ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፦

✍️የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና ይጫወታል

✍️ሀገራት ቀውሶች ከመከሰታቸው በፊት የመቋቋም አቅም ሊገነቡ ይገባል።በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ ፈተናን መቋቋም የሚያስችሉ ስርዓቶችን እየገነባች ትገኛለች

✍️መንግስት በምግብ ዋስትና ላይ ባከናወነው ተግባር ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ ስንዴ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ ወጥታ ራሷን ችላለች

✍️ኢትዮጵያ ለታቀደው የብሪክስ የሰብል ልውውጥ ማዕቀፍ (BRICS Grain Exchange) እንደ አምራችም ሆነ አቅራቢ ሆና ለመሳተፍ ዝግጁ ናት

✍️ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የሚያጋጥሙ ቀውሶችን ለመቋቋም የሀገር ውስጥ የማምረት አቅሟን እያሳደገች ነው። የፋርማሲዩቲካልና የመድኃኒት ማምረቻዎችንም እያስፋፋች ነው

✍️በቴክኖሎጂው ዘርፍ ዲጂታል መሠረተ ልማት፣ ዲጂታል መታወቂያ (Digital ID)፣ የክፍያ ሥርዓቶች እና የመረጃ ልውውጥ በስፋት እየተገነቡ ነው

✍️መረጃዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ በሕግ አግባብ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ነው።ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ይህንን ለውጥ የበለጠ ያጠናክረዋል

✍️በቀጣዩ ትውልድ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ይበልጥ ሰዎችን ማገልገል፣ ብዙ ቋንቋዎችን መረዳት እና ሰፊ የሰው ልጅ እውቀት ማካተት አለበት

✍️አፍሪካ የነገውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን በባለቤትነት ለመምራት የምርምር፣ የኮምፒውቲንግ አቅም፣ ክህሎት እና ተቋማት ያስፈልጋሉ

✍️ኢትዮጵያ አፍሪካን የሚወክል የቴክኖሎጂ አቅም ለመገንባት ከብሪክስ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት አላት

✍️አፍሪካ የበርካታ ማዕድናት ሀብት ባለቤት ናት።የብሪክስ አባል ሀገራት ደግሞ የካፒታል፣ የቴክኖሎጂ እና የገበያ አማራጭ አላቸው

✍️ኢትዮጵያ በማዕድናት፣ በታዳሽ ኢነርጂ እና እያደገ ያለውን የኢንዱስትሪ አቅሟን መሰረት ባደረገ መልኩ አጋርነቶችን ለመፍጠር ዝግጁ ናት

✍️ ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የምታቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል ለሀገራቱ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

✍️ሀገራት በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ያላቸው ውክልና ፍትሃዊና ውክልናውም ተጨባጭ ውጤት ማምጣት አለበት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም