አርእስተ ዜና
የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል በተጀመረው ንቅናቄ የሚዲያና ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
May 8, 2024 17
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016 (ኢዜአ)፡- የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል በተጀመረው ንቅናቄ የሚዲያና ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ጠየቀ። በአዲስ አበባ ከሚያዝያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ”ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ሃሳብ የንቅናቄ መርሃ-ግብር መጀመሩ ይታወሳል። የመርሃ-ግብሩ መሳካት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎችና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች አስተዋጽኦ በሚያደርጉበት ጉዳይ ላይ ባለሥልጣኑ ውይይት አድርጓል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ፤ የአካባቢ ብክለት በሰዎች ጤና እና አኗኗር ላይ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና ጉዳቱን ለመቀነስ የግንዛቤ መፍጠር ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ የሚዲያና ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። የአካባቢ ብክለትን መከላከል ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ባለመሆኑ አጠቃላይ ነዋሪው፣ ግለሰቦችና ተቋማት አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። ለዚህም የሚዲያና ኪነ-ጥበብ ሰዎች የግንዛቤ መፍጠርና የጉዳቱን ልክ በማሳየት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሁነኛ አጋዥ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።   በባለሥልጣኑ የአካባቢ ሕግ ተከባሪነት ዳይሬክተር ለሜሳ ጉደታ፤ የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በተቋሙ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በ13 ሺህ ተቋማት ላይ ቁጥጥር ተደርጎ 2 ሺህ የሚሆኑት የብክለት መንስኤ በመሆናቸው እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን አስታውሰዋል። የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የተደረጉ ጥረቶች መኖራቸውንም አንስተዋል።   ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አርቲስት ሙሉነህ ዘለቀ እና አርቲስት ዮሐንስ አፈወርቅ በንፁህ አካባቢ መኖርና ከብክለት ነፃ የሆነ ከተማ መፍጠር የጋራ ጥቅማችን በመሆኑ በሚቻለው ሁሉ ንቅናቄውን ለማገዝ ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል።    
የኢትዮጵያንና የአሜሪካን የ120 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጉዞ የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን ተከፈተ
May 8, 2024 31
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያንና የአሜሪካን የ120 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጉዞ የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን በብሔራዊ ሙዚየም ተከፍቷል። "የ120 አመታት የሁለትዮሽ ግንኙነት ምስላዊ ጉዞ" በሚል መሪ ሃሳብ በተከፈተው በዚሁ የፎቶ ኤግዚብሽን፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር አርቪን ጆሴ ማሲንጋ፤ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር አርቪን ጆሴ ማሲንጋ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያና አሜሪካ 120 ዓመታትን የዘለቀ ጠንካራ ወዳጅነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ በዛሬ እለት ለእይታ የበቃው የፎቶ ኤግዚቢሽን በሁለቱ ሀገራት መካከል ዘርፈ ብዙ ወዳጅነት መኖሩንና የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በየጊዜው እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል በጤና፣ ትምህርት፣ ግብርና፣ ዘላቂ ልማትና በሌሎች የትብብር መስኮች ያለውን ጠንካራ ትስስር የሚያመላክት መሆኑንም እንዲሁ፡፡   የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና ማህበራዊ ዘርፍ ጠንካራ መሰረት ያለው ወዳጅነት መኖሩን ጠቅሰው፤ ግንኙነቱ በባህልና ህዝብ ለህዝብ ትስስር ጭምር እያደገ የመጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዛሬው እለትም ለእይታ የበቃው ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያና በአሜሪካን መካከል ለረዥም ዓመታት የዘለቀውን ወዳጅነት የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በብሔራዊ ሙዚየም የተከፈተው የፎቶ ኤግዚቢሸን እስከ ግንቦት 18 ቀን 20 16 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ ኤግዚቢሽኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ተቋም ከግንቦት 21 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡      
በወለጋና አካባቢው ሰላምን ለማጽናትና ልማትን ለማፋጠን ከመንግስት ጎን በመቆም የበኩላችንን እንወጣለን -- የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች
May 8, 2024 21
ነቀምቴ ፤ሚያዝያ 30/2016 (ኢዜአ)- በወለጋና አካባቢው ሰላምን ለማጽናትና ልማትን ለማፋጠን ከመንግስት ጎን በመቆም የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ከሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎችና ከፌዴራልና ከኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተገኙበት ነቀምቴ ከተማ የለውጡን መንግስት ለመደገፍ ያለመ ሰልፍ ተካሄዷል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከምስራቅ ወለጋ፣ ከምዕራብ ወለጋ፣ ከቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የተውጣጡ ነዋሪዎች ከለውጡ መንግስት ጎን መሆናቸውን በተለያዩ መፈክሮች አረጋግጠዋል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከተገኙ ነዋሪዎች መካከል አቶ ሞሲሳ ፈይሳ፣ በወለጋና አካባቢው ያለው ሰላም ዘላቂ እንዲሆን ከለውጡ መንግስት ጎን መሆናቸውን ለማረጋገጥ ስልፍ መውጣታቸውን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋፍ ሰልፉ ላይ መገኘታቸውም ተስፋ እንደሰጣቸውና የተገኘውን ሰላም በማጽናት ለልማቱ መነሳሳት የፈጠረላቸው መሆኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወለጋ ህዝብ ልማት እና ሰላም ፈላጊ መሆኑን በመረዳት በአካባቢው የተሻለ ልማት እንዲሚሰራ በመጥቀሳቸውም መደሰታቸውን የገለጹት አቶ ሞሲሳ፤የአካባቢው ልማት እንዲፋጠን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። ሌላው ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በድጋፍ ሰልፉ ላይ ለመገኘት መምጣታቸውን ያነሱት ሃደ ሲንቄ ደጊቱ ተስፋ ዛሬ ከመቼውም በላይ ደስተኛ መሆናቸውን አንስተዋል።   የወለጋ ህዝብ አቃፊና ሁሉን ወዳጅ መሆኑን የሚናገሩት ሃደ ሲቄ ደጊቱ፤ "መሬቱም ምርታማ በመሆኑ ከዚህ በኋላ ወደ ልማት መዞር ይገባናል" ብለዋል። ከለውጡ በኋላ በሌሎች አካባቢዎች የተገኘው ሰላምና ልማት በወለጋ አካባቢም ዘላቂ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። ወጣቶችም ከፀጥታ አካል ጋር በመሆን የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ "ወላጆችም ልጆቻችንን መምከር አለብን" ብለዋል። ''የጠቅላይ ሚኒስትራችን ጉብኝትና ያደረጉት ንግግርም በሰላም ተረጋግተን እንደምንኖር ተስፋ የሚሰጠን ነው'' ሲሉም ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወለጋና አካባቢው እየታዩ ያሉ ለውጦች ለፀጥታው መስፈን ማሳያ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላዋ ተሳታፊ ወይዘሮ ከዲጃ አብዱልቃድር ናቸው። በቀጣይም የአካባቢውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግና ልማትን ለማፋጠን ከመንግሥት ጎን በመቆም የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። ከምዕራብ ወለጋ ዞን ሰልፉ ላይ የተገኙት አቶ ናስር ሐሺን በበኩላቸው፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋፍ ሰልፉ ላይ መገኘት ትልቅ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። በቀጣይም ከአካባቢያቸው ህዝብ ጋር በመተባበር ዘላቂ ሰላም እንዲኖርና ልማት እንዲፋጠን የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ አንስተዋል። ሰልፉ ላይ ''ለውጡን እናጸናለን''፣ ''በሰላምም፣ በልማትም ምሳሌ ሆነን እናኮራዎታለን''፣ ''ሁሉንም አይነት ጽንፈኝነት እናወግዛለን'' የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች ተደምጠዋል።  
በድሬዳዋ የደም ልገሳው መርሃ ግብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪ ቀረበ
May 8, 2024 22
ድሬዳዋ ፤ሚያዝያ 30/2016 (ኢዜአ)፡- በበጎ ፍቃደኝነት ደም መለገስ የሰውን ህይወት መታደግ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ጥሪ አቀረበ። በድሬደዋ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀንን ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄዷል። ደም የለገሱት የማህበሩ በጎ ፍቃደኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸውም ታውቋል። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ በሐር አደም በአደጋዎችና የተለያዩ ችግሮች ሳብያ የደም ፈላጊ ህሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን አንስተው የእነዚህን ወገኖች ህይወት ለመታደግ በበጎ ፍቃደኝነት የሚደረገው የደም ልገሳ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።   ቀኑን አስመልክቶ ደም የለገሰው ወጣት አና አህመድ እንደተናገረው፤ ደም በመለገስ የሰው ህይወት ማዳን የመሰለ የህሊና ደስታ የሚሰጥ ነገር የለም ብሏል። እኔ በለገስኩት ደም አንዲት ወላድ እናት ህይወቷን መታደግ መቻል የሚሰጠው መንፈሳዊ ደስታ ታላቅ በመሆኑ ሁሉም በዚህ ተግባር መሳተፍ እንዳለበት ተናግረዋል። ቀኑን ምክንያት በማድረግና በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር ከተማዋን የማፅዳት፣ ችግኝ የመትከል እንዲሁም የጎዳና ተዳዳሪዎችን የመመገብ ተግባራትም ተከናውነዋል። እነዚሁ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት እስከሚቀጥለው እሁድ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ታውቋል። በእለቱ በተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብር 50 ዩኒት ደም መሰብሰቡ ተገልጿል።  
የፓስፖርት፣ ዲጂታል መታወቂያና የኤ ቲ ኤም ካርድ ማምረቻ ፋብሪካው መገንባት ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለምታደርገው ጉዞ አቅም የሚፈጥር  ነው - አቶ አህመድ ሽዴ
May 8, 2024 30
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- የፓስፖርት፣ ዲጂታል መታወቂያና የኤ ቲ ኤም ካርድ ማምረቻ ፋብሪካ መገንባት ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለምታደርገው ጉዞ አቅም የሚፈጥር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ። በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የፓስፖርት፣ የዲጂታል መታወቂያ፣ የኤ ቲ ኤም ካርድና መሰል የደኅንነት ሕትመቶች ማምረቻ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃያት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብዱራህማን ኢድ ተገኝተዋል። በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ፣ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፣ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ እና የቶፓን ግራቪቲ ኩባንያ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፋብሪካው መገንባት ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለምታደርገው ጉዞ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል። በእውቀት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር በኩልም ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል። የፋብሪካው መገንባት የሕትመት ዘርፉን ከማሳደግ እና ከማዘመን በተጨማሪ በምስራቅ አፍሪካ በዘርፉ መሪ ለመሆን በር ከፋች መሆኑንም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በበኩላቸው፤ ቶፓን ግራቪቲ 120 ዓመት ያስቆጠረ አንጋፋ የሕትመት ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል። በ137 ሀገራትም በምስጢራዊ ሕትመት ዘርፍ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ዛሬ መሠረቱ የተቀመጠው በአፍሪካ የመጀመሪያ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያና ጃፓን በተለያዩ መስኮች ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፤ ይህ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
የሚታይ
የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን እውን ለማድረግ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ መጠናከር አለበት
May 8, 2024 50
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠንና የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን እውን ለማድረግ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ መጠናከር እንዳለበት የምጣኔ ሀብት ባለሙያና የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርሃተስፋ (ዶ/ር )ገለጹ። በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂን እውን ለማድረግ በመንግስት የተሰጠውን ትኩረት ተከትሎ ''ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025'' ስትራቴጂ ወጥቶ እየተተገበረ ይገኛል። ስትራቴጂው ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርምና የ10 አመት መሪ የልማት እቅድ ስትራቴጂዎች እንዲሁም ከአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ጋር ተሳስሮ የሚተገበር ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያና የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርሃተስፋ (ዶ/ር)ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ዓለም በፍጥነት እየሄደበት የሚገኝ ወሳኝ ጉዳይ ነው። በሀገሪቷ ያሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግና ቴክኖሎጂውን ለማስረጽ ድርሻቸውን ወስደው መንግስትና የግሉን ዘርፍ ማገዝ ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። ዲጂታላይዜሽንን ለማስረጽ በቴሌኮም ዘርፉ እየተወሰደ ያለው እርምጃ የሚበረታታ ሲሆን በአሁኑ ወቅት እስከ 5G ኔትዎርክ መዘርጋቱ ለዚሁ አካሄድ አመቺ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በመጪው ጊዜያት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ስለሚኖራት ቴክኖሎጂውን እውን ለማድረግ ሰፊ እድል እንዳላት ተናግረዋል፡፡ በፋይናንስ ፖሊሲ እየታዩ ያሉ አበረታች ለውጦች ፣ የካፒታል ገበያ መቋቋሙ ፣የውጭ ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች መጠናከር ወጣቶች በፈጠራ የታገዘ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ እንዲሳተፉ ያስችላቸዋል ነው ያሉት። ስትራቴጂው በመንግስትና በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ብቻ ሊተገበር ስለማይችል የዩኒቨርሲቲዎች ተሳትፎ መጠናከር አለበት ነው ያሉት። ዲጂታል ኢትዮጵያ የመንግስት፣ የግሉን ዘርፍና የልማት ኤጀንሲዎችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ የሀገሪቷን የዲጂታል ጉዞ ከአህጉሪቱ ስትራቴጂ ጋር በማስተሳሰር ለማሳለጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አንስተዋል። ኢትዮጵያም በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ በመታገዝ ስትራቴጂውን እውን ለማድረግ ጥረት እያደረገች መሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል። በፖሊሲ አቅጣጫ የሚተገበረው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ በመንግስት አሰራር ላይ ኢ-ገቨርንመንት አስተዳደርን ለመተግበር ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል። ስትራቴጂው የኢ-ኮሜርስ ንግድን በዲጂታል ለማስኬድ፣ የምርምር ስራዎችንና አጠቃላይ የትምህርት ዘርፉን በዲጂታል ለማሳለጥ የሚያስችል እንደሚሆን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን እውን ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር የወጣቱን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።      
ኢትዮጵያ የሱዳንን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት መደገፏን አጠናክራ ትቀጥላለች 
May 8, 2024 60
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የሱዳንን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ረገድ እስካሁን የተጫወተችውን ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የሱዳን ሪፐብሊክ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሁሴን አዋድ አሊ መሃመድን በዛሬው እለት ተቀብለው አነጋግረዋል። ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ እና በሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ምስጋኑ በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያ የሱዳንን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ረገድ እስካሁን የተጫወተችውን ሚና አውስተው አበርክቶዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። አክለውም ኢትዮጵያ፣ የሱዳን ሁሉን አቀፍ የሰላም ሂደት በሱዳናውያን ባለቤትነትና መሪነት መከናወን አለበት የሚል ፅኑ እምነት እንዳላትም ገልጸዋል። የሱዳን ሪፐብሊክ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር መሀመድ ሁሴን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በሱዳን ሁለንተናዊ የሰላም ማስፈን ሂደት ውስጥ እየተጫወተችው ያለውን ሚና በማድነቅ በሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ እና ወንድማማቻዊ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ወሳኝ ሚናዋን አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል። አምባሳደር ሁሴን በቅርቡ የሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ኢትዮጵያን የመጀመሪያ የጉብኝታቸው መዳረሻ ማድርጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።  
የነዳጅ ዲፖ ግንባታንና የማጓጓዣ አማራጭን በማስፋት ፈጣን የነዳጅ አቅርቦት ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ ነው
May 8, 2024 95
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- የነዳጅ ዲፖ ግንባታንና የማጓጓዣ አማራጭን በማስፋት ፈጣን የነዳጅ አቅርቦት ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ገለጸ። አልፎ አልፎ በአቅርቦት ላይ የሚታየው መስተጓጎል በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የሚጠቀሙት የነዳጅ ፍላጎት በመጨመሩ ሳቢያ መሆኑም ተገልጿል። የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳህረላ አብዱላሂ፤ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የተጀመረው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ማሻሻያ የመንግሥትን የዕዳ ጫና በመቀነስ፣ የኅብረተሰብን ተጠቃሚነትና የነዳጅ ኮንትሮባንድን በመቀነስ ወሳኝ ሚና መጫወቱን ገልፀዋል። በዚህም 190 ቢሊየን ብር የነበረውን የመንግሥት የዕዳ ክምችት ወደ 100 ቢሊየን ብር ማውረድ መቻሉን ተናግረዋል። በሁለት ዓመት ውስጥ የሕዝብ አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች 29 ቢሊየን ብር ድጎማ ተደርጓልም ነው ያሉት። መንግሥት የነዳጅ ድጎማን ቀስ በቀስ ለማስቀረት ባስቀመጠው አቅጣጫ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አሠራርን የጣሱ ተሽከርካሪዎች ከስምሪት እንዲወጡ ማድረጉን ተናግረዋል። የማሻሻያ ሥርዓቱ ከእንከን የፀዳ ነው ባይባልም፤ የነዳጅ ዋጋን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን መደረጉ ኮንትሮባንድን በእጥፍ በመቀነስ እመርታዊ ለውጥ ማምጣት እንደተቻለ አብራርተዋል። የፖሊሲ ማሻሻያው ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ 1ሺህ 500 የሚሆኑት የነዳጅ ማደያዎች የሥርጭት አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል ብለዋል። የማጓጓዣና ተያያዥ ወጪዎችን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በዓለም የነዳጅ ገበያ ዋጋ የነዳጅ ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠች እንደምትገኝ ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ዓለም አቀፍ የነዳጅ ማደያ ደረጃ ተዘጋጅቶ እየተሰራበት እንደሚገኝም ገልፀዋል። በአዲስ አበባ 60 በመቶ የነበረውን የነዳጅ ስርጭት ወደ 45 በመቶ በክልሎች ደግሞ ከ40 በመቶ ወደ 55 በመቶ በማመጣጠን ፍትሃዊ የነዳጅ አቅርቦትና ሥርጭት መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል። የዲጂታል ነዳጅ አስተዳደር ከወደብ እስከ ማደያ ያለውን የስርጭት ሂደት በቀላሉ ቁጥጥር የሚደረግበትን ትልቅ አቅም እንደፈጠረ አንስተዋል። 98 ከመቶ በሚሆኑት ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ላይ ዘመናዊ አሠራር በመዘርጋት የነዳጅ አቅርቦትና ሥርጭት ሥራን በቀላሉ መቆጣጠር እየተቻለ ነው ብለዋል። የተቀመጠውን የነዳጅ ሥርጭት አሠራር በመተላለፍ ያልተገባ አካሄድ በሚከተሉ ማደያዎች ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በቀጣይም የገንዘብና የእሥራት ቅጣትን ጨምሮ ጠንካራ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል አዋጅ ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትም አስተማማኝ የነዳጅ አቅርቦትና ሥርጭት እንዲኖር ለማስቻል አዋሽ፣ ጅቡቲና ድሬዳዋ ላይ ትልልቅ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዲፖ እየገነባ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ከተሸከርካሪ በተጨማሪ በባቡር ትራንስፖርት በማጓጓዝ የነዳጅ አቅርቦትና ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል። የነዳጅ ማጓጓዝ ስራ በሚካሄድባቸውና የጸጥታ ችግር አለባቸው በሚባሉ አካባቢዎች ጭምር ያለአንዳች መስተጓጎል ሥርጭት እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በመደበኛ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ ችግር እንደሌለ ጠቁመው፤ አልፎ አልፎ የሚከሰተው መስተጓጎልም የልማት ፕሮጀክቶች ከሚጠቀሙት የነዳጅ ፍላጎት የሚመነጭ መሆኑን አስገንዝበዋል። በጸጥታ ችግር ምክንያት የተስተጓጎለ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪም ሆነ ማደያ እንደሌለ ጠቁመው፤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች የነዳጅ ስርጭት ስራ በልዩ ትኩረት መከናወኑን አስታውቀዋል። በተለያዩ አካባቢዎች በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ከፍተኛ የነዳጅ ፍላጎት መኖሩን ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። ከመደበኛው የነዳጅ ስርጭት በተጨማሪም ለሚከናወኑ ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶች የሚውል የነዳጅ አቅርቦት እየተደረገ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት ፈተናዎችን በመቋቋም ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የልማት ስራዎች እውን ሆነዋል- አቶ ሽመልስ አብዲሳ 
May 8, 2024 56
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡-ባለፉት የለውጥ ዓመታት ፈተናዎችን በመቋቋም ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የልማት ስራዎች እውን መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡ በወለጋ ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን፤ በድጋፍ ሰልፉ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡ በድጋፍ ሰልፉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ስኬቶችን የሚገልጹ መልዕክቶችም ተላልፈዋል፡፡ ከተላለፉ መልዕክቶች መካከል ሰላማችንን በመጠበቅ ድላችንን እናጸናለን፤ በሰላምና በይቅርታ መንገድ ሁሉም አሸናፊ ነው፤ ከብልጽግና ጉዟችን የሚገታን ፈተና አይኖርም፤ እና የአሸባሪው ሸኔ ድብቅ ዓላማ የኦሮሞ ሕዝብን ወደ ባርነት መመለስ ነው፤ የሚሉ ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም ለውጡን ለማጽናት ማንኛውንም መስዋዕትነት እንከፍላለን፤ ወለጋ የሰላምና የብልጽግና ምድር፤ ድላችንን እንጠብቃለን ለቀጣይ ስኬት በጋራ እንሰራለን፤ እና መሪያችን ብልጽግናን በማሳካት ህልምህን እውን እናደርጋለን ፤የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶር) መሪነት በርካታ የልማት ድሎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡ ለአብነትም በስንዴ ልማት ፤ አረንጓዴ አሻራ፣በመሰረተ ልማት ተደራሽነትና በሌሎች የልማት ስራዎች ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ልማትን ለማስቀጠል የተጀመሩ ስራዎች በሁሉም መስክ ተጠናክረው መቀጠላቸውንም ነው ያነሱት፡፡ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ፈተናዎችን በመቋቋሙ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የልማት ስራዎች እውን መሆናቸውንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡፡ በኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ የልማት ኢንሼቲቮች በክልለ ትልቅ ለውጥ እንዲመጣ እያደረጉ መሆኑንም እንዲሁ፡፡ የክልሉ ህዝብ ከመንግስት ጎን በመሆን የተጀመረው ለውጥ እንዲቀጥል እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ አንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት፣ ልማትን ለማደናቀፍ እና ሰላም እንዳይረጋገጠ ለማድረግ የሚሰሩ አካላትን ህዝቡ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ሊታገላቸው እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡ ወለጋ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ የሚኖሩበት አካባቢ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህን አብሮነት በማጠናከር ሁሉም ለሰላም መስፈንና ልማት መረጋገጥ በጋራ እንዲሰራም መልዕክት አስተላለፈዋል፡፡ የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ ምስጋኑ ቱሉ በበኩላቸው ባለፉት የለውጥ ዓመታት የነቀምቴና አካባቢው ማህበረሰብን በተጨባጭ ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡      
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 18240
ኢዜአ
ፖለቲካ
የኢትዮጵያንና የአሜሪካን የ120 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጉዞ የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን ተከፈተ
May 8, 2024 31
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያንና የአሜሪካን የ120 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጉዞ የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን በብሔራዊ ሙዚየም ተከፍቷል። "የ120 አመታት የሁለትዮሽ ግንኙነት ምስላዊ ጉዞ" በሚል መሪ ሃሳብ በተከፈተው በዚሁ የፎቶ ኤግዚብሽን፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር አርቪን ጆሴ ማሲንጋ፤ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር አርቪን ጆሴ ማሲንጋ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያና አሜሪካ 120 ዓመታትን የዘለቀ ጠንካራ ወዳጅነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ በዛሬ እለት ለእይታ የበቃው የፎቶ ኤግዚቢሽን በሁለቱ ሀገራት መካከል ዘርፈ ብዙ ወዳጅነት መኖሩንና የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በየጊዜው እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል በጤና፣ ትምህርት፣ ግብርና፣ ዘላቂ ልማትና በሌሎች የትብብር መስኮች ያለውን ጠንካራ ትስስር የሚያመላክት መሆኑንም እንዲሁ፡፡   የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና ማህበራዊ ዘርፍ ጠንካራ መሰረት ያለው ወዳጅነት መኖሩን ጠቅሰው፤ ግንኙነቱ በባህልና ህዝብ ለህዝብ ትስስር ጭምር እያደገ የመጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዛሬው እለትም ለእይታ የበቃው ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያና በአሜሪካን መካከል ለረዥም ዓመታት የዘለቀውን ወዳጅነት የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በብሔራዊ ሙዚየም የተከፈተው የፎቶ ኤግዚቢሸን እስከ ግንቦት 18 ቀን 20 16 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ ኤግዚቢሽኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ተቋም ከግንቦት 21 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡      
በወለጋና አካባቢው ሰላምን ለማጽናትና ልማትን ለማፋጠን ከመንግስት ጎን በመቆም የበኩላችንን እንወጣለን -- የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች
May 8, 2024 21
ነቀምቴ ፤ሚያዝያ 30/2016 (ኢዜአ)- በወለጋና አካባቢው ሰላምን ለማጽናትና ልማትን ለማፋጠን ከመንግስት ጎን በመቆም የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ከሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎችና ከፌዴራልና ከኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተገኙበት ነቀምቴ ከተማ የለውጡን መንግስት ለመደገፍ ያለመ ሰልፍ ተካሄዷል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከምስራቅ ወለጋ፣ ከምዕራብ ወለጋ፣ ከቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የተውጣጡ ነዋሪዎች ከለውጡ መንግስት ጎን መሆናቸውን በተለያዩ መፈክሮች አረጋግጠዋል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከተገኙ ነዋሪዎች መካከል አቶ ሞሲሳ ፈይሳ፣ በወለጋና አካባቢው ያለው ሰላም ዘላቂ እንዲሆን ከለውጡ መንግስት ጎን መሆናቸውን ለማረጋገጥ ስልፍ መውጣታቸውን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋፍ ሰልፉ ላይ መገኘታቸውም ተስፋ እንደሰጣቸውና የተገኘውን ሰላም በማጽናት ለልማቱ መነሳሳት የፈጠረላቸው መሆኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወለጋ ህዝብ ልማት እና ሰላም ፈላጊ መሆኑን በመረዳት በአካባቢው የተሻለ ልማት እንዲሚሰራ በመጥቀሳቸውም መደሰታቸውን የገለጹት አቶ ሞሲሳ፤የአካባቢው ልማት እንዲፋጠን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። ሌላው ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በድጋፍ ሰልፉ ላይ ለመገኘት መምጣታቸውን ያነሱት ሃደ ሲንቄ ደጊቱ ተስፋ ዛሬ ከመቼውም በላይ ደስተኛ መሆናቸውን አንስተዋል።   የወለጋ ህዝብ አቃፊና ሁሉን ወዳጅ መሆኑን የሚናገሩት ሃደ ሲቄ ደጊቱ፤ "መሬቱም ምርታማ በመሆኑ ከዚህ በኋላ ወደ ልማት መዞር ይገባናል" ብለዋል። ከለውጡ በኋላ በሌሎች አካባቢዎች የተገኘው ሰላምና ልማት በወለጋ አካባቢም ዘላቂ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። ወጣቶችም ከፀጥታ አካል ጋር በመሆን የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ "ወላጆችም ልጆቻችንን መምከር አለብን" ብለዋል። ''የጠቅላይ ሚኒስትራችን ጉብኝትና ያደረጉት ንግግርም በሰላም ተረጋግተን እንደምንኖር ተስፋ የሚሰጠን ነው'' ሲሉም ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወለጋና አካባቢው እየታዩ ያሉ ለውጦች ለፀጥታው መስፈን ማሳያ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላዋ ተሳታፊ ወይዘሮ ከዲጃ አብዱልቃድር ናቸው። በቀጣይም የአካባቢውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግና ልማትን ለማፋጠን ከመንግሥት ጎን በመቆም የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። ከምዕራብ ወለጋ ዞን ሰልፉ ላይ የተገኙት አቶ ናስር ሐሺን በበኩላቸው፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋፍ ሰልፉ ላይ መገኘት ትልቅ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። በቀጣይም ከአካባቢያቸው ህዝብ ጋር በመተባበር ዘላቂ ሰላም እንዲኖርና ልማት እንዲፋጠን የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ አንስተዋል። ሰልፉ ላይ ''ለውጡን እናጸናለን''፣ ''በሰላምም፣ በልማትም ምሳሌ ሆነን እናኮራዎታለን''፣ ''ሁሉንም አይነት ጽንፈኝነት እናወግዛለን'' የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች ተደምጠዋል።  
ኢትዮጵያ የሱዳንን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት መደገፏን አጠናክራ ትቀጥላለች 
May 8, 2024 60
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የሱዳንን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ረገድ እስካሁን የተጫወተችውን ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የሱዳን ሪፐብሊክ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሁሴን አዋድ አሊ መሃመድን በዛሬው እለት ተቀብለው አነጋግረዋል። ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ እና በሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ምስጋኑ በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያ የሱዳንን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ረገድ እስካሁን የተጫወተችውን ሚና አውስተው አበርክቶዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። አክለውም ኢትዮጵያ፣ የሱዳን ሁሉን አቀፍ የሰላም ሂደት በሱዳናውያን ባለቤትነትና መሪነት መከናወን አለበት የሚል ፅኑ እምነት እንዳላትም ገልጸዋል። የሱዳን ሪፐብሊክ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር መሀመድ ሁሴን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በሱዳን ሁለንተናዊ የሰላም ማስፈን ሂደት ውስጥ እየተጫወተችው ያለውን ሚና በማድነቅ በሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ እና ወንድማማቻዊ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ወሳኝ ሚናዋን አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል። አምባሳደር ሁሴን በቅርቡ የሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ኢትዮጵያን የመጀመሪያ የጉብኝታቸው መዳረሻ ማድርጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።  
በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን የልማት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል
May 8, 2024 44
ደሴ ፤ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልልዘላቂ ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ አብዱ ሁሴን አስታወቁ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት የሰላምና የፀጥታ ስራዎችን ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ ገምግሟል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ አብዱ ሁሴን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ በክልሉ የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልሉን ካጋጠመው ችግር ታድጓል፡፡ የፀጥታ መዋቅሩ በቅንጅት ባካሄደው ህግ የማስከበር እንቅስቃሴ በክልሉ ሰላም ማስፈን መቻሉን ተናግረዋል። በዚህም የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ማከናወን ተችሏል ብለዋል ። በክልሉ የተገኘውን ሰላም ከህብረተሰቡ ጋር ዘላቂ ከማድረግ ባሻገር የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አስታውቀዋል ። ህብረተሰቡም የጽንፈኞችን ተንኮልና አገር የማፍረስ ሴራ በመረዳት ከመንግስት ጎን ተሰልፎ ሰላሙን በማስከበርና ለልማት ያለውን ንቁ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡    

ሕዝቡ በሰላም፣ በአንድነትና በልማት ላይ በማተኮር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት አለበት -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
May 8, 2024 83
ነቀምት ፤ ሚያዚያ 30/2016 (ኢዜአ)፡- ሕዝቡ በሰላም፣ በአንድነትና በልማት ላይ በማተኮር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት አለበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። በነቀምቴ ከተማ ወለጋ ስታዲየም የለውጡን መንግስት የሚደግፍ''ወለጋ የሰላምና የብልጽግና ምድር'' በሚል መሪ ሀሳብ ከአራቱ የወለጋ ዞኖች ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰልፍ ተካሂዷል። በስፍራው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶር)፣ ህዝቡ በሰላም፣ በአንድነትና በልማት ላይ እንዲያተኩር ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሕዝቡ ሰላሙን በማጽናት አሁን እጅ ለእጅ በመያያዝ ሀገራችንን ማልማት አለብን ብለዋል። ከሁሉም በላይ ለልማት፣ የተለያየ ሀሳብ ለማመንጨት አንድነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤ ትውልዱን የሚጎዳ ነገር ከማድረግ በመቆጠብ በመመካከር አንድነትን ማጽናት ይገባል ብለዋል። ከኢኮኖሚ አኳያ ከለውጡ በፊት ብዙ ችግር ተደቅኖ እንደነበር ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከለውጡ በኋላ ግን በብዙ ችግሮች ውስጥ ትልቅ የኦኮኖሚ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን አብራርተዋል። በለውጡ ዓመታት በተሰራ ስራ ግብርናንና ከተማን የሚለውጥ፣ ሀገር የሚያሻግር ኢኮኖሚ እየተመዘገበ መሆኑን አስረድተዋል። "የጀመርነውን ስራ ከግብ ለማድረስ የሚያስቆመን ሀይል አይኖረም፣ በንጹህ ልባችን ሀገር ለመለወጥ ነው እየሰራን ያለነው'' ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ''አሁንም እንደ ትናንቱ በሙሉ ልብ እናገራለሁ። የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን፣ አንድነቷም ይጠበቃል፣ በአፍሪካ የምትከበር ሀገር ትሆናለች" ብለዋል። ልማትና እድገታችንን የሚያፋጥን ሰላም እንዲጸና መትጋት እንደሚገባ ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ መግለጽ እፈልጋለሁ ሲሉም ተናግረዋል። ወለጋን መቀየር እንፈልጋለን፣ እቅዳችን በጠላት ዓላማ እንዳይደናቀፍ ህዝባችን ከጎናችን መቆም ይገባዋል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሰልፉ ላይ ''ለውጡን እናጸናለን''፣ ''በሰላምም፣ በልማትም ምሳሌ ሆነን እናኮራዎታለን''፣ ''ሁሉንም አይነት ጽንፈኝነት እናወግዛለን'' የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች ተደምጠዋል።      
ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው 480 ተጠቋሚዎች መመዝገቡን አስታወቀ
May 8, 2024 62
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 30/2016(ኢዜአ)፦ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዕጩ ምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂና ዕንባ ጠባቂዎች ምዝገባ አፈፃፀም ሪፖርትና ዝርዝር የምልመላ መስፈርቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በሂደቱም አድናቆት የሚሰጠው ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ መመዝገቡን የገለጸው ኮሚቴው በሪፖርቱም ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው 480 ተጠቋሚ ዕጩዎችን መመዝገቡንም አስታውቋል፡፡ የዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው ሂደቱ የደረሰበትን ደረጃ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦለት ተወያይቷል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሠ ጫፎ በምዝገባ ሂደቱ በመላ ሀገሪቱ ሕዝቡ ያደረገውን ተሳትፎና ባለሙያዎቹ በእረፍት ቀናት ሳይቀር ለመመዝገብ ያደረጉትን ጥረት አድንቀዋል፡፡ ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው በሚያስቀምጠው አቅጣጫና በምልመላ መሥፈርቱ መሠረት በፍጥነት እንዲከናወን ጠቁመዋል፡፡ በሪፖርቱ እንደተመላከተው ለምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂ 200፣ ለዘርፍ ዕንባ ጠባቂ 85 እና ለሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ዕንባ ጠባቂ 195 በድምሩ 480 ተጠቋሚዎች መቅረባቸውን የኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ዕውነቱ አለነ ገልጸዋል። የምዝገባ ሂደቱ ተጠቋሚ እጩዎችን ለመቀበል በስልክ፣ በኦን ላይን እንዲሁም በጥቆማ ለሚያቀርቡ ጠቋሚዎች የመጠቆሚያ ሳጥኖች በማዘጋጀትና በሚዲያ ሽፋን መሠጠቱን አቶ ዕውነቱ አለነ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት አብራርተዋል። ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው በጥልቀት ተወያይቶ ውድድሩን በውጤታማነት ለማጠቃለል የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ማሳለፉንም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው ተጠቋሚዎችን በመለየትና በጥንቃቄ በማወዳደር የተሻለ ውጤት ያመጡትን ዕጩዎች ለሕዝብ በይፋ እንደሚገልፅ ተመላክቷል፡፡            

ማህበራዊ
በድሬዳዋ የደም ልገሳው መርሃ ግብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪ ቀረበ
May 8, 2024 22
ድሬዳዋ ፤ሚያዝያ 30/2016 (ኢዜአ)፡- በበጎ ፍቃደኝነት ደም መለገስ የሰውን ህይወት መታደግ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ጥሪ አቀረበ። በድሬደዋ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀንን ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄዷል። ደም የለገሱት የማህበሩ በጎ ፍቃደኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸውም ታውቋል። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ በሐር አደም በአደጋዎችና የተለያዩ ችግሮች ሳብያ የደም ፈላጊ ህሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን አንስተው የእነዚህን ወገኖች ህይወት ለመታደግ በበጎ ፍቃደኝነት የሚደረገው የደም ልገሳ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።   ቀኑን አስመልክቶ ደም የለገሰው ወጣት አና አህመድ እንደተናገረው፤ ደም በመለገስ የሰው ህይወት ማዳን የመሰለ የህሊና ደስታ የሚሰጥ ነገር የለም ብሏል። እኔ በለገስኩት ደም አንዲት ወላድ እናት ህይወቷን መታደግ መቻል የሚሰጠው መንፈሳዊ ደስታ ታላቅ በመሆኑ ሁሉም በዚህ ተግባር መሳተፍ እንዳለበት ተናግረዋል። ቀኑን ምክንያት በማድረግና በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር ከተማዋን የማፅዳት፣ ችግኝ የመትከል እንዲሁም የጎዳና ተዳዳሪዎችን የመመገብ ተግባራትም ተከናውነዋል። እነዚሁ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት እስከሚቀጥለው እሁድ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ታውቋል። በእለቱ በተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብር 50 ዩኒት ደም መሰብሰቡ ተገልጿል።  
በአማራ ክልል ህብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህሉን ሊያጠናክር ይገባል-የክልሉ ጤና ቢሮ
May 8, 2024 47
ባህር ዳር፤ሚያዚያ 30/2016 (ኢዜአ)-በአማራ ክልል ህብረተሰቡ በፈቃደኝነት ደም የመለገስ ባህሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ ጤና ቢሮ አስገነዘበ። የቢሮው አመራር አባላትና ሠራተኞች ዛሬ በባህር ዳር ከተማ የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አበበ ተምትሜ በሰጡት አስተያየት፤ “ደም የምንለግሰው በደም እጥረት ምክንያት ለሞት አደጋ የተጋለጡ እናቶች፣ ህፃናትና አዋቂዎችን ለመታደግ ነው" ብለዋል።   ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከበጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች 80 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር ቢገባም ማሳካት የተቻለው የዕቅዱን 50 በመቶ ብቻ መሆኑን ጠቅሰዋል። በደም አቅርቦት እጥረት ምክንያት የቀዶ ህክምና አገልግሎት ቀጠሮ ያላቸው ግለሰቦች የህክምና አገልግሎት በወቅቱ ማግኘት እየቻሉ እንዳልሆነም ተናግረዋል። በመሆኑም የተከሰተውን የደም እጥረት ችግር በመፍታት በሕክምና ተቋማት የተሟላ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ህብረተሰቡ በፈቃደኝነት ደም በመለገስ ህይወትን እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል። "ለራሱ ህይወት ዋጋ የሚሰጥ ሰው ለሌሎችም ደም በመለገስ ዋጋ ይሰጣል’’ ያሉት ደግሞ በቢሮው የልብና የደም ስር በሽታዎች ፕሮግራም ማናጀር ዶክተር ሞላ ሞገስ ናቸው።   ደም የሚለግስ ሰው ለህይወት ትልቅ ዋጋ የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመው፤ ደም በመለገስ በሞት አፋፍ የምትገኝን ነፍስ ከማትረፍ በላይ ለህሊና እርካታ የሚሰጥ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ደም የሰውን ህይወት ለመታደግ ያለውን ጥቅም በመረዳት ለ30 ጊዜ ያህል ደም በመለገስ የወገን አለኝታነታቸውን በተግባር ማረጋገጣቸውንም ዶክተር ሞላ ተናግረዋል።   በቢሮው የህክምናና ተሃድሶ ዳይሬክተር ዶክተር ማረው ጌጡ በበኩላቸው፤ የተለገሰው ደም ለሚፈሳቸው እናቶች፣ የደም እጥረት ላጋጠማቸው ህፃናትና በአደጋ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማትረፍ መሆኑን ገልጸዋል። "በክልሉ በጤና ተቋማት ያለውን የደም እጥረት ለማቃለል እኛ የጤና ባለሙያዎችና የቢሮው ሠራተኞች ደም በመለገስ ህይወትን ለመታደግ እየሰራን ነው'' ብለዋል። በደም አቅርቦት እጥረት ምክንያት የሰው ህይወት እንዳያልፍ ሁሉም ሰው ደም በመለገስ ህይወትን መታደግ እንዳለበት አሳስበዋል። በክልሉ በ2015 በጀት ዓመት ከ93ሺህ በላይ ዩኒት ደም ተሰብስቦ ጥቅም ላይ መዋሉን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።    
በክልሉ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት በተደረገው ጥረት ውጤት ተመዝግቧል
May 8, 2024 41
አዳማ ፤ሚያዝያ 30/2016 (ኢዜአ)፡- በክልሉ ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን የግንዛቤ ክፍተት በመሙላት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት በተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት መመዝገቡን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ገለፀ። ቢሮው የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ ግምገማ እያካሄደ ይገኛል። የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶክተር ቡሻ በለኮ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በክልሉ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን የግንዛቤ ክፍተት በመሙላት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት በተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል። ''ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የደም ምርመራ እንዲያደርጉ፣ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ የህክምና ክትትል እንዲያገኙና የዘርፉን ህክምና ማሻሻል እንዲሁም መድኃኒት የጀመሩ ዜጎች በደማቸው ያለው የቫይረስ መጠን እንዲቀንስ ማስቻል ላይ እየሰራን እንገኛለን'' ብለዋል። በተለይ በትምህርት ቤቶች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በኮሌጆች፣ በሜጋ ፕሮጀክቶች አካባቢዎች እንዲሁም በቡና ቤቶች አካባቢ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በሽታውን በመከላከሉ ረገድ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎን በማሳደግ ረገድ የተሻለ ስራ መሰራቱን አብራርተዋል። ጉዳዩ አሁንም ትኩረትን የሚፈልግ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ቡሻ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ምርመራ በማድረግ 8 ሺህ 76 በሚሆኑት ላይ ቫይረሱ በደማቸው መገኘቱን ጠቁመዋል። አዳዲስ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥርን በመቀነስ ረገድ አምና ከነበረው 0 ነጥብ 4 በመቶ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ወደ 0 ነጥብ 3 በመቶ ማውረድ መቻሉን ገልፀዋል። አሁንም በዋና ዋና መንገድ መተላለፊያ ላይ የሚገኙ ከተሞች የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የሚስተዋልባቸው በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ በትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም አመልክተዋል። ቫይረሱ በደማቸው ከሚገኝባቸው 132 ሺህ 685 ዜጎች ውስጥ መድኃኒት የጀመሩት 129 ሺህ 158 መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ በቢሮው የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋዬ ዘርፉ ናቸው። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ቫይረሱ በደማቸው ከተገኘው ከ8 ሺህ በላይ ዜጎች ውስጥ ከ7ሺህ በላይ የሚሆኑት የመድኃኒት አገልግሎት መጀመራቸውን ጨምረው ገልፀዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የአሰላ ከተማ ጤና ጽሕፈት ቤት የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠሪያ አስተባባሪ አቶ ቆርቾ ሃጂ እንደገለጹት፤ በከተማዋ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየተሰራ ናቸው። በተለይ በማህበረሰቡ ውስጥ መዘናጋት እንዳይፈጠር የማንቃትና የማስተማር ስራ በፋብሪካዎች፣ በቡና ቤቶችና የቀን ሰራተኞችን ጨምሮ ረጅም ርቀት ተጓዥ በሆኑ አሽከርካሪዎች ላይ ግንዛቤን የማስጨበጥ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።        
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው
May 8, 2024 57
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው። የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀሉ ዑመር በሰጡት መግለጫ፤ ራስ ገዝ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር መሆኑን ገልፀዋል። ፕሮግራሙ ከሚቀጥለው ዓመት መስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲውን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ ሙሉ ራስ ገዝ ለማስገባት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው በተለይም የሀገሪቱን ፍላጎት ያማከለ የትምህርት ተቋም ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ የሚያሰኘውን በርካታ ሪፎርም እያከናወነ እንደሆነም አመልክተዋል። በዚህም በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚገቡ ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርኃ ግብር መስጠት ለመጀመር መወሰኑን ነው ያነሱት። ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ሲሆን መርኃ ግብሩ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ እንደሆነም አስታውቀዋል። የፕሮግራሙ መጀመር በስራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዶክተር ጀሉ አያይዘውም የሙያ ብቃት ማረጋገጫው በሁሉም ዘርፎች ላይ እንደሚሰጥ ጠቁመው፣ ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ብለዋል። በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ላይ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም ፕሮፌሽናል ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል። በፕሮግራሙ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን እና የግል ምርምር ተቋማት የሚሳተፉበት እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጪ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ማረጋገጫ ስርዓት ያለው መሆኑን ጠቁመዋል። የብቃት ማረጋገጫው የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለፕሮግራሙ ትግበራም ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ገልፀዋል።
ኢኮኖሚ
የፓስፖርት፣ ዲጂታል መታወቂያና የኤ ቲ ኤም ካርድ ማምረቻ ፋብሪካው መገንባት ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለምታደርገው ጉዞ አቅም የሚፈጥር  ነው - አቶ አህመድ ሽዴ
May 8, 2024 30
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- የፓስፖርት፣ ዲጂታል መታወቂያና የኤ ቲ ኤም ካርድ ማምረቻ ፋብሪካ መገንባት ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለምታደርገው ጉዞ አቅም የሚፈጥር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ። በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የፓስፖርት፣ የዲጂታል መታወቂያ፣ የኤ ቲ ኤም ካርድና መሰል የደኅንነት ሕትመቶች ማምረቻ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃያት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብዱራህማን ኢድ ተገኝተዋል። በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ፣ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፣ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ እና የቶፓን ግራቪቲ ኩባንያ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፋብሪካው መገንባት ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለምታደርገው ጉዞ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል። በእውቀት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር በኩልም ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል። የፋብሪካው መገንባት የሕትመት ዘርፉን ከማሳደግ እና ከማዘመን በተጨማሪ በምስራቅ አፍሪካ በዘርፉ መሪ ለመሆን በር ከፋች መሆኑንም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በበኩላቸው፤ ቶፓን ግራቪቲ 120 ዓመት ያስቆጠረ አንጋፋ የሕትመት ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል። በ137 ሀገራትም በምስጢራዊ ሕትመት ዘርፍ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ዛሬ መሠረቱ የተቀመጠው በአፍሪካ የመጀመሪያ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያና ጃፓን በተለያዩ መስኮች ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፤ ይህ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ ተፈቀደ
May 8, 2024 27
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016 (ኢዜአ)፡-በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ መፈቀዱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት ኢንቨስትመንቱን ሊደግፉ የሚችሉ አስቻይ የሆኑ በርካታ የሕግ ማዕቀፍ ሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል። የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለማበረታታት እና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ የአምራች ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተው ወደ ሥራ መግባታቸውን አስታውሰዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች ምርታቸውን ሙሉ በሙሉ ለውጭ ገበያ እንጂ ለሀገር ውስጥ ማቅረብ ሳይፈቀድላቸው መቆየቱን አብራርተዋል። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ተጽዕኖ ሥር የነበሩ ባለሃብቶችን ለማበረታታት በፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ በአዋጅ መፈቀዱን ገልፀዋል። ይህ የእርምጃ ኩባንያዎች ምርታማነትን ለማሳደግ ብቻ ሳይሆን ለሸማቹ ማኅበረሰብም የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል። በሌላ በኩል በቅርቡ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አዋጅ መውጣቱን አስታውሰው፤ አዋጁ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ ዞን እንዲሸጋገሩ የሚያደርግና በማክሮ ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። ከመሬት ፈቃድና አመራር ጋር የተያያዙ ችግሮችን በዘላቂነት እንደሚቀርፍ እና ለሥራ ዕድል ፈጠራም የራሱ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል። አዋጁ የኢንቨስትመንት ከባቢን የሚፈጥር፣ ከአፈጻጸም ጋር ተያይዞ የሀገር ገጽታን የሚያጎድፉ ድርጊቶችን የሚያስወግድ፣ የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራርና መናበብን የሚያጎለብት እንደሆነ ተናግረዋል። በተለይም ከከተሞች መስፋፋት እና በሊዝ መሬት አቅርቦት ዙሪያም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችንም መፍታት የሚችል የፖሊሲ እርምጃ እንደሆነ ነው ያነሱት። በሌላ በኩል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ለውጭ ኩባንያዎች ዝግ በነበሩ ዘርፎች በችርቻሮም ሆነ በጅምላ ንግድ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያ ለኢንቨስትመንት ዘርፉ ትልቅ ዕድል ነው ብለዋል። የገቢና ወጪ ንግዱ ለውጭ ኩባንያዎች ክፍት መደረጉ በአነስተኛ ባለሃብቶች ተይዞ እና ብዙኃኑ በሚማረርበት የአቅርቦት ገበያና የተጋነነ ዋጋን በማቃለል ረገድ ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ አንስተዋል። ለገበያው በሕግ የሚመራ ሥርዓት መበጀቱ ተወዳዳሪነትን፣ የምርት ጥራት የሚጨምር እና የሸማቹን ማኅበረሰብ ክፍል የሚደግፍ እንደሆነ ገልፀዋል።            
የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን እውን ለማድረግ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ መጠናከር አለበት
May 8, 2024 50
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠንና የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን እውን ለማድረግ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ መጠናከር እንዳለበት የምጣኔ ሀብት ባለሙያና የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርሃተስፋ (ዶ/ር )ገለጹ። በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂን እውን ለማድረግ በመንግስት የተሰጠውን ትኩረት ተከትሎ ''ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025'' ስትራቴጂ ወጥቶ እየተተገበረ ይገኛል። ስትራቴጂው ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርምና የ10 አመት መሪ የልማት እቅድ ስትራቴጂዎች እንዲሁም ከአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ጋር ተሳስሮ የሚተገበር ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያና የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርሃተስፋ (ዶ/ር)ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ዓለም በፍጥነት እየሄደበት የሚገኝ ወሳኝ ጉዳይ ነው። በሀገሪቷ ያሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግና ቴክኖሎጂውን ለማስረጽ ድርሻቸውን ወስደው መንግስትና የግሉን ዘርፍ ማገዝ ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። ዲጂታላይዜሽንን ለማስረጽ በቴሌኮም ዘርፉ እየተወሰደ ያለው እርምጃ የሚበረታታ ሲሆን በአሁኑ ወቅት እስከ 5G ኔትዎርክ መዘርጋቱ ለዚሁ አካሄድ አመቺ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በመጪው ጊዜያት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ስለሚኖራት ቴክኖሎጂውን እውን ለማድረግ ሰፊ እድል እንዳላት ተናግረዋል፡፡ በፋይናንስ ፖሊሲ እየታዩ ያሉ አበረታች ለውጦች ፣ የካፒታል ገበያ መቋቋሙ ፣የውጭ ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች መጠናከር ወጣቶች በፈጠራ የታገዘ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ እንዲሳተፉ ያስችላቸዋል ነው ያሉት። ስትራቴጂው በመንግስትና በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ብቻ ሊተገበር ስለማይችል የዩኒቨርሲቲዎች ተሳትፎ መጠናከር አለበት ነው ያሉት። ዲጂታል ኢትዮጵያ የመንግስት፣ የግሉን ዘርፍና የልማት ኤጀንሲዎችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ የሀገሪቷን የዲጂታል ጉዞ ከአህጉሪቱ ስትራቴጂ ጋር በማስተሳሰር ለማሳለጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አንስተዋል። ኢትዮጵያም በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ በመታገዝ ስትራቴጂውን እውን ለማድረግ ጥረት እያደረገች መሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል። በፖሊሲ አቅጣጫ የሚተገበረው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ በመንግስት አሰራር ላይ ኢ-ገቨርንመንት አስተዳደርን ለመተግበር ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል። ስትራቴጂው የኢ-ኮሜርስ ንግድን በዲጂታል ለማስኬድ፣ የምርምር ስራዎችንና አጠቃላይ የትምህርት ዘርፉን በዲጂታል ለማሳለጥ የሚያስችል እንደሚሆን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን እውን ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር የወጣቱን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።      
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሚኒስቴሩ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ውጤታማነትን ለማጠናከር በትኩረት መስራት እንዳለበት የህዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት አሳሰበ
May 7, 2024 81
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2016(ኢዜአ)፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ የህብረተሰቡን የዲጂታል አጠቃቀምና ግንዛቤ ማሳደግ ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 3ኛ አመት የስራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የ2016 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል። ሚኒስቴሩ ለምክር ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚያስችሉ አምስት የትብብር ስምምነቶችን መፈጸሙን ገልጿል። በዚህም ዘመናዊ የስታርት አፕ ከተማ ለመገንባት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ስምምነት መደረሱን አስታውቋል፡፡ ቀሪዎቹ አራቱ ስምምነቶች የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን ለማሳለጥ በውጭ አገራት ካሉ ድርጅቶች ጋር የተፈፀሙ መሆናቸውን አስረድቷል። የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ለማስፋት በቅድመ ደረጃ ስታርት አፖች ሃሳባቸውን እንዲያበለፅጉ ለ558 ጀማሪ ስታርት አፖች የቢዝነስ ስልጠና እና ሜንቶሪንግ ድጋፍ መደረጉ በሪፖርቱ ተመላክቷል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ችግር ፈቺ ምርምሮችን ለመደገፍ በመንግስት ትኩረት በተሰጣቸው የምርምር ዘርፎች ለሚከናወኑ 24 ምርምሮች የገንዘብና ቴክኒካል ድጋፍ መደረጉም ተገልጿል። በምርምር የተገኙ ስምንት ቴክኖሎጂዎችን ማልማት እንዲሁም ሰባት ቴክኖሎጂዎችን ማላመድ መቻሉና የሳተላይትና ጂኦስፓሻል መረጃዎችን በማደራጀት ስድስት ተቋማትን ተጠቃሚ መደረጉም ተመላክቷል። በዚህ ወቅት የምክር ቤቱ የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ(ዶክተር )ሚኒስቴሩ እቅዱን ከሰራተኞቹና ከክልሎች ጋር የጋራ በማድረግ መስራቱ እንደ ጥንካሬ የሚወሰድ ነው ብለዋል።   የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ችግር ፈቺ ምርምሮችን መስራቱ በጥንካሬ እንደሚወሰድና የስፔስና ጂኦስፓሻል መረጃዎች ለአገራዊ ጥቅም እንዲውሉ የተሰሩ ስራዎችም የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል። በስታርት አፕ ላይ የተጀመሩ ስራዎች የሚበረታቱ ቢሆኑም የስራ እድል በመፍጠር ረገድ አሁንም የሚቀሩ ስራዎች መኖራቸውን አንስተዋል። ሚኒስቴሩ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ከግብ እንዲደርስና ህብረተሰቡ ቴክኖሎጂን አውቆ እንዲጠቀም ለማድረግ የግንዛቤ ስራ ላይ አተኩሮ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል። የአዕምሯዊ ንብረት ለአገር እድገት ወሳኝ በመሆኑ የተጀመሩ ሪፎርሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል። የኢኖቬሽን ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶክተር ) በበኩላቸው የዲጂታል 2025 የመካከለኛ ዘመን ግምገማ መካሄዱንና ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መኖራቸውን ማየት መቻሉን ጠቅሰዋል።   ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ዲጂታል ክህሎት ወሳኝ መሆኑን አንስተው በዲጂታል ክህሎት ልማት ላይ ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ስታርት አፖችን የሚያሰራ የህግ ማዕቀፍና የፋይናንስ ስርዓት እንዳልነበር አንስተው አሁን ላይ በተደረገው ማሻሻያ ምቹ ምህዳር በመፈጠሩ ከስራ እድልና ሀብት ፈጠራ አንፃር የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።          
የግል ባለሃብቶች የተሽከርካሪዎች ቻርጅ ስቴሽን ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ
Apr 30, 2024 401
የግል ባለሃብቶች የተሽከርካሪዎች ቻርጅ ስቴሽን ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2016(ኢዜአ)፡- የግል ባለሃብቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ከማስገባት ባለፈ የቻርጅ ስቴሽን ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጥሪ አቀረበ። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ምትኩ አስማረ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በከተማዋ በቀን ውስጥ ከሚደረገው 3 ነጥብ 4 ሚሊየን የትራንስፖርት ምልልስ ውስጥ 31 በመቶው በብዙኃን ትራንስፖርት የሚሸፈን ነው። የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን መጠቀም አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደ አገር እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለመደገፍ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው።   በተለይም ኢትዮጵያ ነዳጅ ከውጭ ለማስገባት የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንዲቀር በማድረግ ለኢኮኖሚው አበርክቶ ይኖረዋል ነው ያሉት። መንግሥትም ለብዙኃን ትራንስፖርት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል። በከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች አብዛኞቹ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በከተማው ያለው የተሽከርካሪዎች ቻርጅ ስቴሽን በቂ ስላልሆነ ባለሃብቱ በዚህ ላይ ቢሳተፍ እራሱንና አገሩን ይጠቅማል ብለዋል። ቢሮው በዘርፉ ለተሰማራው የግል ትራንስፖርት ሰጪ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የግል ባለሃብቶች በኤሌክትሪክ ቻርጅ ስቴሽኖች ላይ እንዲሰማሩም ጥሪ አቅርበዋል።   መንግሥት 100 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የከተማ አውቶቡሶች ግዥ በመፈፀም በአጭር ጊዜ ለማስገባት ሥራ መጀመሩንም ነው የገለፁት። በተጨማሪም አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የከተማ አውቶቡሶችን በቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። ሕብረተሰቡ አውቶቡሶች በስንት ሰዓት እንደሚደርሱ መረጃ የሚያገኙበት የመረጃ ሥርዓት በመርካቶ ተርሚናል ሥራ መጀመሩንና በሌሎች ለማስፋት እንደሚሰራም ተናግረዋል። የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የሕዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች እየገጣጠመ እንደሚገኝና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የመጀመሪያዎቹ 216 ተሽከርካሪዎች መገጣጠማቸውን የገለፁት ደግሞ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ሰጠኝ እንግዳው ናቸው።   በቬሎሲቲ ኤክስፕረስ ድርጅት አማካኝነት 20 የኤሌክትሪክ ሚኒባሶችና ሁለት ኤሌክትሪክ ከተማ አውቶቡሶች በሙከራ ደረጃ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል። አውቶቡሶቹ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከመሆናቸው ባሻገር ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሆነው መዘጋጀታቸውንም ነው የገለፁት።    
በኢትዮጵያ ስታርት አፖችን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ድጋፍ ይቀጥላል
Apr 30, 2024 215
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ስታርት አፖችን ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ሃንዳክ ጆ ገለጹ። በኢትዮጵያ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በመደገፍና በማበረታታት ስታርት አፖች በስፋት እየተዋወቁ ይገኛሉ። በዘርፉ የተሻለ የፈጠራ ስራ እንዲኖር ምቹ ምህዳር እየተፈጠረ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) የኢትዮጵያ ተወካይ ሃንዳክ ጆ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሁን ላይ የፈጠራና ቴክኖሎጂ ትግበራ ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በኢትዮጵያ በተለይም በቅርብ አመታት በስታርት አፖች ለተሻለ የፈጠራ ስራ ምቹ ምህዳር መኖሩን አድንቀዋል። ኮይካ የ10 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በመያዝ ለስታርት አፖች የተቋማት ኢንኪዩቤሽን ማዕከላት ግንባታ ምቹ ምህዳር ለመፍጠር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በኢትዮጵያ በዘርፉ የሚደረጉ ጥረቶችን በማገዝ ረገድ የኮይካ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ በስታር አፖች እንዲሁም በአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ ዘርፍ በኢትዮጵያ የተጀመሩ ጥረቶች የሚደነቁ ናቸው ብለዋል። በኢትዮጵያ ከለውጡ በፊት 50 ብቻ የነበሩት ስታርት አፖች አሁን ላይ ከ900 በላይ ጀማሪ፣ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ እና ወደ ገበያ የገቡ ስታርት አፖች እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሳይንስ ሙዚየም ተከፍቶ በነበረው አውደ ርዕይ 300 የሚደርሱ ስታርት አፖች ለእይታ ቀርበው የተሻሉ የስራ ሃሳብ የነበራቸው ስታርት አፖች መሸለማቸው ይታወሳል።
በአማራ ክልል ከተሞችን በማዘመን አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል- የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን 
Apr 29, 2024 213
ደሴ ፤ ሚያዚያ 21/2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ከተሞችን በቴክኖሎጂ በማበልጸግና በማዘመን አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በደሴ ከተማ አስተዳደር በአምስቱም ክፍለ ከተሞች የ"ስማር ሲቲ" ፕሮጀክት ዛሬ ተጀምሯል፡፡ የአማራ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የቻለ ይግዛው በማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ እንዳሉት፤ በክልሉ ከተሞችን በማዘመንና አሰራራቸውን በቴክኖሎጅ በማገዝ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተሰራ ነው፡፡ ለዚህም የ"ስማር ሲቲ" ፕሮጀክት ዛሬ በደሴ ከተማ መጀመሩን አብስረዋል። ባህር ዳርን ጨምሮ በክልሉ ስምንት ከተሞችም በቅርቡ እንደሚጀመር አመላክተዋል፡፡ “አሰራሩ ከተለመደ አሰራርና ከወረቀት መረጃ አያያዝ በመውጣት በቴክኖሎጂ ወደ ዲጅታል የሚቀይር እንዲሁም የከተሞችን ደህንነት፣ እድገት፣ መሬት አያያዝ፣ አገልግሎት አሰጣጥና ሌሎችም የሚያሻሻል ነው” ብለዋል፡፡ “ህብረተሰቡና ተቋማት መንግስት የሚጀመረውን አሰራር በመከተልና በመደገፍ የክልሉን ሁለተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል” ሲሉም አክለዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፤ በከተማው ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል፣ የከተማውን ሁለተናዊ እድገት ለማፋጠን፣ አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዛሬ የ"ስማር ሲቲ" አዲስ የቴክኖሎጂ አሰራር መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ አሰራሩ አስፈላጊው ዝግጅትና ግብዓት ተሟልቶ መጀመሩን ጠቁመው፤ ቀደም ብሎ በአንድ ክፍለ ከተማ የተካሄደው ሙከራ ውጤታማ መሆኑን መረጋገጡን አብራርተዋል። በዚህም መሰረት ዛሬ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የ"ስማር ሲቲ" ፕሮጀክት እንዲጀመር መደረጉን ተናግረዋል። “ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት የከተማውን ሁለተናዊ እድገትና የቴክኖሎጂ አሰራር ውጤታማ ለማድረግ የድርሻችንን እንወጣለን” ያሉት ደግሞ የኢትዮ-ቴሌኮም ሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ማስረሻ ገበየሁ ናቸው፡፡ አሰራሩ መሰረተ ልማቶችን ለማፋጠን፣ አሰራሩን ለማዘመንና ለዜጎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ጠቁመው፤ “ በተሻለ በኢንተርኔት ዳታና ቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ሪጅኑ የራሱን ዝግጅት አድርጓል” ብለዋል፡፡ በማስጀመሪያ ስነ ስርአት ላይ የክልልና የከተማ አመራር አባላት፣ የተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
ስፖርት
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ወልቂጤ ከተማን በማሸነፍ ወደ ድል ተመለሰ 
May 5, 2024 107
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ወልቂጤ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል። በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ለመቻል አጥቂው ምንይሉ ወንድሙ በ13ኛው፣ 24ኛው እና 43ኛው ደቂቃ 3 ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል። የአማካይ ተጫዋቹ ጋዲሳ መብራቴ በ75ኛው ደቂቃ ለወልቂጤ ከተማ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል። መቻል ከሶስት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት መመለስ ችሏል። ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው መቻል ነጥቡን ወደ 44 ከፍ በማድረግ ከመሪው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ዝቅ አድርጓል። ወልቂጤ ከተማ በ16 ነጥብ በነበረበት 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የመቻል የፊት አጥቂ ምንይሉ ወንድሙ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ወደ 12 ከፍ በማድረግ ተመሳሳይ የግብ መጠን ካለው የሃዋሳ ከተማው አጥቂ አሊ ሱሌማን ጋር በመስተካከል የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በጋራ መምራት ችሏል። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሃዋሳ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።  
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል
May 5, 2024 106
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 27/2016(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በወጣው መርሐ-ግብር መሠረት መቻል ከወልቂጤ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚሰለጥነው መቻል በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት 5 ተከታታይ ጨዋታዎች 2 ጊዜ ሲያሸንፍ 1 ጊዜ ተሸንፏል። 2 ጊዜ አቻ ወጥቷል። በእነዚህ 5 ጨዋታዎች መቻል 5 ግቦችን ሲያስቆጥር 3 ጎሎችን አስተናግዷል። በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚመራው መቻል በ41 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ወልቂጤ ከተማ ካለፉት 5 የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 1 ጊዜ ብቻ ነው። 2 ጊዜ ሲሸነፍ በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ ነጥብ ተጋርቷል። ወልቂጤ በ5ቱ ጨዋታዎች 2 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 5 ጎሎች ተቆጥረውበታል። በሙሉጌታ ምሕረት የሚሰለጥነው ወልቂጤ ከተማ በ16 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ መቻል 2 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም። በ23ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የአምናው የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካለፉት 5 የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 1 ጊዜ ብቻ ነው። 2 ጊዜ ሲሸነፍ 2 ጊዜ ደግሞ ነጥብ ጥሏል። ፈረሰኞቹ ባለፉት 5 ጨዋታዎች 4 ግቦችን ሲያስቆጥሩ በተመሳሳይ 4 ግቦችን አስተናግደዋል። በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ39 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ተጋጣሚው ሀዋሳ ከተማ ባለፉት 5 የሊጉ ጨዋታዎች 2ቱን ሲያሸንፍ 2 ጊዜ ተሸንፏል። 1 ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በእነዚህ 5 ጨዋታዎች 9 ግቦችን ሲያስቆጥር 8 ጎሎችን አስተናግዷል። ዘርዓይ ሙሉ የሚያሰለጥነው ሀዋሳ ከተማ በ29 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። በተያያዘም ትናንት በተደረጉ የ23ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻ እንዲሁም ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳዕናን በተመሳሳይ 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል በተጀመረው ንቅናቄ የሚዲያና ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
May 8, 2024 17
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016 (ኢዜአ)፡- የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል በተጀመረው ንቅናቄ የሚዲያና ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ጠየቀ። በአዲስ አበባ ከሚያዝያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ”ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ሃሳብ የንቅናቄ መርሃ-ግብር መጀመሩ ይታወሳል። የመርሃ-ግብሩ መሳካት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎችና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች አስተዋጽኦ በሚያደርጉበት ጉዳይ ላይ ባለሥልጣኑ ውይይት አድርጓል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ፤ የአካባቢ ብክለት በሰዎች ጤና እና አኗኗር ላይ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና ጉዳቱን ለመቀነስ የግንዛቤ መፍጠር ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ የሚዲያና ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። የአካባቢ ብክለትን መከላከል ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ባለመሆኑ አጠቃላይ ነዋሪው፣ ግለሰቦችና ተቋማት አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። ለዚህም የሚዲያና ኪነ-ጥበብ ሰዎች የግንዛቤ መፍጠርና የጉዳቱን ልክ በማሳየት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሁነኛ አጋዥ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።   በባለሥልጣኑ የአካባቢ ሕግ ተከባሪነት ዳይሬክተር ለሜሳ ጉደታ፤ የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በተቋሙ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በ13 ሺህ ተቋማት ላይ ቁጥጥር ተደርጎ 2 ሺህ የሚሆኑት የብክለት መንስኤ በመሆናቸው እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን አስታውሰዋል። የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የተደረጉ ጥረቶች መኖራቸውንም አንስተዋል።   ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አርቲስት ሙሉነህ ዘለቀ እና አርቲስት ዮሐንስ አፈወርቅ በንፁህ አካባቢ መኖርና ከብክለት ነፃ የሆነ ከተማ መፍጠር የጋራ ጥቅማችን በመሆኑ በሚቻለው ሁሉ ንቅናቄውን ለማገዝ ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል።    
በሐረሪ ክልል የአካባቢ ብክለትን የሚያስከትሉ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
May 8, 2024 50
ሐረር፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል የአካባቢ ብክለትን የሚያስከትሉ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ አስታወቁ። "ብክለት ይብቃ! ውበት ይንቃ!" በሚል መሪ ሀሳብ በሀረሪ ክልል ለስድስት ወራት የሚተገበር የአካባቢ ብክለትን የመከላከል የንቅናቄ መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።   ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን እንደገለጹት የአካባቢ ብክለት በሰው ልጅ ጤና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ በእንስሳትና እጽዋት ላይ ከፍተኛ ጉዳትያስከትላል። የአካባቢ ብክለት በአየር፣ በውሃ፣ በአፈርና በሌሎችም የተፈጥሮ ሀብቶች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተጠነሰሰው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አመርቂ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተከታታይ አመታት የተተከሉ ችግኞች በአካባቢ ጥበቃ ረገድ ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ የፕላስቲክ ቆሻሻ በሚያደርሰው የአፈር ለምነት መቀነስ፣ ምርትና ምርታማነትን ለማጎልበትና የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በሚከናወኑ ስራዎች ላይ ተግዳሮት እየሆነ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በክልሉ የፕላስቲክ ብክለት የሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ምርቶቹን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል የጉዳት መጠኑን ለመቀነስ "ኪዩቤክ" ከተባለ ድርጅት ጋር ስምምነት ተደርሶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል። የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻን በአግባቡ ከማስወገድ አንፃርም የተጠናከረ ስራ እንደሚሰራ ጠቁመው ለንቅናቄው ስኬታማነትም ሁሉም በአርበኝነት ስሜት በመስራት ለሚቀጥለው ትውልድ እዳን ሳይሆን ምንዳን ማውረስ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል። የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተሾመ አቡኔ በወቅቱ እንዳሉት መርሃ ግብሩ በአየር ንብረት ለውጥ ችግር ምክንያት እየተራቆተ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሀብት መመናመን በመቀነስ በኩል ከፍተኛ እምርታ እያሳየ ነው። መርሃ ግብሩን በተለያዩ አጋዥ የንቅናቄ ስራዎች ማገዝና ውጤቱን ማጽናት ትኩረት የተሰጠው ሀገራዊ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል። የክልሉ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ ሰሚር በክሪ በበኩላቸው በንቅናቄው የክልሉ ሕዝብ በአካባቢ ብክለት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመያዝ ድርሻውን እንዲወጣ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።
ሀገራዊ የከተሞች የጽዳት እና አረንጓዴ ልማት ስራዎች ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ
May 8, 2024 63
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 30/2016(ኢዜአ)፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው የከተሞች የጽዳት እና አረንጓዴ ልማት ስራዎች ሀገራዊ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ። የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የከተሞች የጽዳት እና አረንጓዴ ልማት ስራዎች ሀገራዊ ንቅናቄ "ጽዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። በመርኃ ግብሩ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ ሚኒስትሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በዚሁ ወቅት ፤ንቅናቄው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው የ"ጽዱ ጎዳና- ኑሮ በጤና" ንቅናቄ አካል ነው ብለዋል። ንቅናቄው ዘመናዊ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን እውን በማድረግ ጤናማ ህብረተሰብ ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ይፋ የተደረገው ንቅናቄ በቀጣይ ወደ ሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚሰፋ ተናግረዋል።  
የአካባቢ ብክለት መከላከል ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው
May 8, 2024 61
ሐረር፣ ሚያዝያ 30/2016 (ኢዜአ)፡-በሐረሪ ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል የንቅናቄ መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው። የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄው "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ሐሳብ ለስድስት ወራት እንደሚካሄድ ታውቋል።   ንቅናቄው በክልሉ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራትን ለማጎልበትና የማህበረሰብ ተሳትፎ ንቅናቄውን ከግብ ለማድረስ ያለመ መሆኑም ተገልጿል። በከተማው እየተካሄደ ባለው ንቅናቄ በአየር፣ ድምጽ፣ ውሃ፣ በአፈርና ሌሎች ብክለቶች እና በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮሩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ በከተማው ንቅናቄውን የሚያበስር ቢል ቦርድ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተመርቋል። በንቅናቄ መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተሾመ አቡኔ፣ የክልሉ ካቢኔ አባላትን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 1382
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 2272
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 1584
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።  
ሐተታዎች
ነገረ - አስተውሎት
Apr 24, 2024 340
ሰው በሀሳብ ከሕይወታዊያን ፍጥረት ይለያል። ከፍጥረቱ ጀምሮ ኑሮውን ቀላል ለማድረግ አስቧል። ሀሳቡም መላ ፈጥሯል። ድንጋይ አፋጭቶ እሳትን አንድዷል። እንስሳትን አላምዶ፣ ሰብልን አባዝቶ፣ መጠለያውን ቀልሶ… ኑረቱን አሳልጧል። ዕለታዊ ተግባሩን ለማቃለል በቁስ ላይ ተመራምሮ አጋዥ ቁስ ፈጥሯል። በሂደትም የኢንዱስትሪን አብዮት አፈንድቷል። በ18ኛው ክፍለ ዘመን በባተው የኢንዱስትሪ አብዮት ዓለም አዲስ ክስተት አስተናግዳለች። ፋብሪካዎች፣ መኪናና አውሮፕላን፣ የእንፋሎትና የኤሌክትሪክ ኃይልና የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች ተፈብርከው ምርትና ምርታማነት ጨምሯል። ከተሜነት አብቧል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ ሮቦቲክስና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች በሰው ተፈጥረዋል። ሳይንስን ለመፍትሔ-እንከን አውሏል። ቴክኖሎጂን ለሁለንተናዊ ሕይወት ማቃለያ ተጠቅሟል። ጊዜ፣ ጉልበትና ሀሳብን ከፈጠራ ጋር አዋዶ ኑሮና ሕይወት አቅልሏል። ኮምፒዩተር ፈበረከ፤ ኢንተርኔትን ፈጠረ፣ ዓለምን አስተሳሰረ። የተዓምር ዘመን ሆነ። ሰው እያስተዋለ... እያስተዋለ… በረቀቀ ጥበብና ግኝት ዛሬ ከዘመነ-አስተውሎት ደረሰ። ሰው ሰራሽ አስተውሎት!! የዘመኑ ቴክኖሎጂ ልህቀት ደረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) እንደሆነ ይጠቀሳል። ዳሩ የቴክኖሎጂው እምርታ የዘመን ክስተት ሳይሆን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት ጀምሮ እርሾ ሲያቦካ እንደነበር የዘርፉ ምሁራን ይጠቅሳሉ። ዋረን ማክኩሎች እና ዋልተር ፒትስ ለዛሬው ሰው ሰራሽ አስተውሎት እርሾ የሆነ በነርቭ አውታረ መረብ የሚታገዝ ሒሳባዊ ሞዴል የፈጠሩት በ1943 ዓ.ም ነበር። በ1950 ዓ.ም ደግሞ አለን ተርኒግ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ማሽን ፈለሰፈ። በተመሳሳይ በ1960ዎቹ አጠቃላይ ችግር ፈቺ፣ ሎጂክ ቴዎሪስትና መሰል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፕሮግራሞች በልፅገዋል። በ1950 ዓ.ም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ራሱን ችሎ እንዲጠና ተወሰነ። ለውስብስብ ችግሮች አይነተኛ መፍትሄ መሆኑ ታመነበት። በ1970 እና 80ዎቹ የዘርፉ ሊቃውንት የሰውን ልጅ የመወሰን አቅም የሚተካ የኮምፒውተር ፕሮግራም ለማበልጸግ ጥረት አድርገዋል። በ1990ዎቹ ምርምሮቹ መቀዛቀዝ ጀምረው ነበር። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዳግም አንሰራርቷል። ስልተ ቀመርን (algorithm) የሚረዱ ማሽኖች ስራ ላይ ውለዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የጥናት ዘርፍ የሰውን ስራና ሃሳብ በኮምፒዩተር መራሽ ቁሶች መተካት ነው። የሰው ልጅ ፍጥረት የሆኑ ማሽኖች መገንዘብ፣ መማርና ችግሮችን እንዲቀርፉ ማስቻልም ነው። ማሽኖች በሰው ልጅ ምትክ አካባቢን ማመዛዘን፣ መማር፣ ማቀድና መፍጠር፣ መተንተንና እንከኖችን ማምከን እንዲችሉ ማድረግ ነው። የሰውን የማሰብ ኅይል በኮምፒዩተር አዳብሮ በሰውኛ ጥበብ ሕይወትን ማቅለል ነው። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅ ያሉትን የስሜት ህዋሳት ክህሎቶች ለማሽኖች በማስተማር ሰዎች ነገሮችን በቀላሉ እንዲያገኙና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው። በዚህም የኮምፒውተር ሊቃውንት ስልተ ቀመር ወይም አልጎሪዝምና አስበው የሚሰሩ ማሽኖች ወደ ስራ እያስገቡ ነው። ለአብነትም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥበብ ቤት የሚያጸዱ ሮቦቶች፣ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች፣ ሰው አልባ ጦር መሳሪያዎች፣ የደህነንት ጥበቃ ካሜራዎች፣… በልጽገው ስራ ላይ ውለዋል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጀመረው ይህ ቴክኖሎጂ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተስፋም ስጋትም ይዞ መምጣቱ ይነገራል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዛሬ ላይ በሁሉም መስክ ገቢራዊ እየተደረገ ነው። በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በግብርና ዘርፎች ምርትና አገልግሎትን ለማቀላጠፍና ለመጨመር ቁልፍ አማራጭ ተደርጓል። ቴክኖሎጂው ከዓለም ገበያ ከ350 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድርሻ አለው። አፍሪካም እያደገ የመጣውን ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ገበያ 10 በመቶ ድርሻ መያዝ ከቻለች እኤአ 2030 አሁን ያለው አህጉራዊ ጥቅል ምርቷ (ጂዲፒ) 50 በመቶ ይጨምራል። ኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በፊት ዘርፉን የሚመራ ተቋም መስርታለች፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን። ኢንስቲትዩቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምህዳር ተጠቃሽ ሀገር ለማድረግ አበክሮ እየሰራ ነው። በቅርቡ የተመረቀው “አስተውሎት” የተሰኘ ፊልም ደግሞ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት በሰው ልጅ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የማይገባበት ሕይወት እንደሌለ ፊልሙ ያስረዳል። በጤና፣ በማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ በመረጃ ፍለጋ፣ በፖለቲካ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በማዕድን ፍለጋና፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የዚህ ቴክኖሎጂ ቁልፍ ሚና ተንጸባርቋል። ዘርፉ ከቅንጦት ይልቅ አስፈላጊነቱ ጨምሯል። ለበሽታ መከላከል፣ ለጤና እንክብካቤ፣ ለትምህርት መሻሻልና ድህነት ቅነሳ ይውላል። ለዚህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረቱ መተግበሪያዎች ፈጠራና አቅም እያደገ መምጣቱ በፊልሙ ተገልጿል። ፊልሙ የኢትዮጵያ የቡና ዛፎችን የበሽታ ስርጭት ለይቶ ለማከም ያለውን ውጤታማነት ያወሳል። ሰው ሠራሽ አስተውሎት የአገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ የሳይበር ደህንነትን ለመጠበቅ፣ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ፣ ምርታማነትን ለመጨመር፣ ገበያን ለማስፋት እና ለመሳሰሉት ሥራዎች በእጅጉ አስፈላጊ ነው። በአሁኑ ወቅት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እየተስፋፉ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል ማሽን ትራንስሌት ወይም የቋንቋ ትርጉም አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያም አንዱን ቋንቋ ወደ ሌላ በመተርጎም አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በዚህም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም በአንድ መተግበሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን መማር እንዲሁም ከድምጽ ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችል ሥርዓትን አበልጽጎ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል። መተግበሪያው አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በድምጽ እና በጽሁፍ ለመማር የሚያስችል ሲሆን ድምጽን ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችለው የመተግበሪያው አካል ድምጽን በመቅዳት ወይም ከመዛግብት (አርካይቭ) የድምጽ ፋይሎችን ወደ መተግበሪያው በማስገባት የጽሁፍ ቅጂውን ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ከፊልሙ መገንዘብ ተችሏል። በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የደረሰበትን ልህቀት ያማከሉና ከዘርፉ ውጤት ለማግኘት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተኬደው ርቀት ይበል የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልህቀት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የዘርፉን ውጤቶች የበለጠ ማላቅ ያስፈልጋል። በዓለም የዕለት ተለት እንቅስቃሴ ውስጥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እያሳደረ የሚገኘውን ተጽዕኖ በመረዳት ለዘርፉ ምርምሮች የሚደረገውን ድጋፍ የበለጠ ማጠናከር ያሻል። ዓለም የሚሄድበትን ፍጥነት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶችን ለመተግበር በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል። (በሰለሞን ተሰራ)      
ብሩህ ነገን የሰነቁ እንስቶች
Apr 19, 2024 581
የሰው ልጆች ከፍጥረት እስከ ዕለተ ሞት ባሉት የሕይወት ዑደቶች ውስጥ በሚገጥሟቸው መልከ ብዙ ፈተናዎች ሳቢያ ራሳቸውን ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋሉ፤ ተገደውም ወደ ማይፈልጉት ሕይወት ይገባሉ። በተለይም ሴቶች በሚገጥሟቸው አይነተ ብዙ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጫናዎች ሳቢያ በበርካታ የህይወት ውጣ ውረድ ወስጥ ያልፋሉ፤ በሂደቱም ለአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የተዳረጉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ቃልኪዳን በላይነህ (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በወጣትነቷ ትዳር መስርታ፣ልጆችን ወልዳ ለመሳም በቅታለች፡፡ ዳሩ ግን ባለቤቷ በድንገተኛ አደጋ በመሞቱ ምክንያት ህጻን ልጆቿን ይዛ ለአስከፊ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጓን ትናገራለች። በዚህም ራሷንና ልጆቿን ህይወት ለማቆየት ወደ ማትፈልገው የወሲብ ንግድ ሕይወት ውስጥ ለመግባት መገደዷን ነው የገለጸችው፡፡ በህፃንነት ዕድሜ ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረገችው ሳምራዊት (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በበኩሏ በአካል ጉዳተኝነቷ ምክንያት ተንቀሳቀሳ መስራት ባለመቻሏ ከተወለደችበት ገጠራማ ስፍራ ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በአዲስ አበባም ህይወቷን በልመና ስትመራ ቆይታለች፡፡ ሌላኛዋ ባለታሪካችን ሔዋን (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) ወደ ማትፈልገው ህይወት ውስጥ ስትገባ የሚያጋጥማት ማህበራዊ ፣ አካላዊ ጥቃት እና ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ትላለች። እሷም ኑሮን ለማሸነፍ የገባችበት የህይወት መስመር ወደ አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንድትገባና ለስነ ልቦናዊ ቀውስ እንድትጋለጥ እንዳደረጋት ገልጻለች። መንግስት በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመታደግ የሚያስችልና “ለነገዋ” የተሰኘ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አንዱ ነው፡፡ ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ ልቦና የምክር አገልግሎት እና በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት ብሩህ ነገን ለማቀዳጀት ስራ ጀምሯል። እነ ቃልኪዳን፣ ሳምራዊት፣ ሔዋንና ሌሎች በችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ‘የነገዋ’ የተሰኘውን የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ተቀላቅለው የተሻለ ነገን ለመኖር ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በማዕከሉ በሚሰጣቸው ሙያዊ ስልጠናና የምክር አገልግሎትም ወደ ተረጋጋ መንፈስ እንዲመለሱ፣ የሕይወት ተሞክሮ እንዲቀስሙ፣ ነጋቸውን ለማሳመር እንዲነሳሱ ስለማድረጉም ይናገራሉ። ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸው፤ መሰል ማዕከላትም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   “የነገዋ” የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄርጳሳ ጫላ ማዕከሉ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ 500 ሴቶችን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከማዕከሉ ሲወጡ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ የሚያደርግ በልዩ የክህሎት፣ የስነ ልቦና እና የሙያ በአጠቃላይ በ18 አይነት የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ስፌት፣ ስነ ውበት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የከተማ ግብርና፣ የሕጻናት እንክብካቤና ሌሎች ዘርፎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንደሚያሰለጥን ነው የገለጹት። ከስልጠናው በኋላ ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማዕከሉ በትብበር እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል፡፡ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 1717
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 2623
  "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።  
ትንታኔዎች
መልከ ብዙው የ"ዳሞታ ተራራ"
Apr 23, 2024 411
የዳሞታ ተራራ ወላይታዎች የሚታወቁበት የራሳቸው የሆነ ባህል፣ ቅርስ እንዲሁም መለያ ምልክት ነው። ዳሞታ የወላይታ የልምላሜ መገለጫና የተፈጥሮ መስህብ ነው። ተራራው በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ 12 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ32 ምንጮችና በ12 ጅረቶች ታጅቦ በኩራት ተንሰራፍቶ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ መጠሪያ ነው። ከዚህ የተነሳ የወላይታ ሶዶ ከተማን ተፈጥሮ ካደላት የዳሞታ ተራራ ሞገሷ የተነሳም ተራራው ፀዳሏ ነው ብለው የሚጠሩትም አልጠፉም። የዳሞታ ተራራ ለአካባቢው ነዋሪም ሆነ አካባቢውን ሊጎበኙ ለሚመጡ እንግዳ ተቀባይነቱን በአረንጓዴ የተፈጥሮ መስህቦቹ በማሸብረቅ ውበቱን በመግለፅ የሚያሳይ ተራራ ነው። ተራራውን ወደ ላይ ለሚመለከተው ዳሞታ ብዙ የሚያሳየውና የሚነግረው ታሪክ እንዳለው ያሳብቃል። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የዳሞታ ተራራ ለ800 ዓመታት ገደማ የቆየ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራ ነው። በጥቅጥቅ ደኖች፣ በወራጅ ወንዞችና ጅረቶች፣ ለመድኃኒትነት በሚያገለግሉ ቁጥር ስፍር በሌላቸው የእፅዋት ዘሮችም የተሸፈነ ነው። በወላይታ ዞን እምብርት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከፍታ ላይ የሚገኘው የዳሞታ ተራራ ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር እንዲሁም የዙሪያ ልኬቱ ከ68 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነም ይነገራል። በአንድ ወቅት ተራራው በአካባቢ መራቆት፣ በአየር ሚዛን መዛባትና በሌሎች ምክንያቶች ግርማውንና ልምላሜውን እያጣ መጣ። ይህም የወላይታን ህዝብ በማሳሰቡ ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ልጅ አዋቂ ሳይል ርብርብ በማድረግ ወደ ቀደመ አቋሙና ሙላቱ ለመመለስ ብርቱ ተፈጥሮን የመከላከል ፍልሚያ አደረገ። ፍልሚያውም በአካባቢው ማህበረሰብ አሸናፊነት በመጠናቀቁ ተራራው ልምላሜውን ጠብቆ አሁን የተላበሰውን ግርማ እንዲይዝ በማድረግ ሊያጣው የነበረውን ጥቅጥቅ ደን በመመለስ የመሬት መሸርሸርን ከመከላከልና የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አልፎ ትልቅ የአይበገሬነት ታሪክ እንደፃፈም ይወሳል። ለዚህም ነው ዳሞታን ከወላይታዎች ማህበረሰቡን ከተራራው ለመለየት እንደማይቻልና ጠንካራ ተዛምዶን የመሰረቱ መሆናቸው የሚገለፀው። የወላይታ ዞን የሀገር ሽማግሌ አቶ አብርሃም ባቾሬ እንደሚሉትም ዳሞታ በርካታ የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የሀገር በቀል እፅዋት፣ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ የወላይታ ነገስታት መናገሻ ስፍራዎች ባለቤት ነው። የዳሞታ ተራራ ከወላይታ ህዝብ ታሪክና ጀግንነት እንዲሁም ከአሸናፊነት ወኔው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑም ያነሳሉ። በዙሪያው ዘመናትን ያስቆጠረ የጥቅጥቅ ደንና የነገስታት መኖሪያ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት የሚገኙበት መሆኑን አንስተው ለወላይታ ሶዶ ከተማም የተለየ ግርማ ሞገስን እንዳላበሳት ተናግረዋል። በዳሞታ ተራራ ዙሪያ የተኮለኮሉት ወንዞችም መነሻቸውን ከተራራው በማድረግ ወደ ታች እየተገማሸሩ ይነጉዳሉ። ወይቦ፣ ቁሊያ፣ ካልቴ ቶቦቤ፣ ሀመሳ፣ ሊንታላ፣ አይከሬ፣ ዋላጫ፣ ጫራቄ፣ ቦልዖ፣ ካዎ ሻፋ፣ ጋዜና ሻፋና ሌሎች ወንዞች ከዚሁ ተራራ ተጎራብተው፣ ከተራራው ያገኙትን መዳኛ ፀበል ለሌሎች ለማቋደስ አየተንደረደሩ ይወርዳሉ። ለአካባቢው ማህበረሰብም ልምላሜያቸውን ያጋባሉ፤ ብርቱውን መሬቱን ምሶ ገበታውን እንዲያበለፅግ ያተጋሉ። ሁሉም ግን የዳሞታ መልዕክተኞች፣ የዳሞታ ተጧሪዎች ናቸው። እንደ አቶ አብርሃም ገለፃ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ የክርስትና ሀይማኖትን በአካባቢው በማስፋፋት ስመ ገናና የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ክርስትናን ለመስበክና መንፈሳዊ ክዋኔዎች ለመፈጸም ዳሞታ ተራራን ይወጡ እንደነበረ ከልጅነታቸው ይነገራቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ ድካም ሲሰማቸው እረፍት የሚያደርጉበት ለመንፈስ ሃሴትን የሚያጎናፅፍ ስፍራ ነው የዳሞታ ተራራ። በዚህ ምክንያት "ጦሳ ፔንጊያ" የእግዜር መተላለፊያ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠውና "ጣዛ ጋሯ" የንጉስ ሞቶሎሚ ቤተ-መንግስት፣ የንጉስ ሞቶሎሚ የጥምቀት ሥፍራ፣ ቆሊ ቦርኮታ፣ ዳጌቾ፣ ቦቄና ሶዶ፣ ጦማ ገሬራና ሌራቶ ጎዳ የተሰኙ ታሪካዊና የሚጎበኙ ስፍራዎች ይጎበኙበታል በዳሞታ ተራራ። ካዎ ሞቶሎሚ፣ ካዎ ዳሞቴ፣ ካዎ ጎቤና ካዎ ጦና የሚባሉ የወላይታ ነገስታት ቤተ-መንግስታቸውን በተራራው አናትና ግርጌ ላይ ይገነቡ እንደነበር አቶ አብርሃም ይናገራሉ። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዳሞታ ተራራ በወላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያለው መሆኑን ይገልፃሉ። ከተራራው አናት መነሻቸውን የሚያደርጉ ወንዞች የወላይታን ምድር አጥግበው ሰዎችና እንስሳቱን አጠጥተው ወደ ብላቴ እና ኦሞ ወንዝ ይፈሳሉ። የዳሞታ ተራራ ሌላው ጠቀሜታው መሬት እንዳይሸረሸር ቀጥ አድርጎ በዛ ግዝፈቱ ይዟል ይሄም ለመንገድ ደህንነትና የአካባቢውን አየር ተስማሚ ከማድረግ አኳያ አይተኬ ሚና አለው። በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነው የዳሞታ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከዘመናት በፊት ተጀምሮበታል ይላሉ አስተዳዳሪው። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በከፊል ለሶዶ ከተማ የሚያጠጣውን የዳሞታ ተራራ የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ከዩኒቨርስቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነውም ብለዋል። የዳሞታ ተራራ ታሪካዊ ይዘቱን ስንመለከት አካባቢው ቀደም ሲል የነገስታት መናገሻ ቦታ ነበር የሚሉት ደግሞ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር አበሻ ሽርኮ ናቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከወላይታ ሥርወ-መንግስት መካከል ካዎ ሳቴ ሞቶሎሚና የሌሎች ነገሥታት መናገሻ ስፍራ ስለነበር በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ታሪካዊ ስፍራ ነው። የዳሞታ ተራራ ለአብዛኞቹ በወላይታ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች የስያሜያቸው መነሻ ነው። ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞታ ወይዴ፣ ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎችና ሌሎች ቀበሌያት የተራራውን ስም መነሻ ያደረጉ መሆኑ ተራራውን ታሪካዊ ያደርገዋል። እዚሁ ተራራ ላይ ካሉ የተለያዩ መስህቦች መካከል የጥንታዊ ዋሻ "ሞቼና ቦራጎ" ዋሻ አንዱ ነው። ይህ ዋሻ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ የጥንት ሰው መኖሪያ ዋሻ ነበር። ዋሻው በዳሞታ ተራራ ከሚገኙ ከአምስት በላይ ዋሻዎች አንዱ ሲሆን በተራራው በስተምዕራብ አቅጣጫ በኩል የሚገኝና ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ሰዎች በዚሁ ዋሻ ይኖሩ እንደነበረም ታሪክ ያስረዳል። ሞቼና ቦራጎ ዋሻ ስፋቱ 38 ሜትር፣ የጣሪያው ከፍታ 33 ሜትር፣ የዋሻው ዙሪያ ልኬት ደግሞ 58 ሜትር፣ እንዲሁም በውስጡ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የመያዝ አቅም ያለው እንደሆነም መረጃዎች ያመላክታሉ። ሌላው ከዳሞታ ተራራ መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን ደብረ-መንክራት አቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም ላስተዋውቃችሁ። ይህ ገዳም ለአቡነ ተክለኃይማኖት መታሰቢያነት በ1887 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ከመመስረቱ ጋር በተያያዘ የተገነባና በዳሞታ ተራራ ምዕራባዊ ራስጌ የሚገኝ የቱሪስት መስህብ ሥፍራ እንደሆነ ነው ዶክተር አበሻ የሚናገሩት። ገዳሙ የአምልኮና የፀበል አገልግሎት እየሰጠ ከአንድ ክፈለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ በወላይታ ዞን ካሉ መንፈሳዊ ስፍራዎች አንዱ ሲሆን በውስጡ በርካታ ሐይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ ጉዞ ከሚደረግባቸው መዳረሻዎች አንዱ ነው። በመሆኑም አካባቢው ለቱሪስት መዳረሻነት፣ ለአካባቢው ልማት ብሎም ለአየር ንብረት ሚዛንን መጠበቅ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።            
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 3984
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2745
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 2608
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11954
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16404
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 8447
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 9552
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 26968
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 22313
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16404
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12508
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11954
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 11328
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 11089
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 10602
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 26968
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 22313
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16404
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12508
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
ከፈተናዎች ባሻገር . . . !
May 4, 2024 173
ከፈተናዎች ባሻገር . . . ! (በቀደሰ ተክሌ ከሚዛን አማን ኢዜአ) በዓለም ውስጥ ሆኖ በአንዳች ምክንያት የወደቀ ይነሳል፤ የታመመ ይድናል፤ የፈረሰ ይጠገናል፤ የደከመ ይበረታል፤ የተኛ ወይም ያንቀላፋም ይነቃል። ይህን እውነት ሰው በልቡ ተስፋ አድርጎ ውሎ ያድራል።ነገን ያልማል። "ሲጨልም ይነጋል" እያለ ለራሱ ይጽናናል። መከራ ሲበዛበት "ሊነጋ ሲል ይጨልማል" በሚል አዲስ ተስፋን በውስጡ ይዘራል። ከእነዚህ ተቃራኒ የሰው ልጅ ከህይወት ዑደት ኩነቶች ባሻገር በተለያዩ የእምነት ተቋማት አስተምህሮ ደግሞ የሞተ የሚነሳበት መንፈሳዊ ተስፋ አለ። ይህም ትንሣኤ ይባላል- ከሞት በኋላ የሚኖር ሕይወትን የሚያሳይም መነጽር። "ትንሣኤ" ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን፤ ቀጥተኛ ትርጉሙ መነሳት ነው። መነሳት የሚነገረው ለወደቀ፤ ለደከመ እና ለሞተ ነው። እንዲሁም ከነበረበት ከፍ ማለት ቀና ማለት መለወጥና ወደ አዲስ መልካም ነገር መሸጋገርን ያመለክታል። በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትንሣኤ የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስን ከሞት መነሳትን መሠረት በማድረግ ነው። ክርስቶስ በምድር ሲመላለስ የሰው ልጆች ማድረግ ስለሚገባቸው በጎ ምግባራት እርሱ በመተግበር አስተምሯል። የበጎ ተግባራት ውጤት ደግሞ ከሞት በላይ ራስን ከፍ አድርጎ በሕይወት ዙፋን ላይ መቀመጥ እንደሆነ አሳይቷል። ፍቅር እንዲጎለብት ለሌላው መኖርና አልፎም መስዋዕት መሆንን በግልጽ አንጸባርቋል። እርሱ መልካም ነገር አድርጎ "እናንተ እንዲሁ አድርጉ" ብሏል። ለአብነትም ፍቅር በቀዳሚነት የሚጠቀስ ትምህርቱ ነው "እርስ በእርስ ትዋደዱ ዘንድ ትዕዛዜ ይህች ናት" ብሏል። ፍቅሩን ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ በመስጠት ገልጧል። ነገ ምን እንዲያውም ከደቂቃዎችና ሰዓታት በኋላ ምን እንደሚፈጠር በማናውቀው ተገድቦና ተተምኖ በተሰጠን የህይወት ዑደት ውስጥ በምናልፋቸው የትኞቹም ጎዳናዎች ምህረትን፣ ይቅር ባይነትን ይጠየቃል። ለሰው ልጅ ለራሱም ቢሆን ቂምና ቁርሾ ያላደረበት ልብ ያስፈልገዋል። የወደደንን ወይም የሰበሰበንን ሳይሆን ተቃራኒውን የፈጸመብንን የመውደድና ፍቅርን በተግባር የማሳየት ልምምድ እንዲኖረን ያስተምራል። ይህም ከራሳችን ጀምሮ ለአካባቢያችን ሁሉ ሰላምና መረጋጋትን ይፈጥራል። ሌላው የተግባር ትምህርቱ ትህትና ነው። የሰው ልጆችን ለማክበር ራሱን ዝቅ አድርጓል። የደቀ መዛሙራቱን እግር ተንበርክኮ አጥቧል። "እናንተም እንዲሁ ለሌሎች አድርጉ" ሲልም አስተምሯል። የዚህ ዓይነቱ ተግባር ዛሬም በኢትዮጵያውያን እሴት ውስጥ ይስተዋላል። በትውፊት ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፉ መጥቷል። ቤታችን የወላጆቻችንን አልፎም የመጣን እንግዳ እግር ማጠብ የመልካም ሥነ ምግባር ምገለጫችን ሆኖ ቆይቷል። ይህ እርስ በርስ መከባበር እያጠነከረ ይመጣል፤ ውሎ ሲያድርም በስነ ምግባር የታነጸ የጠንካራ ማህበረሰብ መገለጫም ይሆናል። ትህትና ከአንገትን ጎንበስ ብሎ ሰላምታ መሰጣጣት ብቻ አይደለም። ሌሎች የተሻሉ እንዲሆኑ ማሰብን ያካተተ ከልብ የሚፈልቅ ተግባር ነው። በትዕቢት አውቃለሁ ባይነት ሳይሆን ራስን ዝቅ በማድረገ መንፈስ የተገዛ ማንነት ማዳበርን ይጠይቃል። ድርጊት የሀሳብ ውጤት ነው። ስለሆነም እርስ በርሳችን ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ እንዲሁም በስራ ቦታችን ካሉ ባልደረቦቻችንን ከልብ በመነጨ ትህትና መቀበልና ማስተናገድ አልፎም መታዘዝ ይጠበቅብናል። ይህ ነው የትህትና ጥቅ እሴቱ። በጎነት፣ ፍቅር፣ ትህትና፣ ለጋስነትና ቅንነትን የሰው ልጅ ገንዘቡ ቢያደርግ ሞትን አሸንፎ ይከብራል። ከመውደቅ ባሻገር መነሳት አለ። ከጨለማ በኋላ ብርሃን ይኖራል። ይህም ከጽልመትና ከአስቸጋሪ ነገሮች አልፈን ብርሃን ማየት እንደሚቻል የጸና ተስፋ በመያዝ ነጋችንን ማየት ይኖርብናል። ትንሣኤ ደስታ ነው፥ ከድቅ ድቅ ጨለማ በኋላ የሚገኝ ልዩ ብርሃን፤ ከመቃብር በላይ የሚገኝ ሐሴት ነው። የትላንት መከራ ላይ የታነጸ ጽኑዕ ደስታ፤ የትላንት መልካም ነገርን መነሻ አድርጎ የሚገኝ ክብር ነው። የሰው ልጅ በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ነገን ተስፋ አድርጎ ጠንክሮ መስራት ከቻለ መልካም ነገር ሁሉ ማግኘት ይችላል። ዛሬም ዓለም ብዙ ውጣ ውረዶችን ታስተናግዳለች። እንደ አገር ኢትዮጵያ ብዙ ችግሮች እያጋጠሟት ነው። ችግሮቹና መከራው ማብዛቱ የነገን ትንሣኤ ለማምጣት ነው። ከፈተናዎች ባሻገር ድል አለ፤ ትንሣኤ ይገለጻል። ለዚህም ነው ምንም ፈታኝ ነገር ቢኖር፣ ችግሮች ቢደራረቡም ተግቶ ሰርቶ ወደ ብርሃኑ መውጣት ይቻላል የምን ለው። የትንሣኤ በዓል ከበዓል ባሻገር በበጎ እይታ በመቃኘት፣ በፍቅር በመታነጽና የቅንነት ጎዳናን በመያዝ ለአገር እና ለራሳችን ክብርን ለመጎናጸፍ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት መሆን አለበት።      
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ 
Mar 5, 2024 3916
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም