የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የትራንስፎርሜሽናል ዕቅድ ዝግጅት ወርክ ሾፕ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የትራንስፎርሜሽናል ዕቅድ ዝግጅት ወርክ ሾፕ መካሄድ ጀመረ።

የአስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩል መልዕክት ዛሬ የከተማ አስተዳደራችን ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት የትራንስፎርሜሽናል ዕቅድ ዝግጅት ወርክ ሾፕ ማካሄድ ጀምረናል ብለዋል።

በወርክሾፑ አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተመራጭ ከተማ ለማድረግ በሚያስችሉ በተመረጡ ስድስት አጀንዳዎች ላይ በዓለም አቀፍ የዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

በተጨማሪም የትራንስፎርሜሽን እቅድ ዝግጅት እንደሚከናወንም ጠቁመዋል።

ሃገራችንን ለማበልጸግ በሁሉም ዘርፍ ያለ እረፍት መስራታችን ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉም ከንቲባ አዳነች አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም