ቀጥታ፡

የአውሮፓ ምሽት፡ ፒኤስጂ ከቪያሪያል፣ ባርሴሎና ከአስቶንቪላ እና አትሌቲኮ ከባየር ሙኒክ የሚያደርጓቸው ተጠባቂ ፍልሚያዎች

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል።

ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በስታዲዮ ዴላ ሴራሚካ ቪያሪያል ከፒኤስጂ ይጫወታሉ።

ባለሜዳው ቪያሪያል በሶስት ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ፒኤስጂ በሊግ ምዕራፉ እስከ አሁን ያደረጋቸውን ሶስት ጨዋታዎችን በማሸነፍ በዘጠኝ ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዟል።

ያለፉትን ተከታታይ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያነሳው ፒኤስጂ ጨዋታውን የማሸነፍ የቅድሚያ አግኝቷል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ባርሴሎና ከአስቶንቪላ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በካምፕ ኑ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።




ባርሴሎና በስድስት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። አስቶንቪላ በዘጠኝ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሶስተኛው ዙር መርሐ ግብር በፒኤስጂ የ4 ለ 2 ሽንፈት ያስተናገደው ባርሴሎና ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።

ተጋጣሚው አስቶንቪላ በድል ጉዞው ለመቀጠል ይፋለማል። ጨዋታው ተመልካችን የሚያዝናና እንቅስቃሴ ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም አትሌቲኮ ማድሪድ ከባየር ሙኒክ የሚያደርጉት ጨዋታም ትኩረትን ስቧል።

የማድሪዱ ክለብ በአራት ነጥብ 16ኛ ደረጃን ሲይዝ ባየርን በአምስት ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሁለቱ ክለቦች በተመሳሳይ ባለፉት ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች አላሸነፉም።

ቡድኖቹ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።




ማንችስተር ዩናይትድ ምሽት አምስት ላይ ሮማን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ያስተናገዳል።

ባለፉት ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግ ሽንፈት ያስተናገደው ዩናይትድ በሶስት ነጥብ 20ኛ ደረጃን ይዟል። በሶስተኛው ዙር በኮሞ ያስተናገደው የ4 ለ 1 ሽንፈት ቡድኑን የበለጠ ጫና ውስጥ ከቶታል።

ሮማ በአራት ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በሶስተኛው ዙር መርሐ ግብር ስሎቫን ብራቲስላቫን 4 ለ 0 ረትቷል።

ጨዋታው ዩናይትድ ወደ ድል መንገድ ለመመለስ፣ ሮማ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ የሚያደርጉት ነው።

በሌሎች መርሐ ግብሮች ፌይኖርድ ከኢንተር ሚላን፣ ቦዶ ግሊምት ከሊል እና ላስክ ከስሎቫን ብራቲስላቫ በተመሳሳይ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ጋላታሳራይ ከስቱትጋርት እና ሻካታር ዶኔስክ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም