ቀጥታ፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

ድሬደዋ፣ ጥቅምት 24/2019(ኢዜአ)፡- የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 4ተኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት አስቸኳይ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

ጉባኤው የምክር ቤቱን 4ተኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት የመስራች መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ መካሄድ ጀምሯል።


 

ጉባኤው የድሬዳዋ አስተዳደር ንብረት ታክስ ረቂቅ ደንብ ላይ እየተወያየ ይገኛል።

አስቸኳይ ጉባኤው ረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ የሚያፀድቅ ሲሆን የተለያዩ ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ ተመላክቷል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም