ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት መልህቅ በመሆኗ በቀይ ባህር አካባቢ ህልውና እንዲኖራት መፈለጓ ተገቢ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት መልህቅ በመሆኗ በቀይ ባህር አካባቢ ህልውና እንዲኖራት መፈለጓ ተገቢ ነው
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና ደኅንነት መልህቅ እንደመሆኗ በቀይ ባህር አካባቢ ህልውና እንዲኖራት መፈለጓ ተገቢ ነው ሲሉ በአፍሪካ የደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ፖል ሲሞን ሃንዲ (ዶ/ር) ገለጹ።
ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ብቻ ሳይሆን በአስተዳደርና ቢዝነስ ዘርፍም ገንቢ ሽግግር አድርጋለች ብለዋል።
በአፍሪካ የደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ፖል ሲሞን ሃንዲ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የጣና ፎረምን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በማስተናገድ የቀጣናው መልህቅ መሆኗን አሳይታለች።
ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ላይ ገንቢ ሚና እየተወጣች መሆኑን ገልጸው፤ ችግሮችም በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ትፈልጋለች ብለዋል።
የባህር በር ፍላጎት የኢትዮጵያ ቋሚ ፍላጎት ነው ያሉት ፖል ሲሞን ሃንዲ (ዶ/ር)፤ የመንግሥት ሰላማዊ መንገድን መከተል የሚደገፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት መልህቅ እንደመሆኗ በቀይ ባህር አካባቢ ውክልና እንዲኖራት መፈለጓ ተገቢ መሆኑን ገልጸው፤ ፍላጎቷን ከቀንዱ ሀገራት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ማግኘት አለባት ብለዋል።
በናይጀሪያ የኦባፌሚ አዎሎዎ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ቻርለስ ዑኬጄ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት ከሀገራት ጋር በውይይትና በንግግር ሊፈታ ይገባል ብለዋል።
ባለፉት አስር ዓመታት በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ብቻ ሳይሆን በአስተዳደርና ቢዝነስ ዘርፍም ገንቢ ሽግግር አድርጋለች ብለዋል።
የጣና ፎረም የኢትዮጵያን መንግስት፣ ህዝቡንና የአፍሪካ ሀገራትን አሸናፊ የሚያደርግ ወሳኝ መድረክ መሆኑንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ታላቅ ሀይል መሆኗን ገልጸው፤ የባህር በር ፍላጎቷን ማሳካትና ሁሉንም አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ ከጎረቤት ሀገራት ጋር መወያየት አለባት ብለዋል።