ቀጥታ፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት ያጠናቀቁበት የጓድላሃራ ግማሽ ማራቶን 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 16 /2018 (ኢዜአ)፡- በሜክሲኮ የጓድላሃራ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል። 

በወንዶች አትሌት ገመቹ ዲዳ 1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ38 ሴኮንድ አሸንፏል። 

በሴቶች ውድድር አትሌት ኮሎሌ መካሹ 1 ሰዓት ከ12 ደቂቃ ከ49 ሴኮንድ አሸንፋለች።

ደራርቱ ኃይሉ 1 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ06 ሴኬንድ ስምንተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም