ሲዳማ ቡና ቻዱ ክለብ ኤግሎስን 3ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና ቻዱ ክለብ ኤግሎስን 3ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
አዲስ አበባ፤መስከረም 3 /2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያን በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ እየወከለ የሚገኘው ሲዳማ ቡና ቻዱ ክለብ ኤግሎስን 3ለ0 በማሸነፍ ወደ ሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ማለፉን አረጋግጧል።
የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች አቤል ያለው ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር እና ደስታ ደሙ ቀሪዋን ማስቆጠር ችለዋል። በሁለተኛው ዙር ሲዳማ ቡና ከሱዳኑ ክለብ አል ሂላል ጋር የሚጫወት ይሆናል።