ኤቨርተን ድል አድርጓል - ኢዜአ አማርኛ
ኤቨርተን ድል አድርጓል
3አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤቨርተን ኒውካስትል ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ትናንት ማምሻውን በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቲዬርኖ ባሪ በ49ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
በጨዋታው ኤቨርተን የተሻሉ የግብ ማግባት እድሎችን ፈጥሯል።
ተጋጣሚው ኒውካስትል የኳስ ቁጥጥር ብልጫውን ወደ ግብ መቀየር አልቻለም።
የኒውካስትሉ ጃኮብ ራምሴይ በ98ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ወጥቷል።
ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኤቨርተን በ13 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 7ኛ ከፍ አድርጓል።
ኒውካስትል ዩናይትድ በ11 ነጥብ ከነበረበት 12ተኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።
ጨዋታውን ተከትሎ ዘጠነኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የ10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከጥቅምት 27 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።