የኢጋድ አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ጅግጅጋ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016(ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት(ኢጋድ) አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የአባል ሀገራቱ ሚኒስትሮች ዛሬ ማለዳ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር)ን ጨምሮ የኬኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳና ጅቡቲ የውሃ ሚኒስትሮች ጅግጅጋ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።


 

በክልሉ ሸበላይ ወረዳ በሚካሄደው በቀጣናው ሀገራት መካከል የሚኖሩ ዜጎችን ታሳቢ ያደረገ ድንበር ተሻጋሪ የከርሰምድር ውሃ አጠቃቀም ላይ የሚመክረው መድረክ ላይ ከውሃ ሚኒስትሮች በተጨማሪ የዩኒሴፍና ሌሎች አጋር ድርጅቶች መገኘታቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም