የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመጀመሪያ አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ያካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመጀመሪያ አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ያካሄዳል
ድሬዳዋ፤ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 4ተኛው የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የመጀመሪያውን አስቸኳይ ጉባኤ ነገ እንደሚያካሂድ አፈ-ጉባኤ ጫልቱ ሁሴን ተናገሩ፡፡
አፈ-ጉባኤዋ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፣ ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባኤው የተለያዩ ደንቦችና ሹመቶችን ያጽድቃል።
አክለውም ምክር ቤቱ የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎች ሹመት እንደሚያጸድቅ ጠቅሰው፣ የፕሮፐርቲ ታክስና ሌሎች ደንቦችም ይጸድቃሉ ብለዋል።