የፓስፖርት፣ ዲጂታል መታወቂያና የኤ ቲ ኤም ካርድ ማምረቻ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሚገነባው የፓስፖርት፣ የዲጂታል መታወቂያ፣ የኤ ቲ ኤም ካርድ እንዲሁም መሰል የደህንነት ህትመቶች ማምረቻ ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ መርኃ-ግብር እየተካሄደ ነው።

በስነ ስርዓቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ፤ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ አብዱራህማን ኢድ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ፤ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ እና የቶፓን ግራቪቲ ኩባንያ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የስ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም