ቀጥታ፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ድል ተቀዳጁ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ አገራት በተካሄዱ  ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል።

በቻይና ሃንግዡ ማራቶን የሴቶች ውድድር ኩፍቱ ጣሂር አንደኛ በመውጣት ድል ተቀዳጅታለች።

በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ማራቶን ሚኪያስ ባረጋ አንደኛ በመውጣት ሲያሸንፍ፣ አበባው ሙንየ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በኢስታንቡል ማራቶን በሴቶች ውድድር ካሳነሸ አየነው አንደኛ ወጥታለች። አዝመራ አብርሃ ሁለተኛ እና ድርቤ ሂርቆ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።




በሌላ በኩል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአምስት ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች ፈይሳ ቡሎ አሸናፊ ሲሆን፣ ገብሩ አብርሃ እና ጫላ ጉደታ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሴቶች ሃና መኮንን ስታሸንፍ፣ ማርታ ቦሬማ እና ሴና ተሰማ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል።

በአቡዳቢ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች ሰውመሆን አንተነህ አንደኛ ሲወጣ፣ አባይነህ አየል ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።




በሴቶች አልማዝ ባራኪ ሁለተኛ፣ መገርቱ ሚዴቅሳ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በስፔን በተካሄደው የሴባስቲያን ሀገር አቋራጭ ውድድር ወገኔ አዲሱ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ መጨረሱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም