ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ሴኔጋል ድል ቀንቷታል
Jul 6, 2025 46
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29 /2017 (ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አንድ ሁለተኛ መርሃ ግብር ሴኔጋል ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች። በኤል ባቺር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ማማ ዲዮፕ እና ንጌናር ንዳዬ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል። በጨዋታው ሴኔጋል በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ላይ ከፍተኛ ብልጫ ወስዳለች። ውጤቱን ተከትሎ ሴኔጋል ምድብ አንድን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች። በዚሁ ምድብ ትናንት በተካሄደ የመጀመሪያ ጨዋታ አዘጋጇ ሞሮኮ ከዛምቢያ ሁለት አቻ ተለያይታለች።
የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ሥርዓት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ገንቢ ሚናችንን እንወጣለን - ኢዜማ
Jul 6, 2025 51
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ዴሞክራሲ ሥርዓት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ገንቢ ሚናውን እንደሚወጣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ "በሀሳብ እንፎካከራለን፤ ስለሀገር እንተባበራለን" በሚል መሪ ሀሳብ ያካሄደው 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቋል። ከሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በተካሄደው የፓርቲውን ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሲያጠናቅቅም የፓርቲውን ሊቀ-መንበር እና ምክትል ሊቀ-መንበር መርጧል። በዚህም መሰረት ሙሉዓለም ተገኘወርቅ(ዶ/ር) ሊቀመንበር፣ አቶ ማዕረጉ ግርማ ምክትል ሊቀ መንበር እንዲሁም አቶ ዋሲሁን ተስፋዬን የፓርቲው ዋና ጸኃፊ በማድረግ ሰይሟል። በተጨማሪም የፋይናንስና ትሬዠሪ፣ የሕገ-ደምብና ትርጉም እንዲሁም የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ኃላፊዎችን መርጧል። በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ምክትል መሪ አርኪቴክት ዮኃንስ መኮንን÷ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ባህል ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ፓርቲያቸው በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በዳበረ የዴሞክራሲ ባህል የተሻለና ሰላማዊ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲኖራት ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች ጋር በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በቀጣይም ጠንካራ ተፎካካሪና አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ ለመቅረብ ተመሳሳይ ፍላጎት ካላቸው ሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑንም አንስተዋል። ለዚህም የፓርቲው አመራርና አባላት ፍጹም ሰላማዊ የፖለቲካ አካሄድን በመከተል ለተሻለ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ አብራርተዋል። የፖለቲካ ፓርቲ የሪዮተ-ዓለማዊ ሃሳብ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ በሚያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞችና ፍላጎቶች ላይ በትብብር መስራት እንደሚያስፍልግም አስገንዝበዋል። በፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት በማስቀደም ለዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት መምከሩን ተናግረዋል። የፓርቲው ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀ መንበር፣ ዋና ጸኃፊ፣ የፋይናንስና ትሬዠሪ፣ የሕገ-ደምብና ትርጉም እንዲሁም የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኃላፊዎች ምርጫ ሂደትም የውስጠ ዴሞክራሲ ባህል ግንባታን ባሳየ መልኩ መከናወኑን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) በሊቀ-መንበርነት የተመረጡት ሙሉዓለም ተገኘወርቅ(ዶ/ር)÷ ለተሻለ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህል ግንባታ የበኩላቸውን ገንቢ ሚና በመወጣት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Jul 6, 2025 59
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከብሪክስ መሪዎች ጋር በሪዮ ዲ ጄኒሮ በዚህ አመቱ ጉባኤ ላይ ተገኝተናል ብለዋል። የበለጠ እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን ሲሉም ገልጸዋል በመልዕክታቸው። የብሪክስ መድረክ የጋራ የልማት እና አለምአቀፋዊ ትብብርን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ሆኖ ቀጥሏል ነው ያሉት።
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እርስ በእርስ የተሳሰረና የዳበረ አሰባሳቢ ትርክት ለማስረጽ የጎላ ሚና እንዳለው ተመላከተ
Jul 6, 2025 42
ሀዋሳ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በእርስ ትስስርንና ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም የዳበረ አሰባሳቢ ትርክት ለማስረጽ የጎላ ሚና እንዳለው ተመላክቷል። የ2017 ዓ/ም ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች ሀዋሳ ከተማ የገቡ ሲሆን የተለያዩ በጎ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አስፋው ጎኔሳ አገልግሎቱ የእርስ በእርስ ትስስርን ለማጠናከር ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ ይህም እርስ በእርስ የተሳሰረና የዳበረ አሰባሳቢ ትርክት እንዲሰርፅ የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችም ከሰብዓዊ ተግባራቶቻቸው ጎን ለጎን የየአካባቢውን ባህል፣ ቋንቋና ሌሎች መገለጫዎች በውል እንዲገነዘቡና የጋራ መልካም እሴቶችን እንዲያዳብሩ ዕድልን የሚሰጥ ኩነት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ እመቤት ኢሳያስ፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ወጣቱ ትውልድ ሀገሩን ለመገንባት የሚያስችለውን አንድነት እንዲፈጥር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ ወጣቶቹ በሀዋሳ ቆይታቸው በየአካባቢያቸው ያለውን መልካም እሴት ለሌሎች የማስተዋወቅ፤ እነርሱም የሲዳማን የአብሮነትና የሠላም እሴት በሚገባ ተረድተው የሚመለሱበት አጋጣሚን እንደሚፈጥርም አመልክተዋል፡፡ ወጣቶቹ በቆይታቸው የፅዳት፣ የደም ልገሳ፣ አረጋውያንን የመንከባከብ፣ ህሙማንን የመጠየቅና ሌሎች በጎ ተግባራትን እንደሚከናውኑም ጠቁመዋል፡፡ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች በጎ-ፈቃድ አገልግሎት ዴስክ ባለሙያ የሆኑትና የቡድኑ አስተባባሪ እንደገና ፍቃዱ ይህ ኩነት እንደ ሀገር ለአራተኛ ጊዜ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በአጠቃላይ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ 102 የሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በሁለት ቡድን ተከፍለው ወደተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ አገልግሎቱን እየሰጡ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡ ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መካከል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመጣው ወጣት ደሳለኝ ማሞ እንደገለፀው፤ በጉዟቸው የተለያየ ባህልና እሴት እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ እንዲገነዘቡ ዕድል መፍጠሩን ገልጿል፡፡ በሀዋሳ ከተማ ተገኝቶ ደም መለገስ መቻሉ ልዩ ስሜት እንዳሳደረበት የገለፀው ወጣቱ ደም በመለገስ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት በመታደጌ ትልቅ ደስታ ይሰማኛል ብሏል፡፡ የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ከተማ ፍቅር ሀይቅ ዳርቻ የጽዳት ስራ ያከናወኑ ሲሆን በቀጣይም የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡
በኮሞሮስ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል - ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ
Jul 6, 2025 82
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ በኮሞሮስ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ገለጹ። ኮሞሮስ ነፃነቷን የተጎናጸፈችበትን 50ኛ ዓመት የነፃነት በዓል የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች በተገኙበት በድምቀት አክብራለች። በክብረ በዓሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ፣ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን፣ የሞሪታንያ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ኡልድ ጋዙዋኒ እንዲሁም የሴኔጋል፣ የማዳጋስካር፣ የሞሮኮ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ የፈረንሳይና የሌሎች ሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል። በዓሉን የታደሙት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ በኢትዮጵያ እና በኮሞሮስ መካከል ያለው ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራል ብለዋል። ኢትዮጵያ በኮሞሮስ የነፃነት በዓል መሳተፏ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ መምጣቱን ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የቆየ ወዳጅነት በማጠናከር አህጉራዊ ትስስርና አንድነት እንዲጎለብት እንደምትሰራ ተናግረዋል። በበዓሉ ላይ የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ባስተላለፉት መልዕክት በፀረ ቅኝ ግዛት ትግል ሂደት መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ክብር ይገባቸዋል ብለዋል። ከነፃነት በኃላ ባለፋት 50 ዓመታት የተገኙ ለውጦች ሀገሪቱን ወደ ተሻለ የታሪክ ምዕራፍ እንዳሸጋገራት መናገራቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። በትምህርት፣ በጤና፣ በገቢ፣ በቱሪዝም እና በመሰረተ ልማት ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እንደተመዘገቡም ነው ፕሬዚዳንቱ የገለጹት። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2023/2024 ለ1 ዓመት ያክል የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በመሆን ያገለገሉት ፕሬዚዳንቱ ኮሞሮስ ባለፋት ጥቂት አመታት ለአፍሪካ ሰላም፣ ፀጥታና አንድነት መረጋገጥ የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች ነው ብለዋል። አሁን ጊዜው የተሻለ የፖለቲካ መረጋጋት የተገኘበት በመሆኑ ህዝቡ ትኩረቱን ወደ ልማት ማድረግ እንደሚገባውም ነው ያስገነዘቡት። በተለይ ወጣቱ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚው በመግባት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ዘመናዊ፣ አስተማማኝና የላቀ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል። ኮሞሮስ ቀላል የማይባል ገቢ ከዳያስፖራው እንደምታገኝ ፕሬዚዳንቱ ጠቁመው ዳያስፖራዎች በሀገሪቱ የተፈጠረውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሀገራቸው ኢንቨስት በማድረግ የወቅቱ የኮሞሮስ ጥያቄ የሆነውን ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲያፋጥኑም ጠይቀዋል። ኮሞሮስ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣችው በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኔ 29/1967 ዓ.ም ነው።
ፖለቲካ

ወጣቶች አስተሳሳሪ ትርክትን በመላበስ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለሚያጠናክሩ ተግባራት ትኩረት ሊሰጡ ይገባል - አቶ አደም ፋራህ
Jul 6, 2025 97
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ ወጣቶች አስተሳሳሪ ትርክትን በመላበስ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ ይበልጥ እንዲያተኩሩ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ አስገነዘቡ። ”ወጣቶች በሀገርና በሀገረ-መንግሥት ግንባታ ውስጥ ያላቸው ሚና” በሚል ርዕስ በተከታታይ ሲካሄድ የቆየው ውይይት የማጠቃለያ መድረክ የሰላም ሚኒስቴር ከብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጋር በመተባበር “ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴንም እወጣለሁ” በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል። አቶ አደም ፋራህ በውይይት መድረኩ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በምጣኔ ሃብት፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ እና በዲፕሎማሲ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ራዕይ አስቀምጣ እየሰራች ትገኛለች። ይህንን ራዕይ ለማሳካት አሻጋሪ ዕሳቤዎችና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ይዛ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል። ኢትዮጵያ ሰፊ የህዝብ ቁጥር ያላት ከዚህ ውስጥም አብዛኛው ወጣት እንዲሁም የተፈጥሮ ሃብቶቿ በአጭር ጊዜ ለመበልጸግ ካሏት ሰፊ እድሎችና አቅሞች መካከል መሆናቸውን አንስተዋል። መንግስት ወጣቱን ተጠቃሚ ለማድረግና በምጣኔ ሃብት እድገት ውስጥ በማሳተፍ የወጣቱን ህልም የሚያለመልሙ እቅዶች በመተግበር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ወጣቶች በብሔራዊና አለም አቀፍ ደረጃ ወቅቱ የሚፈልገውን የስራ ገበያ ክህሎት እንዲይዙ በኮደርስ ስልጠናና ሌሎች የትምህርትና ስልጠና ዘርፎች ኢንቨስት እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት። ወጣቶች የግል ራዕያቸውን ከሀገር ራዕይ ጋር በማጣጣም ማዘጋጀት፣ ሀገርን በአርበኝነት ማገልገል፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር ለሀገራቸው ማበርከት ከሚገባቸው ቁልፍ ጉዳዮች መካከል መሆናቸውን ዘርዝረዋል። አስተሳሳሪ ትርክትን በመላበስ የማህበረሰብን፣ የአካባቢንና የብሔርን የእርስ በእርስ ግንኙነት የሚያጠናክሩ ስራዎችን እንዲሰሩ አስገንዝበዋል። በተመሳሳይ በጋራ ራዕይ በመመራት ለሀገርና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ቁልፍ ሚና በቁርጠኝነት እንዲወጡ ጠይቀዋል። ግጭትን የሚያባብሱ ግለሰቦችና ማህበራዊ ሚዲያ የጥላቻና ሃሰተኛ ንግግሮችን በምክንያታዊነት በመጠየቅ ለዘላቂ ሰላም የበኩሉን እንዲወጣም በአጽንኦት አንስተዋል። ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ያላትን የመበልጸግ ዕድልን እውን ለማድረግ ወጣቱ ያለውን ጉልህ ድርሻ በመረዳት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው፤ ወጣቶች ኢትዮጵያ በተለያየ ወቅት የገጠሟትን ፈተናዎች ለማሻገር የተጫወቱት ሚና ጉልህ መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም በማህበራዊ ትስስርና ሀገራዊ አንድነት ያላቸውን ቁልፍ ሚና በመገንዘብ ልዩነቶች በሰለጠነ መንገድ በውይይት እንዲፈቱ ሚናቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል ነው ያሉት። የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት አክሊሉ ታደሰ የተካሔዱ ውይይቶች በፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብትና ማህበራዊ ዘርፎች የወጣቱን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እንዲሁም በሚስተዋሉ ክፍተቶች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል። በተመሳሳይ በዘላቂ ሰላም ግንባታ ጥልቅ ውይይት የተደረገበትና ቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ ከመግባባት የተደረሰበት እንደሆነም ገልጸዋል። በውይይት መድረኩ ላይ አስተያየት የሰጡ ወጣቶች በበኩላቸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበሩ የሚገኙ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ወጣቱን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸውን አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር ተወያዩ
Jul 6, 2025 61
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር 55 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገናል ብለዋል። ግንኙነታቸው በሁኔታዎች ሁሉ እንደማይቀያየር አጋሮች (all weather strategic partners) ባለፉት ሰባት ዓመታት ትብብራችን ጉልህ ፍሬዎችን አፍርቷል ነው ያሉት። ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና አይሲቲን ባካተቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዓምዶች ላይ ትኩረታችን እንዳለ ሆኖ ሌሎች የትብብር መስኮችን ለማጠናከርና እንደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ ሎጂስቲክስ እና ንጹሕ የኃይል ምንጮች ልማት ላይ ያለንን ዕምቅ ዐቅም ለመመልከትም ችለናል ሲሉም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም ልዩነት አያግድም - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
Jul 6, 2025 125
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም ልዩነት እንደማያግድ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ "በሀሳብ እንፎካከራለን፤ ስለሀገር እንተባበራለን" በሚል መሪ ሃሳብ ከሰኔ 28/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል። የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊ የስራ ኃላፊዎችና አባላትም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሸገር ፓርክ ውስጥ ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፖለቲካ ባህላችን በዜጎች ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገር ይኖርበታል ብለዋል። የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅም ከመወነጃጀል የጸዳ የፖለቲካ ባህልን በመገንባት በሀገር ጉዳይ ላይ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ርዕዮተ-ዓለማዊ የሃሳብ ልዩነት ተጠባቂና ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ ይህም የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በትብብር ከመስራት እንደማያግድ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲም የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለማዊ የሃሳብ ልዩነት ሳይገድበው ከገዥው ፓርቲ ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያውያንም በሀገራቸው ብሔራዊ ጥቅምና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር እንዲኖረው በትብብር መስራት እንደሚኖርባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ አባል ግርማ ሰይፉ ፓርቲው የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ወደ ሰለጠነ ምዕራፍ ለማሸጋገር ገንቢ ሚናውን እየተወጣ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያውያንም በሀገራቸው ጉዳይ ከሚፎካከሩባቸው ይልቅ የሀገራቸውን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ የሚተባበሩባቸው በርካታ አጀንዳዎች ያሏቸው ህዝቦች መሆናቸውን ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የሚያጋጥማትን ጫና ለመቀነስ ኢትዮጵያ እየሰራችበት የሚገኝ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የልማት አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል። የጅማ ዞን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ አባል ታደሰ ተፈራ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የጋራ የልማት አጀንዳችን ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው የፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሸገር ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖራቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሰኔ 20/2017 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
ወጣቶች በጋራ ራዕይ በመመራት ለሀገር ግንባታ ያላቸውን ቁልፍ ሚና ሊወጡ ይገባል - አቶ አደም ፋራህ
Jul 6, 2025 81
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ ወጣቶች በጋራ ራዕይ በመመራት ለሀገር ግንባታ ያላቸውን ቁልፍ ሚና እንዲወጡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ጥሪ አቀረቡ። ”ወጣቶች በሀገርና በሀገረ-መንግሥት ግንባታ ውስጥ ያላቸው ሚና” በሚል ርዕስ በተከታታይ ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ማጠቃለያ የሰላም ሚኒስቴር ከብልጽግና ወጣቶች ክንፍ ጋር በመተባበር “ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴንም እወጣለሁ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በመድረኩ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በምጣኔ ሃብት፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና በዲፕሎማሲ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ራዕይ አስቀምጣ እየሰራች ትገኛለች። ኢትዮጵያ ይህንን ራዕይ ለማሳካት አሻጋሪ ዕሳቤዎችና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ይዛ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል። ኢትዮጵያ ሰፊ የህዝብ ቁጥር ያላት ከዚህ ውስጥም አብዛኛው ወጣት እንዲሁም የተፈጥሮ ሃብቶቿ ካሏት ሰፊ እድሎች መካከል መሆናቸውን አንስተዋል። መንግስት ወጣቱን ተጠቃሚ ለማድረግና በምጣኔ ሃብት እድገት ውስጥ በማሳተፍ የወጣቱን ህልም የሚያለመልሙ እቅዶችን በመተግበር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ወጣቶች የግል ራዕያቸውን ከሀገር ራዕይ ጋር በማጣጣምና በማዘጋጀት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር መስራት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። በተለይም አንድነትን የሚያጠናክሩ፣ መቻቻልን የሚያጎለብቱ እንዲሁም በዘላቂ ሰላም ግንባታ ላይ በስፋት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በዚህም ወጣቶች በጋራ ራዕይ በመመራት ለሀገር ግንባታ ያላቸውን ቁልፍ ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመው መንግስት ሁኔታዎችን በማመቻቸት ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው፤ ወጣቶች ኢትዮጵያ በተለያየ ወቅት የገጠሟትን ፈተናዎች ለማሻገር የተጫወቱት ሚና ጉልህ መሆኑን አንስተዋል። የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት አክሊሉ ታደሰ የተካሔዱ ውይይቶች በፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብትና ማህበራዊ ዘርፎች የወጣቱን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እንዲሁም በሚስተዋሉ ክፍተቶች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል። በተመሳሳይ በዘላቂ ሰላም ግንባታ ጥልቅ ውይይት የተደረገበትና ቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ መግባባት የተደረሰበት እንደሆነም ገልጸዋል። በውይይት መድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የፌዴራልና የክልል መንግስታት ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ወጣት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የብልፅግና ጉዞን ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለመምራት ወጣቶች በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Jul 6, 2025 68
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦የብልፅግና ጉዞን ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለመምራት ወጣቶች በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉባኤው ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ለአብነትም ከተማ አስተዳደሩ በአመራር ዘርፍ የወጣቶችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ አካታች የፖለቲካ ስርዓትን ተግባራዊ ማድረጉን አንስተዋል። እንዲሁም የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማእከላት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጨምሮ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት የከተማ አስተዳደሩ የትኩረት አቅጣጫ ነው ብለዋል። የብልፅግና ጉዞን ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለመምራት ወጣቶች በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባም ከንቲባዋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በስነ-ምግባር የታነፁ በእውቀትና በአቅም የዳበሩ ወጣቶችን ማፍራት ላይ እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት። ወጣቱ የትኛውንም አስቸጋሪ ሁኔታ ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር በአገር ሁለንተናዊ እድገት ላይ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ከአገራዊ ሪፎርሙ ወዲህ ለ174 መገናኛ ብዙሃን ህጋዊ ፍቃድ ተሰጥቷል
Jul 5, 2025 128
አዲስ አበባ፣ሰኔ 28/2017 (ኢዜአ)፦ከአገራዊ ሪፎርሙ ወዲህ ለ174 መገናኛ ብዙሃን ፍቃድ መስጠቱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎችን አፈጻጸም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የዲሞክራሲያዊ ተቋማት የጋራ መድረክ ላይ ሪፖርት አቅርቧል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናታን ተስፋዬ እንደገለጹት ባለስልጣኑ ከአገራዊ ለውጡ በኋላ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅና የሚዲያ ነፃነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን ሰርቷል። የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት ለመወጣት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አብራርተዋል። ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት የሚያስችል የህግ ማሻሻያ ማድረጉንም እንዲሁ። ከለውጡ በፊት በዘርፉ የሚሰሩ የሙያና ሲቪክ ማህበራት ከስድስት የማይበልጡ እንደነበሩ አንስተው፤ አሁን ላይ ለውጡን ተከትሎ 38 ማህበራትና አደረጃጀቶች ወደ ስራ መግባታቸውንም ነው ያብራሩት። ከአገራዊ ለውጡ በኋላ በትምህርት በማህበረሰብ ሬዲዮ፣ በሃይማኖት፣ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ እንዲሁም በዲጂታል ሚዲያ ላይ ፍቃድ ወስደው የሚሰሩ መገናኛ ብዙሃን ቁጥር መጨመሩንም ነው የገለጹት። በዚህም ከአገራዊ ለውጡ በኋላ 174 አዳዲስ መገናኛ ብዙሃን ከባለስልጣኑ ፍቃድ ወስደው ወደ ስራ መግባታቸውን አብራርተዋል። የመገናኛ ብዙሃኑ የቋንቋ ተደራሽነትም ከነበረበት 39 አሁን ላይ ወደ 63 ከፍ ማለቱን አመልክተዋል።

ማህበራዊ
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እርስ በእርስ የተሳሰረና የዳበረ አሰባሳቢ ትርክት ለማስረጽ የጎላ ሚና እንዳለው ተመላከተ
Jul 6, 2025 42
ሀዋሳ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በእርስ ትስስርንና ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም የዳበረ አሰባሳቢ ትርክት ለማስረጽ የጎላ ሚና እንዳለው ተመላክቷል። የ2017 ዓ/ም ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች ሀዋሳ ከተማ የገቡ ሲሆን የተለያዩ በጎ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አስፋው ጎኔሳ አገልግሎቱ የእርስ በእርስ ትስስርን ለማጠናከር ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ ይህም እርስ በእርስ የተሳሰረና የዳበረ አሰባሳቢ ትርክት እንዲሰርፅ የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችም ከሰብዓዊ ተግባራቶቻቸው ጎን ለጎን የየአካባቢውን ባህል፣ ቋንቋና ሌሎች መገለጫዎች በውል እንዲገነዘቡና የጋራ መልካም እሴቶችን እንዲያዳብሩ ዕድልን የሚሰጥ ኩነት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ እመቤት ኢሳያስ፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ወጣቱ ትውልድ ሀገሩን ለመገንባት የሚያስችለውን አንድነት እንዲፈጥር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ ወጣቶቹ በሀዋሳ ቆይታቸው በየአካባቢያቸው ያለውን መልካም እሴት ለሌሎች የማስተዋወቅ፤ እነርሱም የሲዳማን የአብሮነትና የሠላም እሴት በሚገባ ተረድተው የሚመለሱበት አጋጣሚን እንደሚፈጥርም አመልክተዋል፡፡ ወጣቶቹ በቆይታቸው የፅዳት፣ የደም ልገሳ፣ አረጋውያንን የመንከባከብ፣ ህሙማንን የመጠየቅና ሌሎች በጎ ተግባራትን እንደሚከናውኑም ጠቁመዋል፡፡ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች በጎ-ፈቃድ አገልግሎት ዴስክ ባለሙያ የሆኑትና የቡድኑ አስተባባሪ እንደገና ፍቃዱ ይህ ኩነት እንደ ሀገር ለአራተኛ ጊዜ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በአጠቃላይ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ 102 የሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በሁለት ቡድን ተከፍለው ወደተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ አገልግሎቱን እየሰጡ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡ ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መካከል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመጣው ወጣት ደሳለኝ ማሞ እንደገለፀው፤ በጉዟቸው የተለያየ ባህልና እሴት እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ እንዲገነዘቡ ዕድል መፍጠሩን ገልጿል፡፡ በሀዋሳ ከተማ ተገኝቶ ደም መለገስ መቻሉ ልዩ ስሜት እንዳሳደረበት የገለፀው ወጣቱ ደም በመለገስ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት በመታደጌ ትልቅ ደስታ ይሰማኛል ብሏል፡፡ የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ከተማ ፍቅር ሀይቅ ዳርቻ የጽዳት ስራ ያከናወኑ ሲሆን በቀጣይም የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡
ሆስፒታሉ የህክምና አሰጣጡን በዘመናዊ መሳሪያ በማደራጀት የአገልግሎት ጥራት የሚያስጠብቁ ተግባራት እያከናወነ ነው
Jul 6, 2025 50
ወልዲያ፤ ሰኔ 29/2017 (ኢዜአ)፡- የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና አሰጣጡን በዘመናዊ መሳሪያ በማደራጀት የአገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ። ሆስፒታሉ 80 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው የሲቲ ስካን ማሽን ከክልሉ ጤና ቢሮ በድጋፍ አግኝቷል። የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍስሃ የኋላው ለኢዜአ እንደገለጹት ሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና፣ የላብራቶሪ፣ የራጅና ሌሎች የህክምና አገልግሎቶችን በዘመናዊ መሳሪያ በማደራጀት የተሻለ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በሆስፒታሉ በዚህ አመት የኦክስጅን ማምረቻ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ጠቅስዋል። በዛሬው እለትም ከክልሉ ጤና ቢሮ 80 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የሲቲ ስካን ማሽን የተበረከተለት መሆኑን ጠቁመው ማሽኑ እስከ ከሐምሌ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ተከላው ተጠናቆ ስራ እንደሚጀምር አመላክተዋል ። ሆስፒታሉ ለከፍተኛ ህክምና ሪፈር ከሚልካቸው ህሙማን ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት የሲቲ ስካን መሳሪያ አገልግሎት የሚፈልጉ መሆናቸውን ጠቁመው የመሳሪያው መገኘት ህሙማንን ከእንግልት የሚታደግ ጭምር መሆኑን አስታውቀዋል ። የወልዲያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባና የሆስፒታሉ የቦርድ ስብሳቢ አቶ ዱባለ አብራሬ በበኩላቸው ሆስፒታሉ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ። ዛሬ ከክልሉ ጤና ቢሮ የተገኘው የሲቲ ስካን ማሽንም የጥረቱ አካል መሆኑን አስታውቀዋል ።
በሶማሌ ክልል የመምህራንን እጥረት ለመቅረፍ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው
Jul 6, 2025 39
ጅግጅጋ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የመምህራንን እጥረት ለመቅረፍ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የዶክተር አብዱልመጂድ ሁሴን የመምህራን ኮሌጅ ለ31ኛ ጊዜ ያስተማራቸውን 230 መምህራንን ለመጀመሪያ ጊዜ በመጀመሪያ ዲግሪ ዛሬ ያስመረቀ ሲሆን ከተመራቂዎቹ መካከል 13ቱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ መሐመድ ሼክ ዓደን፣ ምሩቃን በቀሰሙት ዕውቀት ህዝባቸውን ለማገልገል መትጋት አለባቸው ብለዋል። ከክልሉ ስፋት አንጻር አሁንም ከፍተኛ የመምህራን እጥረት ያለ ሲሆን የዛሬ ተመራቂዎች ከዚህ አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ የተሻለ ትውልድ ማፍራት ይቻል ዘንድ የመምህራን እጥረትን ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑንና በክልሉ ከሚገኙ ሶስት መምህራን ኮሌጆች ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ጎን ለጎን የትምህርት ጥራትን ማሻሻል የሚያስችሉ አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላት ተግባር በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። የዶክተር አብዱልመጂድ ሁሴን የመምህራን ኮሌጅ ዲን መሀመድ ዓሊ አያንሌ በበኩላቸው ኮሌጁ የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገትና የለውጥ ጉዞ ለማፋጠን አስተዋጽኦ የሚያበረከቱ መምህራንን እያፈራ ይገኛል ብለዋል። ኮሌጁ ከዚህ ቀደም መምህራንን በሰርተፊኬትና በዲፕሎማ ሲያሰለጥን እንደቆየ ጠቅሰው ዛሬ ደግሞ ለመጀመሪያ በዲግሪ ደረጃ ያሰለጠናቸውን መምህራን ማስመረቁን ገልፀዋል። ተመራቂዎቹ በቀሰሙት ዕውቀት በመታገዝ ህዝብና ሀገርን በቁርጠኝነት ማገልገል እንዳለባቸውም አሳስበዋል። በስነ-ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ማህበረሰብን በማሳተፍ በትኩረት እየተሰራ ነው
Jul 6, 2025 89
ወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ማህበረሰብን በማሳተፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ። በወላይታ ሶዶ ከተማ በአንድ ባለሃብት በ60 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ የትምህርት ቤት ህንፃ ዛሬ ተመርቋል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዱጼ ታምሩ እንዳሉት በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል። ትምህርት ላይ መስራት ትውልድ ላይ መስራት መሆኑን ጠቁመው ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት የክልሉን ማህበረሰብ በማሳተፍ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በተለየ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልና በግብዓት ማደራጀት እንዲሁም የመምህራንን አቅም ማሻሻልን ጨምሮ ለዚሁ ስራ ውጤት የሚያግዙ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውንም ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በተቀናጀ መልኩ በተደረጉ ጥረቶች የተማሪ ውጤት እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቅሰው ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ባለድርሻ አካል ለትምህርት ጥራት መሻሻል የሚደረገውን ጥረት ሊያጠናክር ይገባል ብለዋል። የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፍሬው ሞገስ(ዶ/ር) በበኩላቸው ከለውጡ ወዲህ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመረው ስራ ውጤት ተመዝግቦበታል ብለዋል። ባለሀብቶች በከተማው ያለውን የከፍተኛ ትምህርት ፍላጎት ለመሙላት የሚደረገውን ጥረት እየደገፉ መሆኑን ገልፀዋል። የትምህርት ዘርፉን በመደገፍ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ይሰራል ያሉት ከንቲባው የባለሀብቶችን ጥያቄ በመመለስ በዘርፉ የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል ይሰራል ብለዋል። ትምህርት ቤቱን ያስገነቡት አቶ ተስፋዬ ጎአ፤ 60 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ህንፃ በ2 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ማረፉን ገልፀው ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ዘርፉን በመደገፍ በኩል የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸው ከክልል ጀምሮ እስከ ከተማ አስተዳደር ያሉ የመንግስት አካላት እየሰጡት ያለው አገልግሎት ይበል የሚያሰኝና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ነው ብለዋል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የክልል እና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል።
ኢኮኖሚ
እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Jul 6, 2025 59
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከብሪክስ መሪዎች ጋር በሪዮ ዲ ጄኒሮ በዚህ አመቱ ጉባኤ ላይ ተገኝተናል ብለዋል። የበለጠ እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን ሲሉም ገልጸዋል በመልዕክታቸው። የብሪክስ መድረክ የጋራ የልማት እና አለምአቀፋዊ ትብብርን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ሆኖ ቀጥሏል ነው ያሉት።
በክልሉ ከተረጂነት ለመላቀቅ የተጀመሩ ውጤታማ ተግባራትን ለማስቀጠል በትጋት ይሰራል
Jul 6, 2025 54
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ከተረጂነት ለመላቀቅ የተጀመሩ ውጤታማ ተግባራትን ለማስቀጠል በትጋት እንደሚሰራ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ኃይሉ አዱኛ ገለጹ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ባለፉት አምስት ቀናት በደቡብ ኦሮሚያ በሚገኙ አምስት ዞኖች ያደረጉት ጉብኝት ስኬታማ መሆኑ ተገልጿል። የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ሀይሉ አዱኛ ጉብኝቱን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ጉብኝቱ የልማት ስራዎችን ውጤታማነት ያረጋገጠ ብሎም የቀበሌ አደረጃጀቶች ለህዝቡ እየሰጡ የሚገኙትን የአገልግሎቶች አሰጣጥ የቃኘ መሆኑንና የታለመለትን ግብ ያሳካ ነው ብለዋል። በክልሉ ፕሬዚዳንት የተመራ ቡድን በቦረና፣ በምዕራብ ጉጂ፣ በምስራቅ ቦረና፣ በጉጂ እና በባሌ ዞኖች የመስክ ምልከታ ማድረጉን ገልጸዋል። በዚህም ከተረጂነት ለመላቀቅ ምርታማነትን ለማሳደግ የተያዙ ግቦችን አፈጻጸም በመመልከት ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ የተሰጠበት መሆኑን አንስተዋል። በተለይም በቦረና፣ በምዕራብ ጉጂ፣ በምስራቅ ቦረና እና በጉጂ ቆላማ አካባቢዎች ለዘመናት ያልለሙ መሬቶችን በማልማት ለውጥ መምጣት መጀመሩን ገልጸዋል። በዚህም የስንዴ ምርትን ጨምሮ ሌሎች የሰብል ዓይነቶችን በክላስተር በማምረት ከተረጂነት ለመላቀቅ የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማነት በማረጋገጥ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው፤ ለቀጣይነቱም በትጋት ይሰራል ብለዋል። ለዚህም በክልሉ መንግስት እየተገነቡ የሚገኙ የፊና የመስኖ ግድብ ፕሮጀክቶች አጋዥ መሆናቸውን በማከል። በሌላ መልኩ በክልሉ መንግስት ተደራጅቶ ወደ ስራ የገባው የቀበሌ አደረጃጀት ለሕዝቡ በቅርበት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ የተረጋገጠበት ጉብኝት ነው ብለዋል። በዚህም አደረጃጀቱ የሕዝቡን የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎች በመፍታት ላይ እንደሚገኝ ታይቷል ብለዋል። በአጠቃላይ ፕሬዚዳንቱ እና የስራ ሃላፊዎች ያደረጉት ጉብኝት ውጤታማ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከኢንዱስትሪ ፓርኩ እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት ወደ ውጪ ከተላከ የአቮካዶ ዘይት 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ተገኝቷል
Jul 6, 2025 58
ሀዋሳ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ ከይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት ወደ ውጪ ከተላከ የአቮካዶ ዘይት 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ መገኘቱን የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ። የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሀይሉ ዬተራ ለኢዜአ እንዳሉት ፓርኩ ባለፉት ዓመታት በግብርና ሽግግር እና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ከማሳደግ አንጻር አበረታች ስራ እየሰራ ይገኛል። መንግስት ፓርኩን ለማጠናከር የሚያደርጋቸው ድጋፎች ውጤት እያመጡ መሆኑን አንስተው ከጊዜ ወደ ጊዜ የባለሀብቱ ተሳትፎም እየጨመረ መጥቷል ብለዋል። በዚህ ወቅትም ከ30 በላይ ኩባንያዎች በፓርኩ እያለሙ መሆናቸውን ገልጸው ከእነዚህም ስምንቱ አቮካዶ፣ ወተት፣ ማርና ቡና ምርቶች በማቀነባበር ለውጪ ገበያ እያቀረቡ ሲሆን ቀሪዎቹ በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት ፓርኩ ለውጪ ገበያ ካቀረበው የአቮካዶ ዘይት ከ20 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውሰው በተመሳሳይ 15 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ተኪ ምርት ማምረት መቻሉንም አመልክተዋል። ፓርኩ ለበርካታ ዜጎች በቀጥታ የስራ ዕድል መፍጠሩንና ከክህሎት ሽግግር አንጻርም አበረታች እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡ ከ137 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ጋር የገበያ ትስስር መፍጠሩንም ጨምረው ጠቁመዋል። በቀጣይ በፓርኩ ውስጥ ስራ ለመጀመር በሂደት ላይ የሚገኙ 32 ኩባንያዎች በሙሉ አቅማቸው ስራ ሲጀምሩ ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጠርም አመልክተዋል። እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት ወደ ውጪ ከተላከ የአቮካዶ ዘይት 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚጠጋ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል። የሲዳማ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊና የኮርፖሬሽኑ ቦርድ ሰብሳቢ አራርሶ ገረመው(ዶ/ር) በበኩላቸው ለኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚቀርቡ የግብርና ግብዓቶችን ማስፋትና ጥራትን ማስጠበቅ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። ለዚህም ከፍተኛ የምርት ሰንሰለት ባለባቸው ሰባት ወረዳዎች የሚገኙ ከ40ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኩ የአቮካዶ ዘይት በማቀነባበር ለውጪ ገበያ እያቀረበ የሚገኘው የ'ጎልደን ኦርጋኒክ አቮካዶ ኦይል' ፋብሪካ ተወካይ ሚሊዮን ቴጎ፤ በመጀመሪያ ዙር 80ሺህ ኪሎ ግራም ድፍድፍ የአቮካዶ ዘይት ለውጪ ገበያ መቅረቡን ተናግረዋል። ፋብሪካው ከበርካታ የአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር የምርት ገበያ ትስስር በመፍጠር እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በዚህም ከ60 በላይ ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል። በፋብሪካው የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሆነው ወጣት ብሩክ ባጥሶ፤ የኮሌጅ ተመራቂ ሲሆን ከአካባቢው ሳይርቅ ባገኘው የስራ ዕድል ተጠቅሞ ራሱንና ቤተሰቡን እየረዳ መሆኑን ተናግሯል። የፋሚሊ የማር ምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ዘርይሁን ንጉሴ፣ በየካቲት ወር 2017 ዓ.ም ወደ ስራ የገባው ፋብሪካው በፓርኩና አካባቢው ያለውን ምርትና ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በማር ማቀነባበር ላይ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ማር በዓለም ደረጃ ተፈላጊ መሆኑን አንስተው ጥራት ያለውን የማር ምርት በማቀነባበር ገበያው ላይ በስፋት ለመግባት እንደሚሰሩም ተናግረዋል። በ294 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንደስትሪ ፓርክ በ2013 ዓ.ም መጋቢት ወር ላይ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።
በክልሉ ግብርናን በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የባለሃብቶች ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ
Jul 6, 2025 48
ጋምቤላ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል ግብርናውን በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የባለሃብቶች ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሯ በጋምቤላና አበቦ ወረዳዎች ከዘርፍ አመራሮች ጋር በመሆን በባለሃብቶች የለማ የእርሻ ማሳ ዛሬ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ርዕሰ መስተዳድሯ በጉብኝቱ ወቅት ለኢዜአ እንደገለጹት ለአንድ ሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የኢንቨስትመንት ዘርፍ ዋነኛ ድርሻ አለው። ባለሀብቶች ባሉት ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች በመሰማራት ለክልሉ ልማትና አድገት ተሳትፏቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተናግረዋል። በክልሉ በተለይም የግብርናውን ልማት በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ለተጀመረው ጥረት በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች አርሶ አደሩን በቴክኖሎጂ በመደገፍ በኩል የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል። በክልሉ የተፈጠረውን ሰላም በመጠቀም ባለሃብቶች በግርናው ዘርፍ እያከናወኑ ያለው ስራ በእጅጉ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው ሌሎች ባለሃብቶች ወደ ክልሉ በመምጣት በተመሳሳይ ልማት ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል። የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሎው ኡቡፕ(ዶ/ር) በክልሉ አስተማማኝ ሰላም በመፈጠሩ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሰማራት ወደ አካባቢው የሚመጡ ባለሃብቶች ፍሰት እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። በተለይም በግብርናው ዘርፍ ፍቃድ የወሰዱ ባለሃብቶች በዘንድሮው የመኸር እርሻ ከመቸውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ወደ ልማት በመግባት ውጤታማ ሰራዎችን እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። የእርሻ ማሳቸውን ካስጎበኙ ባለሃብቶች መካከል አቶ ፍቅሩ ገብረመድን በሰጡት አስተያየት በክልሉ በተለይም በግብርናው ዘርፍ መሰማራታቸውን ተናግረዋል። የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በሁሉም ዘርፍ አስፈለጊውን ድጋፍና አገዛ እያደረገላቸው መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ብልጽግናን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ከጠባቂነት የተላቀቀ አስተሳሰብ መገንባት ቁልፍ ጉዳይ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Jul 5, 2025 115
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 28/2017(ኢዜአ)፦ብልጽግናን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ከጠባቂነት የተላቀቀ አስተሳሰብ መገንባት ቁልፍ ጉዳይ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው "የሚሰሩ እጆች ወግ" የተሰኘ ፕሮግራም በይፋ አስጀምሯል ። በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የቦርድ ሰብሳቢና የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የሃይማኖት አባቶች፡ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ ወጣቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ፕሮግራሙ በየ15 ቀኑ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሚቀርብ ሲሆን በስራ ፈጠራ ረገድ ትውልድን የሚቀርጹ ሃሳቦችን የሚያንሸራሽሩበት መሆኑ ተመልክቷል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት ከተረጅነት በመላቀቅ ወደ ብልጽግና የሚያደርሱ ትልሞችን ይዘን እየሰራን ነው ብለዋል። የተያዘው ትልም የሚሳካው ጠንክረን ስንሰራ ብቻ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች ለዚህም ሰርተው የተለወጡ አገራት አብነት ሊሆኑን ይገባል ነው ያሉት። ከስራ ማማረጥና ስንፍና መላቀቅ እንደሚገባ ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ ማህበረሰቡ ውስጥ ግንዛቤን የማስፋቱ ጉዳይ አጽንኦት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል። በመሆኑም የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችን ጨምሮ ትውልድን የሚያንጹ ተቋማት የዜጎችን የስራ ባህል ለመቀየር የሚያስችሉ ግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን አበክረው ሊሰሩ እንደሚገባ አመልክተዋል። በትምህርት ተቋማትና በስራ ቦታዎችም ዜጎችን የማንቃት ስራ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል። የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፤ የስራ ባህልን ለማሳደግ እንደሀገር የማህበረሰብ ምርታማነት ምክክር መርሃ ግብር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል ። የምክክር መርሃ ግብሩ ማህበረሰቡ በየአካባቢው ያለውን ጸጋ በማየትና በመስራት ውጤታማ እንዲሆን በር የሚከፍት መሆኑን ጠቅሰዋል ። ፕሮግራሙ ለስራ ባህል ማደግ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ትልቅ እርምጃ መሆኑንም ተናግረዋል። ዘመኑ የሚጠይቀው አርበኝነት ሰርቶ በመለወጥ ራስን መቻል ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ የሚሰሩ እጆች ግለሰብንም አገርንም የሚያሳድጉ መንገዶች ናቸው ብለዋል ። በትኩረት ከተያዘ የስራ ባህል ላይ ተጨባጭ ውጤት እንደሚመጣ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ማሳያ መሆኑንም አንስተዋል። አገርን ለማሻገር ስራን የማሰቢያ መንገድ፤ ትጋትና ታታሪነትን መርህ በማድረግ ልንረባረብ ይገባል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ ለ366ሺህ ስራ ፈላጊዎች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል ። የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች ሃሳባቸውን ወደ ተግባር የሚቀይሩበት ስርአት መዘርጋቱንም ጠቁመዋል።
የግብርናውን ዘርፍ እድገት ለማስቀጠል የምርምር ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ-የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት
Jul 4, 2025 111
አዲስ አበባ፤ሰኔ 27/2017(ኢዜአ)፦የግብርናውን ዘርፍ እድገት ለማስቀጠል የተጀመሩ የምርምር ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት ገለፀ። ኢንስቲትዮቱ በቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሃሳብ የ2017 አረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል። በቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል የተለቀቁ ቴክኖሎጂዎችን የሚያሳይ ኤግዚቢሽንም ከፍቷል። የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢንስቲትዩቱ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እየሰራ ነው። የተሻሻሉ ዝርያዎችን በማውጣት የማባዛትና ለአርሶ አደሩ ተደራሽ የማድረግ፣ በአስተራረስና አመራረት ሂደት ዘዴዎች ላይ ክህሎት የማሳደግ ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ ባሉት 23 ማዕከላት የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በማከናወን ዘርፉን የመደገፍ ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤በቀጣይም የግብርናውን እድገት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል። በኤግዚቢሽኑ የቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከልም የተለያዩ ምርምሮችን በማካሄድ የሰብልና እንስሳት ዝርያዎችን የማባዛትና ተደራሽ የማድረግ ስራ እያከናወነ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀዋል። ኢንስቲትዩቱ ዛሬ በቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ማስጀመሩን አንስተው፤ በ23ቱም ማዕከላት መርሃግብሩ እንደሚከናወን ጠቁመዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ብለዋል። የቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ዳኜ ሞጆ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ማዕከሉ ከ70 ዓመት በላይ በተለያዩ ሰብልና እንስሳት ላይ ምርምር በማድረግ ዝርያዎችን ሲያሻሽል መቆየቱን ገልጸዋል። ያከናወናቸው ተግባራት ለግብርናው ዘርፍ እድገት አስተዋፅኦ ያላቸው እንደሆኑም ተናግረዋል። በማዕከሉ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉት የአቮካዶና ፓፓዬ የቡናና ወይራ ችግኞች መሆናቸውን ተናግረዋል። የማዕከሉ የጤና ስፖርት ማህበር ሊቀ መንበር ግዛቸው ካባ እና የሰው ሀብት ክፍል ሰራተኛ የሆኑት ወይዘሮ ድንቅነሽ አየለ፤ ዕጽዋቱ የአካባቢ ስነ ምህዳርን ለመጠበቅ የሚረዱ መሆናቸውን ጠቁመው፤ችግኞችን ከመትከል ባለፈ በመንከባከብ ለፅድቀት ለማድረስ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የተቀናጀ የአረምና የተባይ መከላከል ዘዴን ለማስፋፋት እየተሠራ ነው-ግብርና ሚኒስቴር
Jul 4, 2025 91
አርባምንጭ ፤ሰኔ 27/2017 (ኢዜአ)፡- በሀገሪቱ የተቀናጀ የአረምና የተባይ መከላከል ዘዴን በማስፋፋት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ በተቀናጀ የአረምና የተባይ መከላከያ ዘዴ ዙሪያ በአርባ ምንጭ ከተማ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው። በመድረኩ ላይ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር) የግብርናው ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚ ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የተቀናጀ የአረምና የተባይ መከላከያ ዘዴን ለማስፋፋት እየሠራ ይገኛል ብለዋል። ፓርቲኒየም ወይም የቅንጨ አረም በእርሻና በግጦሽ መሬት ላይ በመስፋፋት እንዲሁም ኋይት ስኬል (Mango White scale) የተሰኘው የማንጎ በሽታ በምርትና ምርታማነት ብሎም በእንስሳትና ሰዎች ጤና ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ መሆኑን ገልጸዋል። አካባቢን ከሚበክል አሠራር በመውጣት አረምና ተባዮችን በተፈጥሯዊ ወይም ባዮሎጂካል መንገድ ለማስወገድ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በተለይ ድንበር ዘለል የሆኑ አንበጣ፣ ወፎችና ሌሎች ተባዮችን ለመከላከል የአሰሳና የኬሚካል ርጭት ሥራ የሚያከናውኑ አምስት አይሮፕላኖችን ተገዝተው ወደ ሥራ መገባቱን ጠቅሰዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ዓለም አቀፍ የስነ-ነፍሳትና ስነ-ምህዳር ምርምር ተቋም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባ ምንጭ ዕፅዋት ማዕከል የገነባውን ስነ-ህይወታዊ ፀረ-ተባይና ፀረ-አረም ላቦራቶሪ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል። ዓለም አቀፍ የስነ-ነፍሳትና ስነ-ምህዳር ምርምር ተቋም ተወካይና ተመራማሪ ሚናሌ ካሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው ተቋሙ የህብረተሰቡን የጤና፣ የሰብል፣ የስነ-ምህዳርና ሌሎች ችግሮችን በተቀናጀ መንገድ ለመፍታት ጥናትና ምርምር ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል። ፓርቲኒየም የተሰኘውን አረም ከሌሎች ከሚወገዱ ቁሶች ጋር በማደባለቅ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማምረት የሚያስችል ሥራ ከአርባ ምንጭ ዕፅዋት ማዕከል ጋር መስራቱን ተናግረዋል። በተጨማሪም የማንጎ በሽታን የሚከላከል ነፍሳት ማራቢያ ላቦራቶሪ ገንብተው ለዕፅዋት ማዕከሉ ማስረከባቸውን ገልጸዋል። በአርባ ምንጭ ዕፅዋት ማዕከል የተገነባው ተባይን በተባይ የመቆጣጠር ዘዴ እንዲሁም በፓርቲኒየም የተፈጥሮ ማዳበሪያ የማዘጋጀት ዘዴ ለግብርና ምርታማነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው የጠቆሙት ደግሞ የማዕከሉ ኃላፊ አቶ ሙላለም መርሻ ናቸው። ቴክኖሎጂው ህብረተሰቡን ከኬሚካል ጥገኝነት የሚያላቅቅ ከመሆኑም በላይ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ፣ ንጹህ አካባቢን ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚያግዝ ነው ብለዋል። ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው መድረክም ከኬኒያ የመጡ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጨምሮ የፌዴራል መንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ዓለም አቀፍ የስነ-ነፍሳትና ስነ-ምህዳር ምርምር ተቋም ተወካዮች፣ ተመራማሪዎች እና ማህበራት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
የኮደርስ ስልጠና የተሻለ የዲጂታል እውቀትና ክህሎት እንድናገኝ መልካም አካጣሚ ፈጥሮልናል - ወጣቶች
Jul 4, 2025 107
ጂግጂጋ፤ ሰኔ 27/2017(ኢዜአ)፦ የኮደርስ ስልጠና የተሻለ የዲጂታል እውቀትና ክህሎት እንድናገኝ መልካም አካጣሚ ፈጥሮልናል ሲሉ በጂግጂጋ ከተማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ተናገሩ። የሶማሌ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በበኩሉ በክረምቱ በእረፍት ላይ የሚገኙ ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከወሰዱ ወጣቶች መካከል ሸርማርኬ ሸኪብ አብዲ፤ የስልጠናው እድል በተለይም ለወጣቶች ጥሩ አጋጣሚ በመሆኑ ጥሩ የዲጂታል እውቀት እና ክህሎት እንድንጨብጥ እያደረገን ነው ብሏል። ከስልጠናው በቀሰመው እውቀት እና ክህሎት በመታገዝ ዌብሳይት በማበልጸግ የራሱን የንግድ ስራ ለማስተዋወቅ እየተጠቀመበት መሆኑን አንስቶ በነፃ እንዲህ አይነት የትምህርት እድል በማግኘቱ አመስግኗል። የሚገኘው እውቀት ከሀገርም ባለፈ ዓለም አቀፍ ተፈላጊ የሚያደርግ መሆኑን አንስቶ ሌሎች ወጣቶችም እድሉ እንዳያመልጣቸው መክሯል። ሌሎች ስልጠናውን ያገኙት ወጣት አብዲሸኩር መሀመድ አብዲ እና ሰከሪዬ አብዲረህማን ዓሌ፤ የኮደርስ ስልጠናው በብዙ መልኩ ጠቃሚ መሆኑን ካገኘነው እውቀትና ክህሎት ተገንዝበናል ብለዋል። የአሁኔ ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን መሆኑን የገለጹት ወጣቶቹ መማር፣ መዘጋጀትና ከወቅቱ ጋር መጓዝ የግድ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም በተለይም በክረምቱ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ዝግ በመሆናቸው ወጣቶች ጊዜያቸውን የኮደርስ ስልጠና በመውሰድ እንዲጠቀሙበት አስገንዝበዋል። የክልሉ የመረጃ ማዕከል አስተዳደር ዳይሬክተር አብዲአዚዝ አብዲላሂ፤ የኢትዮ ኮደርስ ስለጠና እድሜ ሳይገድበው ለሁሉም ዜጎች በነፃ የሚሰጥ የዲጂታል እውቀት በመሆኑ ሁሉም እድሉን እንዲጠቀምበት መክረዋል። በተለይም ወጣቶች ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ እውቅት በማዳበር ብቁና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ስልጠናው በእጅጉ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ እስካሁን ከ48ሺህ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደው ሰርተፊኬት የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸው በክረምቱ በእረፍት ላይ የሚገኙ ወጣቶች ሁሉ የኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፖርት
ሴኔጋል ድል ቀንቷታል
Jul 6, 2025 46
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29 /2017 (ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አንድ ሁለተኛ መርሃ ግብር ሴኔጋል ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች። በኤል ባቺር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ማማ ዲዮፕ እና ንጌናር ንዳዬ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል። በጨዋታው ሴኔጋል በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ላይ ከፍተኛ ብልጫ ወስዳለች። ውጤቱን ተከትሎ ሴኔጋል ምድብ አንድን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች። በዚሁ ምድብ ትናንት በተካሄደ የመጀመሪያ ጨዋታ አዘጋጇ ሞሮኮ ከዛምቢያ ሁለት አቻ ተለያይታለች።
በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
Jul 6, 2025 59
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የሁለተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። በምድብ አንድ ሴኔጋል ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በኤል ባቺር ስታዲየም ይጫወታሉ። ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም እርስ በእርስ ባደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች ዶሜክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሁለት ጊዜ ስታሸንፍ ቀሪውን ጨዋታ ሴኔጋል አሸንፋለች። በፊፋ የሴቶች የሀገራት እግር ኳስ ደረጃ ሴኔጋል 81ኛ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 109ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በዚሁ ምድብ ትናንት በተደረገው የመክፈቻ ጨዋታ ሞሮኮ እና ዛምቢያ ሁለት አቻ ተለያይተዋል። የአፍሪካ ዋንጫን ዘጠኝ ጊዜ በማንሳት የውድድሩ ቁንጮ ሀገር የሆነችው ናይጄሪያ ከቱኒዚያ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ሁለቱ የአፍሪካ ሴቶች እግር ኳስ ተቀናቃኝ ሀገራት እስከ አሁን ዘጠኝ ጊዜ እርስ በእርስ ተገናኝተዋል። ናይጄሪያ ሶስት ጊዜ ስታሸንፍ ቱኒዚያ ሁለት ጊዜ አሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። በዘጠኙ ጨዋታዎች ናይጄሪያ 11 ግቦችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ፣ ቱኒዚያ 9 ጎሎችን አስቆጥራለች። በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ከፍተኛ የበላይነት ያላት ናይጄሪያ ጨዋታውን የማሸነፍ የቅድሚያ ግምት አግኝታለች። በፊፋ የሴቶች የሀገራት እግር ኳስ ደረጃ ናይጄሪያ 36ኛ፣ ቱኒዚያ 89ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በዚሁ ምድብ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አልጄሪያ ከቦትስዋና በፔሬ ጄጎ ስታዲየም ይጫወታሉ። ሁለቱ ሀገራት በውድድር ጨዋታዎች ሲገናኙ የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ያደረጓቸውን ሶስት ጨዋታዎች አልጄሪያ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዛለች። አልጄሪያ በጨዋታዎቹ 10 ግቦችን ስታስቆጥር ቦትስዋን ማግባት የቻለቸው አንድ ጎል ብቻ ነው። ጨዋታው አልጄሪያ በቦትስዋና ላይ ያላትን የበላይነት ለማስቀጠል፣ ቦትስዋን በተጋጣሚዋ ላይ የመጀመሪያ ድሏን ለማስመዝገብ የሚያደርጉት ጨዋታ ነው። በፊፋ የሴቶች የሀገራት እግር ኳስ ደረጃ አልጄሪያ 82ኛ፣ ቦትስዋና 153ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ሪያል ማድሪድ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል
Jul 6, 2025 57
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ በፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫ የመጨረሻ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን 3 ለ 2 አሸንፏል። ትናንት ማምሻውን በሜትላይፍ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ጎንዛሎ ጋርሺያ፣ ፍራንሲስኮ ጋርሺያ እና ኪሊያን እምባፔ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ማክሲሚሊያን ቤየር በጨዋታ እና ሴርሁ ጉይራሲ በፍጹም ቅጣት ምት ለቦሩሲያ ዶርትሙንድ ግቦቹን አስቆጥረዋል። የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ዲን ሀውሰን በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። በጨዋታው ሪያል ማድሪድ በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድሎችን በመፍጠር ከተጋጣሚው የተሻለ ነበር። ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል። ለፍጻሜ ለማለፍ ከፒኤስጂ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ወጣቱ አጥቂ ጎንዛሎ ጋርሺያ በውድድሩ ላይ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ አራት ከፍ አድርጓል። ጋርሺያ ከውድድሩ ከተሰናበቱት የአል ሂላሉ ማርኮስ ሌኦናርዶ እና የቤኔፊካው አንጌል ዲ ማሪያ ጋር በግብ ተስተካክሏል። ታዳጊው አጥቂ ተጨማሪ ግቦችን አስቆጥሮ ኮከብ ግብ አግቢ የመሆን እድል አለው። ትናንት በተደረገው ሌላኛው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ ባየር ሙኒክን 2 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። ሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በፍሉሜኔንሴ እና ቼልሲ መካከል ይደረጋል። የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ሐምሌ 1 እና 2 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳሉ።
በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ሞርሮኮ እና ዛምቢያ አቻ ተለያዩ
Jul 6, 2025 56
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ አዘጋጇ ሞሮኮ ከዛምቢያ ሁለት አቻ ተለያይታለች። ትናንት ማምሻውን በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ አንድ ጨዋታ ኢብቲሳም ጂራይዲ እና ጊዝላን ቼባክ ግቦቹን ለሞሮኮ አስቆጥረዋል። ባርባራ ባንዳ እና ራቼል ኩንዳንናንጂ ለዛምቢያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በጨዋታው ሁለቱ ሀገራት ተመጣጣኝ ፉክክር አድርገዋል። ውጤቱን ተከትሎ በምድብ አንድ ሞሮኮ እና ዛምቢያ በምድቡ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል። በዚሁ ምድብ ሴኔጋል ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ዛሬ ከቀኑ 11 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ከጨዋታው በፊት ደማቅ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ተካሂዷል። እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየው ውድድር 12 ሀገራት በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
አካባቢ ጥበቃ
ጽዳትን ባህል በማድረግ ምቹ እና ማራኪ የመኖሪያ አካባቢ መፍጠር የሁሉም ድርሻ መሆን አለበት - የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
Jul 6, 2025 63
ሰመራ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፡- ጽዳትን ባህል በማድረግ ምቹ እና ማራኪ የመኖሪያ አካባቢ መፍጠር የሁሉም ድርሻ መሆን አለበት ሲሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ ተናገሩ። ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ በተገኙበት "ፅዳትን ባህል እናድርግ" በሚል መሪ ሀሳብ የፅዱ ኢትዮጵያ የንቅናቄ መርሃ ግብር በሰመራ ከተማ ተካሄዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ እንዳሉት ከከተሞች መስፋፋትና ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የአካባቢ ብክለትም እየሰፋ መጥቷል። በተለይም ከፕላስቲክ ምርቶች አጠቃቀም ጉድለት የተነሳ እየደረሰ ያለው ብክለት ተፈጥሮን እየጎዳ መምጣቱንም ተናግረዋል። በዚህም ሳቢያ በከተሞች ቆሻሻዎች እየተበራከቱ በመሆኑ ይህንን ለመከላከል በጋራ ፅዱ አካባቢን በመፍጠር ለመኖሪያ ምቹ እና ማራኪ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። ፅዱ አካባቢን ለመፍጠር የጋራ ስራ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት የሰጡት ዋና ዳይሬክተሯ በተለይም የአካባቢ ጥበቃ ላይ የወጡ ህጎችን መፈፀምና ማስፈፀም ብሎም ማስገንዘብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። በተጀመረው ንቅናቄም 15 ሚሊዮን ሰዎችን ገፅ ለገፅ ለመድረስ እና በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ደግሞ 50 ሚሊዮን ሰዎች ጋር ተደራሽ ለመሆን መታቀዱን ተናግረዋል። የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በበኩላቸው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የ"ፅዱ ኢትዮጵያ" ንቅናቄን ከግብ ለማድረስ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። ንቅናቄው በክልሉ የተጀመሩ የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ስራዎች እንዲጎለብቱና ውጤት እንዲኖራቸው ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል። መርሃ ግብሩ እንዲሳካም የክልሉ መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስረድተዋል። የክልሉ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አደን ሀመና፣ የፅዱ ኢትዮጵያ መርሃ ግብርን አውን ለማድረግ የግንዛቤ ማሳደግ ስራዎች ለተከታታይ ስድስት ወራት በትኩረት እንደሚከናወኑ አስረድተዋል። በንቅናቄ መርሃ ግብሩ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በዞኑ በተለያየ ምክንያት በተራቆተ 5 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ችግኝ እየተተከለ ነው
Jul 6, 2025 62
ነገሌ ቦረና፤ ሰኔ 29/2017 (ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን በተለያየ ምክንያት በተራቆተ 5 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ችግኝ እየተተከለ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ። በጽህፈት ቤቱ የተፈጥሮ ሀብት ቡድን መሪ አቶ አልዬ አረባ ለኢዜአ እንደገለፁት የችግኝ ተከላው እየተከናወነ የሚገኘው በተፈጥሯዊ እና በሰው ሰራሽ ምክንያት በተራቆተ 5 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ነው፡፡ በዞኑ ባለው የአየር ጸባይ ምክንያት ተከላው የተጀመረው ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ መሆኑን ተናግረዋል። የችግኝ ተከላው የተራቆተ መሬት እንዲለመልም ከማድረግ ባሻገር የድርቅ ተጋላጭነትን በዘላቂነት መቋቋምን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ዘንድሮ እየተተከሉ ከሚገኙ ችግኞች መካከል የደን፣ የጥላ ዛፍ፣ የእንስሳት መኖ እንዲሁም ከፍራፍሬ ችግኞች ማንጎ፣ ሙዝና ዘይቱን ዋና ዋና ዎቹ እንደሆኑ አመልክተዋል፡፡ የችግኝ ተከላው የዞኑን ነዋሪዎችና በጎ ፈቃደኞችን ባሳተፈ መልኩ እየተከናወነ ሲሆን የተያዘው እቅድ እስከሚሳካ ድረስ ተከላው በትኩረት እንደሚከናወንም አስረድተዋል። በዞኑ በበጋ ወራት ዘንድሮ በ99 ተፋሰሶች ውስጥ 63 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ መከናወኑን አስታውሰዋል፡፡ የተፋሰስ ልማት ስራው ዓላማ በዋናነት ድርቅና የአካባቢ መራቆትን ከመከላከል ባለፈ በዘላቂ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ እና የችግኝ ተከላ ስራም የተፋሰስ ልማቱን ጭምር በእጽዋት ለማልበስ ታቅዶ የተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
በክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሁሉም በንቃት በመሳተፍ አሻራውን ሊያኖር ይገባል
Jul 5, 2025 88
ሶማሌ፤ ሰኔ 28/2017 (ኢዜአ)፡- በክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሁሉም በንቃት በመሳተፍ አሻራውን ሊያኖር ይገባል ሲሉ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ። የክልሉ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና አረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ርእሰ መስተዳድሩ በተገኙበት በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ፤ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ጨምሮ በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት አመታት በተከናወኑ ስራዎች አካባቢን በመጠበቅና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ሂደት ስኬቶች መታየታቸውን አንስተዋል። በመሆኑም በዘርፉ ልማት ዘንድሮም ዝግጅት መደረጉን ገልጸው በመርሃ ግብሩ ሁሉም በነቂስ በመሳተፍ አሻራውን እንዲያሳርፍ አስገንዝበዋል። ከችግኝ ተከላ በተጨማሪ በክረምት በጎ ፈቃድ የአረጋውያንና አቅመ ደካሞችን ቤት በማደስና በመገንባት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣በደም ልገሳ እና ሌሎችም መስኮች ነፃ አገልግሎቱ እንዲጠናከር አፅእኖት ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል።
የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በተግባር የተገነዘብን በመሆኑ ችግኞችን ለመትከል እና ለመንከባከብ ተዘጋጅተናል
Jul 5, 2025 93
አሶሳ፤ ሰኔ 28/2017 (ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በተግባር የተገነዘብን በመሆኑ ችግኞችን ለመትከል እና ለመንከባከብ ተዘጋጅተናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ። የ2017 የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በክልሉ በኡራ ወረዳ ሰልጋ 20 ንዑስ ተፋሰስ ልማት ላይ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል። በመርሃ ግብሩ ላይ ከተገኙት መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በተግባር የተገነዘብን በመሆኑ ችግኞችን ለመትከል እና ለመንከባከብ ተዘጋጅተናል ብለዋል። ካነጋገርናቸው መካከል አቶ አብዱላሂ ሙሀመድ እና ወይዘሮ ሺዋጋ አለሙ፤ የአረንጓዴ አሻራ ውጤት ምግብም፣ ጥላና ከለላም እየሆነ እኛንም ተፈጥሮንም እየጠበቀ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል። በአካባቢያቸው መሬት እንዲያገግም እና ለእንስሳት መኖ በቅርበት እንዲያገኙ እያደረገም ስለመሆኑ አንስተዋል። በተለይም በተፋሰስ ልማት ላይ የሚተከሉ ችግኞች የመጽደቅ መጠናቸው ከፍተኛ በመሆኑ የተፋሰስ ልማት እና የችግኝ ተከላን በተጠናከረ መልኩ የሚያስቀጥሉ መሆኑን አረጋግጠዋል። ሌላው በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉት መቶ አለቃ በሱፍቃድ ገላን፤ የመከላከያ ሰራዊት የሀገርን ዳር ድንበር ከማስጠበቅ ባለፈ በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ የነቃ ትብብርና ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም መሰረት የልማት አጋር በመሆን በዛሬው እለት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሻራቸውን ማኖራቸውን ገልጸዋል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተሳተፈችው ተማሪ ፎዚያ ሙሀመድ፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለትውልድ የሚተርፍ አሻራ በመሆኑ የዚሁ ታሪክ አካል ለመሆን ተገኝቻለሁ ብላለች። በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የፀጥታ አካላት እና የአካባቢው ማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የ204 ዜጎች ህይወት አልፏል- የሕንድ ፖሊስ
Jun 12, 2025 671
አዲስ አበባ፤ሰኔ 5/2017 (ኢዜአ)፦በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የ204 ዜጎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቷ ፖሊስ አስታወቀ። በሕንድ 242 መንገደኞችን ይዞ በህንድ ሰሜን ምዕራባዊ ክፍል አህመዳባድ ከተማ ከሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ለንደን ጋትዊክ ለማምራት በተነሳበት ቅፅበት በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ላይ ተከስክሷል። በቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላን ውስጥ 169 ህንዳውያን፣ 53 የብሪታኒያ ዜጎች፣ 7 ፖርቹጋላዊ እና አንድ ካናዳዊ ነበሩ። በአደጋው የተረፈ ሰው ለማግኘት የሚቻልበት እድል እጅጉን የጠበበ ነው ሲል የአህመዳባድ ፖሊስ ኃላፊ ለአሶሲዬትድ ፕሬስ ገልጾ ነበር። ይሁንና ማምሻውን በወጣ መረጃ የ40 ዓመት የህንድ እና ብሪታኒያዊ ጥምር ዜግነት ያለው ቪሽዋሽ ኩማር ራሜሽ ከአደጋው መትረፉ ተጠቁሟል። እስከ አሁን የ204 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። የአውሮፕላኑ አካል የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ላይ ወድቆ ቢያንስ አምስት የህክምና ተማሪዎች መሞታቸውን እና 50 ገደማ የሚሆኑት መጎዳታቸው ተገልጿል። የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ መልዕክት አደጋው ቃል ከሚገልጸው በላይ ልብ የሚሰብር ነው ሲሉ ገልጸዋል። በአደጋው ለተጎዱ በሙሉ ልባዊ ሀዘናቸውን በመግለጽ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ኮሚሽኑ በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ማስፈን ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫው አድርጎ ይሰራል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 12, 2025 1180
አዲስ አበባ፤ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ አስተዳደር በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ማስፈን ዋንኛ የፖሊሲ የትኩረት አቅጣጫው በማድረግ እንደሚሰራ የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ ሊቀ-መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ ከሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር ዛሬ ትውውቅ እና ቆይታ አድርገዋል። ሊቀ-መንበሩ በስልጣን ጊዜያቸው ሊያሳኳቸው ስላቀዷቸው ተቋማዊ ግቦችና ቅድሚያ ሰጥተው ለመፈጸም ያሳቧቸውን ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ አስተዳደር በሰላም፣ ደህንነት፣ ልማትና ዓለም አቀፍ ትብብር ላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸዋል። መሐመድ አሊ ዩሱፍ ሰላምና ደህንነት የኮሚሽኑ ዋንኛ የትኩረት ማዕከል መሆኑን አመልክተዋል። ኢ-ሕገ መንግስታዊ የመንግስት ለውጦች በአፍሪካ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀናቸውን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት መሰል ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም ሰላምን በማስፈንና የዴሞክራሲ ስርዓትን በማረጋገጥ የህብረቱ አባል ሀገራትን ሉዓላዊነት እና ደህንነት መጠበቅ ላይ አበክሮ ይሰራል ነው ያሉት። ሊቀ-መንበሩ በገለጻቸው ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ መድረክ የአፍሪካን ድምጽ የበለጠ ለማጉላት እንደሚሻ ገልጸዋል። በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ውስጥ የአፍሪካ ህብረትን ሚና ማጠናከር ቁልፍ ግብ መሆኑን ጠቅሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግበት በጽኑ ሁኔታ እንደሚሟገት አመልክተዋል። ሊቀ-መንበሩ የፀጥታው ምክር ቤት አሁናዊ መዋቅር የታሪክ ኢ-ፍትሃዊነት በማለት የገለጹት ሲሆን አፍሪካ በዓለም አስተዳደር የሚገባትን ትክክለኛ ስፍራ በሚገልጽ ሁኔታ ምክር ቤቱ ማሻሻያ ሊደርግበት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። በሌላ በኩል በዲጂታል ኢኮኖሚና ሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት በአፍሪካ ፈጠራ እና ዘላቂ ልማትን ማሳለጥ ሌላው የትኩረት አቅጣጫ ነው ብለዋል። የህብረቱ ኮሚሽን ከቀጣናዊ ኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር ያለውን ትብብር የበለጠ በማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ወጥነት ባለው መልኩ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሊቀ-መንበሩ በአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል አማካኝነት ወረርሽኝን የመከላከል ዝግጁነት እና ምላሽ አቅም ላይ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱንም አንስተዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዲሱ ሊቀ-መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ በቀጣይ ከሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋር በየሶስት ወር ጊዜ ቆይታ እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል። በየካቲት ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መሐመድ አሊ ዩሱፍ ሙሳ ፋቂ ማህማትን በመተካት የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ነው።
ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ያላትን የአፈጻጸም ሪፖርቶች ማቅረብ ጀመረች
May 10, 2025 860
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2017(ኢዜአ)፦ በፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው። በጋምቢያ ባንጁል የአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት እየተካሔደ ባለው ስብሰባ ላይ በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር (ባንጁል ቻርተር) ወቅታዊ የኢትዮጵያ አፈጻፀምና በአፍሪካ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) መነሻ ወቅታዊ አፈጻፀም ላይ ልኡኩ ሪፖርቶችን ማቅረብ ጀምሯል። ሚኒስትር ዴኤታው ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በሪፖርት ዘመኑ በቻርተሩና ፕሮቶኮሉ መሰረት ያሉባትን ግዴታዎች ለመወጣትና የሰብአዊ መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር የተወሰዱ የፖሊሲ፣ የህግ እና ተቋማዊ እርምጃዎችን የሚመለከቱ ለውጦች ሪፖርት በዝርዝር ቀርቧል። በኮሚሽኑ መርሃ-ግብር መሰረትም ሪፖርቱን ተከትሎ ከኮሚሽነሮች ለተነሱ ጥያቄዎች ኢትዮጵያ በልዑካን ቡድኑ አማካኝነት ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2017 ምላሾችን ትሰጣለች ተብሎ እንደሚጠበቅም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል። መድረኩ ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ስምምነቶች መሰረት በአገሪቱ የሰብዓዊ መብቶችን እና የፆታ እኩልነትን ለማጎልበት ያላትን ቁርጠኝነት የምታሳይበት እንደሆነም ተገልጿል።
በቱርኪዬ ኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
Apr 23, 2025 1482
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2017(ኢዜአ)፦በዛሬው እለት በቱርኪዬ ኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። እንደ አናዶሉ የዜና ወኪል ዘገባ ዛሬ ቀትር ላይ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የኢስታንቡል እና ጎረቤት አካባቢ ነዋሪዎች በፍርሃት የመኖሪያ ህንጻቸውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓቸዋል። በሌላም በኩል ረፋዱ ላይ በኢስታምቡል አቅራቢያ የባህር ዳርቻ ቡዩኪክሚ የተባለ ስፍራ ላይ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አናዶሉ የዜና ወኪል የሃገሪቱን የድንገተኛ አደጋ መቆጣጠር ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል። በአደጋው ምንም የተመዘገበ ጉዳት እንዳልተከሰተ የጠቀሰው ዘገባው ነዋሪዎች የዚህ ዓይነት አጠራጣሪ ሁኔታ ሲገጥም የተጎዱ ሕንጻዎች ውስጥ እንዳይገቡ የግድ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ተሽከርካሪዎችን እንዳይጠቀሙና ሌሎች የጥንቃቄ መልዕክቶችን ባለስልጣኑ ማስተላለፉም ተገልጿል። የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውንና ለዜጎችም መልካም ሁኔታ እንዲገጥማቸው መመኘታቸው ተገልጿል። ፕሬዝዳንቱ ከሃገሪቱ የድንገተኛ አደጋ መቆጣጠር ባለስልጣንና ከሚመለከታቸው አካላት መረጃዎችን በመቀበል በቅርበት እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተገልጿል።
ሐተታዎች
የህንድ የፈጠራ ማዕከል - ባንጋሎሩ
Jul 2, 2025 205
ቤተልሄም ባህሩ(ኢዜአ) የዴልሂና አግራ ቆይታችንን ጨርሰን ወደ ቀጣይ መዳረሻችን ባንጋሎሩ ከተማ ልንጓዝ ስንሰናዳ አብዛኛው የጋዜጠኛ ልዑክ ያሳሰበው እንደሰም የምታቀልጠውን የአግራ ፀሀይና ሙቀት በባንጋሎሩም ታገኘን ይሆን? የሚለው ነበር። ሆኖም ከዴልሂ ኢንድራ ጋንዲ አየር ማረፊያ ተነስተን ለሶስት ሰዓት ከተቃረበ በረራ በኋላ ያገኘናት ባንጋሎሩ የተለየች ሆነን አገኘናት። ባንጋሎሩ ቀዝቀዝ ባለ አየር ነበር እንግዶቿን የተቀበለችን። በዕለቱ ከክፍሎቻችን ወጥተን በጋራ ወደአየር ማረፊያ የሚወስደንን ትራንስፖርት ስንጠባበቅ ከጋዜጠኛ ቡድኑ ስድስት አባላት ከአጠገባችን እንዳልነበሩ አስተዋልን። የት ጋር እንደተነጣጠልን አላስታውስም። በዚህ ምክንያት ግን የእለቱ ጉዟችን ተሰርዞ ከተማዋን ለማየት ስንዘዋወር የማውቀው ዓይነት እንጂ የተለየ ሙቀት አላስተናገድኩም። የ13 ወር ፀጋ በመባል የምትታወቀው አገሬ ኢትዮጵያ ከዳሎል እስከ ራስ ዳሽን ባላት የመልከዓ ምድር አቀማመጥና ልዩ ልዩ የአየር ጠባይ ሙቀቱንም፣ ቅዝቃዜውንም ማወቃችን እንደዚህ ለአለ አጋጣሚ መልካም ስሜት ይፈጥራል። በተወሰነ ደረጃ በህንድ ያጋጠመኝ የአየር ባህሪ ከአገሬ ጋር ቢመሳሰልብኝ የፈጣሪንና የተፈጥሮን ስራ አጃኢብ ብዬ እንዳልፍ አድርጎኛል። ባንጋሎሩ ከተማ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ማዕከል በመሆኗ የህንድ ሲልከን ቫሊ በመባል ትታወቃለች። ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ስፍራዎችም ከመገለጫዎቿ መካከል ናቸው። የጠፈር ጠበብቶቹ - ባንጋሎሩ ደርሰን በመጀመሪያ ያየነው ዓለም በስፔስ ሳይንስ እየሰራች ያለችውና እያስመዘገበችው የምትገኘው ውጤት ማሳያ የሆነውን የህንድ ስፔስ ምርምር ድርጅትን ነው። ተቋሙ የህንድ መንግስት የስፔስ ዲፓርትመንት አካል ሲሆን፤ ዶክተር ቪክራም ሳራብሃይ በተሰኙ ባለራዕይ በ1962 የተወጠነና አሁን ላይ በዘርፉ ተገዳዳሪ መሆን የቻለ ነው። የተቋሙ ዓላማ የስፔስ ቴክኖሎጂዎችን በማልማትና በመተግበር ለተለያዩ አገራዊ ጥቅሞች ማዋል መሆኑን ተከትሎ የሳተላይት ማምጠቂያ መሳሪያዎችን የማምረት ስራን ጨምሮ ከአገሩ አልፎ ለሌሎች አገራትም በዘርፉ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። የተደረገልን ገለፃ አብዛኛውን ጋዜጠኛ ያስደመመ ነበር ከገለፃ በኋላ በጋዜጠኞች የተነሳው ሃሳብም ህንድ በስፔስ ዘርፍ ያላት ልምድና ያከናወነችው ተግባር በቀጣይም ልትሰራ የወጠነቻቸው ሃሳቦች የአገሪቱን መዳረሻ የተለሙ በአገራቸው እንዲተገበር የሚናፍቁት መሆኑን ነው። ተቋሙ በዘርፉ ለተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን የአቅም ግንባታ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና በቀጣይም ትብብሩን የሚያጠናክር መሆኑን ከተደረገልን ገለፃ ተገንዝበናል። በሳይንስ፣ ኢንጂነሪንግና አስተዳደር ምሁራንን በማስተማር እያበረከተ ያለው የህንድ የሳይንስ ኢንስቲትዩት በባንጋሎሩ ከጎበኘናቸው መካከል የሚጠቀስ ነው። ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የተውጣጡ ተማሪዎችን የሚያስተምርና ከተቋማት ጋርም በዘርፉ የሚሰራ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ከጅማ፣ በተግባር ለመቀየር ሲታትሩ የስታርት አፖችን የምርት ውጤቶቻቸውን ሲፈትሹና ሲሞክሩ ተመልክቻለሁ። በኢትዮጵያም አሁን ላይ ለስታርት አፖች በተሰጠው ትኩረትና በተፈጠረው ምቹ ስነ ምህዳር የፈጠራ ውጤቶች እያደጉና እየተበራከቱ መሆናቸው የሚታወቅ ነው። እንደ አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተቋማት የተማሪዎችን ፈጠራ ወደ ውጤት ለመቀየር እየተጉ መሆኑና የስታርት አፕ ኤግዚቢሽንና የሰመር ቡት ካምፖች ፈጠራን ምን ያህል እያበራከቱ መሆናቸው በጉብኝቱ ወቅት ወደ አዕምሮዬ የመጣ የአገሬው ህዝብ በውጤት የታጀበ ጥረት ነው። ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በባዩቴክኖሎጂ ዘርፍ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘው ባዮኮንም ከባላንጎሩ የጉብኝት መዳረሻችን መካከል የሆነና አስፈላጊ መድሀኒቶችን የሚያመርትና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ላይም እየሰራ ያለ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት የአቅም ግንባታ ስልጠናው ተጠቃሚ ናቸው። ከ120 በላይ በሆኑ አገራት ለስኳርና ካንሰር ህመም የሚያገለገሉ መድሀኒቶችን በማምረትና በማሰራጨት ለህሙማን ፈውስና ለጤናው ዘርፍ ስርዓት አስተዋፅኦ እያበረከተም ይገኛል። የተቋሙ ላቦራቶሪና ዘመኑን የዋጀና ደረጃውን የጠበቀ ማምረቻ ፋብሪካን መጎብኘቴ አለም በፋርማሲዩቲካልስ ዘርፍ ያለችበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። የባንጋሎሩ ቤተመንግስት - ይህን ቤተ መንግስት ማስቃኘቴን ከመጀመሬ በፊት በስፍራው ካስገረመኝ ነገር ላወጋችሁ ወደድኩ። ቤተ መንግስቱን ለመጎብኘት ያቀናነው በእለተ ሰኞ ነበር። ሆኖም ምድረ ግቢውን ቃኝተን ስለህንፃው ሰምተን ከመመለስ ውጪ ወደ ውስጥ አልዘለቅንም። ለምን? ለሚለው ምላሹ በዚህ ስፍራ "ሰኞ የእረፍት ቀን ናት" ነው። እንዴት ካላችሁ ቤተ መንግስቱ ቅዳሜና እሁድ በበርካታ ሰዎች የሚጎበኝ መሆኑን ተከትሎ በስፍራው ለሚሰሩ ሰራተኞች የእረፍት ቀናቸው ሰኞ በመሆኑ ነው። የቤተ መንግስቱ ምድረ ግቢ ሰፊና ልምላሜ የተላበሰ ሲሆን፤ የሚያምርና ለዓይን የሚስብ ኪነ ህንፃ ያለው ነው። አሰራሩና ውጥኑም እንደሚከተለው ነው። በዎዲየር ስርወ መንግስት ንጉስ ቻማራጃ ዋዲያር ወደ እንግሊዝ ባደረጉት ጉዞ በለንደን ዊንሶር ግንብ ይደነቃል። ተደንቆም አልቀረ የባንጋሎሩ ቤተ መንግስትን በተመሳሳይ ሁኔታ ይገነባል። ይህ ቤተ መንግስት በተወሰነ መልኩ የመካከለኛው ዘመን የኖርማንሲና የእንግሊዝ ግንቦችን ይመስላል። ቪድሃና ሶውዳ የካራንታካ ህግ አውጪ አካል መናገሻ በጉብኝታችን ያየነው ሌላው መዳረሻ ስፍራችን ነው። የህግ አውጪና የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የያዘው ይህ ህንፃ ህንድ ነፃነቷን ካገኘች በኋላ በራሷ መሀንዲስ የሰራችው የመጀመሪያው ህንፃ መሆኑ ተገልፆልናል። የህንፃ ግንባታ ጥበብ ማሳያ፣ የፖለቲካ መናገሻ እንዲሁም የባህል ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል። እንደአጠቃላይ በቆይታዬ የተመለከትኩት የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ማበረታቻ እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስራ ኢትዮጵያ እያከናወነች ካለው የኮሪደር ልማትና ስታርት አፕን የማበረታታት ብሎም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስነ ምህዳር ምቹነት ስራዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ነው። በህንድና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረ፤ ለሁለት ሺህ ዓመታት የዘለቀ መሆኑን የታሪክ መዛግብት ያሳያል። የህንድና ኢትዮጵያ ግንኙነት በአክሱም ስርወ መንግስት ኢትዮጵያና ህንድ በአዱሊስ ወደብ በኩል የንግድ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በወቅቱ ኢትዮጵያ ቅመማ ቅመምና ሐርን ከህንድ ትገበይ ነበር። ህንድ ደግሞ ወርቅና የዝሆን ጥርስን ከኢትዮጵያ ትሸምት ነበር። ህንድ ከንግድ ልውውጥ ባሻገር በኢትዮጵያ ኪነ ህንፃ ግንባታ ላይ አሻራዋን አኑራለች። በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍም ትልቅ አበርክቶ ያላት አገር ናት። ህንድ ነፃነቷን ካገኘችበት እኤአ 1948 አንስቶ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ኢትዮጵያና ህንድ ሌላው የሚያመሳስላቸው ነገር ሆኖ ያገኘሁት የአምራች ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እያከናወኑ ያሉት ንቅናቄ ነው። ህንድ እ.አ.አ ከ2014 ጀምሮ የአምራች ዘርፉን ለማበረታታት "ሜድ ኢን ኢንዲያ" በሚል ለአስር ዓመት የተገበረችውና በርካታ ለውጥ የተመዘገበበት ንቅናቄ በኢትዮጵያ ከ2014ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ ካለውና የሃገር በቀል ምርቶች እና አምራቾችን ማጠናከር፣ የኢንዱስትሪያል ማህበረሰብ ግንባታን ማሳደግ ፣ ምቹ የቢዝነስ ከባቢ መፍጠር እና የጥናት እና ምርምር ችግር ፈቺነትን ማሳደግን ዓላማ ካደረገው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ጋር የተመሳሰለ ነው። ንቅናቄ በኢትዮጵያ መተግበሩ ዓመታዊ የዘርፍ ዕድገት፣ የማምረት አቅም አጠቃቀምና ገቢ ምርት በመተካት በኩል ጉልህ ሚና እየተወጣ መሆኑም ይታወቃል። በህንድ ተዘዋውሬ በተመለከትካቸው ከተማዎች ባሉ ጎዳናዎች ከታዘብኩት ነገር ሰዎች ከሱቅ ለሚገበያዩት ነገር ሳይቀር በዲጂታል መንገድ ክፍያ መፈፀማቸውን ነው። በባጃጅና በሞተር የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘትም ጭምር ሞባይሉን በመጠቀም “ይህ ቦታ የት ነው?” ሳይል ያሻዎት ስፍራ መድረስም ሌላው ትዝብቴ ነው። ይህ ነገር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትኩረት አግኝተው እየተሰራባቸው ካሉት የዲጂታል ክፍያና ዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ መርሃ ግብር ጋር የሚመሳሰል ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በቆይታችን ልክ እንደአትሌቶቻችን ሁሉ በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርጎ የሚያስነሳውን ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝናና ክብር ለማስተዋል ችያለሁ። ፀጉረ ልውጥ መሆናችንን የተገነዘቡ በገበያ ማዕከላት የሚያገኙን እንዲሁም በምንጎበኛቸው ተቋማት የምንተዋወቃቸው ህንዳውያን "ከየት ናችሁ?" ብለው ሲጠይቁ፤ ለእኔና አንድ ከሌላ መገናኛ ብዙሃን የሄድን "ከኢትዮጵያዊ" ስንል የሚከተልልን ምላሽ "አሃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ" የሚል ነው። ይህም አየር መንገዱ ስሙ ከኢትዮጵያ ተሰናስሎ የሚጠራ የአገሪቷ መታወቂያ ተቋም መሆኑን ያስገነዘበኝ ነው። ከህንዳውያን ጋር ብቻ ሳይሆን አብረን ከተጓዝን ጋዜጠኞች አንዱ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእናንተ የብቻ ሳይሆን እኛንም እንደራሳችን ሆኖ እያገለገለን ያለ የጋራ አየር መንገዳችን ነው" ሲል ነው የገለፀው። ይሄ ለእኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ኩራት ብቻ ሳይሆን መለያ ምልክትም ጭምር መሆኑን የተረዳሁበት አጋጣሚ ነው። በቀናት ቆይታዬ በእንግዳ አክባሪነታቸውና በለገሱን ፍቅርና እንክብካቤ ከአገሬ የራቅኩ ያህል ሳይሰማኝ ብቸኝነትን ሳላስተናግድ እንደውም እየናፈኳቸው እንድመለስ ላደረጉኝ ህንዳውያን በከበረ ሰላምታ ላመሰግን እወዳለሁ።
ውበትና ትጋት በህንድ
Jun 27, 2025 332
በቤተልሄም ባህሩ (ኢዜአ) በልጅነቴ እያየሁ ያደግኳቸው አብዛኛዎቹ ፊልሞች የህንድ ናቸው። ይህ ደግሞ ከአገራችን አርቲስቶች በላይ የህንድ የፊልም ተዋንያኑን ስም ለመለየት አስችሎኛል። የህፃንነት ዘመኔን የሚያስታውሱኝን ፊልሞች ከትዝታ ማህደሬ እያወጣሁ ከመተረክ በስተቀር ህንድን የማይበት አጋጣሚ ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም። እነዚያን በህንድ ፊልም የማደንቃቸውን የምደመምባቸውን የህንዳውያንን ሶስት ከተሞች ለመጎብኘት ከተመረጡ ከሰሜንና ምስራቅ አፍሪካ የተውጣጡ ጋዜጠኞች መካከል መሆን ድንገቴ ሆነብኝ። እኔም ብቻ ሳይሆን አብዛኛዎቹ የጋዜጠኞች ልዑካን ህንድ ከልጅነት ትዝታቸው ጋር የተሳሰረ አንዳች ነገር አለው። ህንድ በፊልሞቿ የሚያቋት ስለመሆኑ ጉብኝቱን ተከትሎ በተካሄደው በዶርሻን የቴሌቪዥን ጣቢያ ውይይት ላይ ሲያነሱ ሰምቻለሁ። በዓለም ላይ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚዋ ህንድ የብዝሃ ባህል፣ ቋንቋና ሃይማኖት አገር ናት። በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኪነ ጥበብ ስራዎቿ በዓለም ላይ ትታወቃለች። ለጉብኝት ከተጋበዙት የጋዜጠኞች ቡድን መካከል አባል ሆኜ በዴልሂ፣ አግራና ባንጋሎሩ ከተሞች በተጓዝንባቸው ስፍራዎች ሁሉ የታዘብኩት ህንዳዊያን በስራና ትጋት ላይ መሆናቸውን ነው። ሁሉም ነገውን ለማሳመር የራሱን ድርሻ ለማኖር፤ ለሀገሩ እድገትና ልማት አሻራውን ለማኖር እንደሚታትር መረዳት ይቻላል። ባረፍንበት ሆቴል ያሉ ሰራተኞች፣ በገበያ ስፍራ የምናገኛቸው ሰዎች እንዲሁም በጎበኘናቸው ስፍራዎች ያሉ ሰዎች ሁሉ ለሀገራቸው እድገትና ልማት ብሎም ነጋቸውን ለማሳመር የራሳቸውን ድርሻ ለማኖር ይታትራሉ። አብሬ ከነበርኳቸው ጋዜጠኞች ጋር ስናወጋ የምናነሳው በከተማዋ በተጓዝንባቸው ጎዳናዎች የምናየው የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በየተቋማት የሚታትሩ ሰራተኞች እንዲሁም በንግድ የተሰማሩ ሰዎች ደፋ ቀና ማለት ለአገር የሚያደርጉትን ልፋት ነው። አንድ ቀን በጋራ ሆነን ወደገበያ ስፍራ ስናቀና በፍጥነት የሚደርሱ ምግቦች ተመግበው ለመሄድ የሚፋጠኑ ህንዳውያንን ያየ የጋዜጠኛ ቡድኑ አባል መሰል ልምድና ጊዜ አጠቃቀም በአፍሪካም ሊለመድ የሚገባውና የአህጉራችንን የስራ ባህልና እድገት የሚያረጋግጥ መሆኑን የገለጸበት ሁኔታ ለአገሬው ህዝብ ታታሪነት እንደማሳያ አድርጌ ላነሳው ወደድኩ። በሄድንባቸው አካባቢዎች ሁሉ አዲስ ሰው ሲያዩ ለማገዝ አና ስለነገሮች ለማስረዳት የሚፈጥኑ ዜጎችን ተመልክቻለሁ። በተጓዝኩባቸው ከተማዎች ያየኋቸውን ስፍራዎች ከማስታወሻዬ እየነቀስኩ ለእናንተ ላካፍል ወደድኩ። በቅድሚያ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የስድስት ሰዓት ተኩል በረራ በማድረግ የመጀመሪያ መዳረሻ ያደረግናትን ዴልሂን እንቃኛለን። ዴልሂ- ታሪካዊ ህንፃዎችን ከአዲሶቹ ጋር አጣምራ የያዘች ጥንታዊ ስልጣኔን ከዘመናዊው ጋር አዋህዳ የምታንፀባርቅ ከተማ ናት። በከተማዋ በተዘዋወርንባቸው ስፍራዎች ሁሉ ከጎዳናዎቿ እስከ ህንፃዎቿ ምድረ ግቢ ድረስ በእፅዋት የተሞላችና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትኩረት የሰጠች መሆኗን በግልፅ ያሳየች ከተማ ናት። በዴልሂ ብቻም ሳይሆን በተዘዋወርንባቸው በሶስቱም ከተሞች ጎዳና ስንጓዝ ያየናቸው ግዙፍ ዛፎች ትናንት አገሪቷ ለእፅዋት የሰጠችው ትኩረት ዛሬ ላይ ፍሬ አፍርቶ አስተዋልኩ። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ዓመታት እየተከናወነ ያለው ተግባር እንዲሁም በኮሪደር ልማት ከተሞችን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት አሁን ላይ ካመጡት ለውጥ ባለፈ ለወደፊት የሚኖራቸውንም መዳረሻ አሻግሬ ለማየት አስችሎኛል። አሰላሳዮቹ - በዴልሂ ቆይታችን በመጀመሪያ ያቀናነው ጥናቶችን በመስራትና ውይይቶችን በማድረግ በኩል አበርክቶ እያደረገ ያለውን ኦብዘርቨር ሪሰርች ፋውንዴሽን የተሰኘ አሰላሳይና ሃሳብ አመንጪዎች ቡድን (ቲንክ ታንክ ግሩፕ) ነው። ተቋሙ በአገር ውስጥ ባሉ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የመስራት ተልዕኮን አንግቦ የተነሳ ቢሆንም አሁን ላይ ከኢኮኖሚና እድገት ባለፈ በኢነርጂ፣ አካባቢ፣ በደህንነትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑና ለውሳኔ የሚጠቅሙ ሃሳቦችን በማመንጨት የአገሪቷን ህዝብና መንግስት እያገዘ ይገኛል። ከተቋሙ አባላት ጋር ባደረግነው ቆይታ ለራስ ችግር የራስ መፍትሄ ማምጣት ተገቢ ስለመሆኑ በአጽንኦት አንስተዋል። የአፍሪካ አገራት ትብብር የአህጉሪቷን ልዕልና ለማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑም ተነስቷል። የአሰላሳይና ሃሳብ አመንጪዎች ቡድን አባላቱ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ጨርሰን በቀጣይ ያመራነው በህንድ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ባሉ አገራት ጭምር በባቡር መንገድ መሰረተ ልማት ላይ አሻራ እያኖረ ወዳለው ራይትስ ወደተሰኘው ተቋም ነው። የህንድ የባቡር መንገድ የቴክኒካልና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት (Rail India Technical and Economic Service) የተሰኘው ይህ ተቋም ላለፉት 51 ዓመታት በባቡር መንገድ ጠበብቶች አማካኝነት በህንድና በመላው ዓለም ባሉ 62 አገራት በዘርፉ ሲሰራ ቆይቷል። የእጅ ጥበብ ገበያ - ቀጣይ መዳረሻችን ደግሞ ዲል ሃት ኢና የተሰኘው የባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጦች እንዲሁም የቤት ማስዋቢያዎች መገኛ ወደ ሆነው ገበያ ነው። ገበያው ባይገበዩበትም ዞረው እንዲቃኙ የሚያስገድድ አንዳች ድምቀትን የተላበሰ መሆኑን ባደረኩት ቆይታ አስተውያለሁ። የንግድ ማህበር የሆነው የህንድ ኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን (ሲአይ አይ) በዴልሂ ቆይታችን ካየናቸው ተቋማት መካከል የሚጠቀስ ነው። ተቋሙ የንግድ፣ ፖለቲካ፣ የትምህርትና የሲቪል ማህበረሰብ አመራር አባላትን በጋራ በማሰለፍ ዓለም አቀፍና የኢንዱስትሪ አጀንዳዎችን እንዲቀርፁ የሚሰራ ነው። አደጋን የሚቋቋም መሰረተ ልማት ጥምረት (CDRI) በነበረን ቆይታ ጥምረቱ ከአገራት፣ ከተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎችና መርሃግብሮች፣ ከፋይናንስና የግል ተቋማት ጋር በመተባበር የአየር ንብረትና የአደጋ ስጋትን የሚቋቋም መሰረተ ልማት አስተዳደር ላይ እየሰራ መሆኑን ተገንዝበናል። ጥምረቱ የአደጋ ምላሽና መልሶ ማቋቋም፣ በተቋማትና ህብረተሰብ አቅም ግንባታ ድጋፍ ላይ ይሰራል። ጥምረቱ 46 አባል አገራትና ስምንት አጋር ድርጅቶች ያሉበት ሲሆን፤ አገራትና ዓለም አቀፍ አካላትን በማስተባበር የገንዘብና ቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ የጥናትና ፈጠራዎች ውጤቶች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን የሚጋሩበትም ነው። የህንድ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዴልሂ(IIT Delhi) ሌላው የጉብኝት መዳረሻችን ነበር። ኢንስቲትዩቱ በኢንጂነሪንግና ሳይንስ ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በርካታ ሰዎችን አስተምሮ ያስመረቀ ሲሆን፤ የተለያዩ ሳይንቲስቶች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ስራ ፈጣሪዎችን ማፍራት የቻለ ተቋም መሆኑን መገንዘብ ችለናል። ብሄራዊ ሙዝየም - በኒው ዴልሂ የሚገኘው የህንድ ብሄራዊ ሙዚየም በአገሪቱ ያለ ትልቁ ሙዚየም ሲሆን፤ በጉብኝታችን ወቅት ለዘመናት የቆየች ቅሪተ አካልን ጨምሮ፣ የተለያዩ የጥበብ ውጤቶችና የታሪክ አሻራ ማሳያ ስራዎችን ቀርበው ይጎበኙበታል። በዴልሂ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተደረገልን የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባባልና ውይይት ህንድና አፍሪካ የጠነከረ ቁርኝት ያላቸውና በንግድ አጋርነትት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ መሆኑ ተመላክቷል። በተደረገልን ገለፃ ህንድና የአፍሪካ የንግድ መጠን 100 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ነው። ህንድ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ ፋርማሲዩቲካል ፣ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪዎች ፣ ማዕድን እና የባንክ ዘርፎችን ያላት የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ወደ 75 ቢሊዮን ዶላር ገደማ መድረሱም ተገልጿል። ኢትዮጵያም ከህንድ ጋር ለዘመናት የዘለቀ ወዳጅነት ያላትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷም ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑ ተነስቷል። ሁለቱ አገራት ያላቸው ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን በባህል ትስስር ጭምርም የተጋመደ መሆኑ ተመላክቷል። ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአህጉሪቱ ካሉ አገራት ጋር የምታደርገው ትብብርና ወዳጅነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተነስቷል። አግራ- የህንድ ታሪክ፣ ባህልና ኪነ ህንፃ መገለጫ በሆነችው አግራ ተገኝተን የጎበኘነው ህንድ ስትነሳ ስሙ ተያይዞ የሚነሳውን ታጅ መሃልን ነው። ታጅ መሃል በእምነ በረድ የተሰራ ውብ ኪነ ህንፃ ሲሆን፤ ንጉስ ሻህ ጃሃን ከሌሎች ሚስቶቹ ሁሉ አስበልጦ ለሚወዳት ሚስቱ ሙምታዝ መሀል ክብር ሲል የገነባው ድንቅ የእጅ ስራ ውጤት ነው። ታጅ መሃልን ስንጎበኝ የነበረው ሙቀት ሀይለኛ ቢሆንም ላባችን እየተንቆረቆረ ንጉሱ ለፋርስ ልዕልቷ ሚስቱ የነበረውን ፍቅር በተመለከተ በአስጎብኚያችን የሚሰጠንን ማብራሪያ ስናደምጥና የፍቅር ሃያልነትን ስናደንቅ ነበር። በዴልሂ ከጉብኝታችን ባሻገር በኢንዲያን ጌትና በገበያ ቦታዎች እንዲሁም በከተማዋ ጎዳናዎች ተዘዋውረን የህዝቡን ፍቅርና ተባባሪነት አይተናል። በተለይ ቦታ የጠፋን መሄድ ያሰብንበት ቦታ እንዳለ የሚያመላክት ፍንጭ በግርታችን ያስተዋሉ ከመሰላቸው "እዚህ መሄድ ፈልገህ ነው ይህን እዚህ ማግኘት ትችላለህ" የሚል ጥቁምታ በመስጠት እንግዳ ተቀባይነትና ሰው አክባሪነታቸውን ይገልፁልሃል። በዴልሂና አግራ የነበረንን ጉብኝትና ትዝታ እያሰላሰልን ቀጣይ መዳረሻ ያደረግናት ባንጋሎሩ ከተማን ነው። ባንጋሎሩ ቀጣይ ትረካችን ይሆናል።
ስራዋን በውጤታማነት በማስቀጠል ለሌሎች ወጣቶችም መትረፍ የቻለችው ወጣት
May 22, 2025 873
ብርሃኑ ፍቃዱ - ከሰቆጣ ኢዜአ በ2013 ዓ.ም የልብስ ስፌት ስራ የጀመረችው ወጣት ማህደር አስማረ፤ ነዋሪቷ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ሰቆጣ ከተማ ነው። ስራዋን በውጤታማነት የቀጠለችው ወጣት ከአንድ የልብስ ስፌት መኪና ተነስታ ወደ ሶስት የልብስ ስፌት መኪና የደረሰች ሲሆን ካፒታሏንም ከዓመት ዓመት በማሳደግ ላይ ትገኛለች። ስራዋን ለመጀመርም ባጠራቀመችው አነስተኛ ገንዘብ ቤት ተከራይታ ነበር። ከልብስ ስፌት መኪናው በተጨማሪ የሌዘርና የጥልፍ ማሽኖችን በማስመጣት የፋሽንና ዲዛይን ስራና ማሰልጠኛ ማዕከል በመክፈት ለሌሎች ወጣቶች መትረፍ የቻለችበትን አቅም ገንብታለች። የማሰልጠኛ ማዕከሉን ለመክፈት እስከ 500 ሺህ ብር ወጪ ማድረጓን የገለፀችው ወጣት ማህደር፤ 30 ተማሪዎችን ተቀብላ አጫጭር ስልጠና ለመስጠት የምዝገባና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቃለች። "ውጤታማ ለመሆን ጠንክሮ ከመስራት ውጪ ሴትነቴም ሆነ ሌላ ምንም የሚያግደኝ ነገር የለም" የምትለው ወጣት ማህደር ፤ የፋሽንና ዲዛይን ማሰልጠኛ ማዕከልን ከማስፋት ባለፈ በቀጣይ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት አቅዳ እየሰራች መሆኑን ገልፃለች። ወጣት መሰረት ጌታቸው በማህደር የልብስ ስፌትና የፋሽንና ዲዛይን ማሰልጠኛ ማዕከል ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የስራ እድል ተጠቃሚ ሆናለች። ከድርጅቱ በቂ የልብስ ስፌት ሙያ፣ ልምድና እውቀት መቅሰሟንና ለዚህም ማህደር እውቀቷንና ልምዷን ሳትሰስት በማከፈሏ ብቁ ሰራተኛ እንድትሆን አድርጋታለች ። የማሰልጠኛ ማዕከሉ በከተማዋ መከፈቱ በተለይም ሴቶችና ወጣቶችን በዘርፉ ሰልጥነው የሙያ ባለቤት በመሆን ሰርተው የሚለወጡበት እድል የከፈተ ነው በማለት ትገልጻለች። ከወጣት ማህደር ጊዜን በአግባቡ መጠቀምና ጠንክሮ መስራትንና ቁርጠኝነትን ትምህርት ወስጃለሁ ያለችው ወጣት መሰረት ፤ በልብስ ስፌት ዘርፍ ላይም ውጤታማ ለመሆን እየተጋች መሆኑን ትናግራለች። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስራና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ ዲያቆን ኪዳነ ማርያም ገብረህይወት፤ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ለይተው ከተንቀሳቀሱ ውጤታማ እንደሚሆኑ ወጣት ማህደር ትልቅ አርአያ ናት ይላሉ። ለአብነትም እንደ ወጣት ማህደር ያሉ ታታሪ ወጣቶችን በስፋት ለማፍራት በስራ እድል ፈጠራ ላይ በማተኮር እየተሰራ እንደሚገኝ ያስረዳሉ። የወጣቷን አርአያነት ለማስፋት በቀጣይ የብድር፣ የመስሪያና መሸጫ ቦታና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ እንደሚያበረታቱ አረጋግጠዋል። ወጣቶች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በባለፉት ወራት ለ11 ሺህ ሰዎች የስራ እድሉ ተጠቃሚ መሆናቸውንም አውስተዋል።
የኢትዮጵያ የእናቶች ሞትን ምጣኔ ቅነሳ ስኬቶች እና ቀሪ የቤት ስራዎች
May 13, 2025 987
የዓለም የጤና ድርጅት (ደብሊውኤችኦ) የ2025 ዓለም የጤና ቀንን እ.አ.አ አፕሪል 7, 2025 አክብሯል። የዘንድሮው ዓመት የቀኑ መሪ ሀሳብ “ የእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ፣ ለመጻኢው ብሩህ ጊዜ” የሚል ነው። የዓለም የጤና ጉዳዮች የበላይ አካል የሆነው ደብሊውኤችኦ መሪ ሀሳቡን መሰረተ በማድረግ ዓመቱን ሙሉ የእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ አስመልክቶ ንቅናቄ ያደርጋል። በኢትዮጵያም የዓለም የጤና ቀን ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው እንጦጦ ፓርክ “ ከቃል ያለፈ የተግባር ምላሽ” በተሰኘ ሁነት ተከብሯል። በአከባበሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች፣ የጤና ሰራተኞች፣ ቤተሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። የጤና ሚኒስቴር፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሁነቱን በጋራ አዘጋጅተውታል። በእንጦጦ ፓርክ የነበረው የዓለም የጤና ቀን አከባበር ሁነቱን አስቦ ከመዋል ያለፈ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ ለእናቶች እና ህጻናት ሞት ቅነሳ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳየቷን ገልጿል። የእናቶች እና ህጻናት ጤና የጤና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊ መብት፣ የማህበራዊ ልማት እና የብሔራዊ ልማት ጉዳይም ጭምር እንደሆነ የዘንድሮው የዓለም የጤና ቀን አከባበር ያሳየ እንደሆነ ተገልጿል። እንደ ዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ከ100 ሺህ እናቶች መካከል ከ400 በላይ የሚሆኑት ህይወታቸውን ያጡ ነበር። ኢትዮጵያ ይሄን አሃዝ በመቀየር የራሷን ታሪክ ፅፋለች። በአሁኑ ሰዓት የእናቶች ሞት ምጣኔ ከ100 ሺህ እናቶች ወደ 195 ዝቅ ብሏል። ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ኢትዮጵያ በጤናው ስርዓት፣ የሰው ኃይል ስልጠና እና የአገልግሎት አቅርቦት ላይ እያደረገች ያለውን ዘላቂ ኢንቨስትመንት እንደሚያሳይ ድርጅቱ ገልጿል። ይሁንና አሁንም በኢትዮጵያ በየአመቱ በአማካይ 8 ሺህ ገደማ እናቶች በወሊድና ከወሊድ ጋር በተገናኘ ችግር እንደሚሞቱ መረጃው ያመለክታል። በእናቶች እና ህጻናት ጤና ጥበቃ እየተደረገው ያለው ዓመታዊ ንቅናቄ ለለውጦች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ቀሪ የቤት ስራዎች ማጠናቀቅ እንደሚገባ የሚያመላክት ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የሰው ኃይል ስልጠናን በማስፋት፣ የእናቶች እና ህጻናት ክብካቤን ማሻሻል፣ በዲጂታል መሳሪያዎች አማካኝነት የአገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር ላይ መልካም ስራዎች ቢያከናውንም አሁንም የአገልግሎት ተደራሽነት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት ድርጅቱ አሳስቧል። የጤና መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ቁጥርን መጨመር ሌሎች ትኩረት የሚያሻቸው ጉዳዮች ናቸው ብሏል። የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቅኝትና ምላሽ ስርዓትን ማጠናከር ሌላኛው በድርጅቱ የቀረበ ምክር ሀሳብ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ቤጆይ ናምቢያር በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በማደግ ላይ በሚገኙ ሀገራት ያለው የእናቶች እና ህጻናት ሞት አሳሳቢ እንደሆነና ጠንካራ ምላሽ እንደሚያስፈልገው አመልክተዋል። በዘላቂ ልማት ግቦች እ.አ.አ በ2030 ከ100 ሺህ እናቶች የሚሞቱን ወደ 70 ዝቅ የማድረግ ግብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራት ለማሳካት እየሄዱበት ያለው ርቀት አመርቂ አለመሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከተቀመጠው ግብ አንጻር ብዙ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባት የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል። ይሁንና ኢትዮጵያ በዓለም የፋይናንስ ፈተናዎች እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በግልጽ ያሳየች ሀገር መሆኗ ተገልጿል። ዓለም በተግባር የታገዘ ምላሽ ከሰጠ መከላከል የሚቻሉ የእናቶች እና ህጻናትን ሞት ማስቀረት ሊሳካ የማይችል ህልም አይደለም። ከእንጦጦ ፓርክ ጎዳናዎች አንስቶ በሀገሪቷ ክፍሎች በሚገኙ የጤና ማዕከላት የእናቶች እና ህጻናትን ሞትን ለመቀነስ የሚወሰዱ እያንዳንዱ እርምጃዎች የወደፊቱን የዓለም መጻኢ ጊዜ ብሩህ የማድረግን ራዕይን የሚያሳካ ነው ሲል የዓለም የጤና ድርጅት ጽሁፉን ቋጭቷል።
ትንታኔዎች
የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አሻራ ያረፈበት የኢትዮ-ታንዛንያ ወዳጅነት
Dec 17, 2024 3140
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ እና ምሥራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ማሕሙድ ታቢት ኮምቦ በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል። ስብስባው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ትስስር እና የጋራ ትብብር የማጠናከር ዓላማ የያዘ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም ከታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከነበሩት ጃንዋሪ ማካምባ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት የኮሚሽኑን ስብስባ ለማካሄድ ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ወዳጅነት በቅርበት ለመረዳት የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄን ማየት ግድ ይላል። የመላው ጥቁር ሕዝቦች ንቅናቄ የሆነው ፓን አፍሪካኒዝም ጅማሮ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የፓን አፍሪካኒዝም መሰረት የሆነችው ኢትዮጵያ የንቅናቄው ፋና ወጊ በመሆን ወሳኝ ሚና ተጫውታለች። የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው በመቆም ትግል ሲያደርጉ ከነበሩት አገራት መካከል ታንዛንያ ትገኝበታለች። በፓን አፍሪካኒዝም ትግል ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ መሪዎች መካከል ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ እና የታንዛንያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጁሊዬስ ኔሬሬ ተጠቃሽ ናቸው። መሪዎቹ ለአፍሪካ አገራት ከቅኝ አገዛዝ መውጣት ትልቅ ሚና በመጫወት ሕያው አሻራቸውን አሳርፈዋል። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በእነዚህ መሪዎች ጊዜ የተጀመረ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። አገራቱ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጣር ግንቦት 25 ቀን 1963 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (በአሁኑ መጠሪያው የአፍሪካ ኅብረት) መቋቋሙ ሲበሰር መስራች አባል አገራት ነበሩ። ኢትዮጵያና ታንዛንያ በየአገራቱ ኤምባሲያቸውን በይፋ በመክፈት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናክር እየሰሩ ይገኛሉ። አገራቱ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችላቸው በርካታ አቅሞች አሉ። ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ባላቸው የቁም እንሥሳት ኃብት ከአፍሪካ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ አገራት ናቸው። ሁለቱ አገራት በሚያደርጓቸው የጋራ ምክክሮች ይሄን ሰፊ ኃብት በመጠቀም የንግድ እና ኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጊዜ ያነሳሉ። ግብርና፣ የሰብል ምርት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ እና አቪዬሽን ከሁለቱ አገራት የትብብር መስኮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ በርካታ ታንዛንያውያን ፓይለቶች እና ኢንጂነሮችን አሰልጥኖ አስመርቋል። አቪዬሽንም የሁለቱ አገራት ቁልፍ የትብብር መስክ በሚል ይነሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም በታንዛንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። አገራቱ በወቅቱ በባህልና ኪነ-ጥበብ፣ በግብርና እንዲሁም በኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቶቹ የሁለቱ አገራት ትብብር ይበልጥ ለማጠናክር ትልቅ ፋይዳ አላቸው። የዛሬው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም የስምምነቶችን አፈፃጸም በመገምገም ትግበራውን ማፋጠን የሚያስችል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰሞኑ የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ይታወቃል። የቀጣናው ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ (ሃይዌይ) ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ትስስር ኢትዮጵያና ኬንያን ያስተሳሰረ መሆኑ ይታወሳል። የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ክፍል ደግሞ ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተዘረጋ ሲሆን የኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ተጠናቆ የሙከራ ኃይል አቅርቦት መጀመሩን የውኃና ኢኒርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ይህ ቀጣናዊ የኃይል ትስስር በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በማረጋገጥ በሀገራት መካካል ትብብርን እና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ከኢትዮጵያ እና ታንዛንያ አልፎ በቀጣናው ያለውን ትስስር ለማፋጠን ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል። ሁለቱ አገራት በቅርቡ ወደ ትግብራ ምዕራፍ የገባው የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን በአገራቸው ፓርላማ ማጽደቃቸው ይታወቃል። ስምምነቱ በናይል ተፋስስ የውኃ ኃብትን ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ በበጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው። አገራቱም በውኃ ኃብት ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ያስተሳሰራቸው ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ትብብራቸውን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሸጋግር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።
ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረው የኢትዮ-አልጄሪያ ወዳጅነት
Dec 16, 2024 2648
የኢትዮ-አልጄሪያ ግንኙነት ታሪካዊ ነው፡፡ታሪካዊነቱ በዘመንም፣ በጸና ወዳጅነትም ይለካል።ትናንት ማምሻውን የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የሀገሪቷን ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልክዕት ይዘው አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል። ዛሬ ማለዳ ደግሞ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የፀና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል። የፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልዕክትም ተቀብለዋል። ጉብኝቱን አስመልክቶ የሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ እና የኢትዮጵያን ወዳጅነት የትመጣ እና ሂደት በወፍ በረር እንቃኝ። የኢትዮ-አልጀሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሰባት አስርት ዓመታትን ተሻግሯል። ሁለቱ ሀገራት ከመደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ወንድማማችነትና ወዳጅነት መስርተዋል። የፈረንሳይ ቅኝ ተገዥ የነበረችው አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 1960ዎቹ መባቻ ነጻነቷን ለመቀዳጀት ትንቅንቅ ላይ በነበረችበት ዘመን ኢትዮጵያ አጋርነቷን አሳይታለች። ይህን ደግሞ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር የነበሩት ኤልሃምዲ ሳላህ ‘አልጀሪያ የኢትዮጵያን ውለታ አትረሳውም’ ሲሉ በአውሮፓውያኑ 2022 ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀው ነበር። አልጀሪያ በ1962(በአውሮፓዊያኑ) ነበር ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ያረጋገጠችው። ከዚህ ዘመን ጀምሮ ሁለቱ ሀገራት ወዳጅነታቸውን መሰረቱ። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረት እና የፓን አፍሪካኒዝም እንዲያብብ ንቅናቄ አድርገዋል። በ1960ዎቹ መጨረሻም ይፋዊ ዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን በይፋ ጀመሩ። አልጄሪያ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት(የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት) መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን በ1976(እ.ኤ.አ) ከፈተች። ኢትዮጵያም በ2016 ኤምባሲዋን በአልጀርስ ከፍታለች። ሁለቱ ሀገራት በአውሮፓዊያኑ 2014 በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ንግድ፣ ባህል እና በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ ኮሚቴ ፈጥረዋል። ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ጥበቃ እና ማስተዋወቅ እንዲሁም ተደራራቢ ታክስ ማስቀረትን ጨምሮ ከ20 በላይ የትብብር መስኮች በጋራ መስራት ስምምነት ተፈራርመዋል። ከሁለትዮሽ ባሻገርም ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የትብበር መስኮች ያላቸውን ትብብር የማጠናከር ፍላጎት አላቸው። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም በኒውዮርክ በተካሄደው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ከአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ይታወቃል። በዚሁ ውይይት ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አልፎም በዓለም የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል። አምስተኛውን የኢትዮ-አልጄሪያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በቅርብ ጊዜ ለማከናወን የተጀመረውን ዝግጅት ለማፋጠን ተስማማተዋል። አልጄሪያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት ከአውሮፓዊያኑ ጃንዋሪ 2024 አንስቶ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና በመስራት ላይ ትገኛለች። ይህም ሁለቱ ሀገራት በባለብዝሃ ወገን የዲፕሎማሲ መድረክ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጎለብት ነው። አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ በ2021 የአረብ ሊግ ሊቀመንበር በነበረችበት ወቅት ተቋሙ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተዛባ አረዳድ ለማስተካከል እና ሚዛናዊ እይታ እንዲኖረው ጥረት አድርጋለች። የኢትዮ-አልጄሪያ የሁለትዮሽ ትብብር የሚያጠናክሩ የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እያደጉ መጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም በአልጄሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። በወቅቱም ከአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ ጋር ተወያይተው ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮ-አልጄሪያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ በሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር የሚቻለባቸው ዘርፎች እንዳሉ ገልጸው ነበር። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በሀገራቱ መካከል የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እየጨመሩ መጥተዋል። ለአብነትም በአውሮፓዊያኑ በ2021 የያኔው የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው ነበር፤ የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውም አይዘነጋም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ደግሞ በሩሲያ ሶቺ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ከተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ-ሩሲያ የትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ስብስባ ጎን ለጎን ከአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጋር መክረዋል። በውይይታቸውም የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያስጠብቁ ቀጣናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። እናም ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ የትብብር መስኮች ግንኙነታቸውን ማጎልበት ቀጥለዋል። በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ በቅርቡ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ቴቡኔ ሲያቀርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴን ልባዊ ሰላምታ እና የወዳጅነት መልዕክት ለፕሬዝዳንቱ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው። ዛሬ ደግሞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ቴቡኔን መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አድርሰዋል። የሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጉብኝት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው እና የኢትዮ-አልጀሪያ ሁለትዮሽ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት አካል ስለመሆኑ የአልጄሪያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጋርም ተወያይተዋል። በውይይቱ በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው አገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትስስር በማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር አድማሶችን በመፈለግ አጋነታቸውን ለማጎልበት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እና አልጄሪያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባን በቅርቡ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። እናም ኢትዮጵያና አልጄሪያ ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ነው። ሁሉን አቀፍ በሆኑ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረጉ ትብብር መስኮች እየተወዳጁ ነው። የስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ እየጎለበተ ይመስላል። የአገራቱ መጻዒ የትብብር ጊዜ ብሩህ እና ፍሬያማ እንደሚሆን አያጠራጥርም።
ቀጣና ዘለል አንድምታ ያለው የአንካራው ስምምነት
Dec 13, 2024 2851
የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ አንድምታ ከቀንዱ ሀገራት የተሻገረ ነው። የቀጣናው ሀገራት ትስስርና ትብብርም እንደዚያው። በነዚህ ሀገራት መካከል የሚፈጠር መቃረን የሚያሳድረው ተጽዕኖም አድማስ ዘለል ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያና ሶማልያ መካከል ተፈጥሮ የነበረው የግንኙነት መሻከር ከሁለቱ ሀገራት ባሻገር በቀጣናው ስውርና ገሀድ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኃይሎችን ያሳሰበና ያስጨነቀ ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው። በቱርክዬ ርዕሰ ከተማ አንካራ የተደረሰው የኢትዮ-ሶማልያ ሥምምነት ግን ለበርካቶች እፎይታን ይዞ መጥቷል። ከኢትዮጵያና ሶማልያ ጋር መልካም ወዳጅነት ያላት ቱርክዬ የሁለቱን አገራት ለማሸማገል ጥረት ከጀመረች ውላ አድራለች። ምንም እንኳ ጥረትና ድካሟ በተደጋጋሚ ሳይሳካ ቢቆይም ካለፈ ሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በሚኒስትሮች ደረጃ ለማረቅ ተግታለች። በሦስተኛው ዙር በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ደረጃ የተደረገው ድርድር ግን ፍሬ አፍርቶላታል። ቱርክዬ እየተገነባ ባለው የብዝሃ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ጎልተው እየወጡ ካሉ ኃያላን ሀገራት መካከል አንዷ ናት። በአፍሪካ ውስጥ ያላት ተፅዕኖ ፈጣሪነትም እያደገ መምጣቱ ይታወቃል-በተለይ በአፍሪካ ቀንድ። ቱርክዬ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ታሪካዊና ዘርፈ ብዙ ትስስር ጠንካራ የሚባል ነው። ቱርክዬ ከቻይና ቀጥላ በኢትዮጵያ ግዙፍ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ያፈሰሰች ሀገር ናት። ከኢኮኖሚያዊ ቁርኝቱ ባሻገር ሁለቱ አገራት በፖለቲካዊና ማኅበራዊ እንዲሁም ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ያላቸው ትብብርም የላቀ ነው። ቱርክዬ ከሶማልያ ጋር ያላት አጋርነትም እየተጠናከረ የመጣ ነው። እናም የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ለቱርክዬ ሳንካ ነበር። ስለዚህ የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት በአንካራው ድርድር ዲፕሎማሲያዊ እልባት ማግኘቱ ለፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ወሳኝ እርምጃ ሆኖላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማልያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በአንካራ ተገኝተው ያደረጉት ውይይት የቀንዱን ውጥረት አርግቧል። ስምምነቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ለመውሰድ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል። በሶማልያ በኩል ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ዘላቂነት ያለው የባሕር በር የማግኘት መብትን ዕውቅና ለመስጠት እና በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮ ለመስራት መስማማት ችላለች። በተመሳሳይ ኢትዮጵያም የሶማልያን የግዛት አንድነት ለማክበር የነበራትን የቆየ አቋም አጽንታለች። ሁለቱ ሃገራት የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት እውን ለማድረግ በቀጣይ አራት ወራት በቱርክዬ አስተባባሪነት ዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ለማካሄድ ተስማምተዋል። መሪዎቹ በመግለጫቸው ኢትዮጵያ በሶማልያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት ዙሪያ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር ይሁንታቸውን ሰጥተዋል።ይህ የወደብ አማራጮችን በስፋት ለመጠቀም ለምትፈልገው ኢትዮጵያ ትልቅ እርምጃ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለምታደርገው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያና የሶማልያ ሕዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በጉርብትና ብቻ ሳይሆን በደም የተሳሰሩ ወንድማማቾች እና እህታማማች ሕዝቦች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውስተዋል። ይልቁንስ ሶማልያን ከአሸባሪዎች ለመከላከልና ሠላሟን ለማረጋገጥ ሲባል በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል አባላት በከፈሉት መስዋዕትነት ጭምር የተሳሰረ መሆኑን ነው ግልጽ ያደረጉት። ኢትዮጵያ ለጋራ ሠላምና ልማት ከሶማልያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። የሶማልያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድም ለዚህ ሀቅ ጠንካራ እማኝነታቸውን ሰጥተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለአገሪቱ ሠላም መጠበቅ ለዓመታት የከፈለውን ዋጋ መቼም አይዘነጋም ሲሉ የሚገባውን ክብር አጎናጽፈውታል። ሶማልያ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ ሆና ትቀጥላለች ሲሉም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሠላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግሥታቸው ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። በጥቅሉ የአንካራው የአቋም መግለጫ የሁለቱን አገራት የጋራ አሸናፊነት ያንጸባረቀ ነው። ለዘመናት በተለይም ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ፈጽሞ የተዘነጋ እና የማይታሰብ ይመስል የነበረውን የኢትዮጵያን የባሕር በር ጉዳይ በድፍረት ዓለም አቀፍ አጀንዳ ለማድረግ ያስቻለ ነው። የኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከሃገር አልፎ ለቀጣናው ሁለንተናዊ ትስስር ጭምር ወሳኝ መሆኑ መግባባት የተደረሰበት ሆኗል። በተለያዩ አሰራሮች እና አግባቦች፣ በሠላማዊ መንገድ እና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዘላቂ የባሕር በር ሊኖራት እንደሚገባ መግባባት የፈጠረ ነው። ይህን ሥምምነት ዕውን ለማድረግ በዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ ድርድሮች በማካሄድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገቢራዊ ለማድረግ ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ መግባባት ችለዋል። በዚህ ረገድ ቱርክዬ ሂደቱን ለማሳለጥ እና ለማገዝ ኃላፊነት መውሰዷ ደግሞ ዘላቂነት እንዲኖረው እንደ መልካም ዕድል የሚወሰድ ነው። ኢትዮጵያና ሶማልያ በአንካራ የደረሱት ስምምነት ከአውሮፓ ኅብረት እስከ አፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እስከ ተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና አገራት አድናቆት የቸሩት ሆኗል። ይህ ስምምነት የሁለት አገራት ስምምነት ብቻ አይደለም። የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አፍሪካ የመፍጠር ህልም አካልም ጭምር ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። የውዳሴው መነሻና መድረሻውም ደግሞ ስምምነቱ የአፍሪካ ቀንድን ከግጭት አዙሪት ወጥቶ ወደ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ብሎም ወደ አህጉራዊ ትብብር የሚወስድ መሆኑ ነው። በእርግጥም ሥምምነቱ የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ከመባቱ በፊት ለቀንዱ አገራት የቀረበ ሥጦታ ነው። እናም የአንካራው ስምምነት ከኢትዮጵያና ከሶማልያ ባለፈ አንድምታው ቀጣናውን የተሻገረ በመሆኑ የአፍሪካውያንና የወዳጅ ሀገራት በቅን መንፈስ የተቃኘ ድጋፍ ያሻዋል። ሠላም!
ህዳሴ - በመስዋዕትነት የተገነባ ነገ
Nov 2, 2024 3965
ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ከፕሮጀክት ባለፈ የኢትዮጵያውያን በጋራ የመቻል ትምህርት ነው። የወል ዕውነታቸው፣ የወል አቅማቸው፣ የጋራ ተስፋቸው በግልጽ የተንጸባረቀበት የአይበገሬነት ምልክት ጭምር ነው። ኢትዮጵያውያን ነጋቸውን እንዴት በጋራ መገንባት እንደሚችሉ በሚገባ ያሳዩበት ዳግማዊ አድዋ ነው - ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ። አድዋ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ለነጻነት የተዋደቁበት ደማቅ የታሪክ ምዕራፍ ሲሆን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ደግሞ ለኢኮኖሚ ሉአላዊነት የደም ዋጋ የተከፈለበት የትውልዱ የብሄራዊነት ማሳያ ነው። ህዳሴን ዕውን ለማድረግ ኢትዮጵያ ከሴራ ዘመቻዎች እስከ ዛቻና ማስፈራሪያዎች የደረሱ እንቅፋቶችን አልፋለች። በተለይም የግድቡ ግንባታ ወደማይቀበለስበት ደረጃ በደረሰባቸው ያለፉት 6 ዓመታት ፈተናዎቹ በርትተው ነበር። ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተጓጉዘው እንዳይደርሱ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርት እንዳያመርቱና እንዳያቀርቡ በተለየዩ ቦታዎች ጥቃቶች ይሰነዘሩ ነበር። ቢሆንም ግን የማያባሩ የኢትዮጵያ ጠላቶችን የተንኮል ወጥመዶች በጣጥሶ ለማለፍ ኢትዮጵያውያን አይተኬ ህይወታቸውን ጭምር ገብረው ነገን ዛሬ መስራትን በህዳሴ ዕውን አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሕዳሴ ግድብ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ በርካታ መስዋዕትነት መከፈሉን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሁሌም በጋራ የመልማት እሳቤ ማዕከል መሆኗን ገልጸው፤ታላቁ ህዳሴ ግድብም በኢትዮጵያዊያን ብርቱ ልጆች ከአፍሪካ ለአፍሪካ የተሰጠ ገጸ በረከት እንዲሁም ጣፋጭ ፍሬውም ከኢትዮጵያ ባለፈ ለተፋሰሱ አገራትም ብስራት መሆኑን ነው ያስረዱት። የታላቁ የኢትዮጵየ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ አኩሪ ደረጃ ላይ ለመድረስ ኢትዮጵያውያን ከገንዘብ፣ ጉልበትና እውቀታቸው ባሻገር የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉበት ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመዋል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 2464
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 2259
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
የአርሶ አደሮችን ጓሮና ኑሮ የለወጡ ቁጥሮች- “30-40-30”
Nov 15, 2024 3701
ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ የሚሆን ሃብት የሰነቀው የ"30-40-30" ኢኒሼቲቭ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮች መንደር ተገኝቶ ስለ ’30-40-30’ አሃዞች አርሶ አደሮችን የሚጠይቅ ካለ የቁጥሮችን ትርጓሜና ስሌት በቅጡ መረዳት ይችላል። እነዚህ ቁጥሮች በገጠራማው የክልሉ አካባቢዎች አባውራዎች ዘንድ ሕይወትም፣ አስተሳስብም ለውጠዋልና። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኅላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር የ’30-40-30’ ኢኒሼቲቭ የተጠነሰሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን በመመርኮዝ ስለመሆኑ ያስታውሳሉ። እነዚህ ቁጥሮች የተራ አሃዝ ስያሜ ሳይሆኑ በክልሉ ግብርና ወደ እመርታ ለማስፈንጠር የተቀየሱና ትውልድ ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቁ ናቸው። በ2014 ዓ.ም ጀምሮ እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር በሶስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 100 የፍራፍሬ ዛፎች አልምቶ እንዲጠቀም መሰረት የሆኑም ናቸው። በኢኒሼቲቩ የለሙ ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሩን ኑሮ ማሻሻል ያለሙ፣ 'ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ ናቸው' ይላሉ። የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ገቢ ምንጭ ማድረግ፣ ስራ ዕድል መፍጠር፣ ገበያ ማረጋጋት፣ ለኤክስፖርትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማቅረብን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ዓላማዎችም አሏቸው። በእያንዳንዱ አባውራ ጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲለማና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የተወጠነ ነው። በዚህም በ'30-40-30'ን እያንዳንዱ አባወራ ጓሮውን እንደየአካባቢው ስነ-ምህዳር በሙዝ፣ በፓፓያ፣ በማንጎ፣ በቡና፣ በአቮካዶና በሌሎች ፍራፍሬ ችግኞች እንዲያለማ ተደርጓል። 'ያልተሄደበትን መንገድ በመሄዳችን በትግበራ ሂደቱ ፈተናዎች ነበሩ' የሚሉት ሃላፊው፤ ዛሬ ላይ ግን የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ ፍሬ የቀመሱትን ሁሉ አስተሳስብ ለውጧል ይላሉ። ኢኒሼቲቩ ባልተለመዱ አካባቢዎች የፍራፍሬ መንደሮች የተፈጠሩበት፣ የአርሶ አደሩ ኑሮና ጓሮ የተለወጠበት፣ የይቻላል አስተሳስብ የተፈጠረበት እንደሆነ ይናገራሉ። በክልሉ የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ በመተግበር ከሴፍቲኔት የተላቀቁና ኑሯቸውን ያሻሻሉ አረሶ አደሮች ለዚህ ምስክር ናቸው። በስልጤ ዞን ውልባረግ ወረዳ ቶዴ ጠመዳ ነዋሪዎች አቶ ሀምዛ አሊዬ እና ባለቤታቸው አናጃ ኢሳ በሴፍትኔት ታቅፈው ሲረዱ የቆዩ ሲሆን በ30-40-30 ጓሯቸውን በቡና በማልማታቸው ዛሬ ገቢም፣ ምግብም ችለዋል። በ500 የቡና ችግኝ ድጋፍ ጀምረው በየዓመቱ እያሳደጉ ዛሬ ላይ ቡናቸውን ለቅመው በመሸጥ ገቢ ማመንጨትና ነሯቸውን መደጎም ችለዋል። ጓሯቸውን በማልማታቸውም ከሴፍትኔት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ህይወት እንዲሻሻል ስለማድረጉም ገልጽው፤ በቀጣይነትም ሌሎች ፍራፍሬዎችን ለማልማት ተዘጋጅተዋል። በውልባረግ ወረዳ ቢላዋንጃ ባቢሶ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ኢክማላ መሀመድ እና ልጃቸው መካ ኢክማላ ደግሞ አካባቢውን ያልተለመደ የሙዝ መንደር በማድረግ ኑሯቸውን እንዳሻሻሉ ይናገራሉ። የ30-40-30 ንቅናቄ ሲጀመር በአካባቢው "ሙዝ አይለማም" በሚል የተሳሳተ እሳቤ ቅር እያላቸው ችግኞችን ወስደው የተከሉ ቢኖሩም በርካቶች በእምቢታ ጸንተው እንደነበር አስታውሰዋል። በሂደት ውጤቱ ሲታይ ግን የልማቱ ተሳታፊዎች በዝተው በውጤትና የስኬት መንገድ ላይ መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ከሳዑዲ አረቢያ የ10 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ የተመለሰው ልጃቸው መካ ኢክማላ የስደት አስከፊነትን በማንሳት ተፈጥሮ በሰጠችን ጸጋ ሳንጠቀም በመቆየታችን ይቆጨናለ ይላል። የ30-40-30 ንቅናቄም ወጣቶች ከስደት ይልቅ በጓሯቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ ዐይን የገለጠ እና የአስተሳሰብ ለውጥም ያመጣ ስለመሆኑ ይናገራል። በሀድያ ዞን ሻሸጎ ወረዳ ዶዕሻ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ይቴቦ ሽጉጤ፤ ኢኒሼቲቩን በመጠቀም ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የሙዝ መንደር መስርተዋል። የክላስተር ሙዝ መንደራቸው በሶስት ዓመታት ውስጥ የቤተሰባቸው ኑሮ እንዲሻሻል ያደረገና በቀላሉ ጸጋን ተጠቅሞ መለወጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ስለመሆኑም ገልጸዋል። የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ንቅናቄ በርካቶች በተለይም በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ተሳትፈው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአካባቢ ያሉ ጸጋዎችን በመለየት የቡና፣ የሙዝና የአቮካዶ ክላስተር በማልማት ከፍጆታ አልፈው ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረቡ ስለመሆኑም ይናገራሉ። በሀድያ ዞን የሻሸጎ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ወንዱ መለሰ፤ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል። በሙዝ ክላስተር አርሶ አደሮች በትብብር ሰርተው እንዲለወጡ ያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ አርሶ አደሮችም ውጤቱን በማየት ወደተጨማሪ ልማት እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል። የ30-40-30 ኢኒሼቲቩ 'ጥረት ካለ ስኬት እንዳለ ማሳየት የተቻለበት እና የግብርናው ዘርፍ አንኳር መሰሶዎችን ዕውን ለማድረግ ተስፋ ሰጭ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አቶ ዑስማን ይገልጻሉ። በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የግብዓት ፍላጎት በመጨመሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት አንድ አርሶ ወይም አርብቶ አደር በመጀመሪያ ዓመት 30፣ በሁለተኛው ዓመት 40 እና በሶስተኛ ዓመት 30 የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚ የሚሆንበት መርሃ ግብር መሆኑ ይታወቃል።
መጣጥፍ
የዋጋ ንረት ምን ማለት ነው?
Jun 30, 2025 335
የዋጋ ንረት በንፅፅር ለምሳሌ አምና 26 በመቶ ዘንድሮ 14 በመቶ ሲሆን ምን ማለት ነው? ለምሳሌ የአንድን የ100 ብር ዕቃ ወስደን ብንመለከት ካቻምና ከነበረበት 100 ብር አምና 126 ብር ሆኖ ነበር ማለት ነው። ስለዚህ የዕቃው ዋጋ በአመት ብር 26 ጨምሯል ማለት ነው። በተመሳሳይ መንገድ አምና 100 ብር ዋጋ ያለው ዕቃ ዘንድሮ 14 በመቶ ካደገ ዘንድሮ 114 ብር ይሆናል ማለት ነው። በዚህ ስሌት የዕቃው ዋጋ ካምና ወደ ዘንድሮ የጨመረው በ14 ብር በመሆኑ አምና ከጨመረበት ብር 26 ጋር ሲነፃፀር ጭማሪው ቀንሷል ማለት ነው። ዋጋን ያየን እንደሆነ ግን 100 ብር የነበረ ዕቃ 114 በመሆኑ ጨመረ እንጂ አልቀነሰም። የዋጋ ንረት ጨመረ የሚባለው ደግሞ ለምሳሌ አምና 26 በመቶ የጨመረው ዘንድሮ 14 በመቶ ሳይሆን 30 በመቶ ቢሆን የጨመረው አምና 100 ብር የነበረው ዕቃ ዘንድሮ 114 ሳይሆን 130 ብር ይሆናል ማለት ነው። ይህ አምና ከጨመረበት የ26 ብር ይበልጣል ማለት ነው። ስለዚህ ካቻምና 100 ብር የነበረው ዕቃ አምና 26 ብር ጨምሮ 126 ከሆነ በኋላ ዘንድሮም 14 ብር ስለጨመረ በቀላል ቀመር ዘንድሮ 140 ብር ሆኗል ማለት ነው። ስለዚህ በሁለት አመታት የዕቃው ዋጋ 40 ብር ጨምሯል። የዕቃው ዋጋ አልቀነሰም በየአመቱ የጨመረበት ምጣኔ ግን ካምና ዘንድሮ ያነሰ ነው። ይህ ነው የዋጋ ንረት ቀነሰ ማለት። ዋጋ ቀነሰ ማለትስ ምን ማለት ነው? ዋጋ ቀነሰ የሚለውን ከማየት በፊት የዋጋ ንረት የለም ማለት ምን እንደሆነ በዛው 100 ብር ዋጋ ባለው ዕቃ እንመልከት። ይህ ባለፈው አመት ብር 100 የነበረ ዕቃ ዘንድሮም እዛው 100 ብር ላይ ቢቆይ የዋጋ ንረት ዜሮ ነው። ስለዚህ የዕቃው ዋጋ አልተለወጠም ማለት ነው። ዋጋ ቀነሰ ማለት ግን የዋጋ ንረት ከዜሮ በታች ይሆናል ማለት ነው። በምሳሌው ለማስረዳት አምና 100 ብር ዋጋ ያለው ዕቃ ዘንድሮ 90 ብር ቢሆን የዋጋ ንረቱ ወይም ለውጡ ከዜሮ በታች 10 በመቶ ነው። በዚህ ግዜ የዋጋ ንረት ቀነሰ ሳይሆን ዋጋ ቀነሰ ይባላል። እነዚህ ሶስቱ የዋጋ ለውጦች ለሸማቾችና ለአምራቾች ምን ማለት ናቸው? ለሸማቾች ከሁሉም የሚመረጠው ዋጋ ሲቀንስ ማለትም 100 ብር የነበረው ዕቃ 90 ብር ሲሆን ነው። በሁለተኛ ደረጃ ተመራጩ ዋጋ ንረት ሳይኖር አምና 100 ብር የነበረው ዕቃ ዘንድሮም ሳይለወጥ በዜሮ ንረት 100 ብር ላይ ሲቆይ ነው። ሶስተኛው የተሻለ አማራጭ አምና 100 ብር የነበረ ዕቃ ዘንድሮ በ26 በመቶ ጨምሮ ብር 126 ከሚሆን በ14 በመቶ ጨምሮ ብር 114 ሲሆን ነው። ይህ ሶሰተኛው አማራጭ በሁለቱም ዋጋ ስለሚጨምር በትንሽ የጨመረው ተመራጭ ይሆናል ማለት ነው። ከአምራቾች አንፃር ሲታይ ከላይ ለሸማቾች የተሻለ አማራጭ በቅደም ተከተል ያስቀምጥነውን ገልብጠው ማንበብ ነው። አሁን ብሔራዊ ባንክ እያለ ያለው የዋጋ ንረት ወይም አመታዊ ጭማሪው ቢበዛ ከ10 በመቶ እንዳይበልጥ የሚረዳ የገንዘብ ፖሊሲ እተገብራለሁ ነው። የባንኩ አላማ የዋጋ ንረት ዜሮ ወይም ከዜሮ በታች እንዲሆን ሳይሆን 1) ከ10 በመቶ በታች እንዲሆን ሲሆን 2) የትረጋጋና ተገማች እንዲሆን ነው። የተረጋጋ ማለት ከወር ወር ወይም ካመት አመት ዋጋ የሚለወጥበት ሁኔታ በጣም የተራራቀ ያልሆነ ማለት ነው። ለምሳሌ ካንዱ ወር ወደ ቀጣይ ወር ጭማሪው 0.5 በመቶ ሆኖ በቀጣይ ወር ደግሞ የ5 በመቶ ጭማሪ ከዚያም በቀጣይ ወር ከዜሮ በታች የ2 በመቶ ወርሃዊ ለውጥ ቢመዘገብ ያልተረጋጋ ወይም ተገማች ያልሆነ የዋጋ ለውጥ አለ ማለት ነው። ሰለዚህ የተረጋጋና ተገማች የዋጋ ለውጥ እንዲኖር ማድረግ የባንኩ ሁለተኛው አላማ ነው ማለት ነው። ብሔራዊ ባንክ በጣም ዝቅተኛ የዋጋ ንረት ወይም ከዜሮ በታች የዋጋ ለውጥ እንዴት ያየዋል ብለን ያየን እንደሆነ ነገሩ እንዲህ ነው። ቅድም ከላይ እንዳየነው የዋጋ ንረት ከሸማቾችና ካአምራቾች አንፃር የሚታየው በተቃራኒ መንገድ ነው። ስለሆነም ምንም እንኳን የዋጋ ንረት በጣም ዝቅተኛ ወይም ከዜሮ በታች ቢሆን ለሸማቾች ጥሩ ቢሆንም አምራቾችን ግን የማያበረታታ ስለሚሆን ማምረት ያቆማሉ ሠራተኛ ይቀንሳሉ አጠቃላይ የኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ይገታና ጭራሽ ከምርት እጥረት የተነሳ የዕቃዎች ዋጋ መናር ይከሰታል ሥራ አጥነት ይበዛል። ስለዚህ መንግስት ሥራ እንዲፈጠር ኢኮኖሚ እንዲነቃቃም ስለሚፈለግ የተረጋጋና ዝቅተኛ ሸማቹን የማይጎዳ አምራቹንም የሚያበረታተ የዋጋ ሁኔታ እንዲኖር ይሰራል ማለት ነው። ለአንድ ኢኮኖሚ ትክክለኛው የዋጋ ንረት ስንት ነው? ይህ ጥያቄ ሊመለስ የሚገባው ግን ከባድ ነው። ይህን ጥያቄ ለመመለለስ ከሚረዱት ሁኔታዎች አንዱ ኢኮኖሚው ያለበት ደረጃ ነው። ምን ማለት ነው በጣም ባደገና የበለጠ የማደግ እድሉ ጠባብ ለሆነ ኢኮኖሚ 1 በመቶ ወይም 2 በመቶ የዋጋ ንረት ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። በአንፃሩ ደግሞ ገና የማደግ እምቅ አቅም ላለውና በማደግ ላይ ላለ ሀገር ነጠላ አሃዝ የዋጋ ንረት እንደ ሁኔታው የሚለያይ ሆኖ ተመራጭ ሊሆን ይችላል። ስንት ነው የሚለው ግን በሳይንሳዊ መንገድ መረጋገጥ አለበት። ለምሳሌ የሀገራችንን threshold inflation or optimal inflation level ለማወቅ እኔን ጨምሮ የባንኩ ሠራተኞች በሳይንሳዊ መንገድ ለማወቅ ተሞክሯል። በኔ ጥናት 7 በመቶ ሲሆን በሌሎቹም ከዚሁ ያልራቀ ውጤት እንዳለ አይቻለው የመረጃ አጠቃቀምና የሜቶዶሎጂ ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ ማለቴ ነው። ሰለዚህ በነዚህ ጥናት መሰረት ብሔራዊ ባንክ የነጠላ አሃዝ የዋጋ ንረት አላማ አድርጎ መንቀሳቀሱ ትክክለኛ አቅጣጫ ነው ማለት ነው ለኛ ኢኮኖሚ። ለማጠቃለል የዋጋ ንረት ምንነትን በተመለከተ ያለውን ውዥምብር ለማጥራት ይህ አጭር መግለጫ ያግዛል ብዬ እያመንኩ የበለጠ መብራራት ካለበት ወይም ጥያቄ ካለ አንባቢዎች በአስተያየት መስጫው ላይ ማሰቀመጥ ትችላላችሁ። አቶ ፈቃዱ ደግፌ የብሔራዊ ባንክ ም/ገዥ
የሺህ ሀይቆች ምድር
Jun 24, 2025 524
የሺህ ሀይቆች ምድር (በራሔል አበበ) በርካታ መገለጫዎች አሏት። የሺህ ሀይቆች መፍለቂያ። አረንጓዴ ምድር። 75 በመቶ የአገሪቱ ገፀ-ምድር በደን የተሸፈነ። የአምስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ መኖሪያ። በአውሮፓ ከበለጸጉ አገራት አንዷ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለስምንት ተከታታይ ዓመታት በዓለም ቁጥር አንድ የደስተኞች አገር በመባል የተሰየመች ሰሜን አውሮፓዊት አገር - ፊንላንድ። በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋባዥነት በአዲስ አበባ የአገሪቱ ኤምባሲ አስተባባሪነት በቅርቡ ፊንላንድን የመጎብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር። በጉብኝቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ የኬኒያ፣ ታንዛኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሴኔጋል፤ ሞዛምቢክ እና ዛምቢያ ጋዜጠኞች ተሳትፈናል። የአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ነው። ምንም እንኳን የትም አገር ስሄድ ቀድሜ መረጃ የማየት ልምድ ቢኖረኝም በመጀመሪያው ዕለት ለእራት ስንወጣ ያየሁት በምሽት ያልተለመደ የፀሐይ ፍካት ግን እራቱ ቁርስ እንዲመስለኝ አድርጓል። ከዚያ በኋላ ለመድሁት። በእርግጥ በአንድ ወቅት በስፔንም ፀሐይ እስከ እኩለ ሌሊት የማትጠልቅበትን ክስተት ተመልክቻለሁ። በፊንላንድ ያየሁት ግን ተለየብኝ። ፀሐይ ፈጽሞ ለጨረቃ ቦታ መልቀቅ አትፈልግም። ምሽቱ የሚደምቀው በመብራት ሳይሆን በፀሐይ ነው። ሌሊቱ ብርሀን ነው። ሰማይ አይጠቁርም። በየዕለቱ ሳይጨልም ይነጋል። በዚህ ወቅት በተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ አገራት ሰማይ ላይ የሚታየው ሰሜናዊ የቀለማት የብርሀን ፀዳል ሌላው የፊንላንድ መድመቂያ ነው። የሰሜን አውሮፓ/ኖርዲክ አገራት በተፈጥሮ የታደሉ ናቸው። እኔ ደግሞ የተፈጥሮ አድናቂ ነኝ። ያለማጋነን በፊንላንድ ተፈጥሮ ከነክብሯ ተጠብቃ አይቻለሁ። ንጹህ አየሯ የዚህ ውጤት ነው። አድናቆቴ የጀመረው ከኤርፖርት እስካረፍኩበት ሆቴል 15 ኪሎ ሜትር ያህል በመኪና ስንጓዝ የከተማዋን አረንጓዴነትና የምድሪቱን ልምላሜ ስመለከት ነበር። በጉብኝቴም በተግባር አረጋገጥሁ። የአገሪቱ አብዛኛው መሬት በደንና በውሃ ተሸፍኗል። በዋና ከተማዋ ሄልሲንኪና በዙሪያዋ በሚገኙ ውብ ደኖች መሀል ስንጓዝ መሬቱ ለም ስለመሆኑ ዓይን ብቻ ሳይሆን እግርም ምስክር ነው። ሲራመዱ የመሬቱ ምቾትና እንደ ስፖንጅ ስምጥ ስምጥ ማለት ለምነቱን ይናገራል። በሄልሲንኪ ሴኔት እና ካንሳላስቶሪ አደባባዮች እንደእኛዎቹ አራት እና ስድስት ኪሎ አደባባዮች ናቸው። ቤተ-መንግስት፣ ዩኒቨርሲቲ፣ ፓርላማ፣ ቤተ-መጽሐፍት እና ቤተክርስቲያንን አጎራብተው ይዘዋል። የሄልሲንኪ ሕንጻዎች እንደ ሌሎች የአውሮፓ አገራት ውብና የሥነ-ሕንጻ ጥበብ የሚታይባቸው ናቸው። የነዋሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ ከተማዋ አልተጨናነቀችም። በአስፋልትና ደረጃውን በጠበቀ ኮብልስቶን የተሰራው የከተማዋ አውራ ጎዳና ከዘመናዊ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ የህዝብ አውቶቡስና የኤሌክትሪክ ባቡር ያስተናግዳል። ለአውሮፓ ከተሞች አዲስ የሆነ ሰው ኮብልስቶኑ የእግረኛ መንገድ መስሎት መሐል የመኪና መንገድ ላይ ሊገኝ ይችላል። እኔም የተረፍሁት እንዲህ አይነቱን የመኪና መንገድ በአንድ ወቅት በኢጣልያ በማየቴ ነበር። የተፈጥሮ ውበት ደምቆ የሚታይባት ፊልናልድ ሲልቨር በርች የተሰኘው ብርማ ቀለም ቅርፊት ያለው ዛፍ እና ቡናማ ድብ ብሔራዊ መለያዎቿ ናቸው። በረጃጅሞቹ ዛፎች መሐል ከእንስሳት ባሻገር ስትሮበሪና እንጉዳይን ጨምሮ ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ ዕጽዋት ይገኛሉ። በፊንላንድ ብዙ አይነት የእንጆሪ/ስትሮበሪ ዝርያ አለ። ወቅቱ ፍሬ የሚደርስበት አልነበረም እንጂ ከጫካዎቹ መሐል ገብቶ በተለያዩ የስትሮበሪ ፍሬዎች ቅርጫት ሞልቶ መውጣት የተለመደ መሆኑን ተረድቻለሁ። ፊንላንድ የሺህ ሀይቆች ምድር ተብላም ትሞካሻለች። ለቁጥር የሚያዳግቱ በበርካታ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሀይቆችና የውሀ አካላት ከተፈጥሮ ሀብቶቿ መካከል ናቸው። ለጉብኝት በሄድኩባቸው አካባቢዎች ሁሉ የሚቀርብልኝን ኩልል ያለ ንጹህ የመጠጥ ውሃ በፍቅር ነበር የምጠጣው። ግዴታ ካልሆነ የፋብሪካ ውሃ በፊንላንድ ቦታ የለውም። ንጹህ የተፈጥሮ የምንጭ ውሃ ከቧንቧ ይቀዳል። ጽድት ከማለቱ ጣዕሙ። ፊኒሾች ለባህልና ቅርስ ትልቅ ቦታ አላቸው። በተለይ ከተፈጥሮ ጋር ያላቸው ቁርኝት አስገራሚ ነው። በአብዛኛው አፍሪካ ውስጥ የሚነገር አፈ-ታሪክና ተረት በፊንላንድም ከተፈጥሮ በተለይም ከዛፎችና ከእንስሳት ጋር ተያይዞ ሲተረትና የመድረሻቸው መነሻ እንደሆነ ሲነገር ተደንቄያለሁ። በጉብኝታችን በአንዱ ቀን ኑኪሲኦ ብሔራዊ ፓርክ ሄድን። ይህ ደግሞ እጅግ የተለየ ተፈጥሮን ማያ ስፍራ ነው። በረዣዥም ዛፎች መሐል ካደረግነው ጉዞ በኋላ የቀረበልን ባህላዊው የፊንላንድ የሳውና እና የዋና ግብዣ ነበር። ሳውና የፊንላንድ ባህል ነው። በእንግሊዝኛ ቋንቋ መዝገበ ቃላት ውስጥ ያለ የፊኒሽ ቃል “ሳውና” እንደሆነ ይነገራል። ዛሬ በዓለም ላይ በተለይም በባለኮከብ ሆቴሎች በስፋት የምናገኘው ሳውና መነሻው ፊንላንድ ናት። በርካታ የሳውና ስፍራዎች ከመኖራቸው የተነሳ የሳውና ቁጥር በአገሪቱ ከተመዘገቡ መኪኖች ቁጥር ይበልጣል ይባላል። ግብዣውን ሁላችንም በደስታ ነበር የተቀበልነው። በባህሉ መሰረት ሳውና ውስጥ በቅጠል እየተጠበጠብን ከፍተኛ ሙቀት ሲሰማን ከፊት ለፊት ባለው ቀዝቃዛ የተፈጥሮ ሀይቅ ውስጥ በመግባት ዋና የሚችል ዋኝቶ የማይችል ደግሞ በመነከር ሰውነቱን አቀዝቅዞ እንደገና ወደሳውናው ይመለሳል። የተለየ ነው። የጉብኝቱ ዋና አስተባባሪ አና ላሚላ ትባላለች። የ35 ዓመት የስራ ልምድ ያላት ብስል ዲፕሎማት ናት። በተለያዩ አገራት ፊንላንድን ወክላ ሰርታለች። አሁንም በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አምባሳደር ነች። ትክክለኛ የኮሙኒኬሽን ሰው ናት። አንቺ ያልኳት በአንቱታ ላርቃት ባለመፈለጌ ነው። ለነገሩ ስትታይም የ35 ዓመት ወጣት እንጂ የ35 ዓመት የስራ ልምድ ያላት አትመስልም። አንድ ቀን አን “መኮንን” በሚለው የአያቴ ስም እየጠራችኝ ስምሽ እኮ የፊኒሽ/የፊንላንድ ነው ይህን ታውቂያለሽ? ከእኛ ጋር ዝምድና ይኖርሽ ይሆን?" አለችኝ ፈገግ ብላ። "ኸረ በፍፁም ኢትዮጵያዊት ነኝ" አልኳት። ትክክል ነበረች። አጭር የፅሁፍ መልዕክት የመለዋወጥ ሀሳብን ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም ያስተዋወቀው “ማቲ መኮንን” የተባለ ፊንላንዳዊ ኢንጂኒየር ነው። የቴክኖሎጂ ነገር ከተነሳ አብዛኞቻችን ከተንቀሳቃሽ ስልክ ጋር ስንተዋወቅ የያዝነው ኖኪያ የፊንላንድ ምርት ነው። የመኮንንን ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ በተንቀሳቃሽ ስልክ አማካኝነት ለዓለም ይፋ ያደረገውም ኖኪያ ነው። አሁንም ኖኪያ በኔትወርክ ዝርጋታ ጭምር እየሰራ ያለ ግዙፍ የቴሌኮም ተቋም ነው። ኢትዮጵያና ፊንላንድ የረዥም ዓመታት የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው። ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው 66 ዓመታትን ተሻግሯል። ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ከእርዳታና ትብብር ባሻገር በተለያየ መስክ በጋራ ትሰራለች። በጉብኝቴ ወቅት ያገኘኋቸው የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሌና ቫልቶነን ይህን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት መኖሩን ነግረውኛል። ከንግድና ኢንቨስትመንት በተጨማሪ ኖኪያን ከመሰሉ ኩባንያዎች ጋር የሚደረግ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር እጅግ አስፈላጊ መሆኑንና በአገሪቱ ቴክኖሎጂ መዘመኑን የተረዳሁት በአገሪቱ ብሔራዊ የሚዲያ ተቋም ይሌ ያለማንም እርዳታ ዜና ቀርጾ የሚያሰራጭ ሰው አልባ ሮቦትድ የስቱዲዮ ቴክኖሎጂ ስመለከት ነበር። ፊንላንድ በትምሕርት ጥራትም ስሟ በቀዳሚነት ይነሳል። በአገሪቱ ከ800 በላይ፤ በመዲናዋ ደግሞ 40 የሚጠጉ ቤተ-መጻሕፍት አሉ። ከአገሪቱ ፓርላማ አቅራቢያ የሚገኘውና አገሬው የእኩልነት ተምሳሌት ነው የሚለው የሄልሲንኪ ግዙፉ ማዕከላዊ ቤተ-መጽሐፍት ኦዲ ይባላል። በውስጡ በርካታ አገልግሎቶችን ይዟል። ንባብ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የባህልና ፈጠራ ታለንቶችን ያስተናግዳል። ከልጅ እስከ አዋቂ ለሁሉም ቦታ አለው። ፊንላንድ ዜጎቿ በደስታ ግብር የሚከፍሉባት አገር መሆኗን የአገሪቱ የታክስ አስተዳደር ሲናገር በኩራት ነው። ግብር መሰወር፤ ክፈሉ ብሎ በየግዜው መቀስቀስን የመሳሰሉ ነገሮች እዛ ቦታ የላቸውም። የኩባንያም ሆነ የግለሰብ ግብር ከፋዮች በታማኝነት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በወቅቱ እንደሚወጡ አስተዳደሩ ይገልጻል። ይህም የዜጎች ፍላጎትን ለማሟላት በተሰራ ስራ የተፈጠረ መሆኑን የተመለከትኳቸው ተቋማት ሃላፊዎች ይገልጻሉ። ዜጎች በመንግስት ላይ ከፍተኛ እምነት አላቸው። በፊንላንድ የዜጎች ደስተኝነት የሰላምና ነጻነት መገለጫ እንደሆነ ምሁራኖቻቸው በጥናት ስራዎቻቸው ጭምር ይመሰክራሉ። የደስታቸው ምንጭ ነጻና ጥራት ያለው ትምሕርት፣ በአካባቢ ጥበቃ፤ በፍትህና እኩልነት፤ በበጎ አድራጎት ተግባር፤ የእናቶችና ህጻናት ጤናን ጨምሮ አርአያ የሚሆኑ ጠንካራ የማሕበራዊ ደህንነትና ትስስር ስራዎች የመጡ ውጤቶች እንደሆኑ ይገለጻሉ። በጾታ እኩልነት ሴቶች በሁሉም መስክ ጥሩ ስፍራ አላቸው። በፖለቲካውም ከወንዶች ተቀራራቢ ቦታ እንዳላቸው የአገሪቱን ፓርላማ ስንጎበኝ ተረድቻለሁ። ከ200 የምክር ቤት አባላት 91ዱ ሴቶች ናቸው። የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ፊንላንድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደስተኛ አገራት ደረጃ ላይ ለስምንት ተከታታይ ዓመታት የከፍታ ስፍራዋን ሳትለቅ በቁጥር አንድ ላይ እንድትቆይ አድርጓታል። ዜጎቿ በቀጣዩ ዓመትም ለዘጠነኛ ጊዜ የዓለም የደስተኞች አገር ሆና ትቀጥላለች የሚል እምነት አላቸው።