ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ጂኦፓርክ በዩኔስኮ አስመዘገበች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ጂኦፓርክ በዩኔስኮ አስመዘገበች
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ጂኦፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ጂኦፓርኮች ዝርዝር ውስጥ በመካተት ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ።
ይህ ስኬት የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት፣ ልዩ የጂኦሎጂ ቅርስና የቱሪዝም መስህቦች ለዓለም የሚያስተዋውቅ ከፍተኛ ብሔራዊ ድል መሆኑን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ጂኦ ፓርክ (Geopark) ማለት በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ (UNESCO) እውቅና የተሰጠው ልዩ የጂኦሎጂካል ቅርሶች፣ የመሬት ገጽታዎችና ታሪካዊ ቦታዎች ያሉበትን አካባቢ የሚያመለክት ነው።
እነዚህ ፓርኮች የጂኦሎጂካል ታሪካቸውን ለመጠበቅ፣ ለማስተማር እና ለዘላቂ ልማት ለማዋል የሚያስችል የተቀናጀ አስተዳደር ስርዓት አላቸው።