በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወሳኝ ድል አሳክቷል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወሳኝ ድል አሳክቷል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸገር ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ረድኤት አስረሳኸኝ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር እፀገነት ግርማ ቀሪዋን ጎል ለንግድ ባንክ ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ሰናይት ኡራጎ እና ገነሜ ወርቁ ለሸገር ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በውድድር ዓመቱ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ35 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
የወቅቱ የሊጉ ዋንጫ አሸናፊ ንግድ ባንክ ከሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ አድርጓል።
በአንጻሩ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሸገር ከተማ በ27 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ በተደረገ ሌላኛው መርሐ-ግብር ሃዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ 14ኛ ሳምንት ተጠናቋል። የ15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከየካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።