ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ የከፍታ ጉዞ ማሳያ - ብሪክስ
Sep 13, 2026 112
''የብሪክስ ጉባዔ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው" በማለት ነው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር። 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የጥምረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በተገኙበት “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርንና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ በህንድ ኒውዴልሂ እየተካሄደ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የልዑክ ቡድናቸው በዚሁ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ በሚፈጥረው ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድናቸው የብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። ብሪክስ ለአፍሪካ ቀጣና እና በተለይም ለኢትዮጵያ በርካታ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝ አዲስ የዓለም ስርዓት እየተፈጠረበት የሚገኝ ጥምረት ነው። የብሪክስ ጥምረት ለኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። በዚህም እንደ ቻይና፣ ህንድ እና ሩሲያ ካሉ ታላላቅ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣውን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በተለይም በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና እና በኢነርጂ ዘርፍ በማሳደግ በኩል አይነተኛ አማራጭ የኢንቨስትመንት መንገድ ነው። ጥምረቱ ለኢትዮጵያ ከሚያስገኘው ትሩፋት አንጻር ሲታይ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በመቅረፍ፤ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በሚደረጉ የንግድ ልውውጦች የሀገር ውስጥ ገንዘብን የመጠቀም ዕድልን ስለሚፈጥር፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እጥረትን ከመቀነስ አኳያም እንዲሁ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕቅዷ ኢኮኖሚዋን በመሠረታዊነት ለሚያሳድጉ መሠረተ ልማት ግንባታ እና ማስፋፊያ እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ትገኛለች። ከዚህ አኳያ ብሪክስ የመንገድ፣ የባቡር፣ የኃይል ማመንጫዎችና ዲጂታል ቴክኖሎጂ እና መሰል የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን የፋይናንስ ድጋፍ በማመቻቸት በኩል ኢትዮጵያ ለያዘችው ግብ ስኬት ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚያስገኝ ጥምረት ነው። ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ላሳካቻቸው ውጤቶች የዓለም አቀፍ ግንኙነቷን የቃኘችበት አዲስ አካሄድ ተጠቃሽ ነው። ከእነዚህ ስኬቶች መካከል ደግሞ በብሪክስ ጥምረት ውስጥ አባል የሆነችበት መንገድ አንዱ ሲሆን፤ ይህ የብሪክስ ጥምረት ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የራሱን ሚና በመጫወት ኢትዮጵያ በቀጣናው እና በአህጉሪቷ ያላትን መሪነትና ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት በማጠናከር በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ድምፅ እንድታጎላ እና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷ እንዲያድግ እያስቻለ መሆኑም በተጨባጭ ታይቷል። የብሪክስ ጥምረት በአፍሪካ አለፍ ሲልም በጥምረቱ አባል ሀገራት መካከል ተመጣጣኝ ልማት እንዲኖር እና ሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ አስቻይ ምህዳር እየፈጠረም ይገኛል። በተለይ አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት በማልማት የኢኮኖሚ ዕድገቷን እንድታፋጥን አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ መሆን የሚያስችለውን አደረጃጀት እና አሰራር እየዘረጋም ይገኛል። ይህ የጥምረቱ አዳዲስ አደረጃጀት እና አሰራር አዲሱ የልማት ባንክ እንዲወለድ አስችሏል። በዚህ ባንክ አማካኝነት የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጥብቅ መስፈርቶች ነፃ በሆነ መንገድ ለተለያዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ ወይም ብድር እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። በጥምረቱ አማካኝነት የተፈጠረው አዲሱ የልማት ባንክ የአፍሪካ ሀገራት በራሳቸው ሀገራዊ ገንዘብ እና ከአሜሪካ ዶላር ተጽእኖ ውጪ ከታላላቅ የብሪክስ ሀገራት ጋር የንግድ ልውውጥ እንዲያከናውኑ በር እየከፈተ ይገኛል። በተጨማሪም አፍሪካ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ የውሳኔ መድረኮች ላይ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት በማሳደግ፣ ፍትሐዊ የሆነ የዓለም አቀፍ ስርዓት እንዲፈጠር እያስቻለ መሆኑም የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ሰነባብቷል። ይህ የብሪክስ ጥምረት መመስረት፣ መስፋፋትና መጠናከር በዓለም የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስርዓት ላይ በርካታ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጦችንና አንድምታዎችን እያስከተለ ይገኛል። የብሪክስ ጥምረት ተመስርቶ እየፈጠረ ያለው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተጽዕኖ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የምዕራባውያን ሀገራት በዓለም ፖለቲካ ላይ የነበራቸውን የበላይነት በመገዳደር፣ ሥልጣንና ውሳኔ ሰጪነት ለተለያዩ የአህጉራት ኃይሎች እንዲከፋፈል፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ የአሰራር እና የአደረጃጀት ማሻሻያ ጥያቄዎች ጎልተው እንዲሰሙ የማድረግ አቅም እየፈጠረ ነው። በተጨማሪም የብሪክስ ጥምረት አባል ሀገራት በንግድ ልውውጣቸው ወቅት በራሳቸው ሀገራዊ ገንዘቦች የመጠቀም ዝንባሌያቸው በመጨመሩ፣ የአሜሪካ ዶላር በዓለም ንግድና መጠባበቂያ ክምችት ላይ ያለውን ፍጹም የበላይነት በማዳከም፤ አዲሱ ልማት ባንክ የብሪክስ የድንገተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማዕቀፍ የምዕራባውያኑን ጥብቅ የፖለቲካ መስፈርቶች ሳይከተሉ ለታዳጊ ሀገራት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ እንዲያቀርቡ ብሎም የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለምን ከፍተኛ የነዳጅ፣ የጋዝ፣ የብረታ ብረት እና የግብርና ምርቶች አቅርቦት የሚቆጣጠሩ በመሆናቸው፣ በዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች እና የዋጋ ውሳኔዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዲያሳድሩ የውሳኔ ሰጪነት አቅማቸውን እያሳደገ መጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ ያላቸውን የመልማት አቅም ለመጠቀም አማራጭ የልማት ፋይናንስ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። ለዚህ ደግሞ የብሪክስ ጥምረት ይዞት የመጣውን ዕድል በውል አንስተዋል። ለዚህም ነው በብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰፊ ገበያ አለን፤ አሁን ያለው መልካም ዕድል እነዚህን አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ደግሞ ሀብቱ በሚገኝበት ቦታ መመረት እንዲችል ማድረግ ነው ሲሉ ያመላከቱት። ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና እያደገ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን አጋርነቶች ለመገንባት ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአሠራር ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጽናትን መገንባት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የአህጉራችንን ፍላጎት እንዲያገለግል ማድረግ፣ አስተማማኝ የዕዳ እፎይታ ሒደትን ማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከኢኮኖሚ ሽግግር ጋር ማስተሳሰር ከጥምረቱ የሚጠበቅ መሆኑንም ነው ያነሱት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የብሪክስ ጉባዔ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው። የጥምረቱ አቅም ከተናጠል አካሄድ ይልቅ ትብብርና ለጋራ እሴት መጎልበት ያለውን ዕድል ያመላክታል። ኢትዮጵያ ለኮቪድ እና ኤልኒኖን ጨምሮ ለዓለም የኢኮኖሚ እና የንግድ ስርዓት መመሰቃቀል እጅ ሳትሰጥ፤ ይልቁንም መሰል ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ችግሮችን ወደ ዕድል በመቀየር፤ ለችግሮች የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ባከናወነቻቸው ተግባራት ጽናትን ገንዘቧ እያደረገች ትገኛለች። ለዚህም ነው "አካታች ዓለም አቀፍ አስተዳደር እና ባለ ብዙ ወገን ትብብርን ማጠናከር” በሚል አጀንዳ ላይ ትኩረት ባደረገው የጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ውሎ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ችግሮች ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ጽናትን ማጠናከር እና የአስተዳደር ስርዓት አካል የማድረግን መሠረታዊ ጠቀሜታ የገለጹት። ይህ ጽኑ ስርዓት ግንባታ ኢትዮጵያ በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እንድትበረታ ማስቻሉን ለማሳያነት አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ የስንዴ ጥገኝነት ተላቃ በምግብ ራሷን መቻሏን አንስተዋል። በጤና ቅድመ መከላከል ፖሊሲ አካል ሆኖ የሕክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች ማምረትን፣ የዲጂታል ስርዓት ሽግግርንና ደኅንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀም የማስፈን አበይት ተግባራት መከናወናቸውን ነው አጽንኦት የሰጡት። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የጀመረችው የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑን የገለጹት። በእነዚህና መሰል የልማት ትብብሮች ከጥምረቱ አባል ሀገራት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም ነው ያረጋገጡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ጥምረቱ የተቋቋመበትን ዓላማ እና መርህ በተጨባጭ እውን እያደረገች እንደምትገኝ በመጠቆም፤ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ስርዓት ማሻሻያ ባከናወነቻቸው አመርቂ ትግበራዎች፣ በታዳሽ ኃይል መስፋፋት እና የኢንዱስትሪ መሠረት ልማቶቿ፣ በግብርና ስርዓት ማሻሻያ እየተመዘገቡ ያሉ የምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ግዙፍ የአየር መንገድ ግንባታ የአኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ንግድ ትሥሥርን ለማስፋፋት በምታደርገው ጥረት በጥምረቱ ለሚነሱ ተያያዥ የውይይት አጀንዳዎች መሪ ተዋናይ መሆን እንደሚያስችላትም አንስተዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድናቸው የብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ እሙን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው እያደረጉት ካለው ተሳትፎ ጎን ለጎን ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ከተለያዩ የብሪክስ ስብስብ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል። በዚህም ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ከቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ ሚን ሁንግ፣ ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ቃሲም ጆማርት ቶካዬቭ፣ ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያ፣ ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያ እንዲሁም ከሌሎች መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ውጤታማ ውይይቶችን አካሂደዋል። የውይይቶቹ ማጠንጠኛም የጥምረቱን አባል ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያበረታቱ እንደ ኢንቨስትመንት፣ ቀጣናዊ ጉዳዮች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታና ክህሎት፣ ቱሪዝም፣ የማዕድን ልማት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ሊኖሩ ስለሚችሉ ትብብሮች ላይ ያተኮሩ እንደነበሩ ተመላክቷል።
ከታሪክ ዘካሪነት ወደ ታሪክ ሰሪነት፤ የአዲሱ ትውልድ የሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ አብዮት
Sep 13, 2026 175
የአንድ ሕዝብ የነፃነት ድል የሚያበቃው በድል ማግስት በሚተረክ የታሪክ መዛግብት ብቻ አይደለም። በሌላ የታሪክ ገጽ ላይ አዲስ ድል መጎናፀፍ ሲቻል የቀደመውን ድል ትርጉምና ምልዑነት የበለጠ ያጎላዋል። ዓድዋ የክንደ ብርቱ ቅድመ አያቶች የሀገርን ሉዓላዊ ነፃነት የማስጠበቅ አኩሪ የድል ምልክት ነው። የድል ምልክትነቱም ለጭቁኑ የዓለም ጥቁር ሕዝቦች ፅናትና የነፃነት ጎህን በመቅደድ፣ ለአሁኑ ትውልድ ደግሞ የይቻላል መንፈስን አጎናፅፏል። ጀግንነትንና አልበገር ባይነትን ከቅድመ አያቶቹ የወረሰው የአሁኑ ትውልድም በሌላ የታሪክ ገጽ በጉባ ተራሮች ግርጌ በዓባይ የዘመናት ዥረት ላይ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት የራሱን ታሪክ ጽፏል።   የሕዳሴ ምረቃ የተበሰረባት ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለትም የኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌትነት የሚበይኑ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች የተበሰሩባት ድርብ ታሪካዊት ዕለት ሆና ተመዝግባለች። በሕዳሴ የይቻላል መንፈስን የተጎናፀፈችው ኢትዮጵያም በኃይል፣ በግብርና፣ በአቪዬሽን፣ በጋዝ፣ በማዕድንና በሌሎች ዘርፎች ወደ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተሸጋግራለች። የጉባ ብስራቶችም የአንድ ፕሮጀክት ወይም ዘርፍ ስኬት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ሀብቷን በራሷ አቅም በማልማት የብልፅግና ጉዞዋን ለማስፋት የምታደርገው የልማት ጉዞ ሕያው ምልክት ናቸው። የመደመር መንግሥት አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት ኢትዮጵያን በራሷ ልጆች የመቅረጽ ራዕይም ከዓድዋ ነፃነትን፣ ከሕዳሴ የልማት ድልን፣ ከጉባ ተራሮች ግርጌ ብስራትን በመሰነቅ ታሪክን ከመዘከር ወደ አዲስ ታሪክ መጻፍ ተሸጋግሯል። ይህም ሕዳሴ ግድብ በአንድ የታሪክ ምዕራፍ ብቻ ተከትቦ የሚቀር የትውልድ ዓርማ ሳይሆን ለሚቀጥሉት ትውልዶች የመፈጸም አቅምና የይቻላል መንፈስ የሚያስተላልፍ ቅርስ መሆኑን ያሳያል። የአንድ ግዙፍ የትውልዱ ብሔራዊ ፕሮጀክት ምረቃም የሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችን ውልደት በማብሰር ኢትዮጵያ በአዲስ የስኬት ምዕራፍ እየተስፈነጠረች መሆኗን ያመላክታል። የጉባ ብስራት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ፣ የጋዝ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንዲሁም የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አብነቶች ናቸው። ኃይልን ከግብርና፣ ኢንዱስትሪን ከአቬየሽን ያሰናሰሉት የጉባ ብስራት ግዙፍ ፕሮጀክቶችም በዚህ የልማት ጉዞ ቀጣዩን ምዕራፍ መጻፍ ጀምረዋል። ይህም ኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የምታልም ሀገር ብቻ ሳትሆን የመፈጸም አቅም ያላት መሆኗን የሚያሳይ አዲስ የልማት ምዕራፍ ነው። በመደመር መንግሥት ውልደት ማግስት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ያስመዘገበቻቸው እመርታዎች ሀገርን ከመዋቅራዊ ስብራት ወደ ማንሰራራት ያሸጋገሩ ድሎች ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ታሪካዊቷ ዕለት እንዳሉት፤ ሕዳሴ ያስገኘው ወኔና ተስፋ የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ አድማስ የሚያበስሩ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም መንገድ ከፍቷል። በዚህም በጥቂት ዓመታት ውስጥ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት፣ የጋዝ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካዎች፣ እንዲሁም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች እንደሚገነቡ ማብሰራቸው ይታወሳል። እነዚህ ግዙፍ የልማት ዕቅዶች በቁጥር የሚገለጹ ፕሮጀክቶች ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን ከራሷ የመፈጸም አቅም ጋር በማሰናሰል የነገን ሀገራዊ ተስፋ የሚያመላክቱ የልማት አቅጣጫዎች ናቸው። የመደመር መንግሥት ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ትልሞችም የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ የማንሰራራት ምዕራፍ በማብሰር፣ የሀገርን ብልፅግና የሚቀርጹ እመርታዎች የተገኙባቸው ናቸው። ከእነዚህ መካከል የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ የፕሮጀክት ግንባታ ብስራት አንዱ ነው። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላትን አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማጎልበት፣ በኢኮኖሚ፣ በቱሪዝምና በዲፕሎማሲ ዘርፎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚከፍት ቁልፍ መሠረተ ልማት ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፕሮጀክቱን ግንባታ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ዘርፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ ነው። በዚህ መነፅር ሲታይም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት የአቪዬሽን ፕሮጀክት ብቻ አይሆንም። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን የአቪዬሽን መሪነት በማላቅ፣ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት ይሆናል። የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ግዝፈትና ዝማኔ ኢትዮጵያን የአቪዬሽን፣ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ማዕከል የማድረግ ከፍተኛ አቅም አለው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ናቸው። ይህም ሕዳሴ ግድብ ያስተዋወቀው የታላቅ ሀገር ግዙፍ ፕሮጀክትን የመፈጸም ባህል ከኃይል ዘርፍ ወደ አቪዬሽንና ሌሎች ስትራቴጂካዊ የልማት መስኮች እየተስፋፋ መሆኑን ያመላክታል። ሌላኛው የኢትዮጵያን የማንሰራራት አቅጣጫ የሚበይነው ግዙፍ ፕሮጀክትም የተፈጥሮ ጋዝና የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ የማምረት ትልም ነው። የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ከመሬት ሥር ተደብቆ የሚቀር ሳይሆን፣ የምርት፣ የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ ልማት መሠረት የማድረግ አዲስ የዕድገት አቅጣጫ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክትን ባስጀመሩበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ የጋዝ ምርት ፕሮጀክት የኃይል አቅርቦትን ከግብርና ምርታማነት ጋር ያሰናሰለ ነው ብለዋል። ይህም የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ የኃይል አቅርቦትን ከማሟላት ባሻገር፣ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ በስፍራው ለሚገነባው የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግብዓትነት ያገለግላል። በዚህ አተያይም ጋዝን ማልማት የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር፣ የግብርና ምርታማነትን፣ የኢንዱስትሪ ምርትንና የሀገር ውስጥ ግብዓት አቅርቦትን የሚያጠናክር የተሰናሰለ ስልታዊ የልማት አቅም ይፈጥራል። የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለብዝኅ ክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገት የሰጠው ትኩረትም ኢትዮጵያን በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ዘርፎች በስኬት ምሕዋር እንድትገባ አድርጓታል። ይህም የኢትዮጵያን ማዕድን ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ እሴት የታከለበትና ፈጠራ ያለበት የምርት ሰንሰለት የሚሸጋገርበትን ወሳኝ ዕድል ፈጥሯል።   የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ፣ የካሉብ ፋብሪካ የተፈጥሮ ጋዝ ማጣራትና ወደ ፈሳሽነት የመቀየር የማዕድን ልማት ለተሽከርካሪና ፋብሪካ አማራጭ የኃይል ምንጭ ማቅረብ የሚያስችል ነው ብለዋል። ይህ ተፈጥሮ ሀብትን በጥሬ ዕቃነት ከመሸጥ ይልቅ በማቀነባበርና በማልማት የበለጠ እሴት ለማስገኘት የተያዘውን አቅጣጫ ያመላክታል። የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም የግሉን ዘርፍ በማሳተፍና ዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን በመሳብ፣ አዳዲስ የልማትና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ከፍቷል። ለዚህም ነው የዳንጎቴ ግሩፕ ባለቤትና መሥራች አሊኮ ዳንጎቴ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም በኢኮኖሚው ውስጥ ጤናማ ውድድርና ቀልጣፋ አሠራር እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል። ከሕዳሴ ግድብ እስከ አቪዬሽን፣ ከተፈጥሮ ጋዝ እስከ ማዳበሪያ ድረስ ገሃድ የገለጠው የኢትዮጵያ ማንሰራራትም ከማለም ወደ መፈጸም፣ ከመፈጸምም ወደ ዘላቂ የልማት አቅም ለመሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ ያመላክታል። የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያንን አንድነትና የጋራ አቅም ለዓለም ታሪክ ያሳየ ድል እንደነበር ሁሉ፣ ሕዳሴ ግድብም ያንኑ የጋራ አቅም በዘመናዊ ልማት ላይ የገለጠ አዲስ ታሪካዊ ክስተት ሆኗል። የኢትዮጵያውያን አንድነት የዓድዋን ድል ካቀዳጀ፣ ያው በሕብር የተሸመነ አንድነትም ሕዳሴን እውን አድርጓል። ሕዳሴ የተስፋ ብርሃን ካበራ፣ ያ ተስፋም በሌሎች የልማት ሜጋ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሆኖ እየቀጠለ ነው። ይህ የይቻላል መንፈስ ከፕሮጀክት ወደ ፕሮጀክት የሚጓዝ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ስለነገ ሀገራቸው ያላቸውን እምነት የሚያድስ የልማት ብስራት ነው። ሕዳሴ ግድብ የተጀመረውን የተስፋ ጉዞ አዲስ አቅጣጫ አስይዞታል። የሚቀጥለው ታላቅ ተግባር ደግሞ ይህን የመፈጸም አቅም ወደ ዘላቂ ምርታማነት፣ የሥራ ዕድል፣ የዜጎች ተጠቃሚነትና የተሻለ ኑሮ መቀየር ነው። እናም የሕዳሴ ግድብ ብስራት በግድቡ የውሃ ሙሌት ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያውያን የጋራ ህልም፣ በሀገራዊ አንድነትና በመፈጸም አቅም የሚቀጥል የልማት ብስራትን ፈንጥቋል።    
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አፍሪካ ለችግሮቿ መፍትሔ ማቅረብ እንደምትችል ማረጋገጫ ነው
Sep 13, 2026 112
አዲስ አበባ፤መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አፍሪካ ለችግሮቿ መፍትሔ ማቅረብ እንደምትችል ማረጋገጫ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም፣ ሥነ-ምህዳርን በመመለስና ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ለአፍሪካና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አርዓያ የሚሆን ተግባር እያከናወነች መሆኑንም ተናግረዋል። በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ባለሙያ ዮሴፍ አምሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ከከባቢ አየር የሚለቀቁ ሙቀት አማቂ ጋዞችን በመያዝ ለሥነ-ምህዳር ጥበቃ ገንቢ ሚና እየተወጣች መሆኑን ገልጸዋል። መርሃ ግብሩ ለአርሶ አደሩ፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ብለዋል። የፓን አፍሪካ አየር ንብረት ፍትህ ጥምረት ዋና ዳይሬክተር ሚቲካ ምወንዳ (ዶ/ር)፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ሀገራት ችግራቸውን በራሳቸው አቅም ለመፍታት ሊወስዱት የሚገባ ምርጥ ተሞክሮ መሆኑን ገልጸዋል።   ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ያስመዘገበችው ስኬት አፍሪካ ለችግሮቿ መፍትሔ ማቅረብ እንደምትችል ያሳየ ነው ብለዋል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ የአየር ንብረት ሻምፒዮንና የአፍሪካ የግሬት ግሪን ዋል ኢኒሼቲቭ አምባሳደር ታቢ ጆዳ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በጠንካራ አመራር የታጀበ ውጤታማ ሥራ መሆኑን ገልጸዋል።   መንግሥት ፕሮግራሙን ከንግግር ባለፈ መሬት ላይ የሚታይና ሚተረጎም ድንቅ ኢኒሼቲቭ ነው ብለዋል። በአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ አየር ንብረትና ልማት ልዩ ፈንድ አስተዳዳሪ ጀምስ ኪንያንጊ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎችን በመቅረጽና በተግባር ረገድ ለአፍሪካውያን አርዓያ መሆኗን ገልጸዋል።  
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አባልና አጋር ሀገራትን ባሳተፈው የብሪክስ ፕላስ የምክክር መድረክ ላይ፤ጠንካራ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል
Sep 13, 2026 123
አዲስ አበባ፤መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):-አባልና አጋር ሀገራትን ባሳተፈው የብሪክስ ፕላስ የምክክር መድረክ ላይ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠንካራ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነት ይበልጥ እንዲሰፋ እንዲሁም ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ትስስርን ለማሳደግ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል። ‎‎በዚህ አውድም፣ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አድማሱን በመላው አፍሪካ እንዲያስፋፋ የባንኩን ቢሮ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ በሙሉ አቅም ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ‎‎በተጨማሪም በአዲስ አበባ የሚካሄደው ኮፕ 32 በብሪክስ ሙሉ ድጋፍ ለአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎች እና ለዘላቂ ልማት መፋጠን ሁሉንም ድምፆች የሚያሰባስብ ሁሉን አቀፍ መድረክ ሆኖ ማገልገል እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል። ‎‎#PMOEthiopia
የሚታይ

የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ ተስተጋብተዋል-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Sep 13, 2026 132
አዲስ አበባ፣መስከረም 3/ 2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ መስተጋባታቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡ አገልግሎቱ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ብዙ ሀገራት የሚመኙትን የብሪክስ አባል የመሆን መሻት እንድታሳካና ተጠቃሚ እንድትሆን አስችሏታል ብሏል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ የኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ ተስተጋብተዋል! ብሪክስ ወደ ሰፊ ጥምረት አድጓል፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አሁን 11 ሙሉ አባላት ያሉት ሲሆን በሩሲያ ካዛን ጉባኤ ይፋ የተደረጉ 10 አጋር አገራትንም በልዩ የአጋርነት ማዕቀፍ በማካተት ተጽእኖውን አጠናክሯል። የብሪክስ ጥምረት የዓለምን ሕዝብ ቁጥር ግማሽ ያህል፣ የዓለም አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርትን (GDP) 40 በመቶ ገደማ፣ እና የዓለምን ንግድ ሩብ ያህል ይወክላል። መጠኑ እጅግ ግዙፍ ነው። ብሪክስ ከእንግዲህ ተራ ጥምረት ብቻ አይደለም፤ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ ዋነኛ ኃይል እየሆነ ነው።   የብሪክስ አባል ሀገራት በአለምአቀፍ ደረጃ የተጽዕኖ አድማሳቸው የሰፋ፣ የዓለም አቀፍ የሀብት፣ የቴክኖሎጂ እና የሰፊ ገበያ ማዕከል መዳረሻ ናቸው። የኢትዮጵያ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ብዙ ሀገራት የሚመኙትን የዚህ ጥምረት አባል የመሆን መሻት እንድታሳካና ተጠቃሚ እንድትሆን አድርጓታል። በዚህ ሂደት ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ ለአፍሪካ ድምፅ በመሆን የአህጉሪቱን ጥያቄዎች እና የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎችን በቁርጠኝነት እየሠራች ትገኛለች። ከቀሪ የቤት ሥራዎች አንዱ ይህን ታሪካዊ ዕድል በመጠቀም የጥምረቱን ግዙፍ አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ሀብቱ በቀጥታ በሚገኝበት አካባቢ እንዲመረት ማድረግ ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና በማደግ ላይ ባለው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን ስትራቴጂካዊ አጋርነቶች እውን ለማድረግ ሙሉ ዝግጁነት አላት።   በማዕድን ዘርፍ ኢትዮጵያ ያሏትን እንደ ሊቲየም፣ ታንታለም እና ፖታሽ ያሉ ለዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና የኢነርጂ ሽግግር ወሳኝ የሆኑ ሀብቶችን በሀገር ውስጥ በማቀነባበር የኢንዱስትሪ እሴት ሰንሰለቱን ለመቀላቀል ሰፊ ሥራዎችን እየሠራች ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ የሀብት ባለቤት የሆኑ ሀገራት ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወጥተው የተጠናቀቁ ምርቶች አምራች እንዲሆኑ የሚያስችል የጋራ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ይፈጥራል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ያላትን ግዙፍ የታዳሽ ኃይል አቅም በመጠቀም አረንጓዴ እና ንጹህ የኢነርጂ አቅርቦትን ለሀገራት ማዳረስ ትችላለች። የውኃ፣ የጂኦተርማል እና የሶላር ኃይል ሀብቶችን በማልማት ለቀጣናው እና ለአጋሮች አስተማማኝ የኃይል ማዕከል ለመሆን የሚያስችል ጠንካራ መሠረት ይጥላል። ኢኮኖሚያዊ ትስስሩ ከሀብት ማውጣትና ማቀነባበር ባሻገር በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በተቋማዊ ጽናት ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል። የአሠራር ሥርዓቶቻችንን በማጠናከር እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)ን ጨምሮ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የአፍሪካን ልማታዊ እና ማህበራዊ ፍላጎቶች በትክክል እንዲያገለግሉ የጋራ ጥረቶችን ማቀናጀት ያስፈልጋል። ለዚህም ኢትዮጵያ ቁርጠኛ ናት። ለዘላቂ ዕድገት መረጋገጥ የፋይናንስ ሥርዓቶች ፍትሃዊ መሆን አለባቸው፤ በዚህ ረገድ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የዕዳ ጫና የሚያቃልል አስተማማኝ እና ፍትሃዊ የዕዳ እፎይታ ሒደት ማሳደግ ወሳኝ ነው። የብሪክስ መድረክ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን በመጠቀም ፍትሃዊ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲዘረጋ ጠንካራ ድምፅ ማሰማት የሚችልበት አቅም አለው። ከኢኮኖሚ ሽግግር ጎን ለጎን የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከምግብ ዋስትና እና ከዘላቂ ልማት ጋር ማስተሳሰር ይገባል። እንደ ኢትዮጵያ «የአረንጓዴ አሻራ» ተነሳሽነት ያሉ አሠራሮች ለአየር ንብረት ጽናት የሚሰጡትን አስተዋጽኦ በማስፋት የብሪክስ መድረክ የጋራ ትብብርን ወደ ተጨባጭ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ የጋራ ዕድገት ለመለወጥ የሚያስችል ታሪካዊ ዕድል ይፈጥራል። ኢትዮጵያም ይህን ዕድል የአፍሪካ ድምጽ በመሆን ጭምር መጠቀም ጀምራለች ።
የጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ትንሳኤ፡ የመደመር እሳቤ ትሩፋት
Sep 13, 2026 139
ኢትዮጵያ ሺህ ዘመናትን የተሻገሩ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አስመዝግባለች። በዓለም የሚዳሰስ ቅርስነት ዝርዝር ከሰፈሩ የኢትዮጵያ ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የአጼ ፋሲለደስ አብያተ መንግሥታት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የሐረር ጀጎል ግንብ፣ የጢያ ትክል ድንጋይ፣ የአዋሽና የኦሞ ሸለቆዎች፣ የኮንሶ ባህላዊ መልክዓ ምድር፣ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር፣ የራስ ዳሽንና የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮችና ሌሎችም ይገኙበታል።   በማይዳሰስ ቅርስነት ከሰፈሩ የኢትዮጵያ ቅርሶችም የመስቀል ደመራ በዓል፣ ፊቼ-ጫምባላላ፣ የገዳ ሥርዓት፣ ጥምቀት፣ ሹዋሊድ፣ የሶማሌ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት፣ የወላይታ ጊፋታና የመሳሰሉት ሕያው ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ማኅበረሰባዊ ትውፊቶችን ያካትታሉ። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ለዓለም ሕዝብ ያበረከቷቸው የመስህብ ሀብቶችም ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በገጽታ ግንባታና ለአካባቢ ልማት የሚያበረክቱት ዕድል በቀላሉ የሚታይ አይደለም። የመደመር መንግሥትም ይህንን የኢትዮጵያውያንን ሰፊ የቱሪዝም አቅም በመረዳት፣ ቱሪዝምን በብዝኅ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ዕይታው ውስጥ ትኩረት ከሰጣቸው የልማት መስኮች አንዱ አድርጎታል።   በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውም ቱሪዝም ከአምስቱ የብዝኅ የኢኮኖሚ አዕማድ አንዱ እንዲሆን በመደረጉ ዘርፉ የሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የበለጠ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጓል። ይህም ዘርፉ ከነበረበት ተለምዷዊና አዝጋሚ ዕድገት የሚላቀቅበትን ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት፣ ነባር ቅርሶች በማደስና በመጠገን ውጤታማ ሥራ ተሰርቷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገርና በገበታ ለትውልድ የመስህብ መዳረሻ ልማት የቱሪዝሙን ዘርፍ ማንሰራራት ያበስሩ ፕሮጀክቶች እውን ሆነዋል። ለአብነትም በገበታ ለሸገር በአዲስ አበባ የተገነቡ የወዳጅነት፣ አንድነትና የእንጦጦ ፓርኮች፤ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት የመዲናዋን ዓለም አቀፍ ገጽታ መቀየር ያስቻለ ምቹ ምኅዳር ፈጥረዋል።   በገበታ ለሀገርና ለትውልድ የመዳረሻ ልማት ፕሮጀክትም ጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ኮይሻ፣ ሐላላ ኬላ፣ ደንዲ ኢኮ ሎጂ፣ አርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት፣ ሎጎ፣ ሸበሌ ሪዞርት፣ ኒን ሊ ፓልም ሎጂ እና የመሳሰሉት እንዲገነቡ አስችሏል። ይህም የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን የከተማና ገጠር የቱሪዝም መዳረሻ አሰናስሎ በማልማት ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተውን ገንቢ ሚና መወጣት የሚችልበትን ከፍተኛ ዕድል ከፍቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በቱሪዝም ጉዳዮች ላይ ከኤንቢሲ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች በማስፋፋትና የመዳረሻ ብዝሃነትን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለይም ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት የኢኮኖሚ መነቃቃትን በመፍጠር በሥራ ዕድል ፈጠራም ጭምር ከአምስቱ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻዮች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።   በዚህም የጎብኚዎች ፍሰትን በመጨመርና የቆይታ ጊዜ በማራዘም የቱሪዝም ብዝኅ እመርታዊ ውጤቶች በየአካባቢው ኢኮኖሚን በማነቃቃት የገጠርና የከተማ ልማትን ለማስተሳሰር አዲስ ዕድል ፈጥረዋል ብለዋል። የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የቅርስ ዕድሳት ውጤታማ ሥራ የዘርፉን ዳግም ውልደት ያበሰሩ ለውጦችን አምጥቷል ብለዋል። ይህም የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ዘመናዊና የተሰናሰለ የከተማና ገጠር የመስህብ መዳረሻና እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ማስቻሉን ገልጸዋል።   የቱሪዝም አስጎብኚ ድርጅቶች እንደሚሉትም፤ የኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የመዳረሻ ልማትና የቅርስ ጥበቃ ውጤታማ ሥራ ለቱሪስቶች መዳረሻና ጉብኝት ምቹ ምኅዳርን በመፍጠር የሀገርን ገጽታ የገለጡ ናቸው። የታላቁ የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት እንቁ ሙሉጌታ እንደገለጹት፤ የቱሪዝም መሠረተ ልማት መስፋፋት የቱሪዝም ፍሰቱን በማሳደግ ተጠቃሚነትን እያሳደገ ነው።   የኤደን ላንድ ቱር ኤንድ ትራቭል ባለቤት እንዳልካቸው የምሩ፤ ለቱሪዝም ልማት የተሰጠው ትኩረት አማራጭ የመዳረሻ ስፍራዎች በማስፋፋት ለመስህብ መዳረሻ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎች እንደሚሉትም፤ በኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ተፈጥሯዊ መስህቦችን መጎብኘት የሚያስችሉ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል።   ከዓለም አቀፍ ጎብኝዎች መካከል ጀርመናዊው ሉካስ ኩፕፈርናጌል፤ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች የገነባቻቸው አስደማሚ የቱሪዝም መዳረሻዎች ሀገሪቱን አፍሪካዊት ግንባር ቀደም የቱሪስት ማዕከል የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።     ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ የሀገር ውስጥ ጎብኚ ምሕረት አሰፋ በበኩላቸው፤ የለሙት የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገርን ገጽታ የቀየሩ፣ ውብ፣ ጽዱና ዓለም አቀፍ የመስህብ ተወዳዳሪነትን የሚያጎለብቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።   ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በሃይማኖት፣ በባህልና በተፈጥሮ የታደለችውን ሀብት ወደ ኢኮኖሚያዊ አቅም የመቀየር ሥራ በስፋት እያከናወነች ይገኛል። የመደመር መንግሥት ቱሪዝምን የብዝኅ የኢኮኖሚ አዕማድ አካል በማድረግ የገነባቸው ማራኪ የመዳረሻ ስፍራዎች የዘርፉን ማንሰራራት በማጽናት ለኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተውን አቅም ለማጎልበት ያለመ ነው። ቀጣዩ የዘርፉ ጉዞም የኢትዮጵያን ቅርስና ተፈጥሯዊ ጸጋ በመጠበቅ የመዳረሻ ብዝኅነትን በማስፋፋትና የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ ቱሪዝምን ከተስፋ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ውጤት የሚያሻግር ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፦
Sep 13, 2026 197
የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና ይጫወታል ሀገራት ቀውሶች ከመከሰታቸው በፊት የመቋቋም አቅም ሊገነቡ ይገባል።በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ ፈተናን መቋቋም የሚያስችሉ ስርዓቶችን እየገነባች ትገኛለች መንግስት በምግብ ዋስትና ላይ ባከናወነው ተግባር ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ ስንዴ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ ወጥታ ራሷን ችላለች ኢትዮጵያ ለታቀደው የብሪክስ የሰብል ልውውጥ ማዕቀፍ (BRICS Grain Exchange) እንደ አምራችም ሆነ አቅራቢ ሆና ለመሳተፍ ዝግጁ ናት ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የሚያጋጥሙ ቀውሶችን ለመቋቋም የሀገር ውስጥ የማምረት አቅሟን እያሳደገች ነው። የፋርማሲዩቲካልና የመድኃኒት ማምረቻዎችንም እያስፋፋች ነው በቴክኖሎጂው ዘርፍ ዲጂታል መሠረተ ልማት፣ ዲጂታል መታወቂያ (Digital ID)፣ የክፍያ ሥርዓቶች እና የመረጃ ልውውጥ በስፋት እየተገነቡ ነው መረጃዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ በሕግ አግባብ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ነው።ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ይህንን ለውጥ የበለጠ ያጠናክረዋል በቀጣዩ ትውልድ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ይበልጥ ሰዎችን ማገልገል፣ ብዙ ቋንቋዎችን መረዳት እና ሰፊ የሰው ልጅ እውቀት ማካተት አለበት አፍሪካ የነገውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን በባለቤትነት ለመምራት የምርምር፣ የኮምፒውቲንግ አቅም፣ ክህሎት እና ተቋማት ያስፈልጋሉ ኢትዮጵያ አፍሪካን የሚወክል የቴክኖሎጂ አቅም ለመገንባት ከብሪክስ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት አላት አፍሪካ የበርካታ ማዕድናት ሀብት ባለቤት ናት።የብሪክስ አባል ሀገራት ደግሞ የካፒታል፣ የቴክኖሎጂ እና የገበያ አማራጭ አላቸው ኢትዮጵያ በማዕድናት፣ በታዳሽ ኢነርጂ እና እያደገ ያለውን የኢንዱስትሪ አቅሟን መሰረት ባደረገ መልኩ አጋርነቶችን ለመፍጠር ዝግጁ ናት ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የምታቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል ለሀገራቱ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ሀገራት በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ያላቸው ውክልና ፍትሃዊና ውክልናውም ተጨባጭ ውጤት ማምጣት አለበት
የአውሮፓ ህብረትና አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርምና አካታች ልማት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ይቀጥላሉ
Sep 13, 2026 138
አዲስ አበባ፤መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):-የአውሮፓ ህብረትና አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርምና አካታች ልማት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኤምስበርገር ገለጹ። የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ለጀመረችው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ማሻሻያና ሌሎች የልማት ሥራዎች ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኤምስበርገር ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረች ወዲህ አስደናቂ ውጤት አስመዝግባለች። መንግሥት የተሟላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችን ተግባራዊ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል። የኢኮኖሚ ማሻሻያው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው፣ ትግበራውን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ንግድ በማስፋት አህጉራዊ አቅማቸውን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል። ጠንካራ የኢኮኖሚ ትስስር መፍጠር ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እና ለዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የአውሮፓ ህብረት እና አባል ሀገራቱ ለኢትዮጵያ የልማት ግቦች ስኬት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው፤ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በኃይል፣ በጤና እና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዘርፎች የላቀ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ፣ የአህጉሪቱ የዲፕሎማሲ፣ የትብብር እና የፖሊሲ ዋና ማዕከል መሆኗን ጠቅሰው፤ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታዋንም አንስተዋል። የአውሮፓ ህብረት እና ኢትዮጵያ በጠንካራ እና አስተማማኝ አጋርነት ላይ የተመሰረተ መልካም ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ለዚህም ህብረቱና አባል ሀገራቱ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፦
Sep 13, 2026 197
የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና ይጫወታል ሀገራት ቀውሶች ከመከሰታቸው በፊት የመቋቋም አቅም ሊገነቡ ይገባል።በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ ፈተናን መቋቋም የሚያስችሉ ስርዓቶችን እየገነባች ትገኛለች መንግስት በምግብ ዋስትና ላይ ባከናወነው ተግባር ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ ስንዴ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ ወጥታ ራሷን ችላለች ኢትዮጵያ ለታቀደው የብሪክስ የሰብል ልውውጥ ማዕቀፍ (BRICS Grain Exchange) እንደ አምራችም ሆነ አቅራቢ ሆና ለመሳተፍ ዝግጁ ናት ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የሚያጋጥሙ ቀውሶችን ለመቋቋም የሀገር ውስጥ የማምረት አቅሟን እያሳደገች ነው። የፋርማሲዩቲካልና የመድኃኒት ማምረቻዎችንም እያስፋፋች ነው በቴክኖሎጂው ዘርፍ ዲጂታል መሠረተ ልማት፣ ዲጂታል መታወቂያ (Digital ID)፣ የክፍያ ሥርዓቶች እና የመረጃ ልውውጥ በስፋት እየተገነቡ ነው መረጃዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ በሕግ አግባብ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ነው።ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ይህንን ለውጥ የበለጠ ያጠናክረዋል በቀጣዩ ትውልድ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ይበልጥ ሰዎችን ማገልገል፣ ብዙ ቋንቋዎችን መረዳት እና ሰፊ የሰው ልጅ እውቀት ማካተት አለበት አፍሪካ የነገውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን በባለቤትነት ለመምራት የምርምር፣ የኮምፒውቲንግ አቅም፣ ክህሎት እና ተቋማት ያስፈልጋሉ ኢትዮጵያ አፍሪካን የሚወክል የቴክኖሎጂ አቅም ለመገንባት ከብሪክስ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት አላት አፍሪካ የበርካታ ማዕድናት ሀብት ባለቤት ናት።የብሪክስ አባል ሀገራት ደግሞ የካፒታል፣ የቴክኖሎጂ እና የገበያ አማራጭ አላቸው ኢትዮጵያ በማዕድናት፣ በታዳሽ ኢነርጂ እና እያደገ ያለውን የኢንዱስትሪ አቅሟን መሰረት ባደረገ መልኩ አጋርነቶችን ለመፍጠር ዝግጁ ናት ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የምታቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል ለሀገራቱ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ሀገራት በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ያላቸው ውክልና ፍትሃዊና ውክልናውም ተጨባጭ ውጤት ማምጣት አለበት
ሀገራዊ ምክክሩ አዲስ ምዕራፍ የከፈተና መልካም ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው
Sep 13, 2026 167
አዳማ፤መስከረም 3/2019(ኢዜአ)፡-ሀገራዊ ምክክሩ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ከመሆኑም በላይ መልካም ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ። ኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቁ ሀገራዊ ልዩነቶችን፣ የፖለቲካ አለመግባባቶችን እና ውስብስብ የታሪክ ውዝግቦችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለመውን የሀገራዊ ምክክር አካሄዳለች። ሂደቱም ለጋራ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እና መልካም ተሞክሮ የሚወሰድበት ሆኖ ተጠናቋል። የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት ሀገራዊ ምክክሩ ዜጎች ችግሮቻቸውን በአፈሙዝ ከመፍታት ይልቅ ተመካክረው ልዩነታቸውን በማጥበብ ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ነው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ ፓስተር በየነ ደሳላኝ በሰጡት አስተያየት ሀገራዊ ምክክሩ የህዝብ ውክልና ያላቸው አካላት በጋራ ሆነው በሀገራዊ ችግሮች ላይ በሰከነና በሰለጠነ መንገድ ተወያይተው በስኬት ማጠናቀቃቸው አስደሳችና የሚያኮራ ተግባር ነው። ሀገራዊ ምክክሩ የተሳካለት ተልእኮ ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው በተለይ አስቸጋሪ፣ ውስብስብ እና ግራ የሚያጋቡ ሀሳቦችን ጭምር ወደ አንድ መድረክ በማምጣት ዘላቂ መፍትሄ ይሰጣል የሚል ተስፋ መሰነቃቸውን አውስተዋል። ምክክር ማለት ክርክር አይደለም ያሉት ፓስተር በየነ፤ ይልቁንስ ለችግሮቻችን እልባት ለመስጠት ሁሉንም አካል የሚያግባባ እና የመፍትሄ ሀሳብ የሚፈልቅበት መድረክ መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም በምክክሩ የተደረሰበት አጀንዳ በቀጣይ ጊዜያት ወደ ተግባር ሲቀየር የህዝቦችን ዘመናት የተሻገረ ችግር የሚገታ ዓይነተኛ መሳሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል አብራርተዋል።   የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈጻሚና የኦሮሚያ ክልል አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ተሰማ በበኩላቸው፤ የምክክር ሂደቱ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሃይማኖት ተቋማትን እንዲሁም ትጥቅ ፈትተው በሰላም የተመለሱ አካላትን ጭምር ባሳተፈና ባካተተ መልኩ መካሄዱ የህዝብን አመኔታ ያጎናጸፈና ለሀገሪቱ ብሩህ ተስፋን የሚፈነጥቅ እንደሆነ አስታውቀዋል። በምክከሩ የሁሉም የሀሳብ ልእልና በሚገባ የተንጸባረቀበት በመሆኑም በሀገራዊ አጀንዳ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ምቹ መደላድል እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል። ይህም በሀገሪቱ የተረጋጋ የፖለቲካ ምህዳር ከመገንባት ባለፈ ለሌላው ዓለም ምርጥ ተሞክሮና በተምሳሌትነት የሚጠቀስ እንደሚያደርገው አውስተዋል። በአጠቃላይ በሰላም፣ ፍትሕ፣ የሕግ የበላይነት፣ እኩልነትና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በሰፊው የተመከረበት ሁነኛ ምክክር በመሆኑ ለሀገራዊ አጀንዳ ዘላቂ መፍትሄ ይዞ ይመጣል ነው ያሉት።   በኢዜማ የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተባባሪ ወይዘሮ ሠናይት በላይ በበኩላቸው ሀገራዊ ምክክሩ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት፣ ዕርቅን ለማውረድ እና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከርና ለማጽናት ምትክ የለሽ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ምክክሩ ከዚህ በፊት መንግሥትን ለመቃወም አፈሙዝ የመጀመሪያ አማራጭ ተደርጎ ሲወሰድ የነበረውን የዘመናት ልምምድ በመግታት ለችግሮች መንስዔ ለሆኑ ጉዳዮቻችን ሁሉ የውይይት ባሕልን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ነው ብለዋል። ሀገራዊ ምክክሩ ፍጹም ገለልተኛ ሆኖ መካሄዱን የገለጹት አስተያየት ሰጪዎቹ ይህም ዜጎች የጋራ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች በጥልቀት ተመካክረው ይበጃል ያሉትን ምክረ ሀሳብ በማስቀመጥ ስኬታማ ሀገራዊ ምክክር ማካሄዳቸው ለመጪው ትውልድ ብሩህ ተስፋን ያንጸባርቃል ባይ ናቸው ።
18ተኛ የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ውሎ
Sep 12, 2026 406
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ‎በ18ተኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ሕንድ ኒው ዴልሂ አቅንተው፣ ዛሬ መስከረም 2 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ‘‘ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት’’ በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ በዋለው የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል። ‎ ‎ጉባኤው በመጀመሪያ ቀን ውሎ “አካታች ዓለም አቀፍ አስተዳደር እና ባለ ብዙ ወገን ትብብርን ማጠናከር” በሚል ዓቢይ ጉዳይ ላይ የተወያየ ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ አስተዳደር አካታችና ሚዛናዊ የሆነ የሀገራት ተሳትፎ ብሎም ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጥ እንደሚገባ ተጠቁሟል። ‎ ‎በተያያዘም ከተመሰረት 20ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው ይህ ጥምረት በሚቀጥሉት ዓመታት ይበልጥ የተደራጀ፣ ባለብዙ ወገን ትብብሮችን ያጠናከረ፣ ፍትሃዊ፣ አሳታፊና አካታች የሆነ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ እንዲሆን ይበልጥ እንደሚሰራ ተመላክቷል። ‎ ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጉባኤው ባደረጉት ንግግርም፣ ችግሮች ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ጽናትን ማጠናከር እና የአስተዳደር ስርዓት አካል የማድረግን መሰረታዊነት አመላክተው ይህ ጽኑ ስርዓት ግንባታ ኢትዮጵያ በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እንድትበረታ እንዳደረጋት ጠቁመዋል። ‎ ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለውም በምግብ ከውጭ ከሚገባ የስንዴ ጥገኝነት ተላቃ ራሷን መቻሏ፣ በጤና ቅድመ መከላከል ፖሊሲ አካል ሆኖ የህክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች ማምረትን፣ የዲጂታል ስርዓት ሽግግርንና ደኅንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀምን፣ የአኅጉሪቱን የጥናትና ምርምር ብሎም ፈጠራ አዳጊ ፍላጎት ሊያሳካ የሚችል የመደመር ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታን የጠቆሙ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በእነዚህና መሰል የልማት ትብብሮችም ከጥምረቱ አባል ሀገራት ጋር አብሮ ለመስራት ያላትን ተነሳሽነት ገልጸዋል። ‎ ‎ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 2027 COP 32 ጉባኤን በአዲስ አበባ ለማስተናገድ የተጣለባትን ኃላፊነት በተግባርና በተስፋ እንደምትወጣው በመግለጽ፣ እስከ COP 32 ድረስ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ወደ ስምምነት የሚቀይር "የብሪክስ አስተባባሪ መስመር" እንዲቋቋም ሃሳብ አቅርበዋል። ‎ኢትዮጵያ ለዚህ አጋርነት የበኩሏን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። ‎ ‎ከመሪዎቹ ጉባኤ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአባል ሀገራቱና አጋር ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ የሀገራቱ ትብብር ዙሪያ ፍሬያማ ውይይቶችን ያካሄዱ ሲሆን፤ በኢንቨስትመንት፣ ቀጣናዊ ጉዳዩች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታና ክህሎት፣ ቱሪዝም፣ የማዕድን ልማት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ሊኖሩ ስለሚችሉ ትብብሮች በጥልቀት ተወያይተዋል። ‎ ‎ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ስርዓት ማሻሻያ ባካሄደችው አመርቂ ትግበራዎች፣ በታዳሽ ሀይል መስፋፋት እና የኢንዱስትሪ መሠረት ልማቶቿ፣ በግብርና ስርዓት ማሻሻያ እየተመዘገቡ ያሉ የምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ግዙፍ የአየር መንገድ ግንባታ የአኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ንግድ ትሥሥርን ለማስፋፋት በምታደርገው ጥረት በጥምረቱ ለሚነሱ ተያያዥ የውይይት አጀንዳዎች መሪ ተዋናይ እንድትሆን ያስችላታል። ‎ ‎ #PMOEthiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ
Sep 12, 2026 365
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ‎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‎ውይይታችን በመከላከያ እና ደኅንነት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኖሎጂ መስኮች ያለንን ትብብር ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል።   እንዲሁም የትምህርት ልምድ ልውውጦችን ማስፋት፣ በባህል እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል ነው ያሉት። ‎ ‎በተጨማሪም ለኮፕ 32 በሚደረገው ዝግጅት ያለን አጋርነት ጨምሮ ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውንም አስታውቀዋል። በወል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረቱ የንግድ እና የኢኮኖሚ ልውውጦችን ይበልጥ ለማስፋፋትም በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን አረጋግጠዋል።

ማህበራዊ
በትምህርት መሰረተ ልማት ላይ እየተከናወነ ያለው ልማት በትምህርት ተደራሽነት ላይ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው
Sep 12, 2026 342
ነገሌ ቦረና ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን በትምህርት መሰረተ ልማት ላይ እየተከናወነ ያለው ልማት በጥራትና ተደራሽነት ላይ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን የዞኑ ትምህርት ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ በዞኑ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን የተማሪ ክፍል ጥምርታን ለማመጣጠን 18 ቅድመ መደበኛ እና አምስት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸው ታውቋል። በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ቦረና ዞን የትምህርት ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ዲዳ ገልገሎ፤ በአዲሱ ዓመት ለትምህርት የተደረገውን ዝግጅት በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።   በማብራሪያቸውም ለትምህርት ሴክተሩና አጠቃላይ ለመማር ማስተማሩ ሂደት በተለይም ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የተቀናጀ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል። በመሆኑም በአዲሱ የትምህርት ዘመን ከ189 ሺህ 340 በላይ መደበኛ ተማሪዎችን ለመቀበል የተሟላ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። ለአዲሱ የትምህርት ዘመን የተማሪ ክፍል ጥምርታን ለማመጣጠን 18 ቅድመ መደበኛ እና አምስት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውንም ጠቁመዋል። የትምህርት ቤቶቹ መገንባት በ2019 የትምህርት ዘመን ከ1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል መሆኑንም ጠቅሰዋል። በድምሩ ምስራቅ ቦረና ዞን በትምህርት መሰረተ ልማት ላይ እየተከናወነ ያለው ልማት በጥራትና ተደራሽነት ላይ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ይገኛል ብለዋል። የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ኑራ አብዱባ፤ በመንግስት ለትምህርት ሴክተሩ የተሰጠው ትኩረት ልጆቻችን የተሻለ የትምህርት እድል እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።   አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን ከመገንባት በተጨማሪ የቆዩ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በተደረገው የልማት ስራ የሁላችንም ተሳትፎ ተጨምሮበት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ አስደስቶናል ብለዋል። ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ መቶ አለቃ አማረ አስራት፤ የትምህርት ቤት ግንባታ የትውልድ ግንባታ መሰረት በመሆኑ የሁላችንም ተሳትፎ የግድ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በህዝቡና በመንግስት ጠንካራ ትብብርም በዞኑ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና አዲስ በመገንባት ለመማር ማስተማሩ ዝግጁ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል። የትምህርት ተደራሽነትን ከማስፋት በተጨማሪ ለግብአት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ በንቃት መሳተፋቸውን አንስተው ጥረታችን ይቀጥላል ብለዋል።
በትምህርት ዘርፍ የተወሰዱ ውጤታማ የማሻሻያ እርምጃዎች በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው
Sep 12, 2026 503
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ)፦በትምህርት ዘርፍ የተወሰዱ ውጤታማ የማሻሻያ እርምጃዎች በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። የትምህርት ሚኒስትሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ መንግሥት የተሟላ ዜጋ የማፍራት፣ የግብረገብና የእውቀት መለኪያዎችን የማጠናከር እንዲሁም የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶችን የጥራት ልዩነት በማጥበብ የትምህርት አሰጣጡን ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገር ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን አከናውኗል። በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ጥራት ያለውና በእውቀት የተካነ ትውልድ ለማፍራት የተከናወኑት ስራዎች ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡   የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ታማኝነትን ለማረጋገጥ ሲባል የ12ኛ ክፍል ፈተናዎች በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እንዲሰጡ መደረጉ የትምህርት አሰጣጡን እውነተኛ ገጽታ ማሳየት ማስቻሉን ጠቁመዋል። ከውጤት መሻሻል አንጻር በተደረጉ የማሻሻያ ተግባራትና በትምህርት ጥራት ቁጥጥር በ2018 የትምህርት ዘመን ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች ምጣኔ ወደ 12 ነጥብ 8 በመቶ ከፍ ማለቱን አስረድተዋል። ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች በልዩ ድጋፍና ክትትል በማስተማር ለሀገር ዕድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልጸዋል። ሚኒስቴሩ በ2018 የትምህርት ዘመን በቦንጋ፣ በጅግጅጋ፣ በጋምቤላ፣ በወሊሶና ቡኢ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩን ጠቅሰዋል፡፡ ይህንን ውጤታማ አሰራር ለማስፋት በያዘው ዕቅድ መሰረት በ2019 የትምህርት ዘመን የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ቁጥር ወደ ዘጠኝ ለማሳደግ በአርባ ምንጭ፣ በባህርዳር፣ በድሬዳዋ እና በአሶሳ ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ 13 አዳዲስ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል።   ከትምህርት ግብዓትና ቴክኖሎጂ አንጻርም የኮምፒውተር ላቦራቶሪዎችን በማስፋፋት፣ የዲጂታል መጽሐፍትንና የኢንተርኔት መሠረተ ልማቶችን ወደ ትምህርት ቤቶች በመዘርጋት የተማሪዎችን የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት የማሳደግ ስራ መከናወኑን ጠቁመዋል፡፡ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ 146 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ሀብት በገንዘብና በዓይነት ማሰባሰብ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ሀብት 14 ሺህ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለተማሪዎች ምቹ ሆነው መታደሳቸውን ጠቁመዋል፡፡ በሌላ በኩል የተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ የማቋረጥ መጠንን ለመቀነስና የመማር ብቃታቸውን ለማሳደግ በተዘረጋው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደ 8 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ወደ ራስ ገዝነት ለማሸጋገር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምደባም በውድድር፣ በእውቀትና በችሎታ ላይ ብቻ በተመሰረተ ግልጽ አሰራር መዘርጋቱን ጠቁመዋል። ከተከናወኑት የሥርዓተ-ትምህርት ክለሳዎች፣ የግብረገብና የታሪክ ትምህርቶች መካተት እንዲሁም ከመዋቅራዊ ሪፎርሞች አንጻር ሀገሪቱን በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ዘርፎች በብቃት ሊመሩ የሚችሉ ተወዳዳሪ ተማሪዎችን ማፍራት የሚያስችል ትክክለኛ መሠረት ተጥሏል ብለዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ሆነዋል
Sep 12, 2026 207
ደሴ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ) ፦ በደቡብ ወሎ ዞን የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እስካሁን ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የዞኑ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ። በመምሪያው የዜጎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ንቅናቄና ተሳትፎ ቡድን መሪ ምስጋናው ደምሴ፤ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ በዞኑ በክረምቱ የተከናወኑ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ገልጸዋል።በዞኑ በክረምቱ ከ1ጥብ 2 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞች ነፃ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል። በዚህም የቤት እድሳትና ግንባታ፣ የግብርና ስራዎችን የማገዝ፣ ለተማሪዎች የደብተርና ሌሎች ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ እንዲሁም የደም ልገሳና ሌሎችንም ማህበራዊ አገልግሎቶችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ ብለዋል።   በእስካሁኑ አገልግሎታቸው ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቁመው ይህም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። ከአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች መካከል በዞኑ ቃሉ ወረዳ የሚኖሩት አርሶ አደር ደሳለኝ አህመድ፤ ከአንድ ሄክታር በላይ መሬታቸው በበጎ ፈቃደኞች ታርሶ በዘር የተሸፈላቸው መሆኑን ተናግረዋል።   የእርሻ ማሳቸውን በዘር ለመሸፈን አቅመ ደካማ በመሆናቸው ይቸገሩ እንደነበር አንስተው በተደረገላቸው ድጋፍና መልካም ተግባር ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል። በዞኑ ተሁለደሬ ወረዳ የሚኖሩት ወይዘሮ ሰዓዳ የሱፍ፤ የመኖሪያ ቤታቸው በእርጅና ምክንያት በተለይም በክረምት ለዝናብና ለብርድ ይዳርጋቸው እንደነበር አስታውሰው አዲስ ቤት ተሰርቶ የተሰጣቸው በመሆኑ መደሰታቸውን ተናግረዋል። በአዲስ ዓመት በተሰራላቸው ቤት አዲስ ህይወት መኖር መጀመራቸውንም ገልጸው ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በክልሉ የወባ ወረርሽኝን ቀድሞ ለመከላከል የኬሚካል ርጭትና የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ እየተከናወነ ነው
Sep 12, 2026 256
ባህር ዳር፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የክረምት መውጣትን ተከትሎ ሊከሰት የሚችል የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል የኬሚካል ርጭትና የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንክር ለኢዜአ እንደገለጹት በዘንድሮ የክረምት ወቅት የተስተዋለው የዝናብ ሥርጭት መቆራረጥ ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል።   በመሆኑም ቢሮው በክልሉ የወባ በሽታ ስርጭት በስፋት ሊከሰትባቸው ይችላል ተብለው በተለዩ 17 ወረዳዎች ላይ የኬሚኬል ርጭት እያካሄደ መሆኑን ገልፀዋል። የኬሚካል ‎ርጭቱ ከነሀሴ ወር 2018 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ቤት ለቤት እየተካሄደ ሲሆን ለዚህም 224 ሺህ 930 ኪሎ ግራም የፀረ ወባ ኬሚካል ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል ብለዋል። በዚህም 471 ሺህ 578 መኖሪያ ቤቶች ላይ ርጭት እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት አቶ ዳምጤ፣ የኬሚካል ርጭት ሥራው 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚጠጉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ከወባ በሽታ ይታደጋል ብለዋል። እንደእሳቸው ገለጻ ‎ከኬሚካል ርጭቱ በተጨማሪ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበረሰቡን በማስተባበር ለወባ መራቢያ አመቺ የሆኑ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን ሥራ ተከናውኗል። ‎ከተያዘው መስከረም ጀምሮ እስከ ታህሳስ ወር የወባ ትንኝ በስፋት የሚራባበት ወቅት መሆኑን አቶ ዳምጤ ገልጸው፣ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተጀመረው የኬሚካል ርጭትና የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።   በክልሉ "የአርብ ጠንካራ እጆች በሽታን ይገታሉ" በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ በየሳምንቱ ይቀጥላል ብለዋል። ህብረተሰቡ ከአካባቢ ቁጥጥር ሥራው ጎን ለጎን የወባ በሽታ መከላከያ አልጋ አጎበርን በአግባቡ መጠቀም እንዳለበት ገልጸው፣ የወባ በሽታ ምልክት ሲያይም ወደጤና ተቋማት ፈጥኖ በመሄድ እንዲታከም አሳስበዋል። በደቡብ ጎንደር ዞን የፈገራ ወረዳ አርሶ አደር አለሙ ሙጬ በበኩላቸው እንዳሉት፣ የወባ በሽታን ቀድመው ለመከላከል በቤት ውስጥ የአልጋ አጎበር ከመጠቀም ባለፈ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማዳፈንና የማፋሰስ ሥራ እያከናወኑ ይገኛሉ። የክረምት ዝናብ መቆራረጥን ተከትሎ የወባ በሽታ እንዳይቀሰቀሰ የአካባቢ ቁጥጥር ስራን በየጊዜው እያከናወኑ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደር ዳኘ ዋለ ናቸው። ‎ቀደም ሲል የተሰጣቸውን የአልጋ አጎበር በአግባቡ በመጠቀም ቤተሰቦቻቸውን ከወባ በሽታ መታደግ እንደቻሉም ገልፀዋል።
ኢኮኖሚ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አባልና አጋር ሀገራትን ባሳተፈው የብሪክስ ፕላስ የምክክር መድረክ ላይ፤ጠንካራ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል
Sep 13, 2026 123
አዲስ አበባ፤መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):-አባልና አጋር ሀገራትን ባሳተፈው የብሪክስ ፕላስ የምክክር መድረክ ላይ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠንካራ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነት ይበልጥ እንዲሰፋ እንዲሁም ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ትስስርን ለማሳደግ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል። ‎‎በዚህ አውድም፣ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አድማሱን በመላው አፍሪካ እንዲያስፋፋ የባንኩን ቢሮ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ በሙሉ አቅም ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ‎‎በተጨማሪም በአዲስ አበባ የሚካሄደው ኮፕ 32 በብሪክስ ሙሉ ድጋፍ ለአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎች እና ለዘላቂ ልማት መፋጠን ሁሉንም ድምፆች የሚያሰባስብ ሁሉን አቀፍ መድረክ ሆኖ ማገልገል እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል። ‎‎#PMOEthiopia
የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ ተስተጋብተዋል-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Sep 13, 2026 132
አዲስ አበባ፣መስከረም 3/ 2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ መስተጋባታቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡ አገልግሎቱ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ብዙ ሀገራት የሚመኙትን የብሪክስ አባል የመሆን መሻት እንድታሳካና ተጠቃሚ እንድትሆን አስችሏታል ብሏል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ የኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ ተስተጋብተዋል! ብሪክስ ወደ ሰፊ ጥምረት አድጓል፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አሁን 11 ሙሉ አባላት ያሉት ሲሆን በሩሲያ ካዛን ጉባኤ ይፋ የተደረጉ 10 አጋር አገራትንም በልዩ የአጋርነት ማዕቀፍ በማካተት ተጽእኖውን አጠናክሯል። የብሪክስ ጥምረት የዓለምን ሕዝብ ቁጥር ግማሽ ያህል፣ የዓለም አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርትን (GDP) 40 በመቶ ገደማ፣ እና የዓለምን ንግድ ሩብ ያህል ይወክላል። መጠኑ እጅግ ግዙፍ ነው። ብሪክስ ከእንግዲህ ተራ ጥምረት ብቻ አይደለም፤ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ ዋነኛ ኃይል እየሆነ ነው።   የብሪክስ አባል ሀገራት በአለምአቀፍ ደረጃ የተጽዕኖ አድማሳቸው የሰፋ፣ የዓለም አቀፍ የሀብት፣ የቴክኖሎጂ እና የሰፊ ገበያ ማዕከል መዳረሻ ናቸው። የኢትዮጵያ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ብዙ ሀገራት የሚመኙትን የዚህ ጥምረት አባል የመሆን መሻት እንድታሳካና ተጠቃሚ እንድትሆን አድርጓታል። በዚህ ሂደት ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ ለአፍሪካ ድምፅ በመሆን የአህጉሪቱን ጥያቄዎች እና የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎችን በቁርጠኝነት እየሠራች ትገኛለች። ከቀሪ የቤት ሥራዎች አንዱ ይህን ታሪካዊ ዕድል በመጠቀም የጥምረቱን ግዙፍ አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ሀብቱ በቀጥታ በሚገኝበት አካባቢ እንዲመረት ማድረግ ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና በማደግ ላይ ባለው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን ስትራቴጂካዊ አጋርነቶች እውን ለማድረግ ሙሉ ዝግጁነት አላት።   በማዕድን ዘርፍ ኢትዮጵያ ያሏትን እንደ ሊቲየም፣ ታንታለም እና ፖታሽ ያሉ ለዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና የኢነርጂ ሽግግር ወሳኝ የሆኑ ሀብቶችን በሀገር ውስጥ በማቀነባበር የኢንዱስትሪ እሴት ሰንሰለቱን ለመቀላቀል ሰፊ ሥራዎችን እየሠራች ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ የሀብት ባለቤት የሆኑ ሀገራት ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወጥተው የተጠናቀቁ ምርቶች አምራች እንዲሆኑ የሚያስችል የጋራ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ይፈጥራል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ያላትን ግዙፍ የታዳሽ ኃይል አቅም በመጠቀም አረንጓዴ እና ንጹህ የኢነርጂ አቅርቦትን ለሀገራት ማዳረስ ትችላለች። የውኃ፣ የጂኦተርማል እና የሶላር ኃይል ሀብቶችን በማልማት ለቀጣናው እና ለአጋሮች አስተማማኝ የኃይል ማዕከል ለመሆን የሚያስችል ጠንካራ መሠረት ይጥላል። ኢኮኖሚያዊ ትስስሩ ከሀብት ማውጣትና ማቀነባበር ባሻገር በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በተቋማዊ ጽናት ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል። የአሠራር ሥርዓቶቻችንን በማጠናከር እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)ን ጨምሮ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የአፍሪካን ልማታዊ እና ማህበራዊ ፍላጎቶች በትክክል እንዲያገለግሉ የጋራ ጥረቶችን ማቀናጀት ያስፈልጋል። ለዚህም ኢትዮጵያ ቁርጠኛ ናት። ለዘላቂ ዕድገት መረጋገጥ የፋይናንስ ሥርዓቶች ፍትሃዊ መሆን አለባቸው፤ በዚህ ረገድ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የዕዳ ጫና የሚያቃልል አስተማማኝ እና ፍትሃዊ የዕዳ እፎይታ ሒደት ማሳደግ ወሳኝ ነው። የብሪክስ መድረክ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን በመጠቀም ፍትሃዊ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲዘረጋ ጠንካራ ድምፅ ማሰማት የሚችልበት አቅም አለው። ከኢኮኖሚ ሽግግር ጎን ለጎን የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከምግብ ዋስትና እና ከዘላቂ ልማት ጋር ማስተሳሰር ይገባል። እንደ ኢትዮጵያ «የአረንጓዴ አሻራ» ተነሳሽነት ያሉ አሠራሮች ለአየር ንብረት ጽናት የሚሰጡትን አስተዋጽኦ በማስፋት የብሪክስ መድረክ የጋራ ትብብርን ወደ ተጨባጭ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ የጋራ ዕድገት ለመለወጥ የሚያስችል ታሪካዊ ዕድል ይፈጥራል። ኢትዮጵያም ይህን ዕድል የአፍሪካ ድምጽ በመሆን ጭምር መጠቀም ጀምራለች ።
የአውሮፓ ህብረትና አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርምና አካታች ልማት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ይቀጥላሉ
Sep 13, 2026 138
አዲስ አበባ፤መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):-የአውሮፓ ህብረትና አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርምና አካታች ልማት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኤምስበርገር ገለጹ። የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ለጀመረችው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ማሻሻያና ሌሎች የልማት ሥራዎች ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኤምስበርገር ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረች ወዲህ አስደናቂ ውጤት አስመዝግባለች። መንግሥት የተሟላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችን ተግባራዊ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል። የኢኮኖሚ ማሻሻያው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው፣ ትግበራውን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ንግድ በማስፋት አህጉራዊ አቅማቸውን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል። ጠንካራ የኢኮኖሚ ትስስር መፍጠር ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እና ለዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የአውሮፓ ህብረት እና አባል ሀገራቱ ለኢትዮጵያ የልማት ግቦች ስኬት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው፤ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በኃይል፣ በጤና እና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዘርፎች የላቀ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ፣ የአህጉሪቱ የዲፕሎማሲ፣ የትብብር እና የፖሊሲ ዋና ማዕከል መሆኗን ጠቅሰው፤ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታዋንም አንስተዋል። የአውሮፓ ህብረት እና ኢትዮጵያ በጠንካራ እና አስተማማኝ አጋርነት ላይ የተመሰረተ መልካም ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ለዚህም ህብረቱና አባል ሀገራቱ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያና እስራኤል ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጎልበት ምቹ ምኅዳር ፈጥሯል - አምባሳደር አብርሃም ንጉሤ (ዶ/ር) 
Sep 13, 2026 205
አዲስ አበባ፤ መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያና እስራኤል ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጎልበት ምቹ ምኅዳር መፍጠሩን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ። አምባሳደር አብርሃም ንጉሤ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያና እስራኤል ግንኙነት ታሪክን ከዘመናዊ የዲፕሎማሲ ትብብር ጋር በማሰናሰል በሁሉም መስክ እየጎለበተ የመጣ ነው። በአሁኑ ወቅትም በመንግሥት ለመንግሥት፣ በግሉ ዘርፍ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም መንግሥታዊ ባልሆኑ የልማት ድርጅቶች አጋርነት በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ትብብር መፈጠሩን ገልጸዋል። ይህም የሀገራቱን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በማጎልበት በኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ የትብብር መስኮችን በማስፋት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት አስቻይ ምህዳር መፍጠሩን ተናግረዋል። የኢትዮጵያና እስራኤል ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የእርስ በእርስ ይፋዊ የሥራ ጉብኝትም የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት መግባባትን በመፍጠር ጉልህ ሚና እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል። የእስራኤል በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አመልክተው፤ ከነዚህ መካከል በጤናው ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠቃሽ መሆናቸውን አመልክተዋል። የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የልምድ ልውውጥ በማድረግና በተለያዩ መስኮች ላይ የሙያተኞችን አቅም በሥልጠና በማብቃት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር ተችሏልም ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም ከ100 በላይ የሚሆኑ የእስራኤል ኩባንያዎች በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች ተሰማርተው እንደሚገኙ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ለእስራኤል የምሥራቅ አፍሪካ ቁርጠኛ አጋር እንደሆነች ሁሉ እስራኤልም ለኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ቁርጠኛ ወዳጅ መሆኗን አስረድተዋል። የሀገራቱን የጋራ ተጠቃሚነት ለማላቅ በሚደረገው ጥረትም የኢትዮጵያ አየር መንገድና የእስራኤል የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ቁልፍ ሚና እየተወጡ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ከአዲስ አበባ እስከ ቴል አቪቭ የአራት ሰዓታት የቀጥታ በረራ ብቻ የሚወስድ መሆኑም የእርስ በእርስ የንግድና አገልግሎት ልውውጡን በአጭር ሰዓታት ለማሳለጥ መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን አብራርተዋል። ይህም እስራኤል የኢትዮጵያ የግብርና ምርቶችን ኢትዮጵያ ደግሞ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በወጪና ገቢ የንግድ ልውውጥ እንዲሳለጥ በማድረግ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ መመስረት፣ አዲስ አበባ የአፍሪካና የዓለም አቀፍ የፖለቲካል ዲፕሎማሲ ማዕከል ሀገር መሆኗም እስራኤል ለኢንቨስትመንት የምትመርጣት ሀገር እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል። የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል ልማት የእስራኤል ባለሀብቶች በተለያዩ የንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች መዋለ ነዋያቸውን የሚያፈሱበትን ምቹ መደላድል እንደፈጠረ ገልጸዋል። ይህም እስራኤል የኢትዮጵያ የግብርና ምርቶችን፣ ኢትዮጵያ ደግሞ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በወጪና ገቢ የንግድ ልውውጥ እንዲሳለጥ በማድረግ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አብራርተዋል።  
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና ይጫወታል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Sep 12, 2026 277
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ):- አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ዛሬ በህንድ ኒው ዴልሂ መካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ዓለም አቀፍ ቀውሶች የሚያስከትሉት ጉዳት በአንድ ዘርፍ ላይ ብቻ ሳይወሰኑ ተደራራቢ መስተጓጎል እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል። ሀገራት ቀውሶች ከመከሰታቸው በፊት የመቋቋም አቅም ሊገነቡ እንደሚገባ ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ ፈተናን መቋቋም የሚያስችሉ ስርዓቶችን እየገነባች እንደምትገኝ ተናግረዋል። መንግስት በምግብ ዋስትና ላይ ባከናወነው ተግባር ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ ስንዴ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ ወጥታ ራሷን መቻሏን ጠቅሰዋል። በመሆኑም ሀገሪቱ ለታቀደው የብሪክስ የሰብል ልውውጥ ማዕቀፍ (BRICS Grain Exchange) እንደ አምራችም ሆነ አቅራቢ ሆና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል። በጤናው ዘርፍም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ትልቅ ትምህርት መስጠቱን ነው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የሚያጋጥሙ ቀውሶችን ለመቋቋም የሀገር ውስጥ የማምረት አቅሟን እያሳደገች እንደምትገኝ ገልጸው፤ የፋርማሲዩቲካልና የመድኃኒት ማምረቻዎችንም እያስፋፋች መሆኗን ጠቁመዋል። በቴክኖሎጂው ዘርፍ ዲጂታል መሠረተ ልማት፣ ዲጂታል መታወቂያ (Digital ID)፣ የክፍያ ሥርዓቶች እና የመረጃ ልውውጥ በስፋት እየተገነቡ መሆናቸውን አንስተዋል። መረጃዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ በሕግ አግባብ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ይህንን ለውጥ የበለጠ እንደሚያጠናክረው አመልክተዋል። በቀጣዩ ትውልድ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ይበልጥ ሰዎችን ማገልገል፣ ብዙ ቋንቋዎችን መረዳት እና ሰፊ የሰው ልጅ እውቀት ማካተት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። አፍሪካ የነገውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን በባለቤትነት ለመምራት የምርምር፣ የኮምፒውቲንግ አቅም፣ ክህሎት እና ተቋማት እንደሚያስፈልጋት አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችውም የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲም አፍሪካ የወጠነችውን ግብ የማሳካት አላማ እንዳለው አመልክተዋል። ኢትዮጵያ አፍሪካን የሚወክል የቴክኖሎጂ አቅም ለመገንባት ከብሪክስ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላትም ገልጸዋል። በተጨማሪም ሰዎችን ማዕከል ያደረገ የኤአይ አስተዳደር መደገፍ እንዳለበት እና ጥሩ አስተዳደር ከብቃት ጋር ሊጣጣም እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የዲጂታል ግብር ክፍያ ሥርዓት ጀመረ
Sep 12, 2026 145
ሰመራ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ)፦የአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የዲጂታል ግብር ክፍያ ሥርዓት ጀመረ። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሰመራ ሎጊያ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር አህመድ ኑርሳሊም፤ የዲጂታል የግብር ክፍያ ሥርዓት ቀልጣፋ አሰራርን ከመዘርጋት ባለፈ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል ዘመናዊ አሰራር መሆኑን ገልጸዋል።   የግብር አሰባሰብ ሂደቱ ለብልሹ አሰራር እንዳይጋለጥ እና የግብር መሰወር ችግሮችን ለመከላከል የሚያስችል ስለመሆኑም ጠቅሰዋል። በመሆኑም ግብር ከፋዮች ምንም አይነት እንግልት ሳይገጥማቸው ባሉበት ሆነው የሚከፍሉበት ስርአት መዘርጋቱ አስደሳች መሆኑን ተናግረዋል። ግብር ከፋዮች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በቴሌብር አማራጮች ባሉበት ሆነው ግብራቸውን በመክፈል ከእንግልት በጸዳ መልኩ ሃላፊነታቸውን በቀላሉ መወጣት ያስችላቸዋል ብለዋል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት ቢሮ ኀላፊ ኡመር ኑር እና ሌሎችም የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የመንግስታዊ አገልግሎቶችን በማዘመን የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል 
Sep 10, 2026 307
ድሬዳዋ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ የመንግስታዊ አገልግሎቶችን በማዘመን የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ገለጹ። ጳጉሜን 5 "የነገ ቀን" በሚል ስያሜ በድሬዳዋ አስተዳደር በፈጠራና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተመዘገቡ እምርታዎችን የሚያመላክት የፓናል ውይይትና በአውደ ርዕይ ተካሂዷል።   ከንቲባ ከድር ጁሃር በወቅቱ እንደተናገሩት፣ የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን ተደራሽ በማድረግ የነገዋን ታላቅ አገር የመገንባቱ ጉዞ በተጨባጭ ውጤቶች እውን እየሆነ ነው። የተሻለች እና የበለፀገች አገር ለትውልድ ለማስረከብ በየደረጃው የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ከንቲባው ተናግረዋል። በተለይ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎትን የጨበጠ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛ በመገንባት ፈጣንና ቀልጣፋ የመንግስት አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ የነዋሪውን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየተመለሰ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው አንድ ዓመት በከተማ አስተዳደሩ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየተሰጡባቸው ባሉ አከባቢዎች አዎንታዊ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ለአብነት አንስተዋል። በአስተዳደሩ ዲጂታል የአሰራር ሥርዓትን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች፣ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና በግል ተቋማት የተጀመሩ የፈጠራና የቴክኖሎጂ የምርምር ሥራዎች የነገዋን ታላቅ አገር ለመገንባት መደላድል እየፈጠሩ ይገኛሉ ብለዋል።   በድሬዳዋ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ከሙስና የፀዳ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች ይጠናከራሉ ብለዋል። የነገ ቀን በድሬዳዋ ሲከበር ከመድረክ በተጨማሪ በአረጋዊያን መጦሪያ ማዕከል ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ከንቲባው ማዕድ ያጋሩ ሲሆን የድሬዳዋ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርም ተጎብኝቷል።   በስነስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ አብዲ ሙክታር፣ በብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ስፖርት
ሲዳማ ቡና የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል
Sep 13, 2026 99
አዲስ አበባ፤ መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):- በካፍ ሻምፒዮንስ የመጀመሪያ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ሲዳማ ቡና ከቻዱ ኤግሎንስ ጋር ዛሬ ሁለተኛ ጨዋታውን ያከናውናል። ጨዋታው ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል። ሁለቱ ክለቦች ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በቻድ ንጃሚና ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። በጨዋታው ላይ ሲዳማ ቡና ጠንካራ የመከላከል እንስቃሴ ያሳየ ቢሆንም ግልጽ የግብ እድሎች መፍጠር ላይ ክፍተቶች ታይተውበታል። በአንጻሩ ተጋጣሚው አይግሎንስ በቆሙ ኳሶች እና በመልሶ ማጥቃት እንቅሰቃሴ ግብ ለማስቆጠር ሙከራዎችን አድርጓል። ሲዳማ ቡና ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የማጥቃት አቅሙን ማሻሻል ይጠበቅበታል። ከተጋጣሚው በኩል ከቆሙ ኳሶችና ከፈጣን ሽግግሮች የሚመጡ ኳሶችን መግታት ይጠበቅበታል። በያሬድ ገመቹ የሚመራው ሲዳማ ቡና በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የበቃው የ2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንመሆኑን ተከትሎ ነው። በ1999 ዓ.ም የተቋቋመው ሲዳማ ቡና በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ሲዳማ ቡና በዛሬው ጨዋታ ማሸነፍ ወደ ሁለተኛው ዙር ያሳልፈዋል። ሲዳማ ቡና በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከሱዳኑ አል ሂላል እና ከብሩንዲው አይግል ኑዋር አሸናፊ ጋር ይጫወታል።
199ኛው የማንችስተር ደርቢ
Sep 13, 2026 106
አዲስ አበባ፤ መስከረም 3/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ማንችስተር ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ ዛሬ የሚያደርጉት የደርቢ ጨዋታ የተመልካቾችን ቀልብ ስቧል። ጨዋታው ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ይካሄዳል። ማንችስተር ዩናይትድ በአራት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ በዘጠኝ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱ ክለቦች በሁሉም ውድድሮች ሲገናኙ የአሁኑ ለ199ኛ ጊዜ ነው። ቡድኖቹ ከዚህ በፊት ባደረጓቸው 198 ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ 81 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ 63 ጊዜ ሲያሸንፍ 54 ጊዜ ነጥብ ተጋርተዋል። በፕሪሚየር ሊጉ 58 ጊዜ ተገናኝተው ማንችስተር ዩናይትድ 27 ጊዜ ሲያሸንፍ ሲቲ በ21ዱ ድል ቀንቶታል። በቀሪ 10 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ሁለቱም ክለቦች በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ አሸንፈዋል። በቀሪ አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል። ማንችስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ የአንድ ከተማ ባላንጣ ቡድኖች ናቸው። ክለቦቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት እ.አ.አ በ1881 ነበር። በዚህ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ 3 ለ 0 አሸንፏል። ቡድኖቹ ከመጀመሪያ ጨዋታቸው አንስቶ ለ145 ዓመታት የቆየ ፉክክር በእንግሊዝ እና በአውሮፓ መድረክ አድርገዋል። ማንችስተር ዩናይትድ የሊጉን ዋንጫ 20 ጊዜ በማንሳት የበላይነቱን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ 10 ጊዜ የሊጉ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ለመጨረሻ ጊዜ የተጋናኙት በጥር ወር 2018 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱ ማንችስተር ዩናይትድ 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ማንችስተር ዩናይትድ በሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከኤቨርተን ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል። በጨዋታው ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል። የከተማ ተቀናቃኙ ማንችስተር ሲቲ በሶስቱም የሊጉ ጨዋታዎች አሸንፏል። ዛሬ ድል ቀናው የሊጉን መሪነት ከአርሰናል በድጋሚ የመረከብ እድል አለው። ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል። የ41 ዓመቱ ማይክል ኦሊቨር ተጠባቂውን የደርቢ ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል። በዕለቱ ሌላኛው መርሐ ግብር ኮቨንተሪ ሲቲ ከብራይተን በኮቨንተሪ ቢውልዲንግ ሶሳይቲ አሬና ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
አርሰናል የሊጉን መሪነት ከማንችስተር ሲቲ ተረከበ
Sep 12, 2026 247
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ሰንደርላንድን 2 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በስታዲየም ኦፍ ላይት በተደረገው ጨዋታ አዲስ ፈራሚ ብሩኖ ጉማራይሽ በ58ኛው ደቂቃ በግሩም ሁኔታ የመጀመሪያውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በ75 ሚሊዮን ፓውንድ ከኒውካስትል ዩናይትድ የፈረመው ጉማራይሽ የመጀመሪያ ጎሉን አስቆጥሯል። ግቧ የተቆጠረችው የሰንደርላንዱ ኤንዞ ላፌ በ56ኛው ደቂቃ ፍጹም ቅጣት ምት ከሳተበት አጋጣሚ በኋላ ነው። ፍጹም ቅጣት ምቱን የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ በግሩም ሁኔታ አድኖታል። ቡካዮ ሳካ በ97ኛው ደቂቃ ሁለተኛውን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ አሳርፏል። በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ጎሉን አስቆጥሯል። የሰንደርላንዱ ሬናልዶ በሁለት ቢጫ በ96ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ወጥቷል። ጨዋታው ተመጣጣኝ እና አዝናኝ ፉክክር ተደርጎበታል። አራተኛ የሊግ ድሉን ያስመዘገበው የወቅቱ ሻምፒዮን አርሰናል በ12 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከማንችስተር ሲቲ ተረክቧል። በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሰንደርላንድ በአራት ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሰንደርላንድ ከእ.አ.አ 2009 በኋላ አርሰናልን በሊጉ አሸንፎ አያውቅም።
አካባቢ ጥበቃ
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አፍሪካ ለችግሮቿ መፍትሔ ማቅረብ እንደምትችል ማረጋገጫ ነው
Sep 13, 2026 112
አዲስ አበባ፤መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አፍሪካ ለችግሮቿ መፍትሔ ማቅረብ እንደምትችል ማረጋገጫ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም፣ ሥነ-ምህዳርን በመመለስና ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ለአፍሪካና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አርዓያ የሚሆን ተግባር እያከናወነች መሆኑንም ተናግረዋል። በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ባለሙያ ዮሴፍ አምሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ከከባቢ አየር የሚለቀቁ ሙቀት አማቂ ጋዞችን በመያዝ ለሥነ-ምህዳር ጥበቃ ገንቢ ሚና እየተወጣች መሆኑን ገልጸዋል። መርሃ ግብሩ ለአርሶ አደሩ፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ብለዋል። የፓን አፍሪካ አየር ንብረት ፍትህ ጥምረት ዋና ዳይሬክተር ሚቲካ ምወንዳ (ዶ/ር)፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ሀገራት ችግራቸውን በራሳቸው አቅም ለመፍታት ሊወስዱት የሚገባ ምርጥ ተሞክሮ መሆኑን ገልጸዋል።   ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ያስመዘገበችው ስኬት አፍሪካ ለችግሮቿ መፍትሔ ማቅረብ እንደምትችል ያሳየ ነው ብለዋል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ የአየር ንብረት ሻምፒዮንና የአፍሪካ የግሬት ግሪን ዋል ኢኒሼቲቭ አምባሳደር ታቢ ጆዳ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በጠንካራ አመራር የታጀበ ውጤታማ ሥራ መሆኑን ገልጸዋል።   መንግሥት ፕሮግራሙን ከንግግር ባለፈ መሬት ላይ የሚታይና ሚተረጎም ድንቅ ኢኒሼቲቭ ነው ብለዋል። በአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ አየር ንብረትና ልማት ልዩ ፈንድ አስተዳዳሪ ጀምስ ኪንያንጊ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎችን በመቅረጽና በተግባር ረገድ ለአፍሪካውያን አርዓያ መሆኗን ገልጸዋል።  
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስኬታማ ሥራ ተከናውኗል
Sep 10, 2026 248
የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በ2011 ዓም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በይፋ መጀመሩ ይታወቃል። መርሃ ግብሩ እንደ ሀገር ያጋጠሙ በርካታ የዘላቂ ልማት ተግዳሮቶችን የመሬት መጎሳቆል የደንና ብዝሃ ህይወት መጨፍጨፍ፣ የውሃ አካላትን መድረቅና በደለል መሞላት ለመከላከል ታስቦ ወደ ሥራ መገባቱ ይታወቃል። በዚህም በመጀመሪያው ምዕራፍ 50 ቢሊዮን ችግኝ በማህበረሰብ ተሳትፎ ለመትከል ታቅዶ ነበር።   ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት የመርሃ ግበሩ የትግበራ ዓመታት 56 ነጥብ 8 ቢሊዮን ችግኞችን፤ በዚህ ዓመት ብቻ ደግሞ 8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ችግኝን በመትከል በዓለም ላይ አዲስ ታሪክ ፅፋለች። አጠቃላይ ከተተከሉ ችግኞች ከ3 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑት በአንድ ጀምበር የተተከሉ መሆናቸው በዓለም ላይ ትልቅ የችግኝ ተከላ ሆኖ ተመዝግቧል። ከተተከሉ ችግኞች 60 በመቶ የሚሆኑት የጥምር ደን ግብርና (የፍራፍሬ፣ የቡና፣ የመኖ ዝርያዎች) ሲሆኑ 35 በመቶ የደን ዝርያ ናቸው። ይህ ታላቅ የልማት ድል የተሳካው ከላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እስከ ታችኛው የመንግስት አደረጃጀት ለመርሃ ግብሩ በተሰጠው ቁርጠኛ አመራር ነው። በየዓመቱ ከ25 ሚሊየን በላይ ዜጎች በችግኝ ተከላ ተሳትፈዋል።   እስካሁን በተሠራው ሥራ በየዓመቱ ይፈጸም የነበረው የደን ጭፍጨፋ ከ92 ሺህ ወደ 27 ሺህ ሄክታር እንዲቀንስ አስችሏል። በእርሻ ማሳ የአፈር መከላት በዓመት በሄክታር ከ130 ቶን ወደ 54 ቶን ቀንሷል። አረንጓዴ ዐሻራ በየዓመቱ ወደ ውሃ አካላት የሚገባ የአፈር ደለል ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ቶን ወደ 208 ሚሊዮን ቶን ዝቅ እንዲል አስችሏል። በመርሃ ግብሩ ለ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ወጣቶችና ሴቶች አረንጓዴ ሥራ ተፈጥሮላቸዋል።   በበርካታ አካባቢዎች የፍራፍሬና የደን ክላስተር እየተፈጠረ አርሶ አደሮች የላቀ የኢኮኖሚ አቅም እንዲገነቡ እያስቻለ ነው። ኢትዮጵያ ግዙፍ የልማት መርሃ ግብር ቀርጻ መተግበር እንደምትችል ትልቅ ተሞክሮ የተወሰደበትና ለዓለም ያሳየችበትም ነው። ከዚህም ባለፈ ሀገራችን ዓለም እየተፈተነችበት ላለው የአየር ንብረት ለውጥ ተግባራዊ መፍትሔ በመስጠት ምሳሌ መሆኗን ያሳየችበት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ የችግኝ ተከላ አካሄዱ
Sep 10, 2026 194
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል። ‎የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው በዘንድሮው ዓመት «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ ነው የችግኝ ተከላ ያካሄዱት።   የ2018 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መጠናቀቅን ስናበስር የተተከለው እያንዳንዱ ችግኝ የሕብረታችን፣ የሕዳሴያችንና የዘላቂ እድገታችን ሕያው ምልክት መሆኑን በማስታወስ መሆኑንም አስታውቋል። ‎የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ‎በጽኑ አንድነታችንና በጋራ ጥረታችን የታነጸች፣ የበለጸገችና ብሩህ ኢትዮጵያን ለማየት ሙሉ ተስፋ ሰንቀን ወደፊት እንገሰግሳለን ሲልም መልእክት አስተላልፏል።
የአየር ንብረት ለውጥ በማኅበረሰብ ጤና ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Sep 9, 2026 260
አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦የአየር ንብረት ለውጥ በማኅበረሰብ ጤና እና ስነ-ምግብ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ ገለጹ። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር በጤና እና በስነ-ምግብ መጠበቅ ላይ ያለውን ሚና በተመለከተ የምርምር ጉባኤ የዘርፉ ተዋናዮች በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል። ዶክተር መሳይ ሀይሉ በመድረኩ እንደተናገሩት፤ ከተለያዩ የህብረተሰብ ጤና ፈተናዎች መካከል ከውሃ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች እንደሚገኙበት ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለመሻገር እየወሰደቻቸው ያሉ የፖሊሲ እርምጃዎች ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን መትከሏ ተስማሚ የአካባቢ አየር ንብረት እንዲኖር አድርጓል ብለዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለማበረታታት የወሰደቻቸው የፖሊሲ እርምጃዎች የአየር ብክለትን በመቆጣጠር የማኅበረሰብን ጤና ለመጠበቅና ስነ-ምግብን ለማሻሻል የራሳቸው አበርክቶ እንዳላቸው ገልጸዋል።   ኢንስቲትዩቱ በአረንጓዴ ልማት ላይ የሚሰሩ ስራዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናት የደን ልማትና ንጹህ መጓጓዣ የመፍጠር እርምጃዎች ከአየር ንብረት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የበሽታ ጫናዎች እንደሚቀንሱ፣ የአየር ጥራትን እንደሚያሻሽሉ እና የስነ-ምግብ ክትትልን እንዴት እንደሚያጠናክሩ በጥናት የማረጋገጥ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ኢንስቲትዩቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚሰሩ ስራዎች በጤናው ዘርፍ ያላቸውን አበርክቶ በምርምር ስራዎች ለመፈተሽና በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ላይ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ያለውን የትብብር ስራ ለማጠናከር መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ተቋሙ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ የአየር ፀባይ ትንበያዎችን በመተንተንና በማደራጀት ለጤናው ዘርፍና ለልዩ ልዩ ጥቅሞች እንዲውሉ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተገናኙ መረጃዎችን በመለዋወጥ የማህበረሰብ ጤና እንዲጠበቅ ትብብሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ለበሽታ ክትትል፣ ለአደጋ ዝግጁነት እና ለቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚረዱ የአየር ንብረት መረጃዎችን በወቅቱና በቀጥታ ለማድረስ ተግቶ ይሰራል ነው ያሉት።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 291
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 528
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1833
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1489
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች።   ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
ሐተታዎች
የጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ትንሳኤ፡ የመደመር እሳቤ ትሩፋት
Sep 13, 2026 139
ኢትዮጵያ ሺህ ዘመናትን የተሻገሩ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አስመዝግባለች። በዓለም የሚዳሰስ ቅርስነት ዝርዝር ከሰፈሩ የኢትዮጵያ ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የአጼ ፋሲለደስ አብያተ መንግሥታት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የሐረር ጀጎል ግንብ፣ የጢያ ትክል ድንጋይ፣ የአዋሽና የኦሞ ሸለቆዎች፣ የኮንሶ ባህላዊ መልክዓ ምድር፣ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር፣ የራስ ዳሽንና የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮችና ሌሎችም ይገኙበታል።   በማይዳሰስ ቅርስነት ከሰፈሩ የኢትዮጵያ ቅርሶችም የመስቀል ደመራ በዓል፣ ፊቼ-ጫምባላላ፣ የገዳ ሥርዓት፣ ጥምቀት፣ ሹዋሊድ፣ የሶማሌ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት፣ የወላይታ ጊፋታና የመሳሰሉት ሕያው ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ማኅበረሰባዊ ትውፊቶችን ያካትታሉ። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ለዓለም ሕዝብ ያበረከቷቸው የመስህብ ሀብቶችም ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በገጽታ ግንባታና ለአካባቢ ልማት የሚያበረክቱት ዕድል በቀላሉ የሚታይ አይደለም። የመደመር መንግሥትም ይህንን የኢትዮጵያውያንን ሰፊ የቱሪዝም አቅም በመረዳት፣ ቱሪዝምን በብዝኅ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ዕይታው ውስጥ ትኩረት ከሰጣቸው የልማት መስኮች አንዱ አድርጎታል።   በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውም ቱሪዝም ከአምስቱ የብዝኅ የኢኮኖሚ አዕማድ አንዱ እንዲሆን በመደረጉ ዘርፉ የሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የበለጠ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጓል። ይህም ዘርፉ ከነበረበት ተለምዷዊና አዝጋሚ ዕድገት የሚላቀቅበትን ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት፣ ነባር ቅርሶች በማደስና በመጠገን ውጤታማ ሥራ ተሰርቷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገርና በገበታ ለትውልድ የመስህብ መዳረሻ ልማት የቱሪዝሙን ዘርፍ ማንሰራራት ያበስሩ ፕሮጀክቶች እውን ሆነዋል። ለአብነትም በገበታ ለሸገር በአዲስ አበባ የተገነቡ የወዳጅነት፣ አንድነትና የእንጦጦ ፓርኮች፤ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት የመዲናዋን ዓለም አቀፍ ገጽታ መቀየር ያስቻለ ምቹ ምኅዳር ፈጥረዋል።   በገበታ ለሀገርና ለትውልድ የመዳረሻ ልማት ፕሮጀክትም ጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ኮይሻ፣ ሐላላ ኬላ፣ ደንዲ ኢኮ ሎጂ፣ አርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት፣ ሎጎ፣ ሸበሌ ሪዞርት፣ ኒን ሊ ፓልም ሎጂ እና የመሳሰሉት እንዲገነቡ አስችሏል። ይህም የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን የከተማና ገጠር የቱሪዝም መዳረሻ አሰናስሎ በማልማት ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተውን ገንቢ ሚና መወጣት የሚችልበትን ከፍተኛ ዕድል ከፍቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በቱሪዝም ጉዳዮች ላይ ከኤንቢሲ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች በማስፋፋትና የመዳረሻ ብዝሃነትን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለይም ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት የኢኮኖሚ መነቃቃትን በመፍጠር በሥራ ዕድል ፈጠራም ጭምር ከአምስቱ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻዮች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።   በዚህም የጎብኚዎች ፍሰትን በመጨመርና የቆይታ ጊዜ በማራዘም የቱሪዝም ብዝኅ እመርታዊ ውጤቶች በየአካባቢው ኢኮኖሚን በማነቃቃት የገጠርና የከተማ ልማትን ለማስተሳሰር አዲስ ዕድል ፈጥረዋል ብለዋል። የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የቅርስ ዕድሳት ውጤታማ ሥራ የዘርፉን ዳግም ውልደት ያበሰሩ ለውጦችን አምጥቷል ብለዋል። ይህም የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ዘመናዊና የተሰናሰለ የከተማና ገጠር የመስህብ መዳረሻና እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ማስቻሉን ገልጸዋል።   የቱሪዝም አስጎብኚ ድርጅቶች እንደሚሉትም፤ የኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የመዳረሻ ልማትና የቅርስ ጥበቃ ውጤታማ ሥራ ለቱሪስቶች መዳረሻና ጉብኝት ምቹ ምኅዳርን በመፍጠር የሀገርን ገጽታ የገለጡ ናቸው። የታላቁ የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት እንቁ ሙሉጌታ እንደገለጹት፤ የቱሪዝም መሠረተ ልማት መስፋፋት የቱሪዝም ፍሰቱን በማሳደግ ተጠቃሚነትን እያሳደገ ነው።   የኤደን ላንድ ቱር ኤንድ ትራቭል ባለቤት እንዳልካቸው የምሩ፤ ለቱሪዝም ልማት የተሰጠው ትኩረት አማራጭ የመዳረሻ ስፍራዎች በማስፋፋት ለመስህብ መዳረሻ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎች እንደሚሉትም፤ በኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ተፈጥሯዊ መስህቦችን መጎብኘት የሚያስችሉ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል።   ከዓለም አቀፍ ጎብኝዎች መካከል ጀርመናዊው ሉካስ ኩፕፈርናጌል፤ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች የገነባቻቸው አስደማሚ የቱሪዝም መዳረሻዎች ሀገሪቱን አፍሪካዊት ግንባር ቀደም የቱሪስት ማዕከል የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።     ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ የሀገር ውስጥ ጎብኚ ምሕረት አሰፋ በበኩላቸው፤ የለሙት የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገርን ገጽታ የቀየሩ፣ ውብ፣ ጽዱና ዓለም አቀፍ የመስህብ ተወዳዳሪነትን የሚያጎለብቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።   ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በሃይማኖት፣ በባህልና በተፈጥሮ የታደለችውን ሀብት ወደ ኢኮኖሚያዊ አቅም የመቀየር ሥራ በስፋት እያከናወነች ይገኛል። የመደመር መንግሥት ቱሪዝምን የብዝኅ የኢኮኖሚ አዕማድ አካል በማድረግ የገነባቸው ማራኪ የመዳረሻ ስፍራዎች የዘርፉን ማንሰራራት በማጽናት ለኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተውን አቅም ለማጎልበት ያለመ ነው። ቀጣዩ የዘርፉ ጉዞም የኢትዮጵያን ቅርስና ተፈጥሯዊ ጸጋ በመጠበቅ የመዳረሻ ብዝኅነትን በማስፋፋትና የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ ቱሪዝምን ከተስፋ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ውጤት የሚያሻግር ይሆናል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች የመቻል ተምሳሌት 
Sep 9, 2026 271
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች የመቻል ተምሳሌት መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን የጋራ ቃል ኪዳን የታሰረባት ታሪካዊ ክስተት ናት። ዕለቷም የዓባይን የሺሕ ዘመናት ገደብ የሌለው ጉዞ በጉባ ተራሮች ግርጌ ልጓም ለማበጀት የታሰረች ቀለበት ሆና ተመዝግባለች። ኢትዮጵያውያን ቃል ኪዳናቸውን ባሰሩ ማግስት የግብፅና ሌሎች ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጩኸትና የጥፋት ሴራ በግልጽ መታየት ጀመረ። በተለይም ግብፅ ኢትዮጵያ ውስጣዊ መረጋጋት እንዳይኖራት የውስጥ ታጣቂዎችን ከመደገፍ ጀምሮ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በራፍ ጭምር የሀሰት ክሶችን እስከማሰማት የደረሰ የሺሕ ዘመናት ዓባይን በብቸኝነት የመጠቀም አባዜዋን አንጸባርቃለች። ትብብርን ከፅናት አሰናስለው የቀጠሉት ኢትዮጵያውያን ለአሥራ አራት ዓመታት የታላቁ ሕዳሴ ግድብን የማደናቀፍ የታሪካዊ ጠላቶችን ሴራ በጋራ በመመከት ለፍጻሜ አብቅተውታል። የሀገርን ሉዓላዊነት በጽናት የማስከበር የአርበኝነት ተጋድሎን ከዓድዋ ጀግኖች የወረስን እኛ ኢትዮጵያውያን በጉባ ተራሮች ግርጌ በደም፣ በላብ፣ በዕንባና በውኃ ጠብታ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በዓባይ ላይ አንጸናል።   ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ዋዜማም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በማጠናቀቅ ለፍጻሜ በማድረስ አብስሯል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሺሕ ዘመናት የልማት ጥማትን በማርካት የብልፅግና ፍኖት ብስራት ሆኗል። ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለሌላ የልማት ዕቅድ ወጋገን የፈነጠቀ የንጋት ሐይቅ ፈጥሯል። ግድቡ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝቦቿ ትብብር ብቻ ያለ አንዳች የውጭ ድጋፍና ብድር ለፍጻሜ መብቃቱም ለአፍሪካውያን የመቻል ትዕምርት ሆኗል። በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ብስራት በጉባ ተራሮች ግርጌ የከተሙ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሀገራት መሪዎች የመሰከሩት ጥሬ ሐቅም ይህ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምረቃው ዕለት እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦችን የታሪክ ክብር ያደሰና ለአፍሪካውያን የመቻል ውጤት ነው። በወቅቱም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጎህ ያበሰረ፣ ቀጣናዊ የኃይል ትስስርና የጋራ ዕድገት መንገድ የጠረገ ፓን-አፍሪካኒዝም ፕሮጀክት መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ አፍሪካውያን አንጡራ ሀብታቸውን በራሳቸው አቅምና ጥረት በማልማት ታላላቅ የልማት ገድሎችን መፈጸም እንደሚችሉ ያመላከተ የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የኩራት ምንጭ መሆኑንም ጠቁመዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር እና የክብር እንግዳ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ የታዳሽ ኃይል ሽግግርን በማፋጠን የአፍሪካውያንን የጋራ ምኞት የሚያሳካ ህያው ምልክት ነው ማለታቸው ይታወሳል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅና ለምረቃ መብቃትም የኢትዮጵያውያንን ለአንድ ሀገራዊ የልማት ርዕይ በጋራ የመቆም ውጤታማነትን በተግባር ለዓለም የገለጠ ፓን-አፍሪካኒዝም ፕሮጀክት መሆኑን መስክረዋል። በዚሁ ወቅት የተገኙት የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዘመናዊው ዓለም የአፍሪካውያን የኩራት ምንጭ የሆነ የልማት ድል መሆኑንና መላውን ዓለም ያስደነቀ የኢትዮጵያ ስኬትና የወዳጆቿ የጋራ ሀብት ነው። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ብሔራዊ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን አስደማሚ የፓን-አፍሪካኒዝም መግለጫ ፕሮጀክት ነው ያሉት ደግሞ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የታደሙት የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ናቸው።   የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ፕሮጀክት የሆነው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስኬት አፍሪካውያን በተባበረ ክንድ አቅማቸውን በመጠቀም የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ ትምህርት ያስተላለፈ ነው ሲሉም መግለጻቸው ይታወሳል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የምህንድስና ልህቀትም አህጉሪቱ ለብልፅግናዋ የሚረዱና ሁለንተናዊ ለውጥ የሚያመጡ ሁነኛ የልማት ፕሮጀክቶችን በራሷ አቅም የመገንባት ብቃት እንዳላት ማረጋገጫ ነው። በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ የተገኙት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ እንደተናገሩት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አህጉራዊ ትብብርና ግንኙነትን የሚያጠናክር የወንድማማችነት ምልክት ነው። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁላችንንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የጋራ ጉዳያችን ነው በዚህም ዕድለኞች ነን ሲሉ መግለጻቸውም ይታወሳል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ "ለእኛ እንደ አንድ ፕሮጀክት ሳይሆን ሀላፊነትን የምንጋራበት ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ አፍሪካውያን ከተባበርን ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደምንችል ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል። የላይኛውና የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መበልጸግ የሚችሉት በጋራ እንደ አንድ ማህበረሰብ በመስራት ነው። ውሃና ሌሎች ተፈጥሯዊ ሀብቶች በድንበር የተወሰኑ ሳይሆኑ የወደፊት እጣ ፈንታችንን የሚወስኑ ናቸው ብለዋል።   የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በበኩላችው እንደሚሉት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአንድነት እና የመስዋዕትነት ምልክት ነው። ግድቡ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን የአንድነትና የመስዋዕትነት ምልክት ነው፡፡ የግድቡ ግንባታ እውን መሆን ህዝብ ከተባበረ እና ለአንድ ዓላማ በአንድነት ከቆመ ምን መስራት እንደሚችል ማሳያ መሆኑን ነው ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የኩራት ምንጭ ነው ማለታቸው ይታወሳል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ግድቡ የኃይል ፍላጎትን ከማሳካት ባለፈ ለልጆቻችን የምንመኘውን የበለጸገ ሀገርና አህጉር ለማስረከብ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። ይህ በታሪክ ድርሳናት ሰፊውን ድርሻ የሚይዘው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስኬት የኢትዮጵያዊያን የቃል ኪዳናቸው ማህተም ሆኖ ለዘላለም ይኖራል።
የፀጥታና ደህንነት ተቋማት በመጠናከራቸው ኢትዮጵያን የማትበገርና የጸናች ሀገር አድርጓታል
Sep 8, 2026 328
የፀጥታና ደህንነት ተቋማት በመጠናከራቸው ኢትዮጵያን የማትበገርና የጸናች ሀገር አድርጓታል ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን፣ ሰላሟንና የሕዝቦቿን ደህንነት ለማስጠበቅ ባለፉት ዓመታት በጸጥታና ደህንነት ዘርፍ በተቋማዊ አደረጃጀት፣ በሕግ፣ በሙያዊ አቅም ግንባታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በተቀናጀ አሠራር ያካሄደቻቸው ሪፎርሞች የጸጥታ አቅሟን እንድታሳድግ አስችለዋል። በዚህም የፖሊስና የመረጃ ተቋማት የሚመሩበት የሕግ ማዕቀፍና ተቋማዊ አደረጃጀቶችን ከማጠናከር ባሻገር፣ ተቋማቱ የዘመኑን የጸጥታ ተግዳሮቶች መመከት የሚያስችላቸውን አቅም እንዲገነቡ ተደርጓል። በመከላከያ ዘርፍም የሠራዊቱን አደረጃጀትና የማድረግ አቅም ማጎልበት፣ የቴክኖሎጂ አቅሙን ማጠናከር የሪፎርሙ የትኩረት አቅጣጫዎች ነበሩ። በዚህም የምድር ጦርን ጨምሮ የአየር ኃይልና የባሕር ኃይል አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ከዘመናዊ የሰራዊት አሠራር ጋር የሚሄድ የወታደራዊ አቅም መገንባት በዚሁ አቅጣጫ ተካትቷል።   በቅርቡ በሃዋሳ በተካሄደ የኮማንዶ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ የሀገሪቱን ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ በቀጣናውና በአፍሪካ ሰላምና ብልጽግና ላይ አስተዋፅዖ ማድረግ የሚችል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ኤሊት የጦር ኃይል ለመገንባት እየሠራች ነው። በምድርና በአየር የነበረውን ወታደራዊ ሥልጠና ወደ ባሕር ማስፋፋትን ጨምሮ፣ የጦር ኃይሉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማጠናከርና የተለያዩ የውጊያ አቅሞችን ማሳደግ የሠራዊቱን ዘመናዊነት ለማረጋገጥ ከተወሰዱ አቅጣጫዎች መካከል መሆናቸውን መጠቆማቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ በ45ኛው የፅናት ኮርስ የኮማንዶ ምረቃ መርሃ ግብር ላይ እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር የተጠናከረ ወታደራዊ አቅም እንዲኖረው ተሰርቷል። የቴክኖሎጂ ግኝቶችን የታጠቅንበት ዘመን ላይ ነን ያሉት ፊልድ ማርሻሉ፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ውስጥና የውጭ ጠላቶች እንደማይችሏት ገልጸዋል። የጸጥታ ተቋማት በተናጠል ከመሥራት ይልቅ በቅንጅት እንዲሠሩ ማድረግም በሪፎርሙ የተሰጠው ትኩረት ሌላው አቅጣጫ ነው።   የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮችና የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች ሀገራዊ የጋራ የፀጥታ መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ የጸጥታ ተቋማት በጋራ በማቀድ፣ በመቀናጀትና ልምድ በመለዋወጥ የጋራ የጸጥታ ተልዕኮዎችን የሚያከናውኑበት አሠራር ተጠናክሯል። ይህ የተቀናጀ አሠራር በተለያዩ ብሔራዊ ዝግጅቶችና የሀገራዊ ጸጥታ ተልዕኮዎች ወቅት የተቋማትን የጋራ አቅም ለመጠቀም መሠረት መሆኑ በቀደመ ማብራሪያዎች ጠቁመዋል። የሳይበር ደህንነት የሀገራዊ ደህንነት አካል እየሆነ መምጣቱ የሪፎርሙ አንድ አካል እንዲሆን ተደርጓል። በዚህ ረገድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ አምስተኛው ዙር ብሔራዊ የሳይበር ታለንት የሰመር ካምፕ ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ እንደገለጹት፤ አስተዳደሩ ተቋማዊ አቅሙን በማሳደግ ወሳኝ የመረጃ መሠረተ ልማቶችን ከሳይበር ጥቃቶች ለመጠበቅ የሰው ኃይል ልማት፣ የዝግጁነት አቅምና የተቋማት ትብብርን ማጠናከር ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።   የሳይበር ደህንነት የሀገሪቱን ዲጂታል ሽግግር ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ በዘርፉ ብቁ የሰው ኃይል ማፍራትና የተቋማትን ዝግጁነት ማጠናከር ቀዳሚ ትኩረት ነው ብለዋል። በአጠቃላይ በሀገሪቱ የጸጥታና ደህንነት ዘርፉ የተከናወኑት ሪፎርሞች የጸጥታና ደህንነት ሥርዓቱን በተቋማዊ አደረጃጀት፣ በሙያዊ ብቃት፣ በቴክኖሎጂና በቅንጅታዊ አሠራር ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱ የራሷን የጸጥታ አቅም በማሳደግ ሉዓላዊነቷን፣ ሰላሟንና ብሔራዊ ጥቅሟን በበለጠ አቅም ለማስጠበቅ ያላትን ብቃት አጠናክሯል።
በልጆቿ ፀንታ የኖረች ሀገር
Sep 8, 2026 544
በብርሀኑ ፍቃዱ (ሰቆጣ ኢዜአ) የውጪ ወራሪን በጀግኖች አባቶቻችን ክቡር መስዋዕትነትና በጸና ተጋድሎ በማክሸፍ፣ ኢትዮጵያን በትውልድ ቅብብሎሽ አጽንቶ አሁን ላለንበት ማድረስ ተችሏል። ለአብነትም የጣሊያን ወራሪ ኃይል በጥንት አባቶቻችን ተጋድሎ ሽንፈትን ተከናንቦ መመለሱ ለኢትዮጵያዊያን ድልና ለመላው ጥቁር ህዝብ የነፃነት ፋኖስ ሆኖ ሲዘከር ይኖራል። "የአይቻልም" መንፈስን በ"ይቻላል" ለውጠው ያሳዩት እነዚህ ጀግኖች፣ ለጥቁር ህዝቦች የነፃነት ጮራ የፈነጠቁ፣ እኩልነትን ያበሰሩ፣ የሀገር ፍቅርና ጽናትን ለልጅ ልጆቻቸው ያወረሱ እንዲሁም ታሪክን በወርቅ ቀለም የጻፉ ናቸው። የዛሬው ባለታሪኮቻችን ሻለቃ ባሻ ሞገስ የማነብርሃን እና መቶ አለቃ አበባው ገብረ እግዚአብሔር ለሀገራቸው ሉዓላዊነት መከበር በጽናት ታግለው ያሳለፉትን የተጋድሎ ታሪክ «የጽናት ቀን»ን ምክንያት በማድረግ እንደሚከተለው እናስቃኛችኋለን። በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ወረዳ «ቃፋ ሚካኤል» በተባለ መንደር ነዋሪ የሆኑ ሻለቃ ባሻ ሞገስ የማነብርሃን፣ ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ ለ22 ዓመታት ክቡር በሆነው የውትድርና ሙያ ሀገራቸውን አገልግለዋል። "ጀግንነትን፣ አሸናፊነትን እና ለሀገር አንድነት መስዋዕት መክፈልን ከአባቴ ከሻለቃ የማነብርሃን የወረስኩት አኩሪ ታሪክ በመሆኑ፣ እኔም ለሀገሬ ክብር በጽናት ተዋድቄያለሁ" ሲሉ ይገልጻሉ። የውትድርና ሕይወታቸውን በቀብሪ ደሃር ማሰልጠኛ ማዕከል የጀመሩት ሻለቃ ባሻ ሞገስ፤ በዳሎል፣ ምፅዋ፣ ከረን፣ ሙሳቤት፣ ቃሮራ፣ አፋበት፣ ናቅፋ እና በሌሎች የኤርትራ ቆላማና ደጋማ አካባቢዎች የተሰጣቸውን ግዳጅ በጽናት ተወጥተዋል። "የወጣትነት እድሜዬን ክቡር የሆነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በመቀላቀል ሀገር የሰጠችኝን ግዳጅ በጽናት ተወጥቻለሁ" ያሉት ሻለቃ ባሻ ሞገስ፤ ሀገርን በውትድርና የማገልገል እድል ማግኘት ታላቅ ዕድልና ክብር መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያን የመሰለች ጥንታዊት ሀገር ሉዓላዊነቷ፣ አንድነቷና ክብሯ እንዲጠበቅ አባቶቻችንም ሆኑ እኛ ዋጋ ከፍለናል፤ የአሁኑ ትውልድም ሉዓላዊነቷን አጽንቶ ለመዝለቅ ወቅቱ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዘብ መቆም አለበት ሲሉ ይመክራሉ። አሁን ያለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል አቅምና ትጥቅ፣ ከሳይበር እስከ መካናይዝድ ልቆ የተደራጀ በመሆኑ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጠናው ዘብ የሚሆን አስተማማኝ ኃይል መሆኑን እያየን ነው ብለዋል። "ሀገራችን የባሕር በር አልባ መሆኗ ያስቆጨኛል፤ ዕድሜ ልኬን ለሀገሬ ዘብ ብቆም ምኞቴ ነው" ያሉት ሻለቃ ባሻ ሞገስ፤ ወጣቱ ትውልድ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የተጀመረውን ተግባር በሰላማዊ መንገድ ለማሳካት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።   ሌላው የከተማዋ ነዋሪ መቶ አለቃ አበባው ገብረ እግዚአብሔር በበኩላቸው፤ «ታላቋን ሶማሊያ» ለመመስረት በሚል በጦር የሰከረው የዚያድ ባሬ መንግሥት በእብሪት ተነሳስቶ ሀገራችንን በወረረበት ወቅት በ18 ዓመታቸው የቀድሞውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት መቀላቀላቸውን ያወሳሉ። "ወላጅ አባቴ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የቀድሞ አባል ነበር" ያሉት መቶ አለቃ አበባው፤ እሳቸውና ታናሽ ወንድማቸው የአባታቸውን አሻራ በመከተል የመከላከያ ሠራዊቱን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል። የ10ኛ፣ 19ኛ፣ እና 82ኛ ልዩ ኮማንዶ ክፍለ ጦሮች አባል በመሆን በሕክምና ሙያቸው ሠራዊቱን ለ12 ዓመታት ማገልገላቸውን ጠቁመው፤ ውትድርና ጽናትን፣ የሀገር ፍቅርን እና ከራስ በፊት ለወገን መስዋዕት መሆንን የሚጠይቅ የተከበረ ሙያ መሆኑን ገልጸዋል። ከሰራዊት አባልነት ከተገለሉም በኋላ ባካበቱት የሕክምና ሙያ በሰቆጣ ጤና ጣቢያና በተፈራ ኃይሉ ሆስፒታል ተቀጥረው ህዝባቸውን ያገለገሉ ሲሆን፣ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ በመሆንም ሰርተዋል። "ለዘመናት ያዘንኩበት የባሕር በር ጉዳይ አሁን ላይ የትውልዱና የመንግሥት አጀንዳ ሆኖ መነሳቱ አስደስቶኛል" ያሉት መቶ አለቃ አበባው፤ ይህም የሀገራችንን የቀደመ ገናናነት የሚመልስ በመሆኑ ለስኬቱ በአንድነት መሰለፍ ይገባል ብለዋል። የአሸናፊነትና የጀግንነት ወኔ ከጥንት ጀምሮ ያለና የሚቀጥል መሆኑን አሁን ላይ የመከላከያ ሠራዊት ዘመኑን የዋጀ አደረጃጀትና የቴክኖሎጂ አቅም በማየት መገንዘብ ይቻላል ብለዋል። ወጣቱ ትውልድ ጸንታ የተከበረች ሀገሩን በአንድነትና በፍቅር ሉዓላዊነቷን ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለበት መክረዋል።    
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ የከፍታ ጉዞ ማሳያ - ብሪክስ
Sep 13, 2026 112
''የብሪክስ ጉባዔ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው" በማለት ነው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር። 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የጥምረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በተገኙበት “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርንና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ በህንድ ኒውዴልሂ እየተካሄደ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የልዑክ ቡድናቸው በዚሁ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ በሚፈጥረው ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድናቸው የብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። ብሪክስ ለአፍሪካ ቀጣና እና በተለይም ለኢትዮጵያ በርካታ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝ አዲስ የዓለም ስርዓት እየተፈጠረበት የሚገኝ ጥምረት ነው። የብሪክስ ጥምረት ለኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። በዚህም እንደ ቻይና፣ ህንድ እና ሩሲያ ካሉ ታላላቅ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣውን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በተለይም በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና እና በኢነርጂ ዘርፍ በማሳደግ በኩል አይነተኛ አማራጭ የኢንቨስትመንት መንገድ ነው። ጥምረቱ ለኢትዮጵያ ከሚያስገኘው ትሩፋት አንጻር ሲታይ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በመቅረፍ፤ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በሚደረጉ የንግድ ልውውጦች የሀገር ውስጥ ገንዘብን የመጠቀም ዕድልን ስለሚፈጥር፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እጥረትን ከመቀነስ አኳያም እንዲሁ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕቅዷ ኢኮኖሚዋን በመሠረታዊነት ለሚያሳድጉ መሠረተ ልማት ግንባታ እና ማስፋፊያ እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ትገኛለች። ከዚህ አኳያ ብሪክስ የመንገድ፣ የባቡር፣ የኃይል ማመንጫዎችና ዲጂታል ቴክኖሎጂ እና መሰል የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን የፋይናንስ ድጋፍ በማመቻቸት በኩል ኢትዮጵያ ለያዘችው ግብ ስኬት ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚያስገኝ ጥምረት ነው። ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ላሳካቻቸው ውጤቶች የዓለም አቀፍ ግንኙነቷን የቃኘችበት አዲስ አካሄድ ተጠቃሽ ነው። ከእነዚህ ስኬቶች መካከል ደግሞ በብሪክስ ጥምረት ውስጥ አባል የሆነችበት መንገድ አንዱ ሲሆን፤ ይህ የብሪክስ ጥምረት ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የራሱን ሚና በመጫወት ኢትዮጵያ በቀጣናው እና በአህጉሪቷ ያላትን መሪነትና ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት በማጠናከር በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ድምፅ እንድታጎላ እና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷ እንዲያድግ እያስቻለ መሆኑም በተጨባጭ ታይቷል። የብሪክስ ጥምረት በአፍሪካ አለፍ ሲልም በጥምረቱ አባል ሀገራት መካከል ተመጣጣኝ ልማት እንዲኖር እና ሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ አስቻይ ምህዳር እየፈጠረም ይገኛል። በተለይ አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት በማልማት የኢኮኖሚ ዕድገቷን እንድታፋጥን አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ መሆን የሚያስችለውን አደረጃጀት እና አሰራር እየዘረጋም ይገኛል። ይህ የጥምረቱ አዳዲስ አደረጃጀት እና አሰራር አዲሱ የልማት ባንክ እንዲወለድ አስችሏል። በዚህ ባንክ አማካኝነት የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጥብቅ መስፈርቶች ነፃ በሆነ መንገድ ለተለያዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ ወይም ብድር እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። በጥምረቱ አማካኝነት የተፈጠረው አዲሱ የልማት ባንክ የአፍሪካ ሀገራት በራሳቸው ሀገራዊ ገንዘብ እና ከአሜሪካ ዶላር ተጽእኖ ውጪ ከታላላቅ የብሪክስ ሀገራት ጋር የንግድ ልውውጥ እንዲያከናውኑ በር እየከፈተ ይገኛል። በተጨማሪም አፍሪካ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ የውሳኔ መድረኮች ላይ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት በማሳደግ፣ ፍትሐዊ የሆነ የዓለም አቀፍ ስርዓት እንዲፈጠር እያስቻለ መሆኑም የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ሰነባብቷል። ይህ የብሪክስ ጥምረት መመስረት፣ መስፋፋትና መጠናከር በዓለም የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስርዓት ላይ በርካታ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጦችንና አንድምታዎችን እያስከተለ ይገኛል። የብሪክስ ጥምረት ተመስርቶ እየፈጠረ ያለው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተጽዕኖ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የምዕራባውያን ሀገራት በዓለም ፖለቲካ ላይ የነበራቸውን የበላይነት በመገዳደር፣ ሥልጣንና ውሳኔ ሰጪነት ለተለያዩ የአህጉራት ኃይሎች እንዲከፋፈል፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ የአሰራር እና የአደረጃጀት ማሻሻያ ጥያቄዎች ጎልተው እንዲሰሙ የማድረግ አቅም እየፈጠረ ነው። በተጨማሪም የብሪክስ ጥምረት አባል ሀገራት በንግድ ልውውጣቸው ወቅት በራሳቸው ሀገራዊ ገንዘቦች የመጠቀም ዝንባሌያቸው በመጨመሩ፣ የአሜሪካ ዶላር በዓለም ንግድና መጠባበቂያ ክምችት ላይ ያለውን ፍጹም የበላይነት በማዳከም፤ አዲሱ ልማት ባንክ የብሪክስ የድንገተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማዕቀፍ የምዕራባውያኑን ጥብቅ የፖለቲካ መስፈርቶች ሳይከተሉ ለታዳጊ ሀገራት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ እንዲያቀርቡ ብሎም የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለምን ከፍተኛ የነዳጅ፣ የጋዝ፣ የብረታ ብረት እና የግብርና ምርቶች አቅርቦት የሚቆጣጠሩ በመሆናቸው፣ በዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች እና የዋጋ ውሳኔዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዲያሳድሩ የውሳኔ ሰጪነት አቅማቸውን እያሳደገ መጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ ያላቸውን የመልማት አቅም ለመጠቀም አማራጭ የልማት ፋይናንስ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። ለዚህ ደግሞ የብሪክስ ጥምረት ይዞት የመጣውን ዕድል በውል አንስተዋል። ለዚህም ነው በብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰፊ ገበያ አለን፤ አሁን ያለው መልካም ዕድል እነዚህን አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ደግሞ ሀብቱ በሚገኝበት ቦታ መመረት እንዲችል ማድረግ ነው ሲሉ ያመላከቱት። ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና እያደገ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን አጋርነቶች ለመገንባት ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአሠራር ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጽናትን መገንባት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የአህጉራችንን ፍላጎት እንዲያገለግል ማድረግ፣ አስተማማኝ የዕዳ እፎይታ ሒደትን ማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከኢኮኖሚ ሽግግር ጋር ማስተሳሰር ከጥምረቱ የሚጠበቅ መሆኑንም ነው ያነሱት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የብሪክስ ጉባዔ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው። የጥምረቱ አቅም ከተናጠል አካሄድ ይልቅ ትብብርና ለጋራ እሴት መጎልበት ያለውን ዕድል ያመላክታል። ኢትዮጵያ ለኮቪድ እና ኤልኒኖን ጨምሮ ለዓለም የኢኮኖሚ እና የንግድ ስርዓት መመሰቃቀል እጅ ሳትሰጥ፤ ይልቁንም መሰል ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ችግሮችን ወደ ዕድል በመቀየር፤ ለችግሮች የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ባከናወነቻቸው ተግባራት ጽናትን ገንዘቧ እያደረገች ትገኛለች። ለዚህም ነው "አካታች ዓለም አቀፍ አስተዳደር እና ባለ ብዙ ወገን ትብብርን ማጠናከር” በሚል አጀንዳ ላይ ትኩረት ባደረገው የጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ውሎ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ችግሮች ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ጽናትን ማጠናከር እና የአስተዳደር ስርዓት አካል የማድረግን መሠረታዊ ጠቀሜታ የገለጹት። ይህ ጽኑ ስርዓት ግንባታ ኢትዮጵያ በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እንድትበረታ ማስቻሉን ለማሳያነት አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ የስንዴ ጥገኝነት ተላቃ በምግብ ራሷን መቻሏን አንስተዋል። በጤና ቅድመ መከላከል ፖሊሲ አካል ሆኖ የሕክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች ማምረትን፣ የዲጂታል ስርዓት ሽግግርንና ደኅንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀም የማስፈን አበይት ተግባራት መከናወናቸውን ነው አጽንኦት የሰጡት። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የጀመረችው የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑን የገለጹት። በእነዚህና መሰል የልማት ትብብሮች ከጥምረቱ አባል ሀገራት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም ነው ያረጋገጡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ጥምረቱ የተቋቋመበትን ዓላማ እና መርህ በተጨባጭ እውን እያደረገች እንደምትገኝ በመጠቆም፤ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ስርዓት ማሻሻያ ባከናወነቻቸው አመርቂ ትግበራዎች፣ በታዳሽ ኃይል መስፋፋት እና የኢንዱስትሪ መሠረት ልማቶቿ፣ በግብርና ስርዓት ማሻሻያ እየተመዘገቡ ያሉ የምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ግዙፍ የአየር መንገድ ግንባታ የአኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ንግድ ትሥሥርን ለማስፋፋት በምታደርገው ጥረት በጥምረቱ ለሚነሱ ተያያዥ የውይይት አጀንዳዎች መሪ ተዋናይ መሆን እንደሚያስችላትም አንስተዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድናቸው የብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ እሙን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው እያደረጉት ካለው ተሳትፎ ጎን ለጎን ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ከተለያዩ የብሪክስ ስብስብ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል። በዚህም ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ከቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ ሚን ሁንግ፣ ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ቃሲም ጆማርት ቶካዬቭ፣ ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያ፣ ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያ እንዲሁም ከሌሎች መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ውጤታማ ውይይቶችን አካሂደዋል። የውይይቶቹ ማጠንጠኛም የጥምረቱን አባል ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያበረታቱ እንደ ኢንቨስትመንት፣ ቀጣናዊ ጉዳዮች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታና ክህሎት፣ ቱሪዝም፣ የማዕድን ልማት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ሊኖሩ ስለሚችሉ ትብብሮች ላይ ያተኮሩ እንደነበሩ ተመላክቷል።
ከታሪክ ዘካሪነት ወደ ታሪክ ሰሪነት፤ የአዲሱ ትውልድ የሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ አብዮት
Sep 13, 2026 175
የአንድ ሕዝብ የነፃነት ድል የሚያበቃው በድል ማግስት በሚተረክ የታሪክ መዛግብት ብቻ አይደለም። በሌላ የታሪክ ገጽ ላይ አዲስ ድል መጎናፀፍ ሲቻል የቀደመውን ድል ትርጉምና ምልዑነት የበለጠ ያጎላዋል። ዓድዋ የክንደ ብርቱ ቅድመ አያቶች የሀገርን ሉዓላዊ ነፃነት የማስጠበቅ አኩሪ የድል ምልክት ነው። የድል ምልክትነቱም ለጭቁኑ የዓለም ጥቁር ሕዝቦች ፅናትና የነፃነት ጎህን በመቅደድ፣ ለአሁኑ ትውልድ ደግሞ የይቻላል መንፈስን አጎናፅፏል። ጀግንነትንና አልበገር ባይነትን ከቅድመ አያቶቹ የወረሰው የአሁኑ ትውልድም በሌላ የታሪክ ገጽ በጉባ ተራሮች ግርጌ በዓባይ የዘመናት ዥረት ላይ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት የራሱን ታሪክ ጽፏል።   የሕዳሴ ምረቃ የተበሰረባት ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለትም የኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌትነት የሚበይኑ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች የተበሰሩባት ድርብ ታሪካዊት ዕለት ሆና ተመዝግባለች። በሕዳሴ የይቻላል መንፈስን የተጎናፀፈችው ኢትዮጵያም በኃይል፣ በግብርና፣ በአቪዬሽን፣ በጋዝ፣ በማዕድንና በሌሎች ዘርፎች ወደ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተሸጋግራለች። የጉባ ብስራቶችም የአንድ ፕሮጀክት ወይም ዘርፍ ስኬት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ሀብቷን በራሷ አቅም በማልማት የብልፅግና ጉዞዋን ለማስፋት የምታደርገው የልማት ጉዞ ሕያው ምልክት ናቸው። የመደመር መንግሥት አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት ኢትዮጵያን በራሷ ልጆች የመቅረጽ ራዕይም ከዓድዋ ነፃነትን፣ ከሕዳሴ የልማት ድልን፣ ከጉባ ተራሮች ግርጌ ብስራትን በመሰነቅ ታሪክን ከመዘከር ወደ አዲስ ታሪክ መጻፍ ተሸጋግሯል። ይህም ሕዳሴ ግድብ በአንድ የታሪክ ምዕራፍ ብቻ ተከትቦ የሚቀር የትውልድ ዓርማ ሳይሆን ለሚቀጥሉት ትውልዶች የመፈጸም አቅምና የይቻላል መንፈስ የሚያስተላልፍ ቅርስ መሆኑን ያሳያል። የአንድ ግዙፍ የትውልዱ ብሔራዊ ፕሮጀክት ምረቃም የሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችን ውልደት በማብሰር ኢትዮጵያ በአዲስ የስኬት ምዕራፍ እየተስፈነጠረች መሆኗን ያመላክታል። የጉባ ብስራት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ፣ የጋዝ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንዲሁም የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አብነቶች ናቸው። ኃይልን ከግብርና፣ ኢንዱስትሪን ከአቬየሽን ያሰናሰሉት የጉባ ብስራት ግዙፍ ፕሮጀክቶችም በዚህ የልማት ጉዞ ቀጣዩን ምዕራፍ መጻፍ ጀምረዋል። ይህም ኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የምታልም ሀገር ብቻ ሳትሆን የመፈጸም አቅም ያላት መሆኗን የሚያሳይ አዲስ የልማት ምዕራፍ ነው። በመደመር መንግሥት ውልደት ማግስት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ያስመዘገበቻቸው እመርታዎች ሀገርን ከመዋቅራዊ ስብራት ወደ ማንሰራራት ያሸጋገሩ ድሎች ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ታሪካዊቷ ዕለት እንዳሉት፤ ሕዳሴ ያስገኘው ወኔና ተስፋ የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ አድማስ የሚያበስሩ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም መንገድ ከፍቷል። በዚህም በጥቂት ዓመታት ውስጥ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት፣ የጋዝ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካዎች፣ እንዲሁም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች እንደሚገነቡ ማብሰራቸው ይታወሳል። እነዚህ ግዙፍ የልማት ዕቅዶች በቁጥር የሚገለጹ ፕሮጀክቶች ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን ከራሷ የመፈጸም አቅም ጋር በማሰናሰል የነገን ሀገራዊ ተስፋ የሚያመላክቱ የልማት አቅጣጫዎች ናቸው። የመደመር መንግሥት ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ትልሞችም የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ የማንሰራራት ምዕራፍ በማብሰር፣ የሀገርን ብልፅግና የሚቀርጹ እመርታዎች የተገኙባቸው ናቸው። ከእነዚህ መካከል የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ የፕሮጀክት ግንባታ ብስራት አንዱ ነው። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላትን አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማጎልበት፣ በኢኮኖሚ፣ በቱሪዝምና በዲፕሎማሲ ዘርፎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚከፍት ቁልፍ መሠረተ ልማት ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፕሮጀክቱን ግንባታ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ዘርፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ ነው። በዚህ መነፅር ሲታይም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት የአቪዬሽን ፕሮጀክት ብቻ አይሆንም። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን የአቪዬሽን መሪነት በማላቅ፣ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት ይሆናል። የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ግዝፈትና ዝማኔ ኢትዮጵያን የአቪዬሽን፣ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ማዕከል የማድረግ ከፍተኛ አቅም አለው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ናቸው። ይህም ሕዳሴ ግድብ ያስተዋወቀው የታላቅ ሀገር ግዙፍ ፕሮጀክትን የመፈጸም ባህል ከኃይል ዘርፍ ወደ አቪዬሽንና ሌሎች ስትራቴጂካዊ የልማት መስኮች እየተስፋፋ መሆኑን ያመላክታል። ሌላኛው የኢትዮጵያን የማንሰራራት አቅጣጫ የሚበይነው ግዙፍ ፕሮጀክትም የተፈጥሮ ጋዝና የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ የማምረት ትልም ነው። የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ከመሬት ሥር ተደብቆ የሚቀር ሳይሆን፣ የምርት፣ የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ ልማት መሠረት የማድረግ አዲስ የዕድገት አቅጣጫ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክትን ባስጀመሩበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ የጋዝ ምርት ፕሮጀክት የኃይል አቅርቦትን ከግብርና ምርታማነት ጋር ያሰናሰለ ነው ብለዋል። ይህም የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ የኃይል አቅርቦትን ከማሟላት ባሻገር፣ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ በስፍራው ለሚገነባው የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግብዓትነት ያገለግላል። በዚህ አተያይም ጋዝን ማልማት የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር፣ የግብርና ምርታማነትን፣ የኢንዱስትሪ ምርትንና የሀገር ውስጥ ግብዓት አቅርቦትን የሚያጠናክር የተሰናሰለ ስልታዊ የልማት አቅም ይፈጥራል። የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለብዝኅ ክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገት የሰጠው ትኩረትም ኢትዮጵያን በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ዘርፎች በስኬት ምሕዋር እንድትገባ አድርጓታል። ይህም የኢትዮጵያን ማዕድን ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ እሴት የታከለበትና ፈጠራ ያለበት የምርት ሰንሰለት የሚሸጋገርበትን ወሳኝ ዕድል ፈጥሯል።   የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ፣ የካሉብ ፋብሪካ የተፈጥሮ ጋዝ ማጣራትና ወደ ፈሳሽነት የመቀየር የማዕድን ልማት ለተሽከርካሪና ፋብሪካ አማራጭ የኃይል ምንጭ ማቅረብ የሚያስችል ነው ብለዋል። ይህ ተፈጥሮ ሀብትን በጥሬ ዕቃነት ከመሸጥ ይልቅ በማቀነባበርና በማልማት የበለጠ እሴት ለማስገኘት የተያዘውን አቅጣጫ ያመላክታል። የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም የግሉን ዘርፍ በማሳተፍና ዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን በመሳብ፣ አዳዲስ የልማትና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ከፍቷል። ለዚህም ነው የዳንጎቴ ግሩፕ ባለቤትና መሥራች አሊኮ ዳንጎቴ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም በኢኮኖሚው ውስጥ ጤናማ ውድድርና ቀልጣፋ አሠራር እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል። ከሕዳሴ ግድብ እስከ አቪዬሽን፣ ከተፈጥሮ ጋዝ እስከ ማዳበሪያ ድረስ ገሃድ የገለጠው የኢትዮጵያ ማንሰራራትም ከማለም ወደ መፈጸም፣ ከመፈጸምም ወደ ዘላቂ የልማት አቅም ለመሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ ያመላክታል። የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያንን አንድነትና የጋራ አቅም ለዓለም ታሪክ ያሳየ ድል እንደነበር ሁሉ፣ ሕዳሴ ግድብም ያንኑ የጋራ አቅም በዘመናዊ ልማት ላይ የገለጠ አዲስ ታሪካዊ ክስተት ሆኗል። የኢትዮጵያውያን አንድነት የዓድዋን ድል ካቀዳጀ፣ ያው በሕብር የተሸመነ አንድነትም ሕዳሴን እውን አድርጓል። ሕዳሴ የተስፋ ብርሃን ካበራ፣ ያ ተስፋም በሌሎች የልማት ሜጋ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሆኖ እየቀጠለ ነው። ይህ የይቻላል መንፈስ ከፕሮጀክት ወደ ፕሮጀክት የሚጓዝ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ስለነገ ሀገራቸው ያላቸውን እምነት የሚያድስ የልማት ብስራት ነው። ሕዳሴ ግድብ የተጀመረውን የተስፋ ጉዞ አዲስ አቅጣጫ አስይዞታል። የሚቀጥለው ታላቅ ተግባር ደግሞ ይህን የመፈጸም አቅም ወደ ዘላቂ ምርታማነት፣ የሥራ ዕድል፣ የዜጎች ተጠቃሚነትና የተሻለ ኑሮ መቀየር ነው። እናም የሕዳሴ ግድብ ብስራት በግድቡ የውሃ ሙሌት ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያውያን የጋራ ህልም፣ በሀገራዊ አንድነትና በመፈጸም አቅም የሚቀጥል የልማት ብስራትን ፈንጥቋል።    
የዲጂታል አብዮት ለነገዋ ኢትዮጵያ
Sep 9, 2026 346
በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው የቴክኖሎጂ ለውጥ የዛሬን ፈታኝ ሁኔታዎች ከመቅረፍ ባለፈ፣ ኢትዮጵያን ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ምህዳር በፍጥነት እያሸጋገራት ይገኛል። የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታዎች እና የተቋማት ማጠናከሪያ ስራዎች ለዚሁ አገራዊ የነገ ትራንስፎርሜሽን በምሳሌነት የሚጠቀሱ ዋና ዋና እርምጃዎች ናቸው። መንግስት የዲጂታል ዘርፉን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምሶሶ በማድረግ የነደፈውን "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂ በስኬት ማጠናቀቁ፣ 2030 ዲጂታል ስትራቴጂን መጀመሩ ሀገሪቱን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ወደ አዲስ የወደፊት ምዕራፍ እንድትገባ ያስቻለ መሰረታዊ ለውጥ አምጥቷል። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉ፣ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መግባትና የኢትዮ ቴሌኮም መዘመን ለኢንተርኔት ተደራሽነት መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። በተለይም የ5G ቴክኖሎጂ አገልግሎት በስፋት መጀመሩ ሀገሪቱን በምስራቅ አፍሪካ በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና በመሰረተ ልማት ዝግጁነት ቀዳሚ ያደረጋት ሲሆን፣ ይህም ለነገው ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እና ለቀጣይ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቱ መዘመን በፋይናንስ ዘርፉ ላይ አብዮታዊ ለውጥ በማምጣት የነገዋን ስማርት ኢኮኖሚ መደላደል ጥሏል። እንደ ቴሌብር ያሉ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ ባንክ ሂሳብ በስልካቸው ብቻ ግብይት እንዲፈጽሙ በማድረግ ለአካታች ዲጂታል ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም ሆነዋል። ይህ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ምህዳር መስፋፋት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ የዲጂታል ክፍያዎችን እንዲቀበሉና የፋይናንስ ተደራሽነታቸው እንዲያድግ ያስቻለ ሲሆን፣ መደበኛ ያልሆነውን የግብይት ስርዓት ወደ ዘመናዊና ግልጽ የነገ ዲጂታል ስርዓት የመቀየር ሂደቱን አፋጥኖታል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ረገድ የኢትዮጵያ ሰውሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም የሀገሪቱን ታላቅ የነገ ራዕይ ለዓለም አሳይቷል። ኢንስቲትዩቱ በጤናው ዘርፍ የካንሰርና የሳምባ በሽታዎችን ቀድሞ የሚያውቁ የኤአይ ውጤቶችን በማበልጸግ ህይወትን የማዳን ስራ እያከናወነ ይገኛል። በተመሳሳይ በግብርናው ዘርፍ የአፈር ለምነትንና የሰብል በሽታን በቴክኖሎጂ የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ይህም ለነገዋ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥና ለምርታማነት ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ሌላው ትልቅ የለውጡ ስኬት የሀገር በቀል ቋንቋዎችን በዲጂታል አለም ተወዳዳሪ ለማድረግ የተሰሩ የቋንቋ ፕሮሰሲንግ (NLP) ስራዎች ናቸው። ይህም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ ለነገው ትውልድ የባህል እና የእውቀት መተላለፊያ ምቹ መንገድ ፈጥሯል። ከዚሁ ጎን ለጎን የ"ፋይዳ" (Fayda) ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት የዜጎችን መረጃ በማደራጀት ለነገው ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ አስተማማኝ የመረጃ መሰረት ጥሏል። ይህም ለባንክ፣ ለጤናና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ቀልጣፋ አሰራርን ፈጥሯል። በአሁኑ ወቅት ዜጎች እንደ ፓስፖርት ማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ግብር መክፈል ያሉ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ማከናወን መቻላቸው የነገዋን አሰራር ዛሬ ማሳያ ሲሆን፣ የሳይንስ ሙዚየም ደግሞ የነገዎቹን ፈጣሪዎች አቅም የሚያበለጽግ ማዕከል ሆኗል። በተጨማሪም በዲጂታል ክህሎት ግንባታ ረገድ ለወጣቶችና ለባለሙያዎች የሚሰጡ የስልጠና ፕሮግራሞች በስፋት እየተካሄዱ ይገኛሉ። ይህም ኢትዮጵያ በነገው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መድረክ ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል እንድታፈራ ዘላቂ መሰረት እየጣለ ነው።
ነገን በብልሃት ማነጽ - የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ
Sep 9, 2026 262
(በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የጀመረችውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አጠናክራ ለመቀጠል እና ከጊዜው ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ለመራመድ “የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂን በይፋ አድርጋለች። ታኅሣሥ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው ይህ ታላቅ አገራዊ ዕቅድ፤ ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዓለም ከተመልካችነት ይልቅ ተሳታፊና መሪ የምትሆንበትን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው። ይህ አዲስ ስትራቴጂ ከቁጥሮች እና ከኢኮኖሚያዊ ስኬቶች ባሻገር፣ ዛሬን ከመቅረጽ ባለፈ ነገን ከመገንባት እና ለቀጣይ ትውልድ አሻራ ከማስቀመጥ አንጻር ሰፊና ጥልቅ ፋይዳ ያለው ሀገራዊ ትልም ነው። በዲጂታል ዘመን የመረጃ ሉዓላዊነት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው ። በዚህ ዘርፍ የሚያጋጥም ጥገኝነት የሃገር ደህንነት ላይም የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳረፉ አይቀርም። ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚህ ዙሪያ መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው ማለታቸው ይታወሳል። የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻታችንን ማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነውም ብለዋል። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ከወረቀት ባለፈ በህዝብና በሀገር ላይ የሚኖረው ተጨባጭ ማሳያ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሬት የረገጠ እውነታ ነው። ለአብነት ያህል፣ በዓለም ሁለተኛውና ለአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ መጀመሩ እና ከዩኤንዲፒ ጋር በመተባበር የተመረቀው 'AI UniPod' ማዕከል ለወጣቶች የተፈጠረ ትልቅ የቴክኖሎጂ መሠረት ነው። ተቋማቱ ከሀገር ውስጥ አልፎ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል በማመቻቸት ላይ መሆናቸው፣ ኢትዮጵያ የአህጉሪቱ የፈጠራ ማዕከል ሆና እንድትቀጥል የሚያስችላት የትውልድ አሻራ ነው። የሞባይል ተጠቃሚዎችን ቁጥር 128 ሚሊዮን ለማድረስ እንዲሁም የ5G ኔትወርክ ተደራሽነትን ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ የተነደፈው ዕቅድ፣ በከተማና በገጠር መካከል የነበረውን የዲጂታል ክፍተት በማጥበብ የመረጃ እኩልነትን የሚያረጋግጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው። እንደ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከመሳሰሉ መሠረተ ልማቶች ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራው ይህ እቅድ፣ የዜጎችን ተደራሽነት በማስፋት እኩል እድል የሚፈጥር አሰራርን ይዘረጋል። ይህ የዲጂታል መረብ መስፋፋት የዜጎችን ኑሮ በጥራት ከማሻሻል ባለፈ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲቀላጠፉ ትልቅ አቅም ይፈጥራል። የመንግሥት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ ለማድረግ የሚከናወነው አሰራር ግልጽነትን በማስፈን በዜጎችና በተቋማት መካከል መተማመንን ያጎለብታል። ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የዛሬን ስኬት ብቻ ሳይሆን የወደፊቱን ትውልድ አዕምሮ በዕውቀትና በፈጠራ ብርሃን በመቅረጽ የሀገርን የሰው ሀብት በዘላቂነት የሚያለማ የዕድገት ምሰሶ ነው። ስትራቴጂው ካነጣጠረባቸው ቁልፍ ነጥቦች መካከል ተደራሽነትን ማስፋት፣ እኩል እድል መፍጠር እና በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ይገኙበታል። ግልጽነት የሰፈነበት፣ ከወረቀትና ከቢሮክራሲ የጸዳ አሰራር መዘርጋቱ ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ላይ ያላቸውን እምነት ያጠናክራል። ይህ ደግሞ ማህበራዊ መተሳሰርን አጠናክሮ ለአንድነትና ለጋራ ብልጽግና መሰረት የሚጥል ትውልድ ተሻጋሪ ስራም ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ሥራ ዕድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት የወጣቶችን ፈጠራ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም መቀየር ያስችላል። ወጣቱ በዲጂታል ንግድ፣ በሶፍትዌር ልማት እና በዲጂታል አገልግሎቶች ላይ ተሰማርቶ በራሱ ጥረት እያደገ ሲሄድ፣ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ መሠረት የጸና ይሆናል። የዲጂታል ኢኮኖሚ እያደገ ሲሄድ የሳይበር ደህንነት እና የመረጃ ጥበቃ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የሳይበር ደህንነት መሠረተ ልማቶችን ማጠናከሩን እንደ ዋና ዕቅድ ይዞ መንቀሳቀሱ ዜጎችና ተቋማት በአስተማማኝ ዲጂታል ምህዳር ውስጥ እንዲኖሩ ያስችላል። ቴክኖሎጂ የሉዓላዊነት ሌላኛው መገለጫ በመሆኑ፣ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማትን ማስፋት ወሳኝ ነው። መረጃዎች በውጭ አካላት ቁጥጥር ስር ሲሆኑ የሀገር ደህንነት አደጋ ላይ ይወድቃል። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የመረጃ ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም በመፍጠር ለነገው ትውልድ የባለቤትነት ስሜት ያጎናጸፋል። ወጣቶች በሮቦቲክስ፣ በዳታ ሳይንስ እና በሶፍትዌር ልማት ላይ ሲሰማሩ፣ ችግሮችን በፈጠራ ሃሳብ የሚፈቱ አዳዲስ ጅምሮች ይፈጠራሉ። ይህም የወጣቱን የእውቀት አቅምና ክህሎት ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ውጤት በመቀየር ለቀጣዩ ትውልድ ራሱን የቻለ የኢኮኖሚ መሠረት ይጥላል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስኬት ከተቀናጀ የመደመር እሳቤ ጋር የሚተሳሰር ነው። ነገን የተረጋጋ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና የምናረጋግጥበት ሁነኛ መንገድም ጭምር ።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና 
Jun 17, 2026 13088
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል።   የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።   የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 22358
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15386
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 21131
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 106556
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 80577
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 58904
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 56510
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 40267
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 40183
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 39634
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 38116
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 106556
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 80577
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 58904
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 56510
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
በጎነት የሰብዓዊ ክብር መሠረት፤ የመደመር መንግሥት የሰው ተኮር ልማት የተስፋ አድማስ
Sep 11, 2026 430
በጎነት ከኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት ኑሮና እንቅስቃሴ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ፣ ከራስ ቀንሶ ለሌሎች መድረስ የሚገለጽበት ከፍ ያለ ሰብዓዊ እሴት ነው። በጎነት የግለሰብን ችግር ብቻ የሚያቃልል ተግባር አይደለም። የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶችን በመሙላት አብሮነትን፣ መተሳሰብንና የጋራ ኃላፊነትን የሚያጠናክር የማህበራዊ ኃላፊነት ውልም ነው። ''ሃምሳ ሎሚ ለሃምሳ ሰው ጌጡ፤ ለአንድ ሰው ሸክሙ” እንዲል የሀገር ብሂል ሰዎች በአንድነት ቆመው ለአንድ መልካም ዓላማ ከተባበሩ ለመፍታት የማይቻል ችግር እንደሌለ በተግባር የሚያሳዩ ብዙ አብነቶች አሉ። በተለይም በሰው ተኮር ልማትና በበጎ ፈቃድ የሚከናወኑ የቤት ግንባታና እድሳት ሥራዎች ችግርን ከመቅረፍ ባለፈ የሰዎችን ሰብዓዊ ክብር የሚመልሱ የተስፋ ምንጭ ተግባራት ሆነዋል።   ባለፉት ዓመታት በሀገር አቀፍም ሆነ በአዲስ አበባ በበጋና ክረምት ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሮች በርካታ ዜጎችን ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉስቁልና ወደ ልዕልና እንዲሸጋገሩ አስችሏል። ከእነዚህ የሰው ተኮር ተግባራት ተጠቃሚ ከሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች መካከል በመኖሪያ ቤት ችግር ምክንያት ኑሯቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች ይገኙበታል። ቤት ለአንድ ሰው የመኖሪያ ቦታ ብቻ አይደለም። ይልቁንም የዜጎችን የደህንነት፣ የክብር፣ የመረጋጋትና ዘላቂ የተስፋ ወጋገን የሚያቆራኝ መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ለአንድ ቤተሰብ የሚገነባ ወይም የሚታደስ ቤት ከግንባታ ዕቃና ከግድግዳ በላይ ትርጉም አለው፤ የተሰበረ ተስፋን ይጠግናል፣ የተረሳ ክብርን ይመልሳል፣ ለነገም አዲስ እድል ይከፍታል። በአዲስ አበባ በበጎ ፈቃደኞች፣ በባለሀብቶችና በመንግሥት የጋራ ጥረት ቤት ተገንብቶላቸው እፎይታን ያገኙ ነፍሶችም በርካቶች ናቸው።   ወይዘሮ መስከረም ሰለሞን እንደሚሉት፤ ከዓመታት በፊት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ፒያሳ አካባቢ ለሰው ልጅ ክብርን በማይመጥን ጎስቋላ ቤት ውስጥ ሕይወትን ይመሩ ነበር። በተለይም ክረምት በመጣ ቁጥር የጎርፍና የዝናብ ፍሳሽ አደጋ በከፍተኛ ጭንቀት እንዲያሳልፉ ያስገድዳቸው እንደነበር አስታውሰዋል። በሳር ቤት አካባቢ በተሰራላቸው ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የተሰጣቸው የመኖሪያ ቤት አዲስ የሕይወት ተስፋን እንዳጎናጸፋቸው አስረድተዋል። ይህንም ለመኖር ከማይመች ቦታ ወጥቼ ወደ አማረ ቤት በመግባቴ እንደገና የመወለድ ያህል ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል ሲሉ ገልጸዋል። እንደ ወይዘሮ መስከረም ታሪክ ሁሉ የሌሎች ነዋሪዎች የቤት ግንባታና ዕድሳት ሥራዎች ተሞክሮ የሚያሳየው የቁሳዊ እፎይታ ብቻ ሳይሆኑ ሰብዓዊ ክብርን የሚያጎናጽፉ የተስፋ ውጤቶች መሆናቸውን ነው።   በአንድ ወቅት ከፎቅ ላይ ባጋጠማት የመውደቅ አደጋ ሳቢያ የአካል ጉዳት ያጋጠማት ታሪክ ሙሉጌታ፤ በአዲስ አበባ በኪራይና በመንግሥት ቤት ከቤተሰቧ ጋር ሕይወትን ስትገፋ እንደነበር ገልጻለች። የአካል ጉዳተኛ ከሆነች በኋላ ቀደም ሲል ትኖርበት የነበረው ቤትና አካባቢ ከቦታ ቦታ እንደልብ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ እንደነበር በማስታወስ፤ ከቤተሰቧ ጋር ይኖሩበት ከነበረው ባምቢስ አካባቢ ወደ ሳር ቤት አካባቢ የመኖሪያ ቤት ማግኘቷ በሕይወት ዘመን ያገኘሁት ትልቅ የተስፋ ስጦታዬ ነው ብላለች። ቤቱ እንደልብ መንቀሳቀስ የሚያስችል፣ መሠረታዊ የመኖሪያነት መስፈርቶች የተሟላላት መሆኑ ሕይወቴን በትልቅ እፎይታ እንድመራ አስችሎኛል ስትል ተናግራለች። በሰው ተኮር ፕሮጀክት የሚገነቡ ቤቶች የሚያመጡት ለውጥ ለአካል ጉዳተኞች ብቻ የሚወሰን አይደለም። በቤት ውስጥ ልጆች፣ አረጋውያን፣ የሀገር ባለውለታዎችና መላ ቤተሰብ እንዲሁም የተሻለ ኑሮን ለመፍጠር የሚታገሉ እናቶችና አባቶችም የዚህ ተግባር ተጠቃሚዎች ናቸው። በዚህም በጎነት የአንድን ሰው ዛሬ ከማሻሻል ባለፈ የአንድ ቤተሰብን ነገ የሚቀርጽ ኃይል መሆኑን ያሳያል።   ወይዘሮ ጽጌሬዳ ጎበና ፤ ለረጅም ዓመታት ፒያሳ አካባቢ ለመኖር ምቹ ባልሆነ ቤትና ሰፈር ከአንድ ልጃቸው ጋር ይኖሩ ነበር። በፒያሳ አካባቢ የሕይወት ቆይታ ዘመናቸውም ልዩ ድጋፍ የምትሻው ልጃቸው እንደልቧ መንቀሳቀስ የማትችልበትን በርካታ የሰቆቃ ጊዜያት እንዳሳለፈች አስታውሰዋል። በዚህ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ እያሉ በሳር ቤት አካባቢ አዲስ ቤት ማግኘታቸው እንደገና የመወለድ ያህል ትልቅ እፎይታን እንደቸራቸው ገልጸዋል። የተሰጣቸው ቤት ለልጃቸው እንቅስቃሴ ምቹ ከመሆኑ ባለፈ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን እንዲከተሉ ያስቻለ ታላቅ የሕይወት ብስራት መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ ታሪኮች የሚያስረዱት አንድ ቤት ሲታደስ ግድግዳና ጣሪያ ብቻ አለመሆኑን ነው። ከቤቱ ጋር የነዋሪው ተስፋ፣ የቤተሰቡ መረጋጋትና የሰው ልጅ ክብርም አብሮ ይታደሳል። በዚህም በጎነት የችግር መፍቻ ብቻ ሳይሆን ከጊዜ ጊዜ የተስፋ ማስፈንጠሪያና ሰብዓዊ ክብር ማጎናጸፊያ ተግባር እየሆነ መጥቷል።   በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤታቸው ከታደሰላቸው መካከል ታየሁ መኮንን እንደሚሉት፤ ቀደም ሲል ይኖሩበት የነበረው ቤት 'ቤት ነው ለማለት እንኳን አያስደፍርም' ነበር። ዛሬ ግን ታሪካቸው ተቀይሯል። በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት የመኖሪያ ቤት ችግራቸው ተቀርፎ፣ 'ቤቴ በመታደሱ ያለ ሀሳብ ጎኔን ማሳረፍ ችያለሁ' ሲሉም ወይዘሮ ታየሁ ገልጸዋል። ይህ አንድ ነዋሪ ያገኘው የቤት ለውጥ ብቻ አይደለም። ከዓመታት የጭንቀት ኑሮ ወደ መረጋጋት የተሸጋገረ ሕይወት ነው። ከስጋት ወደ እፎይታ፣ ከተስፋ መቁረጥ ወደ ተስፋ የተደረገ ጉዞ ነው። ለበርካታ ዓመታት በማይመች ቤት ኑሮ ሲገፉ እንደቆዩ የገለጹት ወይዘሮ ዘውዲቱ ገብረማርያም ደግሞ፤ አሁን ላይ ቤታቸው በመታደሱ ደስ ብሏቸው የሚኖሩበትን ዕድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።   በሰው ተኮር የልማት መርሃ ግብር አቅመ ደካማ ወገኖችን ለመደገፍ የሚከናወኑ ተግባራትም የበርካቶችን ተስፋ የሚያለመልም አስደናቂ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ የነዋሪዎች ምስክርነቶች በጎነት በተግባር ሲገለጽ የሰውን ክብር እንደሚያጎናጽፍ፣ የተሰበረ ተስፋን እንደሚያድስና ለነገ የሚያስብ ሕይወትን እንደሚፈጥር ያረጋግጣሉ። በተለይም እናቶች፣ አረጋውያን፣ አቅመ ደካሞችና የሀገር ባለውለታዎች የሚያገኙት ድጋፍ በቁሳዊ እርዳታ ብቻ የሚመዘን ሳይሆን 'እናንተም የዚህ ሀገር ክብር ናችሁ' የሚልን ሰብዓዊ መልዕክትን ያስተላልፋል። በዚህ ረገድ የመደመር መንግሥት ሰው ተኮር ልማትን እንደ የልማት ፖሊሲ አቅጣጫ በመያዝ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶች በመሙላት ተስፋን የሚያለመልሙ ተግባራትን እያጠናከረ ይገኛል። የቤት ግንባታና ዕድሳት፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችና ሌሎች ሰው ተኮር መርሃ ግብሮችም ይህንኑ አቅጣጫ በተግባር ከሚያሳዩ ተጨባጭ ለውጦች መካከል ይጠቀሳሉ። አስተያየት ሰጪዎቹ ዛሬ ላይ ውብና ጽዱ በሆነ ቤት የሚኖሩበት ዕድል የተፈጠረው መንግሥት፣ ባለሀብቶችና ሌሎች በጎ ፈቃደኞች ባከናወኑት መልካም ተግባር በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በአዲስ አበባ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት አረጋውያንን፣ አቅመ ደካሞችና የሀገር ባለውለታዎችን አመቺ መጠለያ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። በእርግጥም የበጎነት ዋጋው በሚሰጠው የቁሳቁስ መጠን ብቻ አይለካም። በሰው ልብ ውስጥ በሚፈጥረው ተስፋና በሕይወት ላይ በሚያመጣው ለውጥ ይመዘናል። የተሰራው ቤት ለአንዲት እናት የእፎይታ ምንጭ፣ ለአንድ አረጋዊ የክብር መገኛ፣ ለአካል ጉዳተኛ ደግሞ በራስ መተማመንና ነፃነት መገለጫ ይሆናሉ።   ይህም ሰው ተኮር ልማት ማለት ትልልቅ ፕሮጀክቶችን መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ የአንድ ዜጋን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል፣ የአንድ ቤተሰብን ተስፋ ማደስና የአንድን ሰው ክብር ማስመለስ ጭምር መሆኑን ያሳያል። በጎነት ከአንድ ሰው ወደ ሌላው የሚሸጋገር ቀላል የመልካም ተግባር መገለጫ ቢመስልም በጋራ ሲተገበር ማኅበረሰብን የመለወጥ ታላቅ ኃይል አለው። የእነዚህ ነዋሪዎች ታሪክም ይህንኑ ያረጋግጣል። ከተስፋ መቁረጥ ወደ ተስፋ፣ ከስጋት ወደ እፎይታ፣ ከአስቸጋሪ ኑሮ ወደ የተሻለ ኑሮ የተሸጋገሩ ሕይወቶችን ያሳያል። ስለሆነም በጎነትን እንደ የአንድ ጊዜ ዘመቻ ሳይሆን እንደ የማኅበረሰብ የጋራ እሴት ማጠናከር፣ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖችን መደገፍና ሰው ተኮር ልማትን ማስቀጠል የጋራ ኃላፊነት ነው። ዛሬ የተሰራ ቤት ከግድግዳ በላይ ነው። የነገ ተስፋ መሰረት ነው። ዛሬ የተዘረጋ የበጎነት እጅም ከአንድ ሰው የሚተርፍ ለብዙዎች የሚደርስ የሰብዓዊነት ብርሃን ነው።
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 1368
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።   በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው።   በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም