ሀረር ከተማ የአለም አቀፉ የሀር መንገድ የቱሪዝም ጥምረት አባል ከተማ ሆነች - ኢዜአ አማርኛ
ሀረር ከተማ የአለም አቀፉ የሀር መንገድ የቱሪዝም ጥምረት አባል ከተማ ሆነች
ሀረር፣ ጥቅምት 24/ 2019 (ኢዜአ):- የሀረር ከተማ የአለም አቀፉ የሀር መንገድ የቱሪዝሞ ጥምረት (the International Tourism Alliance of Silk Road Cities) አባል ከተማ ሆነች።
ከተማዋ የዚህ አለም አቀፍ የቱሪዝም ጥምረት አባል መሆኗ በአለም የቱሪዝም መስክ የጎላ ትኩረት እንድትስብ፣ ጎብኚዎችን ከተለያየ አለም ክፍል ለመሳብ፣ የከተማዋ ቅርሶችና የቱሪዝም መስህቦችን በይበልጥ ለማስተዋወቅ፣ ከጥምረቱ አባል ሀገራት ጋር በትብብርና በጋራ ለመስራት፣ ዘርፉን ለማሳደግ የሚያስችል ልምድ ለመለዋወጥና ቱሪዝሙን በይበልጥ ለማልማት ከፍተኛ ዕገዛ ያደርጋል ተብሏል።
ከተማዋ የጥምረቱ አባል የሆነችውም በቻይና ሉዣን ከተማ ዛሬ በተካሄደው የ2026 የሀር መንገድ የቱሪዝም ጥምረት አባል ከተሞች አመታዊ አለም አቀፍ የጉዞ ኤጀንቶች ኮንፈረንስ ላይ ነው።
የሀረር ከተማ በአለም አቀፉ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳዬንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ ሁለት የሚዳሰስና የማይዳሰስ አለም አቀፍ ቅርሶችን ያስመዘገበች፣ የአለም የቅርስ ከተሞች ድርጅት አባል፣ የአለም የቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን እና ሌሎች አለም አቀፍ ጥምረቶች አባል መሆኗ ይታወሳል።