ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያረጋግጡ ውጤታማ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው
May 25, 2026 289
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያረጋግጡ ውጤታማ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ፍትሐዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በዓለም አቀፍ ማዕቀፍ የዲፕሎማሲ መርህ መሳካት የሚችል የህልውና ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል። ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያረጋግጡ ውጤታማ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች። የኢትዮጵያ ፍትሕዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ለመፍጠር ከምታደርገው ጥረት ጋር ተለይቶ የሚታይ እንዳልሆነ አስረድተዋል። በኢትዮጵያዊያን የጋራ መስዋዕትነት በተገነባው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ስትራቴጂ መነሻነት አህጉራዊ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማፋጠን ኢትዮጵያ ፀጋዎቿን በመጠቀም በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ነው ያመለከቱት። ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር ያላትን ቁርኝት ተፈጥሮን ከመልክዓ ምድራዊ ታሪካዊነትን ከሕጋዊነት ያሰናሰለ መሆኑን አስረድተው፤ የባሕር በር ባለቤትነቷን እንድታጣ የተደረገበት በሴራና ተንኮል የተሸረበ አካሄድም የሚያስቆጭና ኢትዮጵያን ደካማ ለማድረግ ካለ እሳቤ የመነጨ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ፀጋዋን በመጠቀም ዕድገትን ካረጋገጠች ስጋታችን ትሆናለች የሚለው ስሌትም የታሪካዊ ጠላቶች ኋላቀርና የተሳሳተ ደምዳሜ ነው ብለዋል። በዚህም የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ታሪካዊ መሠረተ ያለው፣ ተፈጥሯዊና መልክዓ ምድራዊ እውነታ ያለው ሕጋዊና ፍትሐዊነትን አሰናስሎ የያዘ የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ቦሊቪያና ፔሩ፣ ብራዚልና ፓራጓይ፤ በአፍሪካ የማሊ፣ ሴኔጋልና ኮትዲቯር የተጠቀሙባቸውን የጋራ መፍትሔዎች በተሞክሮነት አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ፍትሐዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በዓለም አቀፍ ማዕቀፍ የዲፕሎማሲ መርህ መሳካት የሚችል የህልውና ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም የኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ ሕጋዊ፣ መልክዓ ምድራዊና ፍትሕዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ማሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል። ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ላላት ሀገር የቅንጦት ሳይሆን የኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን የሚያስከብር ቁልፍ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። ለወደብና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በየዓመቱ የምታወጣው ከፍተኛ ሃብት ዓለም አቀፍ የንግድ ተወዳዳሪነትና በጠቅላላው የዕድገት ጉዞ ላይ ትልቅ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አስገንዝበዋል።
በምግብና መጠጥ ማቀነባበር የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ህብረተሰቡ በንጥረ ነገር የበለፀጉ ምርቶችን እንዲያገኝ እያደረጉ ነው
May 25, 2026 162
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ በግብርና ምርት የምግብና መጠጥ ማቀነባበር የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ህብረተሰቡ በንጥረ ነገር የበለፀጉ ምርቶችን እንዲያገኝ እያደረጉ መሆናቸውን የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለጸ። በአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ከቴክኖ-ሰርቭ ጋር በመተባበር የበለፀገ የስንዴ ዱቄትና የምግብ ዘይት የገበያ ትስስር ፎረም በአዲስ አበባ አካሂዷል። የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ደበበ ወርቁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በምግብ ዘርፍ የስንዴና የማሽላ ዱቄት የጨውና የዘይት ምርቶች አስገዳጅ ደረጃ ወጥቶላቸዋል። በዚህም አምራች ኢንዱስትሪዎች የበለፀገ የምግብ ምርት ዝግጅት ሰርተፊኬት በመውሰድ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የምግብ ምርት አምራቾችም በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ምርቶችን ለማህበረሰቡ በማቅረብ ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በንጥረ ነገር በለፀገ የምግብ ምርታማነት አቅም ጤናማና አምራች ዜጋን በማፍራት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው አንስተዋል። በቀጣይም በበለፀገ የምግብ ምርት ማቀነባበር ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ በማድረግ የምርት ጥራትና አቅማቸውን እንዲያሳደጉ ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል። በቴክኖ ሰርቭ ተቋም የሚለር ፎር ኒውትሬሽን ፕሮግራም ማናጀር ገረመው ጣሰው በበኩላቸው፤ አምራቾች የተሳለጠ የምግብ ማበልፀግ ሥራ እንዲያከናውኑ የቴክኒክ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል። በቀጣይም በበለፀገ የምግብ ማቀነባበርና ዝግጅት ለተሰማሩ ድርጅቶች የሚያደርገውን አተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የዋኬኒ ምግብ ፋብሪካ ፕሮዳክሽን ማናጀር አማኑዔል ታደሰ፤ መንግስት ለፋብሪካዎች የሰጠው ልዩ ትኩረት ምርቶቻችንን በጥራትና በስፋት ተደራሽ እንድናደርግ አስችሎናል ብለዋል። ሌላኛው የዲና ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የሽያጭና ስርጭት ሥራ አስኪያጅ እንየው ጫኔ በበኩሉ፤ ኢትዮጵያ ታምርትን ጨምሮ መንግስት ዘርፉን ለማሳደግ የሚያደርገው ድጋፍ እያደገ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ የአርብቶ አደሩ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚነት እያደገ መጥቷል
May 25, 2026 228
ሰመራ፣ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፡- በአርብቶ አደሩ አካባቢ ለንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ በተሰጠው ትኩረት ተጠቃሚነቱ እያደገ መምጣቱን የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት ቢሮ ኀላፊ አቶ ኡመር ኑር ገለጹ ። በክልሉ አፍዴራና ቢዱ ወረዳዎች ከ65 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት ቢሮ ኀላፊ አቶ ኡመር ኑር በወቅቱ እንደገለፁት በአርብቶ አደሩ አካባቢ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ለተቋማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል ። በዚህም አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚነቱ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። በወረዳዎቹ ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁት የውሀ ተቋማትም የጥረቱ አካል መሆናቸውን ጠቅሰዋል ። አካባቢው በረሀማ በመሆኑ የንፁህ መጠጥ ውሃ በቀዳሚነት አሰፈላጊና ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቁመው ከተለያዮ አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት አገልግሎቱ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ አህመድ ሻሚ በበኩላቸው እንዳሉት በክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በወረዳዎቹ ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁት የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋማት በጸሀይ ሀይል የሚሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው ተቋማቱ በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክትና በወርልድ ቪዥን የገንዘብ ድጋፍ በትብብር የተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። በአፍዴራ ወረዳ ነማ ጉቢና ቀበሌና በቢዱ ወረዳ ቢዱ ሶዶምታ ቀበሌ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁት የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋማት ከ30 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ አመልክተዋል። የአፍዴራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲራጅ መሀመድ የውሀ ተቋሙ መገንባት የህብረተሰቡን ጥያቄ የመለሰ መሆኑን አስታውቀዋል።
የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ የመዝናኛ አማራጭ እየፈጠረ ነው
May 25, 2026 221
አሶሳ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ የመዝናኛ አማራጭ እየፈጠረ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን ተናገሩ። ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የከተማዋ የኮሪደር ልማት አካል የሆነውን የአሶሳ ሲቲ ፓርክን ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት፤ በአሶሳ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት በርካታ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አብረው እንዲገነቡ አድርጓል። ልማቱ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ የመዝናኛ አማራጭ እየፈጠረ መሆኑንም ተናግረዋል። ለዚህም የኮሪደር ልማቱ በሚከናወንባቸው አካባቢዎች በዘመናዊ መልኩ የተገነቡትን የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ የሕጻናት መጨዋቻ እና የመዝናኛ ቦታዎች በማሳያነት ጠቅሰው፤ የልማት ሥራዎቹም ለትውልድ የሚተርፉ ናቸው ብለዋል። አሶሳ ሲቲ ፓርክ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት ከመሆኑ ባለፈ ሕፃናት አዕምሯቸው እንዲታደስ የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችን አካቶ መገንባቱንም ተናግረዋል። የክልሉ መንግስት በሌሎች አካባቢዎችም የኮሪደር ልማቱን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማከናወን ለነዋሪዎች ምቹና ጽዱ ከተሞችን ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል ብለዋል። የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አብዱልከሪም አብዱራሂም በበኩላቸው፤ የአሶሳ ሲቲ ፓርክ የከተማዋን የመዝናኛ ማዕከል እጥረት ችግር የፈታና ለሕፃናትም ልዩ ስጦታ መሆኑ ጠቁመዋል።
ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋችንን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
May 25, 2026 257
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋችንን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የተፈጥሮ እውነት ከታሪክ ክብር ጋር በተዋሃደባት፣ በጣና ሐይቅና በዓባይ ወንዝ በታጀበችው የውበት ማማዋ ባሕር ዳር ገብተናል ብለዋል። በመልዕክታቸውም ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋችንን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስንደርስ፣ ፍቅርና አክብሮት በተሞላበት ሁኔታ ለተደረገልን ደማቅ አቀባበል ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉና ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ በጸሎትና በምርቃታቸው ላልተለዩን የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ለመላው የባሕር ዳር ሕዝብ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።
ፖለቲካ
የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ልምምድ እየዳበረ መምጣቱ የታየበት ነው
May 25, 2026 325
ጎንደር፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ልምምድ እየዳበረ መምጣቱ የታየበት መሆኑን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ፡፡ ፓርቲዎች በሃሳብ የበላይነት ክርክር ያካሄዱበትና የዜጎች ሰፊ ተሳትፎ የታየበት መሆኑንም ተናግረዋል። በርካታ ዜጎች ድምጽ ለመስጠት ካርድ የያዙበትና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። በዚህ ታሪካዊ እለትም ዜጎች ድምፃቸውን በመስጠት ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት እለቱን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው። በምርጫ ሂደቱ አጠቃላይ የዜጎች ተሳትፎና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ሲል ኢዜአ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ምሁራንን አነጋግሯል። ምሁራኑ በአስተያየታቸው ጠቅላላ ምርጫው የእስካሁኑ ሂደት የሃሳብና የፖሊሲ ክርክሮች የተካሄዱበት ስለመሆኑ አንስተዋል። በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ አንዳርጋቸው ተስፋሁን፤ የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ልምምድ እየዳበረ መምጣቱን ያመላከተ መሆኑን ገልጸዋል። የምርጫ ሂደት አንዱ የዴሞክራሲ መገለጫ መሆኑን አንስተው በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክርና አጠቃላይ የዜጎች ተሳትፎ ለዚህ ጥሩ መገለጫ መሆኑን አንስተዋል። ሌላው አስተያየት ሰጪ በዩኒቨርሲቲው የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናት ክፍል የስትራቴጂና የወቅታዊ ጉዳዮች ጥናት አስተባባሪ ሀቢብ ሰይድ ናቸው። የምርጫ ሂደቱ እስካሁን በዜጎች ጠንካራ ተሳትፎ በፓርቲዎች ጠንካራ የፖሊሲ ክርክሮች በሃሳብ የበላይነት መካሄዱን አንስተዋል። በመሆኑም ሂደቱ በኢትዮጵያ የህዝብ ተሳትፎ የታየበት የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እውን እየሆነ መምጣቱን ያመላከተ መሆኑን ገልጸዋል። የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መገለጫ ውጤቱ ብቻ ሳይሆን ሂደቱ ፍትሃዊ፣ አካታች፣ ሰላማዊና ተአማኒ መሆን እንዳለበት አንስተው የእስካሁኑ ሂደትም ይህንኑ ያመላከተ መሆኑን ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው የስነ ጽሁፍ መምህር የሆኑት ገብሬ ሙሉዓለም (ዶ/ር)፤ የምርጫ ሂደት የአንድ ሀገር የዴሞክራሲ ባህል የሚጎለብትበት፣ እድገትና ልማትን የሚወስን ትልቅ መሳሪያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ጥሩ መሰረት እያኖረ መሆኑን አንስተው እስከ መጨረሻው በስኬት እንዲጠናቀቅ የሁላችንም ጠንካራ ተሳትፎ ያስፈልጋል ብለዋል። በዩኒቨሲቲው የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል መምህርት የሺወርቅ ተዘራ፤ ምርጫ የአንድ ሀገር የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደትና የስልጡን ፖለቲካ መገለጫ መሆኑን አንስተዋል።
ለህዝብ የገባነውን ቃል ለመፈፀም የማያቋርጡ ተግባራት እየተከናወኑ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
May 25, 2026 202
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ለህዝብ የገባነውን ቃል ለመፈፀምና ብልጽግናን እውን ለማድረግ የማያቋርጡ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሰባተኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት አዲስ ባለ 6 ወለል ህንፃ በመገንባትና በቴክኖሎጂ በማደራጀት ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን አመልክተዋል። ለዘመናት በተንዛዛ አሰራርና እጅ መንሻ እየተጠየቀበት ዜጎችን ሲያማርር የነበረውን የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ስርነቀል በሆነ መልኩ ለመፍታት የመፍጠንና መፍጠር መርህ እየተከተለ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በዚህም የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ፍትሃዊ ለማድረግ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አግልግሎት አንድ ብሎ መጀመሩን ነው ያነሱት። ይህን ዲጂታል አገልግሎት ለማህበረሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ቀንና ሌሊት በከፍተኛ ትጋት ሲሰራ መቆየቱንም እንዲሁ። በዚህም መሰረት ዛሬ ሰባተኛውን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ማዕከል ለአግልግሎት ክፍት ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል። ህዝብ ወደ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች በመሄድ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ በተንቀሳቃሽ የአዲስ መሶብ አገልግሎት ይበልጥ ወደ ህዝቡ እንዲጠጋ በማድረግም አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ነው ያብራሩት። ለህዝብ የተገባውን ቃል ለመፈፀም እንዲሁም ብልጽግና እውን እንዲሆን ተከታታይነት ያለው የማያቋርጥ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይ ህብረተሰቡ በሚቀርበው ማዕከል ያለምንም መንገላታት በመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ -ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
May 25, 2026 273
ሆሳዕና፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ። የክልሉ መንግስት ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል። መድረኩ "ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ ከአደረጃጀት ሽግግር ወደ ልማት ማዕከል" በሚል መሪ ሀሳብ በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ የለውጡ ገፊ ምክንያቶች፣ ከለውጡ በኋላ የተመዘገቡ ስኬቶችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን የሚያሳይ የመነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ ክልሉ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ አንስቶ የማህበረሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረጉ የልማት ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። በተለይም ሀገራዊ የእድገት አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ በተሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቁመው፤ በቀጣይም በትውልድ ግንባታ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ በመቀጠል የክልሉን ፈጣን እድገት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ክልሉ ያለውን ጸጋ ለይቶ በማልማት ረገድ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። አካታች የፖለቲካ ምህዳርን ከመፍጠር አኳያም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትብብር የመስራት እሳቤን በመጠቀም ለክልሉ ፈጣን እድገት በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር በሰጡት አስተያየት፤ በመንግሥት የሚነደፉ አዳዲስ የልማት ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ስራ በመሰራቱ ክልሉ በግብርናውና በሌሎችም መስኮች ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን አስረድተዋል። በፓናል ውይይቱ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ለዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ገለጻ ተደረገ
May 25, 2026 350
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ አዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶችና ለአለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ገለጻ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሰቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለዲፕሎማቶችና ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ስለምርጫው ዝግጅት፣ የመራጮች ምዝገባ፣ የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎ፣ የደህንነት ዝግጅቶች እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዝርዝር በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል። እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ግልፅ እና ነፃ እንዲሆን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት ስለመሰራቱ አብራርተዋል። የቦርዱ ሰብሰቢዋ ምርጫውን በተመለከተ ስለተከናወኑ የቅድመ ምርጫ ስራዎች ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ለምርጫው ከ50 ሚሊየን በላይ መራጮች መመዝባቸውንና 52 ሺህ 29 የምርጫ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን ገልጸዋል። ለተፈናቃዮች፣ ለወታደሮችና ለተማሪዎች ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን እንዲሁም የምርጫ ድምጽ መስጫ ካርዶች ለሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች መሰራጨታቸውን አብራርተዋል። በተጨማሪም ምርጫው ሰላማዊ፣ አሳታፊ እና ነጻ እንዲሆን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ቦርዱ እየሰራ መቆየቱን ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በበኩላቸው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በተከታታይ ሲደረጉ የቆዩ ምርጫዎች ቀጣይ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም በሀገሪቱ ለተገነባው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰረት የጣለ መሆኑን አብራርተዋል። ከገለጻው በኋላ በተደረገ ውይይት የተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ምርጫው ሰላማዊና አሳታፊ እንዲሆን ስለተደረገው እንቅስቃሴ ግንዛቤ እንዳገኙ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።
በብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል - ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ
May 25, 2026 334
ጉኑኖ ሐሙስ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፡- በብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ተናገሩ። በወላይታ ዞን የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ እና የዳሞት ሶሬ ወረዳ በጥምረት ያዘጋጁት የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በጉኑኖ ሐሙስ ከተማ ተካሂዷል። ሚኒስትር ሸዊት በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ በፓርቲው የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ በርካታ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል፡፡ በዞኑ ጤና፣ ትምህርት፣ መንገድ እና ኮሪደርን ጨምሮ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ሥራዎች የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውንም አስረድተዋል። በፓርቲው መሪነት በተከናወኑ ሥራዎች የወላይታ ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዩኔስኮ መመዝገቡን አውስተው፤ የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል የሕዝቡ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። በብልጽግና ፓርቲ መሪነት የሕዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የፈቱ በርካታ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን ያነሱት ደግሞ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ናቸው። በፓርቲው መሪነት እንደ ወላይታ ዞን የሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች እየተፈቱ መጥተዋል ብለዋል። ይህንን የሕዝብን የልማት ተጠቃሚነት ለማስቀጠል ብልጽግና ፓርቲን መምረጥ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል። የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ ዋጃ በበኩላቸው፤ ብልጽግና ፓርቲ የሚመራው መንግሥት የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሠራው ሥራ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል። በዚህም ከ500 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድ፣ የመብራት፣ የትምህርት፣ የጤና እንዲሁም ሌሎች ልማቶችን በከተማዋ ማከናወን መቻሉን ለአብነት ጠቅሰዋል። መንግሥት የወረዳውን ነዋሪዎች በአጭር ጊዜ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በፖለቲካ ዘርፎች ተጠቃሚ ያደረጉ ልማቶች እንዲከናወን አድርጓል ያሉት ደግሞ የዳሞት ሶሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉቀን መሸሻ ናቸው። በዘንድሮ በጀት ዓመት በ150 ሚሊየን ብር ወጪ ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የመንገድ፣ የጤና፣ የንጹህ መጠጥ ውሃና ሌሎች ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ወደ ሥራ መግባታቸውንም አንስተዋል። በተጨማሪም የ15 ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድ ግንባታ ሥራን ጨምሮ ሌሎችም ልማቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ገጠርን ከከተማ ጋር ለማስተሳሰር በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።
የኢትዮጵያን ተስፋ ብሩህ ሊያደርግ ይችላል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የቦዲቲ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ገለጹ
May 25, 2026 267
ቦዲቲ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በካርዳችን የነገዋ ኢትዮጵያን ተስፋ ብሩህ ሊያደርግ ይችላል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የቦዲቲ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ገለጹ። አስተያየታቸው ለኢዜአ ከሰጡት መካከል አቶ ተመስገን ጫማ እንዳሉት፤ በወሰዱት ካርድ የነገይቱን ኢትዮጵያ ተስፋ ብሩህ ሊያደርግ ይችላል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ዕለቱን እየጠበቁ ነው። ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ መሳተፍ ሳይችሉ መቆየታቸውን የተናገሩት ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ዘነበች ጋንአሞ፤ አሁን ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ በመውሰዳቸው ዕድለኛ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በወሰዱት ካርድ ለሀገር ሰላምና ልማት መጠናከር የተሻለ የሚሠራውን ፓርቲ ለመምረጥ እንደተዘጋጁም አስረድተዋል። አቶ ባሩድ በርገነ እና መምህር ታምራት ዮናስ በበኩላቸው፤ ምርጫው ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በንቃት ለመሳተፍ ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል። በምርጫ ክርክሩ በተከታተልነው መሰረት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማት የተሻለ ፖሊሲና ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢኮኖሚ አማራጭ ያለውን ፓርቲ በመምረጥ ለነገይቱ ኢትዮጵያ መጽናት የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። ዜጎች ለምርጫው ሰላማዊነትና ፍትሐዊነት የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለባቸውም መክረዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በሀገር ጉዳይ እኩል ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እውን አድርጓል
May 25, 2026 277
ቀብሪ ደሃር፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የብልጽግና ፓርቲ በሀገር ጉዳይ እኩል የፖለቲካ ተሳትፎና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እውን ማድረጉን በፓርቲው የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና የዐቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አብዱራህማን አህመድ ገለጹ። ፓርቲው በሶማሌ ክልል ቆረሃይ ዞን ቀብሪ ደሃር ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ እና የማኒፌስቶ ማስተዋወቅ የማጠቃለያ መርሐ-ግብር አካሂዷል። አቶ አብዱራህማን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ብልጽግና ፓርቲ በሀገሪቱ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት እንዲገነባ ራዕይ ሰንቆ እየሠራ ነው። ብልጽግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ በሀገር ጉዳይ እኩል የፖለቲካ ተሳትፎና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እውን ያደረገ መሆኑን አንስተው፤ ዜጎች ፍትሐዊና እኩል የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አቅዶ እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል። ፓርቲው ከዚህ በፊት በሀገሪቱ የተፈጠሩትን ችግሮች በማረምና ስብራቶችን በመጠገን ዕቅዶችን በመንደፍ የተለያዩ ተግባራት በማከናወን ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል። በተለይም የክልሉ ሕዝብ ከሀገሪቱ ፖለቲካ የዳር ተመልካችነት ወጥቶ እኩል ተሳትፎ በማድረግ የልማት ተጠቃሚነቱ የተረጋገጠበት ወቅት መሆኑን አረጋግጠዋል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ያደረጉ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች መከናወናቸውንም ለአብነት አንስተዋል።
ምርጫው በስኬት እንዲከናወን የሚጠበቅብንን እየተወጣን ነው- የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች
May 25, 2026 267
ደሴ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፡- 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ እንዲሆን የአካባቢያችንን ሰላም በማስከበር የሚበጀንን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ። በወረባቦ ወረዳ የቢስቲማ ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ኃይሌ ዮሴፍ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ መብታቸውን ተጠቅመው የሚበጃቸውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል። ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ አንድነታቸውን ጠብቀው የአካባቢያቸውን ሰላም እየጠበቁ መሆናቸውንም አስረድተዋል። ሌላኛው የከተማው ነዋሪ ወጣት ኑሩ መሀመድ በበኩሉ፤ የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ ምርጫው ውጤታማ እንዲሆን ከምናደርገው ጥረት በተጓዳኝ የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብሏል። ዕድሜው 18 ዓመት በመሙላቱ ለመምረጥ የምርጫውን ቀን በጉጉት እየጠበቀ መሆኑንም ጠቁሟል። ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ያሉት ደግሞ በወረዳው የ04 ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ሉባባ ይማም ናቸው። ከአካባቢያቸው ማኅብረሰብ ጋር በመተባበር የቀበሌያቸውን ሰላም በመጠበቅ የምርጫውን ቀን በጉጉት እየጠበቁ እንደሚገኙም አመላክተዋል። የ02 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ሰይድ መሀመድ ደግሞ፤ ምርጫውን ውጤታማና ስኬታማ ለማድረግ እኛም የድርሻችንን እየተወጣን ነው ብለዋል። የመራጭነት ካርድ ወስደን ለምንፈልገው ፓርቲ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናልም ነው ያሉት።
ፖለቲካ
የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ልምምድ እየዳበረ መምጣቱ የታየበት ነው
May 25, 2026 325
ጎንደር፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ልምምድ እየዳበረ መምጣቱ የታየበት መሆኑን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ፡፡ ፓርቲዎች በሃሳብ የበላይነት ክርክር ያካሄዱበትና የዜጎች ሰፊ ተሳትፎ የታየበት መሆኑንም ተናግረዋል። በርካታ ዜጎች ድምጽ ለመስጠት ካርድ የያዙበትና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። በዚህ ታሪካዊ እለትም ዜጎች ድምፃቸውን በመስጠት ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት እለቱን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው። በምርጫ ሂደቱ አጠቃላይ የዜጎች ተሳትፎና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ሲል ኢዜአ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ምሁራንን አነጋግሯል። ምሁራኑ በአስተያየታቸው ጠቅላላ ምርጫው የእስካሁኑ ሂደት የሃሳብና የፖሊሲ ክርክሮች የተካሄዱበት ስለመሆኑ አንስተዋል። በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ አንዳርጋቸው ተስፋሁን፤ የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ልምምድ እየዳበረ መምጣቱን ያመላከተ መሆኑን ገልጸዋል። የምርጫ ሂደት አንዱ የዴሞክራሲ መገለጫ መሆኑን አንስተው በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክርና አጠቃላይ የዜጎች ተሳትፎ ለዚህ ጥሩ መገለጫ መሆኑን አንስተዋል። ሌላው አስተያየት ሰጪ በዩኒቨርሲቲው የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናት ክፍል የስትራቴጂና የወቅታዊ ጉዳዮች ጥናት አስተባባሪ ሀቢብ ሰይድ ናቸው። የምርጫ ሂደቱ እስካሁን በዜጎች ጠንካራ ተሳትፎ በፓርቲዎች ጠንካራ የፖሊሲ ክርክሮች በሃሳብ የበላይነት መካሄዱን አንስተዋል። በመሆኑም ሂደቱ በኢትዮጵያ የህዝብ ተሳትፎ የታየበት የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እውን እየሆነ መምጣቱን ያመላከተ መሆኑን ገልጸዋል። የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መገለጫ ውጤቱ ብቻ ሳይሆን ሂደቱ ፍትሃዊ፣ አካታች፣ ሰላማዊና ተአማኒ መሆን እንዳለበት አንስተው የእስካሁኑ ሂደትም ይህንኑ ያመላከተ መሆኑን ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው የስነ ጽሁፍ መምህር የሆኑት ገብሬ ሙሉዓለም (ዶ/ር)፤ የምርጫ ሂደት የአንድ ሀገር የዴሞክራሲ ባህል የሚጎለብትበት፣ እድገትና ልማትን የሚወስን ትልቅ መሳሪያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ጥሩ መሰረት እያኖረ መሆኑን አንስተው እስከ መጨረሻው በስኬት እንዲጠናቀቅ የሁላችንም ጠንካራ ተሳትፎ ያስፈልጋል ብለዋል። በዩኒቨሲቲው የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል መምህርት የሺወርቅ ተዘራ፤ ምርጫ የአንድ ሀገር የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደትና የስልጡን ፖለቲካ መገለጫ መሆኑን አንስተዋል።
ለህዝብ የገባነውን ቃል ለመፈፀም የማያቋርጡ ተግባራት እየተከናወኑ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
May 25, 2026 202
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ለህዝብ የገባነውን ቃል ለመፈፀምና ብልጽግናን እውን ለማድረግ የማያቋርጡ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሰባተኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት አዲስ ባለ 6 ወለል ህንፃ በመገንባትና በቴክኖሎጂ በማደራጀት ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን አመልክተዋል። ለዘመናት በተንዛዛ አሰራርና እጅ መንሻ እየተጠየቀበት ዜጎችን ሲያማርር የነበረውን የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ስርነቀል በሆነ መልኩ ለመፍታት የመፍጠንና መፍጠር መርህ እየተከተለ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በዚህም የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ፍትሃዊ ለማድረግ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አግልግሎት አንድ ብሎ መጀመሩን ነው ያነሱት። ይህን ዲጂታል አገልግሎት ለማህበረሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ቀንና ሌሊት በከፍተኛ ትጋት ሲሰራ መቆየቱንም እንዲሁ። በዚህም መሰረት ዛሬ ሰባተኛውን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ማዕከል ለአግልግሎት ክፍት ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል። ህዝብ ወደ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች በመሄድ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ በተንቀሳቃሽ የአዲስ መሶብ አገልግሎት ይበልጥ ወደ ህዝቡ እንዲጠጋ በማድረግም አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ነው ያብራሩት። ለህዝብ የተገባውን ቃል ለመፈፀም እንዲሁም ብልጽግና እውን እንዲሆን ተከታታይነት ያለው የማያቋርጥ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይ ህብረተሰቡ በሚቀርበው ማዕከል ያለምንም መንገላታት በመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ -ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
May 25, 2026 273
ሆሳዕና፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ። የክልሉ መንግስት ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል። መድረኩ "ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ ከአደረጃጀት ሽግግር ወደ ልማት ማዕከል" በሚል መሪ ሀሳብ በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ የለውጡ ገፊ ምክንያቶች፣ ከለውጡ በኋላ የተመዘገቡ ስኬቶችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን የሚያሳይ የመነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ ክልሉ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ አንስቶ የማህበረሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረጉ የልማት ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። በተለይም ሀገራዊ የእድገት አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ በተሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቁመው፤ በቀጣይም በትውልድ ግንባታ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ በመቀጠል የክልሉን ፈጣን እድገት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ክልሉ ያለውን ጸጋ ለይቶ በማልማት ረገድ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። አካታች የፖለቲካ ምህዳርን ከመፍጠር አኳያም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትብብር የመስራት እሳቤን በመጠቀም ለክልሉ ፈጣን እድገት በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር በሰጡት አስተያየት፤ በመንግሥት የሚነደፉ አዳዲስ የልማት ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ስራ በመሰራቱ ክልሉ በግብርናውና በሌሎችም መስኮች ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን አስረድተዋል። በፓናል ውይይቱ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ለዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ገለጻ ተደረገ
May 25, 2026 350
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ አዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶችና ለአለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ገለጻ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሰቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለዲፕሎማቶችና ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ስለምርጫው ዝግጅት፣ የመራጮች ምዝገባ፣ የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎ፣ የደህንነት ዝግጅቶች እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዝርዝር በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል። እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ግልፅ እና ነፃ እንዲሆን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት ስለመሰራቱ አብራርተዋል። የቦርዱ ሰብሰቢዋ ምርጫውን በተመለከተ ስለተከናወኑ የቅድመ ምርጫ ስራዎች ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ለምርጫው ከ50 ሚሊየን በላይ መራጮች መመዝባቸውንና 52 ሺህ 29 የምርጫ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን ገልጸዋል። ለተፈናቃዮች፣ ለወታደሮችና ለተማሪዎች ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን እንዲሁም የምርጫ ድምጽ መስጫ ካርዶች ለሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች መሰራጨታቸውን አብራርተዋል። በተጨማሪም ምርጫው ሰላማዊ፣ አሳታፊ እና ነጻ እንዲሆን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ቦርዱ እየሰራ መቆየቱን ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በበኩላቸው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በተከታታይ ሲደረጉ የቆዩ ምርጫዎች ቀጣይ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም በሀገሪቱ ለተገነባው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰረት የጣለ መሆኑን አብራርተዋል። ከገለጻው በኋላ በተደረገ ውይይት የተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ምርጫው ሰላማዊና አሳታፊ እንዲሆን ስለተደረገው እንቅስቃሴ ግንዛቤ እንዳገኙ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።
በብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል - ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ
May 25, 2026 334
ጉኑኖ ሐሙስ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፡- በብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ተናገሩ። በወላይታ ዞን የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ እና የዳሞት ሶሬ ወረዳ በጥምረት ያዘጋጁት የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በጉኑኖ ሐሙስ ከተማ ተካሂዷል። ሚኒስትር ሸዊት በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ በፓርቲው የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ በርካታ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል፡፡ በዞኑ ጤና፣ ትምህርት፣ መንገድ እና ኮሪደርን ጨምሮ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ሥራዎች የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውንም አስረድተዋል። በፓርቲው መሪነት በተከናወኑ ሥራዎች የወላይታ ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዩኔስኮ መመዝገቡን አውስተው፤ የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል የሕዝቡ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። በብልጽግና ፓርቲ መሪነት የሕዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የፈቱ በርካታ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን ያነሱት ደግሞ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ናቸው። በፓርቲው መሪነት እንደ ወላይታ ዞን የሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች እየተፈቱ መጥተዋል ብለዋል። ይህንን የሕዝብን የልማት ተጠቃሚነት ለማስቀጠል ብልጽግና ፓርቲን መምረጥ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል። የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ ዋጃ በበኩላቸው፤ ብልጽግና ፓርቲ የሚመራው መንግሥት የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሠራው ሥራ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል። በዚህም ከ500 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድ፣ የመብራት፣ የትምህርት፣ የጤና እንዲሁም ሌሎች ልማቶችን በከተማዋ ማከናወን መቻሉን ለአብነት ጠቅሰዋል። መንግሥት የወረዳውን ነዋሪዎች በአጭር ጊዜ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በፖለቲካ ዘርፎች ተጠቃሚ ያደረጉ ልማቶች እንዲከናወን አድርጓል ያሉት ደግሞ የዳሞት ሶሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉቀን መሸሻ ናቸው። በዘንድሮ በጀት ዓመት በ150 ሚሊየን ብር ወጪ ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የመንገድ፣ የጤና፣ የንጹህ መጠጥ ውሃና ሌሎች ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ወደ ሥራ መግባታቸውንም አንስተዋል። በተጨማሪም የ15 ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድ ግንባታ ሥራን ጨምሮ ሌሎችም ልማቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ገጠርን ከከተማ ጋር ለማስተሳሰር በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።
የኢትዮጵያን ተስፋ ብሩህ ሊያደርግ ይችላል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የቦዲቲ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ገለጹ
May 25, 2026 267
ቦዲቲ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በካርዳችን የነገዋ ኢትዮጵያን ተስፋ ብሩህ ሊያደርግ ይችላል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የቦዲቲ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ገለጹ። አስተያየታቸው ለኢዜአ ከሰጡት መካከል አቶ ተመስገን ጫማ እንዳሉት፤ በወሰዱት ካርድ የነገይቱን ኢትዮጵያ ተስፋ ብሩህ ሊያደርግ ይችላል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ዕለቱን እየጠበቁ ነው። ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ መሳተፍ ሳይችሉ መቆየታቸውን የተናገሩት ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ዘነበች ጋንአሞ፤ አሁን ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ በመውሰዳቸው ዕድለኛ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በወሰዱት ካርድ ለሀገር ሰላምና ልማት መጠናከር የተሻለ የሚሠራውን ፓርቲ ለመምረጥ እንደተዘጋጁም አስረድተዋል። አቶ ባሩድ በርገነ እና መምህር ታምራት ዮናስ በበኩላቸው፤ ምርጫው ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በንቃት ለመሳተፍ ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል። በምርጫ ክርክሩ በተከታተልነው መሰረት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማት የተሻለ ፖሊሲና ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢኮኖሚ አማራጭ ያለውን ፓርቲ በመምረጥ ለነገይቱ ኢትዮጵያ መጽናት የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። ዜጎች ለምርጫው ሰላማዊነትና ፍትሐዊነት የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለባቸውም መክረዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በሀገር ጉዳይ እኩል ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እውን አድርጓል
May 25, 2026 277
ቀብሪ ደሃር፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የብልጽግና ፓርቲ በሀገር ጉዳይ እኩል የፖለቲካ ተሳትፎና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እውን ማድረጉን በፓርቲው የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና የዐቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አብዱራህማን አህመድ ገለጹ። ፓርቲው በሶማሌ ክልል ቆረሃይ ዞን ቀብሪ ደሃር ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ እና የማኒፌስቶ ማስተዋወቅ የማጠቃለያ መርሐ-ግብር አካሂዷል። አቶ አብዱራህማን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ብልጽግና ፓርቲ በሀገሪቱ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት እንዲገነባ ራዕይ ሰንቆ እየሠራ ነው። ብልጽግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ በሀገር ጉዳይ እኩል የፖለቲካ ተሳትፎና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እውን ያደረገ መሆኑን አንስተው፤ ዜጎች ፍትሐዊና እኩል የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አቅዶ እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል። ፓርቲው ከዚህ በፊት በሀገሪቱ የተፈጠሩትን ችግሮች በማረምና ስብራቶችን በመጠገን ዕቅዶችን በመንደፍ የተለያዩ ተግባራት በማከናወን ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል። በተለይም የክልሉ ሕዝብ ከሀገሪቱ ፖለቲካ የዳር ተመልካችነት ወጥቶ እኩል ተሳትፎ በማድረግ የልማት ተጠቃሚነቱ የተረጋገጠበት ወቅት መሆኑን አረጋግጠዋል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ያደረጉ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች መከናወናቸውንም ለአብነት አንስተዋል።
ምርጫው በስኬት እንዲከናወን የሚጠበቅብንን እየተወጣን ነው- የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች
May 25, 2026 267
ደሴ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፡- 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ እንዲሆን የአካባቢያችንን ሰላም በማስከበር የሚበጀንን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ። በወረባቦ ወረዳ የቢስቲማ ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ኃይሌ ዮሴፍ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ መብታቸውን ተጠቅመው የሚበጃቸውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል። ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ አንድነታቸውን ጠብቀው የአካባቢያቸውን ሰላም እየጠበቁ መሆናቸውንም አስረድተዋል። ሌላኛው የከተማው ነዋሪ ወጣት ኑሩ መሀመድ በበኩሉ፤ የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ ምርጫው ውጤታማ እንዲሆን ከምናደርገው ጥረት በተጓዳኝ የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብሏል። ዕድሜው 18 ዓመት በመሙላቱ ለመምረጥ የምርጫውን ቀን በጉጉት እየጠበቀ መሆኑንም ጠቁሟል። ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ያሉት ደግሞ በወረዳው የ04 ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ሉባባ ይማም ናቸው። ከአካባቢያቸው ማኅብረሰብ ጋር በመተባበር የቀበሌያቸውን ሰላም በመጠበቅ የምርጫውን ቀን በጉጉት እየጠበቁ እንደሚገኙም አመላክተዋል። የ02 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ሰይድ መሀመድ ደግሞ፤ ምርጫውን ውጤታማና ስኬታማ ለማድረግ እኛም የድርሻችንን እየተወጣን ነው ብለዋል። የመራጭነት ካርድ ወስደን ለምንፈልገው ፓርቲ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናልም ነው ያሉት።
ማህበራዊ
በክልሉ የአርብቶ አደሩ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚነት እያደገ መጥቷል
May 25, 2026 228
ሰመራ፣ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፡- በአርብቶ አደሩ አካባቢ ለንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ በተሰጠው ትኩረት ተጠቃሚነቱ እያደገ መምጣቱን የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት ቢሮ ኀላፊ አቶ ኡመር ኑር ገለጹ ። በክልሉ አፍዴራና ቢዱ ወረዳዎች ከ65 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት ቢሮ ኀላፊ አቶ ኡመር ኑር በወቅቱ እንደገለፁት በአርብቶ አደሩ አካባቢ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ለተቋማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል ። በዚህም አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚነቱ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። በወረዳዎቹ ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁት የውሀ ተቋማትም የጥረቱ አካል መሆናቸውን ጠቅሰዋል ። አካባቢው በረሀማ በመሆኑ የንፁህ መጠጥ ውሃ በቀዳሚነት አሰፈላጊና ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቁመው ከተለያዮ አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት አገልግሎቱ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ አህመድ ሻሚ በበኩላቸው እንዳሉት በክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በወረዳዎቹ ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁት የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋማት በጸሀይ ሀይል የሚሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው ተቋማቱ በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክትና በወርልድ ቪዥን የገንዘብ ድጋፍ በትብብር የተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። በአፍዴራ ወረዳ ነማ ጉቢና ቀበሌና በቢዱ ወረዳ ቢዱ ሶዶምታ ቀበሌ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁት የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋማት ከ30 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ አመልክተዋል። የአፍዴራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲራጅ መሀመድ የውሀ ተቋሙ መገንባት የህብረተሰቡን ጥያቄ የመለሰ መሆኑን አስታውቀዋል።
የአረፋ በዓል ሲከበር የተቸገሩ ወገኖችንና አቅመ ደካሞችን በማገዝ ሊሆን ይገባል
May 25, 2026 126
መሃል አምባ፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፡- የአረፋ በዓል ሲከበር የተቸገሩ ወገኖችንና አቅመ ደካሞችን በማገዝ እንዲሁም ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትን በመደገፍ መሆን እንዳለበት የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ገለጸ። በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አንዱ ነው። በብዛት የእርድ ሥነ ስርአት ተከናውኖበት የሚከበረው ይህ ታላቅ በዓል በመላው ዓለም በሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በመጠያየቅ፣ በአብሮነት፣ በመደጋገፍና ማዕድ በመጋራት ይከበራል። በዚሁ መሰረትም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞንና አካባቢው ከሃይማኖታዊ መገለጫዎቹ ባለፈ የአንድነት እና የአብሮነት እሴቶቹን በጠበቀ መልኩ በጋራ ይከበራል። በመሆኑም በዓሉ ሲከበር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ፣ አቅመ ደካሞችን በማገዝና በተለይም ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትን (የቲሞችን) ማዕድ በማጋራት፣ በማብላትና በማልበስ መሆን እንዳለበት የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ አባስ ያሲን ገልጸዋል። እለቱ ሲከበር መተሳሰብንና መረዳዳትን መሰረት አድርጎ መሆኑን አስረድተው በዚሁ መሰረት የዘንድሮውን የአረፋ በዓል ለማክበር ተዘጋጅተናል ብለዋል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ላጫ ጋሩማ፤ የአረፋ በዓል አከባበር የአብሮነት እሴት መገለጫና የመተሳሰብ ምልክት መሆኑን አንስተው በዓሉን በአብሮነት ማዕድ በማጋራትና በመተጋገዝ ማክበር እንደሚገባ ገልጸዋል። የ1447ኛውን የአረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ በዞኑ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጥላሞ ቀበሌ በተዘጋጀ ፌስቲቫል ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የጉራጌ እና የምስራቅ ጉራጌ ዞን አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ዲላን ፔጅ በሀረር የተለያዩ የመስህብ ስፍራዎችን ይጎበኛል
May 25, 2026 279
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ዲላን ፔጅ የተለያዩ የመስህብ ስፍራዎችን ለመጎብኘት ሀረር ከተማ ገብቷል። ከዓለም ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ የሆነው እንግሊዛዊው ዲላን ፔጅ በሀረር በሚኖረው ጉብኝትም በሀረር ኢኮ ፓርክ የጅብ ትርዒት ከመታደም ባለፈ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን ተዘዋውሮ ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል። የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውለታል። ከዲላን ፔጅ በተጨማሪ የኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መገኘታቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
በወረዳው የተገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከእንግልት ታድጎናል - የመንጌ ወረዳ ነዋሪዎች
May 25, 2026 256
አሶሳ፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ በወረዳው የተገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለውሃ ፍለጋ ከሚያደርጉት ረጅም ጉዞ እንደታደጋቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንጌ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንጌ ወረዳ በሚገኙት ቁዱዩ እና ቱመት ጀበሮና ቀበሌዎች፣ የፋሮ ፋውንደሽን የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታን አጠናቆ ለአገልግሎት አብቅቷል። ይህም ከ11 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በወቅቱ ተገልጿል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ የተገነባላቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም ለውሃ ፍለጋ ረጅም ርቀት በመጓዝ ያባክኑት የነበረውን ጊዜና ጉልበት የሚታደግላቸው በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸዋል። ከቀበሌው ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ሰሚራ ሀሚድ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል ንፅህናው ያልተጠበቀ ውሃ ለመቅዳት ረጅም ሰዓታትን በእግር ለመጓዝ ይገደዱ እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን ግን በቀበሌያቸው የተገነባላቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ችግሩን በመቅረፍ በአካባቢያቸው የንፁህ ውሃ ተጠቃሚ መሆን ስላስቻላቸው ይደርስባቸው ከነበረው ድካም እፎይታ አግኝተዋል። ሌላው የወረዳው ነዋሪ አቶ አብዱሰላም ራህማ በበኩላቸው፤ በቀበሌያቸው የተገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለአገልግሎት መብቃቱ የበርካታ ዓመታት የሕዝብ ጥያቄን የመለሰ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ለጤናቸውም ሆነ ለማኅበራዊ እለታዊ ተግባራቸው የሚሆን ንፁህ መጠጥ ውሃ ማግኘት መቻላቸው፣ በውስጣቸው ልዩ ደስታና እርካታን እንደፈጠረባቸው ጠቁመዋል። ፕሮጀክቱ ለረጅም ዘመናት አገልግሎት መስጠት እንዲችል፤ ከእንስሳት ንክኪም ሆነ ከማንኛውም ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች በመጠበቅ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። ሌላዋ የአካባቢው ነዋሪ ወይዘሮ መልሃሴን ሱልጣን በበኩላቸው፤ የውሃ እጦቱ በተማሪዎች ላይ ያደርስ የነበረውን ተፅዕኖ ሲያብራሩ፣ ልጆችም ውሃ ለመቅዳት ረጅም ርቀት ለመጓዝ በመገደዳቸው ምክንያት መደበኛ ትምህርታቸው ያመልጣቸው እንደነበር ገልጸዋል። በመንጌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት አቶ መለስ ሙሉጌታ እንደገለጹት፤ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ የኅብረተሰቡን የውሃ እጥረት ከመቅረፍ ባለፈ፣ ሆስፒታሉ ለረጅም ጊዜ የነበረበትን የውሃ አቅርቦት ችግር የፈታ ነው።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያረጋግጡ ውጤታማ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው
May 25, 2026 289
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያረጋግጡ ውጤታማ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ፍትሐዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በዓለም አቀፍ ማዕቀፍ የዲፕሎማሲ መርህ መሳካት የሚችል የህልውና ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል። ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያረጋግጡ ውጤታማ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች። የኢትዮጵያ ፍትሕዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ለመፍጠር ከምታደርገው ጥረት ጋር ተለይቶ የሚታይ እንዳልሆነ አስረድተዋል። በኢትዮጵያዊያን የጋራ መስዋዕትነት በተገነባው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ስትራቴጂ መነሻነት አህጉራዊ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማፋጠን ኢትዮጵያ ፀጋዎቿን በመጠቀም በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ነው ያመለከቱት። ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር ያላትን ቁርኝት ተፈጥሮን ከመልክዓ ምድራዊ ታሪካዊነትን ከሕጋዊነት ያሰናሰለ መሆኑን አስረድተው፤ የባሕር በር ባለቤትነቷን እንድታጣ የተደረገበት በሴራና ተንኮል የተሸረበ አካሄድም የሚያስቆጭና ኢትዮጵያን ደካማ ለማድረግ ካለ እሳቤ የመነጨ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ፀጋዋን በመጠቀም ዕድገትን ካረጋገጠች ስጋታችን ትሆናለች የሚለው ስሌትም የታሪካዊ ጠላቶች ኋላቀርና የተሳሳተ ደምዳሜ ነው ብለዋል። በዚህም የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ታሪካዊ መሠረተ ያለው፣ ተፈጥሯዊና መልክዓ ምድራዊ እውነታ ያለው ሕጋዊና ፍትሐዊነትን አሰናስሎ የያዘ የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ቦሊቪያና ፔሩ፣ ብራዚልና ፓራጓይ፤ በአፍሪካ የማሊ፣ ሴኔጋልና ኮትዲቯር የተጠቀሙባቸውን የጋራ መፍትሔዎች በተሞክሮነት አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ፍትሐዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በዓለም አቀፍ ማዕቀፍ የዲፕሎማሲ መርህ መሳካት የሚችል የህልውና ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም የኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ ሕጋዊ፣ መልክዓ ምድራዊና ፍትሕዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ማሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል። ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ላላት ሀገር የቅንጦት ሳይሆን የኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን የሚያስከብር ቁልፍ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። ለወደብና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በየዓመቱ የምታወጣው ከፍተኛ ሃብት ዓለም አቀፍ የንግድ ተወዳዳሪነትና በጠቅላላው የዕድገት ጉዞ ላይ ትልቅ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አስገንዝበዋል።
የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ የመዝናኛ አማራጭ እየፈጠረ ነው
May 25, 2026 221
አሶሳ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ የመዝናኛ አማራጭ እየፈጠረ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን ተናገሩ። ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የከተማዋ የኮሪደር ልማት አካል የሆነውን የአሶሳ ሲቲ ፓርክን ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት፤ በአሶሳ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት በርካታ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አብረው እንዲገነቡ አድርጓል። ልማቱ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ የመዝናኛ አማራጭ እየፈጠረ መሆኑንም ተናግረዋል። ለዚህም የኮሪደር ልማቱ በሚከናወንባቸው አካባቢዎች በዘመናዊ መልኩ የተገነቡትን የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ የሕጻናት መጨዋቻ እና የመዝናኛ ቦታዎች በማሳያነት ጠቅሰው፤ የልማት ሥራዎቹም ለትውልድ የሚተርፉ ናቸው ብለዋል። አሶሳ ሲቲ ፓርክ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት ከመሆኑ ባለፈ ሕፃናት አዕምሯቸው እንዲታደስ የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችን አካቶ መገንባቱንም ተናግረዋል። የክልሉ መንግስት በሌሎች አካባቢዎችም የኮሪደር ልማቱን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማከናወን ለነዋሪዎች ምቹና ጽዱ ከተሞችን ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል ብለዋል። የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አብዱልከሪም አብዱራሂም በበኩላቸው፤ የአሶሳ ሲቲ ፓርክ የከተማዋን የመዝናኛ ማዕከል እጥረት ችግር የፈታና ለሕፃናትም ልዩ ስጦታ መሆኑ ጠቁመዋል።
ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋችንን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
May 25, 2026 257
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋችንን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የተፈጥሮ እውነት ከታሪክ ክብር ጋር በተዋሃደባት፣ በጣና ሐይቅና በዓባይ ወንዝ በታጀበችው የውበት ማማዋ ባሕር ዳር ገብተናል ብለዋል። በመልዕክታቸውም ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋችንን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስንደርስ፣ ፍቅርና አክብሮት በተሞላበት ሁኔታ ለተደረገልን ደማቅ አቀባበል ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉና ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ በጸሎትና በምርቃታቸው ላልተለዩን የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ለመላው የባሕር ዳር ሕዝብ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።
በኢሉአባቦር ዞን በቴክኖሎጂ የታገዘ ግብርናን በማስፋፋት ምርታማነትን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው
May 25, 2026 161
መቱ፣ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ):- በኢሉአባቦር ዞን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ግብርናን በማስፋፋት ምርታማነትን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ። በዞኑ በክረምት እርሻ ከ389 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል ዓይነቶች የመሸፈን ስራም ተጀምሯል። በክረምት እርሻው በቆሎ፣ ማሽላ፣ ሩዝ፣ አኩሪ አተርና ሌሎች የሰብል ዓይነቶች የሚዘሩ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በኩታ ገጠም የሚታረስ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ ታከለ ተናግረዋል። ምርታማነትን ለማሳደግም በኩታ ገጠም የማረስ ልማድን በማዳበር እንዲሁም በማዳበሪያና የምርጥ ዘር አቅርቦት ላይ በትኩረት መሰራቱን ኃላፊው ገልጸዋል። ለዚህም ከ161 ሺህ ኩንታል በላይ የኬሚካል ማዳበሪያ እና ከ24 ሺህ ኩንታል በላይ የተለያዩ ምርጥ ዘሮች በክረምት እርሻው በስራ ላይ እንደሚውሉ አስታውቀዋል። ከዚህ ውስጥ 61 ሺህ ሔክታር መሬት በበቆሎ ሰብል የሚሸፈን ሲሆን፤ ለዚሁ ተግባር የሚሆን ከ50 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ መቅረቡንም አክለው ገልጸዋል። በሌላ በኩል በዞኑ ስር በሚገኘው የያዮ ወረዳ በክረምት እርሻ ከ11 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል ዓይነቶች የመሸፈን ስራ እየተከናወነ መሆኑን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ በፈቃዱ ኦልጂራ ገልጸዋል። በቴክኖሎጂ የታገዘ ግብርናን በማስፋፋትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። አርሶ አደሮችም በኩታ ገጠም በማረስ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናቸውንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ለክረምት እርሻው ከፍተኛ ትኩረት መስጠታቸውን ተናግረዋል። በያዮ ወረዳ የአጪቦ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ጌታቸው በቀለ፣ አርሶ አደር ተስፋዬ ሀብተማርያም እና አርሶ አደር ብርሃኔ አሰፋ ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር በመሆን በኩታ ገጠም ከ116 ሔክታር በላይ መሬት ላይ በቆሎ መዝራት መጀመራቸውን ገልጸዋል። አርሶ አደሮቹ የማሳ ዝግጅት ስራቸውን ቀደም ብለው በማከናወናቸው እንዲሁም የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦትም ቀድሞ በመድረሱ ማሳቸውን በዘር የመሸፈን ተግባርን ቀድመው መጀመራቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም የግብርና ስራቸውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በትራክተር የማረስ ስራ እንዲያከናውኑ በወረዳው አስተዳደር በኩል አስፈላጊው እገዛ እንደተደረገላቸውም ገልጸዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በምግብና መጠጥ ማቀነባበር የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ህብረተሰቡ በንጥረ ነገር የበለፀጉ ምርቶችን እንዲያገኝ እያደረጉ ነው
May 25, 2026 163
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ በግብርና ምርት የምግብና መጠጥ ማቀነባበር የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ህብረተሰቡ በንጥረ ነገር የበለፀጉ ምርቶችን እንዲያገኝ እያደረጉ መሆናቸውን የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለጸ። በአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ከቴክኖ-ሰርቭ ጋር በመተባበር የበለፀገ የስንዴ ዱቄትና የምግብ ዘይት የገበያ ትስስር ፎረም በአዲስ አበባ አካሂዷል። የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ደበበ ወርቁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በምግብ ዘርፍ የስንዴና የማሽላ ዱቄት የጨውና የዘይት ምርቶች አስገዳጅ ደረጃ ወጥቶላቸዋል። በዚህም አምራች ኢንዱስትሪዎች የበለፀገ የምግብ ምርት ዝግጅት ሰርተፊኬት በመውሰድ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የምግብ ምርት አምራቾችም በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ምርቶችን ለማህበረሰቡ በማቅረብ ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በንጥረ ነገር በለፀገ የምግብ ምርታማነት አቅም ጤናማና አምራች ዜጋን በማፍራት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው አንስተዋል። በቀጣይም በበለፀገ የምግብ ምርት ማቀነባበር ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ በማድረግ የምርት ጥራትና አቅማቸውን እንዲያሳደጉ ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል። በቴክኖ ሰርቭ ተቋም የሚለር ፎር ኒውትሬሽን ፕሮግራም ማናጀር ገረመው ጣሰው በበኩላቸው፤ አምራቾች የተሳለጠ የምግብ ማበልፀግ ሥራ እንዲያከናውኑ የቴክኒክ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል። በቀጣይም በበለፀገ የምግብ ማቀነባበርና ዝግጅት ለተሰማሩ ድርጅቶች የሚያደርገውን አተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የዋኬኒ ምግብ ፋብሪካ ፕሮዳክሽን ማናጀር አማኑዔል ታደሰ፤ መንግስት ለፋብሪካዎች የሰጠው ልዩ ትኩረት ምርቶቻችንን በጥራትና በስፋት ተደራሽ እንድናደርግ አስችሎናል ብለዋል። ሌላኛው የዲና ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የሽያጭና ስርጭት ሥራ አስኪያጅ እንየው ጫኔ በበኩሉ፤ ኢትዮጵያ ታምርትን ጨምሮ መንግስት ዘርፉን ለማሳደግ የሚያደርገው ድጋፍ እያደገ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በከተማዋ የተተገበሩ ዲጂታል አሰራሮች አገልግሎት አሰጣጥን በተጨባጭ አሻሽለዋል
May 25, 2026 212
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ተግባራዊ በተደረጉ ዲጂታል አሰራሮች አገልግሎት አሰጣጥን በተጨባጭ ማሻሻል መቻሉን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ገለጹ። ምክትል ከንቲባው ከመዲናዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን፣ ሰባተኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል የዲጂታል አገልግሎት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍን መርቀው ወደ ስራ አስገብተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ እንዳሉት፤ በመዲናዋ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ዘላቂ እልባት ለመስጠት ተጨባጭ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ለአብነትም ሁሉንም አገልግሎቶች በተቀናጀ መንገድ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችለውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል የዲጂታል አገልግሎትን በአጭር ጊዜ ውስጥ በስፋት ማዳረስ ተችሏል ብለዋል። ዛሬ ወደ አገልግሎት የገባውን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጨምሮ የዲጂታል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ማለቱን ጠቅሰው፤ በማዕከላቱ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶችም ወደ 150 ማደጋቸውን አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅት የተገልጋዮች እርካታ 98 በመቶ መድረሱን ገልጸው፣ በቀጣይም ተጨማሪ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎችን ወደ ስራ የማስገባት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በመዲናዋ በሌሎች የልማት መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን በአገልግሎት አሰጣጥ ላይም ለመድገም ሁሉን አቀፍ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል። ዛሬ ወደ አገልግሎት የገባው የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት መስጫ ማዕከል የዚህ ማሳያ መሆኑን በመጥቀስ፣ በማዕከላቱ አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን አቅም በመገንባት በኩል በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ ወደ ስራ መግባቱ በሕዝብና በመንግሥት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ድልድይ ነው ብለዋል።
የሥራ ገበያ ምኅዳሩን በዲጂታል ሥርዓት በማዘመን ሥራና ሰራተኛ በቀላሉ የሚገናኝበት ዕድል እየተፈጠረ ነው
May 25, 2026 288
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የሥራ ገበያ ምኅዳሩን በውጤታማ የዲጂታል ሥርዓት በማዘመን ሥራና ሰራተኛ በቀላሉ የሚገናኝበት ዕድል እየተፈጠረ መሆኑን የሥራ ክህሎት ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል ገለጹ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር ያለማውን ሥራና ሰራተኛ በቀላሉ የሚገናኝበት 'ፈልጉልኝ' የተሰኘ ዘመናዊ የዲጂታል መተግበሪያ ይፋ አድርጓል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል በዚሁ ወቅት፤ የዜጎችን የሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያዘምኑ የዲጂታል አማራጭ የማሻሻያ እርምጃዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው ብለዋል። ይፋ የተደረገው 'ፈልጉልኝ' የሥራና ሰራተኛ አገናኝ መተግበሪያም ሥራና ሰራተኛን በቀላሉ የሚያገናኝ የዲጂታል አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል። ሥራና ሰራተኛ በዲጂታል ሥርዓት የሚገናኝበት መተግበሪያም በሁሉም ዘርፍ ሙያና ክህሎት ያላቸው ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት የሚያሰፋ እንደሆነ ተናግረዋል። መተግበሪያውን ከፋይዳና የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሰርዓት ጋር በማስተሳሰር በተለያዩ የቋንቋ አማራጮች ተደራሸ የማድረግ ዕድል መፈጠሩን አስረድተዋል። በመተግበሪያው የተካተቱ የተሟላና አስተማማኝ የቴክኖሎጂ አማራጮች ፍትሐዊ የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ምኅዳርን በመፍጠር የማይተካ ሚና እንዳለው አንስተዋል። የሥራ ገበያ ምኅዳሩን በውጤታማ የዲጂታል ሥርዓት በማዘመን ሥራና ሰራተኛ በቀላሉ የሚገናኝበት ዕድል እየተፈጠረ መሆኑን አብራርተዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ፤ መተግበሪያው በሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ዕውቀት የለማና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ብለዋል። ይህም የመረጃ ሉዓላዊነትና ደህንነትን ለማስጠበቅ ተደማሪ አቅም እንዳለው ገልጸዋል። አምስት የሀገር ዉሰጥ ቋንቋዎችና አጭር የስልክ መልዕክት አማራጭ በመተግበሪያው መካተታቸውም የዜጎች ተጠቃሚነትን ለማላቅ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፈር ለምነትን በዘላቂነት የሚጠብቁ በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራሮች እየተጠናከሩ ነው
May 23, 2026 840
አምቦ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ የአፈር ለምነትን በዘላቂነት የሚጠብቁ በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራሮችን በመተግበር ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ በአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል አዲስ በአፈርና ውሃ ላይ ጥናትና ምርምር ለማድረግ የሚያግዝ ላብራቶሪ ስራ አስጀምሯል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ንጉሤ ደቻሳ (ፕ/ር) እንደገለጹት፤ የአፈር ለምነትን መጠበቅ ለምርትና ምርታማነት እድገት መሰረታዊ በመሆኑ፣ የአፈር ለምነትን የሚቀንሱ ችግሮችን በሳይንሳዊ ዘዴ መለየትና የላብራቶሪ ማዕከላትን ማጠናከር አስፈልጓል። በአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል ዛሬ ተመርቆ ስራ የጀመረው የአፈር እና ውሃ ላብራቶሪም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን ጠቅሰዋል። የላብራቶሪው ዋና ዓላማም የአፈር ለምነትን በመጠበቅ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማድረግና የግብርናውን ዘርፍ ማሳደግ እንደሆነ አንስተዋል። የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ጀማል ቶላ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ማዕከሉ ባለፉት ዓመታት ከአካባቢው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ለእጽዋት ጥበቃ የሚውሉ ሳይንሳዊ የምርምር ውጤቶችን ሲያቀርብ መቆየቱን ተናግረዋል። የምርት መጠንን ለመጨመር የሰብል ልማትን የሚደግፉ ሰፋፊ የግብርና ምርምሮች እየተካሄዱ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ይህም የአካባቢውን አርሶ አደሮች ከመደገፍ ባለፈ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች እንዲከናወኑ ማድረጉን ተናግረዋል። ማዕከሉ ግብርናን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ፣ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችንና የግብርና ግብዓቶችን በማቅረብ የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል። የአምቦ ወረዳ አርሶ አደር ወይዘሮ እሸቱዋ ሚደቅሳ በበኩላቸው፤ ከግብርና ማዕከሉ ባገኙት ስልጠና በመታገዝ የተሻሻለ የበቆሎ ዝርያ ወስደው በመዝራታቸው፣ ምርታቸው ከበፊቱ እጥፍ መጨመሩን ተናግረዋል።
ስፖርት
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈ
May 25, 2026 185
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ የመጀመሪያ የግማሽ ፍፃሜ መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቀሌ 70 እንደርታን በመለያ ምት አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ወደ መለያ አምርቷል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በመለያ ምት 7 ለ 6 በማሸነፍ ለፍጻሜ ያለፈ ሲሆን ዋንጫውን ለማንሳት ከሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ መድን አሸናፊ ጋር ይጫወታል። ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን ነገ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ 70 እንደርታ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ለማለፍ ይጫወታሉ
May 25, 2026 242
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ የመጀመሪያ የግማሽ ፍፃሜ መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ 70 እንደርታ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ጨዋታው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሩብ ፍጻሜው መቻልን በመለያ ምት በማሸነፍ አራት ውስጥ ገብቷል። ተጋጣሚው መቀሌ 70 እንደርታ በበኩሉ በሩብ ፍጻሜው ቦዲቲ ከተማን 3 ለ 2 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። ሁለቱ ቡድኖች በዘንድሮው የውድድር ዓመት ለሶስተኛ ጊዜ ይገናኛሉ። በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሊጉ ሁለት ጊዜ ተገናኝተው በተመሳሳይ አንድ አንድ ጊዜ አሸንፈዋል። ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተገናኝተው መቀሌ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ፍፁም አለሙ እና ኮትዲቯራዊው አብዱላጢፍ ባምባ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። ዳዊት ገብሩ ለወልዋሎ ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ በ40 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው መቀሌ 70 እንደርታ በ34 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። የጨዋታው አሸናፊ ቡድን በፍጻሜው ከሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ መድን አሸናፊ ጋር ይጫወታል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ቀን ውሎ
May 24, 2026 604
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የ2025/26 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል። ሁሉም የ38ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት ተደርገዋል:: የሻምፒዮኖቹ አርሰናል የድል ፌሽታ ሲያነሳ፣ የጎረቤቱ ቶተንሃም ከመውረድ መትረፍ፣ የዌስትሃም ከሊጉ መሰናበት፣ የሊቨርፑል የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ማረጋገጥ እና የብሩኖ ፈርናንዴዝ አዲስ ክብረ ወሰን፤ እለቱን በክስተቶች የታጀበ አድርጎታል። በሳምንቱ አጋማሽ ከ22 ዓመታት የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው አርሰናል ለረጅም ጊዜ የናፈቀውን ዋንጫ በደማቅ ስነ ስርዓት አንስቷል። መድፈኞቹ በሰልኸረስት ፓርክ ባደረጉት ጨዋታ ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። ጋብርኤል ጄሱስ እና ኖኒ ማዱዌኬ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ጂን ፍሊፕ ማቴታ የፓላስን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። አርሰናል በ85 ነጥብ ዓመቱን በአንደኝነት ተጠናቋል። ከጨዋታው በፊት የክሪስታል ፓላስ ተጫዋቾች በግራ እና በቀኝ በመቆም ለሻምፒዮኑ አርሰናል የክብር አቀባበል (Guard of honour) አድርገዋል። ተከታዩ ማንችስተር ሲቲ በአስቶንቪላ የ2 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዷል። ኦሊ ዋትኪንስ ለቪላ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል። አንቶዋን ሴሜኒዮ የሲቲን ጎል ከመረብ አገናኝቷል። ሲቲ በ78 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል። የውሃ ሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ ከጨዋታው በኋላ ክለቡን በይፋ ተሰናብቷል። በርናንዶ ሲልቫም ሲቲን ተሰናብቷል። የማንችስተር ሲቲው አርሊንግ ሃላንድ በ27 ጎሎች የሊጉ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ተጠናቋል። በሊጉ የመዝጊያ ቀን ሲጠበቁ ከነበሩ ጉዳዮች መካከል አንዱ ላለመውረድ የሚደረግ ትግል ነው። ቶተንሃም ሆትስፐርስ በሜዳው ኤቨርተንን አስተናግዶ 1 ለ 0 በማሸነፍ በ41 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል። ጆአኦ ፓሊኒያ የስፐርስን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል። ዌስትሃም ዩናይትድ ሊድስ ዩናይትድን 3 ለ 0 ቢያሸንፍም ከሊጉ ወርዷል። ቫለንቲን ካስቴላኖስ፣ጃሬድ ቦወን እና ካሉም ዊልሰን ግቦቹን አስቆጥረዋል። ዌስትሃም ዩናይትድ በ39 ነጥብ 18ኛ ደረጃን በመያዝ ከሊጉ ተሰናብቷል። የለንደኑ ክለብ ከ14 ዓመታት የሊጉ ቆይታ በኋላ ወደ ሻምፒዮንሺፑ ወርዷል። ሊቨርፑል ከብሬንትፎርድ አንድ አቻ በመለያየት በ60 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋግጧል። መሐመድ ሳላህ እና አንዲ ሮበርትሰን ከጨዋታው በኋላ ሊቨርፑልን በይፋ ተሰናብተዋል። ሰንደርላንድ ቼልሲን 2 ለ 1 በመርታት በ54 ነጥብ የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊነት ትኬቱን ቆርጧል። ቦርንማውዝ ሌላኛው የዩሮፓ ተሳታፊ ክለብ ነው። ቡዱኑ ዛሬ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር አንድ አቻ በመለያየት በ57 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ቼልሲ በ52 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዞ በመጨረስ ከአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ ውጪ ሆኗል። ማንችስተር ዩናይትድ ብራይተንን 3 ለ 0 አሸንፏል። በአሜክስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፓትሪክ ዶርጉ፣ ብሪያን ምቡዌሞ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ለዶርጉ ጎል መቆጠር እጁ የነበረበት ብሩኖ ፈርናንዴዝ በዓመቱ 21 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። ከዚህ ቀደም ቲዬሪ ሄነሪ እና ኬቨን ደ ብሮይን (በተመሳሳይ 20 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል) በጣምራ ይዘው የነበሩትን ክብረ ወሰን አሻሽሏል። ፈርናንዴዝ ትናንት የሊጉ የዓመቱ ምርጣ ተጫዋች በመባል መመረጡ አይዘነጋም። ዩናይትድ በ71 ነጥብ ሶስተኛ ሆኖ ዓመቱን አጠናቋል። ብራይተን በ53 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በኮንፍረንስ ሊግ መሳተፉን አረጋግጧል። ፋልሃም ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ ወራጆቹ በርንሌይ እና ዎልቭስ ባደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይተዋል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እስከ መጨረሻው ደቂቃ በድራማ እና ትዕይንቶች ታጅቦ ተጠናቋል።
የኢትዮጵያ ከ 17 ዓመት በታች ሴት ብሔራዊ ቡድን የቡሩንዲ አቻውን 2ለ1 አሸንፏል
May 24, 2026 441
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ሴት ብሔራዊ ቡድን ከቡሩንዲ ያደረገውን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ 2ለ1 አሸንፏል። አበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ለቡድኑ የማሸነፊያ ሁለት ግቦችን ሊዲያ እያሱ ማስቆጠር ችላለች። ኢትዮጵያ በ2026 ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ደቡብ ሱዳንን በድምር ውጤት 8 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉ ይታወቃል። ተጋጣሚዋ ብሩንዲ በመጀመሪያው ዙር ማላዊን በአጠቃላይ ውጤት 4 ለ 2 አሸፋለች። የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታው ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ቡጁምቡራ ላይ ይካሄዳል። ኢትዮጵያ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈች ለመጨረሻው ዙር ማጣሪያ ትጫወታለች። 10ኛው የፊፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
አካባቢ ጥበቃ
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል
May 25, 2026 254
አዳማ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፡- በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉን የምሥራቅ ሸዋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አብነት ዘገየ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በይፋ ከተጀመረ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል። ይህም የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተጨባጭ በማረጋገጥ ውጤት ማስገኘቱን ጠቁመው፤ የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የጎላ አስተዋጽዖ ማበርከቱን ለአብነት ጠቅሰዋል። ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብርም ለደን ልማት የሚሆኑ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው 269 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞች በሁሉም ወረዳዎች ችግኝ ጣቢያዎች አማካኝነት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል። ዘንድሮ በ45 ሺህ 563 ሔክታር ላይ የችግኝ ተከላ እንደሚካሄድም ነው ያመላከቱት።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለቀጣናው ብልፅግና የላቀ ሚና አለው
May 23, 2026 704
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የተረጋጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንዲሁም ብልፅግናን ለማጎልበት የላቀ ሚና እንዳለው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሰላምና ደህንነት ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የራሷን የተፈጥሮ ሀብት ከመንከባከብ ባለፈ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ አደጋዎችን በጋራ ለመከላከል የአካባቢውን አገራት አብሮ የመልማት ዕቅድ ይዛ እየሠራች ስለመሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለጎረቤት አገራት በርካታ ችግኞችን ማበርከቷ ይታወቃል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ የተፈጥሮ መዛባቶችን ለመከላከል፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና አካባቢን ለመታደግ ታስቦ በከፍተኛ ሀገራዊ ቁርጠኝነት እየተተገበረ የሚገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። ይህ ንቅናቄ በአገር ውስጥ ካስገኛቸው ሁለንተናዊ ጥቅሞች ባሻገር፣ ለጎረቤት አገራትና ለጠቅላላው የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ የምታከናውነው የተፈጥሮ ጥበቃ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለቀጣናው አገሮች የሚተርፍ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ነው፡፡ የኢጋድ ሰላምና ደህንነት ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በቀጣናው እንደ ጎርፍ፣ የበረሃ አንበጣ እና ድርቅ ያሉ ተፈጥሯዊ አደጋዎች የሰዎችን መፈናቀልና ስደት ይፈጥራሉ፡፡ በዚህም ዜጎች ከአካባቢያቸው ችግሩ ወደ ሌለባቸው አካባቢዎችና ድንበሮችን አቋርጠው የሚሰደዱበትን ሁኔታ የሚፈጠር ሲሆን፤ ይህም በቀጣናው ላይ የሚያሳድረው ጫና ቀላል እንዳልሆነ አመልክተዋል። ይህንን ተግዳሮት ለመቋቋም በኢትዮጵያ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ውጤቶችን እያሳየ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ አሁን ላይ የሚታየው መደበኛ የዝናብ ሁኔታ ስኬት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተጠናከረ በሄደ ቁጥር በቀጣናው የተረጋጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር፣ ሰላምና ብልፅግናን ለማጎልበት የራሱ የሆነ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው አንስተዋል። ይህንን የኢትዮጵያን መልካም ተሞክሮ በመረዳት እንደ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ጅቡቲ ያሉ የጎረቤት አገራት ተመሳሳይ አረንጓዴ ልማቶችን እየተከተሉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ከዋና ዋና ዓላማዎቹ መካከል አንዱ የግብርና እና የአካባቢ ጥበቃ ልማት መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ይህንን የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ሀሳብ በጽኑ እንደሚደግፈው ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ተነሳሽነት ሲተገበር ቆይቷል። በመርሀግብሩ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ጉልህ ድርሻ እየተጫወተ ይገኛል። ይህ ግዙፍ ብሔራዊ የልማት ፕሮጀክት በኅብረተሰቡ ዘንድ ችግኞችን የመትከልና የመንከባከብ በጎ ባህል እንዲዳብርና የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ እንዲያድግ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል። በተለይም በችግኝ ማፍላት፣ በተከላና ተያያዥ ሥራዎች ላይ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር በሀገሪቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ
May 22, 2026 1001
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2018 (ኢዜአ)፦በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ ስፍራዎች ላይ ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች አንጻራዊ ጥንካሬ ይኖራቸዋል። ከእርጥበት አዘል የአየር ሁኔታው ጋር ተያይዞም የተሻለ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖር ገልጿል። በዚህም በደቡብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖር አመልክቷል። በሚቀጥሉት ቀናት ከሚኖሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት፤ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ብዙ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብሏል። አልፎ አልፎ በውኃ አካላትና በአካባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት፤ በጥቂት የደቡብ፣ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች መጠቆማቸውን ገልጿል። ይህም ለግብርና ሥራ በቂ የአፈር ውስጥ እርጥበት እንዲኖር በማድረግ ለሰብሎች፣ ለግጦሽ ሳርና ለመጠጥ ውኃ አቅርቦት አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዳለው አስታውቋል። ከተፈጥሮና ሰው ሠራሽ የውኃ ማጠራቀሚያዎችን አቅም ለማሳደግ እንዲሁም ለቋሚ ተክሎችም አዎንታዊ ሚና እንዳለው ገልጿል። በተጨማሪም ለመኸር ሰብሎች የማሳ ዝግጅትና ዘር ለመዝራት፣ ፍሬ በማፍራትና በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎች የውኃ ፍላጎት መሟላት፣ ለአረንጓዴ ዕፅዋት ልምላሜ፣ ለመጠጥ ውኃና ለግጦሽ ሳር አቅርቦት መሻሻል የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተጠቁሟል። በተፋሰሶች ላይ ያለውን የእርጥበት ሁኔታ በተመለከተም ባሮ አኮቦ፣ መካከለኛና ታችኛው አባይ፣ በአብዛኛው ኦሞ ጊቤ፣ በላይኛውና መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ የገጸ ምድር ውኃ ፍሰት ይኖራቸዋል ብሏል። በላይኛው ገናሌ ዳዋ፣ ኦጋዴን፣ ታችኛው ተከዜ እንዲሁም በላይኛውና መካከለኛው ዋቤ ሸበሌ ደግሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር ውኃ ፍሰት እንደሚያገኙ ይጠበቃል ብሏል። በተጨማሪም ደረቅ የገጸ ምድር ውኃ ፍሰት የሚኖራቸው በአብዛኛው አፋር ደናኪል፣ አይሻ፣ መካከለኛና ታችኛው አዋሽ እንዲሁም በታችኛው ገናሌ ዳዋ መሆኑን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ ሲል ገልጿል። በሌላ በኩል በበልግ ወቅት የሚኖረው የሙቀት መጠን መጨመርና በሌሊት ደግሞ የሚታየው ወበቅ አንዱ የዚህ ወቅት ክስተት መሆኑን ጠቁሟል። ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ኃይል ጋር ተያይዞም በተለይም በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቤንሻንጉል-ጉሙዝና በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት ከ32 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል።
በክልሉ ከ261 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ ችግኞችን ለመትከል የ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራ ተጀምሯል
May 20, 2026 1180
ባህርዳር ፤ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ከ261 ሺህ ሔክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ ችግኞችን ለመትከል የጉድጓድ ቁፋሮ ስራ መጀመሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር እስመለዓለም ምህረት ለኢዜአ እንደገለፁት የክልሉን የደን ሽፋን ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ ነው። በመጭው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን በላይ የዋንዛ፣ ወይራ ፣ ዝግባ ፣ ፅድ ፣ አኬሺያ ዲከረንስ፣ ባህር ዛፍ፣ የፍራፍሬና ሌሎች ችግኞችን ለመትከል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የችግኝ ተከላውን በስኬት ለማከናወን እስካሁን 401 ሚሊዮን በላይ ጉድጓዶችን በማስቆፈር ለተከላ ዝግጁ ማድረግ መቻሉን አረጋግጠዋል። በቀጣይም የአረንጓዴ አሻራ ግብን ለማሳካት ተጨማሪ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶችን የማስቆፈር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። ባጠቃላይ በክረምቱ ለሚካሄደው ችግኝ ተከላ 261 ሺህ 297 ሄክታር መሬት ከወዲሁ ተለይቶ የጉድጓድ መቆፈር ስራው እየተካሄደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ አርሶ አደር መኮነን ልንገር እንደገለጹት ፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መጀመሩ ተራቁተው የነበሩ አካባቢዎችን መልሰው በደን እንዲሸፈኑ ለማድረግ አስችሏል። መርሃ ግብሩ ለመኖ ፣ በንብ ማነብና እንስሳት እርባታ እያስገኝ ያለውን ተጠቃሚነት ለማስፋት በመጭው ክረምት በሚካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በግልና በወል ቦታዎች ችግኝ ለመትከል ጉድጓዶችን እያዘጋጀን ነው ብለዋል። የሚተከሉት ችግኞች አያስገኙ ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት በየዓመቱ ችግኞችን እያለማሁ ነው ያሉት ደግሞ በደቡብ ጎንደር ዞን የደራ ወረዳ አርሶ አደር ካሴ መንግስት ናቸው። በመጭው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች ተንከባክበን በማሳደግ ለውጤት ለማብቃት ከወዲሁ ዝግጅት ጀምረናል ነው ያሉት። ባለፈው ክረምት በነቃ የህዝብ ተሳትፎ ከተተከለው ከአንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው መጽደቁን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 291
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 2757
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 1600
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 1520
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 24, 2026 534
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የመደመር ማሳያ ከሳምንቱ አበይት ክስተቶች መካከል የኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የጋምቤላ ክልሎች በአሶሳ ከተማ ያስገነቡት የጋራ ሰላምና ልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የህንፃ ምረቃ ይጠቀሳል። በክልሎቹ ትብብር የተከናወነው የህንፃ ግንባታ በመደመር እሳቤ የዜጎችን የጋራ ሰላም ለማስጠበቅና የልማት ተጠቃሚነትን እውን ማድረግ ጥረት ማሳያ ነው። መርሃ ግብሩ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሐሰን፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) የተገኙበት ነበር። በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም ላይ ያተኮረው መድረክ በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የተካሄደውና በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ላይ ያተኮረው ፎረምም በእዚህ ሳምንት ዐበይት ጉዳይ ነበር። ፎረሙ የተካሄደው “ቀጣናዊ ተቋማትን ማጠናከር ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሆን የተዘጋጀውም በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ በሰላም እና ፖለቲካዊ ምክክር ማዕከል (CRPP)፣ በሶማሌ ክልል መንግስት እና በሌሎች አጋር አካላት ነው። በፎረሙ መክፈቻ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ፣ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ከፍተኛ አመራሮች፣ የማህበረሰብ መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፤ መድረኩ የውጭ ተዋናዮች ሳይገቡበት የቀጣናው አካላት በራሳቸው ጉዳይ፣ ፖሊሲና እርስ በእርስ ግንኙነት ላይ ብቻ የሚመክሩበት መሆኑን ጠቅሰዋል። እርስ በእርስ ለመተዋወቅ፣ ግልጽነትን ለመፍጠርና ጠንካራ ትስስርን ለመገንባት የሚያስችል በመሆኑም በቀጣናው ግጭቶች ለመቀነስ በእጅጉ እንደሚረዳ ነው ያነሱት። ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ምሁራን ጥልቅ ውይይት በማድረግ ለቀጣናው ፈተናዎች ተጨባጭ መፍትሄና አቅጣጫ እንዲያስቀምጡም ያግዛል ብለዋል። የጉባ ላይ ብስራቶች ተግባራዊ ልማት የሳምንቱ የበረራ ቅኝታችን የሚጀምረው ወደ ሶማሌ ክልል ጎዴ ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በስፍራው እየተገነባ ያለውን የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል። ከጉብኝታቸው በኋላም በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን ለማሳካት የመሬት፣ ውሃ እና የሚያለማ የሰው ሃይል አስፈላጊ መሆኑን አንስተው በዚህ ሁሉ ኢትዮጵያ በቂ ሃብት ያላት መሆኑን ገልጸዋል። በምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እነዚህን ካሟላን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የሚተርፍ ነገር ማድረግ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካን ጨምሮ የኒውክለር ሃይል ማመንጫ፣ የቢሾፍቱ አየር መንገድ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የቤቶች ልማት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሲመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ያደረጓቸው የጉባ ብስራቶች መሆናቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞጆ ከተማ የተገነባውን የግራንዴር ሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካ መርቀው ስራ ያስጀምሩትም በዚሁ ሳምንት ነበር። በግራንዴር ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተገነባው ፋብሪካ፣ መሰረት ልማቱ በ300 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ፣ የዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ የሴራሚክና የፎርሲሌን ንጣፎች ማምረቻ ፋብሪካ ነው። የፋብሪካው መገንባት የውጭ ምርት ጥገኝነት ከመቀነስ ባለፈ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሚያደርጋት መሆኑ ታውቋል። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ ጉብኝት በዚሁ ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ወደ ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመጓዝ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። በድሬዳዋ ቆይታቸው ብርቱካንና ሌሎች የፍራፍሬ ልማት ሥራዎች እንዲሁም የእንስሳት ሀብት ልማት ስራን ተመልክተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉራዋ ወረዳም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና የግብርና ልማት ሥራዎችንም ጎብኝተዋል። ከጉብኝታቸው በኋላ ባስተላለፉት መልእክትም የጋራ ሙለታ ተፈጥሯዊ የልማት ፀጋና ከፍታም ታሪክን፣ ውብ መልክዓ ተፈጥሮን የታደለ፣ የኢትዮጵያን ሜዳና ተራሮች ምርት የሚታፈስባቸው የማድረግ ሀገራዊ ጉዞ ትልቅ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ማሳያዎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ ተገኝተው 142 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃና የመንገድ ፕሮጀክቶችን መርቀው ሥራ ያስጀመሩትም በዚህ ሳምንት ነበር። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር በለውጡ ዓመታት ከልማት የራቁ አካባቢዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚ ለማድረግ ብዙ መሰራቱን አንስተዋል። የኮንታ ኮይሻ ወረዳ የንጽህ መጠጥ ውሃና የመንገድ ፕሮጀክቶች ለዚሁ ማሳያ ናቸው ብለዋል። በተመሳሳይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፤ በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የተገነቡ የንጹህ መጠጥ እና የመስኖ ፕሮጀክቶች መርቀው ለአገልግሎት አብቅተዋል። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ በተለይ አርብቶ አደሮች ውሃ ለማግኘት ሩቅ አካባቢዎች ሲሄዱ ይደርስባቸው የነበረን እንግልት የሚያስቀር ነው። የመስኖ ፕሮጀክቱም የክልሉ አርብቶና አርሶ አደሮች በአካባቢው ያለውን ሰፊ መሬት በማልማት ምርታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። በፕሮጀክቶቹ ምረቃ ላይ የፌዴራልና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። በሲዳማ ክልልም በፌደራል መንግስት ድጋፍ በ460 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዳዬ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታም ተመርቋል። ፕሮጀክቱ 75 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። ፕሮጀክቱ የተመረቀው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) ነው። በሌላ በኩል የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ከ543 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 52 የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መመረቃቸው ሌላው የሳምንቱ ክስተት ነበር። በዞኑ ለምረቃ ከበቁ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል የትምህርት፣ የጤና፣ የውሃና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ ቃሉ ወረዳ በ365 ሚሊዮን ብር የተገነባውን የዲርማ ወንዝ መስኖ ፕሮጀክትንም መርቀዋል። ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ የሚደረግበት የሃዋሳ ከተማ ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብርም በዚህ ሳምንት ተካሂዳል። ለፕሮጀክቱ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የፕሮጀክቱ ግንበታ ሲጠናቀቀ ሀዋሳ ከተማዋን ጽዱ በማድረግ የቱሪዝምና የኢንቨስመንት ማዕከልነቷን ያሳድገዋል ተብሏል። አቶ ደስታ የፕሮጀክቱ ግንባታ መንግስት ለከተሞች እድገት የሰጠውን ልዩ ትኩረት ያሳያል ሲሉም ነው የጠቀሱት። የከሰም መስኖ ግድብ የከሰም መስኖ ግድብ የጥገና ማሻሻያ ፕሮጀክትም በዚሁ ሳምንት ተመርቆ ሥራ ጀመሯል። ፕሮጀክቱ የተመረቀው በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ነው። የማሻሻያ ግንባታ መጠናቀቅ ከሚሰጠው ዘላቂ የልማት አገልግሎት ባሻገር የአካባቢውን ማህበረሰብ ለዓመታት ሲፈታተን የነበረውን የጎርፍ ስጋት ያስቀራል ተብሏል። በዚህ ወቅት ሚኒስትር አብርሃም (ዶ/ር) እንዳሉት፥ የከሰም መስኖ ግድብ ቀደም ሲል በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ እንደ ትልቅ ስጋት ይታይ ነበር። የጥገና ማሻሻያው በአካባቢው ማህበረሰብ የነበረውን ይህን የአደጋ ስጋት በማስቀረት ግድቡን ለታለመለት የመስኖ ልማት ለማዋል የሚያስችል ነው። ለፕሮጀክቱም 2 ቢሊዮን ብር በጀት መውጣቱን ሚኒስትሩ አንስተዋል። የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፤ ፕሮጀክቱ ህብረተሰቡን ከስጋት ያዳነ እና በርካታ ጥቅሞች ያሉት ነው ብለዋል። የግድቡ ጥገና መጠናቀቅ የሀዝቡን የቆየ ጥያቄ የፈታ መሆኑንም አንስተዋል። የግንቦት - ታላቁ ሁነት ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ድምጻቸውን ለመስጠት የተመዘገቡበት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ቀርተውታል። የፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳና የምርጫ ሂደቱን ስኬታማ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ አጠቃላይ ዜጎችና የሚመለከታቸው ሁሉ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። በዚሁ ሳምንት "ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚ ና" በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር በአዳማ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፤ የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት የዜጎች ጠንካራ ተሳትፎና የዳበረ የዴሞክራሲ ልምምድ የታየበት መሆኑን አንስተዋል። ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅም መገናኛ ብዙሃን የላቀ ሚናቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። ከተረጅነት የመውጣት ሀገራዊ ጥረት በድሬዳዋ "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የውይይት መድረክም ሌላው የእዚህ ሳምንት ዓቢይ ጉዳይ ነው። መድረኩን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የግብርና ሚኒስቴር በመተባበር ያዘጋጁት ነው። በመድረኩም በምግብ ራሱን የቻለ ትውልድ የመገንባት ጥረት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት እውን የማድረግ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑ ተነስቷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በምግብ ራሱን የቻለ ትውልድ የመገንባት ጥረት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት እውን የማድረግ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በቂና የተሟላ የውሃ ሀብት፣ የተማረና አምራች የሆነ ወጣት የሰው ኃይል እንዲሁም ለም የመሬት ፀጋዎች ያሉባት ሀገር በመሆኗ በማልማት እድገትና ማንሳራራትን ማስቀጠል ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል። ለእዚህም ዋናው መሠረታዊ ጉዳይም ያሉ አቅሞችን በመለየትና ህዝብን ወደ ላቀ ምርታማነት ደረጃ በማሸጋገር በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጡን ሥራ በላቀ ደረጃ ማስቀጠል መቻል መሆኑን አንስተዋል። ለሰላም ጥሪ የተሰጠ ምላሽ የሠላም ጥሪን የተቀበሉ የአማራ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የመረከብ፣ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ የማድረግና የመልሶ ማቋቋም (ዲዲአር) መርሀግብርም በዚህ ሳምንት ተከናውኗል። በብሔራዊ ተሀድሶ ማዕከል ጠዳ ጊዜያዊ ማሰልጠኛ ማዕከል በተዘጋጀው መርሀግብር ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስትሩ መሀመድ እድሪስ የቀድሞ ታጣቂዎች ከስልጠና በኋላ ከምንም በላይ የሰላም ዘብ ሆነው የበደሉትን ህዝብ ለመካስ በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። ታጣቂዎቹ ሠላምን አማራጭ በማድረግና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለሠላም ያደረጉት አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል። የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን፣ መንግስት ለሠላም ባለው ጽኑ አቋምና ፍላጎት የሠላም ጥሪውን ተቀብለው የገቡ የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሀድሶ ስልጠና እንዲያልፉ በማድረግ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ እያደረገ ነው ብለዋል። በተመሳሳይ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ የክልሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በኮምቦልቻ የስልጠና ማዕከል ስልጠና የጀመሩ መሆኑ ይታወቃል። ሐረር- ፕሮጀክቶች ምረቃ የሐረሪ ክለል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙትን የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝትም ሌላው የእዚህ ሳምንት ኩነት ነበር። በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ወቅት በተሻለ አፈጻጸም ላይ ይገኛሉ። በተለይም የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መገንባት የክልሉን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የበለጠ በማሳደግ ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ነው ያነሱት። በዘመናዊ ትምህርት የታነፀና በእውቀት የበለፀገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን በማፍራት ረገድ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑንም አንስተዋል። ፕሮጀክቶቹ በፍጥነትና በጥራት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ለማስቻል በአስተዳደሩ በኩል ተገቢው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል። የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት 672 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባው የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በይፋ የተመረቀውም በዚህ ሳምንት ነው። በምረቃው ላይ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን፣ የክልሉ የመንገዶች ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢድሪስ ሙሴ እና ሌሎችም ተገኝተዋል። የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እንደገለጹት ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት የከተማውን የንግድ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የሚያስችል ነው። የከተማውን ገፅታ በመለወጥ ረገድም የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ነው ያነሱት። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው የመንገድ ፕሮጀክቱ የጂግጂጋ ከተማን ልማትና ዕድገት በማፋጠን በኩል ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የመንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን አስተዳደሩ ሀገራዊ የመንገድ መሰረተ ልማት ዕቅድን ለማሳካት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ የጂግጂጋ ከተማ ተለዋጭ የመንገድ ፕሮጀክትም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል። የመንገድ ፕሮጀክቱ 7 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን 30 ሜትር ስፋት እንዳለውም ታውቋል።
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 17, 2026 1898
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን። 👉የግንቦት - ታላቁ ሁነት የምርጫ ጉዳይ ወቅታዊና ሀገራዊ አጀንዳ ሆኖ በሁሉም አካባቢዎች የዜጎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለበት ሳምንት ነው። መራጮች ካርዳችንን ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተመቻቸላቸው ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምድ የፖሊሲ አማራጮቻቸውንና ማኒፌስቷቸውን እያስተዋወቁ ቀጥለዋል። የተለያዩ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ዜጎች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት በመስጠት ሙያዊና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ለዘንደሮው ጠቅላላ ምርጫ በመራጮች ትምህርት ላይ ለሚሰማሩ 169 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና መስጠቱ ይታወቃል። 👉የመጠጥ ውሃ ችግሮችን የመፍታት ጥረት ማሳያዎች በሳምንቱ በወላይታ ዞን ከ150 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሆቢቻ ወረዳ ብዝሃ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። ፕሮጀክቶቹን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) መርቀዋል። የፕሮጀክቶቹ ተመርቀው ለአገልግሎት መብቃት ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የላቀ ትርጉም እንዳለው ተነስቷል። በተመሳሳይ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ በቀብሪደሃር ከተማ በ407 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄድ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አስጀምረዋል። ከለውጡ በኋላ በክልሉ ከ370 በላይ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ተቆፍረው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በዚህም የመጠጥ ውሃ ሽፋኑ ከ19 ወደ 52 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ታውቋል። በምስራቅ ሐረርጌ ዞንም የደደር ከተማንና የአካባቢውን ማህበረሰብ የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ታስቦ የተገነባው ፕሮጀክትም ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው በዚሁ ሳምንት ነበር። የፕሮጀክቱ ምረቃ ላይ የኦሮሚያ ክልል መሬት ቢሮ ሃላፊ መሰረት አሰፋ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር እና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ደደር ከተማን ጨምሮ ሌሎች በወረዳው ሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። 👉የጤና ጉዳይ የጤና ሚኒስቴር የተቀናጀ የህክምና እና የምርመራ ዘመቻ ከግንቦት 3 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በስምንት ክልሎች በሚገኙ 154 ወረዳዎች የሚያካሄድ መሆኑ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ይሄው መርሃ ግብር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በይፋ ተጀምሯል። መርሃ ግብሩ በተለይም ትምህርት ቤቶችን ማዕከል በማድረግ የሚከናወን ሲሆን ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል አላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል። 👉ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በሐዋሳ ከተማ የተካሄደው የውይይት መድረክም የሳምንቱ አበይት ጉዳይ ነበር። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ ሀገራዊ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት የመውጣት ጥረት ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በግብርና ልማት በተለይም የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ አልፎ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተመዘገበውን የላቀ ስኬት ለአብነት ጠቅሰዋል። በሌሎች የተለያዩ የግብርና የልማት ስራዎችንም በተጠናከረ መልኩ በማከናወን ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ ከተረጂነት የመውጣት ጉዳይ የብሔራዊ ጥቅም አካል ሆኖ የመንግስት ስትራቴጂክ አጀንዳ ተደርጎ በፖሊሲ አቅጣጫ እየተመራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ምርታማነትን በማሳደግ የሀገርን ብልጽግና እውን በማድረግ የኢትዮጵያን የድህነት ታሪክ መቀየር ይኖርብናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዋና ስራ አስፈፃሚ ሠይፈ ደርቤ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በምግብ ራስን ለመቻል የተጀመረው ግብ እንዲሳካ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም ሚዲያ የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸው ኢዜአ ይህንን ሀገራዊ ትልም ለማሳካት የይዘት ስራዎችን በስፋት ተደራሽ የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 👉የምግብ ስርዓት ሽግግር በጋምቤላ ክልል ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የምግብ ስርዓት ሽግግር እና የኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጋምቤላ ከተማ በይፋ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር)፤ በክልሉ የተሟላ ስርዓተ ምግብን በማረጋገጥ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል። 👉ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በአሶሳ በአሶሳ ከተማ ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ የተጀመረው በዚሁ ሳምንት ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ የትምህርት ቤቱን ግንባታ አስጀምረዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 34 ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ መሆኑን ያስታወሱት የትምህርት ሚኒስትሩ፤ በአሶሳ ከተማ የሚገነባው ትምህርት ቤትም በአንድ ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ብለዋል። 👉የሰላምና አብሮነት እሴት ግንባታ የሐረሪ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞንና የማያ ከተማ አስተዳደር "የህዝቦች ሰላምና አብሮነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ የህዝብ ለህዝብ የሰላምና አብሮነት ኮንፍረንስ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፤ የሐረርጌ ህዝቦች ትስስር በሀገሪቱ የታሪክ ማህደር ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጠውና ለታላቅ ማህበራዊ ውህደት ተምሳሌት እንደሚሆን ገልጸዋል። የኮንፈረንሱም ዓላማ የሰላም እሴት ግንባታና የልማት ትስስርን ይበልጥ ማጠናከር ስለመሆኑ አንስተዋል። 👉የግብርና ልማትና ምርታማነት በአማራ ክልል ለዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ያስታወቀው በዚሁ ሳምንት ነው። የአፈር ለምነትን በዘላቂነት ለማሻሻል ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ76 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ኮምፖስት መዘጋጀቱ ታውቋል። 👉በኦሮሚያ ክልልም ለዘንደሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካል የሆነው ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአቮካዶ ተክል እንደሚሸፈን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ኃላፊ ሙሐመድሳኒ አሚን፤ በመጪው ክረምት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም አቮካዶን ጨምሮ አስር አይነት የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች ስለመዘጋጀታቸውም ተናግረዋል። በተለይም አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ዘይቱን፣ ፓፓያ፣ ግሽጣ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ሎሚና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች በስፋት መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በክልሉ የአቮካዶ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን በማዳቀል የችግኝ ዝግጅት ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት። በክልሉ እስካሁን ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመደበኛና በተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞች መሸፈኑንም ገልጸዋል። 👉የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ ሎካ አባያና ደራራ ወረዳዎች በበልግ ወቅት በኩታ ገጠም እየለማ ያለውን የበቆሎ ማሳ በመስክ የተመለከቱትም በዚሁ ሳምንት ነው። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ የሰብል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ገበያን የሚያረጋጋ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ውጤት እየተገኘ ነው። በዚህም በበልግ ወቅትም ፆም የሚያድር መሬት እንዳይኖር በማድረግና ግብአቶችን በወቅቱ በማቅረብ እየተከናወነ ባለው የእርሻ ስራ የምርት ቁመናው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰዋል። በበልጉ ያለውን አመቺ የዝናብ ስርጭት እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅርቦት በመጠቀም የተሻለ ምርት ለማግኘት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት አሁን ላይ ለማሳ እንክብካቤ ስራ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። 👉የኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው የመረቋቸው የምግብ ዘይት እና የቆርቆሮ ማምረቻ ፋብሪካዎች ሥራ የጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው። የከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙሄ፤ በኮምቦልቻ የኢንዱስትሪ ልማት ይበልጥ እያንሰራራ ስለመሆኑ አንስተዋል። በኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ በድምሩ 69 አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ገልጸው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረትና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡትን በመተካት ከፍተኛ የሃብት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 10, 2026 2132
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2018 (ኢዜአ)፡- በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምልከታ- በሱሉልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳምንቱ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ በ2 ሺህ 150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ሰብል ጎብኝተዋል። መንግሥት በግብርናው ዘርፍ በወሰዳቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች እየተገኙ ያሉ ውጤቶች አመርቂና ለቀጣይ ሥራዎች ስንቅ መሆናቸውን በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል። መሬት ጦም ማደር የለበትም በሚል ጽኑ እምነት የተጀመረው የበጋ ስንዴ ልማት አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ስለመሆኑም አንስተዋል። ከልመና ራሳችንን መገላገል አለብን፤ ሊታረስና ሊለማ የሚችል መሬት መታረስ አለበት በሚል ጽኑ እምነት የበጋ ስንዴ ልማት መጀመሩን አስታውሰው፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አሁን ላይ አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። የቱሪዝም ልማት የወፍ በረር ጉዟችን የቀጠለ ሲሆን ከሱሉልታ ቀጥታ ወደ አማራ ክልል ባህር ዳር አምርተናል። የባህር ዳር መዳረሻችን በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ዳርቻ ላይ በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ይሆናል። የሪዞርቱ ግንባታ ተጠናቆ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ባሳምንቱ ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" እቅድ መሰረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት አላማ በማድረግ ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት መገንባቱ ተመላክቷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህርዳር ከተማ ቆይታቸው በ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገነባውን ፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ጣና የሆቴል ፕሮጀክት ግንባታም አስጀምረዋል። በሚድሮክ ኢንቨስትመንት የሚገነባው ይህ ዓለም አቀፍ ሆቴልም በ18 ወራት ውስጥ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ መሆኑ ታውቋል። የመልካ ቁንጡሬ ሁነት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀንን በዩኔስኮ በተመዘገበው በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ በሳምንቱ በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል። የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ ተከብሯል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ህይወት ኃይሉ፤ ባህላዊና የተፈጥሮ ቅርሶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት ይቀጥላሉ ብለዋል። ሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ የሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ልማት የዲዛይን ሥራ ተጠናቅቆ ለህዝብ ይፋ የተደረገውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በወቅቱ እንደገለጹት ከተማዋን ለኑሮ፣ ለስራ፣ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ውጤት እያስገኙ ነው። የልማት ስራዎቹ ከተማዋ ሀገር አቀፍ ስብሰባዎችን¸፣ ስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎች ኩነቶችን በማስተናገድ ተመራጭ እየሆነች እንድትመጣ አድርገዋታል ብለዋል። የሀይቅ ዳርቻ ልማቱ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትና የተወዳዳሪነት አቅም ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ጠቁመው ለተግባራዊነቱ በትብብር እንደሚሰራ አመላክተዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥሉ ብለዋል። የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻን በማልማትና ከአካባቢው መስህቦች ጋር በማስተሳሳር ሀይቁን የቱሪዝም ማዕከል የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል። ጅማ ዞን ጎማ ሁለት በጅማ አጠር ያለ ቆይታችን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅማ ዞን ጎማ ሁለት የምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን በማስተዋወቅ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በዚህ የቅስቀሳ ስነ ስርአት ላይ የፓርቲው አባላትና አመራሮች እንዲሁም ደጋፊዎች በመውጣት የተሳተፉበት መሆኑን ለማየት ችለናል። በመርሃ ግብሩ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ፤ በፓርቲው አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልጸው በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። በተመሳሳይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ርዕሰ መስተዳድሩ በሚወዳደሩበት ምስራቅ ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ የምርጫ ቅስቀሳና እጩ የማስተዋወቅ መርሐ ግብር የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት ብልፅግና ፓርቲ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችንን ሲያከናውን ቆይቷል። በባለፉት የለውጥ ዓመታት የሀገርን እድገትና የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን በመተግበር ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል። የሽንሌ እመርታ በሳምንቱ በሶማሌ ክልል ሽንሌ ወረዳ የተገነባው የ10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስፋልት መንገድና በሽንሌ ጠቅላላ ሆስፒታል የተገነባው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ተመርቋል። በሽንሌ ወረዳ የመርማርሳ ከተማን ከድሬዳዋ ጋር የሚያስተሳስር የ3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታንም አስጀምረዋል። የተገነቡት የልማት ስራዎች በተለይም ለወረዳው እመርታ መሆኑን የገለጹት አመራሮቹ በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት የማልማትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራዎች ይቀጥላሉ ብለዋል። ሳተላይት በሐረር የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀቢያ ጣቢያ ተከላ ስራ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በተገኙበት በዚሁ ሳምንት ተጀምሯል። የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ሲሆን የመረጃ ግብዓት ከመሆን አኳያም ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል። የመንገድ ዲዛይን፣ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራ ለሚያከናውኑ፣ የመሬት አጠቃቀምን በጥንቃቄ ለመቆጣጠር፣ ለይዞታ መረጋገጫና ሌሎችም የተሟላ መረጃ ለመስጠት የሚጠቅም መሆኑ ታውቋል።
የአፍሪካዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣረ ዎዴ ማያ - በአዲስ አበባ
May 6, 2026 1953
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ጉባኤ በአዲስ አበባ፣ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ይህ ጉባኤ ከሚያዚያ 29 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ አህጉራዊ መድረክ ነው። የአህጉሪቷ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎች እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት ይህ መድረክ፤ የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ አልሟል። ታዋቂው የአፍሪካዊ ዲጂታል ታሪክ ተራኪ ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) ጨምሮ የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) በዲጂታል መገናኛ ብዙኅን የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክትና ገፅታ ለዓለም የሚያስተዋውቅ ዓለም አቀፍ አንቱታን ያተረፈ የአህጉሪቷ የዘርፉ ፈርጥ ነው። ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያለው ጋናዊው ታዋቂ ዩቲዩበርና የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) አዲስ አበባ ገብቷል። በጉባኤው ላይ የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) መገኘትም የአፍሪካን የዲጂታል ገፅታ መቀየር የሚያስችል የአህጉራዊ ይዘት ፈጠራ ትብብርን ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ይጠበቃል። የአየር በረራ መሐንዲስ ስልጡኑ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የዲጂታል ታሪክ ተራኪነት ጉዞ በሀገረ ቻይና ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት ነበር የዩቱዩብ ይዘት ፈጠራን መሞከር የጀመረው። የመጀመሪያዎቹ የዲጂታል ይዘት ፈጠራ ሥራዎቹም አስቂኝ የነበሩ ቢሆንም ወላጅ አባቱ የአፍሪካን በጎ ገፅታ ለዓለም ማስተዋወቅ እንዳለበት የሰጡትን ምክር ተከትሎ ጉዞውን ቀይሯል። ባህላዊ ግንኙነትን ለማጠናከር የቻይንኛ ቋንቋ ቪዲዮዎችን ያዘጋጅ የነበረው ዎዴ ማያ፤ ወደ ጋና ተመልሶ በሰራቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራዎቹ የሚፈለገውን ያህል ዕውቅና አላስገኙለትም ነበር። መነሻውን በአዲስ አበባ በማድረግ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉዞ በማድረግ አህጉሪቷን ለማስተዋወቅ ከሰራቸው ይዘቶች ውስጥ በሩዋንዳ የሰራው ቪዲዮ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ዕውቅናው እንዲናኝ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በእርሱ አተራረክ ማዕከላዊ ስፍራ እንዳላት የሚናገረው ዎዴ ማያ፤ የአፍሪካን ያልተነገሩ ስኬቶችና የአፍሪካዊያን ፅናት በተከታታይ ለዓለም ማስተዋወቁን ተያይዞታል። አሁን ላይ የአፍሪካን ለውጥ፣ ተስፋና ዕድሎች ለዓለም ማህበረሰብ የሚያስተዋውቁ ዘጋቢ ፊልሞችን በመስራት የአህጉሪቷን ስሁት ትርክት በመቀየር ረገድ ጉልህ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሰዎች አንዱ ሆኗል። በሚሊዮን የሚቆጠር ዕይታ ያላቸውን ዘጋቢ ፊልሞቹና የጉዞ ታሪኮችም ጊዜ ያለፈባቸው ስሁት ትርክቶችን በመሞገት የአፍሪካን ተስፋና ዕድሎች ለዓለም በመግለጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኢትዮጵያን ዕድገትና ተስፋ ደጋግሞ የተረከው ዎዴ ማያ፤ በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) ወደ አዲስ አበባ መምጣቱም መድረኩን ተምሳሌታዊና ስልታዊ ያደርገዋል። ይህም የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የግል ጉዞ ከመሆኑም በላይ፤ ኢትዮጵያ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረክ ፈጠራና የታሪክ አተራረክ ለውጦች ማዕከላዊ ሚና በተግባር ያስመሰክራል። በዚህ ጉባኤ፤ እንደ ዎዴ ማያ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መሰባሰብ የአፍሪካን የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር በማጠናከር ይዘት ፈጣሪዎች የአህጉራቸውን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ጉልህ ፋይዳ አለው። ለኢትዮጵያም የዎዴ ማያ መገኘት ሀገሪቱ ለአፍሪካ ዲጂታልና ባህላዊ ሕዳሴ ያላትን ቁርጠኝነት የበለጠ በማሳደግ አዲስ አበባን የአፍሪካ የዲጂታል ገፅታ ግንባታ ሃሳቦች መነሻነት በተግባር ያረጋግጣል።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ የመገንባት ሂደት እና የኮሪደር ልማት
May 24, 2026 1490
በኢዜአ ዐይን ...! በዮሐንስ ደርበው ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ የመገንባት ሂደት እና የኮሪደር ልማት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ጥቅምት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙ ጊዜ፤ የኮሪደር ልማት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። ከተማ ሲለማ ደግሞ ለነዋሪም ሆነ ለጎብኝ፤ ለዐይንም፣ ለጤናም ለእንቅስቃሴም ውበትና ምቾት ማላበሱ አይካድም። የኮሪደር ልማት ጽዱ ከተሞችን ይሠራል፤ከትራንስፖርት፣ ከትራፊክ ምልክቶች፣ ከብስክሌትና እግረኛ መንገድ ደኅንነት ጋርም ተጣጥሞ ተሠርቷል። በዚህ ዐውድ የኮሪደር ልማት ውበትም ምቾትም ነው። መሠረተ-ልማት ተጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲጠቅምም የኮሪደር ልማት ሚና የላቀ ነው። እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለአንጀት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች በውል ይታወቃሉ? ቀድሞስ መከላከል ይቻላል? የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ለአገልግሎት ክፍት መሆን ኢትዮጵያ በከተሞቿ እና ገጠራማ አካባቢዎቿ የኮሪደር ልማት እያከናወነች ነው። ይህ በኢትዮጵያ ከውበት በላይ ነው። ለምን ቢሉ? ዘርፈ-ብዙ ጥቅም ስላለው ይሆናል መልሱ። · ማኅበራዊ መሥተጋብርን በመጠገን፡- ኢትዮጵያውያን ከሚታወቁባቸው አንዱ በየዐውዱ የሚገለጠው ጥብቅ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸው ነው። በጋራ መንቀሳቀስ፣ መጫዎት፣ ከቤት ወጣ ብለው መመካከር የኑሯቸው አካል ነው። ይሁንእንጅ በተለይም ከተሜው ከወዳጅ ጋር በኅብረት በእግር ወይም በብስክሌት ለመንቀሳቀስ፣ አረፍ ብሎ የሚያወጋበት በቂ አረንጓዴ ስፍራና ፓርኮች ባለመኖራቸው ማኅበራዊ መሥተጋብሩ እየላላ የመጣ ይመስላል። አሁን የኮሪደር ልማት በደረሰባቸው ከተሞች፤ሰዎች ሲያሻቸው በእግር አሊያም በብስክሌት ከወዳጆቻቸው ጋር የልባቸውን እያወጉ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው መሐል ዐረፍ ማለት ቢሹም ችግር የለም፤ አሁን እንደ ድሮ አይደለምና። አረንጓዴ መናፈሻ ስፍራ ፍለጋ ከከተማ መውጣት አያሻም። በሌላ በኩል ወጣቶች እና ሕጻናት ኳስ የሚጫወቱበት ስፍራ መመቻቸቱ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር፤ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸውን ያጠናክራል። · ጤናማ አከባቢን በመፍጠር፡- የኮሪደር ልማት ለሰው ልጆች ከቸራቸው ጥቅሞች አንዱ፤ ጤናማ ከባቢን መፍጠር ነው። በተለይም በደካማ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ለሚታሙ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሁነኛ መፍትሔ ሆኗል። ይህ ደግሞ በቀጥታ ከነዋሪዎች ጤና ጋር ይገናኛል።ደግሞም በንጹህ አካባቢ የመኖር መብትን ማስጠበቅ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመሥራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሠርተዋል ያሉትም ለዚህ ነው። · በሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኮሪደር ልማት የዘመቻ ሥራ አይደለም።በትንሹ በአንድ ከተማ ወይም አካባቢ ተጀምሮ እየሰፋ ይቀጥላል። በዚህ ሂደት የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ማሰብ አያዳግትም። እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ፤ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያገለግሉ የመኪና ማቆሚያ፣ ሱቆች እና መሰል ለንግድ ተግባራት እንዲበጁ ተደርገው ነው። የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው ይታወሳል። · በገጽታ ግንባታ ረገድ፡- ከተሞች ሲጸዱና ምቹ ሲሆኑ በዐለም ዘንድ መታወቂያ ይሆናሉ። ነዋሪም በኩራት ስለአካባቢው በየሄደበት አምባሳደር ሆኖ ይመሠክራል። ቱሪስቶችንም ይስባሉ። የቆይታ ጊዜያቸውንም ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉ። ዐለም ዐቀፍ፣ አኅጉር ዐቀፍ እና ሀገር ዐቀፍ ጉባዔዎች እንዲካሄድባቸውም እንዲመረጡ ያስችላል። በከተሞች ከሚሠራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት እየተሠራ ነው። ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ ልማት ለዜጎች መቅረቡን ያሳያል። ይህም ኢትዮጵያውያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ተናግረዋል። የተሟላ ብልጽግና የምናረጋግጠው በዚሁ መንገድ ነውም ብለዋል። የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገት በሁሉም አካባቢ ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት መጠናከር ጠቀሜታው የጎላ ነው። የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ብዙ ጥቅም አለው፤ ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል። የከተሞች መዋብና ምቹ መሆን ለነዋሪው ነው፤ በቀጥታ ተጠቃሚውም ሕዝቡ። ስለዚህ መንግሥት ከሚያከናውናቸው በተጨማሪ ባለሃብቱ፣የመንግሥትም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ኅብረተሰቡ የኮሪደር ልማትን በተነሳሽነት ለማስፋፋት መትጋት ይጠበቅበታል። #የኮሪደር_ልማት #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #ኢትዮጵያ
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 23, 2026 663
በዮሐንስ ደርበው ከግንቦት 9 እስከ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … 👉የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ለአገልግሎት ክፍት መሆን የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ጉዟችን አካል እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ እመርታ ትልቅ ማሳያ የሆነው የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስታውቀዋል። ፋብሪካው የዓለም ዓቀፍ ጥራትና ተወዳዳሪነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሴራሚክ ምርቶችን የሚያቀርብ መሆኑንም ገልጸዋል። ለምርቱ የሚያስፈልጉትን ጥሬ ዕቃዎች ከ80 በመቶ በላይ ከሀገር ውስጥ ዐቅም ያገኛልም ብለዋል። ይህ ስኬት ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብትና እምቅ ጸጋ የመጠቀም ብቃቷን ከመገንባቱ ባሻገር፤ በውጭ ገቢ ምርቶች ላይ ያለንን ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል ነው ያሉት። 👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጎዴ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት ያደረጉት ጉብኝት ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጎዴ የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ሥራ የደረሰበትን ደረጃ ለመገምገም የፕሮጀክት ስፍራውን ጎብኝተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ይህ ሥራ ከመሠረተ-ልማት ግንባታም በላይ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንዱስትሪ ዕድገት እና በኢኮኖሚ ራስን የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቨስትመንት መሆኑን አስገንዝበዋል። በፕሮጀክቱ ስፍራ የሚታየው የሥራ ሂደት ፍጥነት አበረታች መሆኑን ጠቁመው፤ ይህን ግዙፍ እና እጅግ ጠቃሚ ሀገራዊ ፕሮጀክት ለመፈፀም ያለውን ቁርጠኝነት እና ትብብር በሚያንፀባርቅ ሁኔታ በተለያዩ የፕሮጀክቱ ክፍሎች ያሉት ግንባታዎች በዕቅዳችን መሠረት እየተጓዙ ይገኛሉ ሲሉም አረጋግጠዋል። 👉የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት “የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት” በተሰኘውና ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችው ትልቅ ድል በተበሰረበት ሀገራዊ ጉባዔና ኤግዚቢሽን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር። በዚሁ ወቅትም፤ የተመለከቱት የዘርፉ እመርታ እጅግ አስደሳች ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብለዋል። መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ መሆኑንም አስገንዝበዋል። የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻታችንን ማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ ዐቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነው ብለዋል። ከሁሉም በላይ፤ የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ሥራ በሀገር ልጆች ዕውቀትና ክኅሎት ሲከወን ማየት ታላቅ ሀገራዊ ኩራት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ ትኩረታችን በቁጥር በሚገለጹ ውጤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሰው ተኮር በሆኑና በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦችም ላይ መሆን አለበት ነው ያሉት። 👉ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሐረሪ ክልል ያደረጉት የልማት ሥራዎች ጉብኝት ባሳለፍነው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሐረሪ ክልል የልማት ሥራዎች የጎበኙ ሲሆን በወቅቱም፤ በሐረሪ ክልል የተመለከትነው የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ በመቀየሩ ረገድ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል። በሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ የተገነቡት ቤቶች የሰዎችን ማደሪያ ከሕጻናትና ከከብቶች ቤት የለዩ፣ የዶሮ እርባታ፣ ሻወርና መፀዳጃ ቤት እንዲሁም የጓሮ የሌማት ትሩፋትን ያካተቱ ሙሉ ፓኬጅ መሆናቸውን ገልጸዋል። የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን ጉልበትና ሀገር በቀል ዕውቀት በመጠቀም፣ በአነስተኛ ወጪ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በሐረር ከተማ እየተከናወኑ ያሉትን የማር፣ የወተትና የዶሮ እርባታ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን የጎበኙ ሲሆን፤ በከተማው በኢኒሼቲቩ በግለሰብና በመንግሥት ደረጃ ሼዶችን በመገንባት የማር፣ የወተት፣ የእንቁላልና የአሳ መንደሮችን የማቋቋም ሥራ በስፋት እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። እንደ ሀገር የአመጋገብ ሥርዓታችንን ከመሠረቱ ለመቀየር እና በምግብ እራስን ለመቻል ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል። የእንስሳት፣ የዶሮና ዓሳ ዝርያ ማሻሻልና መኖ ማቀነባበሪያዎች ላይም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራበት ይገኛል ነው ያሉት። 👉የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ80ኛ ዓመት ክብረ በዓል የእራት መርሐ ግብር ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጽናት፣ የዕድገት እና የጥቁር ሕዝብ የከፍታ ዓርማ ነው ብለዋል። ሀገር ማጽናት የሚቻለው ተቋማትን በማጽናት ነው፤ በዘመናዊ ታሪካችን የገጠሙን የስብራት ወጀቦችን አልፎ፣ የኢትዮጵያን ስምና ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ ታሪክ እየጻፈ የተጓዘው አየር መንገዳችን የጽናታችን ግንባር ቀደም ማረጋገጫ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ለሀገራችንም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማምጣት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ ሀገራችንን በአቪዬሽን መሠረተ ልማት ከፍ በማድረግ፣ የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝና በሌሎች ዘርፎች ባለው ግዙፍ አበርክቶው የዕድገታችን ምሰሶ ሆኗልም ነው ያሉት። ይህ ተቋም በሁለት እግሩ እንዲቆም ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ መሪዎችና ሠራተኞች ነበሩት፤ አሁንም አሉት፣ ወደፊትም ይኖሩታል። ይህ የተቋሙ አንጡራ ሀብት በመሆኑ የመንግስት ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አረጋግጠዋል።
እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት
May 17, 2026 4185
በኢዜአ ዐይን …! በዮሐንስ ደርበው እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለእንግልትና ብልሹ አሠራር አጋላጭ ሁኔታዎች ይስተካከሉን የሚሉ እሮሮዎች በተለያዩ ሕዝባዊ ውይይቶች ሲነሱ ቆይተዋል። በተለይም በአንዳንድ ተቋማት መንግሥታዊ አገልግሎት ለማግኘት እዚያም እዚህም መንከራተት፤ደግሞም ወረፋ በመጠበቅ መጉላላት ብሎም ለጊዜና ገንዘብ ወጪ መዳረግ ይስተዋላል የሚሉ ሐሳቦች ተስተጋብተዋል። ሾተላይ ምንድነው? እንዴትስ ይከሰታል? ቀድሞ መከላከልስ ይቻላል? ባሳለፍነው ሳምንት … መንግሥትም የተነሱ ቅሬታዎችን ማረቅ የሚያስችል አሠራር በመንደፍ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንድ ብሎ አስጀመረ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማዕከሉ አገልግሎት ባስጀመሩበት ወቅትም ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሠራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ብለው ነበር። አሁን ላይም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሁን በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ነው።መስፋፋቱም በማዕከላት ብዛት፣በአገልግሎት መስጫ መስኮቶች ቁጥር እና በአገልግሎት ዐይነቶች እየተገለጠ ነው። በዚህም በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት የተደራጁ ሲሆን ይህ አሃዝም ለዘርፉ የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት እና ያለውን ፈጣን እድገት ያመላክታል። ጉዳዩ የዜጎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ማላቅ፤ ብልሹ አሠራርንም መቅረፍ ነውና መንግሥት በልዩ ትኩረት ይዞታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ አሥተዳደርና በሐረሪ ክልል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅትም፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የምልከታቸው አካል ማድረጋቸው ለጉዳዩ የተሰጠውን ከፍያለ ትኩረት ያሳያል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሶብ የሞባይል አገልግሎትን በመረቁበት ወቅት ደግሞ፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ብለዋል። አክለውም፤በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች ዕርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧል፤ ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል። ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል፤ እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ መሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል ማለቱም ይታወቃል። የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ማሞ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ደግሞ፤ ዘመናዊና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ምኅዳር በመፍጠር የተገልጋዮችን እርካታ ማረጋገጥ ያስቻለ ስኬት ተገኝቷል ብለዋል። በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ የመንግሥት አገልግሎቶችም ዜጋ ተኮር፣ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍልና የተገልጋዮችን ፍላጎት ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል። በዲጂታል 2030 የአገልግሎት አሰጣጥ አመላካች ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚጠቀሱ 50 ሀገራት መካከል አንዷ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዜጎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በኦንላይን በየትኛውም ቦታ ሁሉንም አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ ስለመሆኑም እንዲሁ። አገልገሎቱን ያገኙ አስተያየት ሰጭዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ እንግልትን ያስቀረ፣ ጊዜና ወጭን የቀነሰ ነውና ይስፋፋ፤ ተጠናክሮም ይቀጥል። #መሶብ_የአንድ_ማዕከል_አገልግሎት #የዜጎችን_እንግልትና_ብልሹአሠራርን_መቅረፍ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #በኢዜአ_ዐይን
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 17, 2026 2227
በዮሐንስ ደርበው ከግንቦት 2 እስከ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ጋር መምከራቸው ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር መክረዋል። በዚሁ ወቅትም በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ለነበረን ጠቃሚ የሐሳብ ልውውጥና ቀጣይነት ላለው አጋርነትም ምስጋናዬ የላቀ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ በኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍለዋል። በዚሁ ወቅትም በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት ላይ ከተሞክሯችን የተቀዱ ከፍ ያሉ ሐሳቦች ተነስተዋል ብለዋል። አክለውም፤ ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ሥራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራትና ደስታ ነው ሲሉ ተቀብለዋቸዋል። ከአቀባበሉ በኋላም፤ መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በዚህም መሠረት፤ በታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ብድርን ጨምሮ የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ስምምነት ተፈርሟል። · ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞን ምክንያት በማድረግ፣ "በሰላም አብሮ ለመኖር" በሚል መሪ ቃል ልዩ የመታሰቢያ ቴምብር ስብስብ ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርገዋል። እነዚህ አራት ቴምብሮች እ.ኤ.አ. በ1945 በሳን ፍራንሲስኮ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን ከመፈረም ጀምሮ፤ በኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን እስከማሰማራት እና በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እስከ ማስተናገድ ያለውን የጋራ ታሪካችንን የሚተርኩ ናቸው ብለዋል። በዓለም የፖስታ ኅብረት በኩል ለ192 ሀገራት የተሰራጩት እነዚህ ቴምብሮች፤ ለአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ሁሉ የሚተርፍ የታሪክ ዐሻራ ማሳያ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። በተያያያዘም፤ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለቡድናቸው፣ በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ እጅግ ፈታኝ በሆነ ወቅት ላይ ሰላምን፣ ልማትን እና ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እያሳዩት ላለው ጽኑ አመራር ጥልቅ አድናቆታችንን እንገልጻለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። የተባበሩት መንግሥታት የጸናው ሀገራት ከመከፋፈል ይልቅ ውይይትን ስለመረጡ መሆኑን አስገንዝበው፤ ኢትዮጵያም ይህንኑ የሁልጊዜ ምርጫዋን ታጸናለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም የምክክር ባህል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበው፤ ጠንካራ የሲቪክ ማኅበረሰብ ባህል ግንባታ ደግሞ ያላሰለሰ የመነጋገር ልምምድ እና የሰከነ የወል መደማመጥን ግድ ይላል ብለዋል። የእስካሁን ሂደቱም በማኅበረሰባችን በየደረጃው የመደማመጥን ከፍ ያለ ጠቀሜታ አሳይቷል ሲሉም ገልጸዋል። ሂደቱ በሀገራችን ሁሉም ማዕዘናት የሚገኙ ከ90 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን አመለካከቶች እና የውይይት ውጤቶች ያንፀባረቀ ሆኗልም ነው ያሉት። ለሀገር ወሳኝ ፋይዳ የያዘው የምክክሩ ምዕራፍ ተጨባጭ ውጤት ወደሚያስገኘው ቀጣይ ምዕራፍ በሚሸጋገርበት በዚህ ወቅት፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነት እና ዘላቂ መረጋጋትን የሚያረጋግጥ የጋራ ፅኑ አቋም እና ገንቢ በሆነ መንገድ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። · የገላን ኢንዱስትሪ ፓርክ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አስተማማኝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ተደማሪ እመርታ ነው ብለዋል። ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች ምቹ የንግድ ከባቢ ከመፍጠር ባሻገር በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶቻችን የሥራ ዕድል ይከፍታል ሲሉም ገልፀዋል። ፓርኩ የሀገራችን አምራቾች አቅማቸውን በማጎልበት፣ ምርታማነታቸውን ማሳደግና ተወዳዳሪነታቸውን በመጨመር ለከተማችን፣ ለሀገራችንና ለቀጣናው የሚተርፉበት ታላቅ እድልን ይዟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተኪ ምርቶችን በማምረት በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛና ቀልጣፋ የንግድ ትስስር ይፈጥራል፤ ምርቶችን ደግሞ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል ሲሉ አስረድተዋል። · ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ መጀመር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔን ባስጀመሩበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ቆራጥ ጥረት ውስጥ የሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዋና ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል በማድረግ ሁሉን አቀፍ ሥራ እየተገበረ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በመላ ሀገሪቱ ከ35 ሺህ በላይ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት የነጻና አስገዳጅ ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን እያደረግን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር ላይ መሥራት በመሆኑ ተባብረን፣ በጊዜ የለንም መንፈስና በትጋት እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። · የፖሊሲ ቀን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ ባሳላፍነው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የፖሊሲ ቀን ተከብሯል። በዚሁ ወቅትም፤ ውጤታማ ፖሊሲ ለሀገራዊ ዕድገት የጀርባ አጥንት መሆኑን አስገንዝበው፤ መንግሥት በግልፅ፣ ተተግባሪና ጥራት ባላቸው ፖሊሲዎቹ ለሕዝብ የገባውን ቃል እየተገበረ ስኬትም እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። ሀገራችን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ በጂኦ-ፖለቲካዊና በቴክኖሎጂ ለውጦች ላይ ቀድሞ ምላሽ የሚሰጡ ጥናቶች ያስፈልጋሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት በዕውቀት ላይ ኢንቨስት በማድረግ እና ለማስረጃዎች ዋጋ በመስጠት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነ የፖሊሲ ሥነ-ምኅዳር ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ለዚህ ስኬት ሁላችንም በጋራ እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 7633
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 4567
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 10354
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 8831
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የከተማ ግብርናን ከጤና ሙያው ጋር ያጣመረው ወጣት
May 14, 2026 2293
በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) የሰው ልጅ የሕይወት ኡደት በጊዜ የታጠረ ነው። የሰውነት ሚዛን ተለክቶ ውብ ሆኖ የሚገኘው ደግሞ በዚህ የጊዜ ምጣኔ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ሰርቶ ተገቢው ቦታ ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ጠንካራ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ስኬት ላይ ይደርሳሉ። ለጊዜ ብዙም ትርጉምና ዋጋ የማይሰጡ ሰዎች ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ስለማይገደብና በዚያው ልክ ተሯሩጠው ስለማይሰሩ ስኬታማ ሳይሆኑ ዘመናቸውን በችግር ያሳልፋሉ። ሰው ሲፈጠር ይህን በማመዛዘን የተሻለውን መንገድ ይጠቀም ዘንድ ደግሞ አዕምሮ ተሰጥቶታል። ማንም ሰው በኑሮ ከመመራት ይልቅ ራሱ ኑሮን መምራት የሚችለው ጠንክሮ ሲሰራ ነው። የአንድ ጠንካራ የሥራ ሰው አንዱ መለኪያ ደግሞ የጊዜ አጠቃቀሙ ነው። ጊዜውን በማብቃቃት ካለው ሥራ ተጨማሪ ሥራ ፈጥሮ የሚሰራና ለበለጠ የሚተጋ ስኬታማ ሕይወትን መምራት ይችላል። በሚዛን አማን ከተማ ኢዜአ ያነጋገርው ወጣት ይህን በተግባር በማረጋገጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው። ወጣት ዳዊት ባይቴንስ ይባላል። ከተሰማራበት የጤና ዘርፍ ጎን ለጎን ባለው ትርፍ ጊዜ በከተማ ግብርና ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ይገኛል። ሰርቶ ለመለወጥ ካላው ፍላጎትና ቁርጠኝነት የተነሳ በሕይወቱ ምንም አይነት ጊዜ እንዲባክንበት አይፈልግም። እያንዳንዷን ሰዓትና ደቂቃ ትርጉም ባለው መልኩ ለሥራ ያውላል። ይህ የመነጨው ደግሞ ከሥራ ወዳድነቱ ነው። ሲሰራ ውሎ ሲሰራ ቢያድር ደከመኝና ሰለቸኝን አያውቅም። ለእዚህ ባህሪው እርሾ የሆነው ደግሞ በልጅነቱ ወላጆቹን በግብርና ሥራ እያገዘ ማደጉ ነው። በትምህርቱም ወደ ኋላ ሳይል ጠንክሮ በመማር ስኬታማነቱን አስመስክሯል። የኮሌጅ ትምህርቱን በፋርማሲ የተመረቀው ወጣቱ በአሁን ወቅት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በጤና ባለሙያነት እየሠራ ይገኛል። የጤና ተቋም ሥራው ቀንና ማታ በፈረቃ የሚሰራ በመሆኑ ከሆስፒታል ሥራው ውጪ ሲሆን ከተማ ወጥቶ በመዝናናት አሊያም በዋዛ ፈዛዛ የሚያሳልፈው ጊዜ የለውም። ከጤና ሥራው ጎን ለጎን በቤቱ ዙሪያ ያለውን ባዶ መሬት እያለማ ይገኛል። የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ይህን የግብርና ልማት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የግብርና ሥራውን የጀመረው በጤና ሙያ ሥራው በወር ከሚያገኘው ደመወዝ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አስቦ ነው። "የግብርና ምርቱ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ባውለው እንኳ ወጪዬን ይቀንሳል" የሚለውም ሌላው መነሻ ምክንያቱ ነበረ። በዚህም ባለው ጠባብ መሬት ላይ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና መሰል የጓሮ አትክልቶችን አልምቶ በመጠቀም "ምግቤን ከጓሮዬ" የሚለውንም ንቅናቄ በተግባር አሳይቷል። በጓሮ ያለማቸውን ምርቶች ለቤተሰብ ፍጆታ ማዋሉም ከወጪ እንደታደገው ነው የገለጸው። የአካባቢው መሬት ያለስስት ከሚያበቅላቸው ፍራፍሬዎች መካከል ሙዝ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ወጣት ዳዊትም በጓሮ አትክልት የጀመረውን ሥራ በማስፋት በቤቱ ዙሪያ የሙዝ ልማት ስራውን አጠናክሯል። የሙዝ ምርቱም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያም እያቀረበ ነው። ዛፉም ጥላ ሆኖ እያገለገለው ነው። ሁሌም ለተጨማሪ ሥራ የሚተጋው ይህ ባለ ራዕይው ወጣት ምርጥ የቡና ዘር ከግብርና ባለሙያዎች በመውሰድ ችግኝ አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች ያሰራጫል። አምና የቡና ችግኝ ተከላ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በጓሮው አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆኗል። ከጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባሻገር በቆሎ በማልማትም ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ነው። ወጣት ዳዊት ባለው ጠባብ የከተማ ማሳ ላይ እነዚህን ልማቶች እያከናወነ ያለው በአንድ ጊዜ አይደለም። እንደ የአዝመራው ተስማሚነት አፈራርቆ የማልማት ጥበብንም ተክኗል። በቆሎ ደርሶ የተነሳበት ማሳ ላይ ሌሎች አትክልቶችን ያለማል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር የእርሻ ሥርዓትን በመከተል በሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች ስር ባለ ክፍት ቦታ ላይ ቡና ያለማል፤ የአትክልት ችግኞችንም ያዘጋጃል። ይህ ብልህነት የተሞላው የከተማ ግብርና ልማት ሥራው የከተማ ቤቱን የገጠር ሞዴል አርሶ አደር ማሳ አስመስሎታል። ወደፊት የተቀናጀ የግብርና ልማት ጣቢያን የመፍጠር ዓላማ እንዳለው የገለጸው ወጣቱ፣ በቅርቡም በንብ ማነብ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገረው። ለዚህም የቀፎ ግዥና የቀፎ ማስቀመጫ ቦታ ዝግጅት ሥራ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በገበያ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት መቋቋም የሚቻለው ሰርቶ ውጤታማ ሲኮንና ገቢን ማሳደግ ሲቻል ነው የሚል እምነት አለው። ወጣቱ እንደሚለው ምርት የሚያመርት ሰው እየበዛ ሲመጣ ገበያው ይረጋጋል። በመሆኑም ሰዎች ሁሉንም ነገር ከገበያ ከመግዛት ይልቅ ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የተወሰነ ምርት በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ጎን ለጎን የተሰማራበት የከተማ ግብርና ልማት ሥራ ወጪውን ከመቆጠብ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እያስገኘለት በመሆኑ በቀጣይም ልማቱን ለማጠናከር ሞራል እንደሆነው ተናግሯል። እሱ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው በርካታ ወጣቶች የቤተሰቦቻቸውን ማሳ ትተው በከተማ ያለ ሥራ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የወጣትነት ጊዜን ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ይላል። ወጣቶችም ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ በመጠቀም ሀብት ማፍራት የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ይመክራል። በተለይ የእርሻ መሬት ያላቸው ወጣቶች በግብርና ሥራ ራሳቸውን መለወጥ፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ ገበያ ማረጋጋትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ማሳረፍ እንዳለባቸው ነው የገለጸው። የሚዛን አማን ከተማ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ የወጣት ዳዊት ታታሪነት ለብዙዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ነው የገለጹት። በተለይ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን መሠረት በማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት በትንሽ መሬት መስራት ከተቻለ ገበያን ማረጋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጽህፈት ቤቱ ወጣቱንና የእሱን ፈለግ ተከትለው የሚሠሩ ወጣቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅትም በሌማት ትሩፋት የሥራ ዘርፎች ወጣቶች በብዛት እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በራስ ተነሳሽነት ያላቸውን ጊዜ አብቃቅተው ወደልማት የገቡ እንደ ወጣት ዳዊት ያሉ ወጣቶች ቢበራከቱ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚናም የጎላ ነው። ማንም ሰው ኑሮን አሸንፎ ወጤታማ ለመሆን እንደ ወጣት ዳዊት በሥራ መትጋት ይኖርበታል። ወቅቱ ያለን ጊዜ አብቃቅቶ ተጨማሪ ሥራዎች መስራት የግድ የሚልበት ወቅት ነው። ለብዙዎች በቅጥር ሰርቶ በሚገኝ ገቢ ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለእዚህም እንደወጣት ዳዊት በዙሪያችን ምን ሀብት አለ በሚል ለይቶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ጊዜን ከጉልበት ጋር አጣምሮ መጠቀምም እንዲሁ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሕጻንነትና በእርጅናው ዕድሜ የፈለገውን ማድረግ፣ ወጥቶና ወርዶ ሀብት ማፍራት አይችልም። ይህ የሚሆነው በወጣትነትና በጎልማሳነት ዕድሜ ብቻ ነው። በመሆኑም ለነገ ያለምነውን በጊዜው ማሳካት የምንችለው ዛሬ ጠንክረን ስንሰራ ነው። ስለዚህ የወጣትነት ዕድሜያችንን በውጤት ለማጀብ ጠንክረን ልንሠራበት ይገባል። ሥራ ክቡር ከመሆን በላይ ጠንክሮ የሰራውንም ያስከብራል፤ ይለውጣል፤ ሰላም !
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 2640
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው። በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል። የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል። ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።