ቀጥታ፡

ሲዳማ ቡና የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):- በካፍ ሻምፒዮንስ የመጀመሪያ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ሲዳማ ቡና ከቻዱ ኤግሎንስ ጋር ዛሬ ሁለተኛ ጨዋታውን ያከናውናል።

ጨዋታው ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል።

ሁለቱ ክለቦች ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በቻድ ንጃሚና ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

በጨዋታው ላይ ሲዳማ ቡና ጠንካራ የመከላከል እንስቃሴ ያሳየ ቢሆንም ግልጽ የግብ እድሎች መፍጠር ላይ ክፍተቶች ታይተውበታል።

በአንጻሩ ተጋጣሚው አይግሎንስ በቆሙ ኳሶች እና በመልሶ ማጥቃት እንቅሰቃሴ ግብ ለማስቆጠር ሙከራዎችን አድርጓል።

ሲዳማ ቡና ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የማጥቃት አቅሙን ማሻሻል ይጠበቅበታል።  ከተጋጣሚው በኩል ከቆሙ ኳሶችና ከፈጣን ሽግግሮች የሚመጡ ኳሶችን መግታት ይጠበቅበታል።

በያሬድ ገመቹ  የሚመራው ሲዳማ ቡና በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የበቃው የ2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንመሆኑን ተከትሎ ነው።

በ1999 ዓ.ም የተቋቋመው ሲዳማ ቡና በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ሲዳማ ቡና በዛሬው ጨዋታ ማሸነፍ ወደ ሁለተኛው ዙር ያሳልፈዋል።

ሲዳማ ቡና በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከሱዳኑ አል ሂላል እና ከብሩንዲው አይግል ኑዋር አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም