ቀጥታ፡

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስትል ዩናይትድ ከኤቨርተን ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ  ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በኒውካስትል ዩናይትድ እና በኤቨርተን መካከል ዛሬ ይደረጋል።

ጨዋታው ምሽት አምስት ላይ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ይካሄዳል።

ባለሜዳው ኒውካስትል ዩናይትድ በ11 ነጥብ 12ተኛ ደረጃን ይዟል። 

ተጋጣሚው ኤቨርተን በ10 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ59ኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 58 ጨዋታዎች ኤቨርተን 24 ጊዜ ድል ሲቀናው ኒውካስትል ዩናይትድ በ21ዱ አሸንፏል። በቀሪ 13 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

ኤቨርተን በ58ቱ ጨዋታዎች ላይ 86 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ  ኒውካስትል በበኩሉ 82 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል።

ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ኤቨርተን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይፋለማል።

ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት በካራባኦ ካፕ ባደረጉት ጨዋታ ኤቨርተን ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፉ የሚታወስ ነው።

የ36 ዓመቱ ጆን ብሩክስ   ጨዋታውን በዋና ዳኝነት እንዲመሩ ተመድበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም