በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን የልማት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል

ደሴ ፤ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልልዘላቂ  ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን  የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና  የምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ አብዱ ሁሴን አስታወቁ። 

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት የሰላምና የፀጥታ ስራዎችን ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ ገምግሟል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ አብዱ ሁሴን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ በክልሉ የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልሉን ካጋጠመው ችግር ታድጓል፡፡

የፀጥታ መዋቅሩ በቅንጅት ባካሄደው ህግ የማስከበር እንቅስቃሴ በክልሉ ሰላም ማስፈን መቻሉን ተናግረዋል።

በዚህም የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ማከናወን ተችሏል ብለዋል ።

በክልሉ የተገኘውን ሰላም ከህብረተሰቡ ጋር ዘላቂ ከማድረግ ባሻገር የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አስታውቀዋል ።

ህብረተሰቡም የጽንፈኞችን ተንኮልና አገር የማፍረስ ሴራ በመረዳት ከመንግስት ጎን ተሰልፎ ሰላሙን በማስከበርና ለልማት ያለውን ንቁ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም