ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‎ውይይታችን በመከላከያ እና ደኅንነት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኖሎጂ መስኮች ያለንን ትብብር ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል። 


 

እንዲሁም የትምህርት ልምድ ልውውጦችን ማስፋት፣ በባህል እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል ነው ያሉት። 

‎በተጨማሪም ለኮፕ 32 በሚደረገው ዝግጅት ያለን አጋርነት ጨምሮ ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውንም አስታውቀዋል። 

በወል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረቱ የንግድ እና የኢኮኖሚ ልውውጦችን ይበልጥ ለማስፋፋትም በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን አረጋግጠዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም