ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
በትግራይ ክልል ለሠራተኞች ዛሬ ደመወዝ መከፈል ይጀመራል
Nov 3, 2026 21
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፦ በትግራይ ክልል ከቀን ወደ ቀን ሰላምና መረጋጋት ሙሉ በሙሉ እየተረጋገጠ መምጣቱና ዜጎች ያለ ምንም ሥጋት የቀደመ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወታቸውን በነፃነት መምራት የቻሉበት ብሩህ ድባብ መፈጠሩ ተገለጸ። የባለአደራ አስተዳደሩ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች በመድረስ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ተቋማትም በሙሉ አቅማቸው ወደ ሙሉ አገልግሎት እንዲገቡ የማድረግ ሥራውን በስኬት በማከናወን ላይ ይገኛል። የባለአደራ አመራር አደራጅ ቡድን አስተባባሪው ብርሃነ ገብረፃዲቅ እንደገለጹት፤ ኅብረተሰቡ አሁን ያገኘውን ሰላምና ነፃነት ለማስጠበቅና ላለማጣት ከለውጡ አመራርና ከመንግሥት ጋር በከፍተኛ ቁርጠኝነትና ንቃት እየሰራ ይገኛል። የሕዝቡን ቀጥተኛና ነፃ ምርጫ መሠረት በማድረግ እየተከናወነ ባለው የባለአደራ አመራሩን እስከ ታችኛው መዋቅር የማደራጀት ሂደትም በሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ ምክንያት አሁን ላይ 60 በመቶ መጠናቀቁን አስተባባሪው አረጋግጠዋል።   የባለአደራ አስተዳደሩ መዋቅር እየተሟላ በሄደ ቁጥር የአገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ማስገባት የተቻለ ሲሆን ባንኮች፣ የንግድ ተቋማትና የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አሁን ላይ በሙሉ አቅማቸው ተነቃቅተው ወደ አገልግሎት ገብተዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በባለአደራ አስተዳደሩ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪው ቴዎድሮስ አረጋይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ለመንግሥት ሠራተኛው የደመወዝ ክፍያ እንዲጀምር በተደረገው ጥረት መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ደመወዝ መክፈል ይጀመራል ብለዋል።   የባለአደራ አስተዳደሩ የትግራይ ክልል ሕዝብ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ያሳየውን ሁለንተናዊ ድጋፍና ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
በዞኑ ለበጋ መስኖና ለመጪው መኸር የሚውል የተፈጥሮ ማዳበሪያ ተዘጋጅቷል
Nov 3, 2026 18
ባህር ዳር፣ ጥቅምት 24/2019(ኢዜአ)፡-በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ለበጋ መስኖና ለመጪው መኸር ሰብል ልማት የሚውል ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ። የመምሪያው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቡድን መሪ አቶ ነጋ መከተ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለበጋ መስኖና ለመጪው መኸር ሰብል ልማት 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ ስራው እየተከናወነ ይገኛል። በተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅቱ ከ155 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ እስካሁን በተደረገ ጥረት የዕቅዱን 75 በመቶ ማሳካት እንደተቻለም ገልጸዋል። ከመደበኛ ኮምፖስት በተጨማሪ ከ10 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ የባዮጋዝ ተረፈ ምርትና ከ14 ሺህ 800 ኩንታል በላይ ቨርሚ ኮምፖስት ተዘጋጅተው አሁን ላይ ለመስኖ ልማት ስራው ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑን አመልክተዋል። የተፈጥሮ ማዳበሪያ የአፈር ንጥረ ነገር ይዘት እንዲሻሻልና ምርታማነት እንዲጨምር ከማድረግ ባለፈ፣ አርሶ አደሩ ለፋብሪካ ማዳበሪያ ያወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ እየቀነሰ እንዲመጣ አስችሏል። የአርሶ አደሩ በተፈጥሮ ማዳበሪያ ጠቀሜታና ዝግጅት ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ፣ በአካባቢው በቀላሉ ከሚገኙ አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎችና ከተረፈ ምርት ጥራቱን የጠበቀ ማዳበሪያ አዘጋጅቶ እየተጠቀመ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በዞኑ የጓንጓ ወረዳ አርሶ አደር መኮንን ፈንታው እንዳሉት፤ ባለፈው ዓመት የጥራት ደረጃውን ጠብቀው ባዘጋጁት የተፈጥሮ ማዳበሪያ በአንድ ሄክታር መሬት የበቆሎ ሰብል በማልማት ጥሩ ምርት ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ዘንድሮም አንድ ሄክታር የእርሻ መሬታቸውን በተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማልማት አቅደው ወደ ስራ በመግባት እስካሁን 20 ኩንታል ማዘጋጀት እንደቻሉ አመልክተዋል። ባለሙያ በሚሰጣቸው ሙያዊ ምክረ ሃሳብ ታግዘው የተፈጥሮ ማዳበሪያን አዘጋጅተው መጠቀም ከጀመሩ ዓመታትን እንዳስቆጠሩ የገለጹት ደግሞ የዚሁ ወረዳ አርሶ አደር አልጋነህ አካል ናቸው። በዚህ ዓመትም ከ30 ኩንታል በላይ ለማዘጋጀት አቅደው እስካሁን 10 ኩንታል የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጀት እንደቻሉ ገልጸው፣ በቀጣይ ዕቅዳቸውን በማሳካት ለፋብሪካ ማዳበሪያ መግዣ ሊያወጡ የሚችሉትን ወጪ ለማስቀረት እየሰሩ መሆኑን ገለጸዋል። በዞኑ በበጋ መስኖና በመጪው መኸር ሰብል ልማት ከ165 ሺህ 700 በላይ ሄክታር መሬት የተፈጥሮ ማዳበሪያን ተጠቅሞ ለማልማት የተቀመጠው ግብ እንዲሳካ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ታሪክ የማይዘነጋው ክህደት እና የኢትዮጵያዊያን አኩሪ ጽናት!
Nov 3, 2026 56
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት መሆኑ ይታወቃል። ለዚህ ጀግና እና ህዝባዊ ሰራዊት ተገቢውን ክብርና ምስጋና መስጠት ሲገባ ክህደት ሲፈፀምበት ግን እጅግ አሳዛኝ ነው።ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በባንዳዎች ድንገት የተፈፀመበት ክህደት ታሪክ የማይዘነጋው የክህደት ጥግ ነው። በመሆኑም የዛሬው እለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት በባንዳዎች የተፈጸመበትን ታሪካዊ ክህደት እና በጽናት የታለፈበት የሚታወስበት መሆኑ ይታወቃል።   እለቱ ሲታወስ ሰራዊቱ ለአመታት የህዝብን ሰላም፣የሀገር ዳር ድንበር እና የልማት ስራዎችን በሚያግዘው ህዝባዊ ሰራዊት ላይ በውስጥ ባንዳዎች አረመኔያዊ ድርጊትና ታሪክ የማይረሳው ክህደት የተፈፀመበት በመሆኑ የሚዘከርበት ነው። በዕለቱ የተፈጸመው ድርጊት የትኛውንም ሰብአዊነትና ወታደራዊ ስነ-ምግባር ያልተከተለ የአረመኔያዊ ድርጊት ነበር ማለት ይቻላል። በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሀገር ክብርና ሉአላዊነት ለዜጎች ፍቅርና አክብሮት ሲል የከፈለው መስዋዕትነት መቼም ቢሆን ሊረሳ አይችልም።   የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት በማውገዝ ከሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ምሰሶ ነው በማለት ከጎኑ በመሰለፍ እገዛና ድጋፉን በተግባር አሳይቷል። ህዝቡ በከሃዲዎቹ ድርጊት በማዘንና በመቆጨት ሀገር ለማፍረስ የተንቀሳሰቀውን የጥፋት ቡድን መመከት ችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወታደራዊ ልብሳቸውን ለብሰው ወደ ግንባር በመዝመት ሀገራቸውን ከጥፋት የታደጉበት አጋጣሚም የዚሁ ታሪክ አካል ነው። በመሆኑም ጥቅምት 24ን ስንዘክር፣ በዕለቱ ሕይወታቸውን ላጡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና ዜጎች ክብር በመስጠት፣ እንዲህ አይነት ክህደት ሀገር የማፍረስ እቅድ በመሆኑ እንዳይደገም ትውልድ እያወቀው እንዲሄድ በማድረግ ይሆናል።ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ተገቢውን ክብርና ፍቅር በመስጠት ሁላችንም ሀገራዊ አደራችንን መወጣት ይኖርብናል።
የሚታይ
በትግራይ ክልል ለሠራተኞች ዛሬ ደመወዝ መከፈል ይጀመራል
Nov 3, 2026 21
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፦ በትግራይ ክልል ከቀን ወደ ቀን ሰላምና መረጋጋት ሙሉ በሙሉ እየተረጋገጠ መምጣቱና ዜጎች ያለ ምንም ሥጋት የቀደመ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወታቸውን በነፃነት መምራት የቻሉበት ብሩህ ድባብ መፈጠሩ ተገለጸ። የባለአደራ አስተዳደሩ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች በመድረስ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ተቋማትም በሙሉ አቅማቸው ወደ ሙሉ አገልግሎት እንዲገቡ የማድረግ ሥራውን በስኬት በማከናወን ላይ ይገኛል። የባለአደራ አመራር አደራጅ ቡድን አስተባባሪው ብርሃነ ገብረፃዲቅ እንደገለጹት፤ ኅብረተሰቡ አሁን ያገኘውን ሰላምና ነፃነት ለማስጠበቅና ላለማጣት ከለውጡ አመራርና ከመንግሥት ጋር በከፍተኛ ቁርጠኝነትና ንቃት እየሰራ ይገኛል። የሕዝቡን ቀጥተኛና ነፃ ምርጫ መሠረት በማድረግ እየተከናወነ ባለው የባለአደራ አመራሩን እስከ ታችኛው መዋቅር የማደራጀት ሂደትም በሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ ምክንያት አሁን ላይ 60 በመቶ መጠናቀቁን አስተባባሪው አረጋግጠዋል።   የባለአደራ አስተዳደሩ መዋቅር እየተሟላ በሄደ ቁጥር የአገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ማስገባት የተቻለ ሲሆን ባንኮች፣ የንግድ ተቋማትና የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አሁን ላይ በሙሉ አቅማቸው ተነቃቅተው ወደ አገልግሎት ገብተዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በባለአደራ አስተዳደሩ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪው ቴዎድሮስ አረጋይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ለመንግሥት ሠራተኛው የደመወዝ ክፍያ እንዲጀምር በተደረገው ጥረት መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ደመወዝ መክፈል ይጀመራል ብለዋል።   የባለአደራ አስተዳደሩ የትግራይ ክልል ሕዝብ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ያሳየውን ሁለንተናዊ ድጋፍና ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
አዲስ አበባ፤ በዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት መድረኮች ተከታታይ እውቅና እያገኘች ያለች ከተማ
Nov 2, 2026 269
ከተማን መለወጥ የሚቻለው በግልጽ ራዕይ፣ በተቀናጀ ጥረትና የሰው ልጅን ሕይወት ማዕከል ባደረገ የልማት አቅጣጫ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ አዲስ አበባም ይህንን እሳቤ በተግባር እየተረጎመች መሆኗን በዓለም አቀፍ መድረክ ዳግም አስመስክራለች ብለዋል። በቅርቡ በቻይና ሻንሃይ ከተማ በተካሄደው የ2026 የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማት ውድድር፣ አዲስ አበባን ጨምሮ አምስት ከተሞች ተሸላሚ ሆነዋል ነው ያሉት። በዘንድሮው የሻንሃይ ሽልማት እውቅና ያገኙት፦ 1. አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) 2. ሳንቲያጎ ዴ ካሊ (ኮሎምቢያ) 3. ኢስታንቡል (ቱርኪዬ) 4. ጂንግዴዠን (ቻይና) 5. ካቶቪስ (ፖላንድ) መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ ሽልማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአራተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዲስ አበባ በአራቱ ዙሮች ሁለት ጊዜ እውቅና አግኝታለች በማለት አስታውሰዋል። በ2024 የሴኡል ስማርት ሲቲ ሽልማትን፣ በ2026 ደግሞ የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማትን አግኝታለች ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ በ2023 አዲስ አበባ በምገባ ፕሮግራምና በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዘርፎች ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች ያለች ከተማ በመሆኗ ዓለም አቀፍ እውቅናና ሽልማት ማግኘቷን ጠቁመዋል። ይህ እውቅና ለሀገራችን ታላቅ ክብር ከመሆኑም በላይ፣ እየሠራን ላለነው ሥራ ብርታትና ተጨማሪ ተነሳሽነት የሚሰጥ ነው ሲሉም አክለዋል። ከሁሉም በላይ፣ በከተማችን የምንተገብራቸው ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃና የአኗኗር ሁኔታ ለማሻሻል የምናደርገው ጥረት፣ እንዲሁም የከተማዋን የተፈጥሮና ማኅበራዊ ፀጋዎች ወደ ልማትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የመቀየር ሥራችን ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የሚያረጋግጥ ዓለም አቀፍ ምስክርነት ነው። የመደመር እሳቤያችንም ልማትን ከሰው ሕይወትና ደኅንነት ጋር አጣምሮ ያያል። ከተሞች የሥልጣኔ መገለጫ እንዲሆኑ፣ ያላቸውን ፀጋዎች በመለየትና በማልማት፣ የሰውን አቅም ከተፈጥሮና ከኢኮኖሚያዊ ሀብቶች ጋር በማቀናጀት ለጋራ ብልፅግና መሥራትን ይጠይቃል። በከተማችን የልማት ጉዞ እስካሁን የተጓዝነው ርቀት ጠንካራ መሠረት የጣለ ቢሆንም፣ የሚቀረን ረጅም ጉዞ እንዳለ እናውቃለን። ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዘመናት ከተጫኗት ድህነትና ልዩ ልዩ ችግሮች በዘላቂነት ለመላቀቅ፣ ቀጣይነት ያለው ለውጥ ለማምጣትና ወደ ብልፅግና ለመሸጋገር የጀመረችው ጉዞ ፍሬ እያፈራ ይገኛል። ሆኖም ይህንን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ወደ ተሟላና ዘላቂ ለውጥ ለመቀየር የሁሉንም ዜጎች ርብርብ፣ ቁርጠኝነትና ተሳትፎ ያስፈልጋል። ስለሆነም ሁላችንም ለለውጡ በቁርጠኝነት መትጋት ይገባናል ብለዋል። ያገኘነውን ዓለም አቀፍ እውቅናም እንደ መዳረሻ ሳይሆን፣ እንደ ተጨማሪ ኃላፊነትና ለበለጠ ሥራ ማበረታቻ እንወስደዋለን ሲሉም አክለዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ አያይዘውም፣ ይህንን ተነሳሽነት በመያዝ፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች የሥልጣኔና የብልፅግና መሠረት እንዲሆኑ እንሠራለን ብለዋል። አቅሞቻችንን በመደመር፣ ፀጋዎቻችንን ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር፣ ክብራችንን የሚመጥን የብልፅግና ግብ ለመድረስ ትጋታችንን እናጠናክራለን በማለትም ገልጸዋል። ከተሞቻችን የመደመር ሥልጣኔ መዳረሻ፣ ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ተስማሚ የኑሮ አካባቢ፣ ለቀጣዩ ትውልድም ዘላቂ የብልፅግና ውርስ እንዲሆኑ በጋራ እንሠራለን ሲሉም አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ አስቻይ የንግድና ኢንቨስትመንት የፖሊሲ እርምጃ ለአልሚ ባለሃብቶች ምቹ ምኅዳር ፈጥሯል
Nov 2, 2026 244
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አስቻይ የንግድና ኢንቨስትመንት የፖሊሲ እርምጃ ለተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አልሚ ባለሃብቶች ምቹ ምኅዳር መፍጠሩን የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የሴቶች ቢዝነስ ምክር ቤት ገለጸ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ፍኖት የማድረግ ትልም በሁሉም መስክ እመርታዊ ውጤቶችን ማስገኘቱን ቀጥሏል። የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብርም የኢትዮጵያን የግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና የዲጂታል ዘርፍ ንግድና ኢንቨስትመንት በማበረታታት ጸጋን ወደ ጥቅም ቀይሯል። ይህም የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ በማስፋት የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አልሚዎችን ንቁ ተሳትፎ እያጎለበተ ይገኛል። የኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስርም በሁሉም ዘርፍ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት አቅም ፈጥሯል። የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የሴቶች ቢዝነስ ምክር ቤት ሊቀመንበር አይሻ መሐመድ ሰኢድ አል ሙላ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የሀገራቱ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ዕድገትም በሀገራቱ መንግሥታት ጠንካራ ትብብር የተገነባ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመንት አስቻይ የፖሊሲ እርምጃም ለተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አልሚ ባለሃብቶች ምቹ ምኅዳር መፍጠሩን ተናግረዋል። የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ሴት አልሚዎችም በኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚሰማሩበትን ትልቅ መሰረት መጣሉን አንስተዋል። የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የሴቶች ቢዝነስ ምክር ቤትም በኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች መሳተፍ የሚያስችሉ ጉዳዮችን እየለየ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። በቀጣይም በግብርና፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በግብርና ማቀነባበርና በሌሎች በርካታ የንግድና የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍና የንግድ ትስስርን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። "አዲስ አጋርነትን ማጠናከር እና የወደፊቱን አብሮ መምራት" በሚል መሪ ሃሳብ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች እና የኢትዮጵያ የንግድ ልዑካን የ2026 የንግድ ፎረም ላይ መሳተፋቸው ይታወሳል።  
5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የማህበረሰብ ጤና ጉባኤ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ አስፈላጊ ዝግጅት እየተደረገ ነው- ዶክተር መቅደስ ዳባ
Nov 2, 2026 242
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦አምስተኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የማህበረሰብ ጤና ጉባኤ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ አስፈላጊ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ አስታወቁ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን አምስተኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የማህበረሰብ ጤና ጉባኤ ዝግጅት አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኅን መግለጫ ሰጥተዋል።   በመግለጫቸውም፤ በጤና ሚኒስቴርና በአፍሪካ የጤና መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (African-CDC) ትብብር የተዘጋጀው 5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የማህበረሰብ ጤና ጉባኤ ከኅዳር 14 እስከ 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት፣ አፍሪካ የጤና መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (African-CDC) እና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗ ጉባኤውን ለማስተናገድ ዕድሉ እንደተሰጣት ተናግረዋል። ጉባኤዉም ''የአፍሪካ ጤና ደህንነትና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነትና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነትና የመቋቋም አቅም መሸጋገር'' በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ገልጸዋል። ኢትዮጵያም ጉባኤውን በስኬት በማስተናገድ በጤና ዘርፍ የተገኙ ልምድና ተሞክሮዎችን ለአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለማሳየት እንደምትጠቀምበት አንስተዋል። የጉባኤው ዋና መሪ ሃሳብ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ በአፍሪካ የጤና ራስን መቻል፣ የጤና ሥርዓት ጥንካሬና የወረርሽኝ መከላከል አቅምን ማሳደግ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ በጤና ዘርፍ የራሷን አቅም በማጠናከር፣ በሳይንሳዊ ምርምር፣ በቴክኖሎጂና በአህጉራዊ ትብብር የጤና ችግሮቿን በራሷ ለመፍታት የሚያስችላትን አቅም ማዳበር እንደሚጠበቅ አመልክተዋል። በጉባኤው የሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ሙያተኞች፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች በአፍሪካ ጤና አጀንዳዎች ላይ የጋራ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሚያግዝ ገልጸዋል። የአፍሪካ ሲዲሲ በአህጉሪቱ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን በመከላከልና በመቆጣጠር እንዲሁም የአፍሪካን የጤና አጀንዳ በዓለም አቀፍ መድረኮች በጋራ በማቅረብ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።   ጉባኤው የጤና ዘርፍ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ፣ የጤና መሠረተ ልማትን ለማጠናከር፣ የድንገተኛ ጤና አደጋ ምላሽ አቅምን ለማሳደግና ሳይንሳዊ ምርምርና ዲጂታል ጤናን ለማስፋፋት እንደሚያግዝ ገልጸዋል። በአፍሪካ የመድኃኒትና የሕክምና ቴክኖሎጂ ምርት፣ የጤና ኢንቨስትመንትንና በአህጉሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን ክህሎት ማሳደግ በጉባኤው የሚመከርባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቁመዋል። በጉባኤውም እስከ አሁን ድረስ ከ29 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ለመታደም መመዝገባቸውንና ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎች እንደሚጠበቁ ገልጸዋል። ከእነዚህም 18 ሺህ በላይ የሚሆኑት ተሳታፊዎች የእውቅና ሰርተፊኬት አግኝተው የመግቢያ ሂደታቸውን ማጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል። በቀጣይም ለአገር ውስጥ ተሳታፊዎች ተጨማሪ የምዝገባ እድሎች እንደሚከፈቱ አስታውቀዋል። የጉባኤው ዝግጅት ከጤና ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ከትራንስፖርት፣ ከሎጂስቲክስ፣ ከደኅንነት፣ ከቱሪዝምና ከሌሎች ዘርፎች ጋር በተቀናጀ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል። የጉባኤው ዝግጅት እስከ መጨረሻው የማስተናገድ ሂደት መድረሱን ገልፀዉ፤ የቪዛ፣ የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ዝግጅቶችም እየተጠናቀቁ መሆኑን አስረድተዋል።  

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
እንዳይደገም ሁሌም እንዘክራለን!
Nov 3, 2026 58
አንዳንድ ቀናት አሉ፤ ትውልድ በእምባ የሚያስታውሳቸው፣ ለዘላለም እንዳይደገሙ የሚመኛቸው፣ ከታሪክ በመማር የወደፊት ስህተቶችን ለመከላከል እንደ ትምህርት የሚወስዳቸው። እነኝህ ቀናት በትውልድ ልብ ውስጥ የሚቀሩ በታሪክ ተከትበው ዘመን የሚሻገሩ ናቸው። ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በዚህ ዕለት ለዓመታት ሕዝባቸውን ሲጠብቁ የኖሩ ጀግኖች በሚያምኑት ወገን ክዳት ተፈጽሞባቸዋል። ለሀገርና ለሕዝብ ክብር የቆሙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከፊት ይጠብቁት በነበረው ጠላት ሳይሆን ከኋላቸው በመጣ ወገን ክህደት ተመትተዋል። ሀገሬንና ሕዝቤን ብለው የተሰለፉ ወታደሮች በእጅጉ አሳዛኝ የሆነ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል። የሕዝብ ሰላም እንዲጠበቅ፣ ዜጎች በነፃነት ወጥተው እንዲገቡና ሀገር በሰላም እንድትኖር የራሳቸውን ሕይወት ሳይሰስቱ ለአደጋ የሚያጋልጡ ጀግኖች ናቸው። በዱር በገደሉ ኑሯቸውን አድርገው የሀገር ዘብ የሆኑ፣ ታሪክን ያስጠበቁና ሉዓላዊነትን ከጥቃት የተከላከሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት የጀግንነት ተምሳሌቶች ናቸው። እነዚህን ጀግኖች ያሰባሰባቸው የሀገር ፍቅር፣ አንድ ያደረጋቸው የሠንደቅ ዓላማ ክብርና ለኢትዮጵያ የገቡት ቃለ መሐላ ነው። በአንዲት ሀገር ያምኑ፣ በኢትዮጵያዊነት የጋራ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ወታደሮች በዚያ ዕለት ከባድ ክህደት ደረሰባቸው። ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ኢትዮጵያዊያን ልብ የሚሰብር ዜና የሰሙበት፣ እናቶች የልጆቻቸውን አሳዛኝ ሞት እያሰቡ በሐዘን ያነቡበትና ሀገር የተከዘችበት ዕለት ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ የተከዱት ጀግኖች በሐዘንና በተስፋ መቁረጥ አልተሸነፉም። ለሀገራቸው በገቡት ቃል ኪዳንና በሉዓላዊነቷ ላይ ባላቸው ጽኑ እምነት ተመስርተው ተነስተዋል። ክህደትና መከራ ቢደርስባቸውም የሀገር ግዴታቸውን አልተዉም፤ ጽናታቸውን አስመስክረው በወታደራዊ ብቃትና በጀግንነት ታሪክ ሠርተዋል። ጥቅምት 24ን የምናስታውሰው ክህደትን ለመወገዝ፣ የሠራዊቱን መሥዋዕትነት ለማክበር፣ የሕዝብና የሠራዊትን ትስስር ለማጠናከርና ታሪክ ዳግም እንዳይደገም ለመማር ነው። እንዳይደገም ሁሌም እንዘክራለን! የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት መልህቅ በመሆኗ በቀይ ባህር አካባቢ ህልውና እንዲኖራት መፈለጓ ተገቢ ነው
Nov 2, 2026 256
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና ደኅንነት መልህቅ እንደመሆኗ በቀይ ባህር አካባቢ ህልውና እንዲኖራት መፈለጓ ተገቢ ነው ሲሉ በአፍሪካ የደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ፖል ሲሞን ሃንዲ (ዶ/ር) ገለጹ። ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ብቻ ሳይሆን በአስተዳደርና ቢዝነስ ዘርፍም ገንቢ ሽግግር አድርጋለች ብለዋል። በአፍሪካ የደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ፖል ሲሞን ሃንዲ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የጣና ፎረምን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በማስተናገድ የቀጣናው መልህቅ መሆኗን አሳይታለች። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ላይ ገንቢ ሚና እየተወጣች መሆኑን ገልጸው፤ ችግሮችም በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ትፈልጋለች ብለዋል። የባህር በር ፍላጎት የኢትዮጵያ ቋሚ ፍላጎት ነው ያሉት ፖል ሲሞን ሃንዲ (ዶ/ር)፤ የመንግሥት ሰላማዊ መንገድን መከተል የሚደገፍ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት መልህቅ እንደመሆኗ በቀይ ባህር አካባቢ ውክልና እንዲኖራት መፈለጓ ተገቢ መሆኑን ገልጸው፤ ፍላጎቷን ከቀንዱ ሀገራት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ማግኘት አለባት ብለዋል። በናይጀሪያ የኦባፌሚ አዎሎዎ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ቻርለስ ዑኬጄ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት ከሀገራት ጋር በውይይትና በንግግር ሊፈታ ይገባል ብለዋል። ባለፉት አስር ዓመታት በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ብቻ ሳይሆን በአስተዳደርና ቢዝነስ ዘርፍም ገንቢ ሽግግር አድርጋለች ብለዋል። የጣና ፎረም የኢትዮጵያን መንግስት፣ ህዝቡንና የአፍሪካ ሀገራትን አሸናፊ የሚያደርግ ወሳኝ መድረክ መሆኑንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ታላቅ ሀይል መሆኗን ገልጸው፤ የባህር በር ፍላጎቷን ማሳካትና ሁሉንም አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ ከጎረቤት ሀገራት ጋር መወያየት አለባት ብለዋል።
የአቪዬሽን ደኅንነት ስምሪት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታላቅ ስሙንና የሀገር ኩራት መሆኑን ጠብቆ እንዲቀጥል አስችሏል
Nov 2, 2026 253
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ) ፦ የአቪዬሽን ደኅንነት ስምሪት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታላቅ ስሙንና የሀገር ኩራት መሆኑን ጠብቆ እንዲቀጥል አስችሏል ሲሉ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሲሳይ ቶላ (ዶ/ር) ገለጹ። በአቪዬሽን ደኅንነት ዘርፍ ለተገኘው ስኬት የዕውቅናና ምስጋና መርሃ-ግብር ተካሒዷል።   በመርሀ-ግብሩ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሲሳይ ቶላ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ የአቪዬሽን ዘርፍ ከሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት ቀጣይነት፣ ከዓለም-አቀፍ ግንኙነትና ከአየር ትራንስፖርት ትስስር ባሻገር ከብሔራዊ ደኅንነታችን ጋር የተያያዘ ስትራቴጂክ ጉዳይ ነው።   የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ደኅንነት ዘርፍ ስምሪትን ለማጠናከር አደረጃጀቱንና አሠራሩን በማሻሻልና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር፣ በመረጃ ላይ የተመሠረተ ፈጣንና ወቅታዊ ውሳኔ የመስጠት አቅሙን በማሳደግ እንዲሁም ቴክኖሎጂን የተልዕኮ አፈጻጸም ዋና አስቻይ መሣሪያ በማድረግ ባከናወናቸው የሪፎርም ተግባራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታላቅ ስሙንና የሀገር ኩራት መሆኑን ጠብቆ እንዲቀጥል አግዟል ያሉት ዶ/ር ሲሳይ፤ የዘርፉ አመራሮችና አባላትም ዓለም-አቀፋዊ፣ ቀጣናዊና ሀገራዊ ፈተናዎችን በመመከት ተልዕኳቸውን በላቀ ደረጃ መወጣታቸውን አመልክተዋል። ከአቪዬሽን ደኅንነት ጋር በተያያዘ በብሔራዊ ደረጃ የተቀናጀና ቅድመ መከላከልን የሚያስቀድም ሥርዓት እየተጠናከረ እንደሚሄድ፤ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ቋሚ ብሔራዊ የአቪዬሽን ስጋት ግምገማና ማስተባበሪያ ሥርዓት እንዲቋቋም እንደሚሠራ፤ እአአ በ2027 ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው ኮፕ-32 ጉባኤ በቂ ዝግጅት እንደሚደረግ እና እየተገነባ የሚገኘው የቢሾፍቱ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ታሳቢ ያደረገ አቅምና ሥርዓት እንደሚፈጠር ተናግረዋል።   የአቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አስራት ቀጄላ፣ የአቪዬሽን ደኅንነት ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት የሚፈልግ ዘርፍ መሆኑን በማንሳት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና ሌሎችንም ኦፕሬተሮችን የሚመጥን አቅም ለመገንባት ራዕይ ተሰንቆ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ረታ መላኩ በበኩላቸው፤ አየር መንገዱ በየጊዜው ለሚያሳየው እድገት እንዲሁም በዓለም-አቀፍ ደረጃ በአስተማማኝነቱ ተመራጭና እምነት የሚጣልበት ሆኖ እንዲዘልቅ በማድረግ ረገድ ከአየር መንገዱ ራዕይ፣ ስትራቴጂና አሠራር ባሻገር የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ደኅንነት ዘርፍ ስምሪት ወሳኝ ሚና እንደሚያበረክት አመልክተዋል። በአቪዬሽን ደኅንነት ዘርፍ የተገኘውን ስኬት በተመለከተ የተለያዩ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በታደሙበት መርሐ-ግብር ላይ በተለያየ ደረጃ የላቀ ሚና ያበረከቱ አባላት እንዲሁም ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ዕውቅናና ምስጋና ተችሯቸዋል።
በኦሮሚያ ክልል የተመዘገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስኬቶችን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር በተግባር እየተሠራ ነው
Nov 2, 2026 230
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የተመዘገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስኬቶችን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል እቅድ ወጥቶ በመተግበር ላይ መሆኑን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በመግለጫቸው፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሁለንተናዊ የልማት ግቦችን ለማሳካት በቁጭትና በጊዜ የለኝም መንፈስ እቅዶችን አውጥቶ ሲተገበር ቆይቷል ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበር በኢኮኖሚ እና በተለያዩ የልማት ዘርፎች ራስን መቻል ላይ ያተኮረ ስልታዊ ዕቅድ ይፋ አድርጎ እየተገበረ ይገኛል ብለዋል። ይህ ዕቅድ ክልሉ ያለውን ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት፣ የመሬት ለምነትና የሰው ኃይል በመጠቀም የውጭ እርዳታና ጥገኝነትን ማስቀረት እንዲሁም የኑሮ ውድነትን መቀነስ እንደ ዋና ዓላማ አድርጎ የያዘ ነው። በተለያዩ ደረጃዎች ሰፊና ጥልቅ ውይይት የተደረገበት ይህ የአምስት ዓመቱ ስልታዊ ዕቅድም ወደ ሙሉ ትግበራ መግባቱን አቶ ሃይሉ አመልክተዋል። በዕቅዱ የተቀመጡ ዋና ዋና ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ አምስት ዋና ዋና የልማት ሞተሮችን ለይቶ ወደ ሥራ መገባቱንም አስታውሰዋል። እነዚህም የሰው ኃይል ክህሎትን ማሳደግና የሥራ ፈጠራን ማበረታታት፣ ማሽነሪና ቴክኖሎጂን ማስፋፋት፣ ገቢን በማሳደግ የፋይናንስ አቅርቦትን ማጠናከር፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ማሳደግ፣ እንዲሁም ሞዴል የገጠር መንደርና ከተሜነትን ማረጋገጥ ናቸው ብለዋል። የዕቅዱ ዋና ዓላማ ሁሉንም ተግባራት በመደመር አስተሳሰብ በመምራት ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር መሆኑን የገለጹት አቶ ሃይሉ፣ ይህንንም ዓላማ ከእቅድ በላይ ለማሳካት ሰፊ ውይይት ተካሂዶ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን አስረድተዋል። ይህንንም ለማሳካት ኢኮኖሚን ማጠናከር፣ ማኅበራዊ ልማትን መምራትና የክልሉን ሰላም ማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል። ዕቅዱን ለማሳካት በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች፣ ከመንግሥት ሠራተኞችና ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይቶች እየተካሄዱ መሆኑንና የጋራ መግባባት መፈጠሩንም አመልክተዋል። በዚህም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ክልሉን ወደ ከፍተኛ የለውጥ ጉዞ ለማሸጋገር በተግባር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የመደመር መንግሥት ወጣቶች በሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸው እንዲጎለብት በልዩ ትኩረት እየሠራ ነው - ከንቲባ አብዱላሂ አደም
Nov 2, 2026 228
ድሬደዋ፣ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፡-የመደመር መንግሥት ወጣቶች በሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸው እንዲጎለብት በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አብዱላሂ አደም ተናገሩ። አስተዳደሩ "የዛሬ ወጣት፣ የነገ የድሬዳዋና የኢትዮጵያ ተስፋ" በሚል መሪ ሐሳብ ከከተማዋ ወጣቶች ጋር ዛሬ የውይይት መድረክ አካሄዷል።   ውይይቱን የመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አብዱላሂ አደም በወቅቱ እንዳሉት፣ የመደመር መንግሥት ወጣቶች በሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ ውስጥ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸው እንዲጎለብት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው። በዚህም በማኅበራዊ፣ በምጣኔ ሀብታዊና በፖለቲካው ዘርፎች የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በተጨባጭ እመርታ እየተጓዘ መሆኑን አንስተዋል። አዲሱ የድሬዳዋ አስተዳደር የተጀመሩትን ጥረቶች ይበልጥ ፍሬያማ ለማድረግ ከገጠርና ከከተማ ወጣቶች ጋር የቀረበ ትስስር በመፍጠር የተሻለ ውጤታማ ሥራ እንደሚከናወን ገልጸዋል። በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አብዱልጀዋድ መሐመድ በበኩላቸው፣ ወጣቶች ለሰላም፣ ለልማትና ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት መጠናከር እያበረከቱ ያለው አስተዋጽኦ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው ብለዋል።   የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ይበልጥ እያሳደገና አገር ገንቢነታቸውን በተግባር እያረጋገጠ መሆኑንም ገልጸዋል። በየደረጃው የሚገኘው ወጣት የእርስ በርስ ትስስርንና አንድነቱን በማጠናከር ለአገር ከፍታና ብልጽግና እያከናወነ የሚገኘው የበጎ ፈቃድ ልማት መጠናከር እንዳለበት የገለጹት ደግሞ የድሬዳዋ የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ ናቸው። ለዚህም አስፈላጊው አሠራርና አደረጃጀት ተዘርግቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን አስታውሰው ወጣቶች ጤናማ ዜጎች ሆነው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በየወረዳው ዘመናዊ የስፖርት ሜዳዎችና ማዕከላት መስፋፋታቸውን አንስተዋል። በውይይቱ ከተሳተፉ ወጣቶች መካከል ወጣት ደሃቦ አደምና ወጣት አሸናፊ ስዩም፣ የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅና በክረምትም ሆነ በበጋ በሚካሄዱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ወጣቱ በየወረዳቸው በሚከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ ለድሬዳዋ ዕድገት ኃላፊነቱን በተሻለ ደረጃ እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል።    
በክልሉ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ-አቶ ሃይሉ አዱኛ
Nov 2, 2026 311
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ ገለጹ። አቶ ሃይሉ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን፣በሽርካ ወረዳ፣በብርቦ ጮሌ ቀበሌ የተፈጸመውን የጽምዶ ቡድን ጥቃት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የተጎዳውን ማኅበረሰብ መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ሕዝቡ ያስመዘገባቸውን ድሎች በመጠበቅና በአንድነት ወደ ፊት መራመድ እንዳለበት ገልፀው፣ጥቃቱን የፈፀሙ እነዚህ ኃይሎች አዲስ የተጀመረውን የልማትና የለውጥ ሂደት ለማደናቀፍ በሽብር ተግባር በመሰማራት ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ብለዋል። በ2019 ዓ.ም.ጥቅምት 14 ቀን በሽርካ ወረዳ፣ በብርቦ ጮሌ ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃት የንጹሐን ዜጎች ሕይወት መጥፋቱ፣የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት መቃጠሉ፣እንዲሁም ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤቶቻቸውና ከንብረቶቻቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል። ጥቃቱን ተከትሎ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተካሄዱ የጸጥታ ሥራዎች 73 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ መሆናቸውን፣ እንዲሁም እነዚህ ኃይሎች እንቅስቃሴ የሚያደርጉባቸው የነበሩ ስድስት ቀበሌዎች ጸጥታቸው መረጋገጡን ገልጸዋል። መንግሥት በአንድ በኩል የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እርምጃ እየወሰደ፣ በሌላ በኩል ከመኖሪያ ቤቶቻቸውና ከንብረቶቻቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰብዓዊ፣የምግብና የሕክምና ድጋፍ እያቀረበ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም ተፈናቃይ ዜጎችን ወደ መኖሪያ ቤቶቻቸውና ንብረቶቻቸው ለመመለስ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን መግለጫው ያመለክታል።

ማህበራዊ
አዲስ አበባ፤ በዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት መድረኮች ተከታታይ እውቅና እያገኘች ያለች ከተማ
Nov 2, 2026 269
ከተማን መለወጥ የሚቻለው በግልጽ ራዕይ፣ በተቀናጀ ጥረትና የሰው ልጅን ሕይወት ማዕከል ባደረገ የልማት አቅጣጫ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ አዲስ አበባም ይህንን እሳቤ በተግባር እየተረጎመች መሆኗን በዓለም አቀፍ መድረክ ዳግም አስመስክራለች ብለዋል። በቅርቡ በቻይና ሻንሃይ ከተማ በተካሄደው የ2026 የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማት ውድድር፣ አዲስ አበባን ጨምሮ አምስት ከተሞች ተሸላሚ ሆነዋል ነው ያሉት። በዘንድሮው የሻንሃይ ሽልማት እውቅና ያገኙት፦ 1. አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) 2. ሳንቲያጎ ዴ ካሊ (ኮሎምቢያ) 3. ኢስታንቡል (ቱርኪዬ) 4. ጂንግዴዠን (ቻይና) 5. ካቶቪስ (ፖላንድ) መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ ሽልማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአራተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዲስ አበባ በአራቱ ዙሮች ሁለት ጊዜ እውቅና አግኝታለች በማለት አስታውሰዋል። በ2024 የሴኡል ስማርት ሲቲ ሽልማትን፣ በ2026 ደግሞ የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማትን አግኝታለች ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ በ2023 አዲስ አበባ በምገባ ፕሮግራምና በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዘርፎች ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች ያለች ከተማ በመሆኗ ዓለም አቀፍ እውቅናና ሽልማት ማግኘቷን ጠቁመዋል። ይህ እውቅና ለሀገራችን ታላቅ ክብር ከመሆኑም በላይ፣ እየሠራን ላለነው ሥራ ብርታትና ተጨማሪ ተነሳሽነት የሚሰጥ ነው ሲሉም አክለዋል። ከሁሉም በላይ፣ በከተማችን የምንተገብራቸው ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃና የአኗኗር ሁኔታ ለማሻሻል የምናደርገው ጥረት፣ እንዲሁም የከተማዋን የተፈጥሮና ማኅበራዊ ፀጋዎች ወደ ልማትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የመቀየር ሥራችን ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የሚያረጋግጥ ዓለም አቀፍ ምስክርነት ነው። የመደመር እሳቤያችንም ልማትን ከሰው ሕይወትና ደኅንነት ጋር አጣምሮ ያያል። ከተሞች የሥልጣኔ መገለጫ እንዲሆኑ፣ ያላቸውን ፀጋዎች በመለየትና በማልማት፣ የሰውን አቅም ከተፈጥሮና ከኢኮኖሚያዊ ሀብቶች ጋር በማቀናጀት ለጋራ ብልፅግና መሥራትን ይጠይቃል። በከተማችን የልማት ጉዞ እስካሁን የተጓዝነው ርቀት ጠንካራ መሠረት የጣለ ቢሆንም፣ የሚቀረን ረጅም ጉዞ እንዳለ እናውቃለን። ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዘመናት ከተጫኗት ድህነትና ልዩ ልዩ ችግሮች በዘላቂነት ለመላቀቅ፣ ቀጣይነት ያለው ለውጥ ለማምጣትና ወደ ብልፅግና ለመሸጋገር የጀመረችው ጉዞ ፍሬ እያፈራ ይገኛል። ሆኖም ይህንን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ወደ ተሟላና ዘላቂ ለውጥ ለመቀየር የሁሉንም ዜጎች ርብርብ፣ ቁርጠኝነትና ተሳትፎ ያስፈልጋል። ስለሆነም ሁላችንም ለለውጡ በቁርጠኝነት መትጋት ይገባናል ብለዋል። ያገኘነውን ዓለም አቀፍ እውቅናም እንደ መዳረሻ ሳይሆን፣ እንደ ተጨማሪ ኃላፊነትና ለበለጠ ሥራ ማበረታቻ እንወስደዋለን ሲሉም አክለዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ አያይዘውም፣ ይህንን ተነሳሽነት በመያዝ፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች የሥልጣኔና የብልፅግና መሠረት እንዲሆኑ እንሠራለን ብለዋል። አቅሞቻችንን በመደመር፣ ፀጋዎቻችንን ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር፣ ክብራችንን የሚመጥን የብልፅግና ግብ ለመድረስ ትጋታችንን እናጠናክራለን በማለትም ገልጸዋል። ከተሞቻችን የመደመር ሥልጣኔ መዳረሻ፣ ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ተስማሚ የኑሮ አካባቢ፣ ለቀጣዩ ትውልድም ዘላቂ የብልፅግና ውርስ እንዲሆኑ በጋራ እንሠራለን ሲሉም አረጋግጠዋል።
5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የማህበረሰብ ጤና ጉባኤ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ አስፈላጊ ዝግጅት እየተደረገ ነው- ዶክተር መቅደስ ዳባ
Nov 2, 2026 242
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦አምስተኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የማህበረሰብ ጤና ጉባኤ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ አስፈላጊ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ አስታወቁ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን አምስተኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የማህበረሰብ ጤና ጉባኤ ዝግጅት አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኅን መግለጫ ሰጥተዋል።   በመግለጫቸውም፤ በጤና ሚኒስቴርና በአፍሪካ የጤና መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (African-CDC) ትብብር የተዘጋጀው 5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የማህበረሰብ ጤና ጉባኤ ከኅዳር 14 እስከ 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት፣ አፍሪካ የጤና መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (African-CDC) እና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗ ጉባኤውን ለማስተናገድ ዕድሉ እንደተሰጣት ተናግረዋል። ጉባኤዉም ''የአፍሪካ ጤና ደህንነትና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነትና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነትና የመቋቋም አቅም መሸጋገር'' በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ገልጸዋል። ኢትዮጵያም ጉባኤውን በስኬት በማስተናገድ በጤና ዘርፍ የተገኙ ልምድና ተሞክሮዎችን ለአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለማሳየት እንደምትጠቀምበት አንስተዋል። የጉባኤው ዋና መሪ ሃሳብ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ በአፍሪካ የጤና ራስን መቻል፣ የጤና ሥርዓት ጥንካሬና የወረርሽኝ መከላከል አቅምን ማሳደግ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ በጤና ዘርፍ የራሷን አቅም በማጠናከር፣ በሳይንሳዊ ምርምር፣ በቴክኖሎጂና በአህጉራዊ ትብብር የጤና ችግሮቿን በራሷ ለመፍታት የሚያስችላትን አቅም ማዳበር እንደሚጠበቅ አመልክተዋል። በጉባኤው የሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ሙያተኞች፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች በአፍሪካ ጤና አጀንዳዎች ላይ የጋራ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሚያግዝ ገልጸዋል። የአፍሪካ ሲዲሲ በአህጉሪቱ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን በመከላከልና በመቆጣጠር እንዲሁም የአፍሪካን የጤና አጀንዳ በዓለም አቀፍ መድረኮች በጋራ በማቅረብ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።   ጉባኤው የጤና ዘርፍ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ፣ የጤና መሠረተ ልማትን ለማጠናከር፣ የድንገተኛ ጤና አደጋ ምላሽ አቅምን ለማሳደግና ሳይንሳዊ ምርምርና ዲጂታል ጤናን ለማስፋፋት እንደሚያግዝ ገልጸዋል። በአፍሪካ የመድኃኒትና የሕክምና ቴክኖሎጂ ምርት፣ የጤና ኢንቨስትመንትንና በአህጉሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን ክህሎት ማሳደግ በጉባኤው የሚመከርባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቁመዋል። በጉባኤውም እስከ አሁን ድረስ ከ29 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ለመታደም መመዝገባቸውንና ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎች እንደሚጠበቁ ገልጸዋል። ከእነዚህም 18 ሺህ በላይ የሚሆኑት ተሳታፊዎች የእውቅና ሰርተፊኬት አግኝተው የመግቢያ ሂደታቸውን ማጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል። በቀጣይም ለአገር ውስጥ ተሳታፊዎች ተጨማሪ የምዝገባ እድሎች እንደሚከፈቱ አስታውቀዋል። የጉባኤው ዝግጅት ከጤና ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ከትራንስፖርት፣ ከሎጂስቲክስ፣ ከደኅንነት፣ ከቱሪዝምና ከሌሎች ዘርፎች ጋር በተቀናጀ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል። የጉባኤው ዝግጅት እስከ መጨረሻው የማስተናገድ ሂደት መድረሱን ገልፀዉ፤ የቪዛ፣ የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ዝግጅቶችም እየተጠናቀቁ መሆኑን አስረድተዋል።  
መንግሥት የመገናኛ ብዙሃን ምህዳሩን ምቹ የሚያደርጉ ውጤታማ ተግባራት አከናውኗል       
Nov 2, 2026 234
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦መንግሥት የመገናኛ ብዙሃን ምህዳሩን ምቹ የሚያደርጉ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ ገለጹ። አልጀዚራ ሚዲያ ኔትወርክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት አክብሯል። በበዓሉ አከባበር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣አምባሳደሮች፣የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት መንግሥት የመገናኛ ብዙሃን ምህዳሩን ምቹ የሚያደርጉ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል። የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ተደራሽ ከማድረግ ጀምሮ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ አሰራሮችና የፖሊሲ እርምጃዎችን መውሰዱንም አንስተዋል። ይህ የለውጥ እርምጃ የውጭ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አመልክተው፤ አልጀዚራ ሚዲያ ኔትወርክም የዚህ ለውጥ ፍሬ ተቋዳሽ ነው ብለዋል። አልጀዚራ በተለያዩ መስኮች በኢትዮጵያ ሽፋን በመስጠት የሚያበረታታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው፤ በተለይ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግንዛቤው እንዲሰፋ የሰራው ስራ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው ብለዋል። የአልጀዚራ ሚዲያ ለኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች አቅም ግንባታ ስልጠናዎች በመስጠት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የሙያ ደረጃ እንዲያድግ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል። እንደ ዋና ዳይሬክተሯ ገለጻ፤ አልጀዚራ ሚዲያ በኢትዮጵያ ያሉ ታሪካዊ መስህብ ቦታዎች፣ የተፈጥሮ ሀብት እና የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስተዋወቅ ላይ የጀመረውን ስራ ሊያጠናክር ይገባል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን በኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙሃን ጋር ገንቢ የሆነ ትብብሩን እንደሚያጠናክርም አረጋግጠዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሳልማ ሀዳዲ በበኩላቸው፤ አፍሪካ ብዝሃነት፣ ትልቅ ዕድልና ማህበራዊ ተልዕኮ ያላት አህጉር መሆኗን አስታውሰዋል። ለዚህም የአፍሪካ ተቋማት ስኬቶች፣ እርምጃዎችና ህዝቦቿ ሙሉ ትኩረት ይፈልጋሉ ነው ያሉት። አፍሪካ የምትጠይቀው ወገንተኛ ዘገባ እንዲሰራላት አይደለም ያሉት አምባሳደር ሳልማ፤ ለአፍሪካውያን ድምፅ፤ ስለ አህጉሪቱ አጠቃላይ መጻኢ እድል በሚደረጉ ውይይቶች ውስጥ ተገቢውን ቦታ የሚሰጥ ትክክለኛ፣ ፍትሃዊ እና ሁኔታዎችን ያገናዘበ ዘገባ እንዲቀርብ ነው ሲሉም ተናግረዋል። የአልጀዚራ ሚዲያ ኔትወርክ የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ መሀመድ ተወከል በበኩላቸው፤ ሚዲያው በኢትዮጵያ ከምስረታው ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት ላደረጉት ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል። ሚዲያው ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆን የሚለውን መርህ በመከተል በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸው አሁን ላይ ሚዲያው የሚያሰራጭበትን ቻናል ወደ ሦስት ከፍ ማድረጉን አብራርተዋል። አልጀዚራ ሚዲያ ኔትወርክ አብረው ለሰሩ የመንግሥት ተቋማት፣ አህጉራዊ ድርጅቶችን ጨምሮ ለተለያዩ አካላት እውቅና ሰጥቷል።  
በመዲናዋ የሚከናወኑ ልማቶች ሰው ተኮር እና የማኅበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ናቸው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Nov 1, 2026 322
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናወኑ ልማቶች ሰው ተኮር እና የነዋሪዎችን ማኅበራዊ ትስስር በማጠናከር ወደ ተሻለ የአኗኗር ዘይቤ የሚያሸጋግሩ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የተገነባውን የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የመኖሪያ መንደር መርቀው ለተጠቃሚዎች አስተላልፈዋል።   ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት አዲስ አበባን በጋራ፣ በትብብር እና በውጤታማነት እያለማን እንገኛለን ብለዋል። ይህም አዲስ አበባን በዓለም አቀፍ መድረክ እንድትሸለም እያስቻላት መሆኑን ተናግረዋል። እውቅናው የሁሉም ትብብር ውጤት መሆኑን አንስተው፣ የልማት ተነሺዎች ለልማት ተባባሪ መሆናቸው ለዚህ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል። አዲስ አበባን የማልማቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ከንቲባዋ፣ ዛሬም ለልማት ለተነሱ አርሶ አደሮች ዘመናዊ የሆነ የመኖሪያ ቤት ተገንብቶ መሰጠቱን ተናግረዋል። ልማት ማለት የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ አቅሙን ማጠናከርና የነገ ተስፋውን ማለምለም ጭምር ነው ሲሉ ተናግረዋል።   መኖሪያ መንደሩ የነዋሪዎቹን ማኅበራዊ ትስስር በማጠናከር ወደ ተሻለ የአኗኗር ዘይቤ የሚያሸጋግርና ሰው ተኮር የአሠራር አቀራረብን የተከተለ ነው ብለዋል፡፡ ለአርሶ አደሮቹ የኑሮና የገቢ ምንጮቻቸውን የሚያሳድጉበትን ዕድል የሚፈጥሩ በርካታ አቅርቦቶችን ያካተተ መሆኑንም አብራርተዋል። የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራ በበኩላቸው፣ የተገነባው ቤት ነዋሪዎቹ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ለማስቻል ታስቦ በዘመናዊ መንገድ መገንባቱን አስታውቀዋል። የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በአንድ ላይ የሚያስተሳስሩ ዘርፈ ብዙ መሠረተ ልማቶች የያዘ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።   በመኖሪያ መንደሩ የቤት ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ወ/ሮ ዘውድነሽ መስቀላ፣ የተሰጣቸው ቤት ከቀደመው የተሻለ፣ ዘመናዊ እና ውብ በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ኑሯቸውን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችሉ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶች በተሟሉበት መንደር በመግባታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው የቤት ተጠቃሚ አብራሳ ዱመቻ ናቸው፡፡ በዚህም ለከተማ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርበዋል።        
ኢኮኖሚ
በትግራይ ክልል ለሠራተኞች ዛሬ ደመወዝ መከፈል ይጀመራል
Nov 3, 2026 21
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፦ በትግራይ ክልል ከቀን ወደ ቀን ሰላምና መረጋጋት ሙሉ በሙሉ እየተረጋገጠ መምጣቱና ዜጎች ያለ ምንም ሥጋት የቀደመ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወታቸውን በነፃነት መምራት የቻሉበት ብሩህ ድባብ መፈጠሩ ተገለጸ። የባለአደራ አስተዳደሩ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች በመድረስ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ተቋማትም በሙሉ አቅማቸው ወደ ሙሉ አገልግሎት እንዲገቡ የማድረግ ሥራውን በስኬት በማከናወን ላይ ይገኛል። የባለአደራ አመራር አደራጅ ቡድን አስተባባሪው ብርሃነ ገብረፃዲቅ እንደገለጹት፤ ኅብረተሰቡ አሁን ያገኘውን ሰላምና ነፃነት ለማስጠበቅና ላለማጣት ከለውጡ አመራርና ከመንግሥት ጋር በከፍተኛ ቁርጠኝነትና ንቃት እየሰራ ይገኛል። የሕዝቡን ቀጥተኛና ነፃ ምርጫ መሠረት በማድረግ እየተከናወነ ባለው የባለአደራ አመራሩን እስከ ታችኛው መዋቅር የማደራጀት ሂደትም በሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ ምክንያት አሁን ላይ 60 በመቶ መጠናቀቁን አስተባባሪው አረጋግጠዋል።   የባለአደራ አስተዳደሩ መዋቅር እየተሟላ በሄደ ቁጥር የአገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ማስገባት የተቻለ ሲሆን ባንኮች፣ የንግድ ተቋማትና የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አሁን ላይ በሙሉ አቅማቸው ተነቃቅተው ወደ አገልግሎት ገብተዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በባለአደራ አስተዳደሩ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪው ቴዎድሮስ አረጋይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ለመንግሥት ሠራተኛው የደመወዝ ክፍያ እንዲጀምር በተደረገው ጥረት መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ደመወዝ መክፈል ይጀመራል ብለዋል።   የባለአደራ አስተዳደሩ የትግራይ ክልል ሕዝብ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ያሳየውን ሁለንተናዊ ድጋፍና ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽግግር-የኮፕ32 ተግባራዊ ማሳያ 
Nov 3, 2026 63
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽግግር-የኮፕ32 ተግባራዊ ማሳያ የብሉምበርግ ጥንክር እንደዘገበው ዓለም ስለ አየር ንብረት ለውጥ እየተጨነቀና እየመከረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ኢትዮጵያ በተግባር ያሳየችው ድንቅ ውሳኔ የመላው ዓለምን ትኩረት ስቧል።የነዳጅ መኪኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት በይፋ በመከልከልና ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ሽግግር በፍጥነት በመግባት ዓለምን ያስደመመችው ኢትዮጵያ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አበረታች ውጤት ማስመዝገቧን የብሉምበርግ ጥንክር አትቷል። በኢትዮጵያ ከሚመነጨው ኃይል 99 በመቶ የሚሆነው ንጹህና አረንጓዴ መሆኑን ያተተው ዘገባው፣ ይህም ለኤሌክትሪክ መኪኖች በርካሽ ኃይል ማቅረብ እንዳስቻላት ገልጿል።   ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ደግሞ በዚህ ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱን አመላክቷል። ይህ ታላቅ ሽግግር ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንም ወጪያቸውን እንዲቆጥቡ አድርጓል ነው ያለው የብሉምበርግ ዘገባ። የኤሌክትሪክ መኪና የሚጠቀሙ ታክሲ ነጂዎችና የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ቀደም ሲል ለነዳጅና ለጥገና ያወጡት የነበረውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት በወር እስከ 150 ዶላር (ከ40,000 እስከ 50,000 ብር) መቆጠብ ችለዋል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ እንደ ቢኬጂ ግሩፕ ያሉ የመገጣጠሚያ ፋብሪካዎች በሀገር ውስጥ ሥራ በመጀመራቸው፣ በርካታ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎችን በማሰልጠን አዲስ የሥራ እድል መፍጠር ተችሏል።   በኢትዮጵያ በሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ድርሻ 6 በመቶ መድረሱን፣ ይህም ከዓለም አቀፉ አማካይ (4 በመቶ) በላይ በመሆን ኢትዮጵያን በዘርፉ ግንባር ቀደም አድርጓታል። ኢትዮጵያ በፈረንጆች 2027 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባኤን (COP32) ስታስተናግድ፣ "ታዳጊ ሀገራት በገንዘብ እጥረት ወይም በነዳጅ ቀውስ ሳይገደቡ እንዴት በፍጥነት ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መሸጋገር ይችላሉ?" ለሚለው ትልቅ ጥያቄ ህያውና በተግባር የተረጋገጠ ማሳያ እንደምትሆንም ነው ብሉምበርግ በዘገባው ያመላከተው። ኢትዮጵያ እስከ ፈረንጆቹ 2033 አምስት መቶ ሺህ (500,000) የኤሌክትሪክ መኪኖችን በመንገድ ላይ ለማሰማራት የያዘችው ታላቅ እቅድም፣ የዚሁ አረንጓዴ እና ዘላቂ ራዕይ አካል መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።
የካፒታል ገበያ፡ የነገዋ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት መሰረት
Nov 2, 2026 83
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የነገዋን ሀገር የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚቀይር እና ለአዲስ ዕድገት መሠረት የሚጥል መዋቅራዊ ሽግግር እያደረገ ይገኛል። የካፒታል ገበያ ሥርዓት በአዲስ መልክ መመለሱ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊና ግልጽ የፋይናንስ አማራጭ የሚያሸጋግር ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ የሀገር ውስጥ ቁጠባን ወደ ምርታማ ኢንቨስትመንት ለመቀየር፣ የንግድ ድርጅቶችን አቅም ለማሳደግ እና የሀገሪቱን የብድርና የዕዳ ጫና በዘላቂነት ለማቃለል ታስቦ የተዘረጋ የነገ መደላደል ነው። ዘመናዊ የካፒታል ገበያ በሕጋዊ መንገድ የተጀመረው የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲጸድቅ ነው። አዋጁን ተከትሎ ገበያውን በበላይነት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) የተቋቋመ ሲሆን፣ ግብይቱን የሚያከናውነው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ (ESX) ደግሞ በመንግሥትና በግል አጋርነት (PPP) ተመሠረተ። ይህ የዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያን (ESX) በሳይንስ ሙዚየም በይፋ መርቀው ያስጀመሩ ሲሆን፣ መደበኛ የቀጥታ የንግድ ግብይት (Live Trading) ደግሞ በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም. ላይ በይፋ ተጀምሯል። የካፒታል ገበያው የነገን ብሩህ ተስፋ በሚያሳይ መልኩ ከጅምሩ በርካታ ግዙፍ ተቋማትን ማሳተፍ ችሏል። የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ በዲጂታል መንገድና በቴሌብር ጭምር በመታገዝ ከ47 ሺህ በላይ አዳዲስ ዜጎችን በማሳተፍ የመጀመሪያው በይፋ የተመዘገበ ኩባንያ በመሆን ታሪክ ሠርቷል። ይህንን ተከትሎ በርካታ የግል የፋይናንስ ተቋማትና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አክሲዮኖቻቸውን በገበያው ላይ በይፋ ማስመዝገብ የጀመሩ ሲሆን፣ ይህም ለገበያው መነቃቃት ትልቅ መሠረት ጥሏል። በተጨማሪም የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለተለያዩ የኢንቨስትመንት ባንኮች፣ አገበያዮችና ደላላ ኩባንያዎች የሥራ ፈቃድ የሰጠ ሲሆን፣ በባንኮች የእርስ በርስ የአጭር ጊዜ የገንዘብ መበዳደሪያ ገበያ ላይ የተመዘገበው አጠቃላይ የግብይት መጠን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ማለፉ የነገውን የገበያ አቅምና አስተማማኝነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል። የዚህ ግዙፍ የፋይናንስ መድረክ ዋና ዓላማና ለነገዋ ኢትዮጵያ ያለው ፋይዳ ሀገሪቱን በባንክ ብድር ላይ ብቻ ከምትመሰረተው የፋይናንስ ጥገኝነት ማላቀቅና አማራጭ የረጅም ጊዜ የካፒታል ምንጭ መፍጠር ነው። ኩባንያዎችና መንግሥት አክሲዮንና ቦንድ በመሸጥ ለትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን ገንዘብ በቀጥታ ከሕዝብ መሰብሰብ እንዲችሉ ያደርጋል። ይህ አሠራር የመደመር መንግሥት ገንዘብ በማተም ወይም ከብሔራዊ ባንክ በመበደር የሚፈጥረውን የዋጋ ግሽበት በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን፣ ማኅበረሰቡም ገንዘቡን በባንክ ቁጠባ ብቻ ከማስቀመጥ ባለፈ በትላልቅ ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት አድርጎ የትርፍ ተካፋይ እንዲሆንና በነገዋ ኢትዮጵያ የሀብት ፍትሐዊ ክፍፍል እንዲሰፍን ያደርጋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገበያውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ ይህ ገበያ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የፋይናንስ ነፃነት የሚያረጋግጥ መሣሪያ ነው። የካፒታል ገበያው ማንኛውም ዜጋ በቀላሉ የትላልቅ ባንኮችና ተቋማት ባለቤት የሚሆንበት የነገ መድረክ ነው። የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ማዛወር ዓላማው ተቋማቱ ዓለም አቀፍ አሠራርን፣ ግልጽነትንና ዘመናዊ ተጠያቂነትን እንዲላበሱ ለማድረግ ሲሆን፣ የግል ዘርፉ የነገዋ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሞተር እንዲሆን መንግሥት ሙሉ ዋስትናና ከለላ ይሰጣል። የካፒታል ገበያው ውጤታማነት በዋናነት የተመሠረተው ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያና የመረጃ ሥርዓቶችን በመተግበር ላይ ሲሆን፣ የኢትዮ ቴሌኮም የመጀመሪያ ዙር አክሲዮን በቴሌብር መጠናቀቁ ለነገው ዲጂታል መሠረተ ልማት ትልቅ ማሳያ ነው። ገበያው ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ የማኅበረሰቡን የፋይናንስ ግንዛቤ ማሳደግ፣ የኩባንያዎችን የሒሳብ አያያዝ ግልጽነት ማረጋገጥ እና ያልተገባ የገበያ ማጭበርበርን መቆጣጠር የመሳሰሉ የቤት ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል። ወደፊት ገበያውን ይበልጥ ለማስፋፋት የተቀመጡት ቀጣይ ስትራቴጂካዊ ትከረቶች ገበያውን ቀጣናዊና ዲጂታል ማድረግ ላይ ያተኮሩ ናቸው።
አዲስ አበባ፤ በዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት መድረኮች ተከታታይ እውቅና እያገኘች ያለች ከተማ
Nov 2, 2026 269
ከተማን መለወጥ የሚቻለው በግልጽ ራዕይ፣ በተቀናጀ ጥረትና የሰው ልጅን ሕይወት ማዕከል ባደረገ የልማት አቅጣጫ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ አዲስ አበባም ይህንን እሳቤ በተግባር እየተረጎመች መሆኗን በዓለም አቀፍ መድረክ ዳግም አስመስክራለች ብለዋል። በቅርቡ በቻይና ሻንሃይ ከተማ በተካሄደው የ2026 የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማት ውድድር፣ አዲስ አበባን ጨምሮ አምስት ከተሞች ተሸላሚ ሆነዋል ነው ያሉት። በዘንድሮው የሻንሃይ ሽልማት እውቅና ያገኙት፦ 1. አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) 2. ሳንቲያጎ ዴ ካሊ (ኮሎምቢያ) 3. ኢስታንቡል (ቱርኪዬ) 4. ጂንግዴዠን (ቻይና) 5. ካቶቪስ (ፖላንድ) መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ ሽልማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአራተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዲስ አበባ በአራቱ ዙሮች ሁለት ጊዜ እውቅና አግኝታለች በማለት አስታውሰዋል። በ2024 የሴኡል ስማርት ሲቲ ሽልማትን፣ በ2026 ደግሞ የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማትን አግኝታለች ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ በ2023 አዲስ አበባ በምገባ ፕሮግራምና በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዘርፎች ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች ያለች ከተማ በመሆኗ ዓለም አቀፍ እውቅናና ሽልማት ማግኘቷን ጠቁመዋል። ይህ እውቅና ለሀገራችን ታላቅ ክብር ከመሆኑም በላይ፣ እየሠራን ላለነው ሥራ ብርታትና ተጨማሪ ተነሳሽነት የሚሰጥ ነው ሲሉም አክለዋል። ከሁሉም በላይ፣ በከተማችን የምንተገብራቸው ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃና የአኗኗር ሁኔታ ለማሻሻል የምናደርገው ጥረት፣ እንዲሁም የከተማዋን የተፈጥሮና ማኅበራዊ ፀጋዎች ወደ ልማትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የመቀየር ሥራችን ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የሚያረጋግጥ ዓለም አቀፍ ምስክርነት ነው። የመደመር እሳቤያችንም ልማትን ከሰው ሕይወትና ደኅንነት ጋር አጣምሮ ያያል። ከተሞች የሥልጣኔ መገለጫ እንዲሆኑ፣ ያላቸውን ፀጋዎች በመለየትና በማልማት፣ የሰውን አቅም ከተፈጥሮና ከኢኮኖሚያዊ ሀብቶች ጋር በማቀናጀት ለጋራ ብልፅግና መሥራትን ይጠይቃል። በከተማችን የልማት ጉዞ እስካሁን የተጓዝነው ርቀት ጠንካራ መሠረት የጣለ ቢሆንም፣ የሚቀረን ረጅም ጉዞ እንዳለ እናውቃለን። ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዘመናት ከተጫኗት ድህነትና ልዩ ልዩ ችግሮች በዘላቂነት ለመላቀቅ፣ ቀጣይነት ያለው ለውጥ ለማምጣትና ወደ ብልፅግና ለመሸጋገር የጀመረችው ጉዞ ፍሬ እያፈራ ይገኛል። ሆኖም ይህንን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ወደ ተሟላና ዘላቂ ለውጥ ለመቀየር የሁሉንም ዜጎች ርብርብ፣ ቁርጠኝነትና ተሳትፎ ያስፈልጋል። ስለሆነም ሁላችንም ለለውጡ በቁርጠኝነት መትጋት ይገባናል ብለዋል። ያገኘነውን ዓለም አቀፍ እውቅናም እንደ መዳረሻ ሳይሆን፣ እንደ ተጨማሪ ኃላፊነትና ለበለጠ ሥራ ማበረታቻ እንወስደዋለን ሲሉም አክለዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ አያይዘውም፣ ይህንን ተነሳሽነት በመያዝ፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች የሥልጣኔና የብልፅግና መሠረት እንዲሆኑ እንሠራለን ብለዋል። አቅሞቻችንን በመደመር፣ ፀጋዎቻችንን ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር፣ ክብራችንን የሚመጥን የብልፅግና ግብ ለመድረስ ትጋታችንን እናጠናክራለን በማለትም ገልጸዋል። ከተሞቻችን የመደመር ሥልጣኔ መዳረሻ፣ ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ተስማሚ የኑሮ አካባቢ፣ ለቀጣዩ ትውልድም ዘላቂ የብልፅግና ውርስ እንዲሆኑ በጋራ እንሠራለን ሲሉም አረጋግጠዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በፍጥነት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው- የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር)
Nov 2, 2026 252
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር )በሌሎች አካባቢዎች የታየው ፈጣንና ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ በመቐለ ከተማም በፍጥነት እንዲጀምር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። በመቐለ ከተማ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በፍጥነት ለማስጀመርና የህዝብን የእለት ተእለት ፍላጎት በዘመናዊ መልኩ ለማሟላት የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል።   የፌደራል የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አመራሮች እና ሞያተኞች በመቐለ ከተማ በመገኘት አገልግሎቱን እውን ለማድረግ ከከተማዋ ባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር የተመካከሩ ሲሆን ይህም በትግራይ ክልል የተጀመረውን የሰላም ተስፋና ሀገራዊ የልማት ትስስር በተግባር ያረጋገጠ ምዕራፍ ሆኗል። በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የፌደራል የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዮናስ አለማየሁ እንደገለጹት አሁን ላይ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስተዋል።   በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 114 አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር መስጠት የተቻለበት ደረጃ ላይ በመደረሱ የዜጎች እርካታ 99 በመቶ መድረሱንም ጠቅሰዋል። በሁሉም ክልሎች ይህ አሰራር በስፋት እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን በነበረው ነባራዊ ሁኔታ በትግራይ ክልል እስካሁን ሳይጀምር ቢቆይም አሁን ላይ የባለአደራ አስተዳደሩ አገልግሎቱን ለማስጀመር ያሳየውን ቁርጠኝነትና ዋና ስራ አስፈፃሚው አድንቀዋል። የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) በሌሎች አካባቢዎች የታየው ፈጣንና ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ በመቐለ ከተማም በፍጥነት እንዲጀምር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። በሌሎች ሀገራዊ አካባቢዎች በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የታየው የፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ተሞክሮ በትግራይ ክልልም በፍጥነት ሊተገበር እንደሚገባ ያነሱት ከንቲባው የፌደራል የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች፣ ስልጠና በመስጠትና የዕውቀት ሽግግር በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በተጨማሪም በሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ለሚገነቡ ማዕከላት በመቐለ ከተማ የሚሰራው አሰራር መነሻ ስለሚሆን በፍጥነት፣ በጥራትና በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀመሩ
Nov 1, 2026 345
ደብረ ብርሃን፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባውን ዘመናዊ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በይፋ መርቀው ስራ አስጀምረዋል። በማስጀመሪያ መርሃግብሩ የክልሉ፣ የዞንና የከተማው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።   ማዕከሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ለህብረተሰቡ የሚያቀርባቸውን የተለያዩ አገልግሎቶች በአንድ ማእከል በማሰባሰብ፤ የህዝብን እንግልትና ውጣ ውረድ በዘላቂነት የሚያስቀር፣ ፈጣን፣ ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። በክልሉ ሕዝብን ከእንግልት ታድገው ዘመናዊ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ መስተንግዶ ለመስጠት የሚያስችሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተገንብተው ለሥራ እየበቁ ይገኛሉ።   ማዕከላቱ የተለያዩ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን በአንድ ጥላ ሥር በማሰባሰብ የዜጎችን ጊዜና ጉልበት የሚቆጥቡና የአስተዳደር በደልን የሚያስቀር አዲስ ምዕራፍ እየከፈቱ መሆናቸው ታውቋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ከሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤሪክ ዩዋን ጋር ተወያዩ
Oct 31, 2026 227
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ የሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን በቅርቡ ሥራ ከጀመሩት ኤሪክ ዩዋን ጋር ተወያይተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በውይይታችን ወቅት መንግሥት የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ለማስቀጠልና ለማፋጠን እየሠራቸው ያሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራዎች እጅግ አበረታች መሆናቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸውልኛል ብለዋል።   ሁዋዌ የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይና ብሔራዊ የልማት ግቦቻችንን ለማሳካት በምናደርገው ጥረት ውስጥ፣ በተለይም በአይሲቲ መሠረተ ልማትና በግንኙነት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጉዞም ከሁዋዌ ጋር በትብብር፣ በብሔራዊ ባለቤትነት፣ በዘላቂነት፣ በደኅንነትና በአካባቢያዊ እሴት ፈጠራ መርሆዎች ላይ ተመሥርተን በምንሠራባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ መክረናልም ብለዋል። የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችን በእመርታ እየተጓዘ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሁዋዌም ለዚህ ዕድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ እና ያለንን የሥራ ግንኙነት አጠናክረን ለመቀጠል ተስማምተናል ሲሉም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ችሎት በተሞክሮነት የሚወሰድ ተምሳሌታዊ አሰራር ነው
Oct 29, 2026 702
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ችሎት በተሞክሮነት የሚወሰድ ተምሳሌታዊ አሰራር መሆኑን የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ልዑካን ቡድን አባላት ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብና ታላቅ ርዕይ ከትናንት ጥቅምት 18 ጀምሮ በአዲስ አበባ መካሄድ የጀመረው የኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤቶች የልምድ ልውውጥ መድረክ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ልዑካን ቡድን አባላትም የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት፣ የኢትዮጵያ ስቶክ ገበያ እና የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ጎብኝተዋል።   የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ሊቀመንበር ኔሚ ኪለካጄንጋ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የታገዘ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በተቋማቱ ጉብኝት ያገኙትን ልምድና ተሞክሮም በታንዛኒያ በመተግበር ዘመናዊና ስሉጥ አሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል። በተለይም የሰው ሠራሽ አስተውሎት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልህቀት የፋይናንስ ዘርፍ የአቤቱታ ጉዳዮችን አፋጣኝና ግልጽ ምላሽ ለመስጠት እንደሚረዳ አስረድተዋል።   የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት፣ የኢትዮጵያ ስቶክ ገበያ እና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አሠራርም ልምድና ተሞክሮ የቀሰሙበት መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አጠቃላይ የዲጂታል ሽግግርም አፍሪካውያንን ዘመናዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ለማሳለጥ በአርዓያነት የሚወሰድ አሠራር መሆኑን አብራርተዋል። በቀጣይም የአፍሪካን የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር በማሳለጥ መልኩ በታንዛኒያ ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠራ አንስተዋል።   የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት የሕግ ባለሙያ ኤልያድ ኢ-መንደም በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የቴክኖሎጂ ችሎት ተምሳሌታዊ ነው ብለዋል። ይህም ለፋይናንስ አለመግባባት ችሎቶች አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥና ታንዛኒያም በተሞክሮነት የምትቀስመው አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
ስፖርት
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ድል ተቀዳጁ
Nov 2, 2026 142
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ አገራት በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል። በቻይና ሃንግዡ ማራቶን የሴቶች ውድድር ኩፍቱ ጣሂር አንደኛ በመውጣት ድል ተቀዳጅታለች። በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ማራቶን ሚኪያስ ባረጋ አንደኛ በመውጣት ሲያሸንፍ፣ አበባው ሙንየ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በኢስታንቡል ማራቶን በሴቶች ውድድር ካሳነሸ አየነው አንደኛ ወጥታለች። አዝመራ አብርሃ ሁለተኛ እና ድርቤ ሂርቆ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በሌላ በኩል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአምስት ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች ፈይሳ ቡሎ አሸናፊ ሲሆን፣ ገብሩ አብርሃ እና ጫላ ጉደታ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በሴቶች ሃና መኮንን ስታሸንፍ፣ ማርታ ቦሬማ እና ሴና ተሰማ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል። በአቡዳቢ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች ሰውመሆን አንተነህ አንደኛ ሲወጣ፣ አባይነህ አየል ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል። በሴቶች አልማዝ ባራኪ ሁለተኛ፣ መገርቱ ሚዴቅሳ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በስፔን በተካሄደው የሴባስቲያን ሀገር አቋራጭ ውድድር ወገኔ አዲሱ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ መጨረሱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስትል ዩናይትድ ከኤቨርተን ጋር ይጫወታል
Nov 2, 2026 172
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በኒውካስትል ዩናይትድ እና በኤቨርተን መካከል ዛሬ ይደረጋል። ጨዋታው ምሽት አምስት ላይ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ይካሄዳል። ባለሜዳው ኒውካስትል ዩናይትድ በ11 ነጥብ 12ተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ኤቨርተን በ10 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ59ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 58 ጨዋታዎች ኤቨርተን 24 ጊዜ ድል ሲቀናው ኒውካስትል ዩናይትድ በ21ዱ አሸንፏል። በቀሪ 13 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ኤቨርተን በ58ቱ ጨዋታዎች ላይ 86 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ኒውካስትል በበኩሉ 82 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ኒውካስትል ዩናይትድ በስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ኤቨርተን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይፋለማል። ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት በካራባኦ ካፕ ባደረጉት ጨዋታ ኤቨርተን ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፉ የሚታወስ ነው። የ36 ዓመቱ ጆን ብሩክስ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት እንዲመሩ ተመድበዋል።
አካባቢ ጥበቃ
ታዳሽ ኃይል-የኢትዮጵያ መለያ!
Nov 2, 2026 228
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የታደለች፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራች የምትገኝ ምድረ ቀደምት ሀገር ናት። በተለይም በታዳሽ የኃይል አቅርቦት ዘርፍ እያከናወነች ያለው አበረታች ተግባር ሀገሪቱን በቀጣናው ብሎም በአህጉር ደረጃ ሞዴል አድርጓታል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከውሃ፣ ከንፋስ፣ ከፀሐይ እና ከጂኦተርማል ሀብቶች አጠቃላይ ከ 60,000 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል የማመንጨት ግዙፍ አቅም ያላት ሲሆን፤ አሁን ላይም የኃይል ማመንጨት አቅሟን ከ 9 ሺህ 760 ሜጋ ዋት በላይ አድርሳለች። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ዓመታት ኃይል የማምረት አቅሟን ከ15 ነጥብ 3 ቴራ ዋት ሰዓት ወደ 29 ነጥብ 5 ቴራ ዋት ሰዓት አሳድጋለች።በተለይም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በሀገሪቱ የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ለአካባቢ ጥበቃና ለታዳሽ ኃይል ልማት ያላትን እውነተኛ ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ህያው ምስክሮች ናቸው። ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማቷን ለራሷ ብቸኛ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ለጎረቤት ሀገራትና ለመላው ምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የጋራ እድገት እያዋለች ትገኛለች። የኤሌክትሪክ ኃይል መስመሮችን ወደ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ እና ኬንያ በመዘርጋት በቀጣናው የኃይል ትስስር እንዲፈጠር እና የኢኮኖሚ ውህደት እንዲጠናከር ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ይገኛል። ይህ የኃይል ትስስር የጎረቤት ሀገራትን የኃይል ፍላጎት ከመሙላቱ ባለፈ፣ አካባቢያዊ ሰላም፣ ወንድማማችነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ትብብር እንዲጎለብት ያደረገ ወሳኝ እርምጃ ነው። ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ ያመጣችው ተጠቃሚነትና ያስመዘገበችው ስኬት በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እያገኘ መጥቷል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32 ጉባኤን ለማስተናገድ በመዘጋጀት ላይ ባለችበት በዚህን ወቅት የታዳሽ ኃይል ልማት የኢትዮጵያ መለያ ከሆኑ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ያላትን መሪነት የሚያረጋግጥ ነው። በአጠቃላይ፣ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት እያከናወነች ያለችው አበረታች ስራ የራሷን የኃይል ሉአላዊነት ከማረጋገጡ በላይ፣ የቀጣናውን ሀገራት በጋራ ተጠቃሚነት ማዕቀፍ ያስተሳሰረና የዓለምን ትኩረት የሳበ ስኬት ነው። ታዳሽ ኃይል በእርግጥም የኢትዮጵያ አዲስ መለያና ኩራት ሆኖ ቀጥሏል።
በኢትዮጵያና ጅቡቲ ኮሪደር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ኔትወርክ ለመዘርጋት የጋራ ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈጸመ
Oct 31, 2026 399
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦በኢትዮጵያና በጅቡቲ ኮሪደር ላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ኔትወርክ ለመዘርጋት ከሶስት የውጭ ኩባንያዎች ጋር የጋራ ኢንቨስትመንት ስምምነት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ-ጅቡቲ የትራንስፖርት መስመር ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ መሙያ አውታር ለመዘርጋት ከቻይና ሮድ ኤንድ ብሪጅ ኮርፖሬሽን፣ ከቤጂንግ ፎርኤቨር ቴክኖሎጂ ሊሚትድ እና ከሁዋዌ ቴክኖሎጂስ ጋር ስምምነት ተደረጓል። ይህ የትብብር ስምምነት ቀደም ሲል የኃይል ፍላጎትን በማጥናት፣ ጣቢያዎቹ የሚገነቡባቸውን አካባቢዎች በመለየት እንዲሁም የቴክኒክ ሞዴሎችን እና የጊዜ ሰሌዳዎችን በማውጣት ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛል። ስምምነቱ በኮሪደሩ ላይ የተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያዎችን በማቀናጀት ተደራሽነታቸውን ለማስፋት ያለመ እንደሆነም ተናግረዋል። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር፣ የባለሙያዎች አቅም እንዲያድግ እና የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። በዚህም አረንጓዴ የትራንስፖርት ሥርዓትን በማስተዋወቅ የነዳጅ ጥገኝነትንና ለነዳጅ ግዢ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ለመቀነስ፣ የአየር ንብረት ብክለትን ለመከላከል እና የታዳሽ ኃይል አጠቃቀምን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያና ሩሲያ በረጅም ዘመናት ውስጥ በተገነባ ትብብር የተሳሰሩ ናቸው - ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
Oct 29, 2026 934
ሞስኮ፤ ጥቅምት 19/2019(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ሩሲያ በረጅም ዘመናት ውስጥ በተገነባ ተምሳሌታዊ ትብብር የተሳሰሩ ሀገራት መሆናቸውን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ3ኛው የአፍሪካ - ሩሲያ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሞስኮ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋርም በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተወያይተዋል።   ኢዜአ ከስፍራው እንደዘገበው በውይይቱ ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ከኢኮኖሚያዊ ትስስር ባሻገር በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ታሪካዊ ቅርበት አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህ የጋራ የሞራል እሴት በብዙ ደረጃ ሕዝቦችን የሚያቀራርብ አስፈላጊ መሠረት መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ አስረድተው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በብዙ የልማት መስኮች በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ የገለጹት ፑቲን፣ በተመድ፣ በብሪክስ እና በሌሎችም ባለብዙ ወገን መድረኮች ውይይቶች መደረጋቸውን አንስተዋል። አፍሪካ በከፍተኛ የእድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ የገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ትብብር የአህጉሪቱን ተስፋ ሰጪ እድገት በጋራ ለማስቀጠል ማሳያ ነው ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት ሁለንተናዊ ብልፅግና ሊሳካ የሚችለውም ወቅቱ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ በመታጠቅ ጭምር መሆኑን ገልጸው፣ በተለይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰው ልጅ የወደፊት እድገት ዋና መሠረት ከሚሆኑ ተስፋ ሰጪ ዘርፎች አንዱ ነው ብለውታል።   እንደሳቸው ገለጻ ዘርፉ እንዲያድግ የሂሳብና የሳይንስ ትምህርት ቤቶች፣ ማዕከላት ፣የሰው ኃይል እና የኃይል አቅርቦት መሠረተ ልማቶች ወሳኝ ናቸው። ሩሲያ በእነዚህ መስኮች ያላትን ዕምቅ አቅም ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማጋራት ዝግጁ መሆኗንም አክለዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ከቀድሞ ሶቪየት ሕብረት ጀምሮ የአፍሪካ ሀገራትን የነፃነት ትግል በመደገፍ የተገነባ ታሪካዊ የትብብር መሠረት እንዳላት ጠቅሰዋል። አሁን ግን የሩሲያ እና የአፍሪካ ትብብር ወደፊት በማተኮር ኢኮኖሚያዊ እድገትን ሊያፋጥን ወደሚችል ምዕራፍ መሸጋገር እንዳለበትም አመልክተዋል። የ3ኛውን የሩሲያ - አፍሪካ ጉባዔ ውይይቶችን ተከትሎ ማጠቃለያ መግለጫዎች የሚጠበቁ ሲሆን ከ2027 እስከ 2029 የሚዘልቀው አዲስ የሩሲያ እና የአፍሪካ አጋርነት የትግበራ ዕቅድ እንደሚፀድቅም ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች
Oct 29, 2026 731
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፦በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክቴን ማስተላለፍ በመቻሌ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል።   በዚህ ታሪካዊ መድረክ የምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ተጨባጭ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የጋራ ቁርጠኝነት እና ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህም በምግብ ዋስትና እና ምርታማነት፣ በአስተማማኝ የኃይል አቅርቦት፣ እንዲሁም በክህሎት እና በዕውቀት ሽግግር ላይ የሚከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ፣ በመከባበር እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የጸና ታሪካዊ ወዳጅነት መሆኑንም አንስተዋል።   ይህንን ወዳጅነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከሩሲያ ጋር በጋራ በመሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራትን በቁርጠኝነት እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል። ይህ ስትራቴጂካዊ ትብብር የኃይል አማራጮቻችንን ከማስፋት ባለፈ የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ በእጅጉ የሚያፋጥን እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት ትስስር ከምንጊዜውም በላይ የሚያጠናክር ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል።
የአፍሪካን የግብርና አቅም እውን ለማድረግ የሳይንስና ኢኖቬሽን ውጤቶችን ወደ ተግባር ማሸጋገር ይገባል
Oct 29, 2026 352
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 /2019 (ኢዜአ)፦ አፍሪካ የግብርና አቅሟን በአግባቡ ለመጠቀም እና የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የግብርና ምርምር፣ የሳይንስ እና የኢኖቬሽን ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማሸጋገር እንደሚገባት የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ማውሪዚዮ ማርቲና ገለጹ። በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም 2026 የማጠቃለያ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።   የፋኦ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ማውሪዚዮ ማርቲና በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የዘርፉን እድገት ለማረጋገጥ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከምርምር ማዕከላት ጋር በየዕለቱ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል። በግብርናና በምግብ ሥርዓት ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማደራጀትና ለማስፋፋት በትኩረት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል። ዘርፉ የተለያዩ አቅሞችንና ሀብቶችን በተለየ መንገድ ማቀናጀትን እንደሚጠይቅ ገልጸው፣ በርካታ እድሎች ያሉት መሆኑንም አመላክተዋል። ፋኦ ተልእኮውን መሰረት በማድረግ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በምርምር ተቋማትና በኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መካከል እንደ ድልድይና አቅም ማስፈጸሚያ መሣሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል ተናግረዋል። የእውቀት ልውውጥ የሚደረግባቸው ቀጣይነት ያላቸው መድረኮችን ማዘጋጀት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በተጨማሪም የምርምር ውጤቶችን በፍጥነት ወደ ተግባርና ወደ ኢንቨስትመንት መቀየር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። እነዚህን እንቅስቃሴዎች በተቀናጀ አካሄድ ማስተዳደር ከተቻለ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት እንደሚቻል ገልጸዋል። ገንዘብ አስፈላጊ ቢሆንም፣ የሰው ኃይል አቅምና ግልጽ የሆነ የአፈጻጸም መንገድ ከሌለ በቂ እንደማይሆን አስረድተዋል። በቂ ገንዘብ የተመደበላቸው አስፈላጊ ፕሮጀክቶች የታሰበውን ውጤት ሳያመጡ የቀሩት በገንዘብ እጥረት ሳይሆን በሰው ኃይል አቅም ማነስ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም የፋይናንስና የሰው ኃይል አቅምን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማቀናጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። አፍሪካ በርካታ እድሎች ያሏት አህጉር መሆኗን ጠቅሰው፣ ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ጋር በመተባበር አስፈላጊ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ወደ ሥራ መግባታቸውን አብራርተዋል። በመሆኑም በግብርናና በምግብ ሥርዓት ዘርፍ በጋራ መሥራትና የሙከራ ፕሮጀክቶችን ወደ ተቀናጀና ዘላቂ የሥራ አካሄድ መቀየር እንደሚገባ አሳስበዋል። ጥረቶች አንድ ጊዜ ብቻ ተከናወነው በሚያበቁ ፕሮጀክቶች ላይ ሳይወሰኑ፣ በቀጣይነት የሚሰፉና ዘላቂ ውጤት የሚያመጡ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል። የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን በመጠቀም በአፍሪካ የምግብና ግብርና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ተደራራቢ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተዘጋጀ አህጉራዊ መድረክ ነው። በተጨማሪም ፎረሙ ምርታማነትን በመጨመር፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በማድረግ እና የግልና የመንግሥት ኢንቨስትመንቶችን በማሳደግ አህጉራዊ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ መሆኑንም አስገንዝበዋል።   በዓለም ባንክ የግብርና ዋና ኢኮኖሚስት እና የአፍሪካ የግብርና ልማት ፕሮግራም (CAADP) የልማት አጋሮች ማስተባበሪያ ቡድን ሊቀመንበር ሚዮ ታካዳ በበኩላቸው፣ የአለም ባንክ አግሪ ኮኔክት በተባለው ፕሮጀክቱ አማካይነት አርሶ አደሮችን እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል ፕሮጀክቱ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ትስስር በመፍጠር ከተለያዩ የልማት አጋሮች የሚሰጡ የተናጠል ድጋፎችን በማቀናጀት የጋራ አቅጣጫ እንዲኖር ማስቻሉን ተናግረዋል።   ለአርሶ አደሮች ፈጠራን ለማስፋፋት የሚያስችል የረጅም ጊዜ የፋይናንስ አቅርቦትን የሚያደናቅፉ ከአቅርቦትና ከፍላጎት ጎን የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ፕሮግራም ኦፊሰር ዳንኤል ሂጊንስ ናቸው። ይህም የግሉ ዘርፍ በቀጣይነት ድጋፉን እንዲረከብና በረጅም ጊዜ ውስጥ ፋይናንስ ማድረጉን እንዲቀጥል የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል።
ብሪክስ ከአፍሪካ ጋር ያለውን የኢንዱስትሪ ትብብር ለማጠናከር አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ አደረገ
Oct 29, 2026 209
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 /2019 (ኢዜአ)፦ ብሪክስ ከአፍሪካ ጋር ያለውን የኢንዱስትሪ ትብብር ለማጠናከር አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ አድርጓል። ይህ የተገለጸው በሞስኮ በተካሄደው በሶስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ “የብሪክስ መድረክ ለሩሲያ-አፍሪካ የንግድ ትብብር እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው። የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ረሼትኒኮቭ፣ ብሪክስ ለአፍሪካ ሀገራት ክፍት የሆነ ገበያ ከመሆኑም በላይ የቴክኖሎጂ፣ የኢንዱስትሪ ምርቶች እና የኢንቨስትመንት አቅርቦት ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸዋል። እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ እየተዘጋጁ ካሉ አዳዲስ አሰራሮች መካከል የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ማህበር እና የእህል የንግድ ልውውጥ (Grain Exchange) ይገኙበታል። በተጨማሪም የአባል ሀገራቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴሮች የኢንዱስትሪ ዲጂታላይዜሽን እና የቴክኖሎጂ ትብብር ማዕቀፍ እንዲዘረጋ ሀሳብ ማቅረባቸውን የቲቪ ብሪክስ ዘገባ ያመለክታል። ረሼትኒኮቭ አክለውም፣ ብሪክስ አሁን ላይ ትብብሩን ከፖለቲካዊ ውይይት ባለፈ ወደ ተጨባጭ ውጤት የሚቀይሩ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ እንደሚገኝና የመንግስታት እንቅፋቶችን በማስወገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል። የንግዱ ማህበረሰብ ለአሰራሮች ውጤታማነት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አመልክተዋል። በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እና ሩሲያ መካከል የኢንዱስትሪ ትብብር ዞን መፈጠሩ ለሁለቱ ወገኖች ትስስር መጠናከር የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት በስብሰባው ላይ ተመላክቷል። በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ በመሰረተ ልማት፣ በትራንስፖርት፣ በሎጂስቲክስ፣ በኃይል እና በሳይበር ደህንነት ዘርፎች ውጤት የሚያመጡ ፕሮጀክቶችን በጋራ መተግበር እንደሚገባ ተመላክቷል። የብሪክስ (BRICS) አባል ሀገራት ነጻ የሆነ የክፍያ ስርዓት የመዘርጋት፣ ኢንቨስትመንትን የሚስቡ አሰራሮችን የመፍጠር እና የኢንዱስትሪ ትብብራቸውን የማስፋት ስራ እያከናወኑ እንደሚገኝም እንዲሁ። የስብሰባው መሪና የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኢሪና አብራሞቫ በአሁኑ ወቅት ከ37 ሺህ በላይ የአፍሪካ ተማሪዎች በሩሲያ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሆኑ መግለጻቸውን የቲቪ ብሪክስ መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
የአፍሪካ የለውጥ ብርሃን፤ የላቀ የዲፕሎማሲ ማዕከል- አዲስ አበባ 
Nov 2, 2026 233
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ የለውጥ ብርሃን፤ የላቀ የዲፕሎማሲ ማዕከል- አዲስ አበባ በሚፍታ ሽፈራ ከተማ የሰዎች የኑሮ ማዕከል፣ የታሪክና የባህል መገለጫ፣ የማኅበራዊ ግንኙነትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መድረክ ነው። የከተማ ልማትም የሚለካው በነዋሪዎች የኑሮ ጥራት፣ በሚፈጥረው የኢኮኖሚ ዕድል፣ በሚጠብቀው ታሪካዊ ማንነትና በሚያጠናክረው ማኅበራዊ ትስስር ጭምር ነው። ይህንን እውነታ በተግባር እያሳዩ ካሉ ጥቂት የዓለም ከተሞች መካከል አዲስ አበባ አንዷ ናት። በቀደሙት ዓመታት አዲስ አበባ ከስሟ፣ ከታሪካዊ ክብሯና ከነዋሪዎቿ የኑሮ ፍላጎት ጋር የማይጣጣሙ በርካታ ችግሮች ይታዩባት ነበር። የአካባቢ ብክለት፣ የአረንጓዴ ስፍራ እጥረት፣ የወንዝ ዳርቻዎች መበከልና የመንገድ መጨናነቅ ከሚጠቀሱት ችግሮች መካከል ነበሩ። ከለውጡ በኋላ በገበታ ለሸገር የተጀመረውና በኋላም ወደ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ የተስፋፋው የልማት አቅጣጫ የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር አዲስ መነሳሳት ፈጥሯል። የዚህ ለውጥ መሠረት ከመደመር እሳቤ ጋር ይገናኛል። መደመር የተለያዩ ሀብቶችን፣ አቅሞችን፣ ባህሎችንና ፍላጎቶችን በማቀናጀት ለጋራ ጥቅም ማዋል ነው። በዚህ እሳቤ ልማት የሰውን ክብር የሚያስጠብቅ፣ ሁሉንም የሚያሳትፍና ለጋራ ተጠቃሚነት የሚያበቃ ነው። በዚህ አቅጣጫ ከተከናወኑት የልማት ሥራዎች መካከል የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ይጠቀሳሉ። የኮሪደር ልማት መንገዶችን ከማስፋትና ከማስዋብ ባለፈ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን፣ የመዝናኛ ማዕከላትንና የንግድ ቦታዎችን በአንድ ላይ ማቀናጀት የቻለ ነው ። ይህም የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የነዋሪዎችን፣የንግድ እንቅስቃሴና የማኅበራዊ ተግባቦት ዕድል አሳድጓል። በተመሳሳይ የወንዝ ዳርቻ ልማት የተፈጥሮ ሀብትን ከሕዝብ ጥቅም ጋር የሚያቀናጅ ግዙፍ የልማት ሥራ ነው። የተበከሉና በተለያዩ ችግሮች የተጎዱ የወንዝ ዳርቻዎችን ወደ አረንጓዴ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዕከላት፣ የንግድና የቱሪዝም መዳረሻዎች የመቀየር ጥረት የአካባቢ ጥበቃንና የማኅበራዊ ጥቅምን አብሮ አስተሳስሯል። መዲናዋን እየቀየሩ ያሉ ሁለገብ የልማት ሥራዎች የመደመር የእይታ አድማስ በተግባር ያሳዩ ናቸው። የተለያየ አቅም፣ እውቀትና ሀብት በማቀናጀት የተከናወኑት እነዚህ ሥራዎች፤ የከተማዋን ነባር ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ከዘመናዊ ግንባታ ጋር በማስማማት ዘላቂ የልማት ውጤት እንዲመዘገብ አስችለዋል። የዘመናዊ መሠረተ ልማቶች መዘርጋት፣ የትራፊክና የመንገድ መጨናነቅ መቃለል እንዲሁም የዲጂታልና የተቀናጁ አገልግሎቶች መስፋፋት የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና የኑሮ ዘይቤ ፈጣንና ቀልጣፋ አድርጎታል። የተዋቡ አረንጓዴ ስፍራዎች፣ የወንዝ ዳርቻ መዝናኛዎች፣ እና የታደሱ ታሪካዊ ቅርሶች አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ያላቸው የኮንፈረንስና የዕረፍት ጊዜ መዳረሻዎች አድርገዋታል። ይህም የቱሪዝም ፍሰቱን በእጅጉ በማሳደግ ለከተማዋ ኢኮኖሚ እጅግ አበረታች ፋይዳ እያስገኘ ይገኛል። አዲስ አበባ የብዙ ብሔር፣ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት መገናኛ ናት። የከተማ ልማት ይህንን ብዝሃነት የሚያከብር፣ የተለያዩ ማኅበረሰቦችን የሚያገናኝና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጠናክር በመሆኑ፤ መዲናዋ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በጋራ የሚገናኙባቸው ደማቅ መድረክ ሆናለች። የእነዚህ ሁሉ የልማት ጥረቶች ተጨባጭ ውጤት በዓለም አቀፍ መድረክም ታላቅ ዕውቅና እያገኘ ነው። አዲስ አበባ የዘንድሮውን የ2026 የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” (Shanghai Award) ሽልማት ማሸነፍ መቻሏ፤ በመዲናዋ የተተገበረው የሰው ተኮር ልማት እይታ፣ የአካባቢ ጥበቃ ጥረት እና የነዋሪዎች የኑሮ ጥራት መሻሻል ምን ያህል የላቀ ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያረጋግጥ ትልቅ ታሪካዊ ማሳያ ነው። ይህ ሽልማት የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ እንዲቀጥሉ፣ አካታችነት እንዲጠናከር እና የነዋሪዎች ሁለገብ ተጠቃሚነት በዘላቂነት እንዲረጋገጥ የሚያደርግ ነው። አዲስ አበባ የተያያዘችው ሁለገብ የልማት እንቅስቃሴ የመላው አፍሪካ መዲናነቷን ክብር በላቀ ደረጃ የሚያጸና ነው። ይህም የአፍሪካውያንን ታሪካዊ ኩራት ከማደስ ባለፈ መዲናዋ የአህጉሪቱ የእድገትና የለውጥ ተምሳሌት ሆና እንድትቀጥል አስችሏታል። ይህ ፈጠራ የታከለበትና አካታች የልማት ጉዞ መዲናዋ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነትና የከበረ የዲፕሎማቲክ ማዕከልነት ድርሻ በጽኑ መሠረት ላይ የጣለ ነው።
ከውበት ባሻገር
Oct 29, 2026 251
ከተሞች የሕዝብ መኖሪያ ብቻ ሳይሆኑ የኢኮኖሚ እድገት፣ የማኅበራዊ ትስስር፣ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ማዕከላት ናቸው። የከተሞች ልማትና ዘመናዊ አሰራር የአንድን አገር ህዝብ የኑሮ ደረጃ፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የወደፊት የልማት አቅጣጫ የሚወስን ነው። በመሆኑም የከተሞች ልማት ከውበት ባሻገር የዜጎችን የኑሮ ደረጃ የማሻሻልና ዘላቂ ልማትን የማረጋገጥ ጉዳይ ሆኖ ይወሰዳል። በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ የከተማ ልማት መሰረታዊ ለውጥ፣ እድገትና ማንሰራራት የታየበት መሆኑን መናገር ይቻላል። ከአፍሪካ መዲና እና የዓለም የዲፕሎማቶች ማእከል ከሆነችው አዲስ አበባ የጀመረው የኮሪደር ልማት ሌሎች ከተሞችንም አዳርሷል። የከተሞች የኮሪደር ልማት ከጅግጅጋ እስከ ወለጋ፣ ከሀረር እስከ ባህር ዳርና ጎንደር፣ ከሰመራ እስከ ጋምቤላ፣ ከሀዋሳ እስከ አሶሳ፣ ከጅማ እስከ አዳማና ነቀምት፣ በአርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳእና እና ሌሎችም ከተሞች ተስፋፍቷል። የከተሞቹ ልማት በተቀናጀ የከተማ ፕላን የሚመራ የወንዝ ዳር ልማትን ጨምሮ የእግረኛና የሳይክል መንገዶች፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች፣ የመዝናኛ ቦታዎችና የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በማካተት እየተከናወነ ይገኛል። ከትራንስፖርት፣ ከውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፣ ከመብራት፣ ከቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ጋር ተሰናስሎ እየተገነባ ነው። በመሆኑም የስማርት ከተሞች ግንባታ ለነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ መሳለጥ ብሎም ወንጀልን ለመከላከል አስችሏል። የከተማ ወንዞችን በማልማት፣ አረንጓዴ ስፍራዎችን በማስፋፋትና ለእግረኞችና ለሳይክል ተጠቃሚዎች ምቹ መንገዶችን በመገንባት የተሻለ ህይወት እንዲመሩና እንዲኖሩ እየተደረገ ነው። በልማቱ የአካል ጉዳተኞች፣ የአረጋውያን፣ የሕፃናትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖችን ማእከል ያደረገ ሰው ተኮር ብሮጀክት መሆኑም ይታወቃል። የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማትን በማሰናሰል በምርት አቅርቦት፣ በገበያ ትስስር፣ በትራንስፖርትና ሌሎችም አገልግሎቶች የተገናኙ እንዲሆኑ እየተደረገም ይገኛል። የከተሞችና የገጠር ልማት ትስስሩም የኢኮኖሚ እድገትን፣ እኩልነትንና የጋራ ተጠቃሚነትን፣ የአካባቢ ጥበቃንና ሌሎችንም መሰረት ያደረገ መሆኑም ይታወቃል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የከተማ ልማት ከውበትና ምቾትም የተሻገረ ሀገር የመገንባት ስትራቴጂ ስለመሆኑ መናገር ይቻላል። የ2026 ዓለም አቀፍ የከተሞች ቀን “Regenerating the City: Adequate Housing for All” “ከተሞችን ማደስ፤ የተሟላ መኖሪያ ቤት ለሁሉም” በሚል መሪ ሃሳብ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም በመላው ዓለም ይከበራል። የክብረ በዓሉ መልእክትም የከተሞችን የወደፊት አቅጣጫ ከሰው ልጆች ደህንነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከኢኮኖሚያዊ እድገትና ከሁሉን አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ጋር በማስተሳሰር ነው። ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ የከተማ ልማት ከማደስና ዘመናዊ አድርጎ ከመስራት ባሻገር የዜጎችን ህይወት የመለወጥ ዓላማን የሰነቀ መሆኑ ይታወቃል።  
የመኸር በረከት፤ የምግብ ሉዓላዊነት መሰረት
Oct 29, 2026 258
ኢትዮጵያ በአራቱ ወቅቶች የተሸለመች፣ በእርሻና በተፈጥሮ በረከት የተባረከች ምድር ናት። ከእነዚህ ወቅቶች መካከል ደግሞ "መኸር" ለአርሶ አደሩና ለአጠቃላይ ሕዝቡ ልዩ ትርጉም ያለው፣ የድካም ውጤት የሚታይበትና የተስፋ ፍሬ የሚለቀምበት ወርቃማ ወቅት ነው። የመኸር በረከት፤ የምግብ ሉዓላዊነት መሰረት ስለመሆኑ መናገር ይቻላል። የአረንጓዴው የመስክ ገጽታ ወደ ቢጫና ወርቃማ ቀለም በሚቀየርበት በዚህ ጊዜ፣ የኢትዮጵያ ገበሬዎች የደስታ፣ የሥራና የምስጋና መንፈስ ይላበሳሉ። የዛሬው የመኸር ወቅት ከቀደሙት ዓመታት የተለየ ትርጉምና ሀገራዊ ተልእኮ ይዞ መጥቷል። ይህ ወቅት የምግብ እጥረትና ጥገኝነትን በማስወገድ፣ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና የሀገርን ክብርን የመመለስ አዲስ የታሪክ ምእራፍ መነሻ ሆኗል። የመኸር ወቅት ሲጠባ ከሰማይ የሚወርደው የክረምት ደመና አልፎ አየሩ መለስ ይላል፤ ፀሐይ በደማቅ ብርሃኗ መስኩን ታበራለች። ክረምቱን ሙሉ በዝናብና በጭቃ ውስጥ ደክሞ፣ ዘርቶና አለስልሶ ያሳደገው አርሶ አደር የድካሙን ፍሬ ለማየት አይኖቹ ወደ ማሳው ያማትራሉ። በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች የመኸር አዝመራ የሥራ ወቅትን ብቻ ሳይሆን የማህበረሰባዊ ትስስርን ያመለክታል። በማለዳ ከወፎች ጫጫታ ጋር የሚነቃው አርሶ አደር ማገዶውንና ማጨጃውን ይዞ ይሰማራል። በአብዛኛው ወንዶች በማጨድ፤ ሴቶችና ህፃናት ደግሞ የታጨደውን ሰብል በስርዓት በማሰርና በመከመር ይተባበራሉ። ይህ የመደመር፣ የህብረትና የደቦ አሰራር የኢትዮጵያውያን የወል ጥበብና የመረዳዳት እሴት መግለጫ ነው። በመኸር ወቅት ትልቁ ፈተና እና ትኩረት ሰብልን ወቅቱን ጠብቆና በጥንቃቄ መሰብሰብ ነው። የመኸር አዝመራ በሰዓቱ ካልተሰበሰበ ያልተጠበቀ ዝናብ መና ሊያስቀረው ይችላል። በመሆኑም አርሶ አደሮች ጊዜ ሳይሰጡ አዝመራቸውን በፍጥነትና በብቃት ለመሰብሰብ ሌሊትና ቀን ይሰራሉ። አዝመራን ያለብክነት መሰብሰብ የምርት ጥራትን ጠብቆ ወደ ጎተራና ወደ ገበያ ለማድረስ ወሳኝ ነው። የሰብል ምርት ከማጨድ እስከ ጎተራ ገቢ እስከሚሆን ድረስ የሚደረግ የጥራትና የፅዳት ጥንቃቄ፣ በድካም የተገኘውን ምርት ከብልሽትና ከብክነት ይከላከላል። ይህም የአርሶ አደሩን የብዙ ወራት ላብና ሀገራዊ ሀብትን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ያስችላል። በመሆኑም አሁን ላይ በዘመናዊ ማሽነሪዎች (ኮምባይነር ሃርቨስተር) ሰብልን የመሰብሰብ ልምድ እያደገ በመሄዱ ሲታጨድም ይሁን ሲወቃ ብክነትን ማስቀረት አስችሏል። በኢትዮጵያ ግብርና ልማት አዲስ የታሪክ ምእራፍ የከፈተው የስንዴ ልማትና ምርታማነት መሆኑ ይታወቃል። የበጋ መስኖን ጨምሮ በመደበኛ ወቅቶች ስንዴን በስፋት በማምረት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ተችሏል። በዚህም ምርታማነትን የማሳደግና ከተረጅነት የመውጣት ጥረት ስኬታማ እየሆነ ይገኛል። የስንዴ ምርት መጠን ከፍተኛ ማንሰራራት በማሳየቱ የዜጎች የምግብ ዋስትና መሰረት ከመሆን አልፎ የጎረቤት አገራትም ሲሳይ ሆኗል። በመሆኑም ኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪካ የእህል ጎተራ የማድረግ ርዕይ እውን እያደረገ ይገኛል። ለዘመናት "የረሃብና የእርዳታ እጅ ዘርጊ" ተደርጋ ትታይ የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ አምርታ በምግብ ፍጆታ ራሷን የምትመግብ መሆኑን በተግባር እያሳየች ትገኛለች። በምግብ ራስን መቻል ማለት የሀገርን ነፃነትና ክብር ማስከበር ነው። በእርዳታ እህል ላይ የነበረውን ጥገኝነት በማስቀረት ሀገራዊ ሰብዓዊ ክብርና ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል። የታጨደው ሰብል ተወቅቶ ወደ ጎተራ ሲገባ፤ ከአርሶ አደሩ አልፎ በከተሞች የምርት አቅርቦት ሲበራከት የገበያ መረጋጋትና የምግብ ዋስትና መሰረት እየተጠናከረ ይሄዳል። ለዚህም ነው የመኸር በረከት፤ የምግብ ሉዓላዊነት መሰረት የሚሆነው። የምርት ማደግና ሰብልን ያለብክነት መሰብሰብ ቀጥታ ወደ የቤተሰብ ብልጽግና ይተረጎማል። አርሶ አደሩ ምርቱን ለራሱ ከተጠቀመ በኋላ ትርፉን ለገበያ በማቅረብ፡ ቤተሰቡን ያስተዳድራል፣ የልጆቹን ትምህርትና ጤና ያሟላል። የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን፣ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ኢንቨስትመንቶችን ለመስራት የሚያስችል የኢኮኖሚ አቅም ይፈጥራል። ገጠሩ ክፍል ከዕለት ጉርስ ፍለጋ ወጥቶ ወደ ሀብት ፈጣሪነትና ወደ አጠቃላይ ብልጽግና ይሸጋገራል። በመሆኑም የመኸር ወቅት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ፅናት፣ የላብና የህብረት ጥረታቸው በውጤት የሚደመደምበት ወርቃማ ጊዜ ነው።  
አዋሽና ትሩፋቱ
Oct 29, 2026 259
አዋሽ ሀገሩን ተሻግሮ ላያልፍ መሃላ የፈፀመ ይመስላል። አዋሽ ሀገር ወዳድ፣ የሀገር ቤት ወንዝ፣ አልሚ እና ጠቃሚ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። የአዋሽ ወንዝ ለኢትዮጵያ ከውሃ ሀብት እስከ መስኖ ግብርና፣ ከኢንዱስትሪ እስከ አረንጓዴ ልማት የሚያገለግል የሀገር ባለውለታ ነው። አዋሽ የግብርና ምርት ማሳደጊያ፣ የኢንዱስትሪ መደገፊያ፣ የሰዎች ኑሮ መሠረትና የኢትዮጵያ የልማት አቅም ማሳያ መሆኑ ይታወቃል። በተለይም የዝናብ እጥረት ለሚገጥማቸው አካባቢዎች የመስኖ ልማትን በማስፋፋት፣ የምግብ ምርትን ለማሳደግና የአካባቢውን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ረገድ የማይተካ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል።     በግምት 1 ሺህ250 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የአዋሽ ወንዝ የውሃ ሀብቱ በአንድ አካባቢ ብቻ የተገደበ አይደለም። ከከፍተኛ ቦታዎች እስከ ደረቅና ከፊል ደረቅ የስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች በመዝለቅ ፈላጊዎቹን ያገለግላል። የውሃና የኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው የአዋሽ ተፋሰስን ስፋት ወደ 110 ሺህ ካሬ ኪሎ ሜትር፣ አማካይ ዓመታዊ የውሃ ምርቱን ደግሞ 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ያደርሰዋል።   የአዋሽ ወንዝ በተለይም የአፋርና የተፋሰሱ ዝቅተኛ አካባቢዎች በመስኖ ለሰብል ልማት፣ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እንዲሁም ለእንስሳት መኖ ምርት ያገለግላል። በወንዙ ተፋሰስ ከተገነቡት የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል የወንጂ፣ የመተሃራ፣ የቀሰምና የተንዳሆ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ። እነዚህ ፕሮጀክቶች የግብርና ምርትን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ፣ በዓመት በተለያዩ ወቅቶች በማምረት ከችግርና ድህነት ለመውጣት እያገዙ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ የስንዴ ምርትን በመስኖ በማልማት የምግብ ዋስትናዋን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት አዋሽ አለኝታነቱን አሳይቶ እየተሰራበት ነው። በተጨማሪም ለስኳር ልማት፣ ለጥጥ፣ ለአትክልትና ለፍራፍሬ ምርት የአዋሽ ውለታ ከፍተኛ ነው። የአዋሽ ተፋሰስ ከግብርና ባሻገር ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እድገት ወሳኝ ስፍራ ነው። በተፋሰሱ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ተቋማት፣ የማምረቻ ዘርፎች፣ የስኳር ፋብሪካዎችና የከተማ ልማት ስራዎች አቅርቦት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። እዎ እርግጥ ነው አዋሽ ውለታው ብዙ ነው፤ በታማኝነቱ የሚታወቅ ሀገር ወዳድ ወንዝ ነው። የወንዙ ተጠቃሚዎችም የከተማ ነዋሪዎችና ገበሬዎች ብቻ አይደሉም። በተለይ በወንዙ የታችኛው ተፋሰስ የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ለእንስሳት፣ ለግጦሽ መሬትና ለኑሯቸው መሰረት ሆኖ ዘመናትን እያገለገለ ይገኛል። በመሆኑም የአዋሽ ጉዳይ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የአርብቶ አደሮች የኑሮ መሰረት ነው። ለተፈጥሮ ሃብትና ለዱር እንስሳት ጥበቃ፣ ለቱሪዝምና ለምርምር ጭምር አገልጋይ መሆኑንም መናገር ይቻላል። የአዋሽ ወንዝ ትልቅ የልማት አቅም ቢኖረውም፣ ይህን ሀብት በዘላቂነት ለመጠቀም መፍትሔ የሚሹ ተግዳሮቶችም አልጠፉም። ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ የከተማ ነዋሪዎችና አርብቶ አደሮች በተመሳሳይ የውሃ ሀብት ላይ ጥገኛ ስለሆኑ በድርቅ ወቅት የውሃ ክፍፍል ውስብስብ ይሆናል። ሌላው ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥና የዝናብ መዛባት ሲከሰት የወንዙን ፍሰት ስለሚዛባ የድርቅና የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ደግሞ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር፣ የጎርፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን ማጠናከር፣ የተፋሰስ ጥበቃ፣ የውሃ ቆጣቢ ቴክኖሎጂና የሕዝብ ተሳትፎ ወሳኝ ስለመሆኑ ይመከራል። የአዋሽ ወንዝን አቅም በሙሉ ለመጠቀም የሚያስፈልገው የውሃ ፕሮጀክቶችን መገንባት ብቻ አይደለም። የተገነቡትን መሠረተ ልማቶች በብቃት ማስተዳደር፣ የውሃ ብክነትን መቀነስ፣ የመስኖ መሬቶችን በተሻለ ቴክኖሎጂ ማልማትና የወንዙን የተፈጥሮ ሥርዓት መጠበቅም ያስፈልጋል። በተመሳሳይ የወንዙ የታችኛው ተፋሰስ ለሚገኙ ማህበረሰቦችና ለተፈጥሮ ሥነ-ምህዳር የሚያስፈልገው የውሃ መጠን መጠበቅ አለበት። የውሃ ሀብት ለአንድ የኢኮኖሚ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም በሚጠቅም መልኩ መመራት ይገባዋል።
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽግግር-የኮፕ32 ተግባራዊ ማሳያ 
Nov 3, 2026 63
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽግግር-የኮፕ32 ተግባራዊ ማሳያ የብሉምበርግ ጥንክር እንደዘገበው ዓለም ስለ አየር ንብረት ለውጥ እየተጨነቀና እየመከረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ኢትዮጵያ በተግባር ያሳየችው ድንቅ ውሳኔ የመላው ዓለምን ትኩረት ስቧል።የነዳጅ መኪኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት በይፋ በመከልከልና ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ሽግግር በፍጥነት በመግባት ዓለምን ያስደመመችው ኢትዮጵያ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አበረታች ውጤት ማስመዝገቧን የብሉምበርግ ጥንክር አትቷል። በኢትዮጵያ ከሚመነጨው ኃይል 99 በመቶ የሚሆነው ንጹህና አረንጓዴ መሆኑን ያተተው ዘገባው፣ ይህም ለኤሌክትሪክ መኪኖች በርካሽ ኃይል ማቅረብ እንዳስቻላት ገልጿል።   ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ደግሞ በዚህ ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱን አመላክቷል። ይህ ታላቅ ሽግግር ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንም ወጪያቸውን እንዲቆጥቡ አድርጓል ነው ያለው የብሉምበርግ ዘገባ። የኤሌክትሪክ መኪና የሚጠቀሙ ታክሲ ነጂዎችና የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ቀደም ሲል ለነዳጅና ለጥገና ያወጡት የነበረውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት በወር እስከ 150 ዶላር (ከ40,000 እስከ 50,000 ብር) መቆጠብ ችለዋል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ እንደ ቢኬጂ ግሩፕ ያሉ የመገጣጠሚያ ፋብሪካዎች በሀገር ውስጥ ሥራ በመጀመራቸው፣ በርካታ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎችን በማሰልጠን አዲስ የሥራ እድል መፍጠር ተችሏል።   በኢትዮጵያ በሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ድርሻ 6 በመቶ መድረሱን፣ ይህም ከዓለም አቀፉ አማካይ (4 በመቶ) በላይ በመሆን ኢትዮጵያን በዘርፉ ግንባር ቀደም አድርጓታል። ኢትዮጵያ በፈረንጆች 2027 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባኤን (COP32) ስታስተናግድ፣ "ታዳጊ ሀገራት በገንዘብ እጥረት ወይም በነዳጅ ቀውስ ሳይገደቡ እንዴት በፍጥነት ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መሸጋገር ይችላሉ?" ለሚለው ትልቅ ጥያቄ ህያውና በተግባር የተረጋገጠ ማሳያ እንደምትሆንም ነው ብሉምበርግ በዘገባው ያመላከተው። ኢትዮጵያ እስከ ፈረንጆቹ 2033 አምስት መቶ ሺህ (500,000) የኤሌክትሪክ መኪኖችን በመንገድ ላይ ለማሰማራት የያዘችው ታላቅ እቅድም፣ የዚሁ አረንጓዴ እና ዘላቂ ራዕይ አካል መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።
የካፒታል ገበያ፡ የነገዋ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት መሰረት
Nov 2, 2026 83
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የነገዋን ሀገር የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚቀይር እና ለአዲስ ዕድገት መሠረት የሚጥል መዋቅራዊ ሽግግር እያደረገ ይገኛል። የካፒታል ገበያ ሥርዓት በአዲስ መልክ መመለሱ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊና ግልጽ የፋይናንስ አማራጭ የሚያሸጋግር ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ የሀገር ውስጥ ቁጠባን ወደ ምርታማ ኢንቨስትመንት ለመቀየር፣ የንግድ ድርጅቶችን አቅም ለማሳደግ እና የሀገሪቱን የብድርና የዕዳ ጫና በዘላቂነት ለማቃለል ታስቦ የተዘረጋ የነገ መደላደል ነው። ዘመናዊ የካፒታል ገበያ በሕጋዊ መንገድ የተጀመረው የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲጸድቅ ነው። አዋጁን ተከትሎ ገበያውን በበላይነት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) የተቋቋመ ሲሆን፣ ግብይቱን የሚያከናውነው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ (ESX) ደግሞ በመንግሥትና በግል አጋርነት (PPP) ተመሠረተ። ይህ የዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያን (ESX) በሳይንስ ሙዚየም በይፋ መርቀው ያስጀመሩ ሲሆን፣ መደበኛ የቀጥታ የንግድ ግብይት (Live Trading) ደግሞ በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም. ላይ በይፋ ተጀምሯል። የካፒታል ገበያው የነገን ብሩህ ተስፋ በሚያሳይ መልኩ ከጅምሩ በርካታ ግዙፍ ተቋማትን ማሳተፍ ችሏል። የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ በዲጂታል መንገድና በቴሌብር ጭምር በመታገዝ ከ47 ሺህ በላይ አዳዲስ ዜጎችን በማሳተፍ የመጀመሪያው በይፋ የተመዘገበ ኩባንያ በመሆን ታሪክ ሠርቷል። ይህንን ተከትሎ በርካታ የግል የፋይናንስ ተቋማትና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አክሲዮኖቻቸውን በገበያው ላይ በይፋ ማስመዝገብ የጀመሩ ሲሆን፣ ይህም ለገበያው መነቃቃት ትልቅ መሠረት ጥሏል። በተጨማሪም የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለተለያዩ የኢንቨስትመንት ባንኮች፣ አገበያዮችና ደላላ ኩባንያዎች የሥራ ፈቃድ የሰጠ ሲሆን፣ በባንኮች የእርስ በርስ የአጭር ጊዜ የገንዘብ መበዳደሪያ ገበያ ላይ የተመዘገበው አጠቃላይ የግብይት መጠን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ማለፉ የነገውን የገበያ አቅምና አስተማማኝነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል። የዚህ ግዙፍ የፋይናንስ መድረክ ዋና ዓላማና ለነገዋ ኢትዮጵያ ያለው ፋይዳ ሀገሪቱን በባንክ ብድር ላይ ብቻ ከምትመሰረተው የፋይናንስ ጥገኝነት ማላቀቅና አማራጭ የረጅም ጊዜ የካፒታል ምንጭ መፍጠር ነው። ኩባንያዎችና መንግሥት አክሲዮንና ቦንድ በመሸጥ ለትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን ገንዘብ በቀጥታ ከሕዝብ መሰብሰብ እንዲችሉ ያደርጋል። ይህ አሠራር የመደመር መንግሥት ገንዘብ በማተም ወይም ከብሔራዊ ባንክ በመበደር የሚፈጥረውን የዋጋ ግሽበት በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን፣ ማኅበረሰቡም ገንዘቡን በባንክ ቁጠባ ብቻ ከማስቀመጥ ባለፈ በትላልቅ ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት አድርጎ የትርፍ ተካፋይ እንዲሆንና በነገዋ ኢትዮጵያ የሀብት ፍትሐዊ ክፍፍል እንዲሰፍን ያደርጋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገበያውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ ይህ ገበያ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የፋይናንስ ነፃነት የሚያረጋግጥ መሣሪያ ነው። የካፒታል ገበያው ማንኛውም ዜጋ በቀላሉ የትላልቅ ባንኮችና ተቋማት ባለቤት የሚሆንበት የነገ መድረክ ነው። የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ማዛወር ዓላማው ተቋማቱ ዓለም አቀፍ አሠራርን፣ ግልጽነትንና ዘመናዊ ተጠያቂነትን እንዲላበሱ ለማድረግ ሲሆን፣ የግል ዘርፉ የነገዋ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሞተር እንዲሆን መንግሥት ሙሉ ዋስትናና ከለላ ይሰጣል። የካፒታል ገበያው ውጤታማነት በዋናነት የተመሠረተው ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያና የመረጃ ሥርዓቶችን በመተግበር ላይ ሲሆን፣ የኢትዮ ቴሌኮም የመጀመሪያ ዙር አክሲዮን በቴሌብር መጠናቀቁ ለነገው ዲጂታል መሠረተ ልማት ትልቅ ማሳያ ነው። ገበያው ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ የማኅበረሰቡን የፋይናንስ ግንዛቤ ማሳደግ፣ የኩባንያዎችን የሒሳብ አያያዝ ግልጽነት ማረጋገጥ እና ያልተገባ የገበያ ማጭበርበርን መቆጣጠር የመሳሰሉ የቤት ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል። ወደፊት ገበያውን ይበልጥ ለማስፋፋት የተቀመጡት ቀጣይ ስትራቴጂካዊ ትከረቶች ገበያውን ቀጣናዊና ዲጂታል ማድረግ ላይ ያተኮሩ ናቸው።
ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ (ዲተረንስ)
Oct 29, 2026 375
ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦ ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ (ዲተረንስ) ጦርነትን በማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ጦርነቱ ሳይጀመር በማስቀረት የሚገኝ ድል ከሁሉ የላቀ ነው። ጥንታዊው የቻይና ጦር ስትራቴጂስት ሱን ዙ "ዘ አርት ኦፍ ዋር" በተሰኘው መጽሐፉ፣ ትልቁ የጦር ጥበብ ጠላትን ሳይዋጉ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሆነ ጽፏል። በዚህም መፅሐፉ መቶ ጦርነትን አሸንፎ መገኘት የላቀ ጥበብ አይደለም፤ ምክንያቱም ድል መንሳት በራሱ የሰው ሕይወትና የአገር ሀብትን ያስከፍላልና። ይህ ሃሳብ በዘመናዊው የደህንነት ጥናት ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ ወይም "ዲተረንስ" ተብሎ ይጠራል። የትርጉሙ ጭብጥም ጠላት ጥቃት ከመሞከር እንዲታቀብ የሚያደርግ እምነትን መፍጠር ነው። ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ መሠረታዊ አመክንዮ ማንኛውም ወገን ጦርነት የሚጀምረው ከጦርነቱ የሚያገኘው ጥቅም ከሚከፍለው ዋጋ እንደሚበልጥ ሲያስብ ነው። ስለዚህ አንድ አገር የጥቃትን ዋጋ በበቂ ሁኔታ ካናረ፣ ጠላት ሒሳቡን ሲሰራ ጦርነት ኪሳራ ሆኖ ይታየዋል። ሮማዊው ወታደራዊ ጸሐፊ ቬጌቲየስ ከ1 ሺህ 600 ዓመታት በፊት በጻፈው መፅሓፍ የከተበው ታዋቂ አባባል ይህንኑ ይገልጻል። "ሰላምን የሚሻት ቢኖር ለጦርነት ይዘጋጅ" ይላል። ይህም በተለያዩ አስረጂ ጉዳዮች ሊዳሰስ ይችላል፤ የመጀመሪያው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ነው። የአየር መከላከያ፣ የመድፍና የሚሳይል አቅም፣ የታጠቁ ኃይሎችና የአየር ኃይል ብቃትን ይመለከታል። ሁለተኛው የሰለጠነ ወታደር ነው፤ ምክንያቱም መሳሪያ በብቁ እጅ ካልተያዘ ክብደት እንጂ ጉልበት አይሆንምና። ተከታታይ ስልጠና፣ ዲሲፕሊንና የዕዝ ሰንሰለት ያለው ሠራዊት ለጠላት ከሚታየው ቁጥር በላይ ግምትን ይፈጥራል። ሦስተኛው በቴክኖሎጂ የታገዘ የውጊያ ብቃት ነው፤ ይኸውም ስለላና የስለላ ድሮኖች፣ ሳይበር፣ የመገናኛና የመረጃ ሥርዓት እንዲሁም ትክክለኛ ኢላማን የመምታት አቅምን ያካትታል። በዘመናችን ጦርነት የሚወሰነው በመረጃ የበላይነት ጭምር ነው፤ ምክንያቱም ጠላቱን አስቀድሞ የሚያይ ወገን ሁልጊዜም አንድ እርምጃን ቀድሟል። ሌላኛው ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚዘነጋው ተዓማኒነት ነው። አሜሪካዊው የስትራቴጂ ምሁር ቶማስ ሼሊንግ “Arms and Influence” በተሰኘው መጽሐፉ እንደሚያስረዳው፣ ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ ወይም "ዲተረንስ" የሚሰራው አቅሙ ብቻ ሳይሆን ያንን አቅም የመጠቀም ፍላጎትና ቁርጠኝነት ጭምር ለጠላት ግልጽ ሲሆን ነው። ምስጢር ሆኖ የተቀመጠ ወይም በማሳየት ያልተረጋገጠ አቅም ጠላትን ሁለቴ ደጋግሞ እንዲያስብ ሊያደርገው አይችልም። ለዚህም ነው ወታደራዊ ልምምዶች፣ ሰልፎችና ግልጽ የመከላከያ ፖሊሲዎች የጥበቡ አካል የሆኑት። የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ልምድም ይህን ያሳያል፤ ሁለቱ ልዕለ ኃያላን አሜሪካና የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት የጋራ ጥፋት የሚያስከትል የኒውክሌር አቅም ስለነበራቸው በቀጥታ ከመዋጋት ተቆጥበው በቃላት ጦርነት ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ አድርጓቸዋል። ኢትዮጵያም ለዚህ ጉልህ ታሪካዊ ምሳሌ አላት። በ1888 ዓ.ም. በዓድዋ አፄ ምኒልክ ከየአቅጣጫው የተሰበሰበውን ሕዝብ በአንድ ዓላማ አሰልፈው፣ እቴጌ ጣይቱንና ሌሎች የጦር መሪዎችን አስተባብረው ጣሊያንን በሚወስን ሁኔታ ድል አድርገዋል። ድሉ ከውጊያ ሜዳ ባሻገር ዲፕሎማሲያዊ ውጤትም ነበረው፤ በዚያው ዓመት በተፈረመው የአዲስ አበባ ውል ጣሊያን የኢትዮጵያን ነጻነት እንድታውቅ ተገደደች። ለሌሎች የአውሮፓ ኃያላንም ኢትዮጵያን መውረር ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንካራ መልዕክት በመሆን ሌላ ጦርነትን ለማስቀረት አገለገለ። ይህ ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ በተግባር የተፈተነ አቅሙ ታይቷል፣ ቁርጠኝነቱም ተረጋግጧል። አሁን ላይም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር አካባቢ ባላት ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ ምክንያት ለውስጣዊና ለውጫዊ ጫናዎች ተጋላጭ ሀገር ናት። ሀገሪቷ የምትገኝበት መልክዓ ምድር በተለያዩ ግጭቶች የሚታወቅ ብቻም ሳይሆን የተለያዩ ኃያላን አገራት ጦር የሚገኝበት ቀጣና ነው። ይህንን ከግምት ባስገባ መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት የመከላከያ ሠራዊቱን በማዘመን ረገድ ተጨባጭ እርምጃዎችን ወስዷል እየወሰደም ይገኛል። ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት አከባበር በዓል ላይ አየር ኃይሉን በማዘመን በ2030 ከአራተኛ ትውልድ ወደ አምስተኛ ለማሻገር እንደሚሰራ መናገራቸው ይታወሳል። አየር ኃይሉ አሁን ካለበት በዕጥፍ የማሳደግ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም አስረግጠው ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በራሱ ጠላት በኢትዮጵያ ላይ ጥቃትን ከመፈፀሙ በፊት ሁለቴና ሦስቴ እንዲያስብበት የሚያደርግ መሆኑን ማንሳቱ ግድ ይላል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከቃል በላይ ለመሆኑ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ አየር ኃይሉ ከዚህ ቀደም ከታጠቃቸው ዘመናዊ የውጊያ አውሮፕላኖች በተጨማሪ ኢትዮጵያ ትናንት 12 የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶችን ከሩሲያ ተረክባለች። በዚህም ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም ላይ በርካታ ሀገራት በሰላሙ ጊዜ አስፈላጊውን ዝግጅት ባለማድረጋቸው ምክንያት ችግር ሲፈጠር ለአደጋ ሲጋለጡ እንደሚታይ ጠቁመው፤ የኢትዮጵያን የአየር ክልል ላለማስደፈር በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ የተረከበቻቸው የሱ-35 ኤርክራፍቶች በዓለም ላይ ካሉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ግንባር ቀደም ናቸው። መሳሪያዎቹ ከአየር ወደ አየር እንዲሁም ከአየር ወደ ምድር ውጊያ የማካሄድ ከፍተኛ አቅም ያላቸውና በተግባር የተፈተኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቃጡ የክሩዝ ሚሳኤል ጥቃቶችን እስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት የመለየት (Detect) እና የማክሸፍ (Intercept) ብቃት እንዳላቸው አስረድተዋል። ይህንን የቴክኖሎጂ አቅም መገንባት ለሀገር ህልውና ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል የነበሩት የሱ-30 እና የአሁኖቹ የሱ-35 ተዋጊ ጄቶች የኢትዮጵያን የአየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄት ባለቤት ከሆኑ በጣት የሚቆጠሩ አገራት መካከል አትዮጵያ አንዷ መሆኗ ደግሞ ከራሷ ሉአላዊትንም ባለፈ ለአህጉሩ እና ለቀጣናው ሰላም መጠበቅ ወሳኝ ሚና ይኖራታል ማለት ነው። ምክንያቱም የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄት በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ የአየር ላይ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ዘመናዊ ተዋጊ ጀት ነው። የጀቱ ሞተሮች አቅጣጫቸውን መቀየር የሚችሉ (3D Thrust Vectoring Nozzles) በመሆናቸው አየር ላይ ባልተለመዱ ማዕዘኖች እና ፍጥነቶች እንዲንቀሳቀስ ያስችሉታል። የሩሲያ አየር ኃይል ከሚጠቀማቸው እጅግ ዘመናዊ እና አደገኛ የጦር ጄቶች መካከል አንዱ ነው። የዚህ ጀት መገለጫ እጅግ ዘመናዊና ተዋጊ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የ5ኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ የተቀላቀለበት ስለመሆኑም ይነገራል። በሰአት 2 ሺህ 400 ኪ.ሜ የመብረርና ያለተጨማሪ የነዳጅ ታንከርም 3 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር መብረር የሚችለው ተዋጊ ጀት በአንድ ጊዜ እስከ 30 ኢላማዎችን የመከታተል እና 8ቱን በአንድ ጊዜ የመምታት አቅም አለው። ራዳሩን ሳያበራ (ምንም ዓይነት የራዳር ሞገድ ሳይለቅ) በኢንፍራሬድ/ካሜራ (IRST) አማካኝነት ጠላትን በድብቅ እስከ 80 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ መከታተል ይችላል። የጠላት ራዳሮችን እና ሚሳይሎችን በመረበሽ (Jamming) ጄቱን ካልተጠበቀ ጥቃት ይከላከላል። የሩሲያ አየር ኃይል ከሚጠቀማቸው እጅግ ዘመናዊ እና አደገኛ የጦር ጄቶች መካከል አንዱ ነው። የዚህ ጀት መገለጫ እጅግ ዘመናዊና ተዋጊ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የ5ኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ የተቀላቀለበት ስለመሆኑም ይነገራል። ለዚህም ነው በሩሲያ በተደረገው የጦር ጀቶቹ ርክክብ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የምናደርገው ሁለንተናዊ ጥረት ዛሬ ሌላ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል ያሉት። ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይል እያደረገች ያለው ዝግጁነት ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም የገነባች መሆኑንም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የየብስ፣ የአየርና የባህር ኃይሎች በሳተላይትና በዲጂታል የመገናኛ መረቦች እንዲተሳሰሩና እንደገና እንዲደራጁ መደረጉም ጠላት ሁለቴ እንዲያስብ የሚያደርግ ነው። ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ብቁና ጠንካራ ሠራዊት የስለላ፣ የትክክለኛ ጥቃትና የፈጣን ምላሽ አቅምን ስለሚጨምር የአየር ክልልን የመጠበቅ ችሎታን ያሳድጋል። ይህ ሁሉ አንድ ላይ ሲታይ ኢትዮጵያን በቀላሉ ለማጥቃት እንደማይቻል የሚያስተላልፈው መልዕክት የጎላ ነው። እውነተኛ ድል ጥይት ሳይተኮስ በሚገኝ ሰላም ይረጋገጣል!!! የሚባለውስ ለዚህ አይደል!
የኢትዮጵያ ጽኑ ሉዓላዊነትና የቀጣናው ዋስትና- ዘመናዊ ጄቶች የታጠቀው አየር ኃይል
Oct 29, 2026 309
በለይኩን አሰፋ ትልቅ ሕዝብ፣ትልቅ ሀገርና ታላቅ ራዕይ ሰማይ ወሰን የሌለው የተፈጥሮ ስፋት ቢሆንም፣ ለአንድ ሀገር ግን የሉዓላዊነት፣ የደኅንነትና የብሔራዊ ጥቅም አካል ነው። በዚህ ሰማይ ላይ የሀገርን ክብር ለመጠበቅ፣ የሕዝብን ደኅንነት ለማረጋገጥና የውጭ ስጋቶችን ለመከላከል የቆመው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገሪቱ የመከላከያ ሥርዓት ወሳኝ አካል ነው። አንድ ሀገር ሉዓላዊነቷን በምድር ላይ ብቻ አትጠብቅም። የአየር ጠፈሯን መጠበቅ፣ ከድንበሯ በላይ የሚንቀሳቀሱ ስጋቶችን መከታተልና ለሀገራዊ ደኅንነት የሚያስፈልገውን የአየር የበላይነት ማረጋገጥ የዘመናዊ መከላከያ አቅም ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። በዚህ የብሔራዊ ደኅንነት ምሰሶ ውስጥ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የራሱ የሆነ ታሪክ፣ የተለየ ተልዕኮና የረጅም ዘመን የአገልግሎት ልምድ አለው። ከታሪካዊ አመሠራረቱ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከአውሮፕላኖችና ከወታደራዊ መሣሪያዎች የበለጠ ትርጉም ይዞ ቆይቷል። ከጀግንነት፣ ከሙያዊ ብቃትና ከሀገር ፍቅር መርህ ጋር የተያያዘ ተቋም ሆኖ በተለያዩ ዘመናት የሀገሪቱን የአየር ደኅንነት ለማስጠበቅ ተልዕኮውን ተወጥቷል። የዚህ ተቋም ታሪክ የሚዘከረው በተከናወኑ ዘመቻዎች ብቻ ሳይሆን፣ ለሀገር ጥቅም በተከፈሉ መሥዋዕትነቶች፣ በተገነባው ሙያዊ ልምድና ከትውልድ ወደ ትውልድ በተላለፈው የአገልግሎት መንፈስ ጭምር ነው። ዛሬ የዓለም ወታደራዊ አሠራር በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት ወቅት፣ የአየር ኃይል አቅም በአውሮፕላኖች ብዛት ብቻ አይለካም። የራዳርና የክትትል ሥርዓቶች፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የአየር መከላከያ፣ የሰው ኃይል ሥልጠና፣ የጥገናና የቴክኒክ ብቃት እንዲሁም የተቀናጀ የውጊያ አሠራር የአቅሙ ወሳኝ መለኪያዎች ሆነዋል። ታዲያ የኢትዮጵያ አየር ኃይልም በየጊዜው ከሚለዋወጡት ዓለም አቀፍ የጂኦፖለቲካ እና የቴክኖሎጂ እድገቶች ጋር አብሮ በመጓዝ አሁን ላይ ሰፊና ጥልቅ የሆነ የዘመናዊነት ሽግግር እያደረገ ይገኛል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከተካሄደው ሀገራዊ የሪፎርም ሂደት፣ ለአየር ኃይሉ መሰረታዊ የላቀ ጥንካሬ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። የመደመር መንግሥት ለአየር ኃይሉ መጠናከር እያበረከተ ያለው የቴክኖሎጂ፣ የመሰረተ ልማት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ግንባታ ድጋፍ ተቋሙን በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ዘመናዊ የጦር ኃይል አድርጎታል። የአየር ኃይሉ የዘመናዊነት ጉዞ ዋነኛው መገለጫ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መታጠቁ ነው። ተቋሙ ወቅታዊ የጦርነት ስልቶችን መሠረት ያደረጉ ዘመናዊ ሲስተም የታጠቁ ድሮኖችን በስፋት በመጠቀም ረገድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህም የቅድመ-ማስጠንቀቂያ እና ተፈላጊውን ኢላማ የመምታት አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ከዚህም በተጨማሪ ነባር የውጊያ አውሮፕላኖችን እና ሄሊኮፕተሮችን ማዘመን ብቻ ሳይሆን፣ አዳዲስ የላቁ የውጊያ አውሮፕላኖችን መታጠቁ የአየር ክልል የበላይነቱን እንዲያረጋግጥ አስችሎታል። ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ ዛሬ ከሩሲያ የተረከበችው የመጀመሪያዎቹን አስራ ሁለት የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች (Su-35 4++ Generation) ተጠቃሽ ናቸው። ይህም የኢትየጵያን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ሌላ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የሚያረጋግጥ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት በሩሲያ ተገኝተው የጦር ጄቶችን በተረከቡበት ወቅት ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይሏ እያደረገች ያለው ዝግጁነት ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ እያላበሳት ይገኛል ብለዋል። እነዚህን እጅግ ዘመናዊ የጦር ጄቶች በመታጠቅ ብቻ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ መሆን ችላለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይህንን ስኬት አስመልክተው ሲናገሩም፦ "ይህ ታሪካዊ ስኬት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን፣ ወደፊትም የጋራ ደህንነታችንን እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የምናደርገውን ጉዞ በልበ ሙሉነት እንድንቀጥል ትልቅ አቅም ይሆነናል።" ብለዋል። በዚህ ድንቅ ዕምርታ የታጀበው የአየር ኃይላችን ዝግጁነት፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ባለፈ ለቀጣናው ሰላም ትልቅ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑን ይህ ታሪካዊ ቀን በግልጽ አሳይቷል። ይህ ሀገራችንን የሰማይ ላይ ጥበቃ (Air Defense) ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ትልቅ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ሱ-35 በአየር ላይ የሚደረጉ ውጊያዎችን በመቆጣጠር፣ የጠላት አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በረጅም ርቀት ላይ የማወቅ፣ የራዳር ሥርዓቶችን የማደናቀፍ እና የማስወገድ ከፍተኛ ብቃት ያለው ሲሆን፤ አየር ኃይሉ ቀደም ሲል ከታጠቃቸው Su-30፣ Su-27 እና ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶች ጋር የተቀናጀ የሰማይ ጥበቃ መረብ ለመፍጠር ያስችላል። የማንኛውም አየር ኃይል ጥንካሬ መሠረቱ የቴክኖሎጂው ጥራት ብቻ ሳይሆን የሰው ኃይሉ ብቃት ነው። ለዚህም ስኬት አጋዥ እንዲሆን የበረራ ባለሙያዎችን፣ የቴክኒክ እና የምህንድስና ባለሙያዎችን የሚያሰለጥንበት አካዳሚ በዘመናዊ የበረራ ልምምድ መሳሪያዎች (Flight Simulators) እና ላቦራቶሪዎች እንዲደራጅ ተደርጓል። ፓይለቶች እና የጥገና ባለሙያዎች ወቅታዊውን ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና የስልት ደረጃ ጠብቀው እንዲሰለጥኑ በመደረጉ በከፍተኛ ደረጃ ፕሮፌሽናል የሆነ የሰው ኃይል መገንባት ተችሏል። ዛሬ ወደ ዘመናዊ አሰራር የሚደረገው ሽግግር የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን እና የሎጂስቲክስ ቅልጥፍናንም ያካተተ ነው። ቢሾፍቱን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ የአየር ኃይል ጣቢያዎች በዘመናዊ መገናኛዎች፣ የበረራ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች እና የደህንነት ሥርዓቶች እንዲደራጁ ተደርገዋል። የመረጃ ልውውጥን እና የዕዝ ሥራዎችን በዲጂታል መንገድ የሚያቀናጁ የቴክኖሎጂ ሥርዓቶችንም መዘርጋት ተችሏል። ከዚህ ባሻገርም ኢትዮጵያ በኤሮስፔስ እና በመከላከያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በሀገር ውስጥ የሰው አልባ አውሮፕላኖች ማምረት እና መገጣጠም መጀመሯ ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። እንደ ኤሮ ዓባይ (Aero Abay) እና ስካይ ዊን (Sky Win Aeronautics) ያሉ የድሮን ማምረቻ ፋብሪካዎች እውን መሆን ሀገሪቷ ከውጭ ጥገኝነት ወጥታ የራሷን የቴክኖሎጂ አቅም እንድትገነባ መንገድ ከፍቷል። ፋብሪካዎቹ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የሚመሩ በመሆናቸው ለከፍተኛ የቴክኖሎጂ ሽግግር ትልቅ መደላደል የፈጠሩ ሲሆን፤ ለስለላ፣ መረጃ ለመሰብሰብ፣ ተፈላጊውን ዒላማ ነጥሎ ውጤታማ እርምጃ ለመውሰድ እንዲሁም ለስልታዊ ወታደራዊ አገልግሎቶች የሚውሉ ድሮኖችን በማምረት ላይ ናቸው። እነዚህ የሀገር ውስጥ ውጤቶች የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባለፈ በዘመናዊ ግብርና፣ በሜጋ ፕሮጀክቶች ጂኦስፓሻል ክትትል፣ በተፈጥሮ አደጋዎች የጉዳት መጠን ዳሰሳ እና በአስቸኳይ የህክምና ቁሳቁሶች ማድረስ ላይ ከፍተኛ ሲቪል አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጥንካሬ የአገራችንን ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ዋስትና ነው። ሱ-35 አውሮፕላኖች እና ዘመናዊ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች መታጠቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሀገራዊ የኢኮኖሚ፣ የኃይል እና የሎጂስቲክስ ማዕከላትን ከአየር ላይ ስጋቶች በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ያስችላል። በወታደራዊ ስትራቴጂ ውስጥ ጥንካሬን ማሳየት ራሱ ግጭቶችን የመከላከል ትልቅ ሚና እንዳለው ሁሉ፣ ኢትዮጵያ የላቀ የአየር የበላይነት አቅም መገንባቷ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሊነሱ የሚችሉ ስጋቶችን በቅድሚያ ለመከላከል የማይደፈር አቅም ይሆናሉ። ይህ ጠንካራ የመከላከል አቅም መኖሩ ኢትዮጵያ በቀጣናው የደህንነት እንቅስቃሴዎች ላይ የሰላም እና የመረጋጋት አምባሳደር ሆና እንድትቀጥል የሚያስችላት ሲሆን፤ በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ወቅትም አስፈላጊውን የአየር ክልል ጥበቃ እና ደህንነት ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጁነትን ፈጥሯል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል እያደረገ ያለው የዘመናዊነት ሽግግር የታሪክ አደራውን ከነገው የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ያጣመረ ነው። በሰው ኃይል ልማት፣ በሀገር ውስጥ የድሮን ማምረቻዎች፣ በዘመናዊ የሱ-35 የውጊያ አውሮፕላኖች ትጥቅ እና ቀልጣፋ የአሰራር ሥርዓት ላይ የተደረጉት ተጨባጭ ለውጦች ተቋሙን በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ካሉ ጠንካራ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ የአየር ኃይሎች አንዱ አድርገውታል። ይህ ጉዞ የኢትዮጵያን ሰማይ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ እና ለአካባቢው ቀጣና ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋት እና የደህንነት ዋስትና የሚሰጥ ስትራቴጂካዊ ምሽግ ሆኗል።      
ልዩ ዘገባዎች
ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር 
Oct 9, 2026 977
ነጋሪ መጽሔት የዓባይ ውሃ አጠቃቀምና የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት በስፋት ተንትናለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ፣ “የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም” በማለት ሀገሪቱ የባሕር መዳረሻ እንድታገኝ በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ይህ ጥረት በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ተጠቃሚነትና በ“ሰጥቶ መቀበል” መርሕ እንደሚመራ በማስገንዘብ፣ ጉዳዩን ከአፍሪካ ቀንድ፣ ከቀይ ባሕርና ከመካከለኛው ምሥራቅ እየተለወጡ ካሉ የጂኦፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው አቅርበዋል። መጽሔቷም በመስከረም 2019 ዓ.ም. እትሟ “የኢትዮጵያ የትንሳኤ መንገድ፡ ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር ፖለቲካ የዘለቀው ፍጥጫ” በሚል ርዕስ ባቀረበችው ትንታኔ፣ የውሃ ሀብት፣ የባሕር መዳረሻ፣ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችና የቀጣናዊ ደኅንነት ጉዳዮች በሀገራት መካከል ባለው የኃይል አሰላለፍ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ዳስሳለች። እንደ መጽሔቷ ትንታኔ፣ ዓባይና ቀይ ባሕር በተፈጥሮ የተለያዩ የውሃ አካላት ቢሆኑም፣ በዘመናዊው የጂኦፖለቲካ ስሌት ውስጥ በውሃ አጠቃቀም፣ በኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ በባሕር መዳረሻና በደኅንነት ጉዳዮች የተሳሰሩ ናቸው። የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያና ለተፋሰሱ ሀገራት ለኃይልና የልማት ጥቅም ሲኖረው፣ ቀይ ባሕር ደግሞ አፍሪካን፣ እስያንና አውሮፓን የሚያገናኝ ወሳኝ የዓለም አቀፍ የንግድና የባሕር መተላለፊያ ነው። በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የዓባይ ውሃን በፍትሐዊነትና በጋራ ተጠቃሚነት የማስተዳደር ጥያቄና የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በቀጣናው የፖለቲካና የደኅንነት ስሌቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ መጽሔቷ በስፋት ተንትናለች። የ1929 እና የ1959 የውሃ ስምምነቶች የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም በበቂ ሁኔታ እንዳልተካተቱ በመግለጽ፣ የወንዙ ውሃ አጠቃቀም በፍትሐዊነት፣ በትብብርና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ ማዕቀፍ መመራት እንዳለበት አመልክታለች። ኢትዮጵያ በ1993 ዓ.ም በኋላ የባሕር በር መዳረሻዋን ማጣቷን ተከትሎ፣ ጉዳዩ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ ከብሔራዊ ደኅንነትና ከረጅም ጊዜ የልማት ፍላጎት ጋር እንደተያያዘ መጽሔቷ አትታለች። የባሕር በር መዳረሻ ማግኘት የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ የወደብ አማራጮችን ለማስፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ወሳኝ መሆኑንም አብራርታለች። በሌላ በኩል፣ ቀይ ባሕር ከእስያ፣ ከአፍሪካና ከአውሮፓ የንግድ መስመሮችን የሚያገናኝ ስትራቴጂካዊ የባሕር መተላለፊያ በመሆኑ፣ በአካባቢው ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከአካባቢያዊ ግንኙነቶች ባለፈ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ፍሰትን ይነካል። መጽሔቷ የቀይ ባሕር የጂኦፖለቲካ አስፈላጊነት ከስዊዝ ቦይና ከባብ-ኤል መንደብ የባሕር መተላለፊያ ጋር በማያያዝ የዳሰሰች ሲሆን፣ በአካባቢው የሚካሄዱ የኃይል ፉክክሮች የንግድና የደኅንነት ስጋቶችን እንደሚያባብሱ ተንትናለች። መጽሔቷ በትንታኔዋ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ከቀጣናው ሀገራት የፖለቲካ አቋሞች ጋር በማያያዝ የተለያዩ ትንታኔዎችን አቅርባለች። ሆኖም እነዚህ በመጽሔቷ የቀረቡ የፖለቲካ ትንታኔዎች ሲሆኑ፣ የተጠቀሱ አቋሞችንና ክሶችን ከተረጋገጡ እውነታዎች መለየት ያስፈልጋል። መጽሔቷ በዓባይ ውሃ አጠቃቀምና በባሕር መዳረሻ ጉዳይ ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ በድርድርና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ መፍትሔ ማግኘት እንዳለባቸው አጉልታለች። የውሃ ሀብትን በፍትሐዊነት ማስተዳደርና የባሕር መዳረሻ ጉዳይን በሰላማዊ ስምምነት መፍታት ለቀጣናዊ መረጋጋት፣ ለኢኮኖሚ ትብብርና ለዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆናቸውን በትንታኔዋ አመልክታለች። የመጽሔቱ ሊንክ https://www.ena.et/web/negari/w/negari_9696604
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 907
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 681
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 688
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 110127
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 83169
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 60752
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 58374
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 41301
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 41270
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 40654
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 39156
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 110127
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 83169
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 60752
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 58374
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ታሪክ የማይዘነጋው ክህደት እና የኢትዮጵያዊያን አኩሪ ጽናት!
Nov 3, 2026 56
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት መሆኑ ይታወቃል። ለዚህ ጀግና እና ህዝባዊ ሰራዊት ተገቢውን ክብርና ምስጋና መስጠት ሲገባ ክህደት ሲፈፀምበት ግን እጅግ አሳዛኝ ነው።ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በባንዳዎች ድንገት የተፈፀመበት ክህደት ታሪክ የማይዘነጋው የክህደት ጥግ ነው። በመሆኑም የዛሬው እለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት በባንዳዎች የተፈጸመበትን ታሪካዊ ክህደት እና በጽናት የታለፈበት የሚታወስበት መሆኑ ይታወቃል።   እለቱ ሲታወስ ሰራዊቱ ለአመታት የህዝብን ሰላም፣የሀገር ዳር ድንበር እና የልማት ስራዎችን በሚያግዘው ህዝባዊ ሰራዊት ላይ በውስጥ ባንዳዎች አረመኔያዊ ድርጊትና ታሪክ የማይረሳው ክህደት የተፈፀመበት በመሆኑ የሚዘከርበት ነው። በዕለቱ የተፈጸመው ድርጊት የትኛውንም ሰብአዊነትና ወታደራዊ ስነ-ምግባር ያልተከተለ የአረመኔያዊ ድርጊት ነበር ማለት ይቻላል። በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሀገር ክብርና ሉአላዊነት ለዜጎች ፍቅርና አክብሮት ሲል የከፈለው መስዋዕትነት መቼም ቢሆን ሊረሳ አይችልም።   የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት በማውገዝ ከሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ምሰሶ ነው በማለት ከጎኑ በመሰለፍ እገዛና ድጋፉን በተግባር አሳይቷል። ህዝቡ በከሃዲዎቹ ድርጊት በማዘንና በመቆጨት ሀገር ለማፍረስ የተንቀሳሰቀውን የጥፋት ቡድን መመከት ችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወታደራዊ ልብሳቸውን ለብሰው ወደ ግንባር በመዝመት ሀገራቸውን ከጥፋት የታደጉበት አጋጣሚም የዚሁ ታሪክ አካል ነው። በመሆኑም ጥቅምት 24ን ስንዘክር፣ በዕለቱ ሕይወታቸውን ላጡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና ዜጎች ክብር በመስጠት፣ እንዲህ አይነት ክህደት ሀገር የማፍረስ እቅድ በመሆኑ እንዳይደገም ትውልድ እያወቀው እንዲሄድ በማድረግ ይሆናል።ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ተገቢውን ክብርና ፍቅር በመስጠት ሁላችንም ሀገራዊ አደራችንን መወጣት ይኖርብናል።
ዓለም አቀፋዊ የሰላም አምባሳደርነት: የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰላም ማስከበር ልዕልና
Nov 3, 2026 81
የመከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበርን ከማስከበር ባሻገር፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር በዓለም አቀፍ መድረክ የሰላም ዋስትና ሆኖ በማገልገል የጎላ ታሪክ ባለቤት ነው። ሠራዊቱ በተሰማራባቸው የሰላም ማስከበር ሀገራት ሁሉ የላቀ ስነ-ምግባርና ፍጹም የሰብዓዊነት እሴት በማሳየት አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ከበሬታን በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ አትርፏል። ይህ ዓይነቱ የጀግንነት ታሪክ ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ መድረኮች ላይ ያላትን ተሰሚነት እና ክብር በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ አድርጎታል። የሀገሪቱ የሰላም ማስከበር ተሳትፎ ታሪካዊ መነሻ የሚጀምረው እ.እአ. በ1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ በኮሪያ ልሳነ ምድር በተሰማራበት የሰላም ማስከበር ተልእኮ ሲሆን፣ የሠራዊቱ አባላት በነበራቸው የማይናወጥ ፅናት እና አስደናቂ የወታደራዊ ጥበብ ዓለምን ያስደመሙበት ወቅት ነበር። በወቅቱ የነበረው የሰላም ማስከበር ስራ የሰራዊቱን ከፍተኛ ወታደራዊ ዲሲፕሊን የሚያሳይ ታሪክ ሆኖ አልፏል። ከዚህ በተጨማሪ፣ እ.አ.አ በ1960 የኮንጎ ሪፐብሊክ ከነፃነት ማግስት የገጠማትን የሀገር ውስጥ ቀውስ ለመፍታት የተመደቡ የመጀመሪያዎቹ የሰላም አስከባሪዎች በመሆን የተሰጣቸውን ከባድ ተልእኮ በላቀ ድል አጠናቀዋል። ከዚያም ባለፈ ሰራዊቱ በሩዋንዳ የተከሰተውን አስከፊ ሰብዓዊ እልቂት ለመግታት በመሃል በመግባት የበርካታ ንጹኃንን ሕይወት መታደግ የቻለ የሰብዓዊነት አርአያ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአሁኑ ወቅትም ቢሆን በአፍሪካ ውስጥ ለሚታዩ ግጭቶች ፍጹም እውነተኛ የሰላም አለኝታ መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥላ ሥር በደቡብ ሱዳን በተሰማራባቸው የሰላም ማስከበር ግዳጆች ላይ ገለልተኛ፣ እውነተኛና ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በማረጋገጥ የተሰጠውን ዓለም አቀፍ ተልእኮ በብቃት እያከናወነ ይገኛል። በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ውስጥ ቀጣናዊ ስጋት የሆነውን አሸባሪ ቡድን በመዋጋትና የመንግሥትን መዋቅር ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ረገድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የከፈለው መስዋዕትነት በታሪክ መዝገብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ አለው። ሠራዊቱ በቁልፍ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ ሰላምን በማስከበር የአካባቢው ማኅበረሰብ በተረጋጋ ሁኔታ ኑሮውን እንዲኖር አስችሏል። ሠራዊቱ የቀጣናውን ተለዋዋጭ የደኅንነት ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የተሰጠውን ተልዕኮ በአስተማማኝ ሁኔታ እየተወጣ ሲሆን፣ አህጉራዊ ችግሮችን በሀገር በቀል አቅምና መፍትሔዎች ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በተግባር ማረጋገጡን ቀጥሏል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም