የአካባቢ ብክለት መከላከል ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው

ሐረር፣ ሚያዝያ 30/2016 (ኢዜአ)፡-በሐረሪ  ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል የንቅናቄ መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው።

የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄው "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ሐሳብ ለስድስት ወራት እንደሚካሄድ ታውቋል።


 

ንቅናቄው በክልሉ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራትን ለማጎልበትና  የማህበረሰብ ተሳትፎ ንቅናቄውን ከግብ ለማድረስ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

በከተማው እየተካሄደ ባለው ንቅናቄ በአየር፣ ድምጽ፣ ውሃ፣ በአፈርና ሌሎች ብክለቶች እና በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮሩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ በከተማው ንቅናቄውን የሚያበስር ቢል ቦርድ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተመርቋል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተሾመ አቡኔ፣ የክልሉ ካቢኔ አባላትን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም