ኢትዮጵያ እና ቻይና በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና በአቅም ግንባታ መስኮች ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ቻይና በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና በአቅም ግንባታ መስኮች ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 24/2019(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ቻይና በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና በአቅም ግንባታ መስኮች ያለውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የሆኑትን አምባሳደር ቼን ሃይን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሚኒስትሩ ከአምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ውይይት በሁኔታዎች የማይለወጠውን የኢትዮጵያ እና የቻይና ስትራቴጂካዊ ትብብር የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሁለቱ አገራት በተለይም በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና በአቅም ግንባታ መስኮች ያለውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል።
በውይይቱ ወቅት የቻይናው አምባሳደር ቼን ሃይ ሀገራቸው የመደመር መንግሥት ትልሞች ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።