ ጥቅም እንዲውሉ የተሰሩ ስራዎችም የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል። በስታርት አፕ ላይ የተጀመሩ ስራዎች የሚበረታቱ ቢሆኑም የስራ እድል በመፍጠር ረገድ አሁንም የሚቀሩ ስራዎች መኖራቸውን አንስተዋል። ሚኒስቴሩ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ከግብ እንዲደርስና ህብረተሰቡ ቴክኖሎጂን አውቆ እንዲጠቀም ለማድረግ የግንዛቤ ስራ ላይ አተኩሮ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል። የአዕምሯዊ ንብረት ለአገር እድገት ወሳኝ በመሆኑ የተጀመሩ ሪፎርሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል። የኢኖቬሽን ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶክተር ) በበኩላቸው የዲጂታል 2025 የመካከለኛ ዘመን ግምገማ መካሄዱንና ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መኖራቸውን ማየት መቻሉን ጠቅሰዋል።   ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ዲጂታል ክህሎት ወሳኝ መሆኑን አንስተው በዲጂታል ክህሎት ልማት ላይ ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ስታርት አፖችን የሚያሰራ የህግ ማዕቀፍና የፋይናንስ ስርዓት እንዳልነበር አንስተው አሁን ላይ በተደረገው ማሻሻያ ምቹ ምህዳር በመፈጠሩ ከስራ እድልና ሀብት ፈጠራ አንፃር የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።          
የግል ባለሃብቶች የተሽከርካሪዎች ቻርጅ ስቴሽን ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ
Apr 30, 2024 380
የግል ባለሃብቶች የተሽከርካሪዎች ቻርጅ ስቴሽን ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2016(ኢዜአ)፡- የግል ባለሃብቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ከማስገባት ባለፈ የቻርጅ ስቴሽን ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጥሪ አቀረበ። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ምትኩ አስማረ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በከተማዋ በቀን ውስጥ ከሚደረገው 3 ነጥብ 4 ሚሊየን የትራንስፖርት ምልልስ ውስጥ 31 በመቶው በብዙኃን ትራንስፖርት የሚሸፈን ነው። የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን መጠቀም አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደ አገር እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለመደገፍ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው።   በተለይም ኢትዮጵያ ነዳጅ ከውጭ ለማስገባት የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንዲቀር በማድረግ ለኢኮኖሚው አበርክቶ ይኖረዋል ነው ያሉት። መንግሥትም ለብዙኃን ትራንስፖርት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል። በከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች አብዛኞቹ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በከተማው ያለው የተሽከርካሪዎች ቻርጅ ስቴሽን በቂ ስላልሆነ ባለሃብቱ በዚህ ላይ ቢሳተፍ እራሱንና አገሩን ይጠቅማል ብለዋል። ቢሮው በዘርፉ ለተሰማራው የግል ትራንስፖርት ሰጪ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የግል ባለሃብቶች በኤሌክትሪክ ቻርጅ ስቴሽኖች ላይ እንዲሰማሩም ጥሪ አቅርበዋል።   መንግሥት 100 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የከተማ አውቶቡሶች ግዥ በመፈፀም በአጭር ጊዜ ለማስገባት ሥራ መጀመሩንም ነው የገለፁት። በተጨማሪም አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የከተማ አውቶቡሶችን በቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። ሕብረተሰቡ አውቶቡሶች በስንት ሰዓት እንደሚደርሱ መረጃ የሚያገኙበት የመረጃ ሥርዓት በመርካቶ ተርሚናል ሥራ መጀመሩንና በሌሎች ለማስፋት እንደሚሰራም ተናግረዋል። የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የሕዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች እየገጣጠመ እንደሚገኝና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የመጀመሪያዎቹ 216 ተሽከርካሪዎች መገጣጠማቸውን የገለፁት ደግሞ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ሰጠኝ እንግዳው ናቸው።   በቬሎሲቲ ኤክስፕረስ ድርጅት አማካኝነት 20 የኤሌክትሪክ ሚኒባሶችና ሁለት ኤሌክትሪክ ከተማ አውቶቡሶች በሙከራ ደረጃ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል። አውቶቡሶቹ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከመሆናቸው ባሻገር ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሆነው መዘጋጀታቸውንም ነው የገለፁት።    
በኢትዮጵያ ስታርት አፖችን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ድጋፍ ይቀጥላል
Apr 30, 2024 197
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ስታርት አፖችን ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ሃንዳክ ጆ ገለጹ። በኢትዮጵያ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በመደገፍና በማበረታታት ስታርት አፖች በስፋት እየተዋወቁ ይገኛሉ። በዘርፉ የተሻለ የፈጠራ ስራ እንዲኖር ምቹ ምህዳር እየተፈጠረ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) የኢትዮጵያ ተወካይ ሃንዳክ ጆ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሁን ላይ የፈጠራና ቴክኖሎጂ ትግበራ ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በኢትዮጵያ በተለይም በቅርብ አመታት በስታርት አፖች ለተሻለ የፈጠራ ስራ ምቹ ምህዳር መኖሩን አድንቀዋል። ኮይካ የ10 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በመያዝ ለስታርት አፖች የተቋማት ኢንኪዩቤሽን ማዕከላት ግንባታ ምቹ ምህዳር ለመፍጠር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በኢትዮጵያ በዘርፉ የሚደረጉ ጥረቶችን በማገዝ ረገድ የኮይካ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ በስታር አፖች እንዲሁም በአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ ዘርፍ በኢትዮጵያ የተጀመሩ ጥረቶች የሚደነቁ ናቸው ብለዋል። በኢትዮጵያ ከለውጡ በፊት 50 ብቻ የነበሩት ስታርት አፖች አሁን ላይ ከ900 በላይ ጀማሪ፣ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ እና ወደ ገበያ የገቡ ስታርት አፖች እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሳይንስ ሙዚየም ተከፍቶ በነበረው አውደ ርዕይ 300 የሚደርሱ ስታርት አፖች ለእይታ ቀርበው የተሻሉ የስራ ሃሳብ የነበራቸው ስታርት አፖች መሸለማቸው ይታወሳል።
በአማራ ክልል ከተሞችን በማዘመን አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል- የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን 
Apr 29, 2024 197
ደሴ ፤ ሚያዚያ 21/2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ከተሞችን በቴክኖሎጂ በማበልጸግና በማዘመን አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በደሴ ከተማ አስተዳደር በአምስቱም ክፍለ ከተሞች የ"ስማር ሲቲ" ፕሮጀክት ዛሬ ተጀምሯል፡፡ የአማራ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የቻለ ይግዛው በማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ እንዳሉት፤ በክልሉ ከተሞችን በማዘመንና አሰራራቸውን በቴክኖሎጅ በማገዝ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተሰራ ነው፡፡ ለዚህም የ"ስማር ሲቲ" ፕሮጀክት ዛሬ በደሴ ከተማ መጀመሩን አብስረዋል። ባህር ዳርን ጨምሮ በክልሉ ስምንት ከተሞችም በቅርቡ እንደሚጀመር አመላክተዋል፡፡ “አሰራሩ ከተለመደ አሰራርና ከወረቀት መረጃ አያያዝ በመውጣት በቴክኖሎጂ ወደ ዲጅታል የሚቀይር እንዲሁም የከተሞችን ደህንነት፣ እድገት፣ መሬት አያያዝ፣ አገልግሎት አሰጣጥና ሌሎችም የሚያሻሻል ነው” ብለዋል፡፡ “ህብረተሰቡና ተቋማት መንግስት የሚጀመረውን አሰራር በመከተልና በመደገፍ የክልሉን ሁለተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል” ሲሉም አክለዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፤ በከተማው ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል፣ የከተማውን ሁለተናዊ እድገት ለማፋጠን፣ አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዛሬ የ"ስማር ሲቲ" አዲስ የቴክኖሎጂ አሰራር መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ አሰራሩ አስፈላጊው ዝግጅትና ግብዓት ተሟልቶ መጀመሩን ጠቁመው፤ ቀደም ብሎ በአንድ ክፍለ ከተማ የተካሄደው ሙከራ ውጤታማ መሆኑን መረጋገጡን አብራርተዋል። በዚህም መሰረት ዛሬ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የ"ስማር ሲቲ" ፕሮጀክት እንዲጀመር መደረጉን ተናግረዋል። “ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት የከተማውን ሁለተናዊ እድገትና የቴክኖሎጂ አሰራር ውጤታማ ለማድረግ የድርሻችንን እንወጣለን” ያሉት ደግሞ የኢትዮ-ቴሌኮም ሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ማስረሻ ገበየሁ ናቸው፡፡ አሰራሩ መሰረተ ልማቶችን ለማፋጠን፣ አሰራሩን ለማዘመንና ለዜጎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ጠቁመው፤ “ በተሻለ በኢንተርኔት ዳታና ቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ሪጅኑ የራሱን ዝግጅት አድርጓል” ብለዋል፡፡ በማስጀመሪያ ስነ ስርአት ላይ የክልልና የከተማ አመራር አባላት፣ የተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
ስፖርት
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ወልቂጤ ከተማን በማሸነፍ ወደ ድል ተመለሰ 
May 5, 2024 89
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ወልቂጤ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል። በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ለመቻል አጥቂው ምንይሉ ወንድሙ በ13ኛው፣ 24ኛው እና 43ኛው ደቂቃ 3 ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል። የአማካይ ተጫዋቹ ጋዲሳ መብራቴ በ75ኛው ደቂቃ ለወልቂጤ ከተማ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል። መቻል ከሶስት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት መመለስ ችሏል። ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው መቻል ነጥቡን ወደ 44 ከፍ በማድረግ ከመሪው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ዝቅ አድርጓል። ወልቂጤ ከተማ በ16 ነጥብ በነበረበት 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የመቻል የፊት አጥቂ ምንይሉ ወንድሙ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ወደ 12 ከፍ በማድረግ ተመሳሳይ የግብ መጠን ካለው የሃዋሳ ከተማው አጥቂ አሊ ሱሌማን ጋር በመስተካከል የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በጋራ መምራት ችሏል። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሃዋሳ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።  
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል
May 5, 2024 89
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 27/2016(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በወጣው መርሐ-ግብር መሠረት መቻል ከወልቂጤ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚሰለጥነው መቻል በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት 5 ተከታታይ ጨዋታዎች 2 ጊዜ ሲያሸንፍ 1 ጊዜ ተሸንፏል። 2 ጊዜ አቻ ወጥቷል። በእነዚህ 5 ጨዋታዎች መቻል 5 ግቦችን ሲያስቆጥር 3 ጎሎችን አስተናግዷል። በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚመራው መቻል በ41 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ወልቂጤ ከተማ ካለፉት 5 የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 1 ጊዜ ብቻ ነው። 2 ጊዜ ሲሸነፍ በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ ነጥብ ተጋርቷል። ወልቂጤ በ5ቱ ጨዋታዎች 2 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 5 ጎሎች ተቆጥረውበታል። በሙሉጌታ ምሕረት የሚሰለጥነው ወልቂጤ ከተማ በ16 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ መቻል 2 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም። በ23ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የአምናው የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካለፉት 5 የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 1 ጊዜ ብቻ ነው። 2 ጊዜ ሲሸነፍ 2 ጊዜ ደግሞ ነጥብ ጥሏል። ፈረሰኞቹ ባለፉት 5 ጨዋታዎች 4 ግቦችን ሲያስቆጥሩ በተመሳሳይ 4 ግቦችን አስተናግደዋል። በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ39 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ተጋጣሚው ሀዋሳ ከተማ ባለፉት 5 የሊጉ ጨዋታዎች 2ቱን ሲያሸንፍ 2 ጊዜ ተሸንፏል። 1 ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በእነዚህ 5 ጨዋታዎች 9 ግቦችን ሲያስቆጥር 8 ጎሎችን አስተናግዷል። ዘርዓይ ሙሉ የሚያሰለጥነው ሀዋሳ ከተማ በ29 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። በተያያዘም ትናንት በተደረጉ የ23ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻ እንዲሁም ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳዕናን በተመሳሳይ 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ልማትና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው - የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር
May 7, 2024 58
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ልማትና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ የሁሉንም ድጋፍ ይሻል ሲሉ የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ፍሎሬንስ አዶንጎ (ዶ/ር) ተናገሩ። የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ፍሎሬንስ አዶንጎ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን ጨምሮ እያከናወነች ያለው የአካባቢ ጥበቃ ሥራ የላቀ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። የአባይ ተፋሰስ ሀገራት በየራሳቸው የአካባቢ ጥበቃ መርሃ-ግብር እያከናወኑ መሆኑን አንስተው፤ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተጠቃሽ ነው ብለዋል። በየዓመቱ በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ ለጎረቤት አገራት ጭምር ችግኞችን በመለገስ እያበረከተች ያለው አስተዋጽኦ አስደናቂ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ልማትና ተጠቃሚነትን የሚያመጣ በመሆኑ የሁሉንም ድጋፍ ይሻል ሲሉ ተናግረዋል። ኤኒሼቲቩ ተፋሰስ አቀፍ ፕሮጀክቶችን እስካሁን ገቢራዊ ማድረግ ባይችልም ሀገራት በብሔራዊ ደረጃ እያካሄዱ ያለውን የደን ልማት ያግዛል ብለዋል። የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚያከናውኗቸው የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በቀጣናው ዘላቂ የአካባቢ ስነ-ምህዳር ጥበቃ ለማድረግ የሚያግዙ መሆናቸውንም ገልፀዋል። የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ይህን ጥረት ለመደገፍ የኃብት ማሰባሰብ ሥራ የሚሰራ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሯ አረጋግጠዋል። የተፋሰሱ ሀገራት የኃይል ማመንጫ ግድቦችን ጨምሮ በተፋሰሱ የሚገነቡ የመሠረተ-ልማቶች ደኅንነትና የአገልግሎት ዘመን ለማራዘም የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ወሳኝ ስለመሆኑም አንስተዋል። በዚህ ረገድ 25 ዓመታትን ያስቆጠረው የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ በተፋሰሱ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ይሰራል ብለዋል።
የባህር ዳር ከተማን ፅዳትና ውበት የመጠበቅ  ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
May 2, 2024 181
ባህር ዳር ፤ ሚያዝያ 24/2016(ኢዜአ)፡- የባህር ዳር ከተማን ጽዳትና ውበት በመጠበቅ ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ህብረተሰቡን በማሳተፍ ተጠናክረው እንደሚቀጥል የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። "የአካባቢ ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ሀሳብ የአካባቢ ብክለት መከላከል የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል። የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አስሜ ብርሌ እንዳሉት፤ የአካባቢን ብክለት ለመጠበቅ በተቀናጀ መንገድ መስራት ይገባል።   በተለይ የኢንዱስትሪ ፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ የአካባቢን ስነ-ምህዳር ከመበከል ባለፈ በሰውና በእንስሳት ላይ ሊያደርስ የሚችለው የጤና መታወክ ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል። በመሆኑም የአካባቢ ብክለትን በዘላቂነት ለመከላከልና የከተማውን ጽዳትና ውበት ለመጠበቅ እየተደረገ ያለው ጥረት ህብረሰተቡን ባሳተፈ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ተገቢውን እገዛ ሊያደርጉ እንደሚገባ አመልክተዋል።   የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ጥበቃ ፅዳትና ውበት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ወርቁ በበኩላቸው እንዳሉት፤ በተለይ ከከተማዋ የሚለቀቁ ፍሳሽና የደረቅ ቆሻሻዎች በጣና ኃይቅና በአባይ ወንዝ ላይ ብክለት እንዳይደርስ በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። በየቦታው የሚጣሉ ፕላስቲኮችን በመሰብሰብ እሴት ጨምረው ለገበያ የሚያቀርቡ 13 ኢንተርፕራይዞች ተቋቁመው እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው፤ "ጥረታቸውን የማገዝ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ብለዋል። በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ብክለት የሚያስከትለውንና በየቦታው የሚጣለውን ፕላስቲክ በአግባቡ ማስወገድ እንደሚገባ የገለፁት ደግሞ የክልሉ አካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ በልስቲ ፈጠነ ናቸው።   በየአካባቢው የሚጣል ፕላስቲክ ለረጅም ዘመን ሳይበሰብስ በመቀመጥ ለጉዳት የሚያጋልጥ መሆኑን ጠቅሰው፤ "ተቀናጅቶ መከላከል የሁሉም አጀንዳ ሊሆን ይገባል" ብለዋል። በንቅናቄ መድረኩ የክልል፣ የከተማ አስተዳደሩና የክፍለ ከተማ አመራር አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።  
በቀጣይ አስር ቀናት የሚጠበቀው እርጥበት የግብርና ተግባራትን ለማከናወን የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል - የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
May 2, 2024 201
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2016(ኢዜአ)፡- በቀጣይ አስር ቀናት የሚጠበቀው እርጥበት የበልግም ሆነ በከፊል የመኸር ወቅት የግብርና ተግባራትን ለማከናወን የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በቀጣይ ቀናት ወቅታዊው ዝናብ ቀስ በቀስ ከበልግ አብቃይ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየቀነሰ በመሄድ ወደ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እንደሚስፋፋ ጠቁሟል። በተጠቀሰው ጊዜ የሚጠበቀው እርጥበት የበልግም ሆነ በከፊል የመኸር ወቅት የግብርና ተግባራትን ለማከናወን የጎላ ጠቀሜታ አለው ብሏል። ቀደም ብለው ለተዘሩ የበልግና የረጅም ጊዜ የመኸር ሰብሎች፣ ለቋሚ ተክሎች፣ በከተማ ግብርና ለሚለሙ የጓሮ አትክልቶች እንዲሁም ለተለያዩ እጽዋት የውሃ ፍላጎት መሟላት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም ገልጿል። የሚጠበቀው እርጥበት ለአርብቶ አደርና ለከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የግጦሽና የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለውና ይህንን መልካም አጋጣሚ የሚመለከታቸው አካላት እንዲጠቀሙበት ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል። በእርጥበቱ የሚገኝ የዝናብ ውሃም ለአርብቶ አደርና ለከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የእንስሳት መኖን በበቂ ሁኔታ ለማሰባሰብና በተገቢው ቦታ ለማከማቸት እንደሚያግዝም ነው ያስታወቀው። በሌላ በኩል በአንዳንድ አካባቢዎች የሚጠበቀው ከፍተኛ መጠን ያለው እርጥበትና የሚኖረው ዝናብ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያስከትል የቅድመ ጥንቃቄ ተግባራትን ማከናወን እንደሚያስፈልግም በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል። መደበኛ የውሃ መፋሰሻዎችን የማጽዳት፣ የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን የማዘጋጀትና ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ የወንዝ ዳርቻዎችን መገደብ እንደሚያስፈልግ ነው ኢንስቲትዩቱ የገለጸው። በተለይም ተዳፋታማና ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ማሳዎች ላይ ሰብሎች በጎርፍ ተጠርገው እንዳይወሰዱ የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን ማዘጋጀት እንደሚገባም እንዲሁ። በእርጥበቱ ምክንያት የሚኖረው ምቹ የአየር ሁኔታ ለበረሃ አንበጣ መራባትና መሰራጨት ምቹ ሊሆን ስለሚችል የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርጉ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።
በክልሉ በየጊዜው ያለአግባብ የሚወገዱ የፕላስቲክ ምርቶች በሰውና እንስሳት ጤና ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት የማስቀረት ተግባር ይጠናከራል
May 1, 2024 187
ጅግጅጋ ፣ሚያዚያ 23/2016 (ኢዜአ)፡- በሶማሌ ክልል በየጊዜው ያለአግባብ የሚወገዱ የፕላስቲክ ምርቶች በሰውና እንስሳት ጤና ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለማስቀረት ቅንጅታዊ ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተመለከተ። በሶማሌ ክልል በየጊዜው ያለ አግባብ የሚወገዱ የፕላስቲክ ምርቶች በአርብቶ አደሩ የቤት እንስሳት ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት፣ የአካባቢ መጎሳቆል እና የአፈር ለምነት ማሳጣት የሚያስከትለው ጉዳት የሚዳሰስ ፓናል ውይይት በጅግጅጋ ከተማ ዛሬ ተካሂዷል።   በክልሉ የአካባቢ ጥበቃና ገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሙህየዲን አብዲ፤ በክልሉ ለስድስት ወር የሚቆይ የአፈር፣ የአየር፣ የውሃ ብክለትንና የድምፅ ሁከትን ለመከላከልና ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወነ ናቸው። በክልሉ በተቀመጠው እቅድ መሰረት ፕላስቲክ የሚያደርስውን ብክለት ለመከላከል በክልሉ አምስት ከተሞች ህብረተሰብን ያሳተፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መካሄዳቸውን ተናግረዋል። "በጅግጅጋ የተዘጋጀው ውይይትም ፕላስቲክ ምርቶች የአርብቶ አደሩ ህብረተሰብ የኢኮኖሚ መሰረት የሆነውን የቤት እንስሳት ከጉዳት ለመታደግ ያለመ ነው" ብለዋል። የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር በየቀኑ ከሚወገደው የደረቅ ቆሻሻ መካከል አብዛኛው ያለ አግባብ የሚጣሉት ፌስታሎች እና ሌሎች የፕላስቲክ ምርቶች መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ሻፊ አህመድ ናቸው። በከተማው በየቀኑ ከሁለት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የፕላስቲክ ውጤቶች እንደሚወገዱ ተናግረዋል ። ከመኖሪያ ቤቶችና ከንግድ ተቋማት በተለያየ መልኩ ጥቅም ላይ ውለው ያለ አግባብ የሚጣሉ የፕላስቲክ ምርቶች በከተማው የጎርፍ መውረጃ ቱቦ በመዝጋትና የአካባቢውን ውበት በማጥፋት የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል። "በክልሉ ከተሞች ያለ አግባብ የሚወገዱና በየቦታው የሚጣሉ ፌስታሎችን የተመገቡ ከብቶች ለሞት እየተዳረጉ ነው" ያሉት ደግሞ የክልሉ አርብቶ አደር ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ገዓል ናቸው።   በቅርቡም በጅግጅጋ እንስሳት በሽታዎች ላብራቶሪ ባለሙያዎች በአንድ ከብት የሆድ እቃ ከፍተኛ መጠን ያለው ፌስታል በቀዶ ህክምና መውጣቱን ለአብነት አንስተዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ አያንሌ በበኩላቸው፤ የፕላስቲክ ውጤቶች በእንስሳትና በሰው ጤና ላይ የሚያስከትሉትን ችግር ለማስወገድ ተቀናጅቶ መስራት ተገቢ መሆኑን አመልክተዋል ።   በመድረኩ ላይ የተገኙት አገር ሽማግሌዎቹ መካከል አቶ አብዲናስር መሀመድ፤ "ከከተሞች የሚወገዱ ቆሻሻዎች የአርብቶ አደሩን እንስሳት በመጎዳት በህብረተሰቡ የጤናና ኢኮኖሚ አደጋ እፈጠሩ ነው" ብለዋል። የችግሩን ስፋት ለአርብቶ አደሩ ለሌላው ህብረተሰብ ለማስገንዘብ እንደሚሰሩም ተናግረዋል ። መድረኩ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ አገር ሽማግሌዎች ፣ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 1361
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 2254
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 1561
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።  
ሐተታዎች
ነገረ - አስተውሎት
Apr 24, 2024 325
ሰው በሀሳብ ከሕይወታዊያን ፍጥረት ይለያል። ከፍጥረቱ ጀምሮ ኑሮውን ቀላል ለማድረግ አስቧል። ሀሳቡም መላ ፈጥሯል። ድንጋይ አፋጭቶ እሳትን አንድዷል። እንስሳትን አላምዶ፣ ሰብልን አባዝቶ፣ መጠለያውን ቀልሶ… ኑረቱን አሳልጧል። ዕለታዊ ተግባሩን ለማቃለል በቁስ ላይ ተመራምሮ አጋዥ ቁስ ፈጥሯል። በሂደትም የኢንዱስትሪን አብዮት አፈንድቷል። በ18ኛው ክፍለ ዘመን በባተው የኢንዱስትሪ አብዮት ዓለም አዲስ ክስተት አስተናግዳለች። ፋብሪካዎች፣ መኪናና አውሮፕላን፣ የእንፋሎትና የኤሌክትሪክ ኃይልና የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች ተፈብርከው ምርትና ምርታማነት ጨምሯል። ከተሜነት አብቧል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ ሮቦቲክስና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች በሰው ተፈጥረዋል። ሳይንስን ለመፍትሔ-እንከን አውሏል። ቴክኖሎጂን ለሁለንተናዊ ሕይወት ማቃለያ ተጠቅሟል። ጊዜ፣ ጉልበትና ሀሳብን ከፈጠራ ጋር አዋዶ ኑሮና ሕይወት አቅልሏል። ኮምፒዩተር ፈበረከ፤ ኢንተርኔትን ፈጠረ፣ ዓለምን አስተሳሰረ። የተዓምር ዘመን ሆነ። ሰው እያስተዋለ... እያስተዋለ… በረቀቀ ጥበብና ግኝት ዛሬ ከዘመነ-አስተውሎት ደረሰ። ሰው ሰራሽ አስተውሎት!! የዘመኑ ቴክኖሎጂ ልህቀት ደረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) እንደሆነ ይጠቀሳል። ዳሩ የቴክኖሎጂው እምርታ የዘመን ክስተት ሳይሆን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት ጀምሮ እርሾ ሲያቦካ እንደነበር የዘርፉ ምሁራን ይጠቅሳሉ። ዋረን ማክኩሎች እና ዋልተር ፒትስ ለዛሬው ሰው ሰራሽ አስተውሎት እርሾ የሆነ በነርቭ አውታረ መረብ የሚታገዝ ሒሳባዊ ሞዴል የፈጠሩት በ1943 ዓ.ም ነበር። በ1950 ዓ.ም ደግሞ አለን ተርኒግ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ማሽን ፈለሰፈ። በተመሳሳይ በ1960ዎቹ አጠቃላይ ችግር ፈቺ፣ ሎጂክ ቴዎሪስትና መሰል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፕሮግራሞች በልፅገዋል። በ1950 ዓ.ም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ራሱን ችሎ እንዲጠና ተወሰነ። ለውስብስብ ችግሮች አይነተኛ መፍትሄ መሆኑ ታመነበት። በ1970 እና 80ዎቹ የዘርፉ ሊቃውንት የሰውን ልጅ የመወሰን አቅም የሚተካ የኮምፒውተር ፕሮግራም ለማበልጸግ ጥረት አድርገዋል። በ1990ዎቹ ምርምሮቹ መቀዛቀዝ ጀምረው ነበር። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዳግም አንሰራርቷል። ስልተ ቀመርን (algorithm) የሚረዱ ማሽኖች ስራ ላይ ውለዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የጥናት ዘርፍ የሰውን ስራና ሃሳብ በኮምፒዩተር መራሽ ቁሶች መተካት ነው። የሰው ልጅ ፍጥረት የሆኑ ማሽኖች መገንዘብ፣ መማርና ችግሮችን እንዲቀርፉ ማስቻልም ነው። ማሽኖች በሰው ልጅ ምትክ አካባቢን ማመዛዘን፣ መማር፣ ማቀድና መፍጠር፣ መተንተንና እንከኖችን ማምከን እንዲችሉ ማድረግ ነው። የሰውን የማሰብ ኅይል በኮምፒዩተር አዳብሮ በሰውኛ ጥበብ ሕይወትን ማቅለል ነው። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅ ያሉትን የስሜት ህዋሳት ክህሎቶች ለማሽኖች በማስተማር ሰዎች ነገሮችን በቀላሉ እንዲያገኙና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው። በዚህም የኮምፒውተር ሊቃውንት ስልተ ቀመር ወይም አልጎሪዝምና አስበው የሚሰሩ ማሽኖች ወደ ስራ እያስገቡ ነው። ለአብነትም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥበብ ቤት የሚያጸዱ ሮቦቶች፣ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች፣ ሰው አልባ ጦር መሳሪያዎች፣ የደህነንት ጥበቃ ካሜራዎች፣… በልጽገው ስራ ላይ ውለዋል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጀመረው ይህ ቴክኖሎጂ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተስፋም ስጋትም ይዞ መምጣቱ ይነገራል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዛሬ ላይ በሁሉም መስክ ገቢራዊ እየተደረገ ነው። በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በግብርና ዘርፎች ምርትና አገልግሎትን ለማቀላጠፍና ለመጨመር ቁልፍ አማራጭ ተደርጓል። ቴክኖሎጂው ከዓለም ገበያ ከ350 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድርሻ አለው። አፍሪካም እያደገ የመጣውን ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ገበያ 10 በመቶ ድርሻ መያዝ ከቻለች እኤአ 2030 አሁን ያለው አህጉራዊ ጥቅል ምርቷ (ጂዲፒ) 50 በመቶ ይጨምራል። ኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በፊት ዘርፉን የሚመራ ተቋም መስርታለች፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን። ኢንስቲትዩቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምህዳር ተጠቃሽ ሀገር ለማድረግ አበክሮ እየሰራ ነው። በቅርቡ የተመረቀው “አስተውሎት” የተሰኘ ፊልም ደግሞ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት በሰው ልጅ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የማይገባበት ሕይወት እንደሌለ ፊልሙ ያስረዳል። በጤና፣ በማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ በመረጃ ፍለጋ፣ በፖለቲካ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በማዕድን ፍለጋና፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የዚህ ቴክኖሎጂ ቁልፍ ሚና ተንጸባርቋል። ዘርፉ ከቅንጦት ይልቅ አስፈላጊነቱ ጨምሯል። ለበሽታ መከላከል፣ ለጤና እንክብካቤ፣ ለትምህርት መሻሻልና ድህነት ቅነሳ ይውላል። ለዚህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረቱ መተግበሪያዎች ፈጠራና አቅም እያደገ መምጣቱ በፊልሙ ተገልጿል። ፊልሙ የኢትዮጵያ የቡና ዛፎችን የበሽታ ስርጭት ለይቶ ለማከም ያለውን ውጤታማነት ያወሳል። ሰው ሠራሽ አስተውሎት የአገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ የሳይበር ደህንነትን ለመጠበቅ፣ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ፣ ምርታማነትን ለመጨመር፣ ገበያን ለማስፋት እና ለመሳሰሉት ሥራዎች በእጅጉ አስፈላጊ ነው። በአሁኑ ወቅት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እየተስፋፉ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል ማሽን ትራንስሌት ወይም የቋንቋ ትርጉም አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያም አንዱን ቋንቋ ወደ ሌላ በመተርጎም አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በዚህም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም በአንድ መተግበሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን መማር እንዲሁም ከድምጽ ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችል ሥርዓትን አበልጽጎ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል። መተግበሪያው አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በድምጽ እና በጽሁፍ ለመማር የሚያስችል ሲሆን ድምጽን ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችለው የመተግበሪያው አካል ድምጽን በመቅዳት ወይም ከመዛግብት (አርካይቭ) የድምጽ ፋይሎችን ወደ መተግበሪያው በማስገባት የጽሁፍ ቅጂውን ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ከፊልሙ መገንዘብ ተችሏል። በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የደረሰበትን ልህቀት ያማከሉና ከዘርፉ ውጤት ለማግኘት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተኬደው ርቀት ይበል የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልህቀት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የዘርፉን ውጤቶች የበለጠ ማላቅ ያስፈልጋል። በዓለም የዕለት ተለት እንቅስቃሴ ውስጥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እያሳደረ የሚገኘውን ተጽዕኖ በመረዳት ለዘርፉ ምርምሮች የሚደረገውን ድጋፍ የበለጠ ማጠናከር ያሻል። ዓለም የሚሄድበትን ፍጥነት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶችን ለመተግበር በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል። (በሰለሞን ተሰራ)      
ብሩህ ነገን የሰነቁ እንስቶች
Apr 19, 2024 567
የሰው ልጆች ከፍጥረት እስከ ዕለተ ሞት ባሉት የሕይወት ዑደቶች ውስጥ በሚገጥሟቸው መልከ ብዙ ፈተናዎች ሳቢያ ራሳቸውን ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋሉ፤ ተገደውም ወደ ማይፈልጉት ሕይወት ይገባሉ። በተለይም ሴቶች በሚገጥሟቸው አይነተ ብዙ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጫናዎች ሳቢያ በበርካታ የህይወት ውጣ ውረድ ወስጥ ያልፋሉ፤ በሂደቱም ለአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የተዳረጉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ቃልኪዳን በላይነህ (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በወጣትነቷ ትዳር መስርታ፣ልጆችን ወልዳ ለመሳም በቅታለች፡፡ ዳሩ ግን ባለቤቷ በድንገተኛ አደጋ በመሞቱ ምክንያት ህጻን ልጆቿን ይዛ ለአስከፊ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጓን ትናገራለች። በዚህም ራሷንና ልጆቿን ህይወት ለማቆየት ወደ ማትፈልገው የወሲብ ንግድ ሕይወት ውስጥ ለመግባት መገደዷን ነው የገለጸችው፡፡ በህፃንነት ዕድሜ ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረገችው ሳምራዊት (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በበኩሏ በአካል ጉዳተኝነቷ ምክንያት ተንቀሳቀሳ መስራት ባለመቻሏ ከተወለደችበት ገጠራማ ስፍራ ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በአዲስ አበባም ህይወቷን በልመና ስትመራ ቆይታለች፡፡ ሌላኛዋ ባለታሪካችን ሔዋን (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) ወደ ማትፈልገው ህይወት ውስጥ ስትገባ የሚያጋጥማት ማህበራዊ ፣ አካላዊ ጥቃት እና ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ትላለች። እሷም ኑሮን ለማሸነፍ የገባችበት የህይወት መስመር ወደ አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንድትገባና ለስነ ልቦናዊ ቀውስ እንድትጋለጥ እንዳደረጋት ገልጻለች። መንግስት በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመታደግ የሚያስችልና “ለነገዋ” የተሰኘ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አንዱ ነው፡፡ ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ ልቦና የምክር አገልግሎት እና በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት ብሩህ ነገን ለማቀዳጀት ስራ ጀምሯል። እነ ቃልኪዳን፣ ሳምራዊት፣ ሔዋንና ሌሎች በችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ‘የነገዋ’ የተሰኘውን የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ተቀላቅለው የተሻለ ነገን ለመኖር ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በማዕከሉ በሚሰጣቸው ሙያዊ ስልጠናና የምክር አገልግሎትም ወደ ተረጋጋ መንፈስ እንዲመለሱ፣ የሕይወት ተሞክሮ እንዲቀስሙ፣ ነጋቸውን ለማሳመር እንዲነሳሱ ስለማድረጉም ይናገራሉ። ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸው፤ መሰል ማዕከላትም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   “የነገዋ” የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄርጳሳ ጫላ ማዕከሉ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ 500 ሴቶችን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከማዕከሉ ሲወጡ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ የሚያደርግ በልዩ የክህሎት፣ የስነ ልቦና እና የሙያ በአጠቃላይ በ18 አይነት የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ስፌት፣ ስነ ውበት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የከተማ ግብርና፣ የሕጻናት እንክብካቤና ሌሎች ዘርፎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንደሚያሰለጥን ነው የገለጹት። ከስልጠናው በኋላ ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማዕከሉ በትብበር እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል፡፡ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 1700
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 2606
  "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።  
ትንታኔዎች
መልከ ብዙው የ"ዳሞታ ተራራ"
Apr 23, 2024 397
የዳሞታ ተራራ ወላይታዎች የሚታወቁበት የራሳቸው የሆነ ባህል፣ ቅርስ እንዲሁም መለያ ምልክት ነው። ዳሞታ የወላይታ የልምላሜ መገለጫና የተፈጥሮ መስህብ ነው። ተራራው በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ 12 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ32 ምንጮችና በ12 ጅረቶች ታጅቦ በኩራት ተንሰራፍቶ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ መጠሪያ ነው። ከዚህ የተነሳ የወላይታ ሶዶ ከተማን ተፈጥሮ ካደላት የዳሞታ ተራራ ሞገሷ የተነሳም ተራራው ፀዳሏ ነው ብለው የሚጠሩትም አልጠፉም። የዳሞታ ተራራ ለአካባቢው ነዋሪም ሆነ አካባቢውን ሊጎበኙ ለሚመጡ እንግዳ ተቀባይነቱን በአረንጓዴ የተፈጥሮ መስህቦቹ በማሸብረቅ ውበቱን በመግለፅ የሚያሳይ ተራራ ነው። ተራራውን ወደ ላይ ለሚመለከተው ዳሞታ ብዙ የሚያሳየውና የሚነግረው ታሪክ እንዳለው ያሳብቃል። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የዳሞታ ተራራ ለ800 ዓመታት ገደማ የቆየ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራ ነው። በጥቅጥቅ ደኖች፣ በወራጅ ወንዞችና ጅረቶች፣ ለመድኃኒትነት በሚያገለግሉ ቁጥር ስፍር በሌላቸው የእፅዋት ዘሮችም የተሸፈነ ነው። በወላይታ ዞን እምብርት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከፍታ ላይ የሚገኘው የዳሞታ ተራራ ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር እንዲሁም የዙሪያ ልኬቱ ከ68 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነም ይነገራል። በአንድ ወቅት ተራራው በአካባቢ መራቆት፣ በአየር ሚዛን መዛባትና በሌሎች ምክንያቶች ግርማውንና ልምላሜውን እያጣ መጣ። ይህም የወላይታን ህዝብ በማሳሰቡ ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ልጅ አዋቂ ሳይል ርብርብ በማድረግ ወደ ቀደመ አቋሙና ሙላቱ ለመመለስ ብርቱ ተፈጥሮን የመከላከል ፍልሚያ አደረገ። ፍልሚያውም በአካባቢው ማህበረሰብ አሸናፊነት በመጠናቀቁ ተራራው ልምላሜውን ጠብቆ አሁን የተላበሰውን ግርማ እንዲይዝ በማድረግ ሊያጣው የነበረውን ጥቅጥቅ ደን በመመለስ የመሬት መሸርሸርን ከመከላከልና የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አልፎ ትልቅ የአይበገሬነት ታሪክ እንደፃፈም ይወሳል። ለዚህም ነው ዳሞታን ከወላይታዎች ማህበረሰቡን ከተራራው ለመለየት እንደማይቻልና ጠንካራ ተዛምዶን የመሰረቱ መሆናቸው የሚገለፀው። የወላይታ ዞን የሀገር ሽማግሌ አቶ አብርሃም ባቾሬ እንደሚሉትም ዳሞታ በርካታ የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የሀገር በቀል እፅዋት፣ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ የወላይታ ነገስታት መናገሻ ስፍራዎች ባለቤት ነው። የዳሞታ ተራራ ከወላይታ ህዝብ ታሪክና ጀግንነት እንዲሁም ከአሸናፊነት ወኔው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑም ያነሳሉ። በዙሪያው ዘመናትን ያስቆጠረ የጥቅጥቅ ደንና የነገስታት መኖሪያ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት የሚገኙበት መሆኑን አንስተው ለወላይታ ሶዶ ከተማም የተለየ ግርማ ሞገስን እንዳላበሳት ተናግረዋል። በዳሞታ ተራራ ዙሪያ የተኮለኮሉት ወንዞችም መነሻቸውን ከተራራው በማድረግ ወደ ታች እየተገማሸሩ ይነጉዳሉ። ወይቦ፣ ቁሊያ፣ ካልቴ ቶቦቤ፣ ሀመሳ፣ ሊንታላ፣ አይከሬ፣ ዋላጫ፣ ጫራቄ፣ ቦልዖ፣ ካዎ ሻፋ፣ ጋዜና ሻፋና ሌሎች ወንዞች ከዚሁ ተራራ ተጎራብተው፣ ከተራራው ያገኙትን መዳኛ ፀበል ለሌሎች ለማቋደስ አየተንደረደሩ ይወርዳሉ። ለአካባቢው ማህበረሰብም ልምላሜያቸውን ያጋባሉ፤ ብርቱውን መሬቱን ምሶ ገበታውን እንዲያበለፅግ ያተጋሉ። ሁሉም ግን የዳሞታ መልዕክተኞች፣ የዳሞታ ተጧሪዎች ናቸው። እንደ አቶ አብርሃም ገለፃ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ የክርስትና ሀይማኖትን በአካባቢው በማስፋፋት ስመ ገናና የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ክርስትናን ለመስበክና መንፈሳዊ ክዋኔዎች ለመፈጸም ዳሞታ ተራራን ይወጡ እንደነበረ ከልጅነታቸው ይነገራቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ ድካም ሲሰማቸው እረፍት የሚያደርጉበት ለመንፈስ ሃሴትን የሚያጎናፅፍ ስፍራ ነው የዳሞታ ተራራ። በዚህ ምክንያት "ጦሳ ፔንጊያ" የእግዜር መተላለፊያ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠውና "ጣዛ ጋሯ" የንጉስ ሞቶሎሚ ቤተ-መንግስት፣ የንጉስ ሞቶሎሚ የጥምቀት ሥፍራ፣ ቆሊ ቦርኮታ፣ ዳጌቾ፣ ቦቄና ሶዶ፣ ጦማ ገሬራና ሌራቶ ጎዳ የተሰኙ ታሪካዊና የሚጎበኙ ስፍራዎች ይጎበኙበታል በዳሞታ ተራራ። ካዎ ሞቶሎሚ፣ ካዎ ዳሞቴ፣ ካዎ ጎቤና ካዎ ጦና የሚባሉ የወላይታ ነገስታት ቤተ-መንግስታቸውን በተራራው አናትና ግርጌ ላይ ይገነቡ እንደነበር አቶ አብርሃም ይናገራሉ። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዳሞታ ተራራ በወላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያለው መሆኑን ይገልፃሉ። ከተራራው አናት መነሻቸውን የሚያደርጉ ወንዞች የወላይታን ምድር አጥግበው ሰዎችና እንስሳቱን አጠጥተው ወደ ብላቴ እና ኦሞ ወንዝ ይፈሳሉ። የዳሞታ ተራራ ሌላው ጠቀሜታው መሬት እንዳይሸረሸር ቀጥ አድርጎ በዛ ግዝፈቱ ይዟል ይሄም ለመንገድ ደህንነትና የአካባቢውን አየር ተስማሚ ከማድረግ አኳያ አይተኬ ሚና አለው። በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነው የዳሞታ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከዘመናት በፊት ተጀምሮበታል ይላሉ አስተዳዳሪው። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በከፊል ለሶዶ ከተማ የሚያጠጣውን የዳሞታ ተራራ የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ከዩኒቨርስቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነውም ብለዋል። የዳሞታ ተራራ ታሪካዊ ይዘቱን ስንመለከት አካባቢው ቀደም ሲል የነገስታት መናገሻ ቦታ ነበር የሚሉት ደግሞ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር አበሻ ሽርኮ ናቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከወላይታ ሥርወ-መንግስት መካከል ካዎ ሳቴ ሞቶሎሚና የሌሎች ነገሥታት መናገሻ ስፍራ ስለነበር በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ታሪካዊ ስፍራ ነው። የዳሞታ ተራራ ለአብዛኞቹ በወላይታ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች የስያሜያቸው መነሻ ነው። ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞታ ወይዴ፣ ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎችና ሌሎች ቀበሌያት የተራራውን ስም መነሻ ያደረጉ መሆኑ ተራራውን ታሪካዊ ያደርገዋል። እዚሁ ተራራ ላይ ካሉ የተለያዩ መስህቦች መካከል የጥንታዊ ዋሻ "ሞቼና ቦራጎ" ዋሻ አንዱ ነው። ይህ ዋሻ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ የጥንት ሰው መኖሪያ ዋሻ ነበር። ዋሻው በዳሞታ ተራራ ከሚገኙ ከአምስት በላይ ዋሻዎች አንዱ ሲሆን በተራራው በስተምዕራብ አቅጣጫ በኩል የሚገኝና ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ሰዎች በዚሁ ዋሻ ይኖሩ እንደነበረም ታሪክ ያስረዳል። ሞቼና ቦራጎ ዋሻ ስፋቱ 38 ሜትር፣ የጣሪያው ከፍታ 33 ሜትር፣ የዋሻው ዙሪያ ልኬት ደግሞ 58 ሜትር፣ እንዲሁም በውስጡ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የመያዝ አቅም ያለው እንደሆነም መረጃዎች ያመላክታሉ። ሌላው ከዳሞታ ተራራ መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን ደብረ-መንክራት አቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም ላስተዋውቃችሁ። ይህ ገዳም ለአቡነ ተክለኃይማኖት መታሰቢያነት በ1887 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ከመመስረቱ ጋር በተያያዘ የተገነባና በዳሞታ ተራራ ምዕራባዊ ራስጌ የሚገኝ የቱሪስት መስህብ ሥፍራ እንደሆነ ነው ዶክተር አበሻ የሚናገሩት። ገዳሙ የአምልኮና የፀበል አገልግሎት እየሰጠ ከአንድ ክፈለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ በወላይታ ዞን ካሉ መንፈሳዊ ስፍራዎች አንዱ ሲሆን በውስጡ በርካታ ሐይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ ጉዞ ከሚደረግባቸው መዳረሻዎች አንዱ ነው። በመሆኑም አካባቢው ለቱሪስት መዳረሻነት፣ ለአካባቢው ልማት ብሎም ለአየር ንብረት ሚዛንን መጠበቅ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።            
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 3963
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2727
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 2595
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11941
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16309
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 8438
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 9534
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 26901
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 22296
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16309
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12501
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11941
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 11308
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 11076
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 10592
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 26901
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 22296
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16309
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12501
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
ከፈተናዎች ባሻገር . . . !
May 4, 2024 158
ከፈተናዎች ባሻገር . . . ! (በቀደሰ ተክሌ ከሚዛን አማን ኢዜአ) በዓለም ውስጥ ሆኖ በአንዳች ምክንያት የወደቀ ይነሳል፤ የታመመ ይድናል፤ የፈረሰ ይጠገናል፤ የደከመ ይበረታል፤ የተኛ ወይም ያንቀላፋም ይነቃል። ይህን እውነት ሰው በልቡ ተስፋ አድርጎ ውሎ ያድራል።ነገን ያልማል። "ሲጨልም ይነጋል" እያለ ለራሱ ይጽናናል። መከራ ሲበዛበት "ሊነጋ ሲል ይጨልማል" በሚል አዲስ ተስፋን በውስጡ ይዘራል። ከእነዚህ ተቃራኒ የሰው ልጅ ከህይወት ዑደት ኩነቶች ባሻገር በተለያዩ የእምነት ተቋማት አስተምህሮ ደግሞ የሞተ የሚነሳበት መንፈሳዊ ተስፋ አለ። ይህም ትንሣኤ ይባላል- ከሞት በኋላ የሚኖር ሕይወትን የሚያሳይም መነጽር። "ትንሣኤ" ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን፤ ቀጥተኛ ትርጉሙ መነሳት ነው። መነሳት የሚነገረው ለወደቀ፤ ለደከመ እና ለሞተ ነው። እንዲሁም ከነበረበት ከፍ ማለት ቀና ማለት መለወጥና ወደ አዲስ መልካም ነገር መሸጋገርን ያመለክታል። በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትንሣኤ የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስን ከሞት መነሳትን መሠረት በማድረግ ነው። ክርስቶስ በምድር ሲመላለስ የሰው ልጆች ማድረግ ስለሚገባቸው በጎ ምግባራት እርሱ በመተግበር አስተምሯል። የበጎ ተግባራት ውጤት ደግሞ ከሞት በላይ ራስን ከፍ አድርጎ በሕይወት ዙፋን ላይ መቀመጥ እንደሆነ አሳይቷል። ፍቅር እንዲጎለብት ለሌላው መኖርና አልፎም መስዋዕት መሆንን በግልጽ አንጸባርቋል። እርሱ መልካም ነገር አድርጎ "እናንተ እንዲሁ አድርጉ" ብሏል። ለአብነትም ፍቅር በቀዳሚነት የሚጠቀስ ትምህርቱ ነው "እርስ በእርስ ትዋደዱ ዘንድ ትዕዛዜ ይህች ናት" ብሏል። ፍቅሩን ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ በመስጠት ገልጧል። ነገ ምን እንዲያውም ከደቂቃዎችና ሰዓታት በኋላ ምን እንደሚፈጠር በማናውቀው ተገድቦና ተተምኖ በተሰጠን የህይወት ዑደት ውስጥ በምናልፋቸው የትኞቹም ጎዳናዎች ምህረትን፣ ይቅር ባይነትን ይጠየቃል። ለሰው ልጅ ለራሱም ቢሆን ቂምና ቁርሾ ያላደረበት ልብ ያስፈልገዋል። የወደደንን ወይም የሰበሰበንን ሳይሆን ተቃራኒውን የፈጸመብንን የመውደድና ፍቅርን በተግባር የማሳየት ልምምድ እንዲኖረን ያስተምራል። ይህም ከራሳችን ጀምሮ ለአካባቢያችን ሁሉ ሰላምና መረጋጋትን ይፈጥራል። ሌላው የተግባር ትምህርቱ ትህትና ነው። የሰው ልጆችን ለማክበር ራሱን ዝቅ አድርጓል። የደቀ መዛሙራቱን እግር ተንበርክኮ አጥቧል። "እናንተም እንዲሁ ለሌሎች አድርጉ" ሲልም አስተምሯል። የዚህ ዓይነቱ ተግባር ዛሬም በኢትዮጵያውያን እሴት ውስጥ ይስተዋላል። በትውፊት ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፉ መጥቷል። ቤታችን የወላጆቻችንን አልፎም የመጣን እንግዳ እግር ማጠብ የመልካም ሥነ ምግባር ምገለጫችን ሆኖ ቆይቷል። ይህ እርስ በርስ መከባበር እያጠነከረ ይመጣል፤ ውሎ ሲያድርም በስነ ምግባር የታነጸ የጠንካራ ማህበረሰብ መገለጫም ይሆናል። ትህትና ከአንገትን ጎንበስ ብሎ ሰላምታ መሰጣጣት ብቻ አይደለም። ሌሎች የተሻሉ እንዲሆኑ ማሰብን ያካተተ ከልብ የሚፈልቅ ተግባር ነው። በትዕቢት አውቃለሁ ባይነት ሳይሆን ራስን ዝቅ በማድረገ መንፈስ የተገዛ ማንነት ማዳበርን ይጠይቃል። ድርጊት የሀሳብ ውጤት ነው። ስለሆነም እርስ በርሳችን ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ እንዲሁም በስራ ቦታችን ካሉ ባልደረቦቻችንን ከልብ በመነጨ ትህትና መቀበልና ማስተናገድ አልፎም መታዘዝ ይጠበቅብናል። ይህ ነው የትህትና ጥቅ እሴቱ። በጎነት፣ ፍቅር፣ ትህትና፣ ለጋስነትና ቅንነትን የሰው ልጅ ገንዘቡ ቢያደርግ ሞትን አሸንፎ ይከብራል። ከመውደቅ ባሻገር መነሳት አለ። ከጨለማ በኋላ ብርሃን ይኖራል። ይህም ከጽልመትና ከአስቸጋሪ ነገሮች አልፈን ብርሃን ማየት እንደሚቻል የጸና ተስፋ በመያዝ ነጋችንን ማየት ይኖርብናል። ትንሣኤ ደስታ ነው፥ ከድቅ ድቅ ጨለማ በኋላ የሚገኝ ልዩ ብርሃን፤ ከመቃብር በላይ የሚገኝ ሐሴት ነው። የትላንት መከራ ላይ የታነጸ ጽኑዕ ደስታ፤ የትላንት መልካም ነገርን መነሻ አድርጎ የሚገኝ ክብር ነው። የሰው ልጅ በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ነገን ተስፋ አድርጎ ጠንክሮ መስራት ከቻለ መልካም ነገር ሁሉ ማግኘት ይችላል። ዛሬም ዓለም ብዙ ውጣ ውረዶችን ታስተናግዳለች። እንደ አገር ኢትዮጵያ ብዙ ችግሮች እያጋጠሟት ነው። ችግሮቹና መከራው ማብዛቱ የነገን ትንሣኤ ለማምጣት ነው። ከፈተናዎች ባሻገር ድል አለ፤ ትንሣኤ ይገለጻል። ለዚህም ነው ምንም ፈታኝ ነገር ቢኖር፣ ችግሮች ቢደራረቡም ተግቶ ሰርቶ ወደ ብርሃኑ መውጣት ይቻላል የምን ለው። የትንሣኤ በዓል ከበዓል ባሻገር በበጎ እይታ በመቃኘት፣ በፍቅር በመታነጽና የቅንነት ጎዳናን በመያዝ ለአገር እና ለራሳችን ክብርን ለመጎናጸፍ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት መሆን አለበት።      
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ 
Mar 5, 2024 3901
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም