ኢትዮጵያ መድን ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ መድን ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3 ለ 1 ረትቷል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሳሙኤል ሳሊሶ፣ ዳዊት አውላቸው እና ወገኔ ገዛኸኝ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሄኖክ ኤርሚያስ የንግድ ባንክን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል መንገድ የተመለሰው ኢትዮጵያ መድን በሰባት ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 6ኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን አሳክቷል።
በአንጻሩ በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስምንት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
ጨዋታውን ተከትሎ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠናቋል።