በማሌዢያ በሄሊኮፕተር አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2016 (ኢዜአ)፦በማሌዢያ ሁለት በበረራ ላይ የነበሩ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች በመጋጨታቸው የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ።

በሮያል ማሌዥያ ባህር ሃይል አካባቢ ሲጓዙ የነበሩት ሁለቱ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች አየር ላይ በመጋጨታቸው በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አናዶሉ ዘግቧል።

በአደጋው ሶስት ሴት መኮንኖችን ጨምሮ የአስር ባለሙያዎች ሕይወት ማለፉ ነው ዘገባው ያመለከተው።

ከሟቾቹ መካከል ሰባቱ በባሕር ኦፕሬሽን ሄሊኮፕተር ሲጓዙ እንደነበርና የቀሩት በአርኤምኤን ፌነክ ሄሊኮፕተር ውስጥ እንደነበሩ ተገልጿል።

የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴርም የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ አንደሚገኝ በገዘባው ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም