ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ እና ቻይና ሁለገብ ወታደራዊ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ
Nov 3, 2026 43
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ እና ቻይና ሁለገብ ወታደራዊ ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ። የመከላከያ ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ሁለቱ ሀገራት የቆየና ፍሬያማ የሆነውን ወታደራዊና ስትራቴጂካዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከርና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚሠሩ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ ሁለቱ ሀገራት ረጅም ዘመን የተሻገረና በብዙ መስኮች ፍሬያማ የሆነ አጋርነት እንዳላቸው ጠቁመው፤ በተለይም በወታደራዊ ዘርፍ የቆየውን ጠንካራ ግንኙነት በማስቀጠል፣ በወታደራዊ ኢንዱስትሪ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በሥልጠና ዕድሎች በኩል ያለውን ትብብር ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ አስምረውበታል። በተጨማሪም አቶ መሐመድ እድሪስ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማስከበር እየሄደችበት ያለው ፍትሐዊ ጥረት ለቀጣናው እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ሰላምና መረጋጋት አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው በማረጋገጥ፣ ቻይና ከኢትዮጵያ ጎን እንድትቆም ጠይቀዋል። በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ በበኩላቸው፤ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወታደራዊና ስትራቴጂካዊ ትብብር የበለጠ ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል። በተለይም በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚደረጉ አጋርነቶችንና በኢንቨስትመንት በኩል የተመዘገቡ ፍሬያማ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከምንግዜውም በላይ ቻይና ዝግጁ መሆኗን እንደገለጹ የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ እና ቻይና ሁለገብ ወታደራዊ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ
Nov 3, 2026 28

ሀረር ከተማ የአለም አቀፉ የሀር መንገድ የቱሪዝም ጥምረት አባል ከተማ ሆነች
Nov 3, 2026 56
ሀረር፣ ጥቅምት 24/ 2019 (ኢዜአ):- የሀረር ከተማ የአለም አቀፉ የሀር መንገድ የቱሪዝሞ ጥምረት (the International Tourism Alliance of Silk Road Cities) አባል ከተማ ሆነች። ከተማዋ የዚህ አለም አቀፍ የቱሪዝም ጥምረት አባል መሆኗ በአለም የቱሪዝም መስክ የጎላ ትኩረት እንድትስብ፣ ጎብኚዎችን ከተለያየ አለም ክፍል ለመሳብ፣ የከተማዋ ቅርሶችና የቱሪዝም መስህቦችን በይበልጥ ለማስተዋወቅ፣ ከጥምረቱ አባል ሀገራት ጋር በትብብርና በጋራ ለመስራት፣ ዘርፉን ለማሳደግ የሚያስችል ልምድ ለመለዋወጥና ቱሪዝሙን በይበልጥ ለማልማት ከፍተኛ ዕገዛ ያደርጋል ተብሏል። ከተማዋ የጥምረቱ አባል የሆነችውም በቻይና ሉዣን ከተማ ዛሬ በተካሄደው የ2026 የሀር መንገድ የቱሪዝም ጥምረት አባል ከተሞች አመታዊ አለም አቀፍ የጉዞ ኤጀንቶች ኮንፈረንስ ላይ ነው። የሀረር ከተማ በአለም አቀፉ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳዬንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ ሁለት የሚዳሰስና የማይዳሰስ አለም አቀፍ ቅርሶችን ያስመዘገበች፣ የአለም የቅርስ ከተሞች ድርጅት አባል፣ የአለም የቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን እና ሌሎች አለም አቀፍ ጥምረቶች አባል መሆኗ ይታወሳል።
ለአፍሪካ ዴሞክራሲ መጻኢ ጉዞ በዓድዋ ጥላ ሥር
Nov 3, 2026 65
አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት፣ የሰው ኃይልና የብዙ ዕድሎች ባለቤት ስትሆን፣ ይህንን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ የልማት ውጤት ለመቀየር የፖለቲካ አመራርና የኢኮኖሚ ዕድገት ትስስር ወሳኝ ነው። ይህንን አህጉራዊ አጀንዳ የሚያስቀድመው ሁለተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ከጥቅምት 26 እስከ 28 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። በሀገራት መሪዎች፣በፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ በፖሊሲ አውጪዎችና በተለያዩ ዘርፎች ተወካዮች ጨምሮ በርካታ ተሳታፊዎች በሚታደሙበት በዚህ ታላቅ ጉባኤ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአፍሪካ ሁለንተናዊ እድገት ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉበት ይጠበቃል። ይህ ጉባኤ በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄዱ የጥቁር ሕዝቦች ነፃነት መነሻ፣የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ጽኑ መሠረት እና የአፍሪካውያን የአንድነትና የድል አርማ ከሆነው ታሪካዊ ሁነት ጋር ያገናኘዋል።ዛሬም በዓድዋ ጥላ ሥር አፍሪካውያን መሪዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድነት ተሰባስበው የአህጉራችንን የዴሞክራሲ መጻኢ ዕጣ ፈንታ መወያየታቸው ያለፉትን አባቶች አርቆ አስተዋይነትና ተጋድሎ የሚዋጅ ታሪካዊ ክስተት ነው። የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ የሆነችው እና በመደመር እሳቤ እየተተገበረ ያለው የኮሪደር ልማት ገጽታዋን በመቀየር አፍሪካን የምታኮራ ተምሳሌታዊ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫና ከሥልጣን ውድድር ባለፈ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ለውጥ የሚመሩ ፖሊሲዎችንና ዘላቂ የልማት ስትራቴጂዎችን ላይ በጋራ ድምጻቸውቅን ያሰማሉ። በጋና አክራ የተካሄደው የመጀመሪያው ጉባኤ በዴሞክራሲ፣ በአካታች አስተዳደርና ልማትን በሚያስቀድም ፖለቲካ ላይ የጋራ ቁርጠኝነትን ያስቀመጠ ሲሆን፣የአዲስ አበባው ጉባኤ ደግሞ ይህንን ቁርጠኝነት ወደ ተግባራዊ ለውጥ የሚያሸጋግር ነው።ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድንና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፎች ያስመዘገበቻቸውን ስኬታማ ተሞክሮዎች በጉባኤው እንደምታቀርብም ይጠበቃል። የአፍሪካ የወደፊት ዴሞክራሲ እውን ሊሆን የሚችለው አህጉራችን ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታና የባህል እሴቶች ባገናዘበ መልኩ፣ በጋራ በመተሳሰብና በልዩነቶች ውስጥ አንድነትን ማጠናከር ሲቻል ነው። አሁን ላይ የአፍርካን የኢኮኖሚ ነፃነትን እና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት የዓድዋ መንፈስ የቀጣይ ዘመን መገለጫ እንዲሆን ይጠይቃል።በዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄደው ይህ ውይይት አፍሪካውያን የራሳቸውን ዕጣ ፈንታ በራሳቸው የሚወስኑበት፣ ጠንካራ ተቋማት የሚገነቡበት እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማጠናከር የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል። ዓድዋ የትናንት የአፍሪካዊያን ታሪክ ብቻ ሳይሆን፣ የነገው የአፍሪካ ዴሞክራሲ እና የነፃነት ብርሃን ማማ ነው።ሁለተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤም በዚሁ ታሪካዊ ስፍራ መካሄዱ አህጉራችን በአንድነት፣ በሰላም እና በጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓተ-መንግስት የተገነባ ብሩህ ተስፋ እንዳላት በሰፊው የሚያረጋግጥ ነው።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የፋይናንስ ዘርፉ ጤናማ እድገት እንዲኖረው አስተዋፅኦ አድርጓል
Nov 3, 2026 87
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦አገር አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የፋይናንስ ዘርፉ ጤናማ እድገት እንዲኖረው አስተዋፅኦ ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ። የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ባደረገው ስምንተኛ ስብሰባ ውሳኔ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በሩብ ዓመቱ የሸቀጦች የወጪ ንግድ፣ በተለይም የወርቅና የቡና አፈፃፀም ገቢ አዎንታዊ ዕድገት ማሳየቱንና የገቢ ሸቀጦች እድገትም ከፍተኛ ነው። አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የፋይናንስ ዘርፉ ጤናማ ዕድገት እንዲኖረው ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል። ማሻሻያው በአጠቃላይ የፋይናንስ ዘርፉ ብሄራዊ ባንክ ካስቀመጠው የአነስተኛ መስፈርት በእጅጉ የላቀ ደረጃ ላይ እንዲገኝ አስችሏል ብለዋል። ከአቅርቦት ችግር ጋር በተያያዘ ከፍ ብሎ የነበረው የዋጋ ግሽበት መቀነስ ያሳየ ቢሆንም በመስከረም 2019 ዓ.ም የታየው 14 ነጥብ 9 በመቶ ግን ከባንኩ የነጠላ አሃዝ የዋጋ ግሽበት ግብ አንጻር ከፍተኛ መሆኑን ኮሚቴው ገምግሟል ብለዋል። በመስከረም 2019 ለታየው የዋጋ ግሽበት በተለይ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ተከትሎ የተፈጠረ የአቅርቦት ችግር ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ኮሚቴው መገንዘቡን አመልክተዋል። ኮሚቴው የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ዕድገት ተጠናክሮ እንደቀጠለ መገንዘቡንና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አመላካቾች በ2019 በጀት ዓመትም የተጠናከረ እድገት እንደሚኖር እንደሚያመላክቱም ገዥው ተናግረዋል። በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በሲሚንቶ ምርት፣ በኤሌክትሪክ ማመንጫና በብረታ ብረት ነክ ምርቶች ላይ መሻሻል መታየቱን አስረድተዋል። በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የባንክ ዘርፉ ዝቅተኛ የተበላሸ ብድርና በቂ ካፒታል ያለው በመሆኑ ጤናማና የተረጋጋ ሆኖ መቀጠሉን ገልጸዋል። የበጀት ፖሊሲ ስርዓት ጥንቃቄ የተሞላበትና ከብሄራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ እንዲሁም ከአጠቃላይ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ጋር የተናበበ መሆኑን ኮሚቴው መገንዘቡንም አስረድተዋል። ፖሊሲው ከብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲና ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ጋር የተናበበ መሆኑን ገልጸዋል። መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ብድር ሳይወስድ ከ27 ወራት በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ ይህም የዋጋ ግሽበቱን ለማረጋጋት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ፖለቲካ

ለኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት የትኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ሁሌም ዝግጁ ነን - የሠራዊት አባላት
Nov 3, 2026 82
ጅማ ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦ ለኢትዮጵያ ክብርና ሉአላዊነት መከበርና ለዜጎች ዘላቂ ሰላም የትኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ሁሌም ዝግጁ መሆናቸውን በሀገር መከላከያ ሰራዊት የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ የሠራዊት አመራሮችና አባላት ገለጹ። የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ አመራሮችና አባላት የሰሜን እዝ የተከዳበትንና ግፍ የተሰራበትን ጥቅምት 24 በማሰብ የውይይትና ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮችን አካሂደዋል። የሰሜን ዕዝ ባልደረባ የነበሩትና አሁን ላይ በዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ኃላፊ የሆኑት ኮሎኔል ሌቺሳ መገርሳ፣ የጥቅምት 24 በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመው ክህደትና ጥቃት የካሃዲዎችና ባንዳዎች እኩይ ተግባር መሆኑን አስታውሰዋል። በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲህ አይነቱን አስቸጋሪ ጊዜ በጽናት በማለፍ ሀገሩንና ህዝቡን በላቀ ዝግጁነት በማገልገል ላይ ይገኛል ብለዋል። የሀገር አለኝታና የሕዝብ መሰረት ያለው ሠራዊት በመሆኑ በህዝቡ ድጋፍ ትብብርና እገዛ ዛሬ ላይ በጠንካራ ቁመና እና የላቀ ዝግጁነት ላይ የሚገኝ መሆኑን ተናግረዋል። የእዙ የሕክምና ዳይሬክተር ኮሎኔል ፍቃዱ ወልደሰንበት፣ ሰራዊቱ በሰው ኃይል፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በውጊያ አቅም የማይበገር አቅም የገነባ መሆኑን አንስተዋል። ለኢትዮጵያ ክብርና ሉአላዊነት መከበርና ለዜጎች ዘላቂ ሰላም የትኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ሁሌም ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል። የቀድሞ የሰሜን ዕዝ ባልደረቦች የነበሩትና አሁን ላይ የዳሎል እዝ መኮንኖች መቶ አለቃ ዘርትሁን ካሳው እና ሻለቃ ባሻ በሀይሉ፤ መከላከያ ሠራዊት ሀገሩን እና ህዝቡን ለማገልገል በላቀ ዝግጁነት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። በሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመው የታሪክ ጠባሳ ሲታወስ ይበልጥ ብርታትና ጥንካሬ የሚሰንቁበትና ለላቀ ሀገራዊ ተልእኮ የሚዘጋጁበት መሆኑን የእዙ አመራሮችና አባላት በመድረኩ ላይ አረጋግጠዋል።
መከላከያ ሰራዊት ጥቅምት 24 የተፈፀመበትን ክህደት በጽናት አልፎ በተደራጀና በላቀ መልኩ እየተገነባ ነው
Nov 3, 2026 182
ባህር ዳር ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦መከላከያ ሰራዊት ጥቅምት 24 የተፈፀመበትን ክህደት በጽናት አልፎ በተደራጀና በላቀ መልኩ እየተገነባ መሆኑን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የበጀትና ፕሮግራም ኃላፊ ኮሎኔል ምህረት ሽፈራው ገለጹ። በሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመውን ክህደት በማሰብ "እንዳይደገም ሁሌም እንዘክራለን" በሚል መሪ ሐሳብ በባህር ዳር ከተማ መኮድ የፓናል ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የበጀትና ፕሮግራም ኃላፊ ኮሎኔል ምህረት ሽፈራው፤ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ የተፈፀመበትን ክህደት በጽናት አልፎ ዛሬ ላይ የላቀና የተደራጀ የሰራዊት ቁመና ማኖሩን አንስተዋል። በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት እንዲሁም የዜጎችን ሰላም በማፅናት ሀገራዊ አደራውን በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። የምሥራቅ ዕዝ ግንባታና ጽሑፍ ዝግጅት ኃላፊ ሻለቃ ሰመረ እሸቱ፤ በመድረኩ ላይ ባቀረቡት የመወያያ መነሻ ጽሁፍ ጥቅምት 24 ቀን የሰሜን ዕዝ በባንዳዎች ከጀርባው የተወጋበትና የተከዳበት መጥፎ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም ሰራዊቱ የከፈለውን ዋጋ በማሰብ ይህንን የጥፋትና የክህደት ድርጊት ትውልዱ በቅጡ እንዲያውቀው ማድረግ ይገባል ብለዋል። የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የስታፍ አባል ሻለቃ ዘውድነህ ሙሉጌታ እና የምሥራቅ ዕዝ ስታፍ ባልደረባ መቶ አለቃ ብርሃኑ ገመዳ፤ በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የፈጸመው የጭካኔ ተግባር ሁልጊዜም የምናስበው ነው ሲሉ ተናግረዋል። በመኮድ በተዘጋጀው የፓናል ውይይትና የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ላይ የምሥራቅ እና የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች እና የስታፍ አባላት ተገኝተዋል።
ሱ-35 ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶች የኢትዮጵያን ወታደራዊ አቅም እና ቀጣናዊ ሚና የሚያሳድጉ ናቸው-እስራኤላዊው ጋዜጠኛ ኤዲ ኮሄን
Nov 3, 2026 145
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በቅርቡ ከሩሲያ የተቀበለቻቸው ሱ-35 (Su-35) ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶች ወታደራዊ አቅም እና በቀጣናው ያላትን ሚና በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ መሆናቸውን የእስራኤሉ ቻናል 14 ጋዜጠኛ እና ተመራማሪ ኤዲ ኮሄን ገለጹ። ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን 12 የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች (Su-35 4++ Generation) ባለፈው ሳምንት ከሩሲያ ተረክባለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት በሩሲያ ተገኝተው የጦር ጄቶችን በተረከቡበት ወቅት ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይሏ እያደረገች ያለው ዝግጁነት ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ እያላበሳት ይገኛል ብለዋል። ይህ ታሪካዊ ስኬት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን፣ ወደፊትም የጋራ ደህንነታችንን እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የምናደርገውን ጉዞ በልበ ሙሉነት እንድንቀጥል ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል። የእስራኤሉ ቻናል 14 ጋዜጠኛ እና ተመራማሪ ኤዲ ኮሄን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ የነበሩባትን መሰናክሎች በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶቿ እና በጠንካራ ዓለም አቀፍ ግንኙነቷ በመሻገር ከሩሲያ ጋር የነበራትን ስምምነት በተሳካ ሁኔታ መፈጸም መቻሏን ተናግረዋል። ይህም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ግንኙነቷን የመምራት እና ስትራቴጂካዊ ጥቅሟን የማስከበር አቅሟ ማደጉን በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በቅርቡ ከሩሲያ የተቀበለቻቸው ሱ-35 (Su-35) ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶች ወታደራዊ አቅም እና በቀጣናው ያላትን ተፅዕኖ በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ መሆናቸውንም ነው ያነሱት። የግብፅና የዐረብ መገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያን ወታደራዊ ዕድገት በቅርበት እየተከታተሉት እንደሚገኙና አገሪቱ አየር ኃይሏን ማጠናከሯ በግብፅ በኩል ትልቅ ስጋት መፍጠሩን ተናግረዋል። በተጨማሪም ኮሄን የግብፅን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተችተዋል። ግብጽ ቀጣናዊ ለውጦችን የሚመጥን ግልጽ የፖለቲካ ራዕይ እንደሚጎድላት ገልጸው፤ እየጨመረ የመጣው የውስጥ ኢኮኖሚ ውጥረት እና የፖለቲካ ፈተናዎች የግብፅ አመራር አገሪቱን የመምራት ብቃት ላይ ጥያቄዎችን እያስነሳ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ እንዲህ ያሉ ዘመናዊ ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት መካከል ቀዳሚዋ ሆናለች። ይህም ሀገሪቷ የጠላት ጥቃትን የመከላከልና የማክሸፍ አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ እንድታጠናከር አስችሏታል።
የተጀመሩትን የልማት ስራዎች ለማስቀጠል የተገኘውን ሰላም በማጽናት ተግባር ውስጥ የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ ነው
Nov 3, 2026 122
አምቦ፤ ጥቅምት 24/2019(ኢዜአ)፡- በከተማው የተጀመሩትን የልማት ስራዎች ለማስቀጠል የተገኘውን ሰላም በማጽናት ውስጥ የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የአምቦ ከተማ ከንቲባ አቶ ደጄኔ ተረፈ ገለጹ፡፡ በየደረጃው ያሉ የፖሊስ አባላት፣ የሥራ ሃላፊዎች እና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የተሳተፉበት የሰላም ምክክር መድረክ ዛሬ በአምቦ ከተማ ተካሂዷል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የአምቦ ከተማ ከንቲባ አቶ ደጄኔ ተረፈ እንዳሉት፤ የከተማው ህብረተሰብ ዋነኛ ፍላጎት የሕግ የበላይነት ተከብሮ ከሰላም ስጋት ነፃ ሆኖ የልማት ሥራዎችን ማከናወን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በከተማው ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ አካላትን ህብረተሰቡ በአንድነት ከመንግስት የፀጥታ አካላት ጎን በመቆምና በአንድነት በመደራጀት አካባቢውን በንቃት መጠበቅ እንዳለበትም ተናግረዋል። በተለይም የጸረ ሰላም ቡድኖች ፍላጎት እንዳይሳካና የተረጋጋ ሰላም እንዲሰፍን በማድረጉ ረገድ ህዝቡ የማይተካ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ በዜጎች ተሳትፎ ሰላምን በማጽናት ሰፋፊ የልማት ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት ጠንካራ ሀገር መገንባት መሆኑን በመጥቀስ፤ ሕብረተሰቡ ሰላሙን በመጠበቅና የከተማዋን የልማት ሥራዎች በማፋጠን የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል። በውይይቱ ላይ የተገኙት የከተማው ነዋሪ አቶ ፈይሳ ዱጉማ በበኩላቸው፤ ሰላምን ለማስፈን የፖሊስ፣ የሚሊሻ እና የጋቸና ሲርና አባላት በአንድነት ከህብረተሰቡ ጋር በመቆምና በመተባበር መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ የተገኘውን ሰላም በማጽናት ውስጥ የህብረተሰቡ በተለይም የወጣቶች ሚና የጎላ መሆኑን በማንሳት፤ ሰላምን በመጠበቅ በከተማው እየተከናወኑ ያሉትን የልማት ስራዎች አጠናክረን ማስቀጠል ይገባናል ብለዋል፡፡ የከተማውን ሰላም በመጠበቅ እየተሰሩ ያሉትን የልማት ስራዎች እንዴት ማገዝ እንዳለባቸው ከውይይቱ ሰፊ ትምህርት ማግኘቷን የተናገረችው ደግሞ ወጣት ውባየሁ ጌታነህ ናት፡፡ ወጣቷ አክላም ሁሉም የከተማው ህብረተሰብ በመተሳሰብና በአንድነት በመቆም በከተማው የሰፈነውን ሰላም በመጠበቅ የአምቦን ከማሳደግ አልፈን ሀገራችን የያዘችውን የእድገት ጎዳና ማፋጠን ይገባናል ብላለች፡፡
አመራሩ የአገልግሎት ፍጥነትና ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ በትኩረት ሊሰራ ይገባል-ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
Nov 3, 2026 119
ባህር ዳር፤ጥቅምት 24/2019(ኢዜአ)፦አመራሩ በሁሉም ዘርፎች ምርታማነትን በማሳደግና የአገልግሎት ፍጥነትና ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ አሳሰቡ። የአማራ ክልል የ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተጀምሯል። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አረጋ ከበደ በመድረኩ እንዳሉት፣ የክልሉን የተፈጥሮ ሀብትና የመልማት አቅም አሟጦ በመጠቀም ይገባል። የመደመር መንግሥት የአመራሩንና የተቋማትን የመፈጸም አቅም በማሳደግ ሥራዎችን ከረጅም ጊዜ ግብና ፍላጎት አንጻር ታሳቢ በማድረግ እያከናወነ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ባለፉት ወራት በርካታ ውጤታማ ሥራዎችን ማከናወን እንደተቻለ አንስተው፣ በቀጣይ ወራት በላቀ ንቅናቄና ቅንጅት ተግባራትን ዘላቂ ለውጥ በሚያመጣ አግባብ እንደሚከናወኑ ገልጸዋል። አመራሩ የአፈጻጸሙን ጥንካሬና ድክመቶች በመለየት፣በሁሉም ዘርፎች ምርታማነትን በማሳደግና የአገልግሎት ፍጥነትና ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል። የብልጽግና ፓርቲ አማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ ባቀረቡት ጽሑፍ እንዳብራሩት፣ብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች የላቀ የመሪነት ሚናውን እየተወጣ ይገኛል። በተለይም ለግጭት ምክንያት የሆኑ የተዛቡ ትርክቶችን በማረም፣ ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ እና የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል በማዳበር ረገድ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣በአገልግሎትና ገበያን በማረጋጋት ረገድ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልጸው በትምህርት፣በጤና፣ መሠረተ ልማትን በማስፋፋትና በሌሎች ዘርፎችም ዕድገት መመዝገቡን አቶ ይርጋ ጠቅሰዋል። ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በማጠናቀቅ አዲስ የሥራ ባህል መገንባቱን ያመለከቱት ኃላፊው፣ በዚህም ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ ለአገልግሎት በማብቃት ረገድ ፓርቲው የመሪነት ሚናውን በተግባር ማሳየቱን ገልጸዋል። በቀጣይ ወራትም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በማረጋገጥ፣ የሴቶችንና ወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማሳደግና ሕገ ወጥነትንና ሙስናን በመከላከል ረገድ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አመልክተዋል። አመራሩ ወቅታዊ ፈተናዎችን ተጋፍጦ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀጣይም የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ፈጥሮ ተግባራትን በላቀ ንቅናቄ መተግበር እንዳለበትም አስገንዝበዋል። መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የፓርቲና የመንግሥት የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶች እና ረቂቅ ደንብ አጸደቀ
Nov 3, 2026 122
ድሬደዋ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፦ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 4ተኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት የመጀመሪያ አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችና ረቂቅ ደንብ በማፅደቅ ተጠናቀቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎችና ምክትል ሰብሳቢዎች እንዲሁም የፅህፈት ቤት ኃላፊ ሹመቶችን አጽድቋል። በዚሁ መሰረት ፦ -ወይዘሮ ከሪማ አሊ የምክር ቤቱ የህግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ -ወይዘሮ ሰአዳ አዋሌን የግብርና፣ ተፈጥሮ ሃብት እና የአካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ -ወይዘሮ ሚስራ አብደላ የሴቶችና ወጣቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፣ -አቶ ቢቂላ ታደሰ የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል። ጉባኤው በተጨማሪም ምክትል ሰብሳቢዎችና አባላት ሹመትን ያፀደቀ ሲሆን የአስተዳደሩ ይግባኝ ሰሚና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ሹመትንም አፅድቋል። ከነዚህ በተጨማሪም በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አብዱላሂ አደም አቅራቢነት አምስት አባላት ያካተተ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ሹመትንም አጽድቋል። ከንቲባው የድሬዳዋ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ የቦርድ ሰብሳቢዎች እና አባላትን ያቀረቡ ሲሆን የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ የቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ማሞ ምክትል ሰብሳቢ በመሆን ተሹመዋል። ምክር ቤቱ ከዚሁ ጎን ለጎን የድሬዳዋ አስተዳደር ንብረት ታክስ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ጫልቱ ሁሴን የፀደቀው ረቂቅ የንብረት አስተዳደር ታክስ ከከተማዋ ዕድገትና የህዝብ መጨመር ጋር ተያይዘው ለሚቀርቡ ማህበራዊ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል። ገቢን ከየዘርፉ በአግባቡ በመሰብሰብ ከከተማው ዕድገት ጋር የሚጣጣም መሠረተ ልማት ለመዘርጋት፣ የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በፍጥነት ለመመለስ እንደሚያስችል ገልፀዋል። የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች አመራሮችና አባላት መደራጀት ምክርቤቱ ለሚያካሂደው እና ለተጣለበት ታላቅ የህዝብ ተልዕኮ መሳካት ወሳኝ ሚና እንደሚያበረክት ተናግረዋል።

ማህበራዊ
የመቀሌ እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ሥራ ጀመሩ
Nov 3, 2026 93
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦ የመቀሌ እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ሥራ መጀመራቸውን ዛሬ አስታውቀዋል። የአክሱምና የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን እየተቀበሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት አዲስና ነባር ተማሪዎቻቸውን በመቀበል የመማር ማስተማር ሥራ ጀምረዋል። የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዓብደልቃድር ከድር (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ገቢና ነባር ተማሪዎችን በመቀበል መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ መጀመሩን አስታውቀዋል። በትምህርት ዘመኑ በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመቀበል ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ አስረድተዋል። የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው አዲስና ነባር ከ1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን በመቀበል በተያዘው ሳምንት የመማር ማስተማር ሥራ ጀምሯል። በአሁኑ ወቅትም በክልሉ ተፈጥሮ በነበረው ወቅታዊ ሁኔታ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ራያ ዩኒቨርሲቲ ተመልሰው እየገቡ መሆኑን አስታውቀዋል። የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ከጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ገቢና ነባር ተማሪዎችን ቅበላ እየተካሄደ ነው ያሉት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ገብረየሱስ ብርሃነ ናቸው። ተማሪዎችንም በተለያዩ የትራንስፖርት አማራጮች ደማቅ አቀባበል በማድረግ የተሟላ የመማር ማስተማር ሥራን ለማስጀመር ሙሉ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል። በዚህም የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ዘመኑ ወደ ስድስት ሺህ የሚጠጉ አዲስ ገቢና ነባር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ሥራ መገባቱን አስረድተዋል። የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ገብረሚካኤል ወልደገብርኤል (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ 1 ሺህ 500 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ጨምሮ የነባር ቅበላ እየተካሄደ ነው ብለዋል። የትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲውን የመማር ማስተማር መስተጓጎል ሂደት በመገምገም ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ተማሪዎችን በመቀበል መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ እየተገባ መሆኑን አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው የሚሰጡትን መመሪያዎችና ደንቦች በአግባቡ በመከተል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና ለውጤት እንዲተጉ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የታሪክና ቅርስ ጥበቃ ስራ ታሪክን ለመጪው ትውልድ ለማቆየት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል
Nov 3, 2026 172
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የታሪክና ቅርስ ጥበቃ ስራ ታሪክን ለመጪው ትውልድ ለማቆየት ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የውጭ ሀገራት ዜጎች ገለፁ። ከካፒታል ማርኬት ተቋማት ጋር ለሶስት ቀናት የሚቆይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በኢትዮጵያ ቆይታ ያደረገው የታንዛንያ ልዑካን ቡድን፣ የሀገሪቱን የታሪክ ሃብት፣ ባህል እና የቅርስ አጠባበቅ ጥረቶች ለመመልከት አንድነት ፓርክን እና የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል። የልዑካን ቡድኑ አባል የሆኑት ማርቲን ደብሊው፤ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ ታሪካዊ ኹነቶችን በስርዓት በመሰነድ ታሪክን ለትውልድ ለማሻገር የጀመረችው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው። በተለይም ጎብኚዎች የሀገሪቱን ታሪካዊ እድገት በጥቅሉ እንዲረዱ ማስቻሉ በእጅጉ እንዳስደመማቸው ገልጸዋል። የታሪክ መረጃዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በዲጂታል ስርዓት መቅረባቸውን አድንቀው፤ ይህም አቀራረብ ቅርሶችን ለመጠበቅ እና የታሪክ መረጃዎችን ለመጪው ትውልድ ተደራሽ ለማድረግ ውጤታማ መንገድ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ ልምድ ለታንዛንያ በተለይም ታሪካዊ እድገቶችን በስርዓት በመሰነድ እንዲሁም ሳይንስና ቴክኖሎጂን ሀገራዊ ቅርሶችን ለመጠበቅ በመተግበር ረገድ ጠቃሚ ትምህርት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። እንዲሁም የዲጂታል መድረኮች የጎብኚዎችን የታሪካዊ ቦታዎች ግንዛቤ ለማሳደግ ያላቸውን ትምህርታዊ እሴት በማጉላት፣ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ከኢትዮጵያ አቀራረብ ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ሌላኛው የልዑካን ቡድኑ አባል ኤሊያድ ኢ. ምንደሜ በበኩላቸው፣ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ያደረጉት ጉብኝት ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ በተለይም ታሪካዊው የዓድዋ ድል ጋር ተያይዞ የነበራቸውን ግንዛቤ እንዳሰፋላቸው ተናግረዋል። የድል መታሰቢያውን መጎብኘታቸው ስለ ታሪካዊ ኹነቶቹ እና ኢትዮጵያውያን ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር ያሳዩትን ጀግንነትና ቁርጠኝነት የበለጠ ግልጽ ግንዛቤ እንደሰጣቸው ገልጸዋል። በዚህም የሀገሪቱን ታሪካዊ ቅርስ ለመጠበቅ የሚደረገውን ጥረት ያደነቁ ሲሆን፣ ዘመናዊ ቁሳቁሶቹና አጠቃላይ ሰነዶቹ ለወጣቱ ትውልድ አስፈላጊ የትምህርት ምንጭ ሆነው እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል። አክለውም ፤ያለፈው ትውልድ የከፈለውን መስዋዕትነትና ያሳየውን ፅናት ለወጣቶች በማስተማር የሀገራቸውን መፃኢ ዕድል እንዲቀርፁ የሚያደርግ ጥሩ አጋጣሚ ነው ብለዋል። ታንዛንያውያኑ ጎብኚዎች፤ ታሪካዊ ቅርሶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የመሰነድ፣ የመጠበቅ እና የማቅረብን አስፈላጊነት አጽንኦት የሰጡ ሲሆን፣ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሃሳብ ሰጥተዋል።
ኮሌጁ በሚሰጣቸው ስልጠናዎች ተጠቅመን በተሰማራንበት የስራ መስክ ውጤታማ ሆነናል
Nov 3, 2026 96
ጂንካ፣ ጥቅምት 24 / 2019 (ኢዜአ) ፡-የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሚሰጣቸው አጫጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች ተጠቅመን በተሰማራንበት የስራ መስክ ውጤታማ ሆነናል ሲሉ የኮሌጁ ሰልጣኞች ተናገሩ። የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ1994 ዓ/ም ተመስርቶ ለጂንካና ለአካባቢው ማህበረሰብ አጫጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና በመስጠት እገዛ እያደረገ የሚገኝ ኮሌጅ ሲሆን፣ አሁን ላይ 650 የሚሆኑ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል። በኮሌጁ የሚሰጡ አጫጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን ወስደው በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ የተሰማሩ ዜጎች፣ ከኮሌጁ በቀሰሙት እውቀት ተቀጥረው ከመስራት ባለፈ ሌሎችን ቀጥረው በማሰራት ረገድ ስኬታማ መሆናቸውን ይናገራሉ። በጂንካ ከተማ የሚገኘው "የነገው ሰው እንጨትና ብረታ ብረት ስራ ማህበር" ስራ አስኪያጅ ወጣት ዳዊት እርኮ፣ ኮሌጁ በሚሰጣቸው አጫጭር ስልጠናዎች ተጠቃሚ መሆኑን ገልጿል። በድርጅቱ እየሰሩ የሚገኙ ሰራተኞችም የአቅም ግንባታ ስልጠና በማግኘት ውጤታማ እንዲሆኑ እንዳገዛቸው ተናግሯል። "ኮሌጁ እያደረገ ያለው ድጋፍ ለስራችን ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል" ብሏል። ኮሌጁ በተለይም ስለ ካይዘን ፍልስፍና፣ ስለ ሂሳብ አያያዝ፣ ስለ ከባድ ማሽን አጠቃቀምና ጥንቃቄ እንዲሁም ስለ ኢንተርፕሪነርሽፕ ስልጠና በመስጠት የማብቃት ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል። በጂንካ ከተማ የ"ባስልኤል ብረታ ብረት ስራ ማህበር" ባለቤት አቶ ጌታቸው ሙሐመድ በበኩላቸው፣ ኮሌጁ የሚሰጣቸው ስልጠናዎች ለአዳዲስ ፈጠራ ስራዎች የሚያነሳሱ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከኮሌጁ መምህራን ጋር በመተባበር የለውዝ መፈልፈያና መፍጫ ማሽን እንዲሁም የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽን በጋራ በመስራት ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል። ማህበሩ ለኮሌጁ ተማሪዎች በተግባር ልምምድ እውቀት የሚቀስሙበትን ሁኔታ ከኮሌጁ ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ካሳሁን ጌታቸው፣ ኮሌጁ በመካከለኛ ደረጃ ያለውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ችግር በመፍታት ረገድ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ኮሌጁ በእርሻ፣ በከብት፣ በዶሮና በዓሳ እርባታ፣ በንብ ማነብ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአውቶሞቲቭ፣ በሰርቬይንግ፣ በአይሲቲ እና በጋርመንት ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል። በተጨማሪም በእንስሳት ጤና አጠባበቅ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በኢንተርፕሪነርሽፕና በካይዘን ፍልስፍና የስልጠና መስኮች ለአካባቢው ማህበረሰብ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና በመስጠት የማብቃት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በርካቶች በኮሌጁ የተሰጣቸውን የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስልጠና በመጠቀም ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና የአካባቢውን ማህበረሰብ የሚጠቅም ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራ እየሰሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት መሻሻል ለአስቸኳይ ሕክምና ምላሽ አሰጣጥ ስኬት መሠረት ሆኗል
Nov 3, 2026 159
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት መሻሻል ለአስቸኳይ ሕክምና ምላሽ አሰጣጥ ስኬት መሠረት መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው 7ኛው የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የድንገተኛ ሕክምና ቡድኖች ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የዓለም ጤና ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት ጉባኤው እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ 7ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዓለም አቀፍ የአስቸኳይ ሕክምና ቡድኖች ጉባኤ እንድታስተናግድ መመረጧ ታላቅ ክብር ነው። ጉባኤው በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ መካሄዱ ከቦታ ለውጥ በላይ አፍሪካ በአለም አቀፍ የአስቸኳይ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ ረገድ አቅሟን፣ አመራሯንና ኃላፊነቷን እያሳደገች መሆኗን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የአደጋ ጊዜ የሕክምና ድጋፍ ቡድን መመስረቷን ገልጸው፤ ይህም ውጤታማ የአስቸኳይ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ ማንኛውም አደጋ ከመከሰቱ በፊት በሚደረግ ዝግጅት እንደሚጀምር በመገንዘብ መሆኑን ተናግረዋል። ቡድኑ በአገር ውስጥ የተለያዩ ተልዕኮዎችን ማከናወኑንና በኢትዮጵያ በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ማኅበረሰቦች አገልግሎት መስጠቱን ጠቁመዋል። በተጨማሪም የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ያቀፈ ብሔራዊ የምላሽ ቡድን መሰማራቱንና አጋርነታቸውን ከድንበር ባሻገር ማሳየታቸውን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋሚ የአስቸኳይ ሕክምና ቡድን በዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ የደረጃ አንድ እውቅና እንደተሰጠው ገልጸው፤ በዚህም በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ከመጀመሪያዎቹ የሲቪል የአስቸኳይ ሕክምና ቡድኖች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል። የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ሕክምና ምላሽ አሰጣጥ ስኬት አጠቃላይ ከጤና ሥርዓቱ መሻሻል ጋር የተያያዘ መሆኑንም ተናግረዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው፣ የአስቸኳይ ሕክምና ቡድኖች በዓለም አቀፍ የጤና ድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰጪ የሰው ኃይል ውስጥ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል። ከ42 አገራት የተውጣጡ 77 ቡድኖች በዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ ምደባ ማግኘታቸውን ገልጸው፤ ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋሚ የአስቸኳይ ሕክምና ቡድን እንደሚገኝበት ተናግረዋል። ይህም በአፍሪካ ዓለም አቀፍ ምደባ ያገኘ የመጀመሪያው የሲቪል የአስቸኳይ ሕክምና ቡድን መሆኑንም ጠቁመዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ማንኛውም ሀገር የጤና ድንገተኛ አደጋን ብቻውን እንዳይጋፈጥ በቀጣይነት መሥራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ ያኩብ ጃናቢ በዚህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአህጉሪቱ በሚካሄደው ጉባኤ አፍሪካ እንደ እንግዳ ተሳታፊ ሳይሆን፣ እንደ መሪና የውይይቱ አጀንዳ ቀራጭ ሆና መገኘቷን ያመለክታል ብለዋል። አፍሪካ በየዓመቱ ከፍተኛ የሕዝብ ጤና አደጋዎች እንደሚጋጥሟት ጠቁመው፣ መንግሥታት የገቡትን ቃል ኪዳን ወደ ብሔራዊ ዕቅድ እንዲቀይሩም ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መልካሙ አብቴ ፣ ጉባኤው ለልምድ ልውውጥ፣ ለትብብርና ለጋራ እርምጃ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር፣ ከክልል ጤና ተቋማት፣ ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት በመሥራት ይህንን አጀንዳ በማሳደግ ረገድ ቁልፍ ሚና መጫወቱን አብራርተዋል።
ኢኮኖሚ
ሀረር ከተማ የአለም አቀፉ የሀር መንገድ የቱሪዝም ጥምረት አባል ከተማ ሆነች
Nov 3, 2026 56
ሀረር፣ ጥቅምት 24/ 2019 (ኢዜአ):- የሀረር ከተማ የአለም አቀፉ የሀር መንገድ የቱሪዝሞ ጥምረት (the International Tourism Alliance of Silk Road Cities) አባል ከተማ ሆነች። ከተማዋ የዚህ አለም አቀፍ የቱሪዝም ጥምረት አባል መሆኗ በአለም የቱሪዝም መስክ የጎላ ትኩረት እንድትስብ፣ ጎብኚዎችን ከተለያየ አለም ክፍል ለመሳብ፣ የከተማዋ ቅርሶችና የቱሪዝም መስህቦችን በይበልጥ ለማስተዋወቅ፣ ከጥምረቱ አባል ሀገራት ጋር በትብብርና በጋራ ለመስራት፣ ዘርፉን ለማሳደግ የሚያስችል ልምድ ለመለዋወጥና ቱሪዝሙን በይበልጥ ለማልማት ከፍተኛ ዕገዛ ያደርጋል ተብሏል። ከተማዋ የጥምረቱ አባል የሆነችውም በቻይና ሉዣን ከተማ ዛሬ በተካሄደው የ2026 የሀር መንገድ የቱሪዝም ጥምረት አባል ከተሞች አመታዊ አለም አቀፍ የጉዞ ኤጀንቶች ኮንፈረንስ ላይ ነው። የሀረር ከተማ በአለም አቀፉ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳዬንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ ሁለት የሚዳሰስና የማይዳሰስ አለም አቀፍ ቅርሶችን ያስመዘገበች፣ የአለም የቅርስ ከተሞች ድርጅት አባል፣ የአለም የቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን እና ሌሎች አለም አቀፍ ጥምረቶች አባል መሆኗ ይታወሳል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የፋይናንስ ዘርፉ ጤናማ እድገት እንዲኖረው አስተዋፅኦ አድርጓል
Nov 3, 2026 87
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦አገር አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የፋይናንስ ዘርፉ ጤናማ እድገት እንዲኖረው አስተዋፅኦ ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ። የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ባደረገው ስምንተኛ ስብሰባ ውሳኔ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በሩብ ዓመቱ የሸቀጦች የወጪ ንግድ፣ በተለይም የወርቅና የቡና አፈፃፀም ገቢ አዎንታዊ ዕድገት ማሳየቱንና የገቢ ሸቀጦች እድገትም ከፍተኛ ነው። አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የፋይናንስ ዘርፉ ጤናማ ዕድገት እንዲኖረው ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል። ማሻሻያው በአጠቃላይ የፋይናንስ ዘርፉ ብሄራዊ ባንክ ካስቀመጠው የአነስተኛ መስፈርት በእጅጉ የላቀ ደረጃ ላይ እንዲገኝ አስችሏል ብለዋል። ከአቅርቦት ችግር ጋር በተያያዘ ከፍ ብሎ የነበረው የዋጋ ግሽበት መቀነስ ያሳየ ቢሆንም በመስከረም 2019 ዓ.ም የታየው 14 ነጥብ 9 በመቶ ግን ከባንኩ የነጠላ አሃዝ የዋጋ ግሽበት ግብ አንጻር ከፍተኛ መሆኑን ኮሚቴው ገምግሟል ብለዋል። በመስከረም 2019 ለታየው የዋጋ ግሽበት በተለይ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ተከትሎ የተፈጠረ የአቅርቦት ችግር ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ኮሚቴው መገንዘቡን አመልክተዋል። ኮሚቴው የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ዕድገት ተጠናክሮ እንደቀጠለ መገንዘቡንና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አመላካቾች በ2019 በጀት ዓመትም የተጠናከረ እድገት እንደሚኖር እንደሚያመላክቱም ገዥው ተናግረዋል። በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በሲሚንቶ ምርት፣ በኤሌክትሪክ ማመንጫና በብረታ ብረት ነክ ምርቶች ላይ መሻሻል መታየቱን አስረድተዋል። በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የባንክ ዘርፉ ዝቅተኛ የተበላሸ ብድርና በቂ ካፒታል ያለው በመሆኑ ጤናማና የተረጋጋ ሆኖ መቀጠሉን ገልጸዋል። የበጀት ፖሊሲ ስርዓት ጥንቃቄ የተሞላበትና ከብሄራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ እንዲሁም ከአጠቃላይ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ጋር የተናበበ መሆኑን ኮሚቴው መገንዘቡንም አስረድተዋል። ፖሊሲው ከብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲና ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ጋር የተናበበ መሆኑን ገልጸዋል። መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ብድር ሳይወስድ ከ27 ወራት በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ ይህም የዋጋ ግሽበቱን ለማረጋጋት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ እና ቻይና በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና በአቅም ግንባታ መስኮች ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
Nov 3, 2026 92
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 24/2019(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ቻይና በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና በአቅም ግንባታ መስኮች ያለውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የሆኑትን አምባሳደር ቼን ሃይን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ሚኒስትሩ ከአምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ውይይት በሁኔታዎች የማይለወጠውን የኢትዮጵያ እና የቻይና ስትራቴጂካዊ ትብብር የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። ሁለቱ አገራት በተለይም በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና በአቅም ግንባታ መስኮች ያለውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል። በውይይቱ ወቅት የቻይናው አምባሳደር ቼን ሃይ ሀገራቸው የመደመር መንግሥት ትልሞች ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
የአፋር ክልል የቱሪዝም ፀጋዎች የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያሳደጉ ነው
Nov 3, 2026 89
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦ በአፋር ክልል የሚገኙ ተፈጥሯዊና ባህላዊ የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማት የህዝቡን ዘላቂ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። የትልቅ ሀገር ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተጋች ትገኛለች። በዚህም የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግና የሀገራችንን ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ጸጋዎች በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ባለፉት ጥቂት ዓመታት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። እነዚህ የተቀናጁ ጥረቶች ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ግዙፍ አቅም ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ጥቅም በመቀየር የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ይገኛሉ። የአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ የፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ አብዱ አህመድ ለኢዜአ እንዳሉት፤ መንግሥት የክልሉን የቱሪዝም አቅም ለማሳደግ የመዳረሻና የመሠረተ ልማት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ከዚህም ባለፈ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ በሆቴል፣ በሎጅ፣ በሪዞርትና በተለያዩ የቱሪዝም አገልግሎቶች ላይ እንዲሳተፉ ምቹ የሥራ ከባቢ ተፈጥሯል ብለዋል። የቱሪዝም ልማት ከመዳረሻዎችና መሠረተ ልማት ግንባታ ባሻገር ማኅበረሰቡን በጽዳት፣ ምግብ አቅርቦት፣ በአስጎብኝነትና በሌሎችም አገልግሎቶች ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። የአፋር ህዝብ ሰው አክባሪና እንግዳ ተቀባይ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የክልሉን ዓመታዊ የጎብኝዎች ቁጥር ከአምስት ሺህ ወደ 40 ሺህ ለማሳደግ ዕቅድ ተይዟል ብለዋል። ለዚህም በሰመራና በዙሪያዋ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን በውሃና ኤሌክትሪክ አቅርቦት፣ በመንገድና መጠለያ አገልግሎቶች ለማስተሳሰር፤ ታሪካዊና ሳይንሳዊ ቅርሶችን በመጠበቅ ለጎብኚዎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት ለኢንቨስትመንት ተስማሚ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በመለየት የመሬት አቀማመጥ፣ የግንባታ ዲዛይንና የኢንቨስትመንት አዋጭነት መረጃዎችን እያዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም ባለሃብቶች የአፋር ክልል ያለውን እምቅ የቱሪዝም አቅም እንዲረዱ እንደሚያደርግ ገልጸው፤ በኤርታሌ አካባቢ የጎብኝዎችን ቆይታ ለማራዘም ለሎጅ ግንባታ ፈቃድ መሰጠቱንም ገልጸዋል። በአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ የፓርኩን ጥበቃ ለማጠናከርና በሰውና በዱር እንስሳት መካከል የሚከሰተው መቀራረብ ችግር እንዳይፈጥር አጥር መሰራቱን እና የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በአላይደጌና በሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎች የመሰረተ ልማት ማስፋፊያዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ የሰመራ ከተማ የኮሪደር ልማት ቱሪስቶች ወደ ክልሉ ሲመጡ ምቹ ከባቢ ይፈጥራል ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በክልሉ ዜጎች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ነው
Nov 3, 2026 68
ጎንደር ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ በማዘመን ዜጎች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂክ ትግበራና አጠቃላይ የዲጂታል አገልግሎትን ማሳለጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በጎንደር ከተማ የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት የዴሊቨሪ ዩኒት ሃላፊ አቶ ሞገስ ተኬ፤ የዲጂታል ስትራቴጂክ ትግበራና የአገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም በክልሉ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለ5 ሚሊዮን ዜጎች የዲጅታል ክህሎት ስልጠና ለመስጠት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚሁ መሰረት በዘንድሮው በጀት ዓመት ሦስት ወራት ብቻ ከ300 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች ስልጠናው መሰጠቱን አንስተዋል። በክልሉ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ በማዘመን ዜጎች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል። የአማራ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አማረ ዓለሙ፤ በዚህ ዘመን የዲጂታል መሰረተ ልማት ለኢኮኖሚ እድገት ዋነኛ መሰረት መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም በክልሉ የዲጂታል ስትራቴጂክ ትግበራን በማሳለጥ፣ በዘርፉ ብቁ የሰው ሃብት በማፍራትና የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የተሻለ ስኬት ለማስመዝገብ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ኒውክሊየር ኃይል የኢትዮጵያን የወደፊት የኃይል ፍላጎት በአስተማማኝ መልኩ ለማሟላት የሚያስችል ነው
Nov 3, 2026 149
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ) ፦ ኒውክሊየር ኃይል በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሟላት የሚያስችል መሆኑን የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሽፈራው ተሊላ ገለጹ። ምክትል ኮሚሽነሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት፣ የከተሞች መስፋፋት፣ የሕዝብ ቁጥር መጨመርና የኢንዱስትሪ ልማት የኃይል ፍላጎትን እያሳደገው መሆኑን ጠቁመዋል። በተለይም ኢንዱስትሪዎችና የዲጂታል ኢኮኖሚው ዘርፎች ያልተቋረጠ የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሚፈልጉ መሆኑን አውስተው፤ ለዚህም አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው የኃይል ምንጭ የማልማትን አስፈላጊነት ገልጸዋል። በዚህ ረገድ የውሃ፣ የፀሐይ፣ የንፋስና የጂኦተርማል ኃይል ልማትን ከማስቀጠል ጎን ለጎን፣ ኒውክሌር ኃይል ከፍተኛ የኃይል ማመንጨት አቅም ያለውና ያልተቋረጠ አቅርቦት ሊያረጋግጥ የሚችል አማራጭ መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብርን ለማስፈጸም የወሰነችው የወደፊቱን የኢኮኖሚ እድገት የሚደግፍና የኃይል አቅርቦትን የሚያረጋግጥ ምንጭ ለማልማት መሆኑን ጠቅሰዋል። ኒውክሊየር ኃይል ከኤሌክትሪክ ማመንጨት ባለፈ በጤና፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በምርምር ዘርፎች ሰፊ ጥቅም የሚሰጥ ቴክኖሎጂ መሆኑን አንስተው፤ በጤናው ዘርፍ ለሕክምና ምርመራ፣ ለካንሰር ሕክምናና ለመድኃኒቶች ምርት፤ በግብርና ደግሞ ለሰብል ምርታማነት ማሻሻያ፣ ለተባይ ቁጥጥርና ለምግብ ጥበቃ እንደሚውል አስረድተዋል። ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ወደ አንድ ዓመት እየተቃረበው መሆኑን አንስተው፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ተቋሙን የማደራጀት፣ የሰው ኃይልና የሥራ ቦታ የማሟላት፣ እንዲሁም ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ተቋሙን ወደ ሥራ የማስገባት ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል። ኮሚሽኑ የኒውክሊየር ኃይል ፕሮግራምን የሚመራ ስትራቴጂ የማዘጋጀት፣ የሀገር ውስጥ አቅም የመገንባትና በዘርፉ የሚሳተፉ ተቋማትን የማስተባበር ኃላፊነት እንደተሰጠው ጠቁመዋል። በቀጣይ የቁፋሮና የጂኦቴክኒክ ጥናቶች በማካሄድ የማመንጫው ትክክለኛ ቦታ የሚወሰን ሲሆን፤ የኒውክሊየር ደህንነት፣ የቴክኒክ መስፈርቶች፣ የሕዝብና የአካባቢ ተስማሚነት እንዲሁም የመሠረተ ልማት ተደራሽነት በጥናቱ የሚገመገሙ መሆኑን አብራርተዋል። ከዚህ ጎን ለጎን የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫውን የሚያስተዳድሩና የሚያንቀሳቅሱ ባለሙያዎችን ማሰልጠን የፕሮግራሙ ቁልፍ ሥራ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም የሀገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች ከኒውክሊየር ቴክኖሎጂ ጋር ተያያዥ የሆኑ የትምህርት ሥርዓቶችን በማሻሻል፣ በዘርፉ የሚያስፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል በሀገር ውስጥ ለማፍራት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። የኒውክሊየር ቴክኖሎጂን በትምህርት፣ በምርምርና በጥናት በመደገፍ አጠቃቀሙንና የማስተዳደር አቅሙን ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸው፤ ይህም ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ላይ የራሷን አቅም እየገነባች በመሄድ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነቷን ለማጠናከር እንደሚያግዝ አብራርተዋል። በኤሌክትሪክ ማመንጨት ሂደት ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለው ቴክኖሎጂ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ኢትዮጵያ የምትከተለውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ በመደገፍ ለዘላቂ የኃይል ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው
Nov 3, 2026 150
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፦የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የተገልጋዮችን እርካታ በማሻሻል የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ አመርቂ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የፌዴራል መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ገለጸ። በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንተነህ ማሞ አስታውቀዋል። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የፌዴራል መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንተነህ ማሞ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከ113 በላይ በሆኑ ማዕከላት ከ1 ሺህ 600 በላይ አገልግሎቶች እየተሰጡ ነው። የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትም የተገልጋዮችን እርካታ 99 ከመቶ በማድረስ ፈጣንና ዘመናዊ የአገልግሎት ምኅዳር መፈጠሩን ገልጸዋል። በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እየተስፋፋ የመጣው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትም የአገልግሎት ተደራሽነትን በማሳለጥ የመልካም አስተዳደርን እያስፈነ መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመመካር የጋራ መግባባት መደረሱን አብራርተዋል። በመቀሌ ከተማ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሲጀመርም ለክልሉ ሕዝብ ፈጣንና ዘመናዊ አገልግሎት ለማቅረብ ዕድል እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሰመረ ጅራታ በበኩላቸው፤ አገልግሎቱ የማኅበረሰቡን እንግልት በማስቀረት ከፍተኛ ፋይዳ እያበረከተ ነው ብለዋል። በክልሉም አራት የመሶብ አንድ ማዕከላትን ወደ ሥራ በማስገባት የተገልጋዮችን እርካታ ወደ 98 በመቶ ማድረስ ያስቻለ የተሳለጠና ዘመናዊ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመትም የመሶብ አንድ ማዕከላትን ወደ 14 ወረዳዎች ለማስፋት የዲዛይን፣ የቦታ መረጣ፣ የእድሳት ግምገማና የካፒታል ወጪ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አብራርተዋል። የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የተገልጋዮችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ አገልግሎት እየቀረበ ነው ያሉት ደግሞ የሲዳማ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንግዳየሁ ዘውዴ ናቸው። በሐዋሳ ከተማና ሌሎች ከተሞች የተገነቡ የመሶብ አንድ ማዕከላትም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የአገልግሎት ልምምድን እያጎለበተ መሆኑን አንስተዋል። የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ማዕከል ብዙ የመንግሥት አገልግሎቶችን በማቅረብ የዜጎችን የአገልግሎት ተደራሽነትና እርካታ በማሳደግ የሕዝብና መንግሥትን እምነት እያጎለበተ ነው ብለዋል።
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በፍጥነት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው- የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር)
Nov 2, 2026 269
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር )በሌሎች አካባቢዎች የታየው ፈጣንና ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ በመቐለ ከተማም በፍጥነት እንዲጀምር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። በመቐለ ከተማ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በፍጥነት ለማስጀመርና የህዝብን የእለት ተእለት ፍላጎት በዘመናዊ መልኩ ለማሟላት የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል። የፌደራል የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አመራሮች እና ሞያተኞች በመቐለ ከተማ በመገኘት አገልግሎቱን እውን ለማድረግ ከከተማዋ ባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር የተመካከሩ ሲሆን ይህም በትግራይ ክልል የተጀመረውን የሰላም ተስፋና ሀገራዊ የልማት ትስስር በተግባር ያረጋገጠ ምዕራፍ ሆኗል። በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የፌደራል የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዮናስ አለማየሁ እንደገለጹት አሁን ላይ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስተዋል። በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 114 አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር መስጠት የተቻለበት ደረጃ ላይ በመደረሱ የዜጎች እርካታ 99 በመቶ መድረሱንም ጠቅሰዋል። በሁሉም ክልሎች ይህ አሰራር በስፋት እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን በነበረው ነባራዊ ሁኔታ በትግራይ ክልል እስካሁን ሳይጀምር ቢቆይም አሁን ላይ የባለአደራ አስተዳደሩ አገልግሎቱን ለማስጀመር ያሳየውን ቁርጠኝነትና ዋና ስራ አስፈፃሚው አድንቀዋል። የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) በሌሎች አካባቢዎች የታየው ፈጣንና ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ በመቐለ ከተማም በፍጥነት እንዲጀምር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። በሌሎች ሀገራዊ አካባቢዎች በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የታየው የፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ተሞክሮ በትግራይ ክልልም በፍጥነት ሊተገበር እንደሚገባ ያነሱት ከንቲባው የፌደራል የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች፣ ስልጠና በመስጠትና የዕውቀት ሽግግር በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በተጨማሪም በሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ለሚገነቡ ማዕከላት በመቐለ ከተማ የሚሰራው አሰራር መነሻ ስለሚሆን በፍጥነት፣ በጥራትና በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ስፖርት
በመዲናዋ የተቀናጀ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ግንባታ የኢትዮጵያን የስፖርት ገጽታ ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ ይገኛል
Nov 3, 2026 84
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የተቀናጀ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ግንባታ የኢትዮጵያን የስፖርት ገጽታ ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ እንደሚገኝ የተለያዩ ስፖርት ዘርፍ አመራሮች ገለጹ። የመደመር መንግሥት በከተሞች ልማት ማዕቀፍ ውስጥ ትውልድን ታሳቢ ያደረጉ ዘመናዊና አካታች የስፖርት መሠረተ ልማቶችን በመገንባት የከተሞችን ገጽታ በተጨባጭ እያዘመነ ይገኛል። በተለይም በአዲስ አበባ የተገነቡት አዳዲስ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት ሕፃናትን፣ ወጣቶችን እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችንም ተጠቃሚ ማድረግ ችለዋል። እነዚህ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከመደገፍ ባለፈ ጤናማና አምራች ተተኪ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችል ዕድል ፈጥረዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ለኢዜአ እንዳሉት፤ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና ስታዲየሞች መገንባት ለአትሌቶች ውጤታማነት እና ታላላቅ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ከፍተኛ ሚና አላቸው። አደይ አበባ ስታዲየም ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ ጠብቆ እየተገነባ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም ለሀገሪቱ ስፖርት ዘርፍ ዕድገት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር በአብነት ጠቅሰዋል። በመዲናዋ የሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ለወደፊት ትውልድ እና ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ወሳኝ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ነው የተናገሩት። ጥራቱን የጠበቀ የስፖርት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በባለቤትነት ለማዘጋጀት የሚያስችል መሆኑንም አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ውሹ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ እያሱ ሰለሞን በበኩላቸው፣ በአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች በከተማ ልማት ተካተው መገንባታቸው በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ችለዋል። ቀደም ሲል በከተማዋ የማዘውተሪያ ሥፍራዎች እጥረት በመኖሩ ወጣቶች በጎዳናዎች ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ይገደዱ ነበር ብለዋል። አሁን ላይ የወጣቶችን ፍላጎት የሚመጥኑ የስፖርት ማዘውተሪያዎች በብዛትና በጥራት መገንባታቸው ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮችን መቅረፍ መቻሉን ተናግረዋል። እነዚህ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ለከተማዋ ውበትና ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማበርከታቸውም ባለፈ በአካል፣ በአእምሮ እና በጤና የበለጸገ አምራች ዜጋን በማፍራት ረገድ ትልቅ ሚና እያበረከቱ መሆኑንም አንስተዋል።
የአውሮፓ ምሽት፡ ፒኤስጂ ከቪያሪያል፣ ባርሴሎና ከአስቶንቪላ እና አትሌቲኮ ከባየር ሙኒክ የሚያደርጓቸው ተጠባቂ ፍልሚያዎች
Nov 3, 2026 141
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል። ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በስታዲዮ ዴላ ሴራሚካ ቪያሪያል ከፒኤስጂ ይጫወታሉ። ባለሜዳው ቪያሪያል በሶስት ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ፒኤስጂ በሊግ ምዕራፉ እስከ አሁን ያደረጋቸውን ሶስት ጨዋታዎችን በማሸነፍ በዘጠኝ ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዟል። ያለፉትን ተከታታይ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያነሳው ፒኤስጂ ጨዋታውን የማሸነፍ የቅድሚያ አግኝቷል። በሌላኛው መርሐ ግብር ባርሴሎና ከአስቶንቪላ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በካምፕ ኑ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ባርሴሎና በስድስት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። አስቶንቪላ በዘጠኝ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በሶስተኛው ዙር መርሐ ግብር በፒኤስጂ የ4 ለ 2 ሽንፈት ያስተናገደው ባርሴሎና ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። ተጋጣሚው አስቶንቪላ በድል ጉዞው ለመቀጠል ይፋለማል። ጨዋታው ተመልካችን የሚያዝናና እንቅስቃሴ ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል። በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም አትሌቲኮ ማድሪድ ከባየር ሙኒክ የሚያደርጉት ጨዋታም ትኩረትን ስቧል። የማድሪዱ ክለብ በአራት ነጥብ 16ኛ ደረጃን ሲይዝ ባየርን በአምስት ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሁለቱ ክለቦች በተመሳሳይ ባለፉት ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች አላሸነፉም። ቡድኖቹ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል። ማንችስተር ዩናይትድ ምሽት አምስት ላይ ሮማን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ያስተናገዳል። ባለፉት ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግ ሽንፈት ያስተናገደው ዩናይትድ በሶስት ነጥብ 20ኛ ደረጃን ይዟል። በሶስተኛው ዙር በኮሞ ያስተናገደው የ4 ለ 1 ሽንፈት ቡድኑን የበለጠ ጫና ውስጥ ከቶታል። ሮማ በአራት ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በሶስተኛው ዙር መርሐ ግብር ስሎቫን ብራቲስላቫን 4 ለ 0 ረትቷል። ጨዋታው ዩናይትድ ወደ ድል መንገድ ለመመለስ፣ ሮማ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ የሚያደርጉት ነው። በሌሎች መርሐ ግብሮች ፌይኖርድ ከኢንተር ሚላን፣ ቦዶ ግሊምት ከሊል እና ላስክ ከስሎቫን ብራቲስላቫ በተመሳሳይ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ጋላታሳራይ ከስቱትጋርት እና ሻካታር ዶኔስክ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ኤቨርተን ድል አድርጓል
Nov 3, 2026 138
3አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤቨርተን ኒውካስትል ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፏል። ትናንት ማምሻውን በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቲዬርኖ ባሪ በ49ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል። በጨዋታው ኤቨርተን የተሻሉ የግብ ማግባት እድሎችን ፈጥሯል። ተጋጣሚው ኒውካስትል የኳስ ቁጥጥር ብልጫውን ወደ ግብ መቀየር አልቻለም። የኒውካስትሉ ጃኮብ ራምሴይ በ98ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ወጥቷል። ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኤቨርተን በ13 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 7ኛ ከፍ አድርጓል። ኒውካስትል ዩናይትድ በ11 ነጥብ ከነበረበት 12ተኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል። ጨዋታውን ተከትሎ ዘጠነኛ ሳምንት ተጠናቋል። የ10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከጥቅምት 27 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ መድን ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
Nov 2, 2026 165
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3 ለ 1 ረትቷል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሳሙኤል ሳሊሶ፣ ዳዊት አውላቸው እና ወገኔ ገዛኸኝ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሄኖክ ኤርሚያስ የንግድ ባንክን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል መንገድ የተመለሰው ኢትዮጵያ መድን በሰባት ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 6ኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን አሳክቷል። በአንጻሩ በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስምንት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። ጨዋታውን ተከትሎ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠናቋል።
አካባቢ ጥበቃ
የስምጥ ሸለቆ ጂኦፓርክ በዩኔስኮ ዝርዝር ውስጥ መካተት የቱሪዝም ጸጋዎችን ለማስተዋወቅና ጥቅም ላይ ለማዋል ተጨማሪ አቅም ነው
Nov 3, 2026 90
ወልቂጤ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ጂኦፓርክ በዩኔስኮ በዓለም ጂኦፓርክ ዝርዝር ውስጥ መካተቱ የክልሉን እምቅ የቱሪዝም ሀብቶች ለማስተዋወቅና ለመጠቀም ተጨማሪ አቅም ይሆናል ሲል የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ጂኦፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ጂኦፓርኮች ዝርዝር ውስጥ ተካቶ ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘቱ ትናንት መዘገቡ ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያ እምቅ የቱሪዝም ሀብቶችን ከማልማት ባለፈ ለዓለም ለማስተዋወቅ የሚያግዝ ብሔራዊ ድል መሆኑን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር መግለጹም የሚታወስ ነው። በጉዳዩ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ቶፊቅ አጫሉ (ዶ/ር) እንደገለጹት ጂኦፓርክ ማለት ልዩ ተፈጥራዊ የመሬት አቀማመጥ ላይ የሚገኙ ቅርሶች፣ የተለያዩ የመሬት ገጽታዎች፣ ተፈጥሮአዊ እና ታሪካዊ ቦታዎች በአንድነት ተቀናጅተው የሚገኙበት ነው። ይህም በእሳተ ገሞራዎች የተፈጠሩ የተለያዩ ቅርጽና መልክ ያላቸው የድንጋይ አይነቶች እንዲሁም የእንስሳት ቅሪተ አካላትን አቀናጅቶ የያዘ ሥፍራ ተብሎ በዓለም የጂኦፓርክ ዝርዝር ተመዝግበዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆም ጂኦፓርክ ልዩ የተራራ አፈጣጠሮች ያሉበት አካባቢ ከመሆኑ በተጨማሪ እፅዋት፣ እንስሳትን፣ እንዲሁም የሰዎችን ባህል፣ ታሪክ እና አፈ ታሪኮች አጣምሮ ያያዘ አካባቢ በመሆኑ በዓለም ጂኦፓርክ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት መደረጉን ተናግረዋል። ይህም የክልሉን የቱሪዝም እምቅ ፀጋዎች ለማስተዋወቅና ጥቅም ላይ ለማዋል ተጨማሪ አቅም መሆኑን ነው የቢሮው ሃላፊ ቶፊቅ (ዶ/ር) የገለጹት። የስምጥ ሸለቆ ጂኦፓርክ በሀገሪቱም ሆነ በክልሉ ያለውን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ለማስተዋወቅና አልምቶ ለመጠቀም የራሱ ፋይዳ እንዳለውም አመልክተዋል። ጂኦፓርኩ በዓለም አቀፍ ቅርስነት መመዝገቡ ክልሉን የሚጎብኙ ቱሪስቶችን እንዲጨምር በማድረግ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግም ያስችላል ነው ያሉት። ስምጥ ሸለቆ በዓለም ጂኦፓርኩ ዝርዝር ውስጥ መካተቱ የባህል እሴቶቻችንን ይበልጥ በማጉላት የኢኮኖሚ አቅምን ከማሳደግ ባሻገር የምርምር እና የጥናት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ያግዛል ነው ያሉት። ለዚህ ታሪካዊ ስኬት መመዝገብ አስተዋጾ ላደረጉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ቶፊቅ (ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ጂኦ ፓርክ በ11ኛው የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርኮች ካውንስል ስብሰባ ላይ ዕውቅና መገኘቱ የሚታወስ ነው።
ታዳሽ ኃይል-የኢትዮጵያ መለያ!
Nov 2, 2026 251
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የታደለች፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራች የምትገኝ ምድረ ቀደምት ሀገር ናት። በተለይም በታዳሽ የኃይል አቅርቦት ዘርፍ እያከናወነች ያለው አበረታች ተግባር ሀገሪቱን በቀጣናው ብሎም በአህጉር ደረጃ ሞዴል አድርጓታል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከውሃ፣ ከንፋስ፣ ከፀሐይ እና ከጂኦተርማል ሀብቶች አጠቃላይ ከ 60,000 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል የማመንጨት ግዙፍ አቅም ያላት ሲሆን፤ አሁን ላይም የኃይል ማመንጨት አቅሟን ከ 9 ሺህ 760 ሜጋ ዋት በላይ አድርሳለች። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ዓመታት ኃይል የማምረት አቅሟን ከ15 ነጥብ 3 ቴራ ዋት ሰዓት ወደ 29 ነጥብ 5 ቴራ ዋት ሰዓት አሳድጋለች።በተለይም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በሀገሪቱ የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ለአካባቢ ጥበቃና ለታዳሽ ኃይል ልማት ያላትን እውነተኛ ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ህያው ምስክሮች ናቸው። ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማቷን ለራሷ ብቸኛ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ለጎረቤት ሀገራትና ለመላው ምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የጋራ እድገት እያዋለች ትገኛለች። የኤሌክትሪክ ኃይል መስመሮችን ወደ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ እና ኬንያ በመዘርጋት በቀጣናው የኃይል ትስስር እንዲፈጠር እና የኢኮኖሚ ውህደት እንዲጠናከር ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ይገኛል። ይህ የኃይል ትስስር የጎረቤት ሀገራትን የኃይል ፍላጎት ከመሙላቱ ባለፈ፣ አካባቢያዊ ሰላም፣ ወንድማማችነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ትብብር እንዲጎለብት ያደረገ ወሳኝ እርምጃ ነው። ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ ያመጣችው ተጠቃሚነትና ያስመዘገበችው ስኬት በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እያገኘ መጥቷል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32 ጉባኤን ለማስተናገድ በመዘጋጀት ላይ ባለችበት በዚህን ወቅት የታዳሽ ኃይል ልማት የኢትዮጵያ መለያ ከሆኑ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ያላትን መሪነት የሚያረጋግጥ ነው። በአጠቃላይ፣ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት እያከናወነች ያለችው አበረታች ስራ የራሷን የኃይል ሉአላዊነት ከማረጋገጡ በላይ፣ የቀጣናውን ሀገራት በጋራ ተጠቃሚነት ማዕቀፍ ያስተሳሰረና የዓለምን ትኩረት የሳበ ስኬት ነው። ታዳሽ ኃይል በእርግጥም የኢትዮጵያ አዲስ መለያና ኩራት ሆኖ ቀጥሏል።
ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ጂኦፓርክ በዩኔስኮ አስመዘገበች
Nov 2, 2026 193
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ጂኦፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ጂኦፓርኮች ዝርዝር ውስጥ በመካተት ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ። ይህ ስኬት የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት፣ ልዩ የጂኦሎጂ ቅርስና የቱሪዝም መስህቦች ለዓለም የሚያስተዋውቅ ከፍተኛ ብሔራዊ ድል መሆኑን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ጂኦ ፓርክ (Geopark) ማለት በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ (UNESCO) እውቅና የተሰጠው ልዩ የጂኦሎጂካል ቅርሶች፣ የመሬት ገጽታዎችና ታሪካዊ ቦታዎች ያሉበትን አካባቢ የሚያመለክት ነው። እነዚህ ፓርኮች የጂኦሎጂካል ታሪካቸውን ለመጠበቅ፣ ለማስተማር እና ለዘላቂ ልማት ለማዋል የሚያስችል የተቀናጀ አስተዳደር ስርዓት አላቸው።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያና ሩሲያ በረጅም ዘመናት ውስጥ በተገነባ ትብብር የተሳሰሩ ናቸው - ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
Oct 29, 2026 957
ሞስኮ፤ ጥቅምት 19/2019(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ሩሲያ በረጅም ዘመናት ውስጥ በተገነባ ተምሳሌታዊ ትብብር የተሳሰሩ ሀገራት መሆናቸውን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ3ኛው የአፍሪካ - ሩሲያ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሞስኮ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋርም በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተወያይተዋል። ኢዜአ ከስፍራው እንደዘገበው በውይይቱ ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ከኢኮኖሚያዊ ትስስር ባሻገር በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ታሪካዊ ቅርበት አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህ የጋራ የሞራል እሴት በብዙ ደረጃ ሕዝቦችን የሚያቀራርብ አስፈላጊ መሠረት መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ አስረድተው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በብዙ የልማት መስኮች በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ የገለጹት ፑቲን፣ በተመድ፣ በብሪክስ እና በሌሎችም ባለብዙ ወገን መድረኮች ውይይቶች መደረጋቸውን አንስተዋል። አፍሪካ በከፍተኛ የእድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ የገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ትብብር የአህጉሪቱን ተስፋ ሰጪ እድገት በጋራ ለማስቀጠል ማሳያ ነው ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት ሁለንተናዊ ብልፅግና ሊሳካ የሚችለውም ወቅቱ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ በመታጠቅ ጭምር መሆኑን ገልጸው፣ በተለይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰው ልጅ የወደፊት እድገት ዋና መሠረት ከሚሆኑ ተስፋ ሰጪ ዘርፎች አንዱ ነው ብለውታል። እንደሳቸው ገለጻ ዘርፉ እንዲያድግ የሂሳብና የሳይንስ ትምህርት ቤቶች፣ ማዕከላት ፣የሰው ኃይል እና የኃይል አቅርቦት መሠረተ ልማቶች ወሳኝ ናቸው። ሩሲያ በእነዚህ መስኮች ያላትን ዕምቅ አቅም ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማጋራት ዝግጁ መሆኗንም አክለዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ከቀድሞ ሶቪየት ሕብረት ጀምሮ የአፍሪካ ሀገራትን የነፃነት ትግል በመደገፍ የተገነባ ታሪካዊ የትብብር መሠረት እንዳላት ጠቅሰዋል። አሁን ግን የሩሲያ እና የአፍሪካ ትብብር ወደፊት በማተኮር ኢኮኖሚያዊ እድገትን ሊያፋጥን ወደሚችል ምዕራፍ መሸጋገር እንዳለበትም አመልክተዋል። የ3ኛውን የሩሲያ - አፍሪካ ጉባዔ ውይይቶችን ተከትሎ ማጠቃለያ መግለጫዎች የሚጠበቁ ሲሆን ከ2027 እስከ 2029 የሚዘልቀው አዲስ የሩሲያ እና የአፍሪካ አጋርነት የትግበራ ዕቅድ እንደሚፀድቅም ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች
Oct 29, 2026 743
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፦በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክቴን ማስተላለፍ በመቻሌ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል። በዚህ ታሪካዊ መድረክ የምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ተጨባጭ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የጋራ ቁርጠኝነት እና ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህም በምግብ ዋስትና እና ምርታማነት፣ በአስተማማኝ የኃይል አቅርቦት፣ እንዲሁም በክህሎት እና በዕውቀት ሽግግር ላይ የሚከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ፣ በመከባበር እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የጸና ታሪካዊ ወዳጅነት መሆኑንም አንስተዋል። ይህንን ወዳጅነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከሩሲያ ጋር በጋራ በመሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራትን በቁርጠኝነት እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል። ይህ ስትራቴጂካዊ ትብብር የኃይል አማራጮቻችንን ከማስፋት ባለፈ የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ በእጅጉ የሚያፋጥን እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት ትስስር ከምንጊዜውም በላይ የሚያጠናክር ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል።
የአፍሪካን የግብርና አቅም እውን ለማድረግ የሳይንስና ኢኖቬሽን ውጤቶችን ወደ ተግባር ማሸጋገር ይገባል
Oct 29, 2026 362
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 /2019 (ኢዜአ)፦ አፍሪካ የግብርና አቅሟን በአግባቡ ለመጠቀም እና የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የግብርና ምርምር፣ የሳይንስ እና የኢኖቬሽን ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማሸጋገር እንደሚገባት የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ማውሪዚዮ ማርቲና ገለጹ። በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም 2026 የማጠቃለያ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የፋኦ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ማውሪዚዮ ማርቲና በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የዘርፉን እድገት ለማረጋገጥ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከምርምር ማዕከላት ጋር በየዕለቱ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል። በግብርናና በምግብ ሥርዓት ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማደራጀትና ለማስፋፋት በትኩረት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል። ዘርፉ የተለያዩ አቅሞችንና ሀብቶችን በተለየ መንገድ ማቀናጀትን እንደሚጠይቅ ገልጸው፣ በርካታ እድሎች ያሉት መሆኑንም አመላክተዋል። ፋኦ ተልእኮውን መሰረት በማድረግ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በምርምር ተቋማትና በኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መካከል እንደ ድልድይና አቅም ማስፈጸሚያ መሣሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል ተናግረዋል። የእውቀት ልውውጥ የሚደረግባቸው ቀጣይነት ያላቸው መድረኮችን ማዘጋጀት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በተጨማሪም የምርምር ውጤቶችን በፍጥነት ወደ ተግባርና ወደ ኢንቨስትመንት መቀየር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። እነዚህን እንቅስቃሴዎች በተቀናጀ አካሄድ ማስተዳደር ከተቻለ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት እንደሚቻል ገልጸዋል። ገንዘብ አስፈላጊ ቢሆንም፣ የሰው ኃይል አቅምና ግልጽ የሆነ የአፈጻጸም መንገድ ከሌለ በቂ እንደማይሆን አስረድተዋል። በቂ ገንዘብ የተመደበላቸው አስፈላጊ ፕሮጀክቶች የታሰበውን ውጤት ሳያመጡ የቀሩት በገንዘብ እጥረት ሳይሆን በሰው ኃይል አቅም ማነስ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም የፋይናንስና የሰው ኃይል አቅምን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማቀናጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። አፍሪካ በርካታ እድሎች ያሏት አህጉር መሆኗን ጠቅሰው፣ ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ጋር በመተባበር አስፈላጊ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ወደ ሥራ መግባታቸውን አብራርተዋል። በመሆኑም በግብርናና በምግብ ሥርዓት ዘርፍ በጋራ መሥራትና የሙከራ ፕሮጀክቶችን ወደ ተቀናጀና ዘላቂ የሥራ አካሄድ መቀየር እንደሚገባ አሳስበዋል። ጥረቶች አንድ ጊዜ ብቻ ተከናወነው በሚያበቁ ፕሮጀክቶች ላይ ሳይወሰኑ፣ በቀጣይነት የሚሰፉና ዘላቂ ውጤት የሚያመጡ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል። የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን በመጠቀም በአፍሪካ የምግብና ግብርና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ተደራራቢ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተዘጋጀ አህጉራዊ መድረክ ነው። በተጨማሪም ፎረሙ ምርታማነትን በመጨመር፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በማድረግ እና የግልና የመንግሥት ኢንቨስትመንቶችን በማሳደግ አህጉራዊ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ መሆኑንም አስገንዝበዋል። በዓለም ባንክ የግብርና ዋና ኢኮኖሚስት እና የአፍሪካ የግብርና ልማት ፕሮግራም (CAADP) የልማት አጋሮች ማስተባበሪያ ቡድን ሊቀመንበር ሚዮ ታካዳ በበኩላቸው፣ የአለም ባንክ አግሪ ኮኔክት በተባለው ፕሮጀክቱ አማካይነት አርሶ አደሮችን እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል ፕሮጀክቱ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ትስስር በመፍጠር ከተለያዩ የልማት አጋሮች የሚሰጡ የተናጠል ድጋፎችን በማቀናጀት የጋራ አቅጣጫ እንዲኖር ማስቻሉን ተናግረዋል። ለአርሶ አደሮች ፈጠራን ለማስፋፋት የሚያስችል የረጅም ጊዜ የፋይናንስ አቅርቦትን የሚያደናቅፉ ከአቅርቦትና ከፍላጎት ጎን የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ፕሮግራም ኦፊሰር ዳንኤል ሂጊንስ ናቸው። ይህም የግሉ ዘርፍ በቀጣይነት ድጋፉን እንዲረከብና በረጅም ጊዜ ውስጥ ፋይናንስ ማድረጉን እንዲቀጥል የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል።
ብሪክስ ከአፍሪካ ጋር ያለውን የኢንዱስትሪ ትብብር ለማጠናከር አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ አደረገ
Oct 29, 2026 220
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 /2019 (ኢዜአ)፦ ብሪክስ ከአፍሪካ ጋር ያለውን የኢንዱስትሪ ትብብር ለማጠናከር አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ አድርጓል። ይህ የተገለጸው በሞስኮ በተካሄደው በሶስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ “የብሪክስ መድረክ ለሩሲያ-አፍሪካ የንግድ ትብብር እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው። የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ረሼትኒኮቭ፣ ብሪክስ ለአፍሪካ ሀገራት ክፍት የሆነ ገበያ ከመሆኑም በላይ የቴክኖሎጂ፣ የኢንዱስትሪ ምርቶች እና የኢንቨስትመንት አቅርቦት ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸዋል። እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ እየተዘጋጁ ካሉ አዳዲስ አሰራሮች መካከል የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ማህበር እና የእህል የንግድ ልውውጥ (Grain Exchange) ይገኙበታል። በተጨማሪም የአባል ሀገራቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴሮች የኢንዱስትሪ ዲጂታላይዜሽን እና የቴክኖሎጂ ትብብር ማዕቀፍ እንዲዘረጋ ሀሳብ ማቅረባቸውን የቲቪ ብሪክስ ዘገባ ያመለክታል። ረሼትኒኮቭ አክለውም፣ ብሪክስ አሁን ላይ ትብብሩን ከፖለቲካዊ ውይይት ባለፈ ወደ ተጨባጭ ውጤት የሚቀይሩ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ እንደሚገኝና የመንግስታት እንቅፋቶችን በማስወገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል። የንግዱ ማህበረሰብ ለአሰራሮች ውጤታማነት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አመልክተዋል። በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እና ሩሲያ መካከል የኢንዱስትሪ ትብብር ዞን መፈጠሩ ለሁለቱ ወገኖች ትስስር መጠናከር የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት በስብሰባው ላይ ተመላክቷል። በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ በመሰረተ ልማት፣ በትራንስፖርት፣ በሎጂስቲክስ፣ በኃይል እና በሳይበር ደህንነት ዘርፎች ውጤት የሚያመጡ ፕሮጀክቶችን በጋራ መተግበር እንደሚገባ ተመላክቷል። የብሪክስ (BRICS) አባል ሀገራት ነጻ የሆነ የክፍያ ስርዓት የመዘርጋት፣ ኢንቨስትመንትን የሚስቡ አሰራሮችን የመፍጠር እና የኢንዱስትሪ ትብብራቸውን የማስፋት ስራ እያከናወኑ እንደሚገኝም እንዲሁ። የስብሰባው መሪና የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኢሪና አብራሞቫ በአሁኑ ወቅት ከ37 ሺህ በላይ የአፍሪካ ተማሪዎች በሩሲያ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሆኑ መግለጻቸውን የቲቪ ብሪክስ መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
ከውጭ ነዳጅ ጥገኝነት ወደ ሀገር ውስጥ ሀብት አጠቃቀም፤ የመደመር መንግስት የከተማ ልማት አዲስ ምዕራፍ!
Nov 3, 2026 80
በአዲስ አበባ የተጀመረው ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተሸጋገሩ የከተማ አውቶቡሶችን ወደ ሥራ ማስገባት ተራ የትራንስፖርት ለውጥ ብቻ አይደለም። በመደመር መንግሥት የልማት ዕይታ ውስጥ ሲታይ፣ የሀገርን ሀብት ወደ ሕዝብ ተጨባጭ ጥቅም የመቀየር፣ የኢኮኖሚ ነፃነትን የማጠናከር፣ የቴክኖሎጂ አቅምን የማሳደግና ሰው ተኮር የከተማ ልማትን የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። በጥቅምት 22 ቀን 2019 የመጀመሪያዎቹ 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተቀየሩ አውቶቡሶች ወደ አገልግሎት ገብተዋል። 400 ተጨማሪ አዳዲስ የጋዝ አውቶቡሶችም እንደሚመጡ ተገልጿል። ይህ ለውጥ ከሚያመጣቸው የታሪፍ፣ የወጪና የአካባቢ ጥቅሞች ባሻገር ትልቅ የልማት ትርጉም አለው። በመደመር መንግሥት ዕይታ ለከተማዋና ለሕዝቡ ያለውን ትርጉም ዋና ዋና ነጥቦች ስንመለከት:- የሀገርን የተፈጥሮ ፀጋዎችን ወደ ሕዝብ ተጨባጭ ጥቅም መቀየር! ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶች ያሏት ሀገር ናት። ነገር ግን የሀብት መኖር ብቻውን ልማት አያመጣም፤ ዋናው ጉዳይ ያለንን ሀብት ወደ ምርታማነትና የሕዝብ ጥቅም መቀየር ነው። በጎዴ የሚመረተውን የተፈጥሮ ጋዝ ወደ መዲናዋ በማምጣት፣ በከተማ ትራንስፖርት ውስጥ መጠቀም መቻሉ የዚህ ሀሳብ ተግባራዊ ማሳያ ነው። ይህም ሀገራችን ከተፈጥሮ ፀጋዎቿ ተጠቃሚ ብቻ ሳትሆን፣ ፀጋዎቿን በመጠቀም ለዜጎቿ የተሻለ ኑሮ መፍጠር እንደምትችል ያሳያል። የውጭ ምንዛሬ ጫናን መቀነስና የኢኮኖሚ ነፃነትን ማጠናከር! የነዳጅ ግዢ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ ከሚያስከትሉ ዘርፎች አንዱ ነው። የከተማ አውቶቡሶች በአገር ውስጥ በሚመረት የተፈጥሮ ጋዝ መንቀሳቀሳቸው ከውጭ የሚገባ ነዳጅ ላይ ያለንን ጥገኝነት ለመቀነስ ያግዛል። ይህም ማለት፦ - ለነዳጅ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ መቆጠብ፤ - የሀገር ውስጥ ሀብትን ለምርታማ ዘርፎች ማዋል፤ - በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መዋዠቅ ምክንያት የሚፈጠርን የኢኮኖሚ ጫና መቋቋም፤ - የሀገርን የኢኮኖሚ መቋቋም አቅም ማጠናከር ማለት ነው። ይህም እንደ ሀገር የተጀመሩ የራሳችንን ሀብት ተጠቅመን የራሳችንን የኢኮኖሚ ጫና የመቀነስ ጉዞ የሚያጠናክር ነው። በዜጎች ላይ ሊደርክ የሚችል ተፈጥሮዋዊና ሰው ሰራሽ ጫናዎችን መቀነስ! የትራንስፖርት ወጪ የከተማ ነዋሪዎችን ዕለታዊ የኑሮ ወጪ ከሚወስኑ ነገሮች አንዱ ነው። የአውቶቡስ የሥራ ማስኬጃ ወጪ ሲቀንስ ይህ በትክክል ወደ ተጠቃሚው ከተላለፈ፣ ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎት ያገኛሉ። የከተማ ልማት ማለት መንገድ፣ ሕንፃና ድልድይ መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎች በንጹህ አየር፣ በጤናማ አካባቢና በተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖሩ ማስቻልም ነው። ከናፍጣ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ መሸጋገር የተሽከርካሪዎችን የተወሰኑ የአየር ብክለት አመንጪ ጋዞችና ቅንጣቶች ለመቀነስ ያግዛል። በዚህም፦ - የአየር ብክለትን መቀነስ፤ - ለከተማ ነዋሪዎች ጤናማ አካባቢ መፍጠር፤ - የአረንጓዴ ከተማ ግንባታን ማጠናከር፤ እና - የከተማን የአካባቢ ዘላቂነት ማሳደግ ማለት ነው። እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች ከናፍጣ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ መሸጋገር ወደ ዘላቂ የኃይል አጠቃቀም የሚወስድ ጠቃሚ የሽግግር እርምጃ ነው። የሀገር ውስጥ አቅምን፣ ቴክኖሎጂንና እውቀትን ማሳደግ! ከዚህ ፕሮጀክት ትልቅ ትምህርት የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝን ማምረት ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊ ጥቅም ማዋል የሚያስችል ቴክኖሎጂና አቅም መገንባት መቻልን ነው። ጋዙን ከማምረቻ ቦታው ወደ አዲስ አበባ ማጓጓዝ፣ የጋዝ ማደያዎችን መገንባት፣ አውቶቡሶችን ማስተካከልና በሀገር ውስጥ የሰው ኃይል ሥራውን ማከናወን አዲስ የእውቀትና የቴክኖሎጂ አቅም ይፈጥራል። ይህም በሀገራችን ልጆች ሆኖ ታይቷል፤ ትልቅ ስኬትም ነው። ይህ በቀጣይ ለሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችም የሚስፋፋ አቅም ነው። የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን ማብቃት፣ የቴክኒክ እውቀትን ማስፋፋት፣ የጥገናና የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪን ማጠናከር ያስችላል። የመደመር መንግሥት የልማት ጉዞን በተግባር ማሳየት! የመደመር ዋና መርህ ያሉንን ሀብቶች፣ አቅሞች፣ እውቀቶችና የልማት እድሎች አቀናጅቶ ለጋራ ዓላማ ማዋል ነው። ይህ ፕሮጀክትም በዚሁ ዕይታ ሲታይ በተለያዩ ዘርፎች ያሉ አቅሞችን አቀናጅቶ ውጤት የማምጣት ተግባራዊ ማሳያ ነው። - የኢነርጂ ዘርፍ የሚያመነጨው ሀብት፤ - የትራንስፖርት ዘርፍ የሚያቀርበው አገልግሎት፤ - የቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚያመነጨው መፍትሔ፤ - የሰው ኃይል የሚያበረክተው እውቀት፤ - የመንግሥት ተቋማት የሚያደርጉት ቅንጅት። እነዚህ ሲዋሃዱ የአንድ ዘርፍ ስኬት ብቻ ሳይሆን የሀገር አጠቃላይ የልማት አቅም ይጠናከራል። አዲስ አበባን አለም አቀፍ ተወዳዳሪና ዘመናዊና ከተማ ማድረግ! አዲስ አበባ የሀገሪቱ መዲና ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ማዕከል ናት። ስለዚህ የከተማዋ የትራንስፖርት ሥርዓት ዘመናዊ፣ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው፣ ቀልጣፋና አካባቢን የሚጠብቅ መሆን አለበት። ይህንንም ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል። የተፈጥሮ ጋዝ አውቶቡሶች መግባት ከኤሌክትሪክ አውቶቡሶች፣ ከቀላል ባቡር፣ ከዘመናዊ የአውቶቡስ መስመሮችና ከእግረኛ ተስማሚ የከተማ መሠረተ ልማቶች ጋር በተቀናጀ መልኩ ሲዳብር አዲስ አበባን የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ያላት ከተማ ያደርጋታል። አዲስ አበባን የብልፅግና ማሳያ ከተማ የማድረጉ ሂደት ከዚህም በላይ ጎልቶ ይቀጥላል።
የታሪክ ማህደር የተሰነደባት፣ የተፈጥሮ ውበት የሞላባት ሀገር
Nov 3, 2026 80
ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ፣ የጥንታዊ ስልጣኔ መሰረት፣ የታሪክ ማህደርና የተፈጥሮ ውበት ማሳያ የሆነች ሀገር ነች። በእምቅ የቱሪዝም ሃብት፣ በኢንቨስትመንትና በአረንጓዴ አሻራ ልማትም ዓለም የመሰከረላት ሀገር መሆኗ ይታወቃል። ታሪክና ተፈጥሮ፣ ባህልና ስልጣኔ፣ የቀደመ ክብርና የወደፊት ተስፋ በአንድ ላይ የተሰናሰሉባት የተስፋዋ ምድር መሆኗም ይታወቃል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ የጥንት ታሪክ አሻራዎችን ከያዙ የአርኪዮሎጂ ቅርሶች እስከ ዘመናትን ተሻግረው የዘለቁ የስልጣኔ አሻራዎች እምቅ ሃብት ያሉበት ምድረ ቀደምት ሀገርም ነች። የኢትዮጵያ የታሪክ ምዕራፍ ከሰው ልጅ መገኛነት ጋር በጥልቅ የተያያዘ ሲሆን በአፋር የተገኙ የጥንት የሰው ቅሪተ አካላትና የአርኪዮሎጂ ማስረጃዎች ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። የአክሱም ስልጣኔ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደር ቤተመንግሥቶች፣ የሶፍ ኡመር ዋሻ፣ ሐረር ጥንታዊ ከተማና ሌሎችም ታሪካዊ ቅርሶች የሀገሪቱ የስልጣኔ ምልክቶች ናቸው። ከታሪካዊ ቅርሶቿ ባሻገር ከዳሎል የሙቀት ምድር እስከ ራስ ዳሸን ከፍታ፣ ከሰሜን ተራሮች እስከ ደቡብ ለምለም ደኖች፣ ከጣና ሐይቅ እስከ አባይ፣ ኦሞና አዋሽ ወንዞች እስከ ኮንሶ መልካአ ምድሮች የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቷ የሀብትና የውበት መገለጫ ሆነው ቀጥለዋል። የሰሜን ሰማይ ተደግፈው የቆሙ የሚመስሉ ተራሮቿ፣ ጥልቅ ሸለቆዎቿ፣ የሐይቆቿና የዱር እንስሳት ሀብቷ ለቱሪዝም ዘርፍ እምቅ ሃብቶች ናቸው። በዩኒስኮ ተመዝግበው የሚገኙ የተለያዩ ቅርሶች የሚገኙባት አስደናቂ ሀገር ነች። ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ምድር በመሆኗም በዓለም ላይ የተለየ ስም አላት። ቡና ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር የማኅበራዊ ትስስር መሰረት፣ የእንግዳ አቀባበል ባህላዊ መገለጫዋ መሆኑም ይታወቃል። በመሆኑም የቡና ሥነ-ሥርዓት የኢትዮጵያን የባህልና የማንነት መገለጫ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ የአፍሪካ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ማዕከል በመሆን ትታወቃለች። የተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በማስተናገድ የአፍሪካ ድምፅ የሚሰማባት የውይይትና የትብብር መድረክ ሆና እያገለገለችም ትገኛለች። የተለያዩ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች የሚካሄዱባት ተመራጭ ከተማ ሆናም ቀጥላለች። በስፖርት ዘርፍም በተለይም በረጅም ርቀት ሩጫ የዓለምን የስፖርት ታሪክ የቀየሩ ታዋቂ አትሌቶችን አፍርታለች። ከጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ እስከ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ ቀነኒሳ በቀለ፤ ከደራርቱ ቱሉ እስከ ጥሩነሽ ዲባባ እና መሰረት ደፋር ስማቸውና ዝናቸው በዓለም የሚታወቁ አትሌሎችን አፍርታለች። ይህም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ውበት ብቻ ሳይሆን የአረንጓደው ጎርፍ የስፖርት መሰረትና የገር ዲፕሎማሲ መገለጫ መሆናቸውን የሚያመላክት ሆኗል። በአካባቢ ጥበቃና በዘላቂ ልማት ዘርፍም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ልማት ትልቅ ጥረት እያደረገች ያለች ሀገር መሆኗን የሚያመላክት ነው። ከ2011 እስከ 2018 ዓ.ም በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል አስደናቂ ተግባር ፈፅማለች። በታዳሽ ኃይል ልማትም ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅም እያለማችና እየተጠቀመች ትገኛለች። የውሃ፣ የንፋስ፣ የፀሐይና የጂኦተርማል ኃይል ሀብቶቿን በማልማት የሀገር ውስጥ የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር ለጎረቤት አገራት ኤሌክትሪክ በማቅረብ የኃይል ትስስር ማእከል ሆና እያገለገለች ትግኛለች። በመሆኑም የኢትዮጵያን እምቅ ሃብቶች በማስተዋወቅና ልማትን ይበልጥ በማስፋፋት፣ ታሪካዊና የተፈጥሮ ቅርሶችን በመጠበቅ የዓለም የስህበት ማእከል ሆና እንድትቀጥል ማድረግ ይገባል። የታሪክ ማህደርነቷ፣ የተፈጥሮ ውበቷ፣ የታሪክና የባህል እሴቷ ተጠብቆና ተሰንዶ ለትውልድ እንዲተላለፍ እየተሰራ ይገኛል።
በጠላት የማይደፈር ጀግና ሰራዊት
Nov 3, 2026 101
የአንድ ሀገር ጥንካሬ የሚለካው በሀብቷና በተፈጥሮ ጸጋዎቿ ብቻ ሳይሆን በሚገጥሟት ፈተናዎች ወቅት ሉዓላዊነቷንና ሕልውናዋን በሚጠብቁ ተቋማት ጥንካሬ ጭምር ነው። ለዚህ ደግሞ የመከላከያና የደህንነት ተቋማት ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ። ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በረጅም የታሪክ ሂደት ውስጥ በርካታ ፈተናዎችን በማለፍ የሀገርን ሉዓላዊነት፣ ነፃነትና የዜጎችን ደኅንነት በመጠበቅ በቆራጥነትና ጀገንነቱ የሚታወቅ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ከገጠሙት ፈተናዎች መካከል የሰሜን እዝ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የተፈፀመበት ክህደት መቼም ቢሆን የሚዘነጋ አይደለም። በወቅቱ የተፈጸመው ክህደት በሰራዊቱ ላይ አረመኔያዊ ድርጊት ከመፈፀምም ባሻገር ኢትዮጵያን ያለ ጠባቂ ጋሻ እና መከታ የማስቀረት እኩይ ተግባር ነበር። ይሁን እንጂ በጀግንነቱ የሚታወቀውና ህዝባዊ መሰረት ያለው መከላከያ ሰራዊት በመስዋእትነት ሀገሩን ከጥፋት ታድጓታል። በሀገር ፍቅር፣ በታማኝነት፣ በሙያዊ ኃላፊነትና በሕዝብ አለኝታነቱ የሚታወቀው ሰራዊት እምቢ ለሀገሬ በማለት የተደቀነውን የጥፋት እቅድ አክሽፎታል። በወቅቱ ተደቅኖበት የነበረውን ከባድ ፈተና በጽናት በማለፍ ሀገሩን በጽናት አስቀጥሏል። የጥቅምት 24ቱ ክስተትና የተመከተበት መንገድም የኢትዮጵያ ሕልውና በካሃዲዎች የማፍረስ መሆኑን ያረጋገጠ፤ በሀገር ክብርና ሉአላዊነት በቆመው መከላከያ ሰራዊትና ሀገር ወዳዱ ህዝብ ላይ የተመሰረተ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ነው። ከዚህ ክህደት የምንማረውም የሕዝቡና የመከላከያ ሰራዊት ትስስር ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑን ነው። ሰራዊቱ የሕዝብ ልጅ፤ ሕዝቡም የሰራዊቱ መሠረታዊ አለኝታና ዋስትና መሆኑ በተግባር ታይቶበታል። በእነዚህ ፈተና ወቅት የተከፈለው መስዋዕትነትም የሀገር የጀግንነት ውርስ መሆኑ ተመላክቷል። ለሀገራቸው ክብርና ለሕዝባቸው ደኅንነት ሕይወታቸውን የሰጡ ጀግኖች የታሪክ አሻራቸው በየትውልዱ የማይረሳ ታሪክ ሆኖ አልፏል። በየትውልዱ ሀገር የሚረከቡ ወጣቶች ከዚህ ጀግና ሰራዊት ሀገር ወዳድነትን፣ ለህዝብና ለሀገር መሞትን የሚማሩበት ነው። የተጋረጠውን ፈተና ማለፍ ብቻ ሳይሆን ከችግሩ ትምህርት በመውሰድ የበለጠ ጠንካራ፣ በሙያ የበቃ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘና ለማንኛውም ተልእኮ ዝግጁ የሆነ ሰራዊት የመገንባት ሂደትን ያስተማረ ክስተት ሆኗል። በዚህም የሰራዊቱ የሰው ኃይልና ሙያዊ ብቃት፣ የተቋማዊ አደረጃጀት፣ የቴክኖሎጂ አቅምና ግዳጅ የመፈፀም ብቃት የላቀ ማድረግ እንደሚገባ ትምህርት በመውሰድ በጠላት የማይደፈር፣ ዘመናዊ፣ ጀግና እና ጠንካራ ሰራዊት መግንባት ተችሏል። በመሆኑም የጥቅምት 24 ታሪክ የክህደትና የመከራ ትዝታ ብቻ ሳይሆን ከከባድ ፈተና በኋላ የመቆም፣ የመማርና የመጠናከር አቅምን ያሰባሰበ ነው። የከሃዲዎች እኩይ ዓላማ ቢኖርም የኢትዮጵያ ሕልውና በጀግኖቿ መስዋዕትነትና በሕዝቡ አለኝታነት የሚቀጥል መሆኑንም ያረጋገጠ ነው።
የአፍሪካ የለውጥ ብርሃን፤ የላቀ የዲፕሎማሲ ማዕከል- አዲስ አበባ
Nov 2, 2026 266
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ የለውጥ ብርሃን፤ የላቀ የዲፕሎማሲ ማዕከል- አዲስ አበባ በሚፍታ ሽፈራ ከተማ የሰዎች የኑሮ ማዕከል፣ የታሪክና የባህል መገለጫ፣ የማኅበራዊ ግንኙነትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መድረክ ነው። የከተማ ልማትም የሚለካው በነዋሪዎች የኑሮ ጥራት፣ በሚፈጥረው የኢኮኖሚ ዕድል፣ በሚጠብቀው ታሪካዊ ማንነትና በሚያጠናክረው ማኅበራዊ ትስስር ጭምር ነው። ይህንን እውነታ በተግባር እያሳዩ ካሉ ጥቂት የዓለም ከተሞች መካከል አዲስ አበባ አንዷ ናት። በቀደሙት ዓመታት አዲስ አበባ ከስሟ፣ ከታሪካዊ ክብሯና ከነዋሪዎቿ የኑሮ ፍላጎት ጋር የማይጣጣሙ በርካታ ችግሮች ይታዩባት ነበር። የአካባቢ ብክለት፣ የአረንጓዴ ስፍራ እጥረት፣ የወንዝ ዳርቻዎች መበከልና የመንገድ መጨናነቅ ከሚጠቀሱት ችግሮች መካከል ነበሩ። ከለውጡ በኋላ በገበታ ለሸገር የተጀመረውና በኋላም ወደ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ የተስፋፋው የልማት አቅጣጫ የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር አዲስ መነሳሳት ፈጥሯል። የዚህ ለውጥ መሠረት ከመደመር እሳቤ ጋር ይገናኛል። መደመር የተለያዩ ሀብቶችን፣ አቅሞችን፣ ባህሎችንና ፍላጎቶችን በማቀናጀት ለጋራ ጥቅም ማዋል ነው። በዚህ እሳቤ ልማት የሰውን ክብር የሚያስጠብቅ፣ ሁሉንም የሚያሳትፍና ለጋራ ተጠቃሚነት የሚያበቃ ነው። በዚህ አቅጣጫ ከተከናወኑት የልማት ሥራዎች መካከል የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ይጠቀሳሉ። የኮሪደር ልማት መንገዶችን ከማስፋትና ከማስዋብ ባለፈ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን፣ የመዝናኛ ማዕከላትንና የንግድ ቦታዎችን በአንድ ላይ ማቀናጀት የቻለ ነው ። ይህም የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የነዋሪዎችን፣የንግድ እንቅስቃሴና የማኅበራዊ ተግባቦት ዕድል አሳድጓል። በተመሳሳይ የወንዝ ዳርቻ ልማት የተፈጥሮ ሀብትን ከሕዝብ ጥቅም ጋር የሚያቀናጅ ግዙፍ የልማት ሥራ ነው። የተበከሉና በተለያዩ ችግሮች የተጎዱ የወንዝ ዳርቻዎችን ወደ አረንጓዴ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዕከላት፣ የንግድና የቱሪዝም መዳረሻዎች የመቀየር ጥረት የአካባቢ ጥበቃንና የማኅበራዊ ጥቅምን አብሮ አስተሳስሯል። መዲናዋን እየቀየሩ ያሉ ሁለገብ የልማት ሥራዎች የመደመር የእይታ አድማስ በተግባር ያሳዩ ናቸው። የተለያየ አቅም፣ እውቀትና ሀብት በማቀናጀት የተከናወኑት እነዚህ ሥራዎች፤ የከተማዋን ነባር ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ከዘመናዊ ግንባታ ጋር በማስማማት ዘላቂ የልማት ውጤት እንዲመዘገብ አስችለዋል። የዘመናዊ መሠረተ ልማቶች መዘርጋት፣ የትራፊክና የመንገድ መጨናነቅ መቃለል እንዲሁም የዲጂታልና የተቀናጁ አገልግሎቶች መስፋፋት የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና የኑሮ ዘይቤ ፈጣንና ቀልጣፋ አድርጎታል። የተዋቡ አረንጓዴ ስፍራዎች፣ የወንዝ ዳርቻ መዝናኛዎች፣ እና የታደሱ ታሪካዊ ቅርሶች አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ያላቸው የኮንፈረንስና የዕረፍት ጊዜ መዳረሻዎች አድርገዋታል። ይህም የቱሪዝም ፍሰቱን በእጅጉ በማሳደግ ለከተማዋ ኢኮኖሚ እጅግ አበረታች ፋይዳ እያስገኘ ይገኛል። አዲስ አበባ የብዙ ብሔር፣ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት መገናኛ ናት። የከተማ ልማት ይህንን ብዝሃነት የሚያከብር፣ የተለያዩ ማኅበረሰቦችን የሚያገናኝና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጠናክር በመሆኑ፤ መዲናዋ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በጋራ የሚገናኙባቸው ደማቅ መድረክ ሆናለች። የእነዚህ ሁሉ የልማት ጥረቶች ተጨባጭ ውጤት በዓለም አቀፍ መድረክም ታላቅ ዕውቅና እያገኘ ነው። አዲስ አበባ የዘንድሮውን የ2026 የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” (Shanghai Award) ሽልማት ማሸነፍ መቻሏ፤ በመዲናዋ የተተገበረው የሰው ተኮር ልማት እይታ፣ የአካባቢ ጥበቃ ጥረት እና የነዋሪዎች የኑሮ ጥራት መሻሻል ምን ያህል የላቀ ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያረጋግጥ ትልቅ ታሪካዊ ማሳያ ነው። ይህ ሽልማት የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ እንዲቀጥሉ፣ አካታችነት እንዲጠናከር እና የነዋሪዎች ሁለገብ ተጠቃሚነት በዘላቂነት እንዲረጋገጥ የሚያደርግ ነው። አዲስ አበባ የተያያዘችው ሁለገብ የልማት እንቅስቃሴ የመላው አፍሪካ መዲናነቷን ክብር በላቀ ደረጃ የሚያጸና ነው። ይህም የአፍሪካውያንን ታሪካዊ ኩራት ከማደስ ባለፈ መዲናዋ የአህጉሪቱ የእድገትና የለውጥ ተምሳሌት ሆና እንድትቀጥል አስችሏታል። ይህ ፈጠራ የታከለበትና አካታች የልማት ጉዞ መዲናዋ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነትና የከበረ የዲፕሎማቲክ ማዕከልነት ድርሻ በጽኑ መሠረት ላይ የጣለ ነው።
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽግግር-የኮፕ32 ተግባራዊ ማሳያ
Nov 3, 2026 113
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽግግር-የኮፕ32 ተግባራዊ ማሳያ የብሉምበርግ ጥንክር እንደዘገበው ዓለም ስለ አየር ንብረት ለውጥ እየተጨነቀና እየመከረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ኢትዮጵያ በተግባር ያሳየችው ድንቅ ውሳኔ የመላው ዓለምን ትኩረት ስቧል።የነዳጅ መኪኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት በይፋ በመከልከልና ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ሽግግር በፍጥነት በመግባት ዓለምን ያስደመመችው ኢትዮጵያ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አበረታች ውጤት ማስመዝገቧን የብሉምበርግ ጥንክር አትቷል። በኢትዮጵያ ከሚመነጨው ኃይል 99 በመቶ የሚሆነው ንጹህና አረንጓዴ መሆኑን ያተተው ዘገባው፣ ይህም ለኤሌክትሪክ መኪኖች በርካሽ ኃይል ማቅረብ እንዳስቻላት ገልጿል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ደግሞ በዚህ ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱን አመላክቷል። ይህ ታላቅ ሽግግር ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንም ወጪያቸውን እንዲቆጥቡ አድርጓል ነው ያለው የብሉምበርግ ዘገባ። የኤሌክትሪክ መኪና የሚጠቀሙ ታክሲ ነጂዎችና የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ቀደም ሲል ለነዳጅና ለጥገና ያወጡት የነበረውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት በወር እስከ 150 ዶላር (ከ40,000 እስከ 50,000 ብር) መቆጠብ ችለዋል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ እንደ ቢኬጂ ግሩፕ ያሉ የመገጣጠሚያ ፋብሪካዎች በሀገር ውስጥ ሥራ በመጀመራቸው፣ በርካታ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎችን በማሰልጠን አዲስ የሥራ እድል መፍጠር ተችሏል። በኢትዮጵያ በሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ድርሻ 6 በመቶ መድረሱን፣ ይህም ከዓለም አቀፉ አማካይ (4 በመቶ) በላይ በመሆን ኢትዮጵያን በዘርፉ ግንባር ቀደም አድርጓታል። ኢትዮጵያ በፈረንጆች 2027 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባኤን (COP32) ስታስተናግድ፣ "ታዳጊ ሀገራት በገንዘብ እጥረት ወይም በነዳጅ ቀውስ ሳይገደቡ እንዴት በፍጥነት ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መሸጋገር ይችላሉ?" ለሚለው ትልቅ ጥያቄ ህያውና በተግባር የተረጋገጠ ማሳያ እንደምትሆንም ነው ብሉምበርግ በዘገባው ያመላከተው። ኢትዮጵያ እስከ ፈረንጆቹ 2033 አምስት መቶ ሺህ (500,000) የኤሌክትሪክ መኪኖችን በመንገድ ላይ ለማሰማራት የያዘችው ታላቅ እቅድም፣ የዚሁ አረንጓዴ እና ዘላቂ ራዕይ አካል መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።
የካፒታል ገበያ፡ የነገዋ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት መሰረት
Nov 2, 2026 110
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የነገዋን ሀገር የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚቀይር እና ለአዲስ ዕድገት መሠረት የሚጥል መዋቅራዊ ሽግግር እያደረገ ይገኛል። የካፒታል ገበያ ሥርዓት በአዲስ መልክ መመለሱ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊና ግልጽ የፋይናንስ አማራጭ የሚያሸጋግር ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ የሀገር ውስጥ ቁጠባን ወደ ምርታማ ኢንቨስትመንት ለመቀየር፣ የንግድ ድርጅቶችን አቅም ለማሳደግ እና የሀገሪቱን የብድርና የዕዳ ጫና በዘላቂነት ለማቃለል ታስቦ የተዘረጋ የነገ መደላደል ነው። ዘመናዊ የካፒታል ገበያ በሕጋዊ መንገድ የተጀመረው የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲጸድቅ ነው። አዋጁን ተከትሎ ገበያውን በበላይነት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) የተቋቋመ ሲሆን፣ ግብይቱን የሚያከናውነው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ (ESX) ደግሞ በመንግሥትና በግል አጋርነት (PPP) ተመሠረተ። ይህ የዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያን (ESX) በሳይንስ ሙዚየም በይፋ መርቀው ያስጀመሩ ሲሆን፣ መደበኛ የቀጥታ የንግድ ግብይት (Live Trading) ደግሞ በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም. ላይ በይፋ ተጀምሯል። የካፒታል ገበያው የነገን ብሩህ ተስፋ በሚያሳይ መልኩ ከጅምሩ በርካታ ግዙፍ ተቋማትን ማሳተፍ ችሏል። የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ በዲጂታል መንገድና በቴሌብር ጭምር በመታገዝ ከ47 ሺህ በላይ አዳዲስ ዜጎችን በማሳተፍ የመጀመሪያው በይፋ የተመዘገበ ኩባንያ በመሆን ታሪክ ሠርቷል። ይህንን ተከትሎ በርካታ የግል የፋይናንስ ተቋማትና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አክሲዮኖቻቸውን በገበያው ላይ በይፋ ማስመዝገብ የጀመሩ ሲሆን፣ ይህም ለገበያው መነቃቃት ትልቅ መሠረት ጥሏል። በተጨማሪም የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለተለያዩ የኢንቨስትመንት ባንኮች፣ አገበያዮችና ደላላ ኩባንያዎች የሥራ ፈቃድ የሰጠ ሲሆን፣ በባንኮች የእርስ በርስ የአጭር ጊዜ የገንዘብ መበዳደሪያ ገበያ ላይ የተመዘገበው አጠቃላይ የግብይት መጠን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ማለፉ የነገውን የገበያ አቅምና አስተማማኝነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል። የዚህ ግዙፍ የፋይናንስ መድረክ ዋና ዓላማና ለነገዋ ኢትዮጵያ ያለው ፋይዳ ሀገሪቱን በባንክ ብድር ላይ ብቻ ከምትመሰረተው የፋይናንስ ጥገኝነት ማላቀቅና አማራጭ የረጅም ጊዜ የካፒታል ምንጭ መፍጠር ነው። ኩባንያዎችና መንግሥት አክሲዮንና ቦንድ በመሸጥ ለትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን ገንዘብ በቀጥታ ከሕዝብ መሰብሰብ እንዲችሉ ያደርጋል። ይህ አሠራር የመደመር መንግሥት ገንዘብ በማተም ወይም ከብሔራዊ ባንክ በመበደር የሚፈጥረውን የዋጋ ግሽበት በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን፣ ማኅበረሰቡም ገንዘቡን በባንክ ቁጠባ ብቻ ከማስቀመጥ ባለፈ በትላልቅ ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት አድርጎ የትርፍ ተካፋይ እንዲሆንና በነገዋ ኢትዮጵያ የሀብት ፍትሐዊ ክፍፍል እንዲሰፍን ያደርጋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገበያውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ ይህ ገበያ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የፋይናንስ ነፃነት የሚያረጋግጥ መሣሪያ ነው። የካፒታል ገበያው ማንኛውም ዜጋ በቀላሉ የትላልቅ ባንኮችና ተቋማት ባለቤት የሚሆንበት የነገ መድረክ ነው። የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ማዛወር ዓላማው ተቋማቱ ዓለም አቀፍ አሠራርን፣ ግልጽነትንና ዘመናዊ ተጠያቂነትን እንዲላበሱ ለማድረግ ሲሆን፣ የግል ዘርፉ የነገዋ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሞተር እንዲሆን መንግሥት ሙሉ ዋስትናና ከለላ ይሰጣል። የካፒታል ገበያው ውጤታማነት በዋናነት የተመሠረተው ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያና የመረጃ ሥርዓቶችን በመተግበር ላይ ሲሆን፣ የኢትዮ ቴሌኮም የመጀመሪያ ዙር አክሲዮን በቴሌብር መጠናቀቁ ለነገው ዲጂታል መሠረተ ልማት ትልቅ ማሳያ ነው። ገበያው ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ የማኅበረሰቡን የፋይናንስ ግንዛቤ ማሳደግ፣ የኩባንያዎችን የሒሳብ አያያዝ ግልጽነት ማረጋገጥ እና ያልተገባ የገበያ ማጭበርበርን መቆጣጠር የመሳሰሉ የቤት ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል። ወደፊት ገበያውን ይበልጥ ለማስፋፋት የተቀመጡት ቀጣይ ስትራቴጂካዊ ትከረቶች ገበያውን ቀጣናዊና ዲጂታል ማድረግ ላይ ያተኮሩ ናቸው።
ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ (ዲተረንስ)
Oct 29, 2026 386
ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦ ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ (ዲተረንስ) ጦርነትን በማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ጦርነቱ ሳይጀመር በማስቀረት የሚገኝ ድል ከሁሉ የላቀ ነው። ጥንታዊው የቻይና ጦር ስትራቴጂስት ሱን ዙ "ዘ አርት ኦፍ ዋር" በተሰኘው መጽሐፉ፣ ትልቁ የጦር ጥበብ ጠላትን ሳይዋጉ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሆነ ጽፏል። በዚህም መፅሐፉ መቶ ጦርነትን አሸንፎ መገኘት የላቀ ጥበብ አይደለም፤ ምክንያቱም ድል መንሳት በራሱ የሰው ሕይወትና የአገር ሀብትን ያስከፍላልና። ይህ ሃሳብ በዘመናዊው የደህንነት ጥናት ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ ወይም "ዲተረንስ" ተብሎ ይጠራል። የትርጉሙ ጭብጥም ጠላት ጥቃት ከመሞከር እንዲታቀብ የሚያደርግ እምነትን መፍጠር ነው። ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ መሠረታዊ አመክንዮ ማንኛውም ወገን ጦርነት የሚጀምረው ከጦርነቱ የሚያገኘው ጥቅም ከሚከፍለው ዋጋ እንደሚበልጥ ሲያስብ ነው። ስለዚህ አንድ አገር የጥቃትን ዋጋ በበቂ ሁኔታ ካናረ፣ ጠላት ሒሳቡን ሲሰራ ጦርነት ኪሳራ ሆኖ ይታየዋል። ሮማዊው ወታደራዊ ጸሐፊ ቬጌቲየስ ከ1 ሺህ 600 ዓመታት በፊት በጻፈው መፅሓፍ የከተበው ታዋቂ አባባል ይህንኑ ይገልጻል። "ሰላምን የሚሻት ቢኖር ለጦርነት ይዘጋጅ" ይላል። ይህም በተለያዩ አስረጂ ጉዳዮች ሊዳሰስ ይችላል፤ የመጀመሪያው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ነው። የአየር መከላከያ፣ የመድፍና የሚሳይል አቅም፣ የታጠቁ ኃይሎችና የአየር ኃይል ብቃትን ይመለከታል። ሁለተኛው የሰለጠነ ወታደር ነው፤ ምክንያቱም መሳሪያ በብቁ እጅ ካልተያዘ ክብደት እንጂ ጉልበት አይሆንምና። ተከታታይ ስልጠና፣ ዲሲፕሊንና የዕዝ ሰንሰለት ያለው ሠራዊት ለጠላት ከሚታየው ቁጥር በላይ ግምትን ይፈጥራል። ሦስተኛው በቴክኖሎጂ የታገዘ የውጊያ ብቃት ነው፤ ይኸውም ስለላና የስለላ ድሮኖች፣ ሳይበር፣ የመገናኛና የመረጃ ሥርዓት እንዲሁም ትክክለኛ ኢላማን የመምታት አቅምን ያካትታል። በዘመናችን ጦርነት የሚወሰነው በመረጃ የበላይነት ጭምር ነው፤ ምክንያቱም ጠላቱን አስቀድሞ የሚያይ ወገን ሁልጊዜም አንድ እርምጃን ቀድሟል። ሌላኛው ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚዘነጋው ተዓማኒነት ነው። አሜሪካዊው የስትራቴጂ ምሁር ቶማስ ሼሊንግ “Arms and Influence” በተሰኘው መጽሐፉ እንደሚያስረዳው፣ ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ ወይም "ዲተረንስ" የሚሰራው አቅሙ ብቻ ሳይሆን ያንን አቅም የመጠቀም ፍላጎትና ቁርጠኝነት ጭምር ለጠላት ግልጽ ሲሆን ነው። ምስጢር ሆኖ የተቀመጠ ወይም በማሳየት ያልተረጋገጠ አቅም ጠላትን ሁለቴ ደጋግሞ እንዲያስብ ሊያደርገው አይችልም። ለዚህም ነው ወታደራዊ ልምምዶች፣ ሰልፎችና ግልጽ የመከላከያ ፖሊሲዎች የጥበቡ አካል የሆኑት። የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ልምድም ይህን ያሳያል፤ ሁለቱ ልዕለ ኃያላን አሜሪካና የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት የጋራ ጥፋት የሚያስከትል የኒውክሌር አቅም ስለነበራቸው በቀጥታ ከመዋጋት ተቆጥበው በቃላት ጦርነት ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ አድርጓቸዋል። ኢትዮጵያም ለዚህ ጉልህ ታሪካዊ ምሳሌ አላት። በ1888 ዓ.ም. በዓድዋ አፄ ምኒልክ ከየአቅጣጫው የተሰበሰበውን ሕዝብ በአንድ ዓላማ አሰልፈው፣ እቴጌ ጣይቱንና ሌሎች የጦር መሪዎችን አስተባብረው ጣሊያንን በሚወስን ሁኔታ ድል አድርገዋል። ድሉ ከውጊያ ሜዳ ባሻገር ዲፕሎማሲያዊ ውጤትም ነበረው፤ በዚያው ዓመት በተፈረመው የአዲስ አበባ ውል ጣሊያን የኢትዮጵያን ነጻነት እንድታውቅ ተገደደች። ለሌሎች የአውሮፓ ኃያላንም ኢትዮጵያን መውረር ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንካራ መልዕክት በመሆን ሌላ ጦርነትን ለማስቀረት አገለገለ። ይህ ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ በተግባር የተፈተነ አቅሙ ታይቷል፣ ቁርጠኝነቱም ተረጋግጧል። አሁን ላይም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር አካባቢ ባላት ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ ምክንያት ለውስጣዊና ለውጫዊ ጫናዎች ተጋላጭ ሀገር ናት። ሀገሪቷ የምትገኝበት መልክዓ ምድር በተለያዩ ግጭቶች የሚታወቅ ብቻም ሳይሆን የተለያዩ ኃያላን አገራት ጦር የሚገኝበት ቀጣና ነው። ይህንን ከግምት ባስገባ መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት የመከላከያ ሠራዊቱን በማዘመን ረገድ ተጨባጭ እርምጃዎችን ወስዷል እየወሰደም ይገኛል። ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት አከባበር በዓል ላይ አየር ኃይሉን በማዘመን በ2030 ከአራተኛ ትውልድ ወደ አምስተኛ ለማሻገር እንደሚሰራ መናገራቸው ይታወሳል። አየር ኃይሉ አሁን ካለበት በዕጥፍ የማሳደግ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም አስረግጠው ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በራሱ ጠላት በኢትዮጵያ ላይ ጥቃትን ከመፈፀሙ በፊት ሁለቴና ሦስቴ እንዲያስብበት የሚያደርግ መሆኑን ማንሳቱ ግድ ይላል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከቃል በላይ ለመሆኑ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ አየር ኃይሉ ከዚህ ቀደም ከታጠቃቸው ዘመናዊ የውጊያ አውሮፕላኖች በተጨማሪ ኢትዮጵያ ትናንት 12 የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶችን ከሩሲያ ተረክባለች። በዚህም ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም ላይ በርካታ ሀገራት በሰላሙ ጊዜ አስፈላጊውን ዝግጅት ባለማድረጋቸው ምክንያት ችግር ሲፈጠር ለአደጋ ሲጋለጡ እንደሚታይ ጠቁመው፤ የኢትዮጵያን የአየር ክልል ላለማስደፈር በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ የተረከበቻቸው የሱ-35 ኤርክራፍቶች በዓለም ላይ ካሉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ግንባር ቀደም ናቸው። መሳሪያዎቹ ከአየር ወደ አየር እንዲሁም ከአየር ወደ ምድር ውጊያ የማካሄድ ከፍተኛ አቅም ያላቸውና በተግባር የተፈተኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቃጡ የክሩዝ ሚሳኤል ጥቃቶችን እስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት የመለየት (Detect) እና የማክሸፍ (Intercept) ብቃት እንዳላቸው አስረድተዋል። ይህንን የቴክኖሎጂ አቅም መገንባት ለሀገር ህልውና ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል የነበሩት የሱ-30 እና የአሁኖቹ የሱ-35 ተዋጊ ጄቶች የኢትዮጵያን የአየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄት ባለቤት ከሆኑ በጣት የሚቆጠሩ አገራት መካከል አትዮጵያ አንዷ መሆኗ ደግሞ ከራሷ ሉአላዊትንም ባለፈ ለአህጉሩ እና ለቀጣናው ሰላም መጠበቅ ወሳኝ ሚና ይኖራታል ማለት ነው። ምክንያቱም የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄት በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ የአየር ላይ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ዘመናዊ ተዋጊ ጀት ነው። የጀቱ ሞተሮች አቅጣጫቸውን መቀየር የሚችሉ (3D Thrust Vectoring Nozzles) በመሆናቸው አየር ላይ ባልተለመዱ ማዕዘኖች እና ፍጥነቶች እንዲንቀሳቀስ ያስችሉታል። የሩሲያ አየር ኃይል ከሚጠቀማቸው እጅግ ዘመናዊ እና አደገኛ የጦር ጄቶች መካከል አንዱ ነው። የዚህ ጀት መገለጫ እጅግ ዘመናዊና ተዋጊ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የ5ኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ የተቀላቀለበት ስለመሆኑም ይነገራል። በሰአት 2 ሺህ 400 ኪ.ሜ የመብረርና ያለተጨማሪ የነዳጅ ታንከርም 3 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር መብረር የሚችለው ተዋጊ ጀት በአንድ ጊዜ እስከ 30 ኢላማዎችን የመከታተል እና 8ቱን በአንድ ጊዜ የመምታት አቅም አለው። ራዳሩን ሳያበራ (ምንም ዓይነት የራዳር ሞገድ ሳይለቅ) በኢንፍራሬድ/ካሜራ (IRST) አማካኝነት ጠላትን በድብቅ እስከ 80 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ መከታተል ይችላል። የጠላት ራዳሮችን እና ሚሳይሎችን በመረበሽ (Jamming) ጄቱን ካልተጠበቀ ጥቃት ይከላከላል። የሩሲያ አየር ኃይል ከሚጠቀማቸው እጅግ ዘመናዊ እና አደገኛ የጦር ጄቶች መካከል አንዱ ነው። የዚህ ጀት መገለጫ እጅግ ዘመናዊና ተዋጊ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የ5ኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ የተቀላቀለበት ስለመሆኑም ይነገራል። ለዚህም ነው በሩሲያ በተደረገው የጦር ጀቶቹ ርክክብ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የምናደርገው ሁለንተናዊ ጥረት ዛሬ ሌላ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል ያሉት። ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይል እያደረገች ያለው ዝግጁነት ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም የገነባች መሆኑንም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የየብስ፣ የአየርና የባህር ኃይሎች በሳተላይትና በዲጂታል የመገናኛ መረቦች እንዲተሳሰሩና እንደገና እንዲደራጁ መደረጉም ጠላት ሁለቴ እንዲያስብ የሚያደርግ ነው። ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ብቁና ጠንካራ ሠራዊት የስለላ፣ የትክክለኛ ጥቃትና የፈጣን ምላሽ አቅምን ስለሚጨምር የአየር ክልልን የመጠበቅ ችሎታን ያሳድጋል። ይህ ሁሉ አንድ ላይ ሲታይ ኢትዮጵያን በቀላሉ ለማጥቃት እንደማይቻል የሚያስተላልፈው መልዕክት የጎላ ነው። እውነተኛ ድል ጥይት ሳይተኮስ በሚገኝ ሰላም ይረጋገጣል!!! የሚባለውስ ለዚህ አይደል!
የኢትዮጵያ ጽኑ ሉዓላዊነትና የቀጣናው ዋስትና- ዘመናዊ ጄቶች የታጠቀው አየር ኃይል
Oct 29, 2026 327
በለይኩን አሰፋ ትልቅ ሕዝብ፣ትልቅ ሀገርና ታላቅ ራዕይ ሰማይ ወሰን የሌለው የተፈጥሮ ስፋት ቢሆንም፣ ለአንድ ሀገር ግን የሉዓላዊነት፣ የደኅንነትና የብሔራዊ ጥቅም አካል ነው። በዚህ ሰማይ ላይ የሀገርን ክብር ለመጠበቅ፣ የሕዝብን ደኅንነት ለማረጋገጥና የውጭ ስጋቶችን ለመከላከል የቆመው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገሪቱ የመከላከያ ሥርዓት ወሳኝ አካል ነው። አንድ ሀገር ሉዓላዊነቷን በምድር ላይ ብቻ አትጠብቅም። የአየር ጠፈሯን መጠበቅ፣ ከድንበሯ በላይ የሚንቀሳቀሱ ስጋቶችን መከታተልና ለሀገራዊ ደኅንነት የሚያስፈልገውን የአየር የበላይነት ማረጋገጥ የዘመናዊ መከላከያ አቅም ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። በዚህ የብሔራዊ ደኅንነት ምሰሶ ውስጥ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የራሱ የሆነ ታሪክ፣ የተለየ ተልዕኮና የረጅም ዘመን የአገልግሎት ልምድ አለው። ከታሪካዊ አመሠራረቱ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከአውሮፕላኖችና ከወታደራዊ መሣሪያዎች የበለጠ ትርጉም ይዞ ቆይቷል። ከጀግንነት፣ ከሙያዊ ብቃትና ከሀገር ፍቅር መርህ ጋር የተያያዘ ተቋም ሆኖ በተለያዩ ዘመናት የሀገሪቱን የአየር ደኅንነት ለማስጠበቅ ተልዕኮውን ተወጥቷል። የዚህ ተቋም ታሪክ የሚዘከረው በተከናወኑ ዘመቻዎች ብቻ ሳይሆን፣ ለሀገር ጥቅም በተከፈሉ መሥዋዕትነቶች፣ በተገነባው ሙያዊ ልምድና ከትውልድ ወደ ትውልድ በተላለፈው የአገልግሎት መንፈስ ጭምር ነው። ዛሬ የዓለም ወታደራዊ አሠራር በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት ወቅት፣ የአየር ኃይል አቅም በአውሮፕላኖች ብዛት ብቻ አይለካም። የራዳርና የክትትል ሥርዓቶች፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የአየር መከላከያ፣ የሰው ኃይል ሥልጠና፣ የጥገናና የቴክኒክ ብቃት እንዲሁም የተቀናጀ የውጊያ አሠራር የአቅሙ ወሳኝ መለኪያዎች ሆነዋል። ታዲያ የኢትዮጵያ አየር ኃይልም በየጊዜው ከሚለዋወጡት ዓለም አቀፍ የጂኦፖለቲካ እና የቴክኖሎጂ እድገቶች ጋር አብሮ በመጓዝ አሁን ላይ ሰፊና ጥልቅ የሆነ የዘመናዊነት ሽግግር እያደረገ ይገኛል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከተካሄደው ሀገራዊ የሪፎርም ሂደት፣ ለአየር ኃይሉ መሰረታዊ የላቀ ጥንካሬ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። የመደመር መንግሥት ለአየር ኃይሉ መጠናከር እያበረከተ ያለው የቴክኖሎጂ፣ የመሰረተ ልማት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ግንባታ ድጋፍ ተቋሙን በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ዘመናዊ የጦር ኃይል አድርጎታል። የአየር ኃይሉ የዘመናዊነት ጉዞ ዋነኛው መገለጫ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መታጠቁ ነው። ተቋሙ ወቅታዊ የጦርነት ስልቶችን መሠረት ያደረጉ ዘመናዊ ሲስተም የታጠቁ ድሮኖችን በስፋት በመጠቀም ረገድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህም የቅድመ-ማስጠንቀቂያ እና ተፈላጊውን ኢላማ የመምታት አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ከዚህም በተጨማሪ ነባር የውጊያ አውሮፕላኖችን እና ሄሊኮፕተሮችን ማዘመን ብቻ ሳይሆን፣ አዳዲስ የላቁ የውጊያ አውሮፕላኖችን መታጠቁ የአየር ክልል የበላይነቱን እንዲያረጋግጥ አስችሎታል። ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ ዛሬ ከሩሲያ የተረከበችው የመጀመሪያዎቹን አስራ ሁለት የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች (Su-35 4++ Generation) ተጠቃሽ ናቸው። ይህም የኢትየጵያን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ሌላ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የሚያረጋግጥ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት በሩሲያ ተገኝተው የጦር ጄቶችን በተረከቡበት ወቅት ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይሏ እያደረገች ያለው ዝግጁነት ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ እያላበሳት ይገኛል ብለዋል። እነዚህን እጅግ ዘመናዊ የጦር ጄቶች በመታጠቅ ብቻ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ መሆን ችላለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይህንን ስኬት አስመልክተው ሲናገሩም፦ "ይህ ታሪካዊ ስኬት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን፣ ወደፊትም የጋራ ደህንነታችንን እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የምናደርገውን ጉዞ በልበ ሙሉነት እንድንቀጥል ትልቅ አቅም ይሆነናል።" ብለዋል። በዚህ ድንቅ ዕምርታ የታጀበው የአየር ኃይላችን ዝግጁነት፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ባለፈ ለቀጣናው ሰላም ትልቅ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑን ይህ ታሪካዊ ቀን በግልጽ አሳይቷል። ይህ ሀገራችንን የሰማይ ላይ ጥበቃ (Air Defense) ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ትልቅ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ሱ-35 በአየር ላይ የሚደረጉ ውጊያዎችን በመቆጣጠር፣ የጠላት አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በረጅም ርቀት ላይ የማወቅ፣ የራዳር ሥርዓቶችን የማደናቀፍ እና የማስወገድ ከፍተኛ ብቃት ያለው ሲሆን፤ አየር ኃይሉ ቀደም ሲል ከታጠቃቸው Su-30፣ Su-27 እና ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶች ጋር የተቀናጀ የሰማይ ጥበቃ መረብ ለመፍጠር ያስችላል። የማንኛውም አየር ኃይል ጥንካሬ መሠረቱ የቴክኖሎጂው ጥራት ብቻ ሳይሆን የሰው ኃይሉ ብቃት ነው። ለዚህም ስኬት አጋዥ እንዲሆን የበረራ ባለሙያዎችን፣ የቴክኒክ እና የምህንድስና ባለሙያዎችን የሚያሰለጥንበት አካዳሚ በዘመናዊ የበረራ ልምምድ መሳሪያዎች (Flight Simulators) እና ላቦራቶሪዎች እንዲደራጅ ተደርጓል። ፓይለቶች እና የጥገና ባለሙያዎች ወቅታዊውን ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና የስልት ደረጃ ጠብቀው እንዲሰለጥኑ በመደረጉ በከፍተኛ ደረጃ ፕሮፌሽናል የሆነ የሰው ኃይል መገንባት ተችሏል። ዛሬ ወደ ዘመናዊ አሰራር የሚደረገው ሽግግር የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን እና የሎጂስቲክስ ቅልጥፍናንም ያካተተ ነው። ቢሾፍቱን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ የአየር ኃይል ጣቢያዎች በዘመናዊ መገናኛዎች፣ የበረራ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች እና የደህንነት ሥርዓቶች እንዲደራጁ ተደርገዋል። የመረጃ ልውውጥን እና የዕዝ ሥራዎችን በዲጂታል መንገድ የሚያቀናጁ የቴክኖሎጂ ሥርዓቶችንም መዘርጋት ተችሏል። ከዚህ ባሻገርም ኢትዮጵያ በኤሮስፔስ እና በመከላከያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በሀገር ውስጥ የሰው አልባ አውሮፕላኖች ማምረት እና መገጣጠም መጀመሯ ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። እንደ ኤሮ ዓባይ (Aero Abay) እና ስካይ ዊን (Sky Win Aeronautics) ያሉ የድሮን ማምረቻ ፋብሪካዎች እውን መሆን ሀገሪቷ ከውጭ ጥገኝነት ወጥታ የራሷን የቴክኖሎጂ አቅም እንድትገነባ መንገድ ከፍቷል። ፋብሪካዎቹ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የሚመሩ በመሆናቸው ለከፍተኛ የቴክኖሎጂ ሽግግር ትልቅ መደላደል የፈጠሩ ሲሆን፤ ለስለላ፣ መረጃ ለመሰብሰብ፣ ተፈላጊውን ዒላማ ነጥሎ ውጤታማ እርምጃ ለመውሰድ እንዲሁም ለስልታዊ ወታደራዊ አገልግሎቶች የሚውሉ ድሮኖችን በማምረት ላይ ናቸው። እነዚህ የሀገር ውስጥ ውጤቶች የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባለፈ በዘመናዊ ግብርና፣ በሜጋ ፕሮጀክቶች ጂኦስፓሻል ክትትል፣ በተፈጥሮ አደጋዎች የጉዳት መጠን ዳሰሳ እና በአስቸኳይ የህክምና ቁሳቁሶች ማድረስ ላይ ከፍተኛ ሲቪል አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጥንካሬ የአገራችንን ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ዋስትና ነው። ሱ-35 አውሮፕላኖች እና ዘመናዊ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች መታጠቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሀገራዊ የኢኮኖሚ፣ የኃይል እና የሎጂስቲክስ ማዕከላትን ከአየር ላይ ስጋቶች በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ያስችላል። በወታደራዊ ስትራቴጂ ውስጥ ጥንካሬን ማሳየት ራሱ ግጭቶችን የመከላከል ትልቅ ሚና እንዳለው ሁሉ፣ ኢትዮጵያ የላቀ የአየር የበላይነት አቅም መገንባቷ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሊነሱ የሚችሉ ስጋቶችን በቅድሚያ ለመከላከል የማይደፈር አቅም ይሆናሉ። ይህ ጠንካራ የመከላከል አቅም መኖሩ ኢትዮጵያ በቀጣናው የደህንነት እንቅስቃሴዎች ላይ የሰላም እና የመረጋጋት አምባሳደር ሆና እንድትቀጥል የሚያስችላት ሲሆን፤ በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ወቅትም አስፈላጊውን የአየር ክልል ጥበቃ እና ደህንነት ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጁነትን ፈጥሯል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል እያደረገ ያለው የዘመናዊነት ሽግግር የታሪክ አደራውን ከነገው የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ያጣመረ ነው። በሰው ኃይል ልማት፣ በሀገር ውስጥ የድሮን ማምረቻዎች፣ በዘመናዊ የሱ-35 የውጊያ አውሮፕላኖች ትጥቅ እና ቀልጣፋ የአሰራር ሥርዓት ላይ የተደረጉት ተጨባጭ ለውጦች ተቋሙን በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ካሉ ጠንካራ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ የአየር ኃይሎች አንዱ አድርገውታል። ይህ ጉዞ የኢትዮጵያን ሰማይ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ እና ለአካባቢው ቀጣና ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋት እና የደህንነት ዋስትና የሚሰጥ ስትራቴጂካዊ ምሽግ ሆኗል።
ልዩ ዘገባዎች
ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር
Oct 9, 2026 995
ነጋሪ መጽሔት የዓባይ ውሃ አጠቃቀምና የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት በስፋት ተንትናለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ፣ “የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም” በማለት ሀገሪቱ የባሕር መዳረሻ እንድታገኝ በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ይህ ጥረት በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ተጠቃሚነትና በ“ሰጥቶ መቀበል” መርሕ እንደሚመራ በማስገንዘብ፣ ጉዳዩን ከአፍሪካ ቀንድ፣ ከቀይ ባሕርና ከመካከለኛው ምሥራቅ እየተለወጡ ካሉ የጂኦፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው አቅርበዋል። መጽሔቷም በመስከረም 2019 ዓ.ም. እትሟ “የኢትዮጵያ የትንሳኤ መንገድ፡ ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር ፖለቲካ የዘለቀው ፍጥጫ” በሚል ርዕስ ባቀረበችው ትንታኔ፣ የውሃ ሀብት፣ የባሕር መዳረሻ፣ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችና የቀጣናዊ ደኅንነት ጉዳዮች በሀገራት መካከል ባለው የኃይል አሰላለፍ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ዳስሳለች። እንደ መጽሔቷ ትንታኔ፣ ዓባይና ቀይ ባሕር በተፈጥሮ የተለያዩ የውሃ አካላት ቢሆኑም፣ በዘመናዊው የጂኦፖለቲካ ስሌት ውስጥ በውሃ አጠቃቀም፣ በኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ በባሕር መዳረሻና በደኅንነት ጉዳዮች የተሳሰሩ ናቸው። የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያና ለተፋሰሱ ሀገራት ለኃይልና የልማት ጥቅም ሲኖረው፣ ቀይ ባሕር ደግሞ አፍሪካን፣ እስያንና አውሮፓን የሚያገናኝ ወሳኝ የዓለም አቀፍ የንግድና የባሕር መተላለፊያ ነው። በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የዓባይ ውሃን በፍትሐዊነትና በጋራ ተጠቃሚነት የማስተዳደር ጥያቄና የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በቀጣናው የፖለቲካና የደኅንነት ስሌቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ መጽሔቷ በስፋት ተንትናለች። የ1929 እና የ1959 የውሃ ስምምነቶች የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም በበቂ ሁኔታ እንዳልተካተቱ በመግለጽ፣ የወንዙ ውሃ አጠቃቀም በፍትሐዊነት፣ በትብብርና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ ማዕቀፍ መመራት እንዳለበት አመልክታለች። ኢትዮጵያ በ1993 ዓ.ም በኋላ የባሕር በር መዳረሻዋን ማጣቷን ተከትሎ፣ ጉዳዩ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ ከብሔራዊ ደኅንነትና ከረጅም ጊዜ የልማት ፍላጎት ጋር እንደተያያዘ መጽሔቷ አትታለች። የባሕር በር መዳረሻ ማግኘት የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ የወደብ አማራጮችን ለማስፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ወሳኝ መሆኑንም አብራርታለች። በሌላ በኩል፣ ቀይ ባሕር ከእስያ፣ ከአፍሪካና ከአውሮፓ የንግድ መስመሮችን የሚያገናኝ ስትራቴጂካዊ የባሕር መተላለፊያ በመሆኑ፣ በአካባቢው ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከአካባቢያዊ ግንኙነቶች ባለፈ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ፍሰትን ይነካል። መጽሔቷ የቀይ ባሕር የጂኦፖለቲካ አስፈላጊነት ከስዊዝ ቦይና ከባብ-ኤል መንደብ የባሕር መተላለፊያ ጋር በማያያዝ የዳሰሰች ሲሆን፣ በአካባቢው የሚካሄዱ የኃይል ፉክክሮች የንግድና የደኅንነት ስጋቶችን እንደሚያባብሱ ተንትናለች። መጽሔቷ በትንታኔዋ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ከቀጣናው ሀገራት የፖለቲካ አቋሞች ጋር በማያያዝ የተለያዩ ትንታኔዎችን አቅርባለች። ሆኖም እነዚህ በመጽሔቷ የቀረቡ የፖለቲካ ትንታኔዎች ሲሆኑ፣ የተጠቀሱ አቋሞችንና ክሶችን ከተረጋገጡ እውነታዎች መለየት ያስፈልጋል። መጽሔቷ በዓባይ ውሃ አጠቃቀምና በባሕር መዳረሻ ጉዳይ ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ በድርድርና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ መፍትሔ ማግኘት እንዳለባቸው አጉልታለች። የውሃ ሀብትን በፍትሐዊነት ማስተዳደርና የባሕር መዳረሻ ጉዳይን በሰላማዊ ስምምነት መፍታት ለቀጣናዊ መረጋጋት፣ ለኢኮኖሚ ትብብርና ለዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆናቸውን በትንታኔዋ አመልክታለች። የመጽሔቱ ሊንክ https://www.ena.et/web/negari/w/negari_9696604
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 918
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 690
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 697
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
መጣጥፍ
ለአፍሪካ ዴሞክራሲ መጻኢ ጉዞ በዓድዋ ጥላ ሥር
Nov 3, 2026 65
አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት፣ የሰው ኃይልና የብዙ ዕድሎች ባለቤት ስትሆን፣ ይህንን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ የልማት ውጤት ለመቀየር የፖለቲካ አመራርና የኢኮኖሚ ዕድገት ትስስር ወሳኝ ነው። ይህንን አህጉራዊ አጀንዳ የሚያስቀድመው ሁለተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ከጥቅምት 26 እስከ 28 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። በሀገራት መሪዎች፣በፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ በፖሊሲ አውጪዎችና በተለያዩ ዘርፎች ተወካዮች ጨምሮ በርካታ ተሳታፊዎች በሚታደሙበት በዚህ ታላቅ ጉባኤ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአፍሪካ ሁለንተናዊ እድገት ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉበት ይጠበቃል። ይህ ጉባኤ በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄዱ የጥቁር ሕዝቦች ነፃነት መነሻ፣የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ጽኑ መሠረት እና የአፍሪካውያን የአንድነትና የድል አርማ ከሆነው ታሪካዊ ሁነት ጋር ያገናኘዋል።ዛሬም በዓድዋ ጥላ ሥር አፍሪካውያን መሪዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድነት ተሰባስበው የአህጉራችንን የዴሞክራሲ መጻኢ ዕጣ ፈንታ መወያየታቸው ያለፉትን አባቶች አርቆ አስተዋይነትና ተጋድሎ የሚዋጅ ታሪካዊ ክስተት ነው። የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ የሆነችው እና በመደመር እሳቤ እየተተገበረ ያለው የኮሪደር ልማት ገጽታዋን በመቀየር አፍሪካን የምታኮራ ተምሳሌታዊ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫና ከሥልጣን ውድድር ባለፈ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ለውጥ የሚመሩ ፖሊሲዎችንና ዘላቂ የልማት ስትራቴጂዎችን ላይ በጋራ ድምጻቸውቅን ያሰማሉ። በጋና አክራ የተካሄደው የመጀመሪያው ጉባኤ በዴሞክራሲ፣ በአካታች አስተዳደርና ልማትን በሚያስቀድም ፖለቲካ ላይ የጋራ ቁርጠኝነትን ያስቀመጠ ሲሆን፣የአዲስ አበባው ጉባኤ ደግሞ ይህንን ቁርጠኝነት ወደ ተግባራዊ ለውጥ የሚያሸጋግር ነው።ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድንና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፎች ያስመዘገበቻቸውን ስኬታማ ተሞክሮዎች በጉባኤው እንደምታቀርብም ይጠበቃል። የአፍሪካ የወደፊት ዴሞክራሲ እውን ሊሆን የሚችለው አህጉራችን ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታና የባህል እሴቶች ባገናዘበ መልኩ፣ በጋራ በመተሳሰብና በልዩነቶች ውስጥ አንድነትን ማጠናከር ሲቻል ነው። አሁን ላይ የአፍርካን የኢኮኖሚ ነፃነትን እና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት የዓድዋ መንፈስ የቀጣይ ዘመን መገለጫ እንዲሆን ይጠይቃል።በዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄደው ይህ ውይይት አፍሪካውያን የራሳቸውን ዕጣ ፈንታ በራሳቸው የሚወስኑበት፣ ጠንካራ ተቋማት የሚገነቡበት እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማጠናከር የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል። ዓድዋ የትናንት የአፍሪካዊያን ታሪክ ብቻ ሳይሆን፣ የነገው የአፍሪካ ዴሞክራሲ እና የነፃነት ብርሃን ማማ ነው።ሁለተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤም በዚሁ ታሪካዊ ስፍራ መካሄዱ አህጉራችን በአንድነት፣ በሰላም እና በጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓተ-መንግስት የተገነባ ብሩህ ተስፋ እንዳላት በሰፊው የሚያረጋግጥ ነው።
ታሪክ የማይዘነጋው ክህደት እና የኢትዮጵያዊያን አኩሪ ጽናት!
Nov 3, 2026 125
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት መሆኑ ይታወቃል። ለዚህ ጀግና እና ህዝባዊ ሰራዊት ተገቢውን ክብርና ምስጋና መስጠት ሲገባ ክህደት ሲፈፀምበት ግን እጅግ አሳዛኝ ነው።ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በባንዳዎች ድንገት የተፈፀመበት ክህደት ታሪክ የማይዘነጋው የክህደት ጥግ ነው። በመሆኑም የዛሬው እለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት በባንዳዎች የተፈጸመበትን ታሪካዊ ክህደት እና በጽናት የታለፈበት የሚታወስበት መሆኑ ይታወቃል። እለቱ ሲታወስ ሰራዊቱ ለአመታት የህዝብን ሰላም፣የሀገር ዳር ድንበር እና የልማት ስራዎችን በሚያግዘው ህዝባዊ ሰራዊት ላይ በውስጥ ባንዳዎች አረመኔያዊ ድርጊትና ታሪክ የማይረሳው ክህደት የተፈፀመበት በመሆኑ የሚዘከርበት ነው። በዕለቱ የተፈጸመው ድርጊት የትኛውንም ሰብአዊነትና ወታደራዊ ስነ-ምግባር ያልተከተለ የአረመኔያዊ ድርጊት ነበር ማለት ይቻላል። በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሀገር ክብርና ሉአላዊነት ለዜጎች ፍቅርና አክብሮት ሲል የከፈለው መስዋዕትነት መቼም ቢሆን ሊረሳ አይችልም። የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት በማውገዝ ከሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ምሰሶ ነው በማለት ከጎኑ በመሰለፍ እገዛና ድጋፉን በተግባር አሳይቷል። ህዝቡ በከሃዲዎቹ ድርጊት በማዘንና በመቆጨት ሀገር ለማፍረስ የተንቀሳሰቀውን የጥፋት ቡድን መመከት ችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወታደራዊ ልብሳቸውን ለብሰው ወደ ግንባር በመዝመት ሀገራቸውን ከጥፋት የታደጉበት አጋጣሚም የዚሁ ታሪክ አካል ነው። በመሆኑም ጥቅምት 24ን ስንዘክር፣ በዕለቱ ሕይወታቸውን ላጡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና ዜጎች ክብር በመስጠት፣ እንዲህ አይነት ክህደት ሀገር የማፍረስ እቅድ በመሆኑ እንዳይደገም ትውልድ እያወቀው እንዲሄድ በማድረግ ይሆናል።ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ተገቢውን ክብርና ፍቅር በመስጠት ሁላችንም ሀገራዊ አደራችንን መወጣት ይኖርብናል።