ቀጥታ፡

ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀመሩ

ደብረ ብርሃን፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባውን ዘመናዊ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በይፋ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ መርሃግብሩ የክልሉ፣ የዞንና የከተማው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።


 

ማዕከሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ለህብረተሰቡ የሚያቀርባቸውን የተለያዩ አገልግሎቶች በአንድ ማእከል በማሰባሰብ፤ የህዝብን እንግልትና ውጣ ውረድ በዘላቂነት የሚያስቀር፣ ፈጣን፣ ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

በክልሉ ሕዝብን ከእንግልት ታድገው ዘመናዊ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ መስተንግዶ ለመስጠት የሚያስችሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተገንብተው ለሥራ እየበቁ ይገኛሉ።


 

ማዕከላቱ የተለያዩ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን በአንድ ጥላ ሥር በማሰባሰብ የዜጎችን ጊዜና ጉልበት የሚቆጥቡና የአስተዳደር በደልን የሚያስቀር አዲስ ምዕራፍ እየከፈቱ መሆናቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም