ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ የችግኝ ተከላ አካሄዱ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ የችግኝ ተከላ አካሄዱ
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው በዘንድሮው ዓመት «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ ነው የችግኝ ተከላ ያካሄዱት።
የ2018 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መጠናቀቅን ስናበስር የተተከለው እያንዳንዱ ችግኝ የሕብረታችን፣ የሕዳሴያችንና የዘላቂ እድገታችን ሕያው ምልክት መሆኑን በማስታወስ መሆኑንም አስታውቋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በጽኑ አንድነታችንና በጋራ ጥረታችን የታነጸች፣ የበለጸገችና ብሩህ ኢትዮጵያን ለማየት ሙሉ ተስፋ ሰንቀን ወደፊት እንገሰግሳለን ሲልም መልእክት አስተላልፏል።